Proverb
stringlengths 4
244
|
---|
ገደል ለገባ ሰው፥ በትርህን እንጂ እጅህን አትስጠው ጎትቶ ይከትሀልና። ገዳም የገባ አይወጣ፤ ከል የገባ አይነጣ። |
ገዳ ገድሽ ለእኔ፥ ሥጋሽ ለአረመኔ። ገድለኛ፥ መንፈሳዊ አርበኛ። |
ገዳይ ሲሸሽ፥ ሟች ይከተላል። ገዳይ ሲደርስ፥ አዳኝ ይደርስ። ገዳይ ሳይገኝ፥ ጉሮ ወሸባዬ። ገዳይ በበለሱ፤ ድሀ በንጉሡ። |
ገዳይ ቢገይ፥ ተገዳይ ይገሰግሳል። ገዳይ ቢያረፍድ፥ ሟች ይገሰግሳል። ገዳይ ከጥይቱ፤ ሥጋ ከብልቱ። |
ገድለው ከአላመለጡ፥ ምንድነው ጌጡ? ገድል በአለቃዬ፤ ከሶ ከጠበቃዬ። ገድል ነበር፥ ሞተ። |
ገድል ከአለቃዬ፤ ከሶ ከጠበቃዬ። |
ገጣባ አህያ ትሰለቻለች፥ ጭና ታበላለች። ገጣጣ ቢሞት፥ የሣቀ ይመስላል። ጉልበት አለኝ የበላ፤ ምላስ አለኝ የሰላ። |
ጉልበት አለኝ የዝኆን፤ አፍ አለኝ ለአንተ የሚሆን። ጉልበት አለኝ የዝኆን፤ አፍ አለኝ የመስፍን። ጉልበት አለኝ የዝኆን፤ አፍ አለኝ የመኮንን። ጉልበት የላለው ወንበዳ፤ ትርፍ የላለው ነጋዳ። ጉልበት የላላት ወይሮ፤ ገደል የላለው ዝንጀሮ። ጉልቻ ቢለዋወጥ፥ ማይክሮ ዌቭ አይሆንም። ጉልቻ ቢለዋወጥ፥ ወጥ አያጣፍጥም። |
ጉልቻ ቢቀየር፥ ወጥ አያጣፍጥም። ጉልቻ ቢቀያየር፥ ወጥ አያጣፍጥ(ም)። |
ጉልቻ የላቀኝ፤ አመድ ያጠለቀኝ አለ አማኑኤል ማን ጠየቀኝ። ጉልቻ የላቀው፤ አመድ ያጠለቀው። |
ጉም መግመጥ፥ ውሃ መግመጥ። |
ጉም ሲለቅ የታባትህ ትገባ፥ አንተ ላባ። |
ጉም ተራራን ያለብሳል፥ ሹም ለሹም ያወርሳል። ጉም ያፈነው፤ ጭጋግ የሸፈነው። |
ጉረኛ ወታደር ጋሻየን ሉቀማኝ፥ አኹንሳ ወሰደዋ! ጉሬዚ ቢውል ከጦጣ፥ ጥፋት ለምድ መጣ። |
ጉሮ ወሸባ፤ አጣልቶ ድረባ። |
ጉሽ መጥራቱ፤ ገፈት መንሳፈፉና፤ አተላ መዝቀጡ አይቀርም። ጉበትን በሳንባ አይለውጡም። |
ጉቦ የለመደ ዳኛ፤ አህያ የለመደ ጅብ አንድ ነው። ጉቦ የበላ ዳኛ፤ የወጋ መጋኛ። |
ጉቦና ላባ፤ በር አይወድም። ጉቦኛ፥ የባሰ መጋኛ። |
ጉታዬን አታጉድይብኝ፤ አሽከሮቼን አትሰርቢብኝ። |
ጉትቻ ለጆሮ፤ ጥሬ ለድሮ። ጉቶም ይቸግራል። |
ጉትቻ ለጆሮ፥ ትንሽ ትመስላለች ዚፈ ጎበዝ ትመልሳለች። ጉትቻ ለጆሮ፤ እልፍኝ ለወይሮ። |
ጉንዳን ሳይደርስ፥ አመድ ነስንስ። |
ጉንዳን ሳይደርስ፥ አስቀድመህ አመድ ነስንስ። |
ጉንዳን ባልንጀራው ሲሞት፥ ብቻውን ተሸክሞ ይዝረዋል። ጉንዳን ቤቱን ይመራል። |
ጉንዳን እስኪወጣ ብቻ ተኛኹ። ጉንዳን እስኪወጣብኝ ተኛኹ። |
ጉንዳን፥ የባልንጀራውን ሬሳ ብቻውን ያነሣ። ጉንዳን ያየህ፥ በአመድ። |
ጉንጭ አልፋ። |
ጉንፋን ሲያድደት፥ በሽታ ይሆናል። |
ጉንፋን የተያና፥ ፍየል ይዝ የተደበቀ፥ ሳይጋለጥ አይቀርም። ጉንፋን የታመመ:_ ውሻ፥ ልጅ፥ ፍየል ይዝ የተደበቀ አይሰወርም። ጉደኛ ውሻ፥ ሥጋ ተቀምጦ ቆል ትሻ። |
ጉዳት ከመጣ፥ መከራ አይታጣ። |
ጉዳት የደረሰበት እረኛ፥ እረጭ አያባርርም። |
ጉዳይ ሳይኖርህ፥ ገበያ አትውረድ፤ የአንደን (ሰው) ነገር ሰምተህ አትፍረድ። ጉዳይ አሳልፍ እንድትታማ፥ አሮጌ ኹን ልትፎክር፥ ሙት ልትመሰገን። |
ጉዳይ የላለህ ገበያ አትውረድ፥ ያንደን ነገር ሰምተህ አትፍረድ። ጉድ ለባለቤቱ፥ ልግም በገላ ነው። |
ጉድ ለባለቤቱ፥ የአንገት ልብስ ነው። ጉድ ሲፈላ፥ ይገኝ የለ ኋላ። |
ጉድ ሳይሰማ፥ መስከረም አይጠባም። ጉድ ሳይታይ፥ መስከረም አይመጣም። |
ጉድ ነሽ የአንኮበር ቅጠል፥ በየኼድሽበት ነገር ማንጠልጠል። ጉድ ነሽ የአንኮበር ቅጠል ነሽ፥ ከመለብለብሽ የመቆጥቆጥሽ። ጉድ ነሽ የአንኮበር ቅጠል፥ እያደር ትለበልቢያለሽ። |
ጉድ ነሽ የአንኮበር ቅጠል፥ ከመለምለምሽ የመለብለብሽ። ጉድ ነው፤ ሲዳሩ ማልቀስ፥ ሲታጩ ደስ ደስ። |
ጉድ ነገር፥ አበድሮ መቸገር። ጉድ እስከ እሐድ። |
ጉድ እንግዳ ነገር፥ አሳድሮ መቸገር። ጉድ ያለው ገንፎ፥ አድሮ ይፋጃል። |
ጉድ ይገርማል ጅብ ከአህያ ጋር እንዳት ይከርማል። ጉድ ጉድ፥ ምን ያንተን ጉድ፥ እየው የኔንም ጉምድ። |
ጉድ ይገርማል፥ አህያ ከጅብ ይከርማል። |
ጉድ ፈላ:_ ሴት ተቀምጣ፥ ወንደ ቡና አፈላ። (ወንደ ~ ወንድ) ጉድሽ፥ ድንቅሽ ና ብለሽ፥ ወዳት ኼድሽ? |
ጉድና ብርቅ እስከ ሦስት ቀን ያስጨንቅ። ጉድና ድንቅ አለ አንድ ጊዛም አይደምቅ። ጉድና ድንቅ፥ አንድ ሰሞን ነው። |
ጉድና ድንቅ፥ አላንድ ሰሞን አይደምቅ። ጉድና ድንቅ እስከ ሦስት ቀን ያስጨንቅ። ጉድና ጅራት በስተኋላ ነው። |
ጉድና ጅራት፥ ከወደኋላ ብቅ ይላል። ጉድድ፥ በራሱ አፈር አይሞላም። ጉጉት ብትጠቃ፥ እርኩም ሆነ ጠበቃ። ጉፋያ ሲነደ ይሸከሙ። |
ጉፋያ ከመብላት፥ ሥብ መሸከም ይሻላል። ጉፋያ ከመብላት፥ ጮማ መሸከም። |
ጉፋያ ከሚያርደ፥ ሥብ ይቀላውጡ። ጉፋያን ሉበሉ፥ ሥብ ይቀላቅሉ። ጉፋያን ሉበሉ፥ ሥብ ይቀላውጡ። ጊዛ መስተዋት ነው። |
ጊዛ ሲከዳ፥ መሬቱ ያድጣል። |
ጊዛ አለው ለሰው፥ ዕድሜ ከአላነሰው። ጊዛ እስኪያልፍ፥ የአባቴ ባሪያ ይግዚኝ። ጊዛ ወርቅ ነው፥ ግን ኀላፊ ነው። |
ጊዛ የላለው የለም ግን፥ ከእድሉ የሚያልፍ የለም። |
ጊዛ የሰጠው ቅል፥ ድንጋይ ይሰብራል። ጊዛ የሰጠው ቅል፥ ጋን ይሰብራል። ጊዛ የሰጠው ቅጠል፥ ሪከርድ ሰበረ። |
ጊዛ የሰጠው ቅጠል፥ ብረትን ያንገረግራል። |
ጊዛ የሰጣት አይጥ፥ ከፈረሰኛ እኩል ትሮጣለች። ጊዛ የጣለው፥ በቁሙ ይወድቃል። |
ጊዛ ያለው፥ ጊዛ አይጠብቅ። ጊዛ ያደርጋል፥ የእንስሳ ሚዛ። ጊዛ ያፈርሳል፤ ቀዳዳ ያፈሳል። ጊዛ ገቢር ለእግዙአብሔር። ጊዛና ቂጣ ተገልባጭ ነው። |
ጊዛና በሽታ፥ ቀን አይቶ ይጥላል። |
ጊዛው ጊዛ ሆኖ ወራቱ ቢመቻት፥ ንድሮስ ድመቴን አይጥ ገደለቻት። ጋለሞታና ጌታ፥ ደጅ የጠኑ ለታ። |
ጋማ ልሠራ ነው፥ አለችው። ጋሪ፥ ድሀን አኩራሪ። |
ጋራና ጉባ፤ ቅልና ደባ። |
ጋሻ ለግንባር፤ መጫሚያ ለጠጠር። ጋሻ ለግንባር፤ ጫማ ለጠጠር። |
ጋሻ ስቀል በኼት ደርሼ? ግማሽ ብላ ከማን አንሼ? ጋሻ ስቀል እንዳት ደርሼ? ግማሽ ብላ ከማን አንሼ? ጋሻ እሰጥ፥ ጋሻ እሰጥ ሲሉ፥ ጦር አገባ። |
ጋሻ ከንግቡ፤ ነገር ከግቡ። ጋሻ፥ ድሮ ቀረሻ። |
ጋሻና ግንባር አይሸሸግም። |
ጋሻን ውጊያ እንዳት ነው? ቢለው ጋሻ ወርውሮ፥ ጦር መመከት ነው አለው። ጋቢ ቢያብር፥ ብርድ ይከላከላል። |
ጋብቻ ለአንድ ሳምንት ብቻ፥ ተመልሶ ጠብና ሽኩቻ። ጋን ሠሪ፥ ምጣድ አይዋጣለትም። |
ጋን ሲለቀለቅ፥ ማድጋን ይሞላል። |
ጋን ሲያሟጥጡት፥ ምንቸት ይሞላል። ጋን በጠጠር ይደገፋል። |
ጋን ቢለቀልቁት፥ ምንቸት ይሞላል። ጋን ቢያሟጥጡት፥ ምንቸት ይሞላል። ጋን ቢያንጫልጡት፥ ማሰሮ ይሞላል። |
ጋኖች አለቁና፥ ምንቸቶች ጋን ሆኑ። ጋይ የለ፥ እሸት ስጡኝ አለ። |
ጋጋሪ ያበስላል፤ ተናጋሪ ያስመስላል። |
ጌታ ለልላው፥ ነጋዳ ለአሞላው (ያስባል)። ጌታ ሲሰጥ፥ ማን ይከለክላል? |
ጌታ ሲወድ ማን ይጠላል፤ ጌታ ሲሰጥ ማን ይከለክላል። ጌታ ቢጫወት፥ ያልኮራ ይመስላል። |
ጌታ ባወቀው ይፈርዳል፥ ሰው ባላወቀው ይጎዳል። ጌታ የዕለቱን፤ አባት የመሠረቱን። |
ጌታ ያዚል፤ ውሃ ያነዝዚል። (ያነዝዚል ~ ያነፃል ~ ያነጻል ~ ይለዚል ~ ይነዚል) ጌታዅን እንዳሻህ ኹን። |
ጌታና ልላ ተሟግቶ፤ ጅብና አህያ ተጋብቶ አይሆንም። |
ጌታና ልላ ተጣልተው፤ ደባና ቅል ተማተው ኧረ አይመስልም ተው። ጌታና ልላ ተጣልቶ፤ ቅልና ድንጋይ ተማቶ። |
ጌታና ገበታ አቅራቢ ነው፤ ሰጭው እግዛር ነው። ጌታና ጋለሞታ፥ ደጅ የጠኑ ለታ። |
ጌታዅን እንደፈቃድህ (ት)ዅን። |
ጌታዋን የምታምን ውሻ፥ ፍሪዳ ሲታረድ እወንዝ ትወርዳለች። ጌታዋን የምታምን ውሻ፥ ፍሪዳ ሲታረድ እወንዝ ወረደች። ጌታውን ከአልናቁ፥ ውሻውን አይመቱ። |
ጌታዋን የምትወድ ላም፥ ትወልዳለች በመስከረም። ጌታዋን ያመነች ላም፥ በመስከረም ትወልዳለች። ጌታዋን ያመነች በግ፥ ላቷ ውጭ ያድራል። |
ጌታውን ያመነ በግ፥ ላቱን ውጭ ያሳድራል። ጌታውን ያየ አሽከር፥ ይጥላል በትግል። ጌታውንና በሽታውን የሚንቅ፥ እያደር ይወድቅ። ጌታዬ ምን አልኩህ? ጠጅ አጠጥተህ ውሃ። ጌታዬ ከአሉበት አግሙኝ። (አግሙኝ ~ እገሙኝ) ጌታዬ ያለበት እገመኝ። |
ጌታዬን ያማ ሰው፥ ነጭ እከክ ይውረሰው። ጌቶች ወደውኛል፥ ጨርቃቸው ነክቶኛል። ጌጥ ያለቤቱ፥ ቁምጥና ነው። |
ግልብጥ ሲሉ ግልብጥ። |
ግልግልና ገንፎ፥ ትኩሱን አያስገባም። ግመል ለተጫነ፥ አህያ ጮኸ። |
ግመል ምን ተጭነሀል? ሽመል ምን ያወዚውዝሀል? አመል። ግመል ሰርቆ፥ ኼደ አጎንብሶ። |
ግመል ሰርቆ፥ ተጎንብሶ (ኼደ)። (ተጎንብሶ ~ አጎንብሶ) ግመል ሰርቆ፥ ጎንበስ ጎንበስ። |
ግመልን የምትውጡ፥ ትንኝ የምታጠሩ። ግማሹን ተላጭታ፥ ግማሹን ተቀብታ። ግማሽ ልጩ፥ ግማሽ ጎፈሬ። |
ግማሽ ተላጭቶ፥ ግማሽ ተሠርቶ። ግም ለግም፥ ቢተቃቀፍ አይነቃቀፍ። ግም ለግም፥ አብረህ አዝግም። ግረፍ (ግን)፥ ከባት አትለፍ። |
ግራ መብል፥ ቀን ገንፎ፥ ላሉት ድፎ። ግራ መብል፥ ቀን ገንፎ፥ ላሉት ድሮ። |
ግራ ነገር፥ ከወንዝ ማድ ፍቅር፥ ከጎረቤት ጥል። ግራር ሲበቃው፥ ልምጭ ይወቃው። |
ግራኝ እና ግንቦት፥ ደረቆች ናቸው። ግርግርታ ለላባ ደስታ። (ለላባ ~ የላባ) ግባ ያላለው ገንብ፥ አጥር ቀድ ይወጣል። ግብ እንደ ግቡ፤ ሙክት እንደ ስቡ። ግብር እስከ መቃብር። |
ግብር ይውጣ። (:_ የማይቀር ዕዳ) |
ግብዝና፥ መቼ እንደ ድቁና። (ድቁና ~ ዱቁና) ግብዝን፥ ኹለት ጊዛ እባብ ነከሰው። |
ግና ንቦ ባርቶ። |
ግንብና ልጅ፥ ስምን ያስጠራሉ። (ግንብና ~ ሕንጻና) ግንብና ድንጋይ፤ ጌታና አባይ። |
ግንቦት ቢዳምን የሚንብ ይመስላል፤ ሀምላ ቢባራ በጋ ይመስላል። ግንቦት ቢዳምን የሚንብ ይመስላል፤ አሮጌ ቢፎክር የሚዋጋ ይመስላል። ግንቦት ቢዳምን ይንብ ይመስላል፤ ሀምላ ቢባራ በጋ ይመስላል። |
ግንድ ለሺ አይከብድ። ግንድ ለሺ አይከብድም። |
ግዚኝ ብለው፥ ለመሸጥ አሰበኝ። |
ግዚኝ ብዬ ብፈቅድለት፥ ሉሸጠኝ አሰበ። ግዚኝ፥ ግዚኝ ብለው፥ ሉሸጠኝ አሰበ። ግደፈኝ ብትለኝ፥ ግድፍ አደረግኋት። |
ግዳይ ለከንፈሬ፤ ጥምጥም ለመምሬ። |
ግዳይ አምሯቸው መቱ። እሳቸውም ሞቱ። ግጦ ከወጥ ባለጌ፤ መረን አግድም አደግ። ግፈኛ የሰይጣን መላክተኛ። |