Proverb
stringlengths
4
244
ዳክዬን ከውሃው፤ ፈረስን ከገለባው። ዳዊት በሹክሹክታ፤ ሰአታት በጋጋታ። ዳዊት በገናውን፤ ዕዝራ መሰንቆውን።
ዳዊትን ያህል መዝሙር፤ ጨለማን ያህል ጥቁር (የለም)። ዳዋ በበላ፤ ጎመን በደላ እንዱሉ።
ዳገት ለወዳጁ አይሰንፍ፤ ሀብታም ካለ ወዳጅ አይተርፍ። ዳገት ሲወጡ ጥግ ጥጉን፤ ዳቦ ሲበሉ ልብ ልቡን።
ዳገት ዕርሙ፤ ሜዳ ወንድሙ። ድል በመታደል፤ ሙያ በመጋደል። ድል እድል፤ በአንድ ድልድል። ድል፥ የባለ እድል።
ድሀ ለወዳጁ አይሰንፍ፤ ሀብታም ካለወዳጁ አይተርፍ።
ድሀ ማታ አሥር ይጠምዳል፤ ጧት አንድ ያጣል። (ማታ ~ በሕልሙ) ድሀ፥ ምን ትሠራለህ እንጂ፥ ምን ትበላለህ የሚለው የለም።
ድሀ ሰው ድሮ ከአረደ፥ ከኹለት አንዳቸው ቢታመሙ ነው። ድሀ ሲቀልጥ፥ አመድ አመድ ይሸታል።
ድሀ ሲቀልጥ፤ አመድ ይቀልጣል።
ድሀ ሲቀመጥ፥ እጁን ይ዗ህ አወዚው዗ው።
ድሀ ሲቀማጠል፥ ከወገቡ ቀምጠል። (ቀምጠል ~ ቅምጥል)
ድሀ ሲቆጣ ከንፈሩ ያብጣል፥ መንገደን ያሰልጣል። ድሀ ሲናገር ሬት ኮሶ፥ ሀብታም ሲናገር የማር በሶ። ድሀ ሲንቀባረር፥ ያለቀሰ ይመስላል።
ድሀ ሲቆጣ፥ መንገድ ያፈጥነዋል። (መንገድ ያፈጥነዋል ~ እግሩ ይፈናጠራል) ድሀ ሲቆጣ፥ እግሩ መንገድ ያሰልጣል።
ድሀ ሲያስለቅሱ፥ ከሥላሴ ይወቀሡ፥ መንግሥተ ሰማያትን አይወርሱ። ድሀ ሲያገኝ፥ ያጣ አይመስለውም።
ድሀ ቅቤ ወድ፥ ማን ሉሸከም ነድ?
ድሀ በሕልሙ ቅቤ ባይጠጣ ኖሮ፥ እከክ በወረሰው። (ኖሮ ~ ኑሮ) ድሀ በሕልሙ ቅቤ ባይጠጣ ኖሮ፥ እከክ ይጨርሰው ነበር።
ድሀ በሕልሙ ቅቤ ባይጠጣ፥ እከክ በፈጀው። (እከክ ~ ንጣት)
ድሀ በሕልሙ ቅቤ ባይጠጣ፥ እከክ ይጨርሰው ነበር። (ይጨርሰው ~ ይገድለው)
ድሀ በሕልሙ፥ ቅቤ ባይጠጣ (ኖሮ)፥ ንጣት ይገለው ነበር። ድሀ በሕልሙ ቅቤ ባይጠጣ፥ ንጣት በገደለው።
ድሀ በመሆኔ፥ ተባልኩኝ ቦ዗ኔ።
ድሀ በሽታ አያውቅም፤ ሀብታም ጤና የለውም። ድሀ፥ በቤቱ ንጉሥ ነው።
ድሀ በአመደ፤ ንጉሥ በ዗መደ። ድሀ በጉልበቱ፤ ባለጸጋ በከብቱ።
ድሀ ቢናገር አያደምቅ፤ ቢጨብጥ አያጠብቅ።
ድሀ ቢያስለቅሱ፥ ከሥላሴ ይወቀሡ፥ መንግሥተ ሰማያትን አይወርሱ። ድሀ ባይ፤ አይኔን አመመኝ።
ድሀ ተበድል ራሱ ይታረቃል፤ ሀብታም በድል ተመልሶ ይሥቃል። ድሀ አገር እንጂ፥ ቤት የለውም።
ድሀ ተበድል፥ ማሩኝ ይላል ቶል።
ድሀ እስኪለብስ፤ ሸንጎ ይበተናል። ድሀ ከንቡ፥ ይደላ። (ይዳላ ~ ይዳራ) ድሀ ከንቡ ይደላል።
ድሀ ከአለቀሰ፥ ቀኑ መች አነሰ።
ድሀ ከአልጣረ፥ ድሮ ከአልጫረ፥ ማን ያበላው ነበረ? ድሀ ከዕርሻ፥ ዳቦዬን ለማንሻ።
ድሀ ከአል዗ራ፤ ድሮ ከአልጫረ (ማን ያበላው ነበረ)? ድሀ ከአልጋረ፤ ድሮ ከአልጫረ።
ድሀ ውሃውን ጠጥቶ እሳቱን ይሞቃል፤ ሀብታም ስለ ገን዗ቡ ይጨነቃል። ድሀ የሚበላው እንጂ፥ የሚከፍለው አያጣም።
ድሀ የሚበላው እንጂ፥ የሚከፍለው አያጣም። (የሚበላው ~ ይበላው ~ ይከፍለው)
ድሀ ያልፍልኛል ይላል፤ ጌታ ቀኑን ይቆጥራል። ድሀ ያመልክት፤ ዳኛ ያሟግት።
ድሀ ይበላው እንጂ፥ ይከፍለው አያጣም። ድሀ ይ዗ረጋ፤ ደረቅ ቆዳ ይጮህ።
ድሀ ጉልበቱን፤ ባለጸጋ ከብቱን።
ድሀና ሹም ተሟግቶ፤ ድንጋይና ቅል ተማትቶ። (የማይሆን ነው ከቶ) ድሀና እመቤት፤ እልፍኝና ማድቤት።
ድሀና እጦት፤ አህያና አመድ (አይተጣጡም)። ድሀና ድመት፥ ሉሞት ሲል ያምርበታል። ድሀና ገበያ፥ ሳይገናኙ ይሞታል።
ድሀና ጌታ ተሟግቶ፤ ድንጋይና ቅል ተማትቶ የማይሆን ነው ከቶ። ድሀና ጨ጑ራ፥ እየጮኸ ይበሎል።
ድሀን ምን ትሠራለህ እንጂ፥ ምን ትበላለህ የሚለው የለም።
ድሀን ቢያስለቅሱ፥ በሥላሴ ይወቀሡ፥ መንግሥተ ሰማያትን አይወርሱ። ድሀን ከአስለቀሱ፥ በሥላሴ ዗ንድ ይወቀሡ።
ድሀን ፈርቼ፥ ደጄን በቀን ዗ግቼ። ድህነት፥ ከአምላክ መስማማት። ድህነት፥ ከአምላክ መስተካከል።
ድል ድል፤ እድልህ እንዳይጎድል። ድልህን፥ በርበሬ አስመሰገነው። ድመት ላመሎ፥ ዚፍ ላይ ትወጣለች።
ድመት መንኰሳ፥ መናከሷን አትረሳ። (መናከሷን ~ አመሎን) ድመት በታች ከሆነች፥ ታሸንፋለች ውሻን።
ድመት፥ ውስጥ ውስጡን አውሬ ናት። ድመትና ቁንጫ፥ ባድ ቤት ይወዳል። ድመትና አይጥ፤ እሳትና ጭድ። ድመትን፥ በቆል መጠርጠር።
ድመትን አይጥ ገደለቻት፥ ወይ ጥቃት ወይ ጥቃት። ድምፅና ቁንጫ፥ ባድ ቤት ይወዳል።
ድምፁን የማያሰማ ባል።
ድሪቶ ከነቅማሉ፤ መጥፎ ሰው ከነአመሉ ወዱያ በሉ። ድሪያ፥ የዝሙት ዋንጫ ዋዛማ።
ድር ቢያብር፥ አንበሳ ያሥር። ድር ቢያብር፥ ጋቢ ይሠራል። ድርብርብ፥ እንደ ደጋ ንብ። ድርና ማግ፤ ለሀጭና ልጋግ። ድርጎ ራቱ፥ ድርጎ ቢቀር ሞቱ።
ድርጎ የለመደች መበለት፤ ወተት ያየች ድመት። ድርጭት ፈንጠር፤ ምዝግዝግ ጎንደር።
ድሮ ላትበላው፥ ታፈስ።
ድሮ በልቶ ብስና፤ ጎመን በልቶ ጤና። ድሮ በልቶ ከብስና፥ ጎመን በልቶ በጤና። ድሮ በልጇ አንጀት ትጫወታለች።
ድሮ በማሰሮ፤ ገደል ለዝንጀሮ። (ማሰሮ ለድሮ ገደል ለዝንጀሮ) ድሮ በጋን።
ድሮ ቢያማት፥ በሬ ተሳሉላት።
ድሮ ቢጠፋ ከቤቱ፥ መነኮሰች እናቱ።
ድሮ ብታልም፥ ጥሬዋን። (ሕልም ብታይ ) ድሮ ብትታመም፥ በግ አረደላት።
ድሮ ነበር እንጂ፥ መጥኖ መደቆስ፥ አዅን ምን ያደርጋል? ወጭት ጥድ ማልቀስ።
ድሮ ከቆጥ፤ በሬ ከጋጥ።
ድሮ ከቤት ውላ፥ ዝናብ ይመታታል። ድሮ ከተከተተ፤ ጅብ ከአኮተኮተ። ድሮ ከአልበሎት፥ አሞራ ናት።
ድሮ ከአልጫረ፤ ድሀ ከአል዗ራ።
ድሮ ከአያታችን፥ ከአጤ ነው ትውልዳችን።
ድሮ ከጋጥ፤ በሬ ከቆጥ። (በሬ ~ አህያ)
ድሮ ከጮኸ ላሉት የለም፤ ከደብረ ታቦር ወዱያ ክረምት የለም። ድሮ ከጮኸ የለም ላሉት፥ ከቡሄ ወዱያ የለም ክረምት።
ድሮ ከጮኸ ላሉት፤ ከደብረ ታቦር ወዱያ ክረምት የለም።
ድሮ ካልጫረ፤ ድሀ ካል዗ራ።
ድሮ ጭራ መታረጃዋን፥ አወጣች ማረጃዋን። ድሮ:_ ጭራ የምታወጣው ምሥጢር።
ደሮ ጭራ ጭራ፥ አወጣች ማረጃዋን ካራ።
ደሮ ጭራ ጭራ፥ የራሷን አጥንት አወጣች።
ድሮ:_ ጭራ ጭራ መታረጃዋን ታወጣለች። ድሮ ጭራ ጭራ፥ ታወጣለች ካራ።
ድሮ፥ ሲሉ ሰምታ፥ ሞተች በጢስ ገብታ። (በጢስ~ ከጢስ ~ እጢስ ~ እጪስ)
ድሮ፥ ቢጠፋት፥ ብታስገኝልኝ በቅል እስጥሀለኹ ባል ተሳለች። ድሮ፥ ባሎ ሲሞት፥ ሞተች እጢስ ገብታ።
ድሮ፥ አንደን እንቁላል በወለደችበት፥ ወታቦ ትሞላለች። ድሮ እቤት ውላ፥ ዝናብ ትመታለች።
ድሮ፥ እኔ ባልበላው፥ ጭሬ አላፈሰውም ወይ አለች። ድሮ ከቆጥ፤ ሴት ከማጀት።
ድሮ(ን) ሲቀጣጥቧት፥ በመጫኛ ጣሎት።
ድሮም ላባ ሲሰርቅ እንጂ፥ ሲካፈል አይስማማም። ድሮም እንዳይሆን ነው፥ የቄስ ልጅ መኮንን (አለ)። ድሮም የቂጥ ወሮታው፥ ፈስ ነው።
ድሮና ቀበሮ፥ ተገናኝተው ጑ሮ። (ተገናኝተው ~ ተገናኝቶ) ድሮና ሴት ከቤት ውላ፥ ዝናብ ትመታ።
ድሮን ሲያታልሎት፥ በመጫኛ (ጠልፈው) ጣሎት። ድሮን ሲያታልሎት፥ አንቺ ሩጭ እኛ እንከተልሽ አሎት። ድሮን ሲያታልሎት፥ ጥምር መንግሥት አሎት።
ድሮን ሲያታልሎት፥ ፎቶ አነሧት። ድሮ(ን) ሲደልሎት፥ በመጫኛ ጣሎት። ድክተር ሲበዚ፥ በሽተኛ ይሞታል።
ድሮን ቢያማት፥ በሬ ተሳሉላት።
ድስት ግጣሙን አያጣም።
ድበላ፥ አንዳንድ ጊዛ ይበላ። ድንቀኛ ተ኱ሽ፥ ድር ይበጥሳል።
ድንቁርና፥ ከልብህ መካከል፥ ተራራ ያህል። ድንቢጥ እንደ አቅሟ በብዕር ትታገማለች። ድንቢጥ እንዳቅሟ፥ በብርዕ ትታገም። ድን኱ን ተገልጦ፤ ዙፋን ረግጦ።
ድንጋይ ለረገጠ ፍለጋ የለውም፤ ውሃ ለጠጣ ሽታ የለውም። ድንጋይ ላይ ተቀማጭ፥ የባለጌ ተለጣጭ።
ድንጋይ ሲያረጅ፥ መጭ ያበቅላል።
ድንጋይ በድንጋይ ላይ ትልቅ ቤት ይሆናል። ድንጋይ ቢቆሉት፥ አይሆንም ቆል።
ድንጋይ ቢያጎኗት፥ ተመልሳ ከአናት። ድንጋይ ትራሱ፥ ዳዋ ልብሱ፥ ኮቾሮ ጉርሡ። ድንጋይ እና ቅል አይፈናከቱም።
ድንጋይ ወርድ እ዗ብጥ ያርፋል፥ ያገኘው ይተርፋል።
ድንጋይ ወርድ ከ዗ብጥ ያርፋል፥ ሰው በሞቱ ወደ መቃብር ያልፋል።
ድንጋይ ወደ ሰማይ ቢወረወር፥ ተመልሶ (ወደ) ምድር።
ድንጋይ ውሃ ውስጥ ስለኖረ ዋና አይለምድም።
ድንግል አልቅሳ፥ አወጣች አንድ አበባ፥ ያን አበባ፥ አስረው ገረፉት እንደ ላባ።
ድንቢን ያየ ባለጌ።
ድንቢን ገልጦ፤ ዙፋን(ን) አጊጦ። (አጊጦ ~ አግጦ ~ ረግጦ) ድንገተኛ ስሕተት፤ የቁልቁለት ውድቀት።
ድከሚ ያላት ጥቁር ሴት፥ እጇን ትነቀሳለች። ድሀ ኹለት፤ ድንበር አለው።
ድክተሮች ሲበዙ፥ በሽተኛው ይሞታል።
ድግስ የላለው ዋዛማ፥ ምልክት የላለው ዛማ። ድግርና ገባር፥ ሲተካከል ያምር።
ድጥ ማንሸራተቱን፤ ባለጌ ማሽሟጠጡን አይተውም። ድማ ለመማሻ፤ ማረሻ ለመፈለሻ።
ጀማሪ ይጥፋ፤ ሰካራም ይትፋ።
ጀምሮ የማይፈጽም፤ ፈጭቶ የማያልም።
ጀምሮ ይጨርሳል፤ ለጉሞ ይተኩሳል አልሞ።
ጀርባ ለባለቤቱ ባዕድ ነው።
ጀርባ ጀርባው ይታያል። ጀርባው ከብድታል።