Proverb
stringlengths 4
244
|
---|
ጥራትና ንጋት፥ እያደር። ጥሬ ለድሮ፤ ግልገል ለቀበሮ። ጥሬ ጠብ፤ ድሮ ቀርቀብ። ጥሬና ነገር ሆድ ያሻክራል። |
ጥሬና ክፉ ንግግር፥ ሆድ ያሻክራል። ጥርሴስ ልማደ ነው፥ አይኔን አታሥቀው። |
ጥርስ የላላት፥ ጥርስ ያላትን ነክሳ፥ አነካከስ ታስተምራለች። |
ጥርስ፥ ለብርድ ይሥቃል። (ለብርድ ~ ለነፋስ) ጥርስ ሳይገጥ፤ ከንፈር ሳይገለጥ። |
ጥርስና ከናፍር፥ ቢደጋገፍ ያምር። (ቢደጋገፍ ~ ተደጋግፎ ~ ሲደጋገፍ) ጥርስና ከንፈር አብሮ ይደማል። |
ጥቁር፥ አሥር ቢበላ አይነጣም። |
ጥቂት ሕመም ታመህ፥ ወዳጅ ጠላትህን እየው። ጥቂት ሥጋ፥ እንደ መርፌ ትወጋ። |
ጥቂት ሽሮ፤ ማታ ድሮ። |
ጥቂት ያለው ዅሉ፥ ብርቁ ነው። ጥቂት ያላት፥ እረፍት የላት እንቅልፍ። |
ጥቂት ጥቂት ዔሉም ትኼዳለች፥ ከአሰበችበት ትደርሳለች። ጥቃት ከጥንብ ይገማል። |
ጥቅልል ላለ ጠጉር፥ ርር ያለ ሚድ። |
ጥቅልል ያለን ጠጉር፥ ርር ያለ ሚድ ያነሣዋል። ጥበበኛ ባሪያ፥ ጌታውን ይገዚል። |
ጥበብ ያስከብራል፤ ሀብት ያስጨፍራል። ጥበብና ዕውቀትን፤ ማስተዋልና እውነትን። ጥኑ ወዳጅ፤ ጥኑ ጠላት ይሆናል። |
ጥኑ ወዳጅ፤ ጥኑ ጠላት፤ ጥኑ ጠላት፤ ጥኑ ወዳጅ ይሆናል። ጥንብ ባለበት፥ ቁራ ይዝራል። |
ጥንብ ባለበት፥ ጅብ አያጡም። ጥንቱ የተውሶ፥ ያውም ጠፋ ጨርሶ። |
ጥንቱን ሲሉህ ቡዳ፥ ቆዳ ይህ ሜዳ። ጥንቱን ባልፈንሽ፥ ከፈንሽም ባላሳፈርሽ። ጥንቱንም ባልፈንሽ፥ ከፈንሽ ባላፈርሽ። ጥንቱንም የተውሶ፥ ያውም ጠፋ ጨርሶ። |
ጥንቱንም የተውሶ፥ ጠፋ ተመልሶ። (ተመልሶ ~ ጨርሶ) |
ጥንት የነበረ ሃይማኖት ተዋሕድ ነበር፥ ቅባት ካራ የሚሉ ሃይማኖት ተጨምሮ፥ ሥጋ አለቀ ንድሮ። |
ጥንቸል እንደ አቅሟ ታግታለች። |
ጥንቸል እንደ ዝኆን እጮሀለሁ ብላ ተሰንጥቃ ሞተች። ጥንቸልም ለሆዶ ዝኆንም ለሆደ አብረው ውሃ ወረደ። ጥይት እይር፤ ፈትል ድውር። |
ጥይት፥ የፈራትን ትወጋለች። |
ጥይትና ማጣትን፥ ተኝቶ ማሳለፍ ነው። ጥድ ለል። |
ጥጃ መጫወቷ እንጂ፥ መራገጧ አያምርም። ጥጃ ሲጠባ፥ በአፉ እናቱን ይለትማል። |
ጥጃ ሣር ይበላል፤ ቤቱ ዕዳ ይሞላል። |
ጥጃ በጥሶ ኺድ ማሰርያው ይጮሀል፥ ቅሉ ተሰብሮ ወተቱ ተሰቅሎል። ጥጃ ቢሳሳት ከእናቱ፤ ነገር ቢሳሳት ከጠዋቱ። |
ጥጃ ቢሳሳት ከእናቱ፤ ነገር ቢሳሳት ከጠዋቱ፤ ሰይፍ ቢመለስ ከአፎቱ። ጥጃ ቢፈነጭ በሜዳ፤ ውሃ ቢሮጥ በጎድዳ ቢኼድ። |
ጥጃ ጠባ፥ ከሆድ ገባ። |
ጥጋበኛ ከርከሮ፥ የነፍጠኛ ጎጆ ይታከካል። ጥጋበኛንና ውሃ ሙላትን፥ ቁመህ አሳልፈው። ጥጋቡን የማይችል፥ አህያ ነው። |
ጥጋብ ቢሻህ ባቄላ፤ ኑሮ ቢሻህ ችላ። |
ጥጋብ ቢያምርህ ጠላ፤ መግዚት ቢያምርህ ችላ። ጥጋብን ወደኛ በል፤ ጥጋበኛን ወዱያ በል። ጥጋብን የማይችል፥ አህያ ነው። |
ጥጥ ለፈታይ፥ ሽልማት ላገልጋይ። |
ጥጥ ቂጥ ይወዳል ቢሎት፥ ጠቅልላ ቁጭ አለችበት። ጥጥና ሹም፥ እያደር ይከዳል። |
ጥፌ ለችፌ። |
ጦሙን የሚውል ሆድ፥ ማለዳ ይርበዋል። ጦም ከማደር፤ ዳቦ ቀርቅር። |
ጦም የሚያድር ሆድ፥ በጠዋት ይራባል። ጦር ለወረወረ፤ መሬት ለገበረ። |
ጦር ለወረወረ፤ ጎራዳ ለሰነረ። ጦር መጣ፤ ሲባል ሶማያ ቆረጣ። ጦር ሲመጣ፤ ዚቢያ ቆረጣ። |
ጦር እንደ ወረወሩት፤ ጎራዳ እንደ ሰነሩበት። ጦር እንደ ወጊው፤ ልጅ እንደ አሳዳጊው። |
ጦር ከወጋው፤ ምላስ የወጋው። ጦር ከፈታው፤ ወሬ የፈታው። |
ጦር ከፈታው፤ ወሬ የፈታው ይብሳል። (ይብሳል ~ ይበዚል) ጦርና ጭሬ፤ አራሽና ገበሬ። |
ጦጣ ባለቤትን ታስወጣ። ጦጣ፥ ተይዚ ትፍን። |
ጦጣ ከዚፍ ላይ ሆና፥ ከአንበሳ ጋር ጸብ ትጭራለች። ጦጣና ዝንጀሮ፤ ተኩላና ቀበሮ። |
ጦጣ፥ መጀመሪያ የመቀመጫዬን አለች አሉ። ጦጣ ምን ትወጃለሽ ቢሎት፥ ከዚፍ ላይ ትግል። ጦጣ በልታ፥ በዝንጀሮ አፍ አበሰች። |
ጦጣ፥ ባለቤቱን ታስወጣ። (ባለቤቱን ~ ባለቤቷን) ጦጣ፥ ባለቤቱን አስወጣ። |
ጧሪ በፈጣሪ። |
ጧሪና ተዝካር፤ አውጪ አያሳጣህ። ጧት ከበላተኛ፤ ማታ ከዕድምተኛ። ጧት ከበላተኛ፤ ማታ ከጦመኛ። |
ጧት ከበላተኛ፤ ማታ ከጦመኛ፤ እንደ ሽመላ በኹለት ይበላ። ጧፍ ያበራል፤ ከሳሽ ይመራል። |
ጨለማ ለብሶ የሚመጣ፥ ክፉ ነው። ጨልጠሽ ጋግሪ፤ ካለ ፈጣሪ። |
ጨምሪ ጨምሪ፥ በወንድ ልጅ ተበከሪ። |
ጨረቃ ብትደምቅ አታሞቅ፤ የሰው ቤት አያደምቅ። ጨረቃ ብትደምቅ፥ አትሞቅ። |
ጨረቃና ሴት፥ ዚሬ ብርሃን፥ ነገ ጽልመት። ጨርቅ አጠርቅሞ፤ መስቀል ተሸክሞ። |
ጨቅጫቃ ሚስትና፤ የሚያፈስ ቤት አንድ ናቸው። ጨቅጫቃ ባል፤ የሚያፈስ ቤት። |
ጨብጦ የቀረ፤ ተጨብጦ ቀረ። ጨካኝ፥ ሰይጣን መሳይ። |
ጨካኝ አልሞተ፥ ፈሪም አልሞተ፥ አጉለኛ ሞተ። ጨካኝና ጭስ መውጫ አያጣም። |
ጨዋ አይነቅፍ፤ እሳት አይታቀፍ። ጨዋታ ለአዋቂ፤ ወሬ ለጠያቂ። ጨዋታን አዳምጦ፤ እህልን አላምጦ። ጨዋነሽ ቢሎት፤ ሣቁ ገደላት። |
ጨው ለራስህ ስትል ጣፍጥ፥ አለዙያ ድንጋይ ነው ብለው ይጥሉሀል። ጨው ለራስህ ስትል ብትጣፍጥ፥ ጣፍጥ። ባትጣፍጥ? ድንጋይ ነው ብለው |
ጨው ለራስህ ብለህ ጣፍጥ፥ አለበለዙያ ድንጋይ ነው ብለው ይወረውሩሀል። |
ጨው ሲበዚ ያቅራል፤ በርበሬ ሲበዚ ይመራል። ጨው ሻጭ በገበያ፤ ጦር በሶማያ። |
ጨው ቢያልጥ በምን ይጣፍጣል? ዳኛ ቢደላ በማን ይሟገቷል። ጨው የላለው ምግብና ሰው የላለው ሰው አንድ ነው። |
ጨው ይወደኝ ብለህ ጣፍጥ፥ አለበለዙያ ግን ድንጋይ ነው ብለው ይጥሉሀል። |
ጨውተው ወይም አጫውተው። ጨውና በርበሬ፤ ጆሮና ወሬ። |
ጨራ ለመፍጨት፤ አንጀት ለመጎተት ብለው ዋተት ዋተት። |
ጨራና እግር ሳይሸት፤ ሽማግላና አሮጊት ሳይሸብት (እንዳት ይሆናል። ) ጩኸት ለሲላ፤ መብል ለአሞራ። (ለሲላ ~ ለቁራ) |
ጩሀ የማታውቅ ወፍ እርሟን ብትጮህ፥ ዕለቁ ዕለቁ። ጫማ ምንም ወርቅ ቢሆን፥ ከእግር በታች ነው። |
ጩኸት ለአሞራ፤ መብል ለቁራ። |
ጫማ የለንም ብለው የሚያጉረመርሙ፥ እግር የላላቸውን አይተው ይጽናኑ። ጫማ የለኝም ብለህ አትን፤ እግር የላለው አለና። |
ጫማን፥ መደብ ላይ አያወጡም። ጫት ሳይቅሙ ምርቃና። |
ጫን ካለ፥ ጫን ይፈጃል። |
ጫን ያለው ኮርቻውን፤ ለምን ያለው ስልቻውን (አያጣውም)። ጫንቃዬን ተገርፌ፤ ጨርቄን ተገፍፌ። |
ጫጩትን አትቁጠር፥ አይሆኑም አጥር። ጭልፊትና ሲላ ተጋብተው ጉጉት ጭልፊትን የወደደ መንጠቅን የለመደ። |
ጭምት ሲሞት ልቡን፤ ንጉሥ ሲሞት ግንቡን። ጭምት ያበደ እንደሆን፤ የጤፍ ቆረን ደኑ። ጭምጭምታ፥ ክፉኛ ያስመታ። |
ጭራሮ፥ የምጣድ ጐረሮ። |
ጭራሮ~ ሰንበላጥ~ ብልኬት~ አስቤስቶስ ~ ኖራ የነገሩ ኹነኛ፤ የጦሩ አርበኛ። |
ጭሰኛ ከአለበት፥ እሳት አይጠፋም። ጭስ እጨሰበት፥ እሳት አይጠፋም። ጭስ ካለ፥ እሳት አለ። |
ጭቃን ማጠብ እንጂ፥ ማስለቀቅ አይቻልም። ጭቅጭቅ ነው፥ አቶ ጨረች ገዝተኹ ልበሱ። |
ጭብጥ ቆል ይህ፥ ተአሻሮ ተጠጋ። (ተአሻሮ ~ ከአሻሮ ~ ወደ አሻሮ) ጭብጥ ያዥ፤ ውርድ ነዥ። |
ጭነት ሽንብራ፤ በመቀንጠብ ያልቅ። |
ጭንቅ ሲመጣ የሚወደት ይቀር፤ ልጅ ሲመጣ ወላጅ ይቀር። ጭንቅ አልጋ ያስታቅፋል። |
ጭንቅ ያለመቃብር የለም። |
ጭንቅላትህ ከቅቤ የተሠራ ከሆነ፥ ዳቦ ጋጋሪ አትኹን። ጭድ ይዝ እሳት፤ ሳል ይዝ ስርቆት። |
ጭድ ይዝ ወት፤ ሳል ይዝ ስርቆት። ጭድና ጭቃ፥ ቡሀና ቦቃ። |
ጭጭ እንደ ጫጩት፥ እንደዝረው ጭልፊት። |
ጮሀ የማታውቅ ወፍ አንድ ቀን ብትጮህ፥ እለቁ እለቁ አለች። ጮላ ሲያረጅ፥ መጋዣ ይሆናል። |
ጮማ ሥጋ የበላችኹ፥ ጎመን ቅጠል የበላነ፥ ነሀሴን አብረን ትክክል ወጣነ። ጮማ በልቶ ከብስና፤ ጎመን በልቶ በጤና። |
ጳጉሜ ቢለግስ፥ ጎታህን አብስ። |
ጳጉሜ ቢወልስ፥ (ገበሬ) ጎተራህን አብስ። |
ጳጉሜን ሲወልስ ጎታህን አብስ፤ ጳጉሜን ብራ አህያህን አብላ። |
ጸልት በጽሞና፤ ነገር በደመና። ጸልት በፍቅር፤ ሃይማኖት በምግባር። |
ጸልት ከፍቅር፤ ሃይማኖት ከምግባር ይበጃል። ጸልት ከፍቅር፤ ሃይማኖት ከግብር። |
ጸልት ያለ ፍቅር፤ ሃይማኖት ያለ ግብር አይረባም። ጸደቅኩ ብዬ ባዝላት፥ ተንጠልጥላ ቀረች። ጸጉራም ውሻ፥ አለ ሲሉት ይሞታል። |
ጸጸት እያደር ይመሠረት። |
ጺም የላለው መምህር፤ አጸድ የላለው ደብር። ጻድቃን ሳይቀጣጠሩ ይገናኛሉ። |
ጻድቃን ሳይቀጣጠሩ ይገናኛሉ፥ ኀጥአን ግን በተቃጠሩበት ይተጣጣሉ። ጻድቅ ሰባት ጊዛ ቢወድቅ፥ ሰባት ጊዛ ይነሣል። |
ጻድቅ ተኩላ፥ የበግ ላት ይልሳል። ጽሕፈት በብራና፤ ፈን በበገና። ጽኑ ወዳጅ፤ ጽኑ ጠላት ይሆናል። ጽዋ በተርታ፤ ሥጋ በገበታ። |
ጽዋውን የገለበጡ፤ ጋኑን የጨለጡ። ጽዳት ለምኔ፤ ቁናስ ባሕላ። |
ጽዳት ከራስ፤ ምሕረት ከመቅደስ (ይጀመራል)። |
ፀሓይ ሳለ ሩጥ፤ አባት ሳለ አጊጥ። |
ፀሓይ ሳለ ይሮጧል፤ አባት ሳለ ያጌጧል። ፀሓይ ብልጭ፤ ወፍ ጭጭ ሲል። |
ፀሓይ እያለች የአላስቀመጡት፥ ሲመሽ አያገኙትም። |
ፀሓይ እያለች፥ የመሸበት (አታድርገን)። |
ፀሓይ ከአልወጣ ከሰፈረበት አይነሣ አንበጣ፤ ሴት ምክንያት አታጣ። ፀሓይ የጠዋት፤ አደኛ የሽበት። |