Proverb
stringlengths
4
244
ለኀጥአን የወረደ መዓት፥ ለጻድቃን ይተርፋል። ለኀጥአን የወረደ፥ ለጻድቃን ይተርፋል። ለዅሉም ጊዛ አለው።
ለነገረኛ መንገድ፤ ለሆዳም ገበታ ይተዋል። ለነገረኛ ሰው፥ ጀርባህን ስጠው።
ለነገረኛ ነገር ተውለት፤ ለሆዳም እህል አቅርብለት። ለነገር ዋነኛ፤ ለጦር አርበኛ።
ለነፍስህ፥ ገዳም አለልህ።
ለንጉሥ የማይረዳ፤ ከባሕር የማይቀዳ። ለንጉሥ የማይገዚ፥ ለእግዙአብሔር(ም) አይገዚ።
ለንጉሥ የቀነቀነ ወርቅ፤ ለእግዛር የቀነቀነ ጽድቅ።
ለንጉሥ ያልረዳ፤ ከባሕር የማይቀዳ። (የማይቀዳ ~ ያልቀዳ) ለንፉግ ሰው፥ የገበያ መንገድ ይጠበዋል። (ይጠበዋል ~ ይጠበው) ለአህያ ማር አይጥመውም።
ለአህያ ማር አይጥመው፤ ለደንቆሮ ምክር አይገባው። ለአህያ ማር አይጥማት፤ ለሴት ምክር አይገባት። ለአህያ ማር አይጥማት(ም)።
ለአህያ ያልከበደው፥ ለመጫኛ ከበደው። ለአህያ ፈስ፥ አፍንጫ አይዙለትም። ለአለው፥ ቅንጭብ ያረግዳል።
ለአለው ይሰጡታልም፥ ይጨምሩለታልም። ለአለው ይጨመርለታል።
ለአለፈ ነገር፥ ቤት አይሠራለትም።
ለአለፈ(ው) አይጸጸቱም፤ ለሚመጣው አይበለጡም።
ለአለፈ(ው) ክረምት፥ ቤት አይሠራለትም። (አይሠራለትም ~ አይሠራም) ለአለፈው ክረምት፥ ውሃ ማቆር አይቻልም።
ለአለፈው ጸልት፥ ከንቱ ጩኸት። ለአሉ ያሉት፥ ለአለዊ ሆነለት። ለአላወቀ(ው) ፎገራ ደር ነው። ለአላየ ልጅ፥ ዳቦ ፍሪዳው።
ለአላየው የሚያስገርም፤ ለሰማው የሚያስደንቅ። ለአላዩ ልጅ፥ ዳቦ ፍሪዳው።
ለአሣር የጣፈው፥ ቢነግድ አይተርፈው። ለአሽከር አደግ፥ ጌታ አትደር።
ለአበባ የለው ገለባ፤ ለወሬ የለው ፍሬ። ለአባይ ልጅ፥ ውሃ ነሡት።
ለአበባ፥ የለው ገለባ።
ለአቤቱታ፥ የለው ይሉኝታ።
ለአንበሳ አታበድር፥ ከአበደርክ አትጠይቅ።
ለአንበሳ አይመትሩ፤ ለብልኅ አይመክሩም። (አይመክሩም ~ አይነግሩም) ለአንበሳ አይመትሩ፤ ለአዋቂ አይነግሩ። (አይነግሩ ~ አይናገሩ)
ለአንተ መምከር፥ ጥቁር ድንጋይ ላይ፥ ውሃ ማፍሰስ ነው። ለአንተ የተባለ እንጀራ ላላ አያገኘውም፥ ሻግቶ ይቀራል እንጂ። ለአንተ ያለውን እንጀራ ይሻግታል እንጂ፥ ማንም አይበላውም። ለአንቺ ቁምነገርሽ፥ በሶብላ ወጥሽ።
ለአንቺ ብርቅሽ፥ በሶብላ ወጥሽ። ለአንቺ ብርቅሽ፥ የ዗ንጋዳ ሙቅሽ።
ለአንደ የ዗ነበለት፥ ለላላው ሳያካፋ አይቀርም። ለአንድ ብርቱ፥ ኹለት መድኀኒቱ።
ለአንድ አልሚ፥ ዗ጠኝ ቋሚ። (አልሚ ~ አራሚ) ለአንድ ያሉት፥ ለኹለት ይተርፋል።
ለአንድ ጭቃ አገር፥ ዗ጠኝ ምስለኔ። ለአኩራፊ፥ ምሳው ራት ይሆነዋል። ለአወቀባት፥ ገረገራም ዋልድባ ናት። ለአዋቂ ምክር፤ ላላዋቂ በትር።
ለአዋቂ አትወቅበት፤ ለረጅም አትከንዳበት። ለአዋቂ አይነግሩ፤ ለአንበሳ አይመትሩ። ለአዋጅ ነጋሪት፤ ለጥጥ ልቃቂት።
ለአያቱ ዕዳ፤ ለአማቱ ፍሪዳ። ለአይነ ስውር መስተዋት። ለአይን አምላክ አለው።
ለአይን የሚከፋ፤ ለአፍንጫ የሚከረፋ። (የሚከረፋ ~ ይከረፋ) ለአይንና ለወዳጅ ጥቂት ይበቃል። (ይበቃል ~ ይበቃዋል) ለአገልጋይ ትዕግሥት፤ ለባለቤት መጠቃት።
ለአገሩ ባዳ፤ ለሰው እንግዳ። ለአገሩ እንግዳ፤ ለሰው ባዳ።
ለአገሩ ፊደል እንግዳ፤ ለአባቱ ቋንቋ ባዳ። ለአገሬ ሰው እን኱ን ነጋሪት፥ አታሞ አይሰጠው። ለአጠፋ ምሕረት፤ ለአጣ ቸርነት።
ለአፈ ግም፤ አፍንጫ ድፍን ያዝለታል።
ለአፈኛ ሰው መመለስ፤ ለትኋን ል጑ም ማጉረሥ። ለአፈኛ ሰው፥ ገደልም ሜዳ ነው።
ለአፉ ለከት የለውም። ለአፍ ዳገት የለውም።
ለአፍ ግም፤ አፍንጫ ድፍን ያዝለታል። ለአፍላ፥ የለው ጎፍላ።
ለአፍታ የለውም ፋታ።
ለእርድ የቀረበ በሬ፥ ቢላዋ አይፈራም። ለእሮሮ ሳይሆን፥ ለአመክሮ።
ለእሳት ዕንጨት፥ ካልነሡት አይጠፋም። (ካልነሡት ~ ካልነፈጉት) ለእሳት ውሃ፤ ለጠጉር ቡሀ።
ለእሳት ፍላት፤ ለጮማ ሥባት።
ለእበጥ ፍላት፤ ለዕንጨት እሳት። ለእባብ እግር የለው፤ ለባዳ ውል የለው።
ለእብለት ሥር የለው(ም)፤ ለእባብ እግር የለው(ም)። ለእብድም ቢሆን ባል አይጠፋም። (ባል ~ ሚስት) ለእኔ ቆንጆ፥ ለሰው ግን አይጥ።
ለእኔ እናት ምን በጃት? ( ተሻላት ~ ረባት)
ለእኔ እናት ምን ደላት? ያም አፈር ያም ድንጋይ ጫነባት። ለእንቁጣጣሽ ያልሆነ፥ ቀሚስ ይበጣጠስ።
ለእኔ፥ ነግ በእኔ።
ለእዙህ ሆዳ፥ ጠላኝ ዗መዳ። ለእጅ ርቆ፤ ለአይን ጠልቆ።
ለእግሩ የተጸየፈ፤ ለቂጡ አስተረፈ። ለእግር የተጸየፈ፤ ለራሱ አተረፈ። ለእግር የፈሩት፤ ለቂጥ ይተርፋል።
ለእግዙአብሔር የቀነቀነ ለጽድቅ፤ ለጌታ የቀነቀነ ለወርቅ። ለእግዛር የተቀናቀነ ጽድቅ፤ ለንጉሥ የተቀናቀነ ወርቅ። ለከለላ ጥላ፤ ቢርብህ ብላ።
ለከርሞ የሚያብድ፥ ዗ንድሮ ሱሪውን ከፍ ከፍ ያደርጋል። ለከርሞ ድሮ፤ እንቁላል ለ዗ንድሮ።
ለከሳሽ የለው መላሽ።
ለካህን ጥምቀት፤ ለገበሬ ግንቦት። ለክፉ ያሉት፥ ለበጎ ይበጃል። ለክፋት ያደለው፤ አሳዳጊ የበደለው። ለኮ መሳቢያ፤ ወፍጮ ማላሚያ። ለወሬ ሞትዅ።
ለዅሉም አጥንት፥ የለው መቅን። ለኺያጅ፥ የለውም ወዳጅ። ለሕልም ምሳላ የለውም።
ለወሬ ሞትኩ፤ ለእህል (ተ)ሰለፍኩ። ለወሬ ወዳጁ ወሬ፤ ለመነኰሴ ጥሬ። ለወሬ የለው ፍሬ።
ለወሬ የለው ፍሬ፤ ለአበባ የለው ገለባ።
ለወሬ የቸኮለ፥ እናቱን በመንገድ (ላይ) ይረዳል። ለወርቅ ያሉት አንገት ላሽክት።
ለወቀጣ አንድም ሰው አልመጣ፤ ለመጠጡ ከየጎሬው ወጡ። ለወታደር፥ ሰፊ መንደር።
ለወታደር ሰፊ መንደር፤ ለወዱላ መልካም ደላ። ለወይ዗ሮ፥ መልካም ድሮ።
ለወደላ፥ መልካም ደላ።
ለወደደት:_ ሰው ልብ ደንገጥ፥ ሹሩባም ዗ርገፍ ይላል። ለወዱላ፥ መልካም ደላ።
ለወዳጁ የሚፈተፍት፤ ለጠላቱ የሚመክት። ለወዳጅ የማር ወለላ፤ ለጠላት አሜኬላ። ለወዳጅ ጠላት፥ አለመተኛት።
ለወዳጁ:_ እሳት ይዞል በእጁ።
ለወዳጅና ለአይን፤ ትንሽ ይበቃዋል። ለወገን ጽናት፤ ለጠላት ቅናት።
ለወጡ ዕ዗ኑለት፤ ከእንጀራውም ጉረሡለት። ለወጡ ጊዛስ፥ ከደረቁም ጉረሡለት።
ለወጡም ዕ዗ኑለት፥ አንዳንድ ጊዛ ደረቅ ጉረሡለት። ለወጡም ዕ዗ኑለት፤ ከእንጀራውም ጉረሡለት። ለወጡም ዕ዗ኑለት፤ ከደረቁም ብሉለት።
ለወጥ የሚሻል፥ ቅልውጥ።
ለዋስ አፍ የለው፤ ለጉንዳን ደም የለው። ለዋንጫ ቡሽ፤ ለውሃ ጉሽ የለውም። ለውሻ ምሳ የለው፥ ራት ብቻ።
ለውሻ ሞት፥ ፊት አይነጩለትም።
ለውሻዬ ያልኹትን፥ ልጄ ቢበላብኝ አልወድም።
ለውሽማ ሞት፥ ፊት አይነጩለት(ም)። (አይነጩለት(ም) ~ አይነጭለት(ም)) ለውጡኝ ባይ፥ የሚሻለውን አውቆ።
ለዓመት ልብስ፤ ለዕለት ጉርሥ። ለአማርኛ ግእዝ (ነው) ዳኛ። ለአምላክ ልንገረው፥ ለማያስቀረው። ለአምጪ(ው) ይግደደው።
ለዕውር ዝማሜ፤ ለመላጣ ጋሜ (አይስማማውም)። ለእውነት ማማ፤ ለውሸት ጨለማ።
ለዝናብ ጌታ፥ ውሃ ነሡ(ት)።
ለዝንብ፥ ከትላንት ወዱያም ድሮ ነው። ለይቶ እንደፈፋ፤ አን጑ል እንዳረፋ።
ለይቶት፥ አባ ንጉሧ። ለደኅና ሰው፥ ዋጋ አነሰው።
ለደኅና ሰው ውሸት፤ ለጅብ እሸት። ለደረቅ የመጣ እሳት፥ ርጥብን ያነዳል። ለደብተራ፥ መቋሚያና ጭራ።
ለደደብ ማስረዳት፥ ድንጋይ ቅቤ መቀባት። ለደግ ንጉሥ፥ ዕለት ዕለት ማልቀስ። ለዱያብልስ ፀሩ መታገስ፤ ለረኃብ ፀሩ ማረስ። ለዳርቻው ሲሣሡ፥ መካከሉን ተነሡ። ለዳርቻው ሲሣሡ፥ ከነመሀሉም ተነሡ። ለዳርቻው የሣሡ፥ መሀሉን ተነሡ።
ለዳባ ለባሽ፥ ነገርህን አታበላሽ። ለዳኛ አመልክት፥ እንዱሆን መሠረት። ለዳኛ የነገሩት፤ በርጥብ ያቃጠሉት። ለዳኛ ዳኛ፤ ለአንበሳ ተኩላ አለው። ለድሀ፥ ማን ሰጠው ውሃ።
ለድሪ ያሉት አንገት፥ ለአሽክት። ለድንገቱ፥ ከእግሬ ስንድድ አለበቱ። ለድንጋይ፥ የለው አይን።
ለድሮ አጥንት፥ መጥረቢያ አያስፈልገውም።
ለድካም የጣፈኝ፥ ብነግድ አይተርፈኝ። ለድሮ ሲነግሩ፥ ምጥማጥ ይሰማል።
ለድህነት የፈጠረው፥ ቢነግድ አያተርፍም። (አያተርፍም ~ አይተርፈው) ለድሪ ያሉት አንገት፥ ለአሸንክታብ።
ለጅል ከመንገር፥ የአንድ ቀን ጎዳና መኼድ ይሻላል። ለጅብ፥ አንጀትን ል጑ም አያደርጉም።
ለጅብም፥ እንዳንተ ያለ ወንድም አለው። ለጆሮ አጥር የለውም።
ለጆሮ ጥርስ፤ ለሆዳም ሥሥ። ለገላጋይ ደም የለውም። ለገበሬ፥ መልካም በሬ። ለገቢህ ተንገብገብ።
ለገና ጨዋታ፥ አይቆጡም ጌታ። ለገደለ ጎፈሬ፤ ላረጋገጠ ወሬ። ለገዳም የረዳ፥ አይጎዳ።
ለጉንዳን ደም የለው፤ ለዝንብ ቤት የለው። ለጉንፋን ምሱ፥ ገንፎ በትኩሱ።
ለጋስ ቢለግስ፥ አበደረ እንጂ (እንዱያው) አልሰጠም። ለጌታ የነገሩት፤ በሠኔ የተከሉት አይጠፋም።
ለጌታም ጌታ አለው።
ለጎበዝ ሰንጋ ፈረስ፤ ለፈሪ ፍርፋሪ። ለጎበዝ፥ ስጠው ሰንጋ ፈረስ።
ለጠጪ ሰው፥ የመጠጥ ወሬ አውራው። ለጣይም ፈንጋይ ያዝለታል።
ለጥልና ለዳኛ ያለው ገን዗ብ፥ አፋፍ ይቆያል።
ለጥምቀት እታጭ ያለች ሙሽራ፥ መስክ አደረች ለከተራ።
ለጥምቀት እንሶስላ ያልሞቀች ኮረዳ፤ በእንተ ማርያም የሚል የቆል ተማሪ ሳይዝ አቁማዳ።
ለጥምቀት ያልሣሡት እንግጣ፥ በወሩ ሙሽራ ያመጣ። (እንግጣ ~ እስክስታ) ለጥምቀት ያልታጨ፤ በሠኔ ያልተላጨ።
ለጥምቀት ያልሆነ ቀሚስ ይበጣጠስ። ለጥምቀት ያልሆነ ዝማሬ፤ ለሠኔ ያልሆነ በሬ።
ለጥርጣሬ ምንጣሬ።
ለጥቅም ሲታጠቁ፥ ከጎን ይጠንቀቁ። (ከጎን ~ ጎንዎን) ለጥፋት የታ዗዗ች ከተማ፥ ነጋሪት ቢጎሰም አትሰማ። ለጦም ግድፈት፤ ለበዓል ሽረት።
ለጨለማ ጊዛ መብራት፤ ለመከራ ጊዛ ብልኀት።
ለጨቅጫቃ ሰው ከማበደር፥ ይሻላል በእጄ ማደር። (በእጄ ማደር ~ በእጅ ማሳደር)
ለጨዋ ልጅ ሸማህን፤ ለባለጌ በቅልህን አታውስ። ለጭሰኛ መሬት፤ ለሣር ቤት ክብሪት።
ለጾም ግድፈት፤ ለባል ሽረት። ለፈረስህ አንገት፤ ለጋሻህ ዕንብርት። ለፈሪ ምድር አይበቃውም።