Proverb,Amharic Description ሀምሳ ሎሚ ለአንድ ሰው ሸክሙ ነው ለሃምሳ ሰው ግን ጌጡ ነው።,በጣም የሚክብድን ሥራ ከተረዳዱበት በጣም ይቀላል፡፡ ሀ ሳይሉ ጥፈት ውል ሳይዙ ሙግት,ምንም መረጃ ሳይኖር አሸንፋለሁ ማለት ዘበት ነው፡: ሀ ባሉ ተዝካር በሉ,ትንሽ በሠሩ ብዙ አንደሠሩ ተቆጥሮላቸው ተጠቀሙ ሀብታም ለሀብታም ይጠቃቀሱ ድሀ ለድዛ ይለቃቀሱ,ቢጤ ለቢጤ ሀብታም ሲሰጥ የድፃ ሙርጥ አበጠ,አንዱ ሲሰጥ ሌላዉ ተመቀኘ ሀብታም ቢወድቅ ከለገነት ድሃ ቢወድቅ ከመሬት,ሀብትም ሲከስር በአንዴ የሚደርስበት የሞራል ውድቀት ከፍተኛ መሆኑ ሲሆን ድሃ ግን ብዙም አይሰማውም ሀብታም በምጽዋቱ፣ ድሃ በጸሎቱ,ሁሉም በየችሎታው አምላኩን ያሰታውሰዋል ሀብታም በከብቱ ድሃ በጉልበቱ,ሁሉም የአኔ ነው የሚለው ነገር አለው ሀብታም በወርቁ ድሃ በጨርቁ,ሁሉም ባለውና በእሱነቱ ይጠቀማል ሀብታም በገንዘቡ ይኮራል ድሃ በጥበቡ ይከብራል,ሁሉም ሰዉ የሚኮራበት የየራሱ ተሰጥኦ አለው ሀብታም በገንዘቡ ድሃ በጥበቡ እርስ በእርስ ይቃረቡ,ሀብታም በገንዘቡ ድሃ በጉልበቱ ሀብታም ቢሰጥ አበደረ እንጅ አልሰጠም,ሀብታም ገንዘብ ቢሰጥ በምትኩ የድሃን ጉልበት ይሻል ሀብታም ነው መባል ያኮራል ድሃ ነው መባል ያሳፍራል,ሕብረተሰብ ያከበረው ሲከበር ያንቋሸሸው ይንኳሰሳል ሀብታም እንደሚበላለት ድሃ እንደሚከናወንለት,ሁሉም በየችግሩ ላይ ያተኩራል ሀብታም ያለ ድሃ አይኮራም፣ ድሃ ያለ ሀብታም አይበላም,ሀብታም ከሌለ ድሃ የለም፣ ድሃ ከሌለ ሀብታም የለም ሀብታም ገንዘቡን ያስባል፣ ድሃ ቀኑን ይቆጥራል,ሀብታም የሀብቱን መጨመር ሲያሰብ ድሃ ግን ገንዘብ የሚያገኝበትን ቀን ይቆጥራል ሀብትና ዕውቀት አይገኝ አንድነት,ሁሉን አሟልቶ አይሰጥ ሀብት የጠዋት ጤዛ ነው,ሃብት ጠፊ ነው መልክም ረጋፊ ነው ሁለተኛ ግፌ፣ ጫንቃዬን ተገርፌ፣ ልብሴን መገፈፌ,የግፍ ግፍ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ ሁለተኛ ግፍ ልብሴን ይገፍ ጀርባዬን ይገርፍ,የግፍ ግፍ ሥራ ነው የተፈጸመብኝ ሁለተኛ ጥፋት፤ ቆሞ ማንቀላፋት,ከመጀመሪያው ጥፋት ሁለተኛው ይባስ ሁለተኛ ጥፋት፤ ከገበያ ማንቀላፋት,ከመጀመሪያ ጥፋት ሁለተኛው የባስ ሆነ ሁለቱን ወንበዴ፤ በአንድ ዘዴ,ሥራን ቶሎ ለመጨረስ በዘዴ መጠቀም ይገባል ሁለቱን የተመኘ፤ አንዱንም አላገኘ,ከሁለት የወደቀ ዛፍ ሁለት ሆነው የተናገሩት በመሬት የቀበሩት,ከራስ ያለፈ ሚስጥር ተደብቆ ሊቆይ አይችልም ሁለት ሞት መጣ ቢለው፤ አንዱን ግባ በለው አለ,የማይቀርን ነገር አምኖ መቀበል ይገባል ሁለት ቁና ሰጥቼ፤ አንድ ጥንቅል,ባጐረስኩ አጄን ተነክስኩ ሁለት ባላ ትከል አንዱ ቢሰበር ባንዱ ተንጠልጠል,ሁለት አማራጭ ይኑርህ ሁለት ብልጥ፤ ኑግ አያደቅ,የፉክከር ቤት ሳይዘጋ ያድራል ሁለት ነዶ ይዞ ወደ ከምር ጠጋ,ትንሽ ቆሎ ያደርሳል ከአሻሮ ሁለት አይወዱ፤ ከመነኮሱ አይወልዱ,ሁለት ነገሮችን በአንድ ጊዜ አትመኝ ሁለት አገር አራሽ ለባለንጀራ አውራሽ,ሩቅ ለፍቶ ደክሞ ለሰው ሁለት እፎች ባይናከሱ፤ ይናቀሉ,ባይጐዳዱም በጥቂቱ መሞካከራቸው የማይቀር ይሆናል ሁለት አግር አለኝ ብሎ፤ ከሁለት ዛፍ አይወጡም,ሁለት ነገሮችን በአንድ ጊዜ ማከናወን አይቻልም ሁለት የተመኘ፤ አንድም አላገኘ,ይሀንንም ያንንም መመኘት ውጤቱ አያምርም ሆድ ሆዱን የምትል ወፍ አለች ምን አለች?,ያለሆዱ የሚያሳስበው ጉዳይ የለውም ሆድ ለማታ በልቶ ለጧት,ምን ዛሬ ብንበላ ነገ ሆድ አዲስ ነው ሆድ ለባሰው ማጭድ አታውሰው,አንኳንስ አናቴ ሞታ አንዲሁም አልቅስ አልቅስ ይለኛል ሆድ ሲሞላ ራስ ባዶ ይቀራል,ለሆድ ብቻ ሳይሆን ለዕውቀትም አንጣር ሆድ ሲሞላ ፍቅሩ ሌላ፤ ሆድ ሲጎድል ሰው ያጋድል,የሰው ልጅ ዋልታው ምግብ ነው። ሰው ካልበላ ቆሞ መራመድ አይችልም። ሆድ ሲያር ጥርስ ይስቃል,ውሰጡን ለቄስ ሆድ ሲያውቅ፤ዶሮ ማታ,ደሮን ሲደልሏት በመጫኛ ጣሏት ሆድ ባዶ ይጠላል,በተለመደው ሰዓት ምንም ይሁን ምን መመገብ አለብህ ሆድና ልጅ አይጣላህ,ልጅንና የሚሞትን ሽማግሌ አታስቀይም ሆድና ግንባር አይሸሸግም,ለመብላት እየፈለክ አትግደርደር ሆድን በጎመን ቢደልሉት ጉልበት በዳገት ይለግማል,እራት የሌለው ቄሰ አንደልቡ አይቀድስ ሆድ እንዳሳዩት ነው,ሆድ እንዳስለመዱት ነው ሆድ ከሁዳድ ይሰፋል,ቻለው፤ ታጋሽ ሁን ሆድ ወዶ፤ አፍ ክዶ፤ ክፉ ለምዶ,የተለመደ ልማድ መታወቁ መገለጡ አይቀርም ሆድ የኔ ነው ሲሉት፤ ቁርጠት ሆኖ ይገላል,የተማመኑበት ዘመድ መልሶ ጠላት ይሆናል ውሻ በበላበት ይጮኻል,ሆድ ያበላውን ያመሰግናል ሆድ ያባውን ብቅል ያወጣዋል,ስካር ቅሬታን ለመናገር ይገፋፋል ሆድ ዘመድ ሳይወድ፤ አፍ እህል ሳይለምድ,የተመኘኸውን ፈጥነህ አከናውን ሆድ ድንጋይ ልበላ ነው ቢል፤ ጉሮሮ በየት አሳልፈህ? አለው,የማይደረግን ነገር ለተቀባይ ሰው ማስፈራራት እማይሆን የማይደረግ ነገር ነው ለሀምሳ ጋን አንድ አሎሎ,ተልባ ቢንጫጫ በአንድ ሙቀጫ ለሀብት መትጋት ሰውነትን ያከሳል፤ገንዘብ ማሰብ አንቅልፍ ይነሣል,ለሀብትና ለገንዘብ የሚደረግ ሩጫ ሰላም መንሳቱ አይቀርም ለሁሉም ጊዜ አለው,ወቅቱን ጠበቆ የሚሆነው ይሆናል ለሂያጅ የለውም ወዳጅ,የተሾመን ይሟገቱለታል፤ የተሻረን ይመስክሩበታል። ለባለጌ ጥሩ የሚመኝለት የለም። ለሆዳም ስው ማብላት ውቅያኖስን ለመደልደል መቃጣት,የማይሆንን ነገር አንዲሆን መሞከር ትርፉ ድካም ብቻ ነው ለሆዳም በሬ ጭድ ያዝለታል,ለአንዳንዱ በለስ ይቀናዋል ለሆዴ ጠግቤ ፤በልብሴ አንግቤ,ሁሉ ሞልቶ ተርፎ ምን ጐድሎ ለሆድ ቁርጠት ብላበት፤ለራለ ምታት ጩሀበት,ያልሆነ ምክር መምከር ለላሙ መንጃ፤ ለሸማው መቅደጃ,መሣሪያ ጠቃሚ ነው። ለማንኛውም ነገር መሣሪያና መጠቀሚያ ያመቻችለታል አግዚአብሔር ለላሙ መንጃ፤ ለሸማው መከንጃ,ሥራን ለመከወን መሣሪያ ጠቃሚ ነው። ሥራን ለማከናወን ቸሩ አግዚአብሔር ያመቻችለታል ለላም ቀንዷ አይከብዳትም,የእኔ ነው የተባለ በሙሉ አያስጨንቅም ለላም ከጥጃዋና፤ ከአላቢዋ ማን ይቀርባታል,ሁለቱም የእሷ ጥገኞች ናቸው ለላም የሣር ለምለም,የሚጠቅምን ነገር መጠበቅ አለበት ለላም ጥጃዋ ለአህያ ውርንጭላዋ,ሁሉም ለራሱ ለሌለው ምን ትለው,ያጣን ሰው ምን አድርግ ትለዋለህ ለሌባ ቅሌቱ ልብሱ ነው,ሌባ ሁሌም አንደተዋረደ ነው ለልጅ ሲሉ ይበሉ፤ ለወዳጅ ሲሉ ይጣሉ,ለምትወደው ነገር ተጠቃ ለልጅ አይሥቁለትም፣ ለውሻ አይሮጡለትም,ለልጅ ፊት ካሳየኸው ያዋርድሃል ለልጅ ጥርስህን ለዝንብ ቁስልህን አታሳይ,ለልጅ ፊት ካሳየህ ያዋርድሃል ለልጅ ጨዋታ ለባለጌ ቧልት,ልጅ ጨዋታ እንደሚወድ ሁሉ ባለጌም ቁም ነገር የለውም ለሎሌው ምን ትለው?,ለተከታይ ምን የምትለው ይኖርሃል? ለሕልም ምሳሌ የለውም,ለአንዳንዱ ጉዳይ ማስረጃ አይገኝም ለመሄድና ለመመለስ፤ አዛዥ ራስ,ሁሉም የሚወሰነው በራስ አዛዥነት ነው ለመሆኑ ሳይሆን አንዴት ይሆናል ቢሆን,የሆነበት ስልትና ዘዴ ምን ይሆን። መጥፎም ደግም ነገር ላይሆን ደግ ቢሆን መልካም መጥፎ ቢሆን ወይም ቢያጋጥም ምን ይሆናል ለመሥራት ያፈረ፤ መብላት ደፈረ,ሥራ አይወድም ግን ሆዳም ነው ለመሪህ ዓሣ ምሰል,ከአለቃህ ጋር ሽርጉድ አያልክ ኑር ለመስማት የፈጠንህ ለመናገር የዘገየህ ሁን,የቸኮለ አፍሶ ለቀመ ነውና ብዙ ከመናገር ጥቂት ማዳመጥ የበለጠ ነው። ለመስጠት አለመቸኮል፤ ከሰጡም ወዲህ አለመጸጸት። ለመስጠት አጥንቶ መስጠት ከተሳሳትክ በኋላ ግን አትጸጸት ለመታማት መፍራት,ይሉኝታ ማለት ተገቢ ነው ለመነኩሴ መልካም ሎሌ,ለነፍሱ ያደረ ጨዋ ረዳት አያጣም ለመከራ የጣፈው፤ቢነግድ አይተርፈው,የአርባ ቀን እድሉ የሆነ ምንም ቢለፋ አያልፍለትም ለመከራ ያለው መነኩሴ ፤ዳዊት ሸጦ አህያ ይገዛል,ያለሙያው የተሠማራ ትርፉ ችግር ብቻ ነው ለመኻን እማዬ፤ለአገልጋይ አትዬ ብርቋ ነው,አይቶ ለማያውቅ ሁሉ ቁልምጫ ብርቁ ነው ለሙት የለው መብት,ላለፈ ለማይመለስ መሟገት ፋይዳ የለውም ለሚመለከት ለሚያየው፤ሞት ቅርብ ነው,ሰው ሟች መሆኑን መረዳት ተገቢ ነው ለሚስት ያጐርሷል፤ለተመታ ይክሷል,ለሚስት እንክብካቤ አንደሚደረግ ሁሉ ለተበደለም ካሳ ያስፈልገዋል ለማረም ማን ብሎት፤ሲሠራው ግን ግድፈት,ለሰው የሠራውን ያጥላላ፤ እራሱ ግን ሥራ አይችልም ለማን አለው ፈጣሪ አለው፤ ጠጅ ለሌለው ውኃ አለው,ምርጡ ባይገኝ አንኳ ተራው ነገር መገኘቱ አይቀርም ለማን ይፍረዱ? ለወደዱ፣ አይደለም ለወደዱ፤ ለወለዱ።,ለሚወዱት ሰው ጥሩ ቢያደርጉም ከአብራክ ለወጣ ልጅ ደግሞ የበለጠ ያደላሉ ለማኝ ቢያብድ ስልቻውን አይጥልም,ዓላማ ካለህ ዓላማህን መሳት የለብህም ለማኝ አያማርጥም፤ ማር አይኮመጥጥም,የቸገረው እርጉዝ ያገባል ለማየት የፈለገ ዐይኑን ይገልጣል,ለሁሉም ነገር መሠረቱ ፍላጐት ነው ለማያውቀው፤ፎገራ ዱሩ ነው,የማያውቁትን ነገር ለማድረግ መሞከር በጣም አስቸጋሪ ነው ለማያውቅሽ ታጠኝ,ስለማውቅሽ አታታልይኝም ለማይሞት መድኃኒት አለው,ችግር የሌለበት ስለችግር አያወራም ለማይሰጥ ሰው ፤ስጡኝ ማለት ማን አሰተማረው,ላም ያልዋበት ከብት ለቀማ ለማዕበል ወደብ ለነፋሰ ገደብ የለውም,ከአቅም በላይ የሆነን ነገር ለማቆም መሞከር ትርፉ ድካም ነው ለምላጭ የሰጡት ገላ አያምም,ተስማምተው ያደረጉት ነገር አይከብድም ለምሽት መብራት፣ ለመከራ ጊዜ ብልሃት,ከመድረሱ በፊት ለችግርህ መፍትሔ መፍጠር አለብህ ለምሽት መብራት፤ ለሥራ ብልሃት,ሥራን ለማከናወን ዘዴና ብልሃት ያስፈልጋል ለምን ተክዤ፤ አምላክን ይዤ,አምላክ እስካለ ያሰብኩትን ሁሉ ይፈጽምልኛል ለምን ያለው ስልቻውን፤ ጫን ያለው ኮርቻውን አያጣም,የአምላክ ሰጦታ የተጓደለ አይደለም ለምን ጊዜው ነቀዝሽ,ምነው አንዲህ ፈጥነሽ መጥፎ ልትሆኝ ቻልሽ? ለምኖ ለማኝ፤ ቆቤን ቀማኝ,ከሌላ ለምኜ ያገኘሁትን ሌላው ለምኖ ወሰደብኝ ለሞኝ ሰኔ በጋው፤ መስከረም ክረምቱ,ሞኝ ማድረግ የሚገባውን ነገር በትክክል በወቅቱ አይሠራም ለሞኝ ንገረው ምን ይሰማ ብዬ፤ ለብልህ ንገረው፤ ምን ይሳተው ብዬ?,ሞኝ የሚነግሩትን አይሰማም፤ ብልህ ግን ነገሮች በሙሉ በቀላል ይገባዋል ለሞኝ ከሣቁለት፤ለቅዘን ከሮጡለት,ለሞኝ ፊት ካሳዩት ይዘረጥጥጣል ለሞኝ ከሣቁለት፤ለውሻ ከሮጡለት,ለሞኝ ፊት ካሳዩት ይዘረጥጥጣል ለሞኝ ጉድጓድ አያሳዩትም፤ ቤት ነው ብሎ ይገባበታል,ሞኝ ጠቃሚና ጎጂውን አያገናዝብም ለሞፈር ቆራጭ፤ እርፍ አይታየውም በግላጭ,ባለማስተዋል በቅርብ ያለውን ነገር ሳይጠቀምበት ይቀራል ለረዥም መንገድ አትሩጥበት፤ ለረዥም ነገር አትቸኩልበት,በእርጋታ የሚሠሩት ሥራ ውጤታማ ይሆናል አብዶ ይሮጣል፤ አትርሳኝ ብሎ ተከትሎታል,ምንም የማይፈጽምልህን ሰው አታስቸግር ለራሉ አያውቅ፤ለሰው አይጠይቅ,አጉል መኮፈስ ለራሉ አያውቅ ነዳይ ፤ ቅቤ ለመነ ላዋይ,ለራሱ አያውቅ ጠንቋይ መድኃኒቱን ሳዋይ ለራሱ የማይረባ ፤ለሰውም ኣይረባ,ወይ አይበላ ወይ ሰው አያስበላ ለራሱ ጥላ፤ ለአግሩ ከለላ,አለኝታ መከታ፣ ጋሻ ለራስ ምታት ጩህበት፤ ለሆድ ቁርጠት ብላበት,ተቃራኒ ምክር ለራስ ሲቆርሱ አያሳንሱ,ራስ ወዳድ መሆንን ያመለክታል ለራስ ከበጁ፤ አይታጡ ክደጁ,ራስን መንከባከብ ከመጥፎ ሁኔታዎች ይጠብቃል ለራበው ሰው ቆሎ፤ ለቁልቁለት በቅሎ,ተስማሚ የሚሆን ነገር መምረጥ ትክክል ነው ለራት የማይተርፍ ዳረጎት,ብዙ የማይጠቅም ለሰውም የማይሆን ለራስም የማይሆን ለርስት ሴቶች ስንኳ ይሞቱበታል,ለጥቅም ሲል የማይታገል አይኖርም ለሰለባ የመጣ ልብስ ቢጥሉለት አይመለስ,ሰውን ለመጉዳት ሆን ብሎ የተነሳን ሰው መመለስ ያስቸግራል ለሰማይ ምሰሶ የለው፤ ለባእድ ሥር የለው,ባዕድ ምንም ቢያቀርቡት ዞሮ ያው ነው ያው ዘመድ ይሻላል ለሰበበኛ ቂጥ መረቅ አታብዛበት,ለቦና ጥጃ ውስ አያንሰውም ለሰባቂ ጆሮህን አትስጠው,ወሬኛን ማዳመጥ የለብህም ለሰው ልጅ ከሚያበሉ፤ ለውሻ ልጅ ያብሉ,በችግር ጊዜ ሰውን ለማይከዳ ውሻ ማብላት ይሻላል ለለው ልጅ ከማብላት ለውሻ ማብላት,በችግር ጊዜ ሰውን ለማይከዳ ውሻ ማብሳት ይሻላል ለሰው ሞት አነሰው,ሌላ ሰውን ማመን ቀብሮ ነው ለሰው ሰው ነው ልብሱ,የሰውን ችግር የሚያቃልል ሰው ነው "ለሰው ቢነግሩት መልሶ ለሰው፤ ጫር ጫር አድርጌ ዐፈር ላልብሰው ",ምስጢር የብቻ የግል ነው ለሰው ብሎ መሞት አምላክነት ያሻል,ከራስ በላይ ነፋስ ለሰው ብሎ ሲያማ፣ለእኔ ብለህ ስማ,ነገ በኔ ለሰው ብትል ትጠፋለህ፤ ለአግዜር ብትል ትለማለህ,እግዚአብሔር የሚወደውን ነገር መፈጸም ጽድቅ ነው ለሰው ከበሬታው ሰው፣ ለወጥ ማጣፈጫው ጨው,ለሰው ሰው ነው ልብሱ ለሰው የማይል ሰው፤ ሞት ሲያንሰው,ለተቸገረ የማያዝን ሰው አያስፈልግም ለሰው ጠላቱ፤ይወጣል ከቤቱ,አንዳንዴ የተማመነበት ዘመድ ጠላት ይሆንብሃል ለሰይጣን አትስጠው ሥልጣን,ጨካኝን ሰው አትሹመው ለሰጭም አያንሰው፤ ለበይም አይደርሰው,በስጦታው ያልረካ ሰው ለስሟ መጠሪያ ቁና ሰፋች,የምትታወስበትን ተግባር አከናወነች ለስሱ ፍትፍት አሳይቶ እበት ማጉረሱ,ለገብጋባ መልካሙን ሳይሆን የማይሆነውን መስጠት ለሸማኔ ማገጃ፤ ለስት ማረጃ,ተስማሚ የሆነ መሣሪያ ያስፈልጋል ለሹመት ካልመከሩለት፤ ለጥርስ ካልከደኑለት,ለመሾም ቅድሚያ ሰውየውን ማጥናት ያስፈልጋል ለሹመት ያደለው፤ የለማኝ አለቃ ይሆናል,ምንም ክብርና ዝና ለሌለው ቦታ መታጨት ለሺ ፍልጥ ማሰሪያው ልጥ,ተልባ ቢንጫጫ ባንድ ሙቀጫ ለበራ ወለባ፤ ለውሻ ገለባ,ያልሆነ ሥራ መሥራት ምንም አይጠቅምም ለበግ ደጋ፤ ለምቾት አልጋ,በተገቢው ቦታ ተስማሚ ነገር ለቡናሽ ቁርስ የለሽ ፤ ለነገርሽ ለዛ የለሽ,ምንሽም ምንሽም አያምርም ለባለጌ ገድሉ ውርደቱ,ባለጌ ውርደታም ስለሆነ ጥሩ እንደሠራ ሁሉ ይኩራራል ለእባብ እግር የለው፤ ለሞኝ መላ የለው,መፍትሔ ለሌለው ነገር ብዙ አትጨነቅ ለባእድ የሰጡት ኮሶ፣ ይጠጣል ደም ጎርሶ,ከማይሆን ሰው ጋር የተዋዋሉት ውሎ አድሮ ችግር ማስከተሉ አይቀርም ለቤት ሳማ፤ ለውጭ ቄጤማ,ለቤቷ ጨቅጫቃ ለውጪ ሰው መሬት ነች ለቤት ሣንቃ፣ ለሰው አለቃ፤ ለነገር ጠበቃ ያስፈልገዋል,አስፈላጊው ሁሉ በቦታው ላይ ቢገኝ ሕይወት የተሟላች ትሆናለች ለቤት ባላ፤ ለችግር ነጠላ ያስፈልገዋል,በችግር ጊዜ ብዙ ባይገኝም በተገኘችው በትንሿ ማዝገም የግድ ነው ለቀላል ምስጢር መንገር፤ በቀዳዳ ጤፍ መቋጠር,ምስጢር ለማይደብቅ ሰው አትናገር ለቀማኛ የለውም እጅ ለበቅሉ የለውም ልጅ,እባብን ሆዱን አይቶ እግር ነሳው ለቀባሪው አረዱት,ለሚያውቀው ሰውዬ ያላወቀ መስሏቸው ነገሩት ለቀንዳም በሬ ቤት አትክልክለው፤ ቀንዱ ይከላከለዋል,የራሱ ባህርይ ይውቀሰው ለቁንጫ ለምድ ያወጣል,የማይጠበቅ ነገር ለቂጡ ጨርቅ የለው፤ ቆንጆ ያባብላል,እሱነቱን የማያውቅ ለቅልብልብ አማት፤ ሲሶ በትር አላት,መቅለብለቧ ስለማይቀር መመታቷ አይቀርም ለቅሶ ሳለ ከቤት፤ ይሄዳል ከጐረቤት,የቤተሰብህን ችግር ሳታቃልል የሌላን ሰው ችግር ለማቃለል አትሞክር ለቅናት የለውም ጥናት,ስሜታዊ ነገሮች ከስሜት የሚመነጩ እንጂ ከልምድ አይገኙም ለቅዘን እግር አንስተውለት፤ ለውሻ ሸሽተውለት,ለሞኝ ፊት ካሳየኽው ይዘረጥጥሃል ለብልህ አይነግሩ፤ ለአንበሳ አይመትሩ,ብልህ ፈጥኖ ስለሚረዳ የተንዛዛ ምክር ሊሰጠው አይገባም ለብልህ አይነግሩ፤ ለድመት አያበሩ,ብልህ ፈጥኖ ስለሚረዳ የተንዛዛ ምክር ሊሰጠው አይገባም ማን ያልነበረ፤ ማን ያልተቀበረ,ሁሉም ጊዜው ሲደርስ ጽዋው ይሞላል ማን ያርዳ የቀበረ፤ ማን ይናገር የነበረ,የሚያውቅ ሰው ብቻ ይናገር ማን ያውቃል ባላገር፤ ማን ያጠብቃል ማገር,ሕዝብ የሚያውቀውን አትደብቅ ማን ያውቅ አገር፤ ማን ያጥብቅ ማገር,ሕዝብ የሚያውቀውን አትደብቅ ማወቅ መላቅ! አለማወቅ መናቅ,አለማወቅ ያስንቃል ማወቅ እናውቃለን ፤ ብንናገር አናልቃለን,ማወቅ አናውቃለን ብንናገር አደጋ ይደርስብናል ማውራት ነው ድህነት፤ መሥራት ነው ጌትነት,ሥራ አንጂ ወሬ ምንም አይሠራም ማዕረገ ቢስ፤ እራቱ ገሚስ,ሲያከብሩት የማይከበር ለው የሚያገኘውን ሙሉ በሙሉ አያገኝ ማየት ከመልአክ፤ መቀበል ከአምላክ,ለሁሉ የሚቸር ዓምላክ ብቻ ነው ማጀት በጎረሰ፤ ደጃፍ በመለሰ,በጠቅላላው ሁሉም ሰው ማጀት ያጠለቀው፤ ጉልቻ የላቀው,ፍጹም ድሃ ነው ማግኘት ማውጣትን ያስለምዳል,ያለው ሲያወጣ ሲመዝ አይጨነቅም ማግኘት ማውጣትን ይመልሳል,ገንዘብ የሚያከብራትን ታከብራለች ማጣትና ማግኘት ጆሮ ለጆሮ,አንድ ጊዜ ቢያገኝ ሌላ ጊዜ ሊያጣ ይችላል ማጣት ከሰማይ ይርቃል,ድህነት አስከፊ ነው ማጥፋት፤ በትንሽዋ ጣት,ገንዘብህን ጨርሰህ አንዳታጠፋ በትንሽ በትንሽ አውጣ ማጭዱም ገመዱም ከሣሩ ውስጥ ነው,መፍትሔው አብሮ አለ ማፈር ከሌለ፤ ክብር የለም,አጸያፊ ተግባር ማከናወን ያስንቃል ማፈር ከብዙ ነገር ይጠበቃል፤ አለማፈር በብዙ ነገር ያስጠይቃል,አጸያፊ ተግባር ካላክናወንክ ያስከብርሃል ፤ አጸያፊ ተግባር ካከናወንክ ያስንቅሃል ምለህ በክርስቶለ ተገዝተህ በቄስ,በጌታ ስም የገባኸው ቃል አክብር ምላሱ አይታጠፍም,ቃሉን ያከብራል ምላስ ቢጥም ቀዶ ይጠቅም,ምላስ ክፉም ደግም ይናገራል፤ ያስከፋልም፤ ያስደስታልም ምላስ ይቀባል፤ ጥርስ ይወጋል,በፍላጐት የፈለጉትን ማድረግ ይቻላል ምላጭ ለምላጭ ፤ጠፍር ለመለመጫ,አንዱን በአንዱ ወደሚፊልጉት ማምራት ምላጭ ምላጭን አይቆርጠው፤ ሰው ሰውን አይበልጠው,ብልጥን ብልጥ አያታልለጡም ምላጭ ቢያብጥ በምን ይበጡ ውኃ ቢያንቅ በምን ይውጡ,መፍትሔ የሚያስገኘው ከተበላሸ መፍትሔ ለማግኘት ያስቸግራል ምላጭ አይበጥ፤ ያበጠውን ያፈርጥ,ብልጥ ሰው አያታልልም ጎበዝ አይደፈርም ምስጢር ከቤት ፤ምክር ከጎረቤት,ምስጢርህን አደባባይ አታውጣ ምስጢር የባቄላ ወፍጮ አይደለም,ምስጢር በአደባባይ የሚነገር አይደለም ምስጢር ይደበቃል፤ ወፍጮ አይደለም,ምስጢር በምስጢርነቱ ይያዛል ምርቅና፤ ፍትፍት,ክፉና ደግ ምሳሌህ ሁሉ አንካሳ ነው,ነገርህ ሁሉ አይጥምም ምስለኔ ሁሉ አንደኔ,የእኔ ነው ያልኩት ሁሉ ከእኔ አይሻልም ቀስ በቀስ እንቁላል በእግሩ ይሄዳል,ዘገምተኛ ትናናሽ ለውጦች ለከፍተኛ ለውጥ መሰረት ናቸው ጅብ ከሄደ ውሻ ጮኸ,አንዳንድ ሰዎች ድፍረትን ወይም በራስ መተማመንን የሚያሳዩት ማስፈራሪያው ሲያልፍ ብቻ ነው የአባይ ልጅ ውሃ ጠማው,የተትረፈረፈ እና በቀላሉ ሊደረስበት የሚችል ነገር ማጣት ጥሩ ውይይት ሁልጊዜ ከጥሩ አልጋ የተሻለ ነው,ሃሳብ መለዋወጥ ከአካላዊ ምቾት ወይም ፍላጎት የሚገኘውን እርካታ ይበልጣል ምከረው ምከረው እንቢ ካለህ መከራ ይምከረው,አንድን ሰው የሚቻለንን ያክል ብቻ እንድንመክር እና እምቢ ካል ግን በራሱ እንዲማር እንድንተወው የሚመክር ምሳሌ ቀድሞ ነበር እንጂ መጥኖ መደቆስ አሁን ምን ያደርጋል ድስት ጥዶ ማልቀስ,አንድን ነገር ከጀመርኩ በኋላ ማልቀስ ወይም መጸጸት ምንም ፋይዳ የለውም። አንድን ተግባር ወይም ጥረት ከመጀመር በፊት አርቆ የማየት እና የዝግጅት አስፈላጊነትን ያጎላል ጽድቅና ኵነኔ ቢኖርም ባይኖርም ከክፋት ደግነት ሳይሻል አይቀርም,ፅድቅና ቅጣቱ እውን ይሁን አይሁን ግፍን ከመፈፀም ልግስናን መለማመድ የተሻለ ነው በቃል ያለ ይረሳል በመጽሐፍ ያለ ይወረሳል,ጠቃሚ መረጃዎችን እና ግንዛቤዎችን ለወደፊት ትውልዶች ለማቆየት የጽሑፍ መዝገቦችን እና ሰነዶችን ዋጋ ያጎላል ያልጠረጠረ ተመነጠረ,የማይናወጥ ወይም ደህንነቱ የተጠበቀ ነው ተብሎ የሚታሰብ ነገር እንኳን ያልተጠበቀ ውጤት ወይም ውድቀት ሊያጋጥመው እንደሚችል ይጠቁማል ቀኝ እጄን ተነከስኩ,ስህተት መሆኑን በመገንዘብ በአንድ ውሳኔ ወይም ድርጊት መጸጸት ምስር መዝራት ሙያ ማጣት፤ አተር መዝራት ወይ ብልሃት እለች ጦጣ,የማይወዱትን ማጣጣል የሚወዱትን ነገር ከፍ ከፍ ማድረግ ምስርሽን በጥጥሽ,እዚያው ወደእኔ አታምጪው ምስር አራቱ ፤ ምስር ቢያጣ ሞቱ,ሰው የፈለገውን ቢያጣ ቅር ይለዋል ምስክር ለበለጠ አውድማ ለመለጠ,አመቺ ሁኔታን ለፈጠረ ድጋፍ ይሰጠዋል ምስክር ቢያድር ይለጠጣል ሽንፍላ ቢያድር ይመለጣል,ማንኛውም ነገር በጊዜው መከወን ይገባል ምስክር ከበለጠ ባቄላ ከፈጠጠ,በበቂ ምስክር ማሸነፍ ይቻላል ምስክር ከተጠራ መስዋዕት ከተሠራ,አንድ ነገር ቆርጠው ካደረጉት በኋላ ለመቀየር ያስቸግራል ምስክር ያለው ሙግት አያዳግትም ለመርታት,ምስክር ከበለጠ ባቄላ ካፈጠጠ ምስጋና አዋቂን ያበራታል ቂልን ያሳብዳል,ምስጋና ያበረታታል ምስጥ ከምድር ውስጥ,ውስጥ ውስጡን ተንኮል የሚፈጽም ሰው ምቀኛ አታሳጣኝ,ምቀኛ ያለው ሰው ላለመውደቅ ተግቶ ይሠራል ምቀኛ የኑሮ መጋኛ,ምቀኛ ጠላት ነው ምቀኛ ጠላቱን ይተካል ወዳጁን ይንቃል,ወዳጁን ለመጉዳት ለጠላቱ ቀዳዳ ይከፍታል ምነው ቢገዙ መድን ካበዙ,ዋስትና ካለው ብዙ አይጨነቅም ምናልባት ቢሰበር አናት ቅቤ ሿ ለመተኮሻ,የከረምት መሸጋገሪያህን በበጋ ተመልከተው ምንም በሙቱ እራድማ ሸምቱ,ምንም ቢሆን ያው ይሻላል ምንም ቢሆን ሥር ነው እንጂ እጢ አይደማም,የማይሆን ሁሉ አይሆንም የሚሆነውን ከማይሆነው እታዛንቅ ምንም ቢሆን ጉፋያ ሥጋ ሥጋ ነው,ባያስደስትም ያው ተመሳሳይ ነው ምንም ቢታረስ በዘጠና ቤቱ አይለቅም ቀጠና,ከድህነት መላቀቅ እልተቻለም ምንም ቢቸገሩ ተበድሮ ጋሬዳ,ያልሆነ ብድር ውሎ አድሮ የከፋ ነገር ያስከትላል ምንም ቢያጠምዱ በዘጠና ቤቱን አይተው ቀጠና,ከድህነት መላቀቅ አልተቻለም ምንም ቢጠም መንገድ ምንም ቢከፋ ዘመድ,ምንም ዘመድ ቢቀየምም ለችግርህ ጊዜ ደራሽ ነው ምንም ቢፋቀሩ አብረው አይቀበሩ,ምንም ቢዋደዱ ለእየቅል ነው መንገዱ ምንም ብቀጥን ጠጅ ነኝ ምንም ብደኸይ ጨዋ ነኝ,ማንነቴን ሳታውቅ እትናቀኝ ምንም ብታውቅ ከዳኛ ጋር አትሟገት,ችግር ውስጥ እንዳትወድቅ ምንም ብታፈገፍጊ ከግድግዳ አታልፊ,የትም እትደርሺ አንዲያው ደከምሽ ምንም ብትሞቺ እንዴት አደርሽ አንቺ,አልረሳሽም ሳስታውሽ እኖራለሁ ምንም ብጠላው በወንድሜ ግንባር ደም አልይብህ,ክፉ ነገር እንዲገጥመው አልመኝም ምንሽም ምንሽም አያምረኝ ከመሄድሽ በቀር,የሚያስደስት ባሕርይ የላትም ምን በአግሩ ቢመጣ በእጁ እንዳይመጣ አለ ዳኛ,የሚያቀብለውን ጉቦ እየተመኘ ምን ቢለፈልፉ ድካም ነው ትርፉ,በጭቅጭቅ ምንም አይገኝም ምን ቢኖሩ ከሞት አይቀሩ,ሞት የማይቀር ዕዳ ነው ምን ቢከፉ አሳብ ነው ትርፉ,ሐሳብ ምንጊዜም ከሰው ራስ አይወርድም ቁጥቋጦ ሲያድግ ዛፍ ይሆናል,ከፍተኛ ደረጃ ለመድረስ ከትንሽ ነገር በመነሳት ነው ቁጥቋቦ፣ ያለ ዛፍ አይሆንም,ለትንሹ ሞገስ የሚሆነው ትልቁ ነው ቁጭትና መረቅ፣ ለጊዜው ይጣፍጥ,ንዴት ለችግር ይዳርጋል ቁጭትና መጠጥ፣ ለጊዜው ይጣፍጥ,ንዴት ለችግር ይዳርጋል ቁፍ ቁፍ ያስኘሽ እንደ ቄብ ዶሮ፣ ለመከራ ላሳርሽ,ለትንከወከዊ መከራ እንዳይደርስብሽ ክፉውንና በጎውን መለየት ያስቸግረዋል,ክፉውንና በጎውን መለየት ያስቸግረዋል ቂልን፣ ለብቻው ስደበው፣ አራሱን በአደባባይ እንዲለድብ,የራሱን ጉድ ያበጀ እየመስለው ለሁሉም ስለሚያወራ ቂል አይሙት፣ እንዲያጫውት,ያዝናናል ያጫውታል ቂል ከጠገበበት እይወጣም,ነገን አያስብም ቂል ያገኘው ፈሊጥ፣ ውሻ የደፋው ሊጥ,ቂል ያማረለት እየመስለው ያገኛትን ነገር ሲደጋግም ይኖራል ቂምህን እትርሣ፣ የወደቀ እንሣ,የወደቀ አንሱ የሞተን አትርሱ ቂም ይዞ አኣሎት፣ ሳል ይዞ ለርቆት,ሁሉን ነገር በጥንቃቄ ሥራ ቂጡ የቆለለ ውሻ፣ እንደልቡ እይጮሀም,ፈስ ያለበት ዝላይ አይችልም ቂጥ ቢወድል፣ ፈስ እያድን,መወፈር ጥቅም የለውም ቃልህ ሳይዘጋ፣ እግርህ ሳይዘረጋ,ሳታርፍ /ሳትሞት/ ቄሱም ዝም፣ መጽሐፉም ዝም,ሁሉም ጸጥ አሉ ቄስ ለትዛዜ፣ ፍቅር ለሚዜ,ሁሉም በየሙያው ቢውል ቄስ ምን ይሻል ጠላ፣ ነገር ምን ይሻል ችላ,መተው ነገሬን ከተተው ቄስና ንብ፣ እያዩ እሳት ይገባሉ,ለሌሉች ጥቅም መሥዋዕትነት መክፈል ቄስ ኤረክስን መምህሩ፣ እናት አያስቀብሩ,የእናትን ውለታና ጥቅም መረዳት ቄስ ካናዘዘው፣ ፅድሜ ያናዘዘው,ስው ከመከረው መከራ የመከረው ቄስ ካፈረስ፣ ዲያቆን ከረከስ,ብርሌ ከነቃ እይሆንም ዕቃ ቄስ ያዘዘህን አርግ፣ ቄስ ያረገውን አታርግ,የእነሱን ባህርይ አትከተል ቅል በአገሩ፣ ድንጋይ ይስብራል,ውሻ በስፈሩ አንበሳ ነው ቅልውጥ እሳስቦ፥ ይጥላል ከዘመቻ,"አንድ ነገር ላይ በማተኮር ሌላውን ሳያስተውሉ አደጋ ውስጥ ይዘፍቃል" ቅመጮ የበዛበት ወጥ፣ አይፋጅ እይኮመጥጥ,ከልክ ያለፈ ነገር አይጥምም ቅማል በጥፍር ቢድጧት፣ ራ ደህና አለች,ዋናው ደህና ከሆነ ሌላ ሌላው ብዙ ጉዳት አይኖረውም ቅማል ከአካላት፣ ምሥጢር ከቤት,የሁሉም ነገር መነሻው ከውስጥ ከቤት ነው ቅማል ውኃ ውረጂ ቢሏት፣ ስንኳለስ መቼ ልደርስ,አቅምን ማወቅ ትልቅ ነገር ነው ቅርብ ያለ ጠበል፣ ልጥ ይነከርበታል,ነቢይ በሀገሩ አይከበርም ቅርናታም ለቅርናታም፣ ስንቡሌ ስንቡሴ ይባባሳል,ቢጤ ከቢጤው ይውላል ቅርንጫፍ እንደዛፉ,ከጨዋ የተወለደ ጨዋ፣ ከባለጌ የተወለደ ባለጌ ቅቤ ሻጭ፣ ድርቅ ያወራል,ቅቤውን ለማስወደድ ሲል ብዙ ያወራል ቅቤ ተነጥሮ ለመብላት፣ ያባት የእናት,ያባትና የእናትን ሀብት ለማግኘት እንዲህ ቀላል አይደለም ቅቤና ቅልጥም፣ ወዴት ግጥምጥም,በፍጸም እይመሳለሉም ቅቤ እንጣሪቱ እያለች፥ መቅመቆ ማሸቱን ምታት መተት,የምጣዱ እያለ፣ የእንቅቡ ተንጣጣ ቅቤ ይፍስስ፣ ከገንፎ አይተርፍ,የትም አይሄድ ቅናት ያደርሳል፣ ከሞት,ቀናተኛ ከሁሉ ጠበኛ ቅናት ጥናት፣ አይገናኝም ከእናት ካባት,የሚቀና ሰው ከቤተሰቡ ጋርም እይኳኳንም ቅን በቅን ከማገልገል፣ ፊት ለፊት ማውደልደል,ከሠራተኛው ይልቅ እውደልዳዮች ይጠቀማሉ ቅንቡርስ የት ትሔዳለህ? መተማ፣ ትደርሳለህ ልብማ,የሚያስበውና የሚደርስበት ይለያያል ቅንነት፣ ለነፍስ መድኃኒት,እግዚአብሔር የሚወደው ነገር ነው ቅዝምዝም ሲወረወር፣ ጎንበስ ብለህ እሳልፈው,የሚመጣብህን ነገር በትዕግስት እና በብልሃት እሳልፈው ቅዝምዝም ወዲያ ፍየል ወዲያ,የማይገናኝ ሐሳብ ቅዥት ተፈርቶ፣ ሳይተኛ አይታደርም,እሳሳታለሁ ብለሀ ሥራህን አትተወውም ቅጡም የምንኩስና ነው,የሚሆን ይመስላል ግነ አይሳካም ቆሉ ለዘር፣ እንዶድ ለድግር,ለተባለው ዓላማ ሊውል የማይችል የማይሆን ቆሉን ቢቆረጥሙት እንጂ፣ ቢያሹት አያልቅ,ማንኛውም ሥራ በስልት ሲሠራ ይቀላል ቆማጣ ቤት፣ አንድ ጣት ብርቅ ነው,ድሃ ቤት ጎመን የተቀቀለ እለት ጭፈራ ነው ቆማጣ ብለው ያው ቁምጥና ነው፣ ሴላ ምን ይመጣል አለ,አካፋን አካፋ እንጂ ሌላ ምን ይሉታል ቆዳ ሲወደድ፣ በሬህን እረድ,ለማንኛውም ወቅቱን ማወቅ ተገዢ ነው ቆጥሮ የማይስጥ ሌባ፣ ቆጥሮ የማይቀበል ሌባ,መተማመን ሊመጣ የሚችለው ግልጽነት ሲኖር ነው ቋንጧና ባለሟል ላያር አይቀርም,እስው ቤት እየሠራ የሚያበሳጭ ነገር የማይገጥመው የለም በሁለት በትር አይማቱ፣ በሁለት ዳኛ አይሟገቱ,ሁሉም ነገር ሥርዓት አለው በለምለም (በለለለስ) ምሳሴ፣ ኮሸሽላ በላሁ አለች አህያ,በዘዴ የምፈልገውን አደረኩ በሉት አለቀ ፈጩት ደቀቀ,ባዶ ቀረ አለቀ በላይ በላዩ ያጎርሳታል፣ የበላችው ያስገሳታል,በሳይ በላዩ የሆነ ነገር ጥቅም የለውም በል በል ይላሉ፣ ሲፈርዱ፣ ጣል ጣል ይሳሉ፣ ሲያርዱ,ያዋከቡት ነገር በልብ አምኖ፣ በእፍ መንኖ,በልብ የታስበውና በአፍ የሚነገረው ሲለያይ በልተው ከጨረሱ፣ ከመኝታ ይነሱ,ጅብ ከሔደ ውሻ ጮኸ በልተው ካልጠጡ እረር፣ ወልደው ካሳኩ አነር,በሥርዓት ያላሳደጉት ልጅ ችግር ይፈጥራል በልቶ መጠጥ ያጣ፣ ተበድሎ ፍርድ አጣ,የፍትሕ መታጣት በልቶ እንዳንበሳ፣ ተኝቶ እንደሬሳ,ሐሳብ የሌለው፣ የተሟላለት በልቶ የማይመርቅ፣ ገብቶ ወጥቶ የማይጠይቅ,ለተደረገለት ውለታ የማይውል ጥሩ እይደለም በልቶ የማይበርዶው፣ የስው ነገር የማይከብደው፣ አንድ ነው,ምንም ቢሆን ሰው ይሉኝታ እለው በልቶ የከሳ፣ የነገሩትን የረሳ,ዝንጉ ለው አይረባም በልቼ እንደአንበሳ፣ ተኝቼ እንደሬሳ,ሁሉ ነገር የተሟላልኝ በል ያለው የበሳላው፣ ተው ያለው የአተተው,ሁሉም አንደየራሱ ሁኔታ የሚፈጸም በልጅ ቆዳ፣ የተቀበረ የለም,መጨነቅ የለብኝም በልጅነት ወደ ገዳም፣ በእርጅና ወደ ዓለም,የተገላቢጦሽ ሥራ በልጅነት ያልተወለደ ልጅ፣ በአባቱ ተዝካር ፈኛ ይለምናል,እንኳን ሊጦር ይጦራል በልጅ አመካኝቶ፣ ይስሳል አንጎቶ,በሰበቡ መምሬ ተሳቡ በሐምሌ በነሐሴ፣ ቀረችልኝ ነፍሴ,የችግሬ ጊዜ አለፈ በሐምሌ ወጨፎ፣ በለኔ አርከፍክፎ,ቀስ በቀለ ሁኔታው እየከበደ መሔድ በሐምሌ ጤፍ ይዘሩ፣ ቤት ይሠሩ,ቆቅ ወዲህ ቅዝምዝም ወዲያ በመልካም፣ አንገት እንቅርት,በጥሩ ነገር ላይ እንከን በመረጡት ዳኛ ቢረቱ፣ በቆረጡት በትር፣ ቢመቱት በማን ያጉተመትም,በመጀመሪያ መጠንቀቅ ነው እንጂ በራለህ ጥፋት ማዘንአይቻልም በመለለው ይናገራል፣ ከበላው ይበሳል,እንደልቡ ነው የሚያድረው በመስታወት ቤት የሚኖሩ አይወራወሩ,በቀላሉ ሊበላሽ የሚችልን ነገር በእንከብካቤ መያዝ በመስከረም የሚያብድ፣ ስለኔ ቡሪውን ከፍ ከፍ ያደርጋል,ከሁኔታው ያስታውቃል በመሸታ የተገዛ ጦር፣ ቢወረውሩት ከድፍድፍ,አይትማመኑበትም በመከሩት ምክር፣ በሸመቁት ጦር,ተንኮል ሠሪውን ያጠፋዋል በመዘንከው ማሜዛን፣ በሰፈርከው ላዳን,አንተው ባነስኸው አንተው ተጎዳህ በመጀመረያ የመቀመጫዬን፣ አለች ዝንጀሮ,መጀመሪያ እራሌን በመጠቃቀም የቆመ ፍቅር፣ አይውል አያድር,ጥቅም ሲቀር መፍረሱ አይቀርም በሚያዚያ ጎመን የዘራ፣ ክረምቱን ሁሉ በላ,ሁሌ ቀደም ብለህ ከተዘጋጀህ አትራብም አትጠቃም በማር ሳይ ወተት፣ ሲረባም ቢለባም,አይገኝም እንጂ ከተገኘ መልካም በማታየው፣ እጅህን አታድርስው,ራስህን ጠብቅ በማን ላይ ተቀምጠሽ፣ እግዜርን ታሚያለሽ,አኔ እየረዳሁህ እኔኑ ታማለህ በማያድሩበት ቤት፣ አያመሻሹበት,በጊዜ ተነስተው ይሂዱ በምን በላህ በሳማ፣ ባይፈጅህማ,ካልፈጀህ፣ ካልጎዳህ እሉማ ጥሩ ነበር በምን ተነሳ በጣቁሳ ምን በጣቁሳ በዳጉሳ,አንዱን አይተህ ከአንዱ ተማር በምንቸት ጠላ ታፈላሳ፣ ከጎረቤት ትጣላ,የማይጠቅምን ተግባር አትፈጽም በምን የተነሣ፥ ይህ ሁሉ ጠባሳ,አንዱን አይተህ ከአንዱ ተማር በምድር መጠቅጥቅ፣ በስማይ መጠየቅ,ምድር ላይ የሠራኸው ግፍ በሰማይ ያስጠይቅሃል በምድር ዓለም፣ አለገንበብ የለም,ገንዘብ ካለ በሰማይ መንገድ አለ በምድር እይቀር ብድር,እንደሥራህ ብድርህ ይከፈልሃል በምድር ድንበር፥ በሴት ከንፈር,ዋናው መከለያና መታፈሪያ ነው በምግባሩ እይታወቅ ማማሩ,በሚሠራው ሥራ ውበቱ አይታወቅም በምጥ በጣሽ! በአንግዴ ልጅ አልጣሽ,ምንግዜም ከኔ ጋር ሁኝ በሞኝ ክምር፣ ዝንጀሮ ልጅዋን ትዳር,ብልጦቹ በሞኝ ንብረት ይጠቀማሉ በሞኝ ክንድ የዘንዶ፣ ጉድጓድ ይለኩበት,አራሱ የማይደፍረውን ነገር ሌላ ሰውን አደፋፍረው ጎል ማበገባት በረጅም ጦር ባይወጉበት፣ ያስፈራሩበት,ወንድምና ወጥ ማስፈራሪያ ነው በራቸውን ክፍተው፣ ሰውን ሌባ ይላሉ,በጨለማ እየሄዱ ጅብን ነገረኛ ያደርጋሉ በሬ ሆይ! ሣሩን አየህና፣ ገደሉን ሳታይ,እበላ ብዬ ተበላሁ፣ ምነው ሳልበላ በቀረሁ በሬ ሲያረጅ፣ ከጥጃ ጋር ይውላል,ያለቦታው ወደኋላ መጓተት በሬ በመቶ፣ ያውስ የት ተገኝቶ ምድር በዶሮ፣ ያውስ ማን ገብሮ,በሌለ ነገር ላይ ትኩረት ማድረግ በሬ በጭብጦ ተዝ ቢለው፣ ያላቦካ ከወዴት ያገኛል አለው,ቅድሚያ ዝግጅት ያላደረገ ይቸገራል በሬ ተንሾካሽኮ ቀንበር፥ ገበሬ ተቸካችኮ ከድንበር,በድንበር አካባቢ ችግርና ንትርክ አይቀርም በሬና ሌት፣ ካገርህ መሬት,ሁሉ ነገር በአገር ያምራል በሬና በሬ መከሩ፣ ቀንበር ሰበሩ,ራስን ከችግር ለማውጣት የሚደረግ ጥረት በሬ አርዶ በበለት፣ ከብት አርብቶ በበረት,ሁሉንም በሥርዓቱ ሲይዙት ይጠቅማል በሬ እንኳ ሰወጉ፣ በፈረስ ያጓራል,ዘመድ ከወገኑ ይደግፋል በሬ ከአንጀቱ እንጂ፣ በአንገቱ አያበብም,ሰው ጠግቦ ከበላ ሥራውን በሚገባ ይሠራል በሬ ከጎለበተ፣ አሽከር ሰነበተ,የሚጠቀምበትን መሣሪያ በአግባቡ የያዘ ይመሰገናል በሬ ካራጁ፣ ይውላል,ስው ሳያውቀው ከባላንጣው ይውላል በሬ ወደአገሩ፣ ይስባል,ለሀገርህ መቆርቆርህ አይቀርም በሬዎች ተረት ለመዱ! ዝም ብለው እንዳይጠመዱ,ወሬ ብቻ ሆነ ሥራውን ትተውት በሬ ያርሳል፣ ምርቱን አህያ ያፍሳል,በጨው ደንደስ በርበሬ ተወደሰ በሬ ግዙ ግዙ፣ አንድ አሞሌ ላይገዙ,መካሪው ብዙ ደጋፊ ግን የለም በርቄ አሞታለሁ ታንቄ,ሥራ ላይ ሊውል የማይችል በርበሬ በገዛ አጁ ገብቶ ይፋጃል,በገዛ እጁ ነገር ፈልጎ ችግር ገጠመው በርበሬ ታልፈጀ፣ ጠበቃ ታረጀ,በሚፈለግበት አገልግሎት ላይ ሊውል አይችልም በርበሬና ሚጥሚጣ፣ ሥጋና ቋንጣ,ሁሉም ለየቅል ነው በርበሬ አይሆን ፅጣን፣ ነገር አይሆን ሥልጣን,ያለቦታው ያደረጉት ነገር ጠቀሜታ የለውም በርቦ ያበድራል፣ በቁና ያስከፍላል,ስግብግብ ነው በርኖበ ሳይገዙ ካባ,መነሻ ነንር ሳይዙ የተሻለ ነገር መመኘት ገረድ የቤት ሞረድ,ገረድ የቤቱን ፅቃ ትፈጀዋለች ገራገሩን ተጫውቶ ይኖራል ተስማምቶ,ላይ ላዩን አየተጫወቱ መኖር ያስማማል ገርነት የእግዜር ቸርነት,ገርነትን አግዚአብሔር የሚወደው ባሕርይ ነው ገርነት ያገባል ገነት,ገርነት መንግሥተሰማያት ያስወርሳል ገርና ልል ሙዳይና አገልግልግ,በሁለቱ መካከል ብዙ ልዩነት የለም ገርን ልጅ አናቱም አትወደው,ማንም ቢሆን ለመብቱ መታገል አለበት ገርገሩን ተጫውቶ ይበሏል ተስማምቶ,"ወደውስጥ ሳይገቡ ላይ ላዩን በመጨዋወት በስምምነት መኖር ይቻላል" ገበሬና ወላድ አንድ አያጣም,ወላድ ከብዙ ልጆች አንድ ሁነኛ ልጅ አታጣም ገበሬ አቆቁጣጥረኝ ወታደር አወራውረኝ,ገበሬ ቤተዘመዱን ሲሸኝ ከየአህል ዓይነቱ ቆጣጥሮ በመስጠት ነው ገበሬ አክባሪውን ባለጌ መካሪውን ይጠላል,ገበሬ የሚያከብረውን ይጠላል ገበያ ቢመቻት ልጂን ሸጠቻት,መሸጥ የለመደ አናቱን ያስማማል ገበያ ነሽ ብለው ይሻሻጡብሻል,አንድ ፍሬ ነሽ ግን አንደትልቅ ተቆጠርሽ /ንቀትን ስመግስጽ/ ገበያ አንደሰስጠህ አንጂ አናትህ አንደላከችህ አይሆንም,ገበያ ሲሰጥ በርካሽ ይሸመታል ገበያ ከደራ ነጋዴም አይፈራ,ገበያው ሞቅ ካለ ነጋዴ ዋጋውን ለቀቅ ያደርጋል ገበያ የሚሰጥህን አናት አትለጥም,ከንግድ ብዙ ጥቅም ይገኛል ገበጣ ላዋቂ ወሬ ለጠያቂ,ካልጠየክ ልታውቅ አትችልም ገበጣ ላዋቂ ወሬ ለጠያቂ ዋዛ ፈዛዛ ከሣቂ,ዋዛ ፈዛዛ የሚያበዛ ሰው ከችግር ላይ ይወድቃል ገቢ በአናት ልጅ ትገቢ,ነገረኛ ሰው አናትና ልጅን ከማጋደል አይመለም ገቢውን ባለቤት ያውቃል,ከባለቤቱ ያወቀ ቡዳ ነው ገቢ ያፈርሳል ቀዳዳ ያፈሳል,ነገረኛ ሰው ሰውና ሰው ያጣላል ገባር ያህያ ግንባር,ገባር ለባለመሬቱ አንደአህያ ግለጋሎት ይሰጣል ገባ ወጣ ነገር ያመጣ,ገባ ወጣ ማለት አንዳች ጣጣ ያመጣል ገብርኤል ያየው ሚስጥር,በታቦት ስም የተደረገ ነገር ምስጢርነቱ ከባድ ነው ገብስ ሲበስል አባቱን ይመስል,ያልዘሩት አይበቅል ገብስና ሽንኩርት ቂጡ ሲለብስ ነው,የተፈለገው ነገር በተፈለገው መጠንና ሁኔታ ካልተገኘ አያስደስትም ገብስና ገብስ አብሮ ይነፍስ,ብጤ ከቢጤው ነው ገናም በሙከቱ ሑዳዴ በአልበቱ ይታወቃል,ሁሉም አንደጊዜውና እንደወቅቱ ይከናወናል ገናና ጥምቀት አኩል ዓውደ ዓመት,ገናና ጥምቀትም ያው ዓመት በዓል ናቸው ገንዘቡ የሰው ቢሆን አዳዩ የኔ ይሁን,አዳዩ የኔ ወገን ከሆነ ማግኘቴ አይቀርም ገንዘቤ አትውጪ ከቤት ታጣይኛለሽ ከጐረቤት,ገንዘብ ለማይመልስ ተው አታበድር ያቀያይማል ገንዘብ ለዕዳ ሙግት ለባዳ,ቋዉቋ ሙግት አለብኝ ከማለት ሥራ አለኝ ማለት ይበልጣል ገንዘብ ማግኘቱ ይቀላል ከማከማቸቱ,ገንዘብ በአግባባቡ ማውጣት እና የተረፈውን ባግባቡ መጠቀም ይከብዳል ገንዘብ በልጅነት ማን ሰብስቦሽ በአርጅና ማን አግኝቶሽ,ገንዘብ የሚገኝ በሃያ ዓመት ልብ የሚገኘው በአርባ ዓመት ገንዘብ ከጅ ከወጣ ያመጣል ጣጣ,ገንዘብ አንዴ ከእጅ ከወጣ ለመመለስ አስቸጋሪ ነው ገንዘብ ከጅ ዘመድ ከደጅ,ገንዘብ ካለህ ዘመድህ ብዙ ነው ገንዘብ ካለ በሰማይ መንገድ አለ,ሀብት ያስው የፈለገውን ማድረግ ይችላል ገንዘብ የልብ ሥር ነው አጥፊውም ሰው ነው,ገንዘብ ሰውን ያጠፋል ፈላ ገነፈለ ተሞላ ጐደለ,ከተጠቀሙበት የማያልቅ ነገር የለም ፈረለኛ ሲሮጥ እግረኛ ምን አቆመው,በማይመለከተው ነገር ምን አገባው ፈረለኛ የወለደው እግረኛ አይመልሰውም,ሁሉም ነገር ያለቦታው ተፈጻሚነት አይኖረውም ፈረሉም ይኸው ሜዳውም ይኸው,ከቻልከ አድርገው ተፈቅዶልፃል ፈረሰ ሲያጠብቅ ልጓም አይለቅ,እደገኛ ሁኔታ እንኳን ቢያጋጥምህ ከቁም ነገር ሳይ እንዳታፈነግጥ ፈረሰ በራሪ በቅሎ ሰጋሪ,ሁሉም እንደየፍጥረቱ ነው የሚያገለግለው ፈረሰ ቢያነክሰ አህያ ታጉዝ,ይታደሉታል እንጂ አይታገሉትም ፈረሰ ቢጠፋው ኮርቻ ገልቦ አየ,የማይደረግ ነገር አረገ ፈረሰ ዐውቃለሁ ስገታ እወድቃለሁ,ላታውቅ ዐውቃስሁ ማለት ጥሩ አይደለም ፈረስ ያደርላል እንጂ አይዋጋም ሽክ,ለሚፈሰገው ነገር እርዳታ ይሰጣል እንጂ ሙሉ በሙሉ አይረዳም ፈረሰ ጥሎ ይደነግጣል በቅሎ ጥሎ ይግጣል,"የጨዋ ልጅ ላደረገው ስሕተተ ይጻጸታል የባለጌ ልጅ የባለ ነገር ይፈጽማል" ፈሩ ፈሩ ማጀት እሩ,እስከመቼ ተፈርቶ ይኖራል ፈሪ ለእናቱ ይገባል,ፈሪ ከእደጋ እራሉን ይጠብቃል ፈሪ ለእናቱ ጀግና ለጀግንነቱ,ፈሪ ከእደጋ አራሉን ይጠብቃል ፈሪ በገዛ ጠቡ ገላጋይ ይሆናል,ከተጣላ እደጋ ላይ ስለሚወድቅ ራሉን ያረጋጋል ፈሪና ንፉግ እያደረ ይቆጨዋል,ማንኛውም ሰው ኋላ ላይ ሲያውቀው ይጸጸታል ፈሪን በውኃ ውስጥ ያልበዋል,ከመጠን በላይ ሰለሰሚፈራ ፈሪ አንዳይሉኝ አንድ ገደልሁ ጀግናም እንዳይሉኝ አልደገምሁ,የማይችሉትን ነገር ለመሞክር አያድርጉ አለመቻል አያዋርድም ፈሪ ካልጋ ላይ ይወድቃል,"ፈሪ በሆነው ባልሆነው ነገር እንደባነነ ነው የሚኖረው ፈሪ የናቱ ልጅ ነው" ፈስቶ ቂጥ መያዝ,ስሕተት ሠርቶ ያልሠሩ መምሰል ፈስ ያለበት ቂጥ ዝላይ አይችልም,ቁስል ያለበት ውሻ አንደልቡ አይጮህም ፈትል ሲረዳዳ አንበሳ ያስራል,ከተባበሩ ከባድ ሥራ መሥራት ይቻላል ፈዛዛ አያንቀላፋ ይገባ ፈፋ,መፍዘዝ ለአደጋ ያጋልጣል ፈጅቶ ከሚያጠግበኝ አስቲበርድ ይራበኝ,ከፍትፍቱ ፊቱ ፈጣሪን ያህል ጌታ ርስትን ያህል ቦታ,ፈጣሪን የሚያህለው የለም ፈጥኖ መስጠት ኋላ ለመጸጸት,የቸኮለች አፍሳ ለቀመች ፈጭታ የነበረች ላመልማሎ ኮራች,ከባዱን ሥራ ሠርታ ለቀላሉ ኮራች ፉት ቢሉት ጭልጥ,ለቅምሻ እንኳን የማይሆን ፊተኛው ወዳጅህን በምን ቀበርከው? በሻሽ ምነው? ኋለኛው አንዳይሸሽ,ሁሉን ነገር በዘዴ ማከናወን ጥሩ ነው ፊት ከወጣ ጆሮ ኋላ የበቀለ ቀንድ በሰጠ,ከበፊቱ የኋለኛው ተሻለ ፊት የተናገረን ሰው ይጠላዋል ፊት የደረስን ወፍ ይብላው,ቀደም ቀደም ማለት ጥሩ አይደለም የደመና ውኃ ጥምና የእናት በደል አይታወቅም,አናትን ትበድላለች ብሎ ማንም አያስብም የደበሎ ተባይ የዳኛ አባይ ቢገልጡት አይታይ,በደበሎ ውስጥ ያለተባይ አንዲህ በቀላሉ ሊታይ ወይም ሊገኝ አይችልም የደባ ገበያ በሬው ባሥር ቆዳው በሃያ,ተንኮስሰኛ የማይሆነውን አንደሚሆን አድርጐ ይናገራል የደጃዝማችን ሚስት አይቼ ሚስቴን ጠላሁ,የማያገኙትን መመኘት ከንቱ ልፋት የተደገመ ተረገመ,ሁለቴ መታለል አርግማን ያስከትላል የደግ ጊዜ ባዕድ የክፉ ጊዜ ዘመድ,ዘመድ ለችግርህ ይደርስልሃል የደፉት ሬሳ የጠበሱት ዓሣ,ለሚቀጥለው ተግባር በዝግጅት ሳይ ያለ ማሰት ነው የዳቦ ልብ ልቡን የዳገት ጥግ -ጥጉን,ለጥቅም መሯሯጥ ለሥራ ጊዜ መሸሽ ጥሩ አይደለም የዳገት በረዶ የቆላ ዘንዶ,በጣም አስከፊ የሆነ ችግር የዳጉሳ እንጀራ በትኩሉ የባዕድ ፍቅር በአዲስ,ፍቅርና ቡና በትኩሱ ይጣፍጣል የድሃ ፃብቱ አንቅልፉ,ድሃ የሚጨነቅስት ሀብት ሰለሌለው እንቅልፉን ሲለጥጥ ያድራል የድሃ መድኃኒቱ የድንገቱ,ድዛ ሲያመው የሚያኝከው ድንገተኛ የተባሰው ሥር ነው የድፃ ማጀት ቃጢ ማር ሰማስቀመጥ አይችልም,አይጥ ቤት ብቅል የድፃ ቁም ነገሩ ገብስ አስክ አስሩ,"ድሃ ገብስ በመብላቱ አንደጠላም አድርጐ በመጠጣቱ ጥቅም ጥንካሬ አግኝቶበታል" የድሃ ነገር ማንገቻ የሰው,የድፃ ነገር የተሟላ አይደለም የድሃ ጉልበት በገቢያ ያልቃል,ድዛ ሲወጣ ሲወርድ ጉልበቱን ያባክናል የድሃ ግድርድር ሀብታም ይጋብዛል,አንግዳ ሲያፍር ባለቤቱን ይጋብዛል የድሃ ጠላ ጧት አልፈላ ማታ አተሳ,መጠት ያነስ ወይም በቂ ያልሆነ ነገር ፅወቅ ያለው ባርባ ቀኑ ዐትወቅ ያለው ባርባ ዘመኑ,የታደለው ገና በጠዋቱ የተሟላ ነገር ያጋጥመዋል ዕውር ምን ዓይቶ ደንቆሮ ምን ሰምቶ,ማያም መሰሚያም በሌለበት በዚህ ጉዳይ ላይ መነጋገር ኣይቻልም ዕውር ምን ይሻል ብርሃን፤ በሽተኛ ምን ይሻል መዳን,የሁሉም ፍላጐት የሚሟላው እንደየችግሩ መፍትሔ ሲገኝ ነው ፅውር ሲወበራ ከመሪው ይጣላ,የኋላውን አለማሰብ ፅውር በዘንጉ ነጋዴ በወርቁ,ሁሉም ባለው ኃይልና ባለው መሣሪያ ይጠቀማል ፅውር ቢጠግብ ዘንጉን ይወርውር,ዕውር ሲቀናጣ ዘንጉን ወርውሮ ፍለጋ ይሔዳል ፅውር አያፍር ፈሪ አይደፍር,የሌለውን ከሌለበት ቦታ መፈለግ ዕውርን ዕውር አይመራውም,ፅውር ከመሪው ሞኝ ከመካሪው አይጣላም ፅው ቀት ኃይል ነው ለላም ጤና ነው,ዕውቀት ለሁሉ ነገር መከፈቻ ቁልፍ ነው ፅውቀትና ፍጥረት አንድ ቀን ነው,ለመተዋወቅና ለመወዳጀት ረጅም ጊዜ አይወስድምዕ ዕውቀት ያኮራል ሥራ ያስከብራል,"ዕፅውቀት ያለው በፅውቀቱ ሥራም ያለው በሥራው ክብር ያገኛል ዕዳ ለቤት ምለጢር ለጐረቤት" ዕዳው ዶሮ መጋቢ ያው ዶሮ,ዞሮ ዞሮ አዚያው ፅድለ ቢስ ሲዳር ውኃ ይሞላል በጥር,ነገሩ ሁሉ ተው እንዳይሆን ነው ፅድለ ቢሰ አሞራ አንበጣ ሲመጣ ዓይኑ ይጠፋል,አትብላ የተመኘኸውን አታሟላ ያለው ፅድላም አሞሌ በቅሎ ይለውጣል,በትንሹ ትልቅ ነገር ላይ ወይም ውጤት ላይ መድረስ ፅድል ተርታውን ዕጣ ፈንታውን,ዕድል በየተራ ለሁሉም የምትደርስ ናት ፅድል ፈንታ ጥዋ ተርታ,ሁሉም የራሱን ዕድል ፈንታ በየተራ ያገኛል ፅድሜ ለንስሐ ዘመን ለፍለሐ,ፅድሜ ካለ ለደስታም ሆነ ለንለሐ ይበጃል ዕድሜና መለተዋት አይጠገብም,ማንም ለው ዕድሜ በቃኝ የሚል የለም የለይጣን ክፋቱ ያለመታየቱ,የሚደርሰብንን ችግሮች አስቀድመን ለማወቅ አንችልም የሰይጣን ገንዘብ የተበደረ ሳይበላው ተቀበረ,ከክፉ ሰው ጋር የተዋዋለ መከራው ብዙ ነው የሰጠኸኝ ሸማ ከደጅህ ተቀማ,ነጣቂዎች አዚሁ ደጅህ ሳይ የሰጡኸኝን ሸማ ነጠቁኝ የስጡህን ተቀበል ያደረጉልህን ቸል አትበል,ውለታን አትዘንጋ የሰጠህን አትንላ ያደረጉልህን አትርላ,ምንጊዜም የሰው ውለታ ሊዘነጋ አይገባም የሰጡን ይሰጧል የገዙን ይነዷል,አንድ ሰው በራሱ ሃብት አዛዥ አሱ ራሱ ነው የሳተ ይምከርህ የዋለ ይንገርህ,ልምድ ካሰው ተማር