topic
stringlengths
16
333
news
stringlengths
16
46.2k
ያላቆመው የአፍሪቃውያን ስደት
በህገ ወጥ መንገድ ከአፍሪቃ ወደ አውሮፓ እንሰደዳለን ብለው አሁን ድረስ በሊቢያ እስር ቤቶች የሚማቅቁ አሉ። ሌሎች ደግሞ በረሃ እና ባህር አቋርጠው አውሮጳ ለመግባት ሲሉ ህይወታቸውን አጥተዋል። ምን ያህል ፈታኝ እንደሆነ በየጊዜዉ ቢነገርም ሰዎች ግን አሁን ድረስ ይሰደዳሉ።
ውይይት ሙስና እና የእስር ዘመቻ
ኢትዮጵያ መንግስት ካለፈው ሳምንት ወዲህ በሙስና ተጠርጥረዋል ያላቸውን የመንግሥት ኃላፊዎች እና ባለሀብቶችን አስሯል። አሁን ቁጥራቸው ከደረሰው የታሰሩት የመንግሥት ሰራተኞች መካከል ብዙ ከፍተኛ የሚባሉ ይገኙባቸዋል።
የአሜሪካ ፕሬዝዳንት መልዕክተኛ ከኢትዮጵያ መልስ ምን አሉ
ሴናተር ኩንስ በአሜሪካ ሕግ መወሰኛ ምክር ቤት የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ ስብሰባ ላይ ትናንት እንደተናገሩት ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድና ከሌሎች ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር ያደረጉት ውይይት አዎንታዊ ውጤት የታየበት ነው የዩናይትድስቴትስ ፕሬዚዳንት ልዩ መልዕክተኛ ሴናተር ክሪስ ኩንስ በኢትዮጵያ ያደረጉኝት ጉብኝት ገንቢ ውጤት የተገኘበት መሆኑን አስታወቁ ሴናተር ኩንስ በአሜሪካ ሕግ መወሰኛ ምክር ቤት የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ ስብሰባ ላይ ትናንት እንደተናገሩት ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድና ከሌሎች ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር ያደረጉት ውይይት አዎንታዊ ውጤት የታየበት ነው በትግራይ ክልል የተሟላ የሰብዓዊ ዕርዳታ አቅርቦት እንዲኖር መስራት ግጭትና ጥላቻን ማስወገድ እንዲሁም ነፃና ፍትሐዊ ምርጫን ማመቻቸት በቀጣይ ትኩረት የሚሹ ጉዳዬች መሆናቸውንም ሴናተሩ አመልክተዋል ታሪኩ ኃይሉ
በፀረ ሽብር አዋጅ የተከሰሱ የኪነ ጥበብ ሰዎች
ሳውዲ አረብያ ህገ ወጥ የምትላቸው የውጭ ዜጎች ከሀገርዋ እንዲወጡ ያስቀመጠችውን ቀነ ገደብ ለአንድ ወር ማራዘምዋ የተፋሰሱ ሀገራት ጉባኤና የዉሃ ፣የመስኖና የኤለክትሪክ ሚንስቴር መግለጫ እንዲሁም የደቡብ አፍሪቃ የፖለቲካ ዉዝግብ ዜና መጽሄት የሚያተኩርባቸው ጉዳዮች ናቸው። አዜብ ታደሰ
የአሜሪካ ፕሬዝዳንት መልዕክተኛ ከኢትዮጵያ መልስ ምን አሉ ይዘት
ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። ስለዚሁ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃዎችን ከሰነድ አጠባበቅ መግለጫችን ማግኘት ይችላሉ።
የትግራይ የምርጫ ኮምሽን ምዝገባ ጀመረ
በትግራይ ክልል ምክር ቤት በአዋጅ የተቋቋመው የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የምርጫ ኮምሽን የተባለው ተቋም ዘንድሮ ሊያካሂደው ባቀደው ምርጫ ተሳታፊ የሚሆኑ የፖለቲካ ፓርቲዎችና የግል እጩዎችን መመዝገብ ጀመረ፡ በቅርቡ በትግራይ ክልል ምክር ቤት በአዋጅ የተቋቋመው የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የምርጫ ኮምሽን የተባለው ተቋም ዘንድሮ ሊያካሂደው ባቀደው ምርጫ ተሳታፊ የሚሆኑ የፖለቲካ ፓርቲዎችና የግል እጩዎችን መመዝገብ ጀመረ፡፡ የኮምሽኑ አመራሮች ከዚህ በፊት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተመዘገቡ ፓርቲዎችን ዳግም በኮምሽኑ መመዝገብ ያስፈለገው የምርጫው ተወዳዳሪ ፓርቲዎችን ለመለየት፣ ሀሳባቸው ለመቀበልና ለመደገፍ ታቅዶ መሆኑ አስታውቀዋል፡፡ ለሦስት ተከታታይ ቀናት በሚቆየው የፖለቲካ ፓርቲዎችና የግል ተወዳዳሪዎች ምዝገባና ሌሎች ተዛማጅ ጉዳዮች ዙርያ ከትግራይ ምርጫ ኮምሽን ኮምሽነር መምህር ሙሉወርቅ ኪዳነማርያም ጋር ቆይታ አድርገናል፡፡ ሚሊዮን ኃይለሥላሴ
ዉይይት፤ የብልጽግናን እና የህወሓትን ዉጥረት በሕግ ወይስ በዉይይት
የዉይይቱ ተሳታፊዎች የሰላም ሚኒስትርዋ የእንወያይ ሃሳብ እጅግ ተገቢ ነዉ እስከ መቼ ያሉ እንዳሉ ሁሉ፤ ህወሓት በሕግ ሊጠየቅ ይገባል ብለዉ የተከራከሩ አሉ። ከሁለቱ አስተያየቶች ወጣ ያሉት የዉይይቱ ተካፋዮች ደሞ፤ ሲጀመር የኢትዮጵያን ስቃይ ያበዛዉ ያለሕዝብ እዉቅና በህወሓት የተቀመጠዉ ሕገ መንግሥት ነዉ፤ ሕገ መንግሥቱ ይቀየር ብለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ወደ ስልጣን ከመጡ ካለፉት ሁለት ዓመት ከመንፈቅ ኢትዮጲያ በለዉጥ ጉዞ ላይ ናት። ይሁንና በእነዚህ ዓመታት በሃገሪቱ ግጭት ጥቃት ግድያ እና ስርዓት አልበኝነት ከቀን ወደ ቀን እየጨመረ መምጣቱ አሁንም እንዳሳሰበ ነዉ። በእነዚህ ሁለት ዓመታት በፊደራል መንግሥት እና በትግራይ ክልላዊ መንግሥት መካከል የተፈጠረዉ አለመግባባትም እየተካረረ ሄድዋል። ችግሩን ለመፍታት የሃገር ሽማግሌዎችና ታዋቂ ሰዎች የሞከሩ ቢሆንም ፤ ችግሩ ከመቃለል እና ከመፈታት ይልቅ፤ አንዱ በአንዱን መዉቀሱ ቀጥሎአል። የፌደሬሽን ምክር ቤት ህወሓት አካሄድኩት ያለዉን ምርጫ ሕገ ወጥ ብሎታል። ባለፈዉ ሰሞን ከፊደራል መንግሥቱ የሰላም ሚኒስትር ከወይዘሮ ሙፈርያት ካሚል የተሰማዉ የእንነጋገር ጥያቄ እና ችግሩ በዉይይት እና በንግግር ይፈታ መልዕክት እያነጋገረም ነዉ። በሌላ በኩል የሰላም ሚኒስትርዋ የእንወያይ ጥሪ በኋላ በዚህ ሳምንት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ ር ዐቢይ አሕመድ ከፓርላማዉ ለቀረበላቸዉ ጥያቄ ከትግራይ ክልላዊ መንግሥት ጋር የሚታየዉ ዉዝግብ በሕግ የሚፈታ ጉዳይ ብቻ መሆኑን አሳዉቀዋል። የሰላም ሚኒስትርዋ የእንነጋገር ጥሪ፤ እንዴትነት እና በክልሎች መካከል የሚታየዉ አለመግባባት፤ መፍትሄ ምን ይሆን። በዉይይቱ ላይ የተሳተፉት አቶ የሽዋስ አሰፋ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ የኢዜማ ፓርቲ ሊቀመንበር ፤ ሻለቃ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ፤ የአፍሪካ የስትራቴጂና ጸጥታ ተቋም ዋና ስራ አስፈጻሚ እንዲሁም፤ ዶክተር ለማ ይፍራሸዋ ፤ በኢትዮጵያ ፌደራሊዝም ጥናት ያካሂዱ የፖለቲካ ሳይንስና የሕግ ምሁር ናቸዉ። ሙሉ ዉይይቱን የድምፅ ማድመጫ ማዕቀፉን በመጫን እንዲከታተሉ እንጋብዛለን። ተወያዮች ፤ ካነስዋቸዉ ሃሳቦች መካከል በጥቂቱ የሰላም ሚኒስትርዋ ወ ሮ ሙፈርያት ካሚል የእንወያይ እንደራደር ጥሪ ተገቢ ነዉ ። ሚኒስትርዋ ይህን መናገራቸዉ ከሰላም ሚኒስትር አንጻር ነዉ ግን እስከዛሬ የት ነበሩ ሚኒስትርዋ ይህን በተናገሩ በነጋታዉ ስልጣን መልቀቅ ነበረባቸዉ ። ሕግ መከበር አለበት ፤ ሕግ ካልተከበረ መንግሥት የለም ማለት ነዉ። ህወሓት እና ብልፅግና ተደብቀዉም ቢሆን መደራደር አለባቸዉ ፤ በነሱ ዉዝግብ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሲጨነቅ አይከርምም። ህወሓት ኢትዮጵያ ዉስጥ ለሚደረገዉ ምርጫ በሩን ክፍት አድርጎ ለትግራይ ሕዝብ እድሉን ሊሰጥ ግድ ይላል። ድርድር ካልን ከህወሓት ጋር ብቻ ሳይሆን በወለጋ ጫካ ካለዉ ታጣቂ ጋርም እንደራደር ማለት አለብን። ኢትዮጵያ ዉስጥ በየቀነዉ የሚገደለዉ ፤ ጥቃት የሚደርስበት ሕዝብ አሳሳቢ ሆንዋል ሥር ዓት አልበኝነት እየበረታ ነዉ። ከመጀመርያዉ ሕገ መንግሥቱ ሊቀየር ይገባል።
በርግጠኝነት ኢዜማ አማራጭ ነው ሊቀመንበሩ
በመጪው ኛው አገራዊ ምርጫ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ኢዜማ መንግስት ለመሆን የሚወዳደር ፓርቲ መሆኑን አስታወቀ። ካሉት የምርጫ ወረዳዎች በ ቱ እጩዎቹን ማቅረቡንም አመልክቷል። ምርጫው ሰላማዊ ሆኖ እንዲጀመርም እንዲጠናቀቅም እሰራለሁ ብሏል፡፡ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ኢዜማ ቀጣዩን አገራዊ ምርጫ ዴሞክራሲያዊ፣ ሰላማዊ እና ዜጎች በነፃ የሚሳተፉበት ሆኖ እንዲጠናቀቅ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ እሁድ መጋቢት ቀን ዓም በባህር ዳር ከተማ ከደጋፊዎቹና ከአባላቱ ጋር ሰፊ ውይይት አድርጓል፡፡ በሙሉዓለም የባሕል ማዕከል በተደረገው ውይይት የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮችና አባላትና ደጋፊዎች የተገኙ ሲሆን የኢዜማ ሊቀመንበር አቶ የሺዋስ አሰፋ በተለይ ለዶይቼ ቬለ እንደተናገት ፓርቲያቸው በፓርላማ ውክልና ለማግኘት ብቻ ሳይሆን መንግስት ለመሆንም ይወዳደራል፡፡ ምርጫው እንደከዚህ በፊቶች እድልን አሳልፎ የሚሰጥ እንዳይሆን ያገባኛል የሚሉ ሁሉ ሂደቱና ውጤቱ ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ መሰራት እንዳለባቸው አቶ የሺዋስ አሳስበዋል፡፡ ምርጫ የህዝብና የህዝብ ብቻ ነው የሚሉት አቶ የሺዋስ፣ ኢዜማ ምርጫው ሰላማዊ እንዲሆን አባላቱ፣ ደጋፊዎቹና አመራሮች ይሰራሉ ሌሎችም ከኢዜማ ትምህርት ሊወሰድ ይገባል ሲሉ ተናግረዋል፡፡ እንደበለፀጉት አገሮች ምርጫው እንከን ሊኖረው አይችልም ባይባልም ከጥቃቅን ችግሮች በቀር እስካሁን ያለውን ሂደት በአዎንታዊ አንስተዋል፡፡ ምርጫው ሰላማዊ ሂደት ኖሮት እንዲጠናቀቅ ገዢው ፓርቲ ታላቁን የቤት ሥራ እንዲያከናውንም ጠይቀዋል፡፡ አስተያየታቸውን ከሰጡን ተሳታፊዎች መካከል አንዱ ምሁራን የዳር ተመልካች ሆነው ለአገሪቱ ችግር ውስጥ መውደቅ ተጠያቂ እንደነበሩ ጠቁመው አሁን ግን በፓርቲ ታቅፈው ለመታገል መወሰናቸውን አብራርተዋል ።ሌላዋ ተሳታፊ በበኩላቸው ማን ምን ይዞ እንደቀረበ ህብረተሰቡ እንዲያውቅ ስለሚያደርግ ውይይቱ መልካም ነው ብለዋል፡፡ ኢዜማ ከዚህ ቀደም ተመሳሳይ ውይይቶችን በትግራይ፣ በአፋር፣ በደቡብና በሌሎቹም አካባቢዎቸ ማድረጉ ይታወሳል። ዓለምነው መኮንን
የኢዜማ ፓርቲ በባህር ዳር ከተማ ያካሄደው ውይይት ራድዮ
ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። ስለዚሁ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃዎችን ከሰነድ አጠባበቅ መግለጫችን ማግኘት ይችላሉ።
ከምርጫው በፊት የጽሞና ቀናትና መገናኛ ብዙኃን
በዚህም መሠረት ማኒፌስትቶዎችን ማስተዋወቅና ዕጩ ተወዳዳሪዎችንም ማነጋገርና መዘገብ የተከለከለ ነው። ይህ ማለት ግን ስለ ድምፅ አሰጣጥ፣ ስለ ምርጫ ሂደቱ፣ ስለ መራጮች ተስፋና ዝግጅት መራጮችንና ምርጫውን የተመለከተ ዘገባ አይሰራም ማለት እንዳልሆነ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል። ማንኛውም የመገናኛ ብዙኃን ድርጅት ከዛሬ ጀምሮ ባሉት አራት የጥሞና ቀናት ማንኛውንም ምርጫ ተኮር የፖለቲካ ፓርቲዎች እንቅስቃሴዎችን መዘገብ እንደማይችል የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የምርጫ ዑደት መመሪያ አስቀምጧል።በዚህም መሠረት ማኒፌስትቶዎችን ማስተዋወቅና ዕጩ ተወዳዳሪዎችንም ማነጋገርና መዘገብ የተከለከለ ነው። ይህ ማለት ግን ስለ ድምፅ አሰጣጥ፣ ስለ ምርጫ ሂደቱ፣ ስለ መራጮች ተስፋና ዝግጅት መራጮችንና ምርጫውን የተመለከተ ዘገባ አይሰራም ማለት እንዳልሆነ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል።መገናኛ ብዙኃኑ ይህንን መመሪያ እንዴት እየተገበሩት እንደሆን የሕትመትና የብሮድካስት መገናኛ ብዙሃንን ጠይቀናል።ሰሎሞን ሙጬ ከአዲስ አበባ ዘገባ አጠናቅሯል ሰሎሞን ሙጬ
የኦነግ አመራር አካላት ውዝግብና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ውሳኔ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ኦነግ አመራር አባላት፤ ሊቀመንበርም ሆነ በሊቀመንበሩ ታግደዋል የተባሉት ስራ አስፈጻሚዎች ህጋዊ የድርጅቱ አካላት ሆነው እንዲቀጥሉ ውሳኔ አስተላለፈ፡፡ መግለጫውን ተከትሎ ሁለቱ ወገኖች መግለጫውን በይሁኝታ መመልከታቸውና አፈጻጸሙንም በቀጣይነት እንደሚከታተሉት ለዶይቸ ቬለ ገልፀዋል። በአመራር አካላት መካከል የተፈጠረውን አለመግባባት አስመልክቶ የተለያዩ አቤቱታዎች ሲደርሱት እንደነበር ያስታወቀው ቦርዱ፤ የፓርቲው የተወሰኑ የስራ አስፈጻሚ አባላት ነሃሴ ቀን ዓ ም በተጻፈ እና በድርጅቱ ምክትል ሊቀመንበር አራርሶ ቢቂላ በተፈረመ ደብዳቤ የድርጅቱ ሊቀመንበር መታገዳቸውን ለቦርዱ ማሳወቃቸውን ጠቅሷል፡፡ በሌላ በኩል የድርጅቱ ሊቀመንበር መስከረም ቀን ዓ ም ድርጅቱ ብሔራዊ ምክር ቤት ስብሰባ አድርጎ የፓርቲውን ምክትል ሊቀመንበር፣ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላትን እንዲሁም የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት እስከሚቀጥለው የድርጅቱ ጠቅላላ ጉባኤ ድረስ ከሃላፊነታቸው ታግደው እንዲቆዩ መወሰኑንም አሳውቆ እንደነበር ቦርዱ ገልጿል፡፡ በፖለቲካ ፓርቲዎች አዋጅ ቁጥር አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ መሠረት ከሁለቱም ወገኖች አንድ አንድ ሰው ተወክለው በተሳተፉበት በባለሙያዎች ጉባኤ ጉዳዩን ለማየት ጥረት ማድረጉንም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል፡፡ ሆኖም በሊቀመንበሩ አቶ ዳውድ ኢብሳ በኩል ተወካይ አለመቅረቡና ቦርዱ ይህንን ጉዳይ ለማየት ፍቃደኛ የሆነ ባለሞያ ባለማግኘቱ በራሱ ጉዳዩን መርምሮ ለመወሰን መገደዱንም ነው ያሳወቀው፡፡ በዚህም መሰረት በሁለቱም ወገን ያሉ የፓርቲው አመራሮችን ማነጋገሩን ያሳወቀው ቦርዱ፤ በድርጅቱ ምክትል ሰብሳቢ አቶ አራርሶ ቢቂላ ፊርማ የተላከለትን የድርጅቱን ሊቀመንበር የታገዱበትን ስብሰባ የሚገልጸውን ቃለጉባኤ ተመልክቶ በቃለጉባኤው ላይ የተገኙት ስራ አስፈጻሚ አባላት ከስምንቱ አምስት መሆናቸውን፣ ከአምስቱ መካከልም አንዱ አባል ከዚህ ቀደም በዜግነታቸው የተነሳ ከስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው የተቀነሱ በመሆናቸው ስራ አስፈጻሚው ስብሰባ የሚጠበቀውን ተኛ ምልዓተ ጉባኤ ያልተሟላበት በመሆኑ ውሳኔ ህጋዊ ተቀባይነት የለውም ብሏል፡፡ በሌላ በኩል በአቶ ዳውድ ፊርማ የብሔራዊ ምክር ቤት ውሳኔ ነው ተብሎ ለቦርዱ የቀረበው የፓርቲውን ምክትል ሊቀመንበር፣ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላትን እንዲሁም የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት እስከሚቀጥለው የድርጅቱ ጠቅላላ ጉባኤ ድረስ ከሃላፊነታቸው ታግደው እንዲቆዩ የተወሰነው ውሳኔ ስብሰባው በትክክል መካሄዱን የሚያሳይ ቃለጉባኤ የሌለው፣ ምን ያህል የምክር ቤት አባላት እንደተሳተፉበት እና በምን አይነት ድምጽ አሰጣጥ የሚለውን የማያሳይ በሊቀመንበሩ ፊርማ ብቻ የተላከ ውሳኔ በመሆኑ ህጋዊ ተቀባይነት የሌለው መሆኑን አክሏል፡፡ በመሆኑም የፓርቲው ሊቀመንበርም ሆነ በሊቀመንበሩ ታግደዋል የተባሉት ስራ አስፈጻሚዎች ህጋዊ የድርጅቱ አካላት ሆነው ይቀጥላሉ ብሏል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በውሳኔው፡፡ ቦርዱ ከሁለቱም ወገኖች ጋር ባደረገው ውይይት የድርጅቱ ጠቅላላ ጉባኤ በታህሳስ ዓ ም መደረግ እንደሚገባው ምክር ቤቱ ቀደም ሲል የወሰነ እንደነበረ በማረጋገጥ፤ ኦነግ እስከ ጥር ቀን ዓ ም ድረስ ጠቅላላ ጉባኤ ማድረግ ከሚገባቸው ፓርቲዎች አንዱ መሆኑንም አስታውቋል፡፡ ሁለቱም ወገኖች የሚገኙበት የመጀመሪያ ስብሰባቸውንም በቦርዱ ስብሰባ አዳራሽ እንዲያከናውኑ መወሰኑንም የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ትናንት ማምሻውን ባወጣው መግለጫ አሳውቋል፡፡ ስዩም ጌቱ
ምርጫው ሰኔ ቀን ዓም ይካሄዳል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
የቦርዱ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ወይዘሪት ሶልያና ሽመልስ ዛሬ ከሰዓት በኋላ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የመራጮች ምዝገባ ባወዛገበባቸውና ጉዳያቸው በፍርድ ቤት የተያዘ የምርቻ ጣቢያዎች እንዲሁም በግጭት ምክንያት የመራጮች ምዝገባ ባልተካሄደባቸው ቦታዎች ግን በእለቱ ምርጫ እንደማይካሄድ ተናግረዋል። ስድስተኛው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ሰኔ ቀን ዓም እንደሚካሄድ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ።የቦርዱ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ወይዘሪት ሶልያና ሽመልስ ዛሬ ከሰዓት በኋላ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የመራጮች ምዝገባ ባወዛገበባቸውና ጉዳያቸው በፍርድ ቤት የተያዘ የምርጫ ጣቢያዎች እንዲሁም በግጭት ምክንያት የመራጮች ምዝገባ ባልተካሄደባቸው ቦታዎች ግን በእለቱ ምርጫ እንደማይካሄድ ተናግረዋል።ቦርዱ ባለፈው ቅዳሜ ነበር ምርጫው እንደሚገፋ ያሳወቀው። የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ጋዜጣዊ መግለጫውን ተከታትሏል። ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ምክር ቤቱ ሦስት ሚኒስትሮችን ሾመ
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዛሬ መደበኛ ጉባኤው ሦስት አዳዲስ ሹመትን ሰጠ። በዚሁ መሠረትም ኛ አቶ ለማ መገርሳን የኢፌዴሪ የመከላከያ ሚኒስት፤ ኛ አቶ ገዱ አንዳርጋቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፤ ኛ ወይዘሮ አይሻ መሃመድን የከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽን ሚኒስትር አድርጎ ሾሟል። ሹመቱ በአምድ የተቃውሞ እንዲሁም በአምስት የድምፅ ተአቅቦ በአብላጫ ድምጽ ነው የውሳኔ ቁጥር ሆኖ የጸደቀው። ብዙ ክርክርና ውይይት ያልተደረገበት ይህ የሹመት አሰጣጥ ከእንድ የምክር ቤት አባል ሹመት ጎርፍ ኾነ የሚል ጥያቄ አስነስቷል። በምክር ቤቱ የመንግሥት ተጠሪ የሆኑት ሚኒስትር ጫላ ደሜ ስለ ሹመቱ በሰጡት ምላሽ አሁን የተሰጠው ሹመት ለውጡን ለማስቀጠል ታልሞ የተደረገ ነው ማለታቸውን የአዲስ አበባው ወኪላችን ሰሎሞን ሙጬ በላከልን ዘገባ ጠቅሷል። ሁለቱ ተሿሚዎች በምክር ቤቱ ቀርበው ቃለ መሃላ የፈጸሙ ሲሆን አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ግን በቃለ መሃላው ላይ አልተገኙም። ስላለመገኘታቸው የተሰጠ ምክንያትም የለም። የሹመት ሂደቱ በአጠቃላይ ደቂቃ ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ነበር የተጠናቀቀው። ሰለሞን ሙጬ
ጉዳያቸው በፍርድ ቤት በተያዘ የምርጫ ጣቢያዎች ምርጫ አይካሄድም ራድዮ
ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። ስለዚሁ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃዎችን ከሰነድ አጠባበቅ መግለጫችን ማግኘት ይችላሉ።
የዞን ዘጠኝ የድረገጽ ጸሐፍት ክስ ዉድቅ ሆነ
ዞን ዘጠኝ በመባል በሚታወቁት አራት የድረገጽ ጸሐፍት እና አንድ ጋዜጠኛ ላይ በሽብርተኝነት የቀረበባቸዉን ክስ ፍርድ ቤት ዛሬ ዉድቅ አደረገ። ፍርድ ቤቱ ተከሳሾቹ ላይ የቀረበዉ ማስረጃ ሁሉ ደካማ መሆኑን ማመልከቱን የፈረንሳይ የዜና ወኪል ከአዲስ አበባ ዘግቧል። ፍርድ ቤቱ መከላከል ሳያስፈልጋቸው በነፃ እንዲሰናበቱ የወሰነላቸው በሌለችበት የተከሰሰችው ሶሊያና ሽመልስ፣ ናትናኤል ፈለቀ ፣ አጥናፍ ብርሃነ እና አቤል ዋበላ ናቸው ። በዚሁ መሠረትም ዛሬ ማምሻዉን ከእስር ቤት እንደሚወጡ ይጠበቃል። በሌለችበት በተመሳሳይ የተከሰሰችዉ የዞን ዘጠኝ አባል ሶልያና ገብረሚካኤልም በስደት ሀገር ብትሆንም ክሱ እንደተነሳላት ተገልጿል። ሶልያና ከ ወራት በኋላም ቢሆን ክሱ ዉድቅ መሆኑ መልካም መሆኑን ለዶቼ ቬለ ገልጻለች። በአንፃሩ ዛሬ ያስቻለው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ኛ የወንጀል ችሎት ፣ላለፉት ወራት ከድረገጽ ጸሐፍቱ ጋር ታስሮ የቆየዉ አራተኛዉ ተከሳሽ ጋዜጠኛ በፈቃዱ ኃይሉ ከሽብርተኝነት ጋር የሚገናኘዉ ክስ ቢነሳለትም ለአመፅ በማነሳሳት በሚለዉ ክስ በእስር እንደሚቆይ መወሰኑን ዘገባዉ አክሎ ገልጿል። የፀረ ሽብር ክስ ተሰርዞ አመጽን በማነሳሳት ወንጀል እንዲቀየርም ወሰነ ። በፍቃዱ ሃይሉ ግን የአሸባሪነት ክሱ ቢነሳለትም ክሱ አመጽ በማነሳሳት ተቀይሯል ።ክሱም እስከ አስር ዓመት እስራት ሊያስበይን እንደሚችልም ተመልክቷል። ከ ወራት በፊት የዞን ዘጠኝ የድረገጽ ጸሐፍት እና ሶስት ጋዜጠኞች ባጠቃላይ ዘጠኝ ነበሩ ጥቃቶችን በማሴርና ግንቦት ከተባለው የኢትዮጵያ መንግሥት ተቃዋሚ ቡድን ጋር በመተባበር ህገ መንግሥታዊ ስርዓቱን ለመናድ ተንቀሳቅሰዋል በሚል ወንጀል ተከሰው ነበር የታሰሩት። ባለፈዉ ዓመት ሐምሌ ወር ከታሳሪዎቹ አራቱ ተለቀዋል። ለጋዜጠኞች መብት የሚሟገተዉ ኢትዮጵያን ጋዜጠኞችን በማሠር ከአፍሪቃ ሁለተኛዋ ሀገር ያደርጋል። የድርጅቱ የአፍሪቃ ተጠሪ ቶም ሮድስ ፍርድ ቤት የድረገጽ ጸሐፍትና ጋዜጠኞቹን ከተከሰሱበት የሽብር ክስ በነፃ ማሰናበቱን አወድሰዋል። ተጨባጭ ማስረጃ ሳይገኝባቸዉም ሂደቱ ረዝም ጊዜ መዉሰዱንም ጠቁመዋል። የዋሽንግተን ዲሲው ዘጋቢያችን ናትናኤል ወልዴ ሶልያና ሽመልስን በስልክ አነጋግሯታል ። ሸዋዬ ለገሠ ናትናኤል ወልዴ
የዞን ዘጠኝ የኢንተርኔት ጸሓፍት ሽልማት
በኢትዮጵያ መንግስት የጸረ ሽብር ህግ ክስ የተሰመሰረተባቸው የዞን ዘጠኝ የኢንተርኔት ጸሓፍት የዓለም አቀፍ የፕሬስ ነጻነት ሽልማት አሸናፊ ሆኑ። ከጦማርያኑ መካከል አራቱ አሁንም በእስር ላይ ሲሆኑ ሁለቱ መፈታታቸው አይዘነጋም። በኢትዮጵያ መንግስት የጸረ ሽብር ህግ የተከሰሱት የዞን ዘጠኝ የኢንተርኔት ፀሃፍት የዓለም አቀፍ የፕሬስ ነጻነት ሽልማት አሸናፊ ሆነዋል። ዓለም አቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት ተለምዷዊው ሚዲያ በፋይናንስ እጦት፤በመንግስት ቀጥተኛና ቀጥተኛ ያልሆነ ጫና በተዳከመበት አገር ውስጥ ለተጫወቱት አዎንታዊ ሚና ፀሃፍቱን እንደሚሸልም አስታውቋል። በዓለም አቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት የምሥራቅ አፍሪቃ ተወካይ ቶም ሮድስ በሽልማቱ የዞን ዘጠኝ ፀሃፍት ሃሳብን ለመግለጽ ነጻነት ላበረከቱት አስተዋጽዖ እውቅና ከመስጠት ባሻገር በኢትዮጵያ ያለውን ነባራዊ ሁኔታ ለማሳየት መታቀዱን ተናግረዋል። እንደ ቶም ሮድስ ከሆነ የዚንተርኔት አምደኖቹ በወጣት ኢትዮጵያውያን ዘንድ ያሳደሩት አዎንታዊ ተጽዕኖም ከፍተኛ ነው። ሰዎች የኢንተርኔት ፀሃፍቱ የሚሰሯቸውን ስራዎችና ፅሁፎቻቸውን ይከታተላሉ። በኢትዮጵያ ነጻ ሚዲያ በተለይም ደግሞ ነጻ የድረ ገጽ ሚዲያ እንዲኖር የሚያደርጉትን ጥረት ይደግፋሉ። ከዞን ዘጠኝ የኢንተርኔት አምደኞች በተጨማሪ ከማሌዥያ ዙልኪፍለ አንዋር፤ከፓራጓይ ካንዲዶ ፊጌሬዶና በሶርያ በድብቅ የሚሰራው የራቃ ማህበረሰባዊ ጋዜጣ ስብስብ በመጪው ሕዳር ቀን ዓ ም ኒውዮርክ ውስጥሽልማት ይበረከትላቸዋል። የዞን ዘጠኝ የኢንተርኔት አምድ በኢትዮጵያ ፖለቲካዊ፤ማህበረሰባዊ፤ኢኮኖሚያዊና ባህላዊ ርዕሰ ጉዳዮችን እያነሳ ይፈትሻል። የጉዞ ማስታወሻዎች፤ሳምንታዊ የኢትዮጵያ ጋዜጣና መጽሄቶች ስራ ዳሰሳዎችም ይቀርቡበት ነበር። ከሶልያና ሽመልስ በስተቀር ስድስቱ በቀረበባቸው ክስ ለእስር ሲዳረጉ አራቱ አሁንም አልተፈቱም። በዞን ዘጠኝ ፀሃፍት ላይ የቀረበው የክስ መዝገብ ላይ በቀዳሚነት የሰፈረው የሶልያና ሽመልስ ስም ነው። ዓለም አቀፍ የፕሬስ ነጻነት ሽልማትን ማግኘት ትልቅ እውቅና ነው። ስትል በሽልማቱ ላይ አስተያየቱን የሰጠችው ሶልያና በተለይ በእስር ላይ ለሚገኙ የዞን ዘጠኝ ጦማሪዎችና ሌሎች ሃሳብን በነጻነት ከመግለጽ መብት ጋር በተያያዘ ዋጋ እየከፈሉ ላሉና ለከፈሉ ሰዎች ኢትዮጵያ ያለው የፕሬስ ጉዳይ በጣም አፋኝ እንደሆነና አስቸጋሪ እንደሆነ እውቅና መሰጠቱ ጥሩ ነው። ብላለች። በዘጠኝ ወጣቶች በኢ መደበኛነት የተመሰረተው ስብስብ በግንቦት ዓ ም በኢንተርኔት አምዱ ካሰፈራቸው ቀዳሚ አረፍተ ነገሮች መካከል ለኢትዮጵያ ፖለቲካ የሚበጁ ምክረ ሐሳቦች ይነሳሉ፤ ይጣላሉ፡፡ መንግስት ይወቀሳል፣ ይተቻል፣ ይከሰሳል፡፡ የሚል ነበር። ስለሚያገባን እንጦምራለን። የሚል መፈክር ላነገቡት የዞን ዘጠኝ የኢንተርኔት አምደኞች ሊበረከት የተዘጋጀው ሽልማት ሃሳብን የመግለጽ ነጻነት መብት በኢትዮጵያ የተጋረጠበትን ፈተና እንደሚያሳብቅ ሶልያና ታምናለች። በዓለም አቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት የምሥራቅ አፍሪቃ ተወካይ ቶም ሮድስ በኢትዮጵያ ያለው የኢንተርኔት ተደራሽነት አሁንም ውስን ቢሆንም በመጪዎቹ አመታት ትርጉም ያለው ለውጥ ለማምጣት በሚችል ደረጃ ያድጋል የሚል እምነት አላቸው። ነጻ የህትመት ውጤቶች በመዘጋታቸውና የነጻ ሚዲያ በመጥፋቱ የኢንተርኔት የዜና አቅርቦት በተለይ በውጭ አገራት በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ዘንድ እያደገ ነው። የዞን ዘጠኝ የኢንተርኔት አምደኞች በወጣቶችና በውጭ አገራት በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ያገኙትን ተቀባይነት ስንመለከት የድረ ገጽ መገናኛ ብዙሃን በመጪዎቹ አመታት ከዚህ በላይ ያድጋሉ። ለዚህም የዞን ዘጠኝ አባላት ላበረከቱት አስተዋጽዖ ምስጋና ይገባቸዋል። የዞን ዘጠኝ የኢንተርኔት አምድ አሁን አሁን እንደወትሮው የበይነ መረብ ዘመቻዎች ማካሄዱን፤የጉዞ ማስታወሻም ይሁን የኢትዮጵያ ጋዜጦች ምን ጻፉ ብሎ መፈተሹን አቁሟል። ሶልያና ሽመልስ አሁን በእስር ላይ የሚገኙትን አራት የዞን ዘጠኝ አባላት ላይ ያተኮረው ስራ ወደ ፊትም እንደሚቀጥል ተናግራለች። እሸቴ በቀለ
ዶ ር መረራ የመሰረቱት ክስ አንደምታ
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ተላልፈዋል፣ ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን በኃይል ለመናድ ተንቀሳቅሰዋል ተብለው በእስር ላይ የሚገኙት የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ኦፌኮ ሊቀመንበር ዶ ር መረራ ጉዲና በኢትዮጵያ መንግስት ላይ ባለፈው ሳምንት ክስ መስርተዋል፡፡ ዶ ር መረራ ክሱን የመሰረቱት በአፍሪካ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን መድረክ ነው፡፡ ዶ ር መረራ በተወካያቸው አማካኝነት ክሱን የመሰረቱት በሶስት ፍሬ ነገሮች ላይ አትኩረው ነው፡፡ የመጀመሪያው ፍሬ ነገር የቀረበባቸው ክስ እና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ኢትዮጵያ ከፈረመቻቸው የአፍሪካ ቻርተርና ከሌሎችም ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ድንጋጌዎች ጋር የሚጋጭ እንደዚሁም የኢትዮጵያ ህገ መንግስት መስፈርቶችን የሚያሟላ አይደለም የሚል ነው፡፡ በእስር ከዋሉ ጀምሮ የተፈጸመባቸው ኢ ሰብዓዊ አያያዝ ሌላው የክስ ጭብጥ ነው፡፡ ሶስተኛው ፍሬ ነገር ደግሞ በኦሮምያ በአማራ እና በደቡብ ክልሎች ተነስተው በነበሩ ህዝባዊ አመጾች የመንግስት ታጣዊዎች በዜጎች ላይ የወሰዱት አላስፈላጊ የኃይል እርምጃ በገለልተኛ ወገን እንዲጣራ የሚጠይቅ ነው፡፡ የዶ ር መረራን ውክልና በመውሰድ ክሱን የመሰረተው የኢትዮጵያ የሰብዓዊ እና የዲሞክራሲያዊ መብቶች ማዕከል ኃላፊ ዶ ር አዎል አሎ ለዶይቸ ቬለ እንደገለጹት የአፍሪካ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ክሱን ለመመስረት ተገቢ ቦታ ነው፡፡ ዶ ር አዎል ከኢትዮጵያ ጋር በተያያዘ ልንሄድ የምንችልባቸው ብዙ መድረኮች አልነበሩም ይላሉ፡፡ የተባበሩት መንግስታት ውስጥ የተወሰኑ መድረኮች አሉ፡፡ እነዚህ መድረኮች ግን የአፍሪካ ኮሚሽን ከሚሰጠው አማራጭ ጋር ሲታይ የተሻሉ አይደሉም፡፡ ይህ ጉዳይ ከሚያነሳቸው ፍሬ ነገሮች ጋር በተያያዘ ስናይ የአፍሪካ ኮሚሽን የተሻለ ዕድል ይሰጣል፡፡ የአፍሪካ ኮሚሽንን ኢትዮጵያ በተወሰነ ደረጃ በቁም ነገር እንደምትወስደም የምናያቸው አንዳንድ ነገሮች አሉ፡፡ ምክንያቱም ሀገሪቷ በአፍሪካ ህብረት ውስጥ ማንጻባረቅ የምትፈልገው ምስል አለ፡፡ ከዚያም አንጻር ሊሆን ይችላል ቢያንስ ከሱ በሚቀርብበት ጊዜ መልስ የመስጠት እና ከኮሚሽኑ ጋር የመስራት የቀደሙ ተሞክሮዎች አሉ፡፡ ኮሚሽኑ አነዚህን ጉዳዮች ፍርድ ቤቶች ጉዳዮች በሚመለከቱበት መልኩ መርምሮ ነው ውሳኔ ላይ የሚደርሰው ይላሉ ዶ ር አዎል፡፡ ክሱን መመስረቱ እና በቀጣይ የሚገኘው ውሳኔ ሊሰጠው የሚችለውን ጠቀሜታ በተመለከተ የተጠየቁት ዶ ር አዎል ተከታዩን ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ ይህ የክስ መዝገብ የሚያደርገው አንድ ነገር የታሰሩ ሰዎች ጉዳያቸው እንዳይረሳ ያደርጋል፡፡ ከጊዜ ወደ ጊዜ የክስ ሂደቱ የራሱ ደረጃዎች አሉት፡፡ እዚያ ደረጃዎች ላይ በሚደርስበት ጊዜ የእነዚህ ሰዎች ስም የመታወስ ዕድል ይኖረዋል፡፡ የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች እዚህ ላይ ተመስርተው የዲፕሎማሲ ስራ መስራት ይችላሉ፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት ላይ ጫና ለማድረግ ዕድል ይሰጣል፡፡ ስለዚህ ከህግ ሂደቱ ያለፈ ብዙ ጠቀሜታ አለው፡፡ ታሪካዊ፣ ፖለቲካዊ እና ዲፕሎማሲያዊ ማለት ነው ሲሉ የክሱን አንደምታ ይዘረዝራሉ፡፡ የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ፕሮጀክት አስተባባሪ ሶልያና ሽመልስ መሰል ክሶች በአህጉራዊ እና ዓለምአቀፋዊ መድረኮች መመስረታቸው በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ጉዳዮች ላይ ለሚሰሩ የቅስቀሳ ስራዎች የጎላ ሚላ እንደሚኖራቸው ታሰምርበታለች፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የሰብዓዊ መብት ሁኔታ ለዓለም አቀፍ ተቋማት ማሳየት ይቻላል፡፡ እንደዚያ ለማሳየት ሰብዓዊ መብት ተቋማት የተለያዩ መንገዶችን እንጠቀማለን፡፡ አንደኛው መገናኛ ብዙሃንን መጠቀም ሊሆን ይችላል ሌላኛው ደግሞ እንዲዚህ ዓይነት ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት መድረኮች በመጠቀም ሀገሪቱ ውስጥ ያለውን የሰብዓዊ መብት ሁኔታ ማሳየት ይቻላል፡፡ የዶ ር መረራ ጉዳይ እንደ አንድ ማሳያ ሆኖ ለሌሎች ሀገሪቷ ውስጥ ላሉ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች መገለጫ ሊሆን ይችላል ተብሎ ስለሚታሰብ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ግንዛቤ ስለሚጨምር አንደኛው ጥቅሙ እርሱ ነው፡፡ ሁለተኛው ደግሞ ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት እንቅስቃሴዎች በተለይ የዓለም አቀፍ ቅስቀሳ በሚሰራበት ቦታ ላይ ሀገር ቤት ያለውን የመንግስት ጭቆና ለማሳየት ይረዳል ፡፡ በዓለም አቀፍ ደረጃ ደግሞ መንግስት የሚሰራቸው የህዝብ ግንኙነት ስራዎች አሉ፡፡ የሰብዓዊ መብት ዘገባዎች ትክክል አይደሉም፣ የሚባሉት ዘገባዎች የሚወጡባቸው ተቋማት ራሳቸው የነጮች ናቸው፣ ርዕዮተ ዓለማዊ ምክንያት አላቸው የሚለውንም የመንግስት ክርክር ለማፍረስ ይረዳል ስትል ታብራራለች፡፡ የአፍሪካ የሰብዓዊ እና የህዝቦች መብት ኮሚሽን በአፍሪካ ቻርተር አማካኝነት እንደጎርጎሮሳዊው በአዲስ አበባ የተመሰረተ እና መቀመጫውን ጋምቢያ መዲና ባንጁል ያደረገ አህጉራዊ ተቋም ነው፡
የይግባኝ ዉሳኔ ለዞን ዘጠኝ ጸሐፍት
ረዥም ጊዜያትን የወሰደዉ የዞን ዘጠኝ የድረገጽ ጸሐፍት ጉዳይ ዛሬ በይግባኝ ሰሚዉ ፍርድ ቤት የይግባኝ ዉሳኔ ተሰጠበት። ይግባኝ ሰሚዉ የላይኛዉ ፍርድ ቤት የሥር ፍርድ ቤቱ ያሳለፈዉን ዉሳኔ በሁለቱ ተከሳሾች ላይ ሲያጸና፤ ሌሎች ሁለቱን መከራከር ሳያስፈልጋቸዉ አሰናብቷል። በዚህም መሠረት ናትናኤል መኮንን እና አጥናፍ ብርሃኔ በሽብር ወንጀል ሳይሆን በመደበኛ የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ጉዳያቸዉ እንዲታይ ወስኗል። ጉዳያቸዉ በፍርድ ቤት ለ ኛ ጊዜ መሆኑ ነዉ።በአሁኑ ጊዜ በዉጭ ሀገር የምትገኘዉን ሶልያና ሽመልስን ጨምሮ፤ የሚሆኑ የዞን ዘጠኝ የድረገጽ ጸሐፍት በማኅበራዊ መገናኛ ብዙሃን ላይ በመጻፍ፤ የሚያደርጉትንም መንግሥት እንዳይደርስበት የተለያዩ ስልጠናዎች በመዉሰድ፤ በሽብር ወንጀል ተፈርዶባቸዉ የተከሰሱ ሰዎች እንዲፈቱ በመገፋፋትና በመብት ላይ ጫና በማድረግ የሽብር ወንጀል ፈጽመዋል በሚል መከሰሳቸዉ ይታወሳል። ይህ ክስ እየተመረመረ ባለበት ሰዓት የተወሰኑት ላይ የቀረበዉን ክስም አቃቤ ሕግ በማንሳቱ ተቋርጦ በአምስቱ ማለትም ሶልያና ሽመልስ፤ ናትናኤል ፈለቀ፤ አቤል ዋበላ ፣ በፍቃዱ ኃይሉ እና አጥናፍ ብርሃኔ ጉዳይ ክርክር ቀጠለ። ጠበቃ አምኃ መኮንን ለዶቼ ቬለ በዝርዝር እንዳስረዱት ፍርድ ቤት ክርክሩን ሰምቶ አቃቤ ሕግ ያቀረበዉ ማስረጃ ክሱን አያስረዳም በሚል ሁሉንም ተከሳሾች በነፃ አሰናብቶ ነበር። አቃቤ ሕግ በቂ ማስረጃ ቀርቦ ሳለ የሥር ፍርድ ቤት አላግባብ ዉድቅ አድርጎብኛል ሲል ይግባኝ አለ። ይግባኝ ሰሚዉ ፍርድ ቤትም ይህን ተመልክቶ ዛሬ ሰፋ ያለ ዉሳኔ ሰጥቷል። ዝርዝሩን ከድምጽ ዘገባዉ ያድምጡ፤ ሸዋዬ ለገሠ
የፀጥታ ጉዳይ በቤኒሻንል ጉሙዝና አማራ ክልል አወሳኝ
በቤኒሻንል ጉሙዝ ክልል እና አማራ ክልል አወሳኝ አካባቢዎች ተፈጥሮ የነበረው ግጭት በአጭር ጊዜ ውስጥ ለመፍታት ያስችላል የተባለ ኮማንድ ፖስት በአዲስ መልክ ተቋቋሙ ስራ ጀመረ፡፡ የኮማንድ ፖስቱ መቋቋም በአካባቢው የህገ ወጥ እንቅስቃሴ መኖር እና ህዝቡ በሰላም ተረጋግቶ እንዳይኖር የሚያደርጉ አካላት በመኖራቸው ምክንያት እንደሆነም ተነግሮአል። በቤኒሻንል ጉሙዝ ክልል እና አማራ ክልል አወሳኝ አካባቢዎች ተፈጥሮ የነበረው ግጭት በአጭር ጊዜ ውስጥ ለመፍታት ያስችላል የተባለ ኮማንድ ፖስት በአዲስ መልክ ተቋቋሙ ስራ ጀመረ፡፡ የኮማንድ ፖስቱ መቋቋም በአካባቢው የህገ ወጥ እንቅስቃሴ መኖር እና ህዝቡ በሰላም ተረጋግቶ እንዳይኖር የሚያደርጉ አካላት በመኖራቸው ምክንያት እንደሆነም የኮማንድ ፖስቱ አዛዥ ኮሎኔል መሐመድ ሐሰን ተናግረዋል፡፡ ኮማንድ ፖስት በበላይነት በመከላያ ሰራዊት የሚመራ ነውም ተብለዋል፡፡ የኮማድ ፖስቱ ዋና ግብ ሰላምና ጸጥታን ማስፈን እንዲሁም ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ ዜጎችን ወደ ቀያቸው ለመመለስ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ ከምሽቱ ሶስት ጀምሮም በከተማውና አካባቢው ወደ ህዳሴ ግድብ ከሚሄዱ ተሸከርካሪዎች ውጭ ማንኛውም ተሸከርካሪም ሆነ ሰው እንዳይንቀሳቀስ የተከለከለ ሲሆን ከተፈቀደላቸው የመንግስት ጸጥታ ሀይሎች ውጭም መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስም እንዲሁ የተከለከለ መሆኑንም ኮማንድ ፖስቱ ገልጸዋል፡፡ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል እና አማራ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች ተከስተው የነበረውና በርካታ ዜጎችን ለሞት እና ከቤት ንብረታቸውን ለመፈናቀል የዳረገውን ግጭት ለማስቆም ለመጀመሪያ ጊዜ በሐምሌ ዓ ም የተቋቋመው ኮማንድ ፖስት የሚፈለገውን ያህል ውጤት ባለማምጣቱ በአዲስ መልክ ኮማንድፖስት ተቋቋመው ወደ ስራ ገብተዋል፡፡ ኮማንድ ፖስቱ በስራ ላይ እያለ ባለፉት ዘጠኝ ወራት በዳንጉር፣ማንዱራ እና ኮንግ በተባለ ሰፍራ እንዲሁም በሌሎችም አካባቢዎች ከአምስት ጊዜ በላይ በተፈጠሩት ግጭቶች ከ በላይ ዜጎች ህይታቸውን አጥተዋል፡፡ የኮማንድ ፖስቱ አዛዠ ኮሎኔል መሐመድ ሐሰን ለዲዳቢሊው እንደገለጹት በመተከል እና ከአማራ ክልል ጋር በሚዋስኑ አካባቢዎች ያለውን የጽጥታ ችግር በመደበኛው የህግ የማስከባር ሂዴት መፍታት ባለመቻሉ በተቀናጀ ሁኔታ በመከላከያ እና በፌደራል ፖሊስ ዘላቂ መፍትሄ ለማምጣት ከባለፈው ሰኞ አንስቶ ኮማንድ ፖስቱ ስራ ጀምሯል፡፡ ኮማንድ ፖስቱ የተለያዩ ክልከላዎችን ያስቀመጠ ሲሆን ከክልከላዎቹ መካከልም ከሚመለከታቸው የመከላከያ እና ፌደራል ፖሊስ ውጭ ታጥቆ መንቀሳቀስ የማይቻል መሆኑንና ከምሽቱ ሶስት ሰዓት በኃላ ወደ ታላቁ ህዳሴ ግድብ ከሚንቀሳቀስ መኪና ውጭም ማንኛውም ተሸከርካሪ መንቀሳቀስ የማይችል መሆንም ተናግረዋል፡፡ ኮማንድ ፖስቱ ከቤኒሻንል ጉሙዝ ክልል ማንዱራ፣ዳንጉርናፓዌ እንዲሁም ከአጎራባች አማራ ክልል አዊ ብሄረሰብ ዞንም ጃዊና ሌሎች ሶስት የሚደርሱ ወረዳዎችን ያካተተ እንደሆነም ኮሎኔል መሐመድ ጠቁመዋል፡፡ የአካባቢውን የጸጥታ ችግር ከመቅረፍ ጎን ለጎንም ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው ለአንድ ዓመት ያህል በተለያዩ መጠለያ ጣቢዎች ተጠልለው ያሉትን ዜጎች ወደ ቀድሞ ቀየአቸው ለመመለስም ኮማንድ ፖስቱ በትኩረት ይሰራል ብልዋል፡፡ ኮማንድ ፖስቱ ለሁለት ወር ይህል የሚቆይ ሲሆን የአካባቢው የጸጥታ ችግር በአጭር ጊዜ ውስጥ ካልተፈታም ሊራዘም እንደሚችልም አስረድተዋል፡፡ በቤኒሻንል ጉሙዝ ክልል የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ጽ ቤት መረጃ መሰረትም ባለፈው ዓመት በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል እና አማራ ክልል አዋሳኝ አካባዎች በተፈጠረው ግጭት ምክንያት ከ ሺ በላይ ዜጎች ተፈናቅለው በመተከል ዞን አራት የተለያዩ ጣቢዎች ተጠልለው ይገኛሉ፡፡ ነጋሳ ደሳለኝ
የኮማድ ፖስቱ ዋና ግብ ሰላምና ጸጥታን ማስፈን ነዉ ይዘት
ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። ስለዚሁ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃዎችን ከሰነድ አጠባበቅ መግለጫችን ማግኘት ይችላሉ።
የምርጫ ዝግጅት በአሶሳና ካማሺ ዞን
ስድስተኛውን የሀገር አቀፍ ምርጫ ላይ ለመሳተፍ ከ ሚሊዩን በላይ መራጮች መመዝገባቸውን የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከዚህ ቀደም ባወጣው መግለጫው ጠቁመዋል፡፡ ከእነዚህም በተጨማሪም የመራጮች ምዝገባ ያልተካደባቸው አካባቢዎች እና በሰኔ ዓ ም ምርጫ የማካሄድባቸውም ስፋራዎችም በርካቶች መሆናቸው ተገልጸዋል፡፡ ስድስተኛውን የሀገር አቀፍ ምርጫ ላይ ለመሳተፍ ከ ሚሊዩን በላይ መራጮች መመዝገባቸውን የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከዚህ ቀደም ባወጣው መግለጫው ጠቁመዋል፡፡ ከእነዚህም በተጨማሪም የመራጮች ምዝገባ ያልተካደባቸው አካባቢዎች እና በሰኔ ዓ ም ምርጫ የማካሄድባቸውም ስፋራዎችም በርካቶች መሆናቸው ተገልጸዋል፡፡ በምዕራብ ኦሮሚያ በሚገኙ የወለጋ ዞኖች አምስት በሚደደረሱ የምርጫ ጣቢዎች ምርጫ በሰኔ ወር እንደማይካድም የምርጫ ቦርድ መግለጫ ያሳያል፡፡፡፡ ምርጨ ካርድ የወሰዱ የአሶሳ ከተማ ነዋሪዎች ይወክለናል የሚሉትን ለመምረጥ ዝግጁ መሆናቸው የተናሩ ሲሆን በተለያዩ ግጭቶች ተፈናቅለው በምእራብ ወለጋ የሚገኙ ነዋሪዎች ደግሞ የአካባቢው ሰላም ተረጋግጠው ወደ ቀድመው ቀአቸው መመለስ እንደሚፈልጉና የእለት ደራሽ ድጋፍ ወቅቱን ጠብቀው እንዲደርሳቸው ሀሳብ አቅርበዋል፡፡ በቀጣይ ሳምንት ሰኞ ሰኔ በሚካሄደው ኛው ሀገራዊ ምርጫ ላይ ለመሳተፍ ምርጫ በሚካሄድባቸው የአሶሳና አሶሳ ዞን ወረዳዎች ከ ሺ በላይ ዜጎች የምርጫ ካርድ መውሰዳቸውን የምርጫ ቦርድ መረጃ ያመለክታል፡፡ አቶ ሙላቱ ክፍሌ የአሶሳ ከተማ ነዋሪ ሲሆኑ በሀገራዊ ምርጫ ላይ ለመሳተፍ የምርጫ ካርድ ካወጡት መካከል ናቸው፡፡ ዘንድሮ ለ ኛ ጊዜ በምርጫ እንደሚሳፉ የተናገሩት አቶ ሙላቱ ምርጫው ሰላማዊ እንዲሆንና ከምርጫው በኀላም በሀገሪቱ ሰላም ይሰፍናል የሚል እምነት እንዳላቸው አስታውቋል፡፡ አቶ ማቲዩስ ታከለ ደግሞ በሚያዚያ ወር ከካማሺ ዞን የተፈናቀሉ ሲሆን በምዕራብ ወለጋ መንዲ ከተማ ይገኛሉ፡፡ ቀድሞ ከነበሩት ስፋራ በነበረው ግጭት ለበርካታ ዓመት ከኖሩበት ሰዳል ወረዳ ሸሽተው በጊዜአዊ መጠለያ ጣቢያ የሚገኙ ሲሆን በሀገራዊ ምርጨ ለመሳፍ እድሉን እዳላገኙም ገልጸዋል፡፡ ከሀገራዊ ምርጫም በኀላም ሰላም ሰፍኖ ወደ ቀድሞ ቀአቸው ለመመስ ፍላጎት እንዳቸው አመልክቷል፡፡ በተጠለሉበት ጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያም ሆነው በምርጫ ለመሳተፉ ፍላጎት እንደነበራቸው እና የምርጫ ካርድ ለማውጣት የከተማው ነዋሪ መሆን አለባችሁ በመባላቸው እንዳልተሳካቸውም ተናግረዋል፡፡ የግብርና ባለሙያ የሆኑት አቶ በቀለ ተስፋሁን ይሰሩበት ከነበረው ካማሺ ዞን ሰዳል ወረዳ ከተፈናቀሉ ሁለት ወር እንደሆናቸው ተናግረዋል፡፡ አሁን ባሉበት ምዕራብ ወለጋ ማናስቡ ወረዳ ከ ሺበላይ ተፈናቃዩች እንዳሉም በመጥቀስ ወደ ነበሩበት አካባቢ ለመመስ ፍላጎት እደለላቸው ገልጸው ከተፈናቀሉበት አካባቢ የጸጥታ ሁኔታም በምርጫ ለመሳፍ አመቺ አለመሆኑን አክልዋል፡፡ የብሔራዊ ምርጫ ቦርደ ሰኔ ባወጣው መግለጫውም በተለያዩ ምክንያቶች ሰኔ ሀገራዊ ምርጫ የማይካሄድባቸው በምዕራቡ ኢትዩጵያ የሚገኙ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞንና ካመሺ ዞን እንዲሁም ከኦሮሚያ ክልል ወለጋ ዞኖች ስድስት የሚደርሱ ጣቢያዎች የድምጽ አሰጣጥ ሂደቱ ጳጉሜ ዓ ም እንደሚከናወን አሳታውቋል፡፡ ነጋሳ ደሳለኝ