Proverb ሀ ሁ፥ ባልኩ ተለከፍኩ። ሀ ባሉ፥ ተዝካር በሉ። ሀ ባሉ፥ ደሞዝ በሉ። ሀሁ ሳይሉ ጽሕፈት፤ ውል ሳይዙ ሙግት። ሀሜተኛ ነው ከዳተኛ። ሀሜተኛ ያፍራል፤ እውነተኛ ይረታል። ሀሜት አይቀር፥ ከድሀም ቤት። ሀሜትና ጅራት በስተኋላ ነው። (በስተኋላ ~ ከበስተኋላ) ሀምላ ቢያባራ፥ በጋ ይመስላል። ሀምላና ሙሽራ ሳይገለጡ ነው። ሀምላን በብጣሪ፤ ነሀሴን በእንጥርጣሪ። ሀረጉን ሲስቡት ዚፉ ይወዚወዚል። ሀረጉን ሳብ፥ ዚፉ እንዱሳሳብ። ሀረጎ አጠጣሽኝ ዕርጎ። ሀረጎ አጠጣችኝ ዕርጎ። ሀሰተኛ ሲናገር ይታወቃል፤ ሥሡ ሲበላ ይታነቃል። ሀሰተኛ ሲናገር ይታወቃል፤ በሶ ሲበሉት ያንቃል። ሀሰተኛ በቃሉ፤ ስደተኛ በቅሉ። ሀሰተኛ ያወራውን፥ ፈረሰኛ አይመልሰውም። ሀሰተኛን ሲረቱ በወንድሙ(ና) በእኅቱ። ሀሰት ሲናገሩ ውቃቢ ይርቃል። ሀሰት ስለበዚ፥ እውነት ሆነ ዋዚ። ሀሰት ቢናገሩ ውቃቢ ይርቃል። ሀሰት ነገር ክፉ፥ ገሃነም እሳት ትርፉ። ሀሰት አያቀላ፤ እውነት አያደላ። ሀሰት አያድንም፥ መራቆት መልክ አያሳምርም። ሀሰት እያደር ይቀላል፥ እውነት እያደር ይበራል። ሀሰት እያደር ይቀላል፥ እውነትና ውሃ እያደር ይጠራል። ሀሰትና ሥንቅ እያደረ ያልቅ። ሀሳቡ ጥልቅ፤ ነገሩ ጥልቅ። ሀሳብ ከውለታ አይቆጠርም ። ሀሳብ ከፊት አይፈታ፤ ሙት አይመታ ። ሀሳብ የለሽ፥ ወጧ ጣፋጭ ነው። ሀሳብ የላለው ሰው፥ ሽንብራ ነቀላ ሲኼድ፥ ምሳዬን ይላል። ሀሳብ ያገናኛል፤ ፍርሀት ያሸኛኛል ። ሀሳብና መንገድ ማለቂያ የለውም ። ሀሳብህን ጨርቅ ያድርገው። ሀብታም ለሀብታም ይጠቃቀሱ፤ ድሀ ለድሀ ይለቃቀሱ። ሀብታም ለሰጠ፥ የድሀ ሙርጥ አበጠ። ሀብታም ለሰጠው፥ ድሀ ይንቀጠቀጣል። ሀብታም ሉሰጥ፥ የድሀ ሙርጥ አበጠ። ሀብታም ሉሰጥ፥ የድሀው ሙርጥ ያብጣል። ሀብታም ሉሰጥ፥ ድሀ ምርጥ ያወጣል። ሀብታም ሉደኸይ፥ ሲል ጠላት ያበዚል። ሀብታም ሲወድቅ፥ ከሰገነት ድሀ ሲወድቅ ከመሬት። ሀብታም በከብቱ፤ ድሀ በጉልበቱ። ሀብታም በወርቁ፤ ድሀ በጨርቁ። ሀብታም በገን዗ቡ ይኮራል፤ ድሀ በጥበቡ ይከበራል። ሀብታም በገን዗ቡ፤ ድሀ በጥበቡ እርስ በርስ ይቃረቡ። ሀብታም ቢሰጥ፥ አበደረ እንጂ አልሰጠም። ሀብታም ቢያብር፥ ድህነትን ያጠፋል። ሀብታም ነው መባል ያኮራል፤ ድሀ ነው መባል ያሳፍራል። ሀብታም እንደሚበላለት፤ ድሀ እንደሚከናወንለት። ሀብታም ያለ ድሀ አይኮራም፥ ድሀ ያለ ሀብታም አይበላም። ሀብታም ገን዗ቡን ያስባል፤ ድሀ ቀኑን ይቆጥራል። ሀብታምና ሀብታም፥ አንተ ለእኔ፥ አንተ ለእኔ ይባባላሉ ምን ነው? ሀብታችኹ ባለበት ልባችኹም ይገኛል። ሀብታችን በውርስ፥ ክብራችን በአዋጅ (ተገፍፎ)። ሀብት እና ዕውቀት አይገኙ(ም) አንድነት። (አይገኙ(ም) ~ አይገኝ(ም)) ሀብት፥ የጠዋት ጤዚ ነው። ሀብትና ዕውቀት አይገኝም በአንድነት። ሀኪም ሲበዚ በሽተኛው ይሞታል። (በሽተኛው ~ በሽተኛ) ሀኪም የያ዗ው ነፍስ፥ ባያድር ይውላል። ሀኪሞች እስኪመካከሩ በሽተኛው ይሞታል። ኀ዗ን ለሰነፎች፤ ደስታ ለብልኆች። ሀገር ሲያረጅ እምቧጮ ያበቅላል። ሀገር ያለ ዳኛ፤ ትብትብ ያለመጫኛ። ሀገርን ያለ አንድ ቸር ሰው አይተዋትም። ኀጢአተኛ ኀጢአቱ ያሳድደዋል። ኀጢአት ለሠሪው፤ ምሕረት ለአክባሪው። ኀጢአት ሲደጋግሙት ጽድቅ ይመስላል። ሃላ ከመዙ፤ ምቀኛህ ብዙ። ሃይማኖት የላለው ሰው፤ ል጑ም የላለው ፈረስ። ሃይማኖት ያለ ፍቅር፤ ጸልት ያለ ግብር። ሆቴል ቢያብር ገን዗ብ ያስገኛል። ሆኖ ከመገኘት፥ መስል መታየት። ሆደ ሰፊ፤ ነገር አሳላፊ። ሆደ ሰፊ፥ ይሻላል ከአኩራፊ። ሆደ ሲሞላ፥ ፍቅሩ ላላ። ሆደ ሲሞላ፥ ፍቅሩ ላላ ፤ ሆደ ሲጎድል ሰው ያጋድል። ሆደ ናረት፤ ሙያው ከጅረት። ሆደ ወድድ፥ አፉ ክድ፤ ክፉ ለምድ። ሆደ ፈሪ፥ እግሩ ዳተኛ፤ አዳም ሲዋጋ፥ እርሱ ይተኛ። ሆደን የወደደ፥ ማዕረጉን የጠላ። (የጠላ ~ ይጠላል) ሆደን ያለ፥ ሆደን ተወጋ። ሆዳ ሆዳ የሚለውን ጌታ ያየዋል፤ አይኔ አይኔ የሚለውን ሰው ያየዋል። ሆዳ በጀርባዬ ቢሆን፥ ገፍቶ ገደል በጣለኝ። ሆዳ፥ ኑር በዳ። ሆዳ፥ አታጣላኝ ከ዗መዳ። ሆዳ ከሞላ፤ ደረቴ ከቀላ። ሆዳ ይሙላ፤ ደረቴ ይቅላ። ሆዳም ሰው ዕንብርት የለውም። ሆዳም (ሰው) ፍቅር አያውቅም። ሆዳም ቢሸከም፥ የበላ ይመስለዋል። ሆዳም ቢፈተፍት፥ የበላ ይመስለዋል። (የበላ ~ የጠገበ) ሆዳን በልቶኝ ጎኔን ቢያኩኝ አይገባኝ። ሆድ ሆደን፥ የምትል ወፍ አለች፥ ምን አለች? ሆድ ለማታ በልቶ፥ ለጠዋት። ሆድ ለባሰው፥ ማጭድ አታውሰው። (ማጭድ ~ ቢላዋ) ሆድ ለተባባሰው፥ ማጭድ አታውሰው። ሆድ ሲሞላ፥ ራስ ባድ ይቀራል። ሆድ ሲሞላ፥ ፍቅሩ ላላ፤ ሆድ ሲጎድል፥ ሰው ያጋድል። ሆድ ሲያር፤ ጥርስ ይሥቃል። ሆድ ሲያውቅ፤ ድሮ ማታ። ሆድ ሲጎድል፥ ሰው ያጋድል። ሆድ በላኹ አይልም። ሆድ ቢሸከም፥ የበላ ይመስለዋል። ሆድ ባድ(ን) ይጠላል። (ባድ ~ ራብ) ሆድ አየኹ አይልም። ሆድ እንዳሳዩት ነው። ሆድ ከአልሞላ፥ ጥርስ መቼ ይሥቃል። ሆድ ከአገር ይሰፋል። ሆድ ከጀርባ ይቀርባል። ሆድ ወድ፥ አፍ ክድ፥ ክፉ ለምድ። ሆድ ዕዳ፥ ያስበላል ጎዳዳ። ሆድ ከሐዳድ ይሰፋል። ሆድ ያባውን ብቅል ያወጣዋል። ሆድ ይርበዋል፥ ቆዳ ይበርደዋል ክረምት። ሆድ ይፍጀው። ሆድ ድንጋይ ልበላ ነው ቢል፥ ጐረሮ በየት አሳልፈህ? አለው። ሆድ ዗መድ ሳይወድ፤ አፍ እህል ሳይለምድ። ሆድ የሸሸገውን ብቅል ያወጣዋል። ሆድ፥ የእኔ ነው ሲሉት፥ ቁርጠት ሆኖ ይገድላል። ሆድ ያበላውን ያመሰገናል። ሆድና ግንባር አይሸሸጉም። (አይሸሸጉም ~ አይሸሸግም) ሆድን በጎመን ቢደልሉት፥ ጉልበት (በ)ዳገት ይለግማል። ሆድህና ልጅህ አይጣላህ። ሆድህና ልጅህ አይጥሉህ። ሆድህን ጎመን ሙላው፥ ጀርባህን ለጠላት አታሳየው። (አታሳየው ~ አታሳይ) ለሀብት መትጋት፥ ሰውነትን ያከሳል፤ ገን዗ብን ማሰብ፥ እንቅልፍ ይነሣል። ለኀጥአን የወረደ፥ ለጻድቃን ይተርፋል። ለሆዳም ሰው ማብላት፤ ውቅያኖስን ለመደልደል መቃጣት። ለሆዳ ጠግቤ፤ ለልብሴ አንግቤ። (ለልብሴ ~ በልብሴ) ለሆድ ቁርጠት ብላበት፤ ለራስ ምታት ጩህበት። ለሆዳም በሬ ገለባ ያዝለታል። (ገለባ ~ ጭድ) ለሆዳም በቅል ጭድ ያዝለታል። ለላላ የሚመክር ለራሱ አያውቅም። ለላባ ቅላት ልብሱ ነው። ለላሙ መንጃ፤ ለሸማው መቀደጃ። (መቀደጃ ~ መከንጃ) ለላም ቀንዶ አይከብዳትም። ለላም ከጥጃዋና ከአላቢዋ፥ ማን ይቀርባታል። ለላም ከጥጃዋና ከአቢላሟ፥ ማን ይቀርባታል። ለላም፥ የሣር ለምለም። ለላም ጥጃዋ፤ ለአህያ ውርንጭላዋ። ለላለው፥ ምን ትለው? ለልደት ያልሆነ ቀሚስ ይበጣጠስ። ለልጅ ሲሉ ይበሉ፤ ለወዳጅ ሲሉ ይጠሉ። (ለወዳጅ ~ ለወገን) ለልጅ አይሥቁለትም፤ ለውሻ አይሮጡለትም። ለልጅ አገዳና ቀራ የለውም። ለልጅ ከሣቁለት፤ ለውሻ ከሮጡለት (ነገር ተበላሸ)። ለልጅ ጨዋታ፤ ለባለጌ ቧልታ። (ቧልታ ~ ቧልት) ለልጅ ጥርስህን፤ ለዝንብ ቁስልህን (አታሳይ)። ለመሀን እምዬ፤ ለአገልጋይ እትዬ ብርቋ ነው። (ለአገልጋይ ~ ለባሪያ) ለመኼድና ለመላወስ፥ አዚዥ ራስ። ለመማር ክፍል መግባት፤ ለመኮረጅ ካሮት መብላት። (ለመኮረጅ ~ ለማለፍ) ለመስማት የፈጠንህ፤ ለመናገር የ዗ገየህ ዅን። ለመሪህ አሣ ምሰል። ለመራመድ ያቃታት እግር፥ ለእርግጫ ተነሣች። ለመስማት የፈጠንህ፤ ለመናገርና ለቁጣ የ዗ገየህ ኹን። ለመሥራት የሚያፍር፥ መብላት አይደፍር(ም)። ለመሥራት ያፈረ፤ ለመብላት ደፈረ። ለመስጠት አለመቸኮል፥ ከሰጡም ወዱያ አለመጸጸት። ለመስጠት አትቸኩል፤ ሰጥተህም አትጸጸት። ለመብላት የጠፋ ቅቤ፥ ስሞት በአፍንጫዬ ይፈስሳል አለ ድሮ። (ይፈስሳል~ይፈሳል) ለመታማት መፍራት። ለመነኰሴ፥ መልካም ለሴ። (:_ ሙቀት ያለው ጢቢኛ፥ ለከት፥ ሙልሙል) ለመነኰሴ፥ መልካም ልላ። ለመከራ የጣፈው፥ ቢነግድ አይተርፈው። ለመከራ ያለው መነኰሴ፥ ዳዊቱን ሸጦ አህያ ይገዚል። ለመጪው ትውልድ፥ አይለጉት ሀኬት። ለመሆኑ ሳይሆን፥ እንዳት ይሆናል? ቢሆን። (ለመሆኑ ~ ለመሆን) ለሙት የለው መብት። ለሚመለከት ለሚያየው፥ ሞት ቅርብ ነው። ለሚስት ያጎርሧል፤ ለተመታ ይክሷል። ለማረም፥ ማን ብልት? ሲሠራው ግን፥ ግድፈት። ለማን ይፈርደ? ለወደደ አይደለም ለወለደ። ለማን ይፈርደ? ለወደደ፥ አይደለም ለወደደ፥ ለወለደ። ለማን ይፈርደ? አይደለም ለወደደ ለወለደ። ለማኝ ቢያብድ፥ ስልቻውን አይጥልም። ለማኝ አያማርጥም፤ ማር አይኮመጥጥም። ለማዕበል ወደብ፤ ለነፋስ ገደብ የለውም። ለማየት የፈለገ፥ አይኑን ይገልጣል። ለማያቅህ ታጠን ብልሀል ሀሰን። ለማያውቁሽ ታጥበሽ ቅረቢ። ለማያውቅ ፎገራ ደሩ ነው። ለማያውቅሽ ታጠኝ። ለማይሞት መድኀኒት አለው። ለማይሥቅ ውሻ ነጭ ጥርስ፤ ለማይገላምጥ ድሮ ቀይ አይን ይሰጠዋል። ለማይችለው አይሰጥ። ለማይሰጥ ሰው፥ ሲቸግረው ስጡኝን ማን አስተማረው? ለማይሰጥ ሰው፥ ስጡኝ ማለትን ማን አስተማረው? ለማይሰጥ ሰው፥ ስጡኝን ማን አስተማረው። ለምላጭ የሰጡት ገላ አያምም። ለምሽት መብራት፤ ለመከራ ጊዛ ብልኀት። ለምሽት መብራት፤ ለሥራ ብልኀት። ለምን ላለው፥ ፈጣሪ አለው፤ ጠጅ ለላለው፥ ውሃ አለው። ለምን ሰርግ ይኼዳል? ሰርግ አለ፥ በቤቱ። ለምን ተክዤ? አምላክን ይዤ። ለምን ያለው ስልቻውን፤ ጫን ያለው ኮርቻውን። (ያለው ~ ላለው) ለምን ያለው ስልቻውን፤ ጫን ያለው ኮርቻውን አያጣም። ለምን ጊዛው ነቀዝሽ። ለምኖ ለማኝ፥ ቆቤን ቀማኝ። ለምክንያት ምክንያት አለው። ለምክንያት ድመት ሞተች። ለሞተ አህያ ሰርድ ቢሰጡት፤ ምን ይጠቅማል? ለሞት የለውም መድኀኒት። ለሞኝ ንገረው፥ ምን ይሰማ ብዬ? ለብልኅ ንገረው ምን ይሳተው ብዬ? ለሞኝ፥ እሳትና ውሃ ቀለብ አይመስለውም። ለሞኝ ከሣቁለት፤ ለቅ዗ን ከሮጡለት። (ለቅ዗ን ~ ለውሻ) ለሞኝ ጉድ጑ድ አያሳዩትም፥ ቤት ነው፥ ብል ይገባበታል። ለሞፈር ቆራጭ፥ ዕርፍ አይታየውም በግላጭ። ለሞኝ፥ ሠኔ በጋው፥ መስከረም ክረምቱ። ለሥልጣን ቢመነኰስ፥ ተያ዗ ሲደንስ። ለሥሡ ፍትፍት አሳይቶ፥ እበት ማጉረሡ። (ማጉረሡ ~ ያጎርሧል) ለሥራ አልደረሱ፤ ከመብሉ አልታገሡ። ለሥራ ወንድ፤ ለሴት ሆድ። ለረጅም መንገድ አትሩጥበት፤ ለረጅም ነገር አትቸኩልበት። ለረጅም ሰው፥ ልብ እና ልብስ ያጥረዋል። ለራሱ ሲቆርስ አያሳንስ። (አያሳንስ ~ አያሳንሱ) ለራሱ አብድ ይሮጣል፥ አትርሳኝ ብል ተከትልታል። ለራሱ አያውቅ ነዳይ፥ ቅቤ ለመነ ለአዋይ። ለራሱ አያውቅ ጠንቋይ፥ መድኀኒቱ ለአዋይ። ለራሱ የማይረባ፥ ለላላም አይረባ። (ለላላም ~ ለሰውም) ለራሱ ጥላ፤ ለእግሩ ከለላ። ለራስ ምታት ጩህበት፤ ለሆድ ቁርጠት ብላበት። ለራስ ሲቆርሱ፥ አያሳንሱ። ለራስ ቢያወሩ፥ ለቅንቅን (ይ዗ሩ)። ለራስ ከበጁ፥ አይታጡ ደጁ። ለራስ ያሉት ማር፤ ለባዕድ ያሉት ሽንኩርት። ለራስ ያሉት ገንፎ አይቀጥን፥ ለላላ ያሉት ገንፎ አይወፍርም። ለራበው ሰው ቆል፤ ለቁልቁለት በቅል። ለራበው ባድ መሶብ ማቅረብ። ለራት የማይተርፍ ዳረጎት። ለርስት ሴቶች ስን኱ ይሞቱበታል። ለሮጠ አይደለም፥ ለቀደመ እንጂ። ለሸማኔ ማገጃ፤ ስለት ማረጃ። ለሰለባ የመጣ፥ ልብስ ቢጥሉለት አይመለስ(ም)። ለሰማይ ምሰሶ፤ የለው ለባዕድ ሥር የለው። ለሰበበኛ ቂጥ፥ መረቅ አታብዚበት። ለሰባቂ ጆሮ(ህን) አትስጠው። ለሰው ልጅ ሲያበሉ፥ ለውሻ ልጅ ያብሉ። (ሲያበሉ ~ ሳያበሉ) ለሰው ልጅ ከሚያበሉ፥ ለውሻ ልጅ ያብሉ። ለሰው ልጅ ከማብላት፥ ለውሻ ልጅ ማብላት። ለሰው ሞት አነሰው። ለሰው ልጅ ዕውቀት፤ ለጦጣ ብልጠት። ለሰው ሞት አነሰው፥ ውሻውንስ ፈሴ መለሰው አለች ቀበሮ። ለሰው ሰው ነው፥ ልብሱ። ለሰው ቢነግሩት ለሰው። ለሰው ቢናገሩ፥ መልሶ ለሰው፥ ጫር ጫር አድርጌ አፈር ላልብሰው። ለሰው ብል መሞት አምላክነት ያሻል። ለሰው ብል ሲያማ፥ ለእኔ ብለህ ስማ። ለሰው ብትል ትጠፋለህ፤ ለእግዛር ብትል ትለማለህ። ለሰው እንግዳ፤ ለአገሩ ባዳ። ለሰው ከበሬታው ሰው፤ ለወጥ ማጣፈጫው ጨው። ለሰው የማይል ሰው፥ ሞት(ም) ሲያንሰው። ለሰው ያስታውቅ፤ ለራሱ አያውቅ። ለሰው ጠላቱ፤ ይወጣል ከቤቱ። ለሰይጣን፥ አትስጠው ሥልጣን። ለሰይጣን እን኱ን ወዳጅ አለው። ለሰጭም አያንሰው፤ ለበዪም አይደርሰው። ለሴት ልጅ እስከ አርባ ቀን ሞቷን፥ ከዙያ ወዱያ ሀብቷን። ለሴት ምሥጢር መንገር፤ በወንፊት ውሃ መቅዳት። (መንገር ~ ማውራት) ለሴት ምክር አይገባትም። ለሴት ምክር አይገባትም፥ መከራ አያስተምራትም። ለሴት ብርቱ፤ ወንድ መድኀኒቱ። ለሴት ደላ፤ ለአህያ ዳውላ። ለሴት ጠላ፤ ለፈረስ ቆላ (አይረባውም)። ለሴትና ለአህያ፥ አይነፍጉም ደላ። ለሴትና ለጉም አይ዗ነጉም። ለስሟ መጠሪያ፥ ቁና ሰፋች። (መጠሪያ ~ መጥሪያ) ለሹመት ካልመከሩለት፤ ለጥርስ ካልነከሩለት። (ካልነከሩለት ~ ካልከደኑለት) ለሹመት ያደለው፥ የለማኝ አለቃ ይሆናል። ለሺ ወፍ፥ አንድ ጉሉንጉፍ። ለሺ ፍልጥ፥ ማሰሪያው ልጥ። ለሽማግላ የሚያስተምር በውሃ ላይ ይጽፋል፥ ለሕፃን የሚያስተምር በድንጋይ ላይ ይጽፋል። ለቀለብላባ አማት፥ ሢሶ በትር አላት። ለቀላል (ሰው) ምሥጢር፤ መንገር በቀዳዳ አቁማዳ ጤፍ መቋጠር። ለቀማኛ የለውም እጅ፤ ለበቅል የለውም ልጅ። ለቀበጠች አማት፥ ሢሶ በትር አላት። ለቀባሪው አረዳት። ለቀን ቀጠሮ፤ ለሴት ወይዘሮ። ለቀንዳም በሬ ቤት አትከልክለው፥ ቀንደ ይከለክለዋል። (ይከለክለዋል ~ ይከልክለው) ለቀጣፊ ይደልዎ ጥፊ፤ ለቀልቃላ ይደልዎ ደላ፤ ለመናጢ ይደልዎ ቡጢ። ለቁንጫ፥ ለምድ ያወጣል። ለቀጣፊ፥ ሬት ሸንኮሩ ነው። ለቀጣፊ ሬት አይመረው። ለቀጣፊ አደራ ስጠው። ለቁንጫ መላላጫ። ለቂጡ ጨርቅ የለው፥ ቆንጆ ያባብላል። ለቅልብልብ አማት፥ ሢሶ በትር አላት። ለቅሶ ሳለ ከቤት፥ ለቅሶ ይኼዳል ጎረቤት። ለቅሶ ሳለ ከቤት፥ ይኼዳል ጎረቤት። ለቅናት፥ የለውም ጥናት። ለቅ዗ን እግር አንሥተውለት፤ ለውሻ ሮጠውለት። (ሮጠውለት ~ ሸሽተውለት) ለቆመ፥ ሰማይ ቅርቡ ነው። ለቅ዗ን እግር አንሥተውለት። ለቆማጣ፥ አንድ ጣት ብርቁ ናት። ለበራ ወለባ፤ ለውሻ ገለባ። ለበሬ መንጃ፤ ለማሩ መውጊያ፤ ለሸማው መከንጃ። ለበጋ ጥጃ ውስ አነሰው ወይ። ለበግ ደጋ፤ ለምቾት አልጋ። ለቡናሽ ቁርስ የለሽ፤ ለነገርሽ ለዚ የለሽ። ለባለጋራህ፥ ብልኅ ኹንበት። ለባለጌ፥ ገድሉ ውርደቱ። ለባዕድ የሰጡት ኮሶ፥ ይወጣል ደም ጎርሦ። ለቤቱ ነጭ ሽንኩርት፤ ለውጭ ግን ቀይ ሽንኩርት። ለቤት ሳማ፤ ለውጭ ቄጤማ። (ቀጤማ ~ ቄጤማ) ለቤት ሳንቃ፤ ለነገር ጠበቃ። ለቤት ሳንቃ፤ ለሰው አለቃ፤ ለነገር ጠበቃ ያስፈልገዋል። ለቤት ባላ፤ ለችግር ነጠላ (ያስፈልገዋል)። ለቤት ሳንቃ፤ ለሰው አለቃ። ለብልኅ ንገረው ምን ይስተው ብዬ፤ ለሞኝ ንገረው ምን ይገባው ብዬ። ለብልኅ አይነግሩ፤ ለድመት አያበሩ። ለብልኅ አይነግሩ፥ ካልጠየቀ በስተቀር። ለብልኅ አይነግሩ(ም)፤ ለንጉሥ አይመክሩ(ም)። ለብቻው የሮጠ፥ የሚቀድመው የለም። ለብልኅ አይነግሩ(ም)፤ ለአንበሳ አይመትሩ(ም)። ለብዙ ጸልት ማሰሪያው አቡነ ዗በሰማያት። ለቦና ጥጃ ውስ አያንሰውም። ለተማሪ ቆል፤ ለወታደር በቅል። ለተሟጋች መ዗዗ኛ፤ የዳኛ ትእግስተኛ። ለተረታው ያበደረ፥ እሳት ጨመረ። ለተራበ ቂጣ፤ ለተጠማ ዋንጫ። ለተራበ በርገር፤ ላፈቀረ ጠበል። ለተራበ በግብር፤ ለተበደለ በነገር (ተገኘ)። ለተራበ ግብር፤ ለተበደለ ነገር። ለተሸሸገ ምግብ፥ የተሸሸገ ሆድ አይጠፋለትም። ለተሾመ ይመሰክሩለታል፤ ለተሻረ ይመሰክሩበታል። (ይመሰክሩለታል ~ ይሟገቱለታል) ለተሾመው ይመሰክሩለታል፤ ለተሻረው ይመሰክሩበታል። ለተቀማጭ፥ ሰማይ ቅርቡ ነው። ለተባባሰው፥ ማጭድ አታውሰው። ለተቸገረ የማያዝን፥ ዕንብርት የለውም። ለተንኮለኛ ሲሉ ይሰበስባሉ፤ ለቅን ይፈርዳሉ። ለትኋን ል጑ም ማጉረሥ፤ ለአፈኛ ሰው መመለስ (አይቻልም)። ለቸኮለ ሰው፥ ዋንጫ አስጨብጠው። ለቸኮለ፥ ዋንጫ አስጨብጠው። ለችግር የጣፈው፥ ቢነግድ አይተርፈው። (የጣፈው ~ የፈጠረው) ለነገ የማይልን ሰው፥ ጅብ በላው። ለኀምሳ ጋን፥ አንድ አልል (ይበቃል)። ለሀብት አባት እንጂ፥ አጎት የለውም። ለኀጥአን የወረደ መዓት፥ ለጻድቃን ይተርፋል። ለኀጥአን የወረደ፥ ለጻድቃን ይተርፋል። ለዅሉም ጊዛ አለው። ለነገረኛ መንገድ፤ ለሆዳም ገበታ ይተዋል። ለነገረኛ ሰው፥ ጀርባህን ስጠው። ለነገረኛ ነገር ተውለት፤ ለሆዳም እህል አቅርብለት። ለነገር ዋነኛ፤ ለጦር አርበኛ። ለነፍስህ፥ ገዳም አለልህ። ለንጉሥ የማይረዳ፤ ከባሕር የማይቀዳ። ለንጉሥ የማይገዚ፥ ለእግዙአብሔር(ም) አይገዚ። ለንጉሥ የቀነቀነ ወርቅ፤ ለእግዛር የቀነቀነ ጽድቅ። ለንጉሥ ያልረዳ፤ ከባሕር የማይቀዳ። (የማይቀዳ ~ ያልቀዳ) ለንፉግ ሰው፥ የገበያ መንገድ ይጠበዋል። (ይጠበዋል ~ ይጠበው) ለአህያ ማር አይጥመውም። ለአህያ ማር አይጥመው፤ ለደንቆሮ ምክር አይገባው። ለአህያ ማር አይጥማት፤ ለሴት ምክር አይገባት። ለአህያ ማር አይጥማት(ም)። ለአህያ ያልከበደው፥ ለመጫኛ ከበደው። ለአህያ ፈስ፥ አፍንጫ አይዙለትም። ለአለው፥ ቅንጭብ ያረግዳል። ለአለው ይሰጡታልም፥ ይጨምሩለታልም። ለአለው ይጨመርለታል። ለአለፈ ነገር፥ ቤት አይሠራለትም። ለአለፈ(ው) አይጸጸቱም፤ ለሚመጣው አይበለጡም። ለአለፈ(ው) ክረምት፥ ቤት አይሠራለትም። (አይሠራለትም ~ አይሠራም) ለአለፈው ክረምት፥ ውሃ ማቆር አይቻልም። ለአለፈው ጸልት፥ ከንቱ ጩኸት። ለአሉ ያሉት፥ ለአለዊ ሆነለት። ለአላወቀ(ው) ፎገራ ደር ነው። ለአላየ ልጅ፥ ዳቦ ፍሪዳው። ለአላየው የሚያስገርም፤ ለሰማው የሚያስደንቅ። ለአላዩ ልጅ፥ ዳቦ ፍሪዳው። ለአሣር የጣፈው፥ ቢነግድ አይተርፈው። ለአሽከር አደግ፥ ጌታ አትደር። ለአበባ የለው ገለባ፤ ለወሬ የለው ፍሬ። ለአባይ ልጅ፥ ውሃ ነሡት። ለአበባ፥ የለው ገለባ። ለአቤቱታ፥ የለው ይሉኝታ። ለአንበሳ አታበድር፥ ከአበደርክ አትጠይቅ። ለአንበሳ አይመትሩ፤ ለብልኅ አይመክሩም። (አይመክሩም ~ አይነግሩም) ለአንበሳ አይመትሩ፤ ለአዋቂ አይነግሩ። (አይነግሩ ~ አይናገሩ) ለአንተ መምከር፥ ጥቁር ድንጋይ ላይ፥ ውሃ ማፍሰስ ነው። ለአንተ የተባለ እንጀራ ላላ አያገኘውም፥ ሻግቶ ይቀራል እንጂ። ለአንተ ያለውን እንጀራ ይሻግታል እንጂ፥ ማንም አይበላውም። ለአንቺ ቁምነገርሽ፥ በሶብላ ወጥሽ። ለአንቺ ብርቅሽ፥ በሶብላ ወጥሽ። ለአንቺ ብርቅሽ፥ የ዗ንጋዳ ሙቅሽ። ለአንደ የ዗ነበለት፥ ለላላው ሳያካፋ አይቀርም። ለአንድ ብርቱ፥ ኹለት መድኀኒቱ። ለአንድ አልሚ፥ ዗ጠኝ ቋሚ። (አልሚ ~ አራሚ) ለአንድ ያሉት፥ ለኹለት ይተርፋል። ለአንድ ጭቃ አገር፥ ዗ጠኝ ምስለኔ። ለአኩራፊ፥ ምሳው ራት ይሆነዋል። ለአወቀባት፥ ገረገራም ዋልድባ ናት። ለአዋቂ ምክር፤ ላላዋቂ በትር። ለአዋቂ አትወቅበት፤ ለረጅም አትከንዳበት። ለአዋቂ አይነግሩ፤ ለአንበሳ አይመትሩ። ለአዋጅ ነጋሪት፤ ለጥጥ ልቃቂት። ለአያቱ ዕዳ፤ ለአማቱ ፍሪዳ። ለአይነ ስውር መስተዋት። ለአይን አምላክ አለው። ለአይን የሚከፋ፤ ለአፍንጫ የሚከረፋ። (የሚከረፋ ~ ይከረፋ) ለአይንና ለወዳጅ ጥቂት ይበቃል። (ይበቃል ~ ይበቃዋል) ለአገልጋይ ትዕግሥት፤ ለባለቤት መጠቃት። ለአገሩ ባዳ፤ ለሰው እንግዳ። ለአገሩ እንግዳ፤ ለሰው ባዳ። ለአገሩ ፊደል እንግዳ፤ ለአባቱ ቋንቋ ባዳ። ለአገሬ ሰው እን኱ን ነጋሪት፥ አታሞ አይሰጠው። ለአጠፋ ምሕረት፤ ለአጣ ቸርነት። ለአፈ ግም፤ አፍንጫ ድፍን ያዝለታል። ለአፈኛ ሰው መመለስ፤ ለትኋን ል጑ም ማጉረሥ። ለአፈኛ ሰው፥ ገደልም ሜዳ ነው። ለአፉ ለከት የለውም። ለአፍ ዳገት የለውም። ለአፍ ግም፤ አፍንጫ ድፍን ያዝለታል። ለአፍላ፥ የለው ጎፍላ። ለአፍታ የለውም ፋታ። ለእርድ የቀረበ በሬ፥ ቢላዋ አይፈራም። ለእሮሮ ሳይሆን፥ ለአመክሮ። ለእሳት ዕንጨት፥ ካልነሡት አይጠፋም። (ካልነሡት ~ ካልነፈጉት) ለእሳት ውሃ፤ ለጠጉር ቡሀ። ለእሳት ፍላት፤ ለጮማ ሥባት። ለእበጥ ፍላት፤ ለዕንጨት እሳት። ለእባብ እግር የለው፤ ለባዳ ውል የለው። ለእብለት ሥር የለው(ም)፤ ለእባብ እግር የለው(ም)። ለእብድም ቢሆን ባል አይጠፋም። (ባል ~ ሚስት) ለእኔ ቆንጆ፥ ለሰው ግን አይጥ። ለእኔ እናት ምን በጃት? ( ተሻላት ~ ረባት) ለእኔ እናት ምን ደላት? ያም አፈር ያም ድንጋይ ጫነባት። ለእንቁጣጣሽ ያልሆነ፥ ቀሚስ ይበጣጠስ። ለእኔ፥ ነግ በእኔ። ለእዙህ ሆዳ፥ ጠላኝ ዗መዳ። ለእጅ ርቆ፤ ለአይን ጠልቆ። ለእግሩ የተጸየፈ፤ ለቂጡ አስተረፈ። ለእግር የተጸየፈ፤ ለራሱ አተረፈ። ለእግር የፈሩት፤ ለቂጥ ይተርፋል። ለእግዙአብሔር የቀነቀነ ለጽድቅ፤ ለጌታ የቀነቀነ ለወርቅ። ለእግዛር የተቀናቀነ ጽድቅ፤ ለንጉሥ የተቀናቀነ ወርቅ። ለከለላ ጥላ፤ ቢርብህ ብላ። ለከርሞ የሚያብድ፥ ዗ንድሮ ሱሪውን ከፍ ከፍ ያደርጋል። ለከርሞ ድሮ፤ እንቁላል ለ዗ንድሮ። ለከሳሽ የለው መላሽ። ለካህን ጥምቀት፤ ለገበሬ ግንቦት። ለክፉ ያሉት፥ ለበጎ ይበጃል። ለክፋት ያደለው፤ አሳዳጊ የበደለው። ለኮ መሳቢያ፤ ወፍጮ ማላሚያ። ለወሬ ሞትዅ። ለዅሉም አጥንት፥ የለው መቅን። ለኺያጅ፥ የለውም ወዳጅ። ለሕልም ምሳላ የለውም። ለወሬ ሞትኩ፤ ለእህል (ተ)ሰለፍኩ። ለወሬ ወዳጁ ወሬ፤ ለመነኰሴ ጥሬ። ለወሬ የለው ፍሬ። ለወሬ የለው ፍሬ፤ ለአበባ የለው ገለባ። ለወሬ የቸኮለ፥ እናቱን በመንገድ (ላይ) ይረዳል። ለወርቅ ያሉት አንገት ላሽክት። ለወቀጣ አንድም ሰው አልመጣ፤ ለመጠጡ ከየጎሬው ወጡ። ለወታደር፥ ሰፊ መንደር። ለወታደር ሰፊ መንደር፤ ለወዱላ መልካም ደላ። ለወይ዗ሮ፥ መልካም ድሮ። ለወደላ፥ መልካም ደላ። ለወደደት:_ ሰው ልብ ደንገጥ፥ ሹሩባም ዗ርገፍ ይላል። ለወዱላ፥ መልካም ደላ። ለወዳጁ የሚፈተፍት፤ ለጠላቱ የሚመክት። ለወዳጅ የማር ወለላ፤ ለጠላት አሜኬላ። ለወዳጅ ጠላት፥ አለመተኛት። ለወዳጁ:_ እሳት ይዞል በእጁ። ለወዳጅና ለአይን፤ ትንሽ ይበቃዋል። ለወገን ጽናት፤ ለጠላት ቅናት። ለወጡ ዕ዗ኑለት፤ ከእንጀራውም ጉረሡለት። ለወጡ ጊዛስ፥ ከደረቁም ጉረሡለት። ለወጡም ዕ዗ኑለት፥ አንዳንድ ጊዛ ደረቅ ጉረሡለት። ለወጡም ዕ዗ኑለት፤ ከእንጀራውም ጉረሡለት። ለወጡም ዕ዗ኑለት፤ ከደረቁም ብሉለት። ለወጥ የሚሻል፥ ቅልውጥ። ለዋስ አፍ የለው፤ ለጉንዳን ደም የለው። ለዋንጫ ቡሽ፤ ለውሃ ጉሽ የለውም። ለውሻ ምሳ የለው፥ ራት ብቻ። ለውሻ ሞት፥ ፊት አይነጩለትም። ለውሻዬ ያልኹትን፥ ልጄ ቢበላብኝ አልወድም። ለውሽማ ሞት፥ ፊት አይነጩለት(ም)። (አይነጩለት(ም) ~ አይነጭለት(ም)) ለውጡኝ ባይ፥ የሚሻለውን አውቆ። ለዓመት ልብስ፤ ለዕለት ጉርሥ። ለአማርኛ ግእዝ (ነው) ዳኛ። ለአምላክ ልንገረው፥ ለማያስቀረው። ለአምጪ(ው) ይግደደው። ለዕውር ዝማሜ፤ ለመላጣ ጋሜ (አይስማማውም)። ለእውነት ማማ፤ ለውሸት ጨለማ። ለዝናብ ጌታ፥ ውሃ ነሡ(ት)። ለዝንብ፥ ከትላንት ወዱያም ድሮ ነው። ለይቶ እንደፈፋ፤ አን጑ል እንዳረፋ። ለይቶት፥ አባ ንጉሧ። ለደኅና ሰው፥ ዋጋ አነሰው። ለደኅና ሰው ውሸት፤ ለጅብ እሸት። ለደረቅ የመጣ እሳት፥ ርጥብን ያነዳል። ለደብተራ፥ መቋሚያና ጭራ። ለደደብ ማስረዳት፥ ድንጋይ ቅቤ መቀባት። ለደግ ንጉሥ፥ ዕለት ዕለት ማልቀስ። ለዱያብልስ ፀሩ መታገስ፤ ለረኃብ ፀሩ ማረስ። ለዳርቻው ሲሣሡ፥ መካከሉን ተነሡ። ለዳርቻው ሲሣሡ፥ ከነመሀሉም ተነሡ። ለዳርቻው የሣሡ፥ መሀሉን ተነሡ። ለዳባ ለባሽ፥ ነገርህን አታበላሽ። ለዳኛ አመልክት፥ እንዱሆን መሠረት። ለዳኛ የነገሩት፤ በርጥብ ያቃጠሉት። ለዳኛ ዳኛ፤ ለአንበሳ ተኩላ አለው። ለድሀ፥ ማን ሰጠው ውሃ። ለድሪ ያሉት አንገት፥ ለአሽክት። ለድንገቱ፥ ከእግሬ ስንድድ አለበቱ። ለድንጋይ፥ የለው አይን። ለድሮ አጥንት፥ መጥረቢያ አያስፈልገውም። ለድካም የጣፈኝ፥ ብነግድ አይተርፈኝ። ለድሮ ሲነግሩ፥ ምጥማጥ ይሰማል። ለድህነት የፈጠረው፥ ቢነግድ አያተርፍም። (አያተርፍም ~ አይተርፈው) ለድሪ ያሉት አንገት፥ ለአሸንክታብ። ለጅል ከመንገር፥ የአንድ ቀን ጎዳና መኼድ ይሻላል። ለጅብ፥ አንጀትን ል጑ም አያደርጉም። ለጅብም፥ እንዳንተ ያለ ወንድም አለው። ለጆሮ አጥር የለውም። ለጆሮ ጥርስ፤ ለሆዳም ሥሥ። ለገላጋይ ደም የለውም። ለገበሬ፥ መልካም በሬ። ለገቢህ ተንገብገብ። ለገና ጨዋታ፥ አይቆጡም ጌታ። ለገደለ ጎፈሬ፤ ላረጋገጠ ወሬ። ለገዳም የረዳ፥ አይጎዳ። ለጉንዳን ደም የለው፤ ለዝንብ ቤት የለው። ለጉንፋን ምሱ፥ ገንፎ በትኩሱ። ለጋስ ቢለግስ፥ አበደረ እንጂ (እንዱያው) አልሰጠም። ለጌታ የነገሩት፤ በሠኔ የተከሉት አይጠፋም። ለጌታም ጌታ አለው። ለጎበዝ ሰንጋ ፈረስ፤ ለፈሪ ፍርፋሪ። ለጎበዝ፥ ስጠው ሰንጋ ፈረስ። ለጠጪ ሰው፥ የመጠጥ ወሬ አውራው። ለጣይም ፈንጋይ ያዝለታል። ለጥልና ለዳኛ ያለው ገን዗ብ፥ አፋፍ ይቆያል። ለጥምቀት እታጭ ያለች ሙሽራ፥ መስክ አደረች ለከተራ። ለጥምቀት እንሶስላ ያልሞቀች ኮረዳ፤ በእንተ ማርያም የሚል የቆል ተማሪ ሳይዝ አቁማዳ። ለጥምቀት ያልሣሡት እንግጣ፥ በወሩ ሙሽራ ያመጣ። (እንግጣ ~ እስክስታ) ለጥምቀት ያልታጨ፤ በሠኔ ያልተላጨ። ለጥምቀት ያልሆነ ቀሚስ ይበጣጠስ። ለጥምቀት ያልሆነ ዝማሬ፤ ለሠኔ ያልሆነ በሬ። ለጥርጣሬ ምንጣሬ። ለጥቅም ሲታጠቁ፥ ከጎን ይጠንቀቁ። (ከጎን ~ ጎንዎን) ለጥፋት የታ዗዗ች ከተማ፥ ነጋሪት ቢጎሰም አትሰማ። ለጦም ግድፈት፤ ለበዓል ሽረት። ለጨለማ ጊዛ መብራት፤ ለመከራ ጊዛ ብልኀት። ለጨቅጫቃ ሰው ከማበደር፥ ይሻላል በእጄ ማደር። (በእጄ ማደር ~ በእጅ ማሳደር) ለጨዋ ልጅ ሸማህን፤ ለባለጌ በቅልህን አታውስ። ለጭሰኛ መሬት፤ ለሣር ቤት ክብሪት። ለጾም ግድፈት፤ ለባል ሽረት። ለፈረስህ አንገት፤ ለጋሻህ ዕንብርት። ለፈሪ ምድር አይበቃውም። ለፈሪ፥ መንገድ አይነሡም። (መንገድ ~ ሜዳ) ለፈሪ፥ ስጠው ፍርፋሪ። (ስጠው ~ ይበቃል) ለፈሪና ለንፉግ እያደር ይቆጨዋል። ለፋሲካ የተዳረች፥ ኹል ጊዛ ፋሲካ ይመስላታል። ለፍቅር ብቀርባት፥ ለጠብ አረገ዗ች። (ብቀርባት ~ ብተተኛ) ለፍቅር፥ የለውም ድውር። ለፍየል ሕመም፥ በሬ ማረድ። ለፍየል ስም አውጣ ቢለው፥ ሞት አይደርስ አለው። (አይደርስ ~ አያድርስ) ለፍየል ቆላ፤ ለሙክት ባቄላ። ለ዗መደ የማያዝን አንጀት፤ ራሱን የማይችል አንገት (የለም)። ለ዗መዳ፥ ያዝናል ሆዳ። ለ዗መድ ጠላት፥ አያገኙለት መድኀኒት። ለዙሁም ትዳሬ፥ ይቆጡኛል ባላ። ለዚፍ ያለው፥ ቁጥቋጦ አይሆንም። ለዝና ሲሉ፥ ቁም ነገር ሠሩ። ለ጑ደኛው ጉድ጑ድ የሚቆፍር፥ ራሱ ይገባበታል። ለጠላትህ፥ እንደ ዳቦ እስኪገምጥህ አትመቸው። ለጠቢብ፥ አንድ ቃል ይበቃል። ሉሻገር ቢያምረው ይዋኛል፤ ሉሟገት ቢያምረው ይዳኛል። ሉቃውንት ይናገሩ፤ መጻሕፍት ይመስክሩ። ሉበሉ የፈለጉትን አሞራ፥ ስሙን ይሉታል ጅግራ። ሉበሉ ያሰቡትን አሞራ፥ ስሙን ይሉታል ጅግራ። ሉበሎት ያሰቧትን አሞራ፥ ይሎታል ጂግራ። ሉበሎት ያሰቧትን አሞራ፥ ጅግራ ናት ይሎታል። ሉነጋ ሲል በጣም ይጨልማል። ሉወጋ የመጣ፥ ጌታዬ ቢሉት አይመለስም። ሉያልፍ ውሃ፥ አደረገኝ ድሀ። ሉያስቡት አይገድም። ሉጎዳቸው ያሰባቸውን ያሳብዳቸዋል። ሉጠጣ ቢሻው ይዋኛል፤ ሉቀማ ቢሻው ይዳኛል። ሉጣላ የመጣ፥ ሰበብ አያጣም። ላሉበላ ኼደሽ፥ ከሕንጻው ብትሰፍሪ፤ አይገኝም ጽድቅ፥ አለ ባሕሪ። ላሉበላ፥ በሰው ሰርግ ይጋባ። ላሉበላ፥ አደራውን አይበላ። ላሉበላ፥ የቃሉን አይበላ። ላሉበላን ከአላጠገቡት ይጮሀል፤ ልላም ከአልሰጡት ይከዳል። ላላወቀ ፎገራ ደሩ ነው። ላሉቱን በጨለማ፤ ቀኑን በደመና። ላሉት ለአራዊት፤ ቀን ለሰራዊት። ላሉት ከጅብ፤ ቀን ከሕዝብ። ላሉት፥ የምክር እናት። ላላ አገር ብትኼድ፥ እንደነሱው ዅን። ላላው ሲታማ፥ ለእኔም ብለህ ስማ። ላባ ለአመሉ፥ ቅድመ እውቅና አገኘ። ላባ ለአመሉ፥ ንግድ ይላል። ላላወቀው ፎገራ ደር ነው። ላላየ ልጅ፥ ዳቦ ፍሪዳው። ላላየው የሚያስገርም፥ ለሰማው የሚያስደንቅ። ላላዩ ልጅ፥ ዳቦ ፍሪዳው። ላሜ ቦራ፥ የልጆቼን ነገር አደራ። ላም ሲበ዗በዝ፥ ጭራ(ዋን) ያዝ። ላም ቀንዶ አይከብዳትም። ላም በረቱን የሰው፤ ልጅ አባቱን አይረሳም። ላም በአልዋለበት፥ ኩበት ለቀማ። ላም በጎፍላ ትታለባለች። ላም ነጂዋን እንጂ፥ አታውቅም ጌታዋን። ላም ነጂዋን እንጂ፥ ጌታዋን አታውቅም። ላም አለች በደረጣ፥ ወተቷ ምን ይነጣ። ላም አለ(ች)ኝ በሰማይ፥ ወተትም አልጠጣ አሉቡንም አላይ። ላም አለኝ በሰማይ፥ ወተቷንም አላይ። ላም አለኝ በሰማይ፥ ገመድ እፈልጋለኹ። ላም አልዋለበት ኩበት ለቀማ፤ ባልታረሰበት ገለባ ሻማ። ላም እሳት ወለደች፥ እንዳትልሰው ነደደች እንዳትጥለው ወለደች። ላም እሳት ወለደች፥ እንዳትልሰው ፈጃት እንዳትተወው ልጇ ሆነባት። ላም ከወንዝ፤ ልጅ ከቦዝ። ላም የላለው፥ አፉን በወተት ይጉመጠመጣል። ላም የዋለችበትን ትመስላለች። ላባ ለአመሉ፥ እጁን ይልሳል። (እጁን ~ ዳቦ) ላባ ላይሰብር፥ ይሰርቃል። ላባ ሰው አያምንም። ላባ ቢያዩኝ እሥቅ፥ ባያዩኝ እሰርቅ ይላል። ላባ ባይሰርቅ፤ ዳኛም ባይገድ። ላባ ተይዝ፤ ደላ (ጥየቃ)። ላባ እናት፥ ልጇን አታምነውም። ላባ እናት፥ ልጇን አታምንም። ላባ፥ ኮሽ ባለ ቁጥር ይደነብራል (አሉ)። ላባ ውሻ፥ ለአፏ ሉጥ፥ ለወገቧ ፍልጥ። ላባ፥ የላሉት ወፍ ትንሽ ወንድም ነው። ላባ ገረድ፥ ድመት አትወድም። ላባ(ው)ን ላባ ሲሰርቀው፥ እንዳት ይደንቀው? ላባና ላባ፥ ተጣሉ በሰው ገለባ። ላባን ላባ ቢሰርቀው፥ ምን(ኛ) ይደንቀው? ላኒን ተማሩ እንጂ፥ ተፈተኑ አላለም። ልማ በሥሉስ፤ ጥፋ በሥሉስ። ላብ ከአጥባቂ፥ ፈረስ ይብሳል። ላታመልጠኝ አታሩጠኝ። ላታመልጥ አትሩጥ። ላታገኝ አትመኝ፤ ላታጣ አትቆጣ። ላት አይሆን፤ ባት አይሆን። ላታገኝ አትመኝ። ላትከፍል አትዋስ፤ ላትደርስ አትገስግስ። ላየ ደኅና፤ ውስጠ ቀጣፊ። ላዩ ካኪ፤ ውስጡ ውስኪ። ላዩ ዳባ፤ ውስጡ ደባ። ላያሸንፉ መታገል፤ ትርፉ ገደል። ላያ዗ልቅ ጸልት፥ ለቅስፈት። ላያጠግቡ መጋበዝ፤ ላይገድሉ ካራ መም዗ዝ። ላያጥብ አይለብስ፤ ላያርም አያርስ። ላይ ላዩን፥ ቅልም ደባ ይመስላል። ላይሆን ቤት፥ በበዓል ስፌት። ላይሆን ዗መድ፥ ገን዗ቤን አልሰድ። ላይሉኝ ወሶ፥ ደርሼ ነበር ከረጋ ለቅሶ። (አለ ጠይብ) ላይመራው አማሰነው። ላይምረው አማሰነው፤ ላይበላው አበላሸው። ላይሞቱ መና዗ዝ፤ ላይመቱ መጋበዝ። ላይሞት ይፈራል፤ ላይድን ይሸሻል። ላይሰጥስ፥ በአፉ ለጋስ። ላይቀር መሞቱ፥ መንጠራወቱ። (መሞቱ ~ ሞቱ) ላይቀር ሞቱ፥ መንጠራራቱ። ላይቀር ሣቁ፥ ችኩ። ላይቀር ጣጂው፥ አታራፍጂው። ላይቀር ጣጂው፥ አታብርጂው። ላይቀርልኝ ዕዳ፥ በጊዛ ልሰናዳ። ላይበላው አበላሸው። ላይተች አይፈርድ፤ ላያተርፍ አይነግድ። ላይችል አይሰጠውም። ላይችል አይሰጥ። ላይችል አይሰጥም፤ ላይጠግን አይሰብርም። ላይኛው ከንፈር ለክርክር፤ ታችኛው ከንፈር ለምስክር። ላይ዗ሩ አያርሱ፤ ከአላረሱ አያጎርሡ። ላይሆን ዗መድ፥ ገን዗ብህን አትስደድ። ላይሉኝ ቸር፥ በየቦታው ስፈነቸር። ላይ዗ንብ ያካፋ፤ በሰበብ ያጠፋ። ላይጠቅመኝ፥ እጄን አረጠበኝ። ላይጸድቅ ይመጻደቅ፤ ላይጦም ይጠም። ላይፈሩ ቁጣ፥ ከእብደት አንድ ነው። ላይፈቱ አይተርቱ። ልላ መስል ቢሠሩ፥ ጌታ መስል ይበሉ። ልላ ሲከብር ጌታውን ይከሳል፤ ሙክት ሲሰባ ሾተሉን ይልሳል። ልላ በአፍላው፥ የአህያ መዥገር ይከላል። ልላ ያገለገለውን ይቆጥራል፤ ጌታ ያስቀየመውን ያስባል። ልላና አሞላ ከአ዗ዙት ይውላል። ልሚ ቢያብብ፥ ቢኖርና፥ መልካም ሽታ ቢሰጥ፥ መኮምጠጡን አይተውም። ልሚ ካልመጠጡት፥ እምቧይ ነው። ልሚ ካልመጠጡት እምቧይ፤ ዳቦ ካልገመጡት ድንጋይ። ልሚና ትርንጎ ሞልቶ በአገልግልህ፥ እንቧይ ታሸታለህ የድሀ ነገርህ። ልሚና ትርንጎ ሞልቶ በአገር፥ እንቧይ ያሸታል አወይ የድሀ ነገር። ልተሪ እንጂ፥ ተስፋ አይቆረጥም። ልማድ ሲቀር፥ ምሰህ ቅበር። ልማድ፥ ከሰይጣን ይከፋል። ልማድ ያሰርቃል ከአመድ። ልማድ፥ ይከብዳል ከግንድ። ልበ ሰፊ፥ ነገር አሳላፊ። ልበ ሳንባ ድሮዬ። ልበ ጥኑ፤ ነፍሰ ጥኑ። ልቡ ለታመመ፤ በመረቅ አትስጠው። ልቡ ነጭ ያቦካል። ልቡ ከቂም ከበቀል፤ ቃሉ ከመበደል፤ እጁ ከመግደል። ልቡ ከቂም ከበቀል፤ እጁ ከመግደል። ልቡ ከቂም ከበቀል፤ ቃሉ ከመበደል። ልባልባ ታጥቆ አዚባ፤ ሱሪ አውልቆ፤ ፈረስ ጋለባ፤ ራስ (ተ)ላጭቶ ወለባ። ልባልባ ታጥቆ አዚባ፤ ሱሪ አውልቆ፤ ፈረስ ጋለባ፤ ጠጉር ሳይኖር ወለባ። ልባልባ ታጥቆ አዚባ፤ ጠጉር ሳይኖር ወለባ። ልባም ሴት፥ ለባሎ ዗ውድ ናት። ልባብ መሳቢያ፤ ል጑ም ማረሚያ። (ማረሚያ ~ ማቆሚያ) ልቤን ያለ በዕለቱ፤ ራሴን ያለ በዓመቱ። ልብ ሲያውቅ፤ ገንፎ ያንቅ። ልብ ሲያውቅ፤ ጥርስ ከደመኛው ይሥቃል። ልብ ሲፈቅድ መግደርደር፤ ራስን መግደል። ልብ ሳይርቅ፤ አይን ቢርቅ አያራርቅ። ልብ ሳይዙ፤ ነገር አያበዙ። (አያበዙ ~ አያብዙ) ልብ አልማ ታጥቆ አዚባ፤ ሱሪ አውልቆ ፈረስ ጋለባ፤ ራስ ተላጭቶ ወለባ። ልብ ዕንቅርት(ን) ይመኛል። ልብ ከአላየ፥ አይን አያይም። (አያይም ~ አይፈርድም) ልብ ከአ዗ነ፥ እንባ አይቸግርም። (አይቸግርም ~ አይገድም) ልብ ከአ዗ነ ዗ንድ፥ ፊት ይጠቁራል። ልብ ከአጥባቂ፥ ፈረስ ይስባል። ልብ ከጎንጅ፤ ትምህርት ከደጅ። ልብ የላላት ውሻ፥ ማር ትቀላውጣለች። ልብ የሚገኝ በስልሳ፤ ገን዗ብ የሚገኝ በሠላሳ። ልብ የአእምሮ፥ መሰብስቢያ ነው። ልብ ያለው፥ አገሩ ሰማይ ነው። ልብ ያሰበውን አፍ ይናገራል፤ አይን ያየውን እጅ ይሠራል። ልብ ያሰበውን፤ ኩላሉት ያመላለሰውን ያውቃል። ልብ ደስ ሲለው ፊት ይበራል፤ ልብ ሲያዝን ፊት ይጠቁራል። ልብ ዳኛ፤ አይን እረኛ። ልብ፥ ዕንቅርትን (ለማየት) ይመኛል። ልብሴን ኖር በለው። ልብስ ይፈጃል ላት መልበስ፤ ወጥ ይፈጃል መጎራረሥ። ልብስህን ለውሃ፤ ገን዗ብህን ለድሀ። ልብስ፥ ለሰውነት ክብሩ ነው። ልብስ በውሃ፤ ገን዗ብ በድሀ። ልብስ በየፈርጁ ይለበሳል። ልብስን አጥቦ ለገላ፤ ብርላን ዓጥቦ ለጠላ። ልብና ነፋስ፤ ከዅሉ ይደርሳል። (ይደርሳል ~ ይደርስ) ልብን ሳይዙ፤ ነገር አያበዙ። (ነገር ~ ፉከራ) ልቧን አሞራ በልቶታል። ልታስቸግር አታበድር፤ ላትከፍል አትበደር። ልታይ ልታይ ማለት፥ ሸሽጉኝ ሸሽጉኝ ያመጣል። ልትሠራ ኺዳ፥ ተላጭታ መጣች። ልትደርቅ የደረሰች ምንጭ፥ ጭልጭል ትላለች። ልክን ማወቅ፥ ከራስ ጋር መታረቅ። ልኺድ ልኺድ ባይ፥ ሥንቅ አጉዳይ። ልዩ ሥጋ፥ በመንጋጋ። ልደት ሲከበር፤ ሞት አያፍር። ልጁ ሲሞት መቶ ኀምሳ፥ እሱ ሲሞት ኀምሳ። ልጁን በረኃብ፤ የእንጀራ ልጁን በጥጋብ። ልጁን አንሡ፤ ምጡን እርሱ። ልጃገረድ፥ አሥር ያጭሽ፥ አንድ ያገባሽ። ልጄ መርውጥ አባቴ፤ እንደ በላህ እሩጥ። (መርውጥ ~ መዝሩጥ) ልጄ ጭራም አትበላ፥ እናይ ኋላ። (:_ ዝንጀሮ) ልጅ ለሣቀለት፤ ውሻ ለሮጠለት። ልጅ ምን ቢሮጥ? አባቱን አይቀድምም። ልጅ ሲያረጅ፥ አባት ይጦራል። ልጅ ሲያባብሉት ያለቅሳል። ልጅ ሳለህ አጊጥ፤ ሞል ሳይ዗ጋ ሸምት። ልጅ በልጅነት። ልጅ በቁንጮ፤ ወተት በጮጮ። ልጅ በጋሜ፤ አረም በጳጉሜ። ልጅ በጡት፤ እህል በጥቅምት (ይፋፋል)። ልጅ ቢያስብ ምሳውን፤ አዝማሪ ቢያስብ ጠላውን። ልጅ ቢያኮርፍ ቁርሱ ራት ይሆናል። ልጅ አባቱን ገደለ ቢለው፥ የእኔ ልጅ እንዳይሰማ አለው። ልጅ አይወልድ፤ እውነት አይፈርድ። ልጅ አባቱን፤ አይብ አ጑ቱን (ይመስላል)። ልጅ እንደ አባቱ፤ ሰው እንደቤቱ። ልጅ እንደ ወለደ፥ በበቅል ሰደደ። ልጅ ከአርጣጣ፤ እህል ከ዗በጣ። ልጅ ከአበጀው፤ አባት ያበላሸው። ልጅ ከአባቱ፤ ሾተል ከአፎቱ። ልጅ ከዋለበት፥ ሽማግላ አይውልም። ልጅ ከደረሰ፥ ቤት ፈረሰ። ልጅ ከዕውር፤ እህል ከጉራንጉር። (ከዕውር ~ ከአጉል) ልጅ ከወረሰ፥ ቤት ፈረሰ። ልጅ ከጦረው፥ ጥርስ የጦረው። ልጅ፥ የቆል ትፋት ያምረዋል። ልጅ የአባቱን፤ ወቄራ የአፎቱን። ልጅ የጫረው እሳት፥ ለጎረቤት ይተርፋል። ልጅ ያለ፥ ልጅ አከለ። ልጅ ያለ እናት፤ ቤት ያለ ጉልላት ከፍ አይልም። ልጅ ያለ እናት፤ ቤት ያለ ጉልላት። ልጅ ያቦካው፥ ለራት አይበቃም። ልጅ ያቦካው፥ ለእራት አይሆንም። ልጅ ያቦካው፤ እብድ የነካው። ልጅ ይሮጣል እንጂ፥ አባቱን አይቀድምም። ልጅ ይወለዳል ከርጉዝ፤ ላም ይገዚል ከወንዝ። ልጅ ይወለዳል ከቦዝ፤ ላም ይገዚል ከወንዝ። ልጅ ደረሰ፤ ቤት ፈረሰ። ልጅ፥ ለእናቷ ምጥ አስተማረች። (ምጥ ~ ምጥን) ልጅ ለወለደው፤ ሙቅ ላሞቀው። ልጅም ከሆነ ይገፋል፤ ድንችም ከሆነ ይጠፋል። ልጅቷ፥ ለቤተሰቦቿ ንብ ናት። ልጅቱ፥ ለቤተሰቦቿ እንደንብ ናት። ልጅነት ጅልነት። ልጅና መስተዋት አይጠገብም። ልጅና ሴት፥ ወደ መሬት። ልጅና ቀራጭ ችግር አያውቅም። ልጅና ቄስ፥ በሰው ገን዗ብ ያለቅስ። ልጅና አትክልትህን፥ ተጠባበቅ ጎረቤትክን። ልጅና እህል፥ እያደር ይበስላል። (ይበስላል ~ ይበስል) ልጅና እሳት፥ ባለቤቱ ያጠፋዋል። ልጅና ወረቀት የያ዗ውን አይለቅም። ልጅና ጉንዳን፥ ኹል ጊዛ እንደተጠቃ ነው። ልጅና ጥሬ፥ አይተጣጡም። (አይተጣጡም ~ አይተጣጣም) ልጅና ጦጣ፥ ውሃ(ውን) ይጠጣ። ልጅና ጫማ አልጋ ሥር። ልጅና ፊት አይበርደውም። ልጅን መርገምና፥ ራስጌ መሽናት ተመልሶ ጉዳት። ልጅን መቅጣት በጡት። ልጅን ሲወደ እስከነንፍጡ ነው። ልጅን በጡት፤ እህልን በጥቅምት። ልጅን በጡት ከአልጠበቁት፤ እህልን በጥቅምት ከአልቆጠቡት። ልጅን አሳዳጊ፤ እሳትን ውሃ ያጠፋዋል። ልጅን ከጡት፤ እህልን ከጥቅምት። ልጡ የተራሰ፤ መቃብሩ የተማሰ። ልፋ ያለው ሉስትሮ፥ እግር ሥር ይውላል። ልፋ ያለው ምረጡኝ አለ። ልፋ ያለው ቆዳ፥ ለመጫኛ ይሆናል። ልፋ ያለው በሬ፥ ቆዳው ለከበሮ (ይወጠራል)። ልፋ ያለው፥ አንድ ዕንጨት ያስራል። ልፋ ያለው፥ በሕልሙ ሲሸከም ያድራል። ልፋ ያለው፥ በሕልሙ ዳውላ ይሸከማል። ልፋት ቢያምርህ መሬት ግዚ፤ ችግር ቢያምርህ ልጅ አብዚ። ልላ ለስሕተት፤ ጌታ ለምሕረት። ሕልሙ አለሙ፥ የአገኙት ነገር ግን የለም። ሕልም ተፈርቶ፥ ሳይተኛ አይታደርም። ሕልም አለ ተብል፥ ሳይተኛ አይታደርም። ሕልም እልም ልበል። ሕልም እልም አድርግልኝ። ሕልም ፈርቶ፥ ሳይተኙ አያድሩም። ሕመሙ ቀርቶ፥ ሞቱን በሰጠኝ። ሕመሙ ቀርቶ፥ ሞቱን በተወኝ። ሕመሙን የሸሸገ፥ መድኀኒት አይገኝለትም። ሕመሙን የሸሸገ፥ መድኀኒት የለውም። ሕመሙን የሸሸገ በሽተኛ፥ ፈውሱ መጋኛ። ሕመሙን የደበቀ፥ መድኀኒቱም አልታወቀ። ሕመሙን የደበቀ፥ መድኀኒት የለውም። ሕንጻና ልጅ ስምን ያስጠራሉ። (ሕንጻና ~ ግንብና) ሕይወት እና ሽንኩርት ያስለቅሳሉ። ሕይወት፥ ከልብ ወለድ ይልቃል። ሕይወትም ሞትም በአፍ ይመጣሉ። ኅዳር መማረሪያ፥ ሠኔ መቃጠሪያ። ሕግ ይኖራል ተተክል፤ ሥርአት ይኖራል ተዚውሮ። ሕግ፥ ዝተትና ጃኖ ያቆራኛል። ሕግን መናቅ፤ በሽቦ መታነቅ። ሕፃን (ልጅ) ብሉ አይል፥ መቃብር ተነሡ አይል። ሕፃንን ምግብ እንጂ፥ ስሞሽ አያሳድገውም። ሆሆሆ፥ ሥቄ ልሙት አለ ሰውየው። መሀላ የማሉለት አይገባም፥ የካደለት ነው እንጅ። መሀይምነት ለድፍረት፤ ፍቀረ ንዋይ ለክህደት ይመቻል። መኼድ መኼድን እያደራጀኹ፤ እንደ ጉሬዚ ከእሬት አረጀኹ። መኼድ መመለስ፤ ከአሰቡት ለመድረስ። መላላጫ፥ ፊት መገለጫ። መላሰኛ ሴት፥ በጎረቤቷ ጠብ በተነሣ ጊዛ፥ መላሷን ትለምጥ ትጀምራለች። መላእክት የፈሩትን፥ ሞኞች ይደፍሩታል። መልከ ጥፉ፥ ቆንጆዋን አስናቀች። መልከ ጥፉ(ን)፥ በስም ይደግፉ። መልከኛ፥ ከአጤ ቤት ይገባል። መልከኛው ኮሶ ቢጠጣ፥ ጪሰኛው አስቀመጠው። መልኩ የእኔ፤ ግብሩ የአረመኔ። መልካም ላባ፥ ከመልካም ወፍ ይገኛል። መልካም፥ ልብ አይነካም። መልካም ሚስት፥ ለባሎ ዗ውድ ናት። መልካም ሠሪ ለልጆቹ፥ የጨረቃ ንጋት በወፎቹ ይታወቃል። መልካም ሱሪ፥ ለተማሪ። (ለተማሪ ~ ከተማሪ) መልካም ሴት፥ ለባሎ ዗ውድ ናት። መልካም ስም፥ ከመልካም ሽቶ ይበልጣል። መልካም ስም ከመቃብር በላይ ይቆማል። (ይቆማል ~ ይውላል) መልካም ቆንጆ፥ የላት መቀናጆ። መልካም በሬ ለዕርሻ፥ ድማም አያሻ። መልካም ባል፥ መጥፎ ሴት ይገራል። መልካም ተመኝ፥ መልካም እንድታገኝ። መልካም ንግግር ቁጣን ያበርዳል፤ መጥፎ ንግግር ልብን ያናድዳል። መልካም አባት፥ ለልጆቹ እጁን ኪሱ ይከታል። መልካም አድራጊ አበደረ፥ ክፉ አድራጊ ተግደረደረ። መልካም ወሬ አጥንት ያለመልማል፥ መጥፎ ወሬ ልብን ያደክማል። (ያደክማል ~ ይሰብራል) መልካም ወገን፤ የፀሓይ ወጋገን። (ወጋገን ~ ውጋገን) መልካም ወጥ፥ እጅን ያስመጥጥ። መልካም ጭራ ለደብተራ። መልካም ፈረስ ለሩጫ፤ ሰጋር በቅል ለኮርቻ። መልክ ስጠኝ እንጂ፥ ሙያ ከጎረቤቴ እማራለኹ። መልክ በግምት ይገኛል፤ ልብ ትልቅ ይመኛል። መልክ ታጥቦ አይጠጣም። መልክ ታጥቦ አይጠጣ? ወይ አይበላ? መልክተኛ ከአጤ፥ ቤት ይገባል። (መልክተኛ ~ መላክተኛ) መልክተኛ፥ ንጉሥ አይፈራም። መል኱ ባያምር፥ አመሎ ይመር። መልፋት መድከም፥ የቆርበት የጉልበት። መመሳሰል የጋራ ነው። መመራመር ያደርሳል፥ (ከ)ቁም ነገር። መመራመር፥ ያገባል ከባሕር። (ያገባል ~ ይከታል) መመከት ጋሻ አንግቦ፤ መደለያ ዳዊት አቅርቦ። መመጽወት፥ ያድናል ከድህነት። (ከድህነት ~ ከጸጸት) መማለጃ እየበሉ፤ ወንድማቸውን እየበደሉ። መማር መሟር። መማር ይቅደም፥ ከመጠምጠም። መምህራን ከአሉ፥ አዋቂዎች ይበዚሉ። መምሩ፥ ያዩትን አይምሩ። መምሩ ገመሩ። መምሬ፥ አይበሉም ጥሬ። መምታት አያውቅ ራስ ይመታል፤ መስጠት አያውቅ የቁና ድርብብ ይሰጣል። መምከርማ ድሀ ይመክራል፥ ሰሚ አጥቶ ይቀራል። መሞት የፈለገ ግልገል፥ ቀበሮ ቤት ኼድ ይጨፍራል። መሠልጠን ወይስ መሰይጠን። መሠረትህ እውነት፤ መጨረሻህ ደግሞ ትዕግሥት ይኹን። መሰንበት፥ የማያሳየው ነገር የለም። መሥራት እንጂ፥ ማፍረስ አያቅትም። መሪ የላለው ጨንባሳ፤ ምርኩዝ የላለው አንካሳ። (ጨንባሳ ~ ጠንባሳ) መሪና ንፉግ እያደር ይቆጨዋል። መሪው ከተመታ፥ መንጋው ይበተናል። መራጭ ይወድቃል ከምራጭ። መሬት ለተሰደደ፥ እንዱያጎበድደ። መሬት ለአራሽ፤ ነፍጥ ለተ኱ሽ። መሬት ላይ ላለ ሥጋ፥ በሰማይ ያለ አሞራ ተጣላ። መሬት ሲያረጅ፥ መጭ ያበቅላል። መሬት በአቅጣጫ፤ መልክ በአፍንጫ። መሬት በአዋቂ፤ ጠጅ በፈላቂ። መሬት በወንዙ፤ እባብ በመርዙ። መሬት በድንበር፤ ውበት በከንፈር። መሬት እናት፤ ዗ር አባት። መሬት ከሠባ፤ ግዳዩ ከሰለባ። መሬት ከደዳላብ፤ ውሃን ከናጌብ። (ከደዳላብ ~ ከኢየሩሳላም) መሬት የወደቀ ሥጋ፥ አፈር ሳይዝ አይነሣም። መርዝ መርዝን፥ ኮሶ ኮሶን ያፈራል። መርዝ ያፈላ፥ ሢሶው ለራሱ። መርጦ ይገዞል፥ ዋጋ ያበዞል። መርፌ መግቢያዋን እንጂ፥ መውጫዋን አታይም። መርፌ ሰርቆ ማረሻ ቢተኩ ልብ አይሞላም። መርፌ ሲለግም፥ ቅቤ አይወጋም። መርፌ ቢሰበሰብ፥ ማረሻ አይሆንም። መርፌ ውጦ፥ ማረሻ መትፋት። መርፌ የራሷን ቀዳዳ ሳታይ፥ ለብዙ ሰው ትጠቅማለች። መርፌ የራሷን ቀዳዳ ሳታይ፥ የላላውን ቀዳዳ ትጠቅማለች። መርፌ የጠፋው፥ ጋን ይፈነቅላል። መርፌ ፈላጊ፥ ማረሻ ቢያነቅፈው አያየውም። መሮጥ ሲበዚ ልብ ያፈርሳል። መሰስ ሲሉ፥ ምን ደስ ይሉ? መሰስ ሲል፥ ምን ደስ ይል? መሠረት ነዋሪ፤ መሪና አስተማሪ። መሳምን ወደሽ፥ ጢምን ጠልተሽ። መሣሣል የጋራ ነው። መሳሳሚያ ከንፈር፤ መገናኛ ድንበር (የለንም)። መሣሪያ ይዝ ጸልት፤ ካባ (ላንቃ) ለብሶ ማእድ ቤት። መስል ከመታየት፥ ሆኖ መገኘት። መስማት ማየትን አያሸንፍም። መስማት ሰለቸው ሕዝቡ ዗ንድሮ፥ ምነው በሰጠው የዝኆን ጆሮ። መስማት ከማይወድ አንሶ፥ የሚሰማ የለም። መስተዋት ፊት ያሳያል፤ መሰንበት ዅሉን ያሳያል። መስከረም ሲጠባም ብንከፍተው፥ ያው ጎታው ሙሉ ገለባ ነው። መስከረም በአበባው፤ ሰርግ በጭብጨባው (ይታወቃል)። መስከረም የሚወልደው፤ ንጉሥ የሚፈርደው አይታወቅም። መስጠት ቤት አይፈታም። መስጠት አያውቅ ራት፤ መምታት አያውቅ አናት። መስጠት የማያውቅ፥ የቁና እኩል። መስጠትን የማያውቅ ሰው፥ መቀበልን ማን አስተማረው? መሶብ ሰፍቼ፥ ለአጤ አበርክቼ። መሸ መሰለኝ ሉጨልም፥ እንደቀን ጣይ የለም። መሸሽማ አንበሳም ይሸሻል፥ መለስ ያለ እንደሆን ሰውን ያበላሻል። መሸከም የለመደ ራስ፥ መናገር የለመደ ምላስ፥ ኹለቱ አንድ ናቸው። መሸጥ የለመደ፥ እናቱን ያስማማል። መቀመጥ መቆመጥ። መቀመጥ በአልጋ፥ ታላቅ ደጋ። መቀመጥ ቦና ነው፤ መኼድ በልግ ነው። መቀመጫዬ ይብሳል አለ ዝንጀሮ። መቀመጫዬ ይቅደም አለች። ዝንጀሮ፥ በሰው ክምር ይዳዳር። ዝንጀሮ ቢሰበሰብ ውሻን አይመክትም። መቀናጆ የላለው በሬ፤ ለምድ የላለው ገበሬ። መቃ እንዱያ ሲያምር አያፈራ፤ ወርቅ ቢሞላ አይ዗ራ። መቃብሩ የተቆፈረለት፤ መግነዙ የተ዗ጋጀለት። መቃን ከመግጨት፥ ዝቅ ብል መግባት። መቃደን ታጥቆ፤ መቋሚያውን ነጥቆ። መቃጀትና መስከር፤ ላይመልሱ መበደር። መቅረቧን ሳታውቅ፥ እጇን ታጠበች። መቅደስ የገባ አይወጣ፤ ከል የገባ አይነጣ። መበለት በቄስ፤ ገበሬ በንጉሥ፤ ደብተራ በጳጳስ ቢቀኑ አይገናኙ። መብሉ እኩል፤ ሥራው ስንኩል። መብላት ከኹለት፤ መፍረድ በእውነት። (በእውነት ~ በእውነቱ) መብላት ከባዕድ፤ ምክርን ከ዗መድ። መብላት ያስለመድከው ሰው፥ ሲያይህ ያዚጋል። መብላቷን ሳታውቅ፥ እጇን ታጠበች። (ሳታውቅ ~ አላወቀች) መብላቷን አላወቀች፥ እጇን ታጠበች። መብላን ሰንቆ፤ ምርኩዛ ሸንበቆ። መብላን ይዤ፤ ቅልውጤን ረሳኹት። መብል ያለ መጠጥ፤ እንጀራ ያለ ወጥ። መብልን ለቁራ፤ ጩኸትን ለአሞራ። መብልን ከሰው ቤት፤ መኝታን ከቤት። መብልን ከባዕድ፤ ኀ዗ንን ከ዗መድ። መብልን ይዤ፤ ቅልውጤን ረሳኹት። መብረቅ ሲመታው፥ እሳት ይ዗ህ አባብለው። መብረቅ የመታውን፥ ወ዗ት አስተኛው። መብራት ለጨለማ፤ አፍንጫ መያዝ እንዳይገማ። መተው ነገሬን ከተተው። መታለል፥ ገደል መንከባለል። መታ዗ዝ፥ ከመሥዋዕት ይበልጣል። መታፈር በከንፈር። መታ዗ዝን ሳያውቁ ማ዗ዝ፥ ታላቅ መ዗ዝ። መታ዗ዝን የማያውቅ፥ ማ዗ዝን አይችልም። መታጠቂያዬን አጥብቁልኝ። መቶ ኹለት መቶ ሲያወጣ ፈረስ፥ በመቶ ተሸጠ የሰው አጋሰስ። መቸም ጨዋታ ነው፥ ውሽማሽ ማን ነው? አለ ያ ሰውየ። መቸር፥ እጅ ሲያጥር። መቼ መጣሽ ሙሽራ? መች ቆረጠምሽ ሽንብራ? ( መች ~ መቼ) መቼ ገባህ ፊት፤ ምን በላህ ፍትፍት። መቼም አላለልኝ፥ ከ዗ሬ ቁዪልኝ። መቼም አላማረበት፥ እሪበት። መች ተጽፎ ትችት፤ መች ተወግዝ ሙግት። መነኰሴ በቆቡ፤ ወንበር በክታቡ። (በክታቡ ~ በክታብ) መነኰሴ ቤት ሲሠራ፥ ሀረግ ትሸሸጋለች። መነኰሴ ከአልሞተ፤ ስንዳ ከአልሸተ አይታወቅም። መነኰሴ ከደብሩ፤ አንበሳ ከደሩ ወጥተው ከአደሩ። መነዚነዝ ያመጣል መ዗ዝ። መነገድ ለማትረፍ፤ መማር ለመጻፍ። መናኝ ለነፍሱ፤ አዳኝ ለጥርሱ (ይገሰግሱ)። መናኝ ዳዋ ለብሶ፤ ጤዚ ልሶ፤ ድንጋይ ተንተርሶ (ይኖራል)። መናከስ ከአልቻልክ፥ ጥርስህን አታሳይ። መናጆ የላለው በሬ፤ ደበል የላለው ገበሬ። (ደበል ~ ለምድ) መናገር መልካም ነው፥ ማዳመጥ ይበልጣል። መናገር ሳያስቡ፤ ምላጭ መሳብ ሳያልሙ። መናገር ብር ነው፤ ዝምታ ወርቅ ነው። መናገር የለመደ ምላስ፤ መታገም የለመደ ራስ። መናፍቅ ለትር጑ሜ፤ ትንባሆ ለልምላሜ። መንቀጥቀጥ፥ እንደ ወላድ ምጥ። መንቻካ ሴት፥ አትሆንም ባለቤት። መንካት፥ ያደርሳል ከመነካት። መንዛ ራቱ በጊዛ፥ ምሳው ኹለት ጊዛ። መንዛ እንደሚለው፥ እስኪ ከቁርበቴ ልምከር። መንደር በልጆች፤ አገር በገበሬዎች። መንደር ከዋለ ንብ፤ አደባባይ የዋለ ዝንብ (ይሰለጥናል)። መንገደኛ ከሥንቁ፤ ነጋዳ ከወርቁ። መንገደ ዗ቀ዗ቀኝ ቢለው፥ ሱሪህን ተንተራሰው ብል መለሰለት። መንገደ፥ የተልባ ወጥ ይኹንልህ። መንገድ ለቀደመ፤ ውሃ ለገደበ። መንገድ ሳለ በደር፤ በቅል ሳለ በእግር። መንገድ፥ በሀሳብ አይደረስም። መንገድ በወሬ፤ ጠላ በአቦሬ። መንገድ በጠዋት፤ ሚስት በልጅነት። መንገድ ከሀገር ልጅ፤ ምክር ከጨዋ ልጅ። መንገድ ከሀገር ልጅ፤ ስደት ከሹም ልጅ። መንገድ ከመንገድ ያደርሳል። መንገድ ወጭ፥ ከላባ ቤት አብሮ ይኑር። መንገድ የምታውቅ አይጥ፥ ከፈረስ የበለጠ ትሮጣለች። መንግሥቴን የነሡ፤ ክብሬን የወረሱ። መንገድ፥ ከሽንት ይቀራል። መንግሥት አልሰማ ሲል ዓመታት፤ ሕዝብ አልሰማ ሲል ዕለታት። መንፈሱ አልበጀ፤ ውቃቢው ሰው ፈጀ። መንፈራገጥ ለመላላጥ። መኖሪያዋን ትታ መዝሪያዋን። መኖሪያውን ትተው መናገሪያውን። መኖር ማለት ብርሃንና መሰንበት። መኖር ማለት ብርሃንና መስተዋት። መኖር በከንቱ፥ ሰው አለቤቱ። መኖር በከንቱ፥ ያለ ባለቤቱ። መከራ ያልፋል፥ እስኪያልፍ ግን ያለፋል። መከራና አፈር፥ ቢዝቁት አያልቅም። መከራና ዕዳ፤ እንግዳና ሞት በድንገት። መከራና ጉም እያደር ይቀላል። መከራን መሸፈን፥ እግዛርን ማመን። መከራን የቻለ አሸናፊ ነው። መከራው ያላለቀለት በሬ፥ ከሞተ በኋላ ቆዳው ለነጋሪት ይጠፈራል። መከር ከአልተከተተ፤ መነኰሴ ከአልሞተ። መከበር በከንፈር። መከፈንና መሸፈን፥ እግዛርን ማመን። መካሪ የላለው ንጉሥ፥ አንድ ዓመት አይነግሥ። መካር አይጥፋ። መካር የላለው ንጉሥ፥ ያላንድ ዓመት አይነግሥ። መክሮ ልብ አይደል፤ አሟጭቶ ጥርስ አይደል። መክዳትና መኮብለል፤ ወድቆ መንከባለል። መክፈልት ሲሹ፥ መቅሰፍት። (መቅሰፍት ~ መቅለፍት) መኮርተሚያን ያላገኘ፥ መ዗ርጊያን ተመኘ። መኮርኮሚያ(ን) ያላገኘ፥ መ዗ርጊያን ተመኘ። መወለድ ቋንቋ ነው። መኼድ መነሣት፤ መከተል መሸኘት። መኼድ በጋ ነው፤ መቀመጥ ክረምት ነው። መኼድ የለ ዚቻ ብቻ፤ መሥራት የለ ሀሳብ ብቻ። መኼድ የለመደ፥ ቢቀመጥ ታከተው። መኼድ ያማረው፥ እራቱን በጨረቃ ይበላል። መኼድና መምጣት፤ ማግኘትና ማጣት። መኼጃ የላለው፤ መውጫውን ያበስራል። መሆን በሆነ፤ ዳሩ ግን ምን ይሆናል፤ አገርህ ሩቅ ሆነ። መለመን የለመደ ምላስ፥ በሕልሙ አቁማዳ ይዋስ። መላ እንደ ሴት፤ ግርማ እንደ ላሉት። መወለድ ካለ፥ ማ዗ን አይገድም። መዋቀስ መራከስ። መዋዕል ለፍስሓ፤ ዕድሜ ለንስሓ። መዋጋት ከድርጅት፤ መብል ከጠቦት። መዋጋት ያብሳል። መውረድና ማፍረስ ይቀላል። መውደደንስ አንተን እወዳለኹ፤ ኋላ ወዳት እገባለኹ? መውጫህን ሳታይ አትግባ። መዝሙር በሃላ፤ ነገር በምሳላ፤ ጠጅ በብርላ። መዝገብ ቢጠፋ ባገር፤ ቤት ቢላላ በማገር። መዝጊያ የላለው ቤት፤ ሴሰኛ ሴት። መዥገር፥ ቁም ነገረኛ እንዱባል፥ ቁርበት ላይ ተጣብቆ ይሞታል። መድረሻ ያጣ ደቄት፥ ከነፋስ ይጠጋል። መጀመሪያ ስሕተት፤ የኋለኛው እብደት። መጀመሪያ የመቀመጫዬን አለች ዝንጀሮ። መገናኛ ድንበር፤ መሳሳሚያ ከንፈር። መገን አንቺን ይዝ፥ ዗መቻ ነው ጉዝ። መገን ይህቺ ዓለም፥ የጀመራት እንጂ፥ የጨረሳት የለም። መገዝገዝ አያርድም። መጋኛና ዗በኛ አርፎ አይተኛ። መግረፉን ግረፍ ግን ከባት አትለፍ። መግነዝ ፍቱልኝ፤ መቃብር ክፈቱልኝ። መግዚት ቢያምርህ ችላ፤ ጥጋብ ቢያምርህ ጥላ። መ጑጑ት ያከሳል። መጠራጠር፥ ያደርሳል ከቁም ነገር። መጠንቀቅ መጠበቅ። መጠንቀቅ ከመለጠቅ። መጠየቅ ያደርጋል ሉቅ። መጠጊያ ያጣ ደቄት፥ ከነፋስ ይጠጋል። መጠጥ ለጨዋታ፤ ወንድም ለግርግርታ። መጠጥ ከጨዋ ልጅ፤ ምክር ከአገር ልጅ። (ከአገር ~ ከድሀ) መጠጥ የጨዋ ልጅ መጫወቻ፥ የባለጌ ልጅ መማቻ። መጠጥና ሴቶች፥ መምህራንን ያስቷቸዋል። መጣ ዝም ብል፥ ኼደ ተናግሮ። መጣደፍ መቸኮል፤ መረዋና ደወል። መጣፍ ከመከረው፤ መከራ የመከረው። መጣፍና ተማሪ፤ ቀለበትና ድሪ። መጥረቢያው የተውሶ፥ ጠፋ ተመልሶ። መጥኖ የሚበላ፥ ሰውነቱ ጤና። መጥፊያው፥ መልሚያው መስል፥ ይታየዋል ለሰው። መጥፎ ሣር፥ ይለመልማል እንጂ፥ አይጠፋም። መጥፎ ሴት ያገባ፤ በሬው በሠኔ ገደል ገባ። መጥፎ ሥጋ ከጥርስ፤ መጥፎ ነገር ከከርስ። መጥፎ ቁራኛ፥ ያለመቃብር አይለቅም። መጥፎ ወሬ ይበራል፥ መልካሙ ይተኛል። መጥፎ ወጥ፥ በጥሩ እንጀራ ይበላል። መጨነቅ፥ የመጠበብ እናት። መጫር ያበዚች ድሮ፥ የመታረጃዋን ቢላዋ ታወጣለች። መጫኛና ስልቻ። መጭ መጭ፤ ከሚሉት በቅል መጫሚያ። መጭ ብል ቢመጣ፥ ብር ብል ቀደመው። መጽሀፍና ተማሪ፤ ቀለበትና ድሪ። መፍረሱ ላይቀረኝ፤ ለምን ፈጠረኝ። መፍራት ለመታማት። መፍታት ሳለ መሞት። መ዗ዙን ሳታይ፥ መልኩን አይታ። መዚወሪያ ትተህ ብላ። ሙሉ ክረምት የአገለገለ፤ በመከር ሰፌድ ያቀበለ። ሙልጭ እንደ ሥብቆ፤ እንጣጥ እንደ ፌቆ። ሙሽራ ሳይዙ፥ ሰርገኛ። ሙሽራ በሚዛ፤ ንስሓ በትካዛ። ሙሽራ በሚዛ፤ ንስሓ በኑዚዛ። ሙሽራዋስ እኔ ድሮዋን ማን በላት ካለእኔ። ሙሽሮች ሲተዋወቁ፥ ምነው ሰርገኛው ልብ መውለቁ። ሙቅ በገንፎ ተደግፎ። ሙቅ ውሃና፥ የሰው ገን዗ብ አይጠቅምም። ሙት ለሙት፥ ያለቅሳል። ሙት መውቀስ፤ ድንጋይ መንከስ። ሙት ማንሣት፤ ዕውር ማብራት። ሙት፥ ምሥጢር አያወጣም። ሙት አይሰማም፥ አይለማም። ሙት፥ ወደ ሙት ይኼዳል። ሙት ይዝ ይሞታል። ሙት፥ ደረቅ አይበላም። ሙክት ሲሰባ ካራ ይታከካል፥ ባለጌ ሲከብር ያፎከፉካል። (ካራ ~ ከካራ፥ ያፎከፉካል ~ ይፎከፉካል) ሙዙን ሳላይ፥ መ዗ዙን። ሙዝ ላጥ፥ ዋጥ። (ሙዝ ~ ሙዙን) ሙያ በልብ። ሙግት ለአፈኛ፤ አቢቹ ለጌኛ። ሙግት ያውቃል ይለቃል። (ይለቃል ~ ይላቀቃል ~ ይልቋል) ሚስቱ ትሻል፥ ብይኗ ያመሻል። ሚስቱ ክፉ፥ ባቄላ እራቱ፥ ብሳና ዕንጨቱ፥ ኀ዗ን ነው እቤቱ። ሚስቱ ደግ፥ ስንዳ እራቱ፥ ወይራ ዕንጨቱ፥ ደስታ ነው እቤቱ። ሚስቱን ገድል፥ አማቱ ቤት ተሸሸገ። ሚስቱን ገድል፥ አማቱ ቤት ተደበቀ። ሚስቱን ጠልቶ ከአማቱ፤ ልጁን ከሶ ከአባቱ። ሚስቱን ጠልቶ፥ ከአማቱ ቤት ተሸሸገ። ሚስቱን ፈትቶ፥ ከአማቱ ቤት ተደበቀ። ሚስቴ እንደምትመኝልኝ እንጂ፥ እናቴ እንደምትመኝብኝ አትስጠኝ። ሚስት ሳታገባ ሀብት አፍራ፤ ልጅ ሳትወልድ ብላ። ሚስት በወቅቱ ከአልተገባ፥ አፈር አላባሽ እንጂ፥ ውሃ አጣጪ አትሆንም። ሚስት ባታብል፥ ባሎን ትወልዳለች። ሚስት ከፈቷት ባዳ፥ ማሽላ ከተቆረጠ አገዳ። ሚስት ፈትቶ፥ ከአማት መቀለብ፥ በእንፉቅቅ መኼድ። ሚስትህ አመዳም፤ ጎራዳህ ጎመዳም። ሚስትህ አረገ዗ች ወይ ቢለው፥ ማንን ወንድ ብላ አለው። ሚስትህን ስደድ፤ በሬህን እረድ ይላል የባለጌ ዗መድ። ሚስትና ዳዊት ከብብት። ሚስጥርህን ለባዕድ ለምን አዋየኸው፤ ወንፊት ውሃ ይዝ የት ሲደርስ አየኸው። ሚካኤል አትቀየመኝ፥ መጭውን ስቀበል ኺያጁን ስሸኝ። ሚዛ ቢከተል፥ አሽከር ይመስላል። ሚያ ባለ፥ ፍየል ከፈለ። ሚያ ባልኩ፥ ፍየል ከፈልኩ። ሚያዙያ ከተበላ፥ እናትና ልጅ ተባላ። ሚዳቋ ቀስ ብላ ስትኼድ፥ የተያ዗ች ትመስላለች። ሚዳቋ፥ እንደ አንበሳ እጮህ ብላ ተሰንጥቃ ሞተች። ሚዳቋ፥ ዗ላ ዗ላ ከመሬት። (ከመሬት ~ ከምድር) ማሕላት በግርግርታ፤ ዳዊት በቀስታ። ማለዳ የምትለቅምን ድሮ፥ ጭልፊት አትጠልፋትም። ማልደው ቢነሡ፥ እኩለ ቀን አይደርሱ። ማማት የለመደ አፍ፥ ሲያለግ ያድራል። (ሲያለግ ~ ሲድልት) ማማው ሞረት፤ ማሽላው ቅንቢቢት። ማማው ከጉልበት፤ ማሽላው ከዕንብርት። ማምሻም ዕድሜ ነው። ማሞ ላላ፤ መታወቂያው ላላ። ማሩን አመረረ፤ ወተቱን አጠቆረ። ማሩን አምርሮ፤ ወተቱን አጥቁሮ። (አምርሮ ~ አምሮ) ማር ሲሰፍሩ፥ ማር ይናገሩ። ማር ሲበዚ ይመራል፤ ነገር ሲበዚ ያጠፋል። ማር ሲበዚ ያስተፋል፤ ነገር ሲበዚ ያጠፋል። ማር ሲበዚ ጭቃ ነው። ማር ሲበዚ ይመራል። ማር ሸጦ ምን ይበሎል? ልጅ ጠልቶ ምን ይወዶል? ማር ሸጦ ምን ይገዞል? ልጅ ጠልቶ ምን ይወዶል? ማር በበላኹበት በጣፈጠው አፌ፥ ጎመን ጎረሥኩበት አይ አለማረፌ። ማር ቢሰጡት ወተት፤ ጠጅ ቢሰጡት ጠላ አሰኘ። ማር ባለበት፥ አያጡም ጉንዳን። ማር ነክቶታል ብለህ እጅህን አትላስ። ማር አገባ አገባ፥ ገደል ገባ። ማር የተሸከመች አህያ፥ ጣዕሙን አታውቀውም። ማርና ቅቤ ይጣፍጣሉ፥ ከየት ይገኛሉ? ማርና ንብ፤ ጽሕፈትና ንባብ። ማርና ወተት፥ ምን አገናኝቶት? ማርና ወዳጅ በልኩ ነው። ማርን መቁረጥ በጥቅምት፤ እህልን መቆጠብ በጥቅምት። ማርገዞን ልታስታውቅ፥ ከደረቷ ትታጠቅ። ማሰለፍማ ታውቃለህ፥ አትሰጥም እንጂ ከጠላህ። ማሰሮ ለድሮ፤ ገደል ለዝንጀሮ። ማሰሮ፥ ጀበናን ጥላሸት ትመስላለህ አለው አሉ። ማሳለፍማ ታውቃለህ፥ አትሰጥም እንጂ ከጠላህ። ማስካካት፥ እንደ ድሮ እንቁላል ጣይ አያደርግም። ማስጠንቀቂያም አትንሣኝ፤ መጠንቀቂያም አታድርገኝ። ማረፍና መራገፍ፤ እየበሉ መንገፍገፍ። ማሽላ ለማሽላ፥ ተያይዝ ቆላ። ማሽላ ሲያር ይሥቃል። ማሽላ ሲያር ይሥቃል፤ ትእቢተኛ ሲንደላቀቅ ይወድቃል። ማሽላ እየፈካ ያራል። ማሽላና ማሽላ ተያይዝ ቆላ። ማሽላና ነገር፤ ከአንገት ከአንገቱ። ማሽላና ዗ንጋዳ፤ መከታና ጑ዳ። ማቅ ለብሶ፤ አመድ ነስንሶ። ማቅ ያሞቃል፤ ሻሽ ይደምቃል። ማቅ ይሞቃል፤ ሻሽ ይደምቃል፤ የሚበጀውን ባለቤቱ ያውቃል። ማቅ ይሞቃል፤ ጋቢ ይደምቃል፤ ገቢውን ባለቤት ያውቃል። ማባበል መቅለል። ማባበልና ማንቆሻበል፤ (ማሞኘትና መደለል)። ማተብና አንገት፤ ክታብና ደረት። ማታ በግፍ የተከማቸ ገን዗ብ፥ ቀን ሲናድ ይውላል። ማነህ ባለ ሳምንት፤ ያስጠምድህ በአሥራ ስምንት። ማን ሉስማት? ታሞጠሙጣለች። ማኅበርህ ቀረ፤ ሤረኛህ ተሻረ (አይበሉህ)። ማሕፀን መዋኛ፤ ቤተ መቅደስ መገናኛ። ማን ሉስምሽ? ታሞጠሙጪያለሽ። ማን ላይ ቆመሽ? እግዛርን ታሚያለሽ። ማን ሙሽራ ቢልሽ? ት኱ያለሽ። ማን በልጅ ቆዳ ተቀብሯል? ማን ቢስምሽ? ታሞጨሙጭ፤ ማን ቢይዝሽ? ትሮጭ። ማን ቢስምሽ? ማሞጥሞጥሽ። ማን ቢስምህ? ታሞጠሙጥ። ማን ቢያሮጠኝ? ሱፋጭ ቆረጠኝ። ማን ቢያሮጥሽ? ሱፋጭ ቆረጠሽ። ማን አለ መርማሪ? አለ ፈጣሪ። ማን ያልነበረ? ማን ያልተቀበረ? ማን ያርዳ? የቀበረ፤ ማን ይናገር? የነበረ። ማን ያውራ? የነበረ፤ ማን ያርዳ? የቀበረ። ማን ያውራ? የነበረ፤ ማን ይጨፍር? የሰከረ። ማን ያውቃል? ባላገር፤ ማን ያጠብቃል? ማገር። ማን ያውቅ? አገር፤ ማን ያጠብቅ? ማገር። ማን ይሙት? ጠላት፤ ማን ይኑር? አባት። ማን ይስጥ? ወላጅ፤ ማን ይንሣ? ፈራጅ። ማን ይንገር? የነበረ፤ ማን ያርዳ? የቀበረ። (የቀበረ ~ የቀበር) ማንን ብዬ ድጌን ጦም኱ት። ማንን ታሸንፋለህ? ሚስቴን። ማንን ታሸንፋለህ? ቢሉት ሚስቴን አለ። ማንን ይዝ ጉዝ። ማን዗ራሽ ስትወለድ አፏን አሞጥሙጣ ነው፤ ለማኝ ግን እጁን አስቀድሞ። ማዕረገ ቢስ፤ እራቱ ገሚስ። ማእድ ጠፋና አንድ ላይ በላን። ማክሰኞ በሰኞ ይሥቃል። ማወቅ መላቅ፤ አለማወቅ መናቅ። ማወቅ እናውቃለን፤ ብንናገር እናልቃለን። ማውራት ነው ሴትነት፥ መሥራት ነው ወንድነት። ማውራት ነው ድህነት፥ መሥራት ነው ጌትነት። ማ዗ዝ ያማረው፥ ሱሪ ባንገት ላይ አውልቁ ይላል። ማየ ጎንደር ይፈሳል በሸንኮር። ማየት ከመልአክ፤ መቀበል ከአምላክ። ማዬ በቀጠነ፤ ቆልዬ ባረረ (ማሩኝ)። ማደሪያ በመሆኗ ሥጋ ነፍስን ትጨቁናታለች። ማዳኑንም ፈርተው፤ ምሬቱንም ጠልተው (እንዳት ይሆናል?)። ማጀት በ(አ)ጎረሠ፤ ደጃፍ በመለሰ። ማጀት ያጎረሠው፤ በራፍ የመለሰው። (በራፍ ~ ደጃፍ) ማጀት ያጠለቀው፤ ጉልቻ የላቀው። ማገር ላያቀብሉ፤ ቤት አስፋ ይላሉ። ማግባቱ ቀርቶብኝ፥ በታጨኹ። ማግኘት ማውጣትን ያስለምዳል። ማግኘት ማውጣትን ይመልሳል። ማግኘት በእድል፤ ሥራ በገድል። ማግኘትና ማጣት፥ ጆሮ ለጆሮ። ማጣት፥ ከሰማይ ይርቃል። ማጣትና ማግኘት፥ ጆሮ ለጆሮ ነው። ማጥፋት፥ በትንሿ ጣት። ማጭደም ገመደም፥ ከሣሩ ውስጥ ነው። ማፈር ከላለ ክብር። (የለ ~ የለም) ማፈር ከላለ፥ ክብርም የለ። ማፈር ከብዙ ነገር፥ አለማፈር በብዙ ነገር። (ያስጠይቃል ~ ይጠበቃል) ሜ ባልኩ፥ ፍየል ከፈልኩ። ሜዳ መራመድ ሳታውቅ፥ መሰላሉን መውጣት ማን አስተማራት። (መሰላሉን ~ መሰላል ~ ከመሰላል) ሜዳውም ያው፥ ፈረሱም ያው። ምለህ በክርስቶስ፤ ተገዝተህ በቄስ። ምሉ ክረምት ያገለገለ፤ በመከር ሰፌድ ያቀበለ። ምላሱ አይታጠፍም። ምላስ ቢጥም፤ ቀድ ይጠቅም። ምላስ የሰበረውን፥ ሺህ ወጌሻ ሉጠግን አይቻለውም። ምላስ ይቀባል፤ ጥርስ ይወጋል። ምላስ ይተባል፤ ጥርስ ይወጋል። ምላስና ጥርስ እን኱ን ይናከሳሉ። ምላጭ ለመላጫ፤ ጠፍር ለመለመጫ። ምላጭ ቢያብጥ፥ በምን ይበጡ? ውሃ ቢያንቅ በምን ይውጡ? ምላጭ ቢያብጥ፥ በምን ይበጣል? ውሃ ቢያንቅ በምን ይዋጣል? ምላጭ አበጠ፤ በምን ይበጡ? ጨው አለጠ፤ በምን ያጣፍጡ? ምላጭ አያብጥ፥ ያበጠውን ያፈርጥ። ምላጭን ምላጭ አይቆርጠው፥ ሰውን ሰው አይበልጠው። ምላጮች ቢያብጡ፥ በምን ይበጡ። ምላጭን ምላጭ አይቆርጠውም። ምሥጢር ሲያረጅ፥ አፋሳ ይሆናል። ምሥጢር ሲያረጅ፥ ወሬ ይሆናል። ምሥጢር ቢያረጅ፥ ይፋ ይሆናል። ምሥጢር ከቤት፤ ምክር ከጎረቤት። ምሥጢር፥ የባቄላ ወፍጮ አይደለም። ምሥጢር ይደበቃል፥ ወፍጮ አይደለም። ምስጥ ከምድር ውስጥ። ምሬት ትጥቁ፤ ወቀሣ ሥንቁ። ምርቅና ፍትፍት። ምርቅና ፍትፍት አይበላም። ምርት ከአላባ፥ ግዳይ ለሰለባ። ምርት ከገለባ፤ ግዳይ ከሰለባ። ምቀኛ፥ የኑሮ መጋኛ። ምሰሶ የመሀል፤ ዳኛ የወል። ምሳ ሲሰጡ ለእራት ትቶ፥ እራት ሲሰጡ ለምሳ ትቶ፥ ሀምላ ይመጣል ጎመን ጎትቶ። ምሳላ ዅሉ አንካሳ ነው። ምስለኔ፥ ዅን እንደኔ። ምስር መዝራት ሙያ ማጣት፥ አለ ጦጣ። ምስር መዝራት ሞያ ማጣት፥ አተር መዝራት ወይ ብልኀት አለች ጦጣ። ምስር ማብላት ሞያ ማጣት፥ አተር መብላት አቦ ብላት። ምስር እራቱ፤ ምስር ቢያጣ ሞቱ። ምስር ይሰብራል፤ ጑ያ ይመረራል። ምስርሽን በጥጥሽ። ምስር፥ ብልት ይቀስር። ምስክር ለበለጥ፤ አውድማ ለመለጥ። (ለበለጥ ~ ለበለጠ፥ ለመለጥ ~ ለመለጠ) ምስክር ላበለጠ፤ አውድማ ለመለጠ። ምስክር በበለጠ፤ ባቄላ ባፈጠጠ። (ባፈጠጠ ~ ከፈጠጠ) ምስክር ቢያድር ይለወጣል፤ ሽንፍላ ቢያድር ይመለጣል። ምስክር ከተጠራ፤ መሥዋዕት ከተራ። ምስክር ከተጠራ፤ መሥዋዕት ከተሠራ (አያድርም)። ምስክር ያለው ሙግት፥ አያዳግትም ለመርታት። ምሥጋና፥ አዋቂን ያበረታል፥ ቂልን ያሳብዳል። ምሥጋና፥ አዋቂን ያበረታል፥ ቂልን ያስረታል። ምሥጢረኛ ምላስ የለውም። ምቀኛ ይተክላል፤ ወዳጁን ይነቅላል። ምቀኛ ጠላቱን፤ ይተክል ራሱን ይነቅል። ምቾት በዕልልታ፤ ችግር በኡኡታ። ምነው ለወጡ፤ ጎጆ ቢወጡ። ምነው ሬሳ ይከብዳል ቢለው፥ አሳቡን በሰው ላይ ጥል ነው አለ። ምነው ቢገዙ፥ መድን ካበዙ። ምነው እናቴ፥ እንቁላል ስሰርቅ በቀጣችኝ። ምነው የማይሠራ ሰው ጥፍሩ ያድግበታል ቢለው፥ ጦሙን ሲያድር ጎኑን ለማከክ እንዳይቸግረው ነው አለ። ምነው? ስልብ ጠጉር አለማብቀሉ ቢለው፥ ኹለተኛ መላጨቱን ቢፈራ ነው አለ። ምነው? ጎማዳ ዕርሻ አይወድ ቢለው፥ ዗ሩን ላባ አሟጦ ወስድት ምን ያርግ አለ። ምናልባት ቢሰበር አናት፤ ቅቤ ሻ ለመተኮሻ። ምን ሲል ተጀምሮ? የአ጑ት አዥራሮ። ምናልባት፥ ቢሰበር አናት። ምን ሴት ብታውቅ፥ በወንድ ያልቅ። ምን በእግሩ ቢመጣ፥ በእጁ እንዳይመጣ አለ ዳኛ። ምን ቢለፈልፉ? ድካም ነው ትርፉ። ምን ቢቃጠሩ? ደረሰ ቀኑ። ምን ቢነግሡ? በእጁ አይካሱ። ምን ቢነግሡ? በገዚ እጅ አይካሱ። ምን ቢኖሩ ከመሬት፤ ምን ቢውሉ ከቤት። ምን ቢኖሩ? ከሞት አይቀሩ(ም)። ምን ቢኖሩ? ከአገር አይቀሩ። ምን ቢከማች? እንደ ውላችን። ምን ቢከማች? ዕዳው ለአንቺ። ምን ቢከፉ? ሀሳብ ነው ትርፉ። ምን ቢወቅሱ? በእጅ አይካሱ። ምን ቢወደ? ለየቅል ነው መንገደ። ምን ቢወደ? ባዕድን አይረደ። ምን ቢዋደደ፥ ለየቅል ነው መንገደ። (ለየቅል ~ እየቅል) ምን ቢያምሩ ሙሽራ አይሆኑ፥ ምን ቢያውቁ ዳኛ አይሆኑ። ምን ቢያስጠምደ በ዗ጠና፥ ቤቱ አይተው ቀጠና። ምን ቢያርሱ? ድንበር አያፈልሱ። (አያፈልሱ ~ አያፋርሱ) ምን ቢያውቁ ዳኛ አይሆኑ፥ ምን ቢያምሩ ሙሽራ አይሆኑ። ምን ቢጠም መንገድ፤ ምን ቢከፋ ዗መድ። ምን ቢያስጠምደ በ዗ጠና፥ ከቤት አይወጣ ቀጠና። ምን ቢያርሱ? እንደ ጎመን አይጎርሡ። ምን ቢጣፍጥ? ማር አይገኝም ካልገዙት። ምን ቢፈሩ? ከሞት አይቀሩ። ምን ቢፋቀሩ? አብረው አይቀበሩ። ምን ብታፈገፍጊ? ከግርጌ አታልፊ። ምን ብታፈገፍጊ? ከግርግዳ አታልፊም። ምን አይሰማ ጆሮ፤ ምን አይውጥ ጉረሮ። ምን እበላ ሲሉ እንግዳ፥ ምን እለብስ ሲሉ ዕዳ። ምን እናት? ታስጠላ ድመት። ምን የሰማ ቀን፥ ያብዳል ደንቆሮ። ምን ያመጣ ድሀ፤ ምን ያገሳ ውሃ። ምን ያመጣል ሠኔ፤ ምን ያመጣል ቦ዗ኔ። ምን ያመጣል ሠኔ፤ ምን ይሠራል ቦ዗ኔ። ምን ያምጣ ድሀ፤ ምን ያግሣ ውሃ። ምን ያስጠምደ በ዗ጠና፥ ቤቱን አይተው ቀጠና። ምን ያህል የተባለው ዝናብ፥ በሰማይ ደረቀ። ምን ይለሰልሳል ቢሉ ጉበት፤ ምን ይጠጥራል ቢሉ ሆድ። ምን ይሰማ ጆሮ፤ ምን ይውጥ ጐረሮ። ምን ይርቅ፤ ምን ይደንቅ። (ጥበብና ተአምራትህ) ምን ይበላል? ነጭ፤ ምን ይጠጣል? ጠጅ። ምን ይበሎል? ነጭ፤ ምን ይጠጧል? ጠጅ። ምን ይዝ? ይኼዶል ጉዝ። ምን ይዝ ጉዝ። ምንም ሴት ብታውቅ፥ በወንድ ያልቅ። ምንም በሙቱ፥ አራድማ ሸምቱ። ምንም ቢለፈልፉ፥ ድካም ነው ትርፉ። ምንም ቢበርደው፥ ቅቤ እሳት አይሞቅም። ምንም ቢታረስ በ዗ጠና፥ ቤቱን አይለቅም ቀጠና። (አይለቅም ~ አይስትም) ምንም ቢቸገሩ፥ ተበድሮ ጋሬዳ። ምንም ቢቸገሩ፥ አራድማ ሸምቱ። ምንም ቢከፋ ዗መድ፥ ምንም ቢጠም መንገድ። ምንም ቢሆን ሥር ነው እንጂ፥ እጢ አይደማም። ምንም ቢሆን ሥር እንጂ፥ እጢ አይደማም። ምንም ቢሆን ጉፋያ፥ ሥጋ ሥጋ ነው ብያ። ምንም ቢዋደደ፥ ባዕድን አይረደ። ምንም ቢያስጠምደ በ዗ጠና፥ ቤቱን አይስትም ቀጠና። ምንም ቢያጠምደ በ዗ጠና፥ ቤቱን አይተው ቀጠና። ምንም ቢጠብ መንገድ፥ ምንም ቢከፋ ዗መድ። ምንም ቢፈቀሩ፥ አብረው አይቀበሩ። ምንም ብቀጥን፥ ጠጅ ነኝ። ምንም ብቀጥን፥ ጠጅ ነኝ፤ ምንም ብደኸይ፥ ጨዋ ነኝ። ምንም ብታውቅ፥ ከዳኛ ጋራ አትሟገት። ምንም ብትኼጂ፥ እንዳት አደርሽ አንቺ? ምንም ብትሞቺ፥ እንዳት አደርሽ አንቺ? ምንም ብትፈጋፈጊ፥ ከግርግዳ አታልፊ። ምንም ብወድህ፥ በወንድሜ ግንባር ደም አልይብህ። ምንም ብደኸይ ጨዋ ነኝ። ምንም ብጠላው፥ በወንድሜ ግንባር ደም አልይበት። ምንም ያህል ቢበርደው፥ ቅቤ ፀሓይ አይሞቅም። ምንሽም ምንሽም አያምረኝ፥ ከመኼድሽ በቀር። ምንና ምን፥ ይተያያል ከካብ። ምንዝር ቢለቅ ላለቃ፤ አለቃ ቢለቅ ለሻለቃ። ምንጃር ጤፍ ተወቃ ቢሉት፥ ሸንኮራ ሆኖ፥ አይኔ ውስጥ እብቅ ገባ አለ። ምኞትና ጉም አይጨበጥም። ምከረው ምከረው፥ ባይሰማ(ህ) ንከረው። ምከረው ምከረው፥ እንቢ ሲል፥ መከራ ይምከረው። (ሲል ~ ቢል) ምከረው ምከረው፥ እንቢ ካለ፥ መከራ ይምከረው። ምከረው ምከረው፥ እንቢ ካለህ፥ መከራ ይምከረው። ምከረው ምከረው፥ እንቢ ያለ እንደሆን፥ መከራ ይምከረው። ምከረው ምከረው፥ እንቢ ያለ እንደሆን፥ በደላ ንከረው። ምከረው ምከረው፥ እንቢ ያለህን ሰው፥ መከራ ይምከረው። ምከር ዝከር በምድር፥ ልጄ ተመከር። ምኩራብ ግምጃ፥ ፈተለች፥ ቤተ ክርስቲያን ለበሰችው። ምክር ለሚሰማ፤ ውሃ ለቄጠማ። ምክር ተቀባይ ሲያጣ፥ ተመልሶ እቤቱ ገባ። ምክር ተቀባይ ሲያጣ፥ ተመልሶ ወደ ባለቤቱ ይመጣ። ምክር ከሽማግላ ነው፥ መሻገር ከወንዝ ነው። ምክር ከሽማግላ ነው፥ መሻገር ከጎበዝ ነው። ምክር ከድሀ ነበርሽ ማን ቢሰማሽ? ምክር የብልኅ፤ ሀብት የግልህ። ምክር የድሀ ነበርሽ፥ ማን ቢሰማሽ?( የድሀ ~ ከድሀ) ምክር ያልመለሰው፤ መከራ ደረሰው። ምክር ያልሰማ ንጉሥ አሟሟቱን ያረክስ። ምክርና ቡጢ፥ ለሰጪው ይቀላል። ምክርን መላልሶ፤ መብልን ለዋውሶ። ምክንያት እንደ ሴት፤ ግርማ እንደ ላት ይስጥህ። ምድር ለገበረ፤ ጦር ለወረወረ። ምዕራፍ ፲ << ቸ >> ምዕራፍ ፲፩ << ነ >> ምዕራፍ ፲፪ << አ፥ አ >> ምዕራፍ ፲፫ << ከ >> ምዕራፍ ፲፬ << ወ >> ምዕራፍ ፲፭ << ዗ >> ምዕራፍ ፲፮ << የ >> ምዕራፍ ፲፯ << ደ >> ምዕራፍ ፲፰ << ጀ >> ምዕራፍ ፲፱ << ገ >> ምዕራፍ ፳ << ጠ >> ምዕራፍ ፳፩ << ጨ >> ምዕራፍ ፳፪ << ጰ >> ምዕራፍ ፳፫ << ጸ፥ ፀ >> ምዕራፍ ፳፬ << ፈ >> ምዕራፍ ፳፭ << ፐ >> ምዕራፍ ፩ << ሀ፥ ሀ፥ ኀ፥ ኸ >> ምዕራፍ ፪ << ለ >> ምዕራፍ ፫ << መ >> ምዕራፍ ፬ << ሰ፥ ሠ >> ምዕራፍ ፭ << ረ >> ምዕራፍ ፮ << ሸ >> ምዕራፍ ፯ << ቀ >> ምዕራፍ ፰ << በ >> ምዕራፍ ፱ << ተ >> ምድር ሲደለደል፤ ማሳ ሲታደል ተወለድኩኝ አለ ጦጣ። ምድር በአለቃ፤ ሰማይ በጨረቃ። ምድር ሲደለደል፤ ማሳ ሲታደል። ምድር በወለደች፥ ነደደች። ምድር በዚፍ፤ ሕግ በመጽሀፍ። ምድር በድሮ፥ ያውስ ማን ገብሮ? ምድር በጭቃ፤ ሰማይ በጨረቃ። ምድር ከነልብሱ፤ ሰማይ ከነግሱ። ምጡን እርሺው፤ ልጁን አንሺው። (እርሺው ~ ርሺው) ምጣደ አንድ፤ ሴቱ ብዙ። ምጣድ አዳጠኝ፤ አክንባል ዳጠኝ። (ልጆች የሚሉት) ምጣድ ጥድ፤ እሳት ጠልቶ። ምጥ ለእናቷ አስተማረች። ምጥማጥና ድሮ አንድ ላይ ሰፈሩ፥ ቢቸግር ነው እንጂ መች አንድ ነበሩ። ምጥን፥ ለእናቷ አስተማረች። ምጽዋት፥ የዕለት እራት። ሞተ በለኝ፤ ከፈኔን አለ በለኝ ቀለቤን። ሞቱ በቀረና፤ በውል በኮነነኝ። ሞታንን ከማመስገን፤ ሕያዋንን ማስተንተን። ሞቴን ሞት ወሰደው። ሞት ላልቀረለት፥ ምክንያት ባልሆነበት። ሞት ላይቀር ፍራት፤ አመል ላይቀር ቅጣት። ሞት ላይቀርለት፥ ምክንያቱ በይሁዳ ሆነበት። (ሆነበት ~ ሆነለት) ሞት ሲደርስ ቄስ፤ ጦር ሲደርስ ፈረስ። ሞት ሲገድል፤ መቃብር ሲቀበል በቃኝ ጠገብኩ አይል። ሞት ርስት ነው፥ መፈራቱ ለምንድን ነው። ሞት በአቤል፥ ተዝካር በሮቤል (ተጀመረ)። ሞት በእንቅልፍ ይለመዳል። ሞት በጥር፥ በነሀሴ መቃብር (የማይመስል ነገር)። ሞት በጥር፥ በነሀሴ መቃብር፥ እንዳት ይሆናል? ሞት ቢ዗ገይ፥ ሲኦል ስለሞላ ነው። ሞት ቢ዗ገይ ነው የምኼደው። ሞት ቢ዗ገይ፥ የቀረ ይመስላል። ሞት ባልቀረለት፥ ምክንያት ባልሆነበት። ሞት አይለመድ፤ ጎሽ አይጠመድ። ሞት አይቀርም፤ ስም አይቀበርም። ሞት፥ እናት ይፈራል። ሞት የሰጠው፥ ቀባሪ አያሳጣውም። ሞትና ዕድሜ ቢፈሩት አይቀርም። ሞትን ማሰብ፥ ከዅሉ መሰብሰብ። ሞትን የሰጠ፥ ቀባሪ አይነሣም። ሞትን ያህል ዕዳ፤ መቃብርን ያህል እንግዳ። ሞትን ያመጣ፥ ቀባሪም አያሳጣ። ሞትህ እንደ ሕይወትህ፥ ሕይወትህ እንደ ሞትህ ነው። ሞትም ሞት ነው፥ የአህያ ጉበት ነው። ሞቶ የተነሣ፥ እግዛርን ረሳ። ( ሞቶ ~ ሞቶ) ሞቼ፥ ጉድ አይቼ። (:_ትርጉሙ ‹‹ሞቼ ፈጣሪ የሚለውን አይቼ!››) ሞኝ፥ ኹለት ጊዛ ይሥቃል። ሞኝ ለማደግ፥ ዝናብ አያስፈልገውም። ሞኝ ለራሱ ብልኅ ነው። ሞኝ ለራሱ ያውቃል። ሞኝ ለጠበቃው፥ ምሥጢር ይሸሽጋል። ሞኝ መርፌ ቢጠፋው፥ ጋን ይፈነቅላል። ሞኝ መካሪውን፤ ባለጌ አክባሪውን (አይወድም)። ሞኝ ሞኝ፥ አያውቁብኝ ባይ። ሞኝ ሰው የትናንቱን፥ ብልኅ የነገውን ያስባል። ሞኝ ሲሥቁ ቢያይ ይሥቃል። ሞኝ ሰው፥ ኹለት ጊዛ ይሥቃል። ሞኝ ሲሥቁበት፥ የሣቁለት ይመስለዋል። ሞኝ ሲረግሙት፥ የመረቁት ይመስለዋል። ሞኝ ሲቃጡበት፥ የመቱት ይመስለዋል። ሞኝ ሲናገር፤ ብልኅ ያደምጣል። (ያደምጣል ~ ያዳምጣል) ሞኝ ሲያከብሩት፥ የፈሩት ይመስለዋል። ሞኝ በብልኅ ይሥቃል። ሞኝ በእናቱ መውደቅ ይሥቃል። ሞኝ ቢመክሩት ከልማደ፤ አህያ ቢያጥቡት ከአመደ። ሞኝ ቢሥቁበት፥ የሣቁለት ይመስለዋል። ሞኝ ቢስቱት፥ የወጉት አይመስለውም። ሞኝ ቢቃጡበት፥ የመቱት ይመስለዋል። (ቢቃጡበት~ ሲቃጡበት) ሞኝ ቢቃጡት፥ የመቱት አይመስለውም። ሞኝ ቢቆጡት፥ የመቱት ይመስለዋል። ሞኝ ቢያድብር ብልኅ ይመስላል። ሞኝ ቢፈርደ፤ ሞኝ ይወልደ። ሞኝ ቢፈርደለት አያውቅ፥ ቢፈርደበት አያውቅ። ሞኝ ባያፍር፥ የሞኝ ዗መድ ያፍር። ሞኝ ባያፍር፤ ዗መደ ይነፍር። ሞኝ ቤት ቢሠራ፥ ብልጥ ይመራ። ሞኝ ተላላ፥ አበላል የት ያውቃል? በኋላ። ሞኝ ተናጋሪ፥ ክፉውን በፊት ደጉን በማምለጡ ይቆጨዋል። ሞኝ ነጋዳ፥ በራሱ መቀማት ሳያዝን፥ ጑ደኛው ቢሉ፥ እምቢኝ ብል። ሞኝ አሉ፥ ብልጥን አሸነፈው ምን ብል ሞኝ አሞራ፥ የአባቱን ዋሻ ይጠየፋል። ሞኝ አሳላፊ ለወንድሙ አይሰጥም። ሞኝ አሳላፊ፥ ወንድሙን ይጎዳል። ሞኝ አንዳጅ ግንደን በውስጥ፥ ጭራሮውን በላይ። ሞኝ አያውቁብኝ ባይ። (እንደመከሩት ~ እንደነገሩት) ሞኝ እንደ መከሩት፥ በቅል እንደ አሰገሩት። ይፈነድቃል። ሞኝ እከኩን እያየች ስትሥቅበት፥ ወደደችኝ ብል ሞኝ ከመካሪው ይጣላል። ሞኝ ከመውለድ፥ ማስወረድ። ሞኝ ከመካሪው፥ ዕውር ከመሪው (ይጣላል)። ሞኝ ከመውለድ፥ ፎናና መውለድ ይሻላል። ሞኝ ከሣቁለት፤ ውሻ ከሮጡለት። ሞኝ ከአመረረ፤ በግ ተበረረ አይመለስም። ሞኝ ከአመረረ፤ በግ ከበረረ (መመለሻ የለውም)። ሞኝ፥ ከአደገ ያስቸግራል። ሞኝ ከአገደደ፤ ልጅ ከለመደ። ሞኝ ከጠገበበት፥ አይወጣም። ሞኝ ወርውሮ ቢስቱት፥ የወጋኝ አይመስለውም። ሞኝ ወርውሮ ቢስት፥ የወጋ አይመስለውም። ሞኝ ወርውሮ ቢስት፥ የወጋ ይመስለዋል። ሞኝ ወታደር፥ ሚስቱን ጥል መንደር። ሞኝ ውሃ ሲወስደው ይሥቃል። ሞኝ የመከሩት ዕለት፥ ቁንጫ የጠረጉት ዕለት ይብሳል። ሞኝ፥ የተቆረጠ እሸት ይጠብቃል። ሞኝ የተከለውን፥ ልባዊ አይነቅለው(ም)። ሞኝ የዕለቱን፤ ብልኅ የዓመቱን (ያስባል)። ሞኝ የያ዗ው ብር፥ ለብልኅ ሥንቁ ነው። ሞኝ የያ዗ው ፈሉጥ፥ ውሻ የያ዗ው ሉጥ። (የያ዗ው ~ የደፈረው) ሞኝ ያገኘው ፈሉጥ፥ ውሻ ያገኘው ሉጥ። ሞኝ ይሥቃል፤ ብልኅ ያለቅሳል። ሞኝ ይጸድቃል ከማለት፥ በመርፌ ቀዳዳ ግመል ይሾልካል ብል ማሰብ ይሻላል። ሞኝ ይጸድቃል፤ ገለባ ይበቅላል ማለት ከንቱ ነው። ሞኝ ይጸድቃልን፤ ገለባ ይበቅላልን። ሞኝ ገበሬ ሹሩባ ይሠራል። ሞኝ ጎረምሳ፥ ሚስቱን ቆሞ ያሳድራል። ሞኝ ጎረምሳ፥ ሚስቴን ቅመሱልኝ ይላል። ሞኝ ጠጉርህ አደገ ቢሉት፥ የጸደቀ ይመስለዋል። ሞኝ:_ ጦር ወርውሮ ቢስት፥ የወጋ አይመስለውም። ሞኝ ፈረስ ቢጠፋው፥ ኮርቻ ገልቦ አየ። ሞኝ ፈትፍተው ሲያጎርሡት መዋጥ ያቅተዋል። ሞኝና መተሬ ይመራል። ሞኝ ዗መድ ከልጅህ እኩል አድርገኝ ይላል። ሞኝ ዝም ሲል፥ አዋቂ ይመስላል። (ሲል ~ ቢል) ሞኝ የላኩትን አይረሳም። ሞኝ፥ ሠኔ በጋው፥ መስከረም ክረምቱ ነው። ሞኝ ሰው፥ ኹለት ጊዛ ያለቅሳል። ሞኝ፥ ከመካሩ ቤት እሳት አይሞቅም። ሞኝ፥ ከተራራ ያደክማል። ሞኝና ብርድ ያስቃል። ሞኝና ወረቀት የያዙትን አይለቁም። (የያዙትን ~ ያስያዙትን) ሞኝና ወረቀት የያ዗ውን አይለቅም። ሞኝና ወረቀት፥ ሉደራደሩ ነው። ሞኝና ወረቀት፥ ኢንተርኔትን ናቁ። ሞኝና ወፍራም፥ ራሱን አያውቅም። ሞኝና ውሃ፥ እንደ ወሰደት ይኼዳል። ሞኝና የመስኖ ውሃ፥ በመሩት ይኼዳል። ሞኝና ጉታ እንዳይንገላታ። ሞኝን ለሣቅ፤ ስልቻን ለሥንቅ። ሞያ የለ፤ መልክ ብቻ። አመል የለ፤ ነገር ብቻ። አስቸጋሪ ለጋብቻ። ሞፈር ቆራጭ፥ ዕርፍ አይታየውም (በግላጭ)። ሠኔ ለብቻው። ሠኔ መቃጠሪያ፤ ኅዳር መገናኛ። ሠኔ ሠላሳ፤ የሴቶች አበሳ። ሠኔ ሠላሳ፤ የለውም ካሳ። ሠኔ ሲመጣ፤ ድግር ቆረጣ። ሠኔ፥ ነግ በእኔ። ሠኔ አቆለቆለ፤ በግማሽ እንጀራ ጎመን ተቆለለ። ሰንበላጥ ለቤት፤ ቀሚስ ለሴት። ሠኔና ሰኞ ሆነበት። ሠኔና ሰኞ። ሠኔን በ዗ራ዗ር፤ ሀምላን በጎመን዗ር። ሣር ማጨድ በማጭድ፤ ቤት መምረግ በጭቃ በጭድ። ሣር ሲበቅል፥ ፈረስ ይሞታል። ሣር ያልሰጧት ላም፥ ወተት አምጪ ቢሎት አትሰጥም። ሣር ይሸከሟል ለበሬ፤ ቆንጆ ያገቧል ለወሬ። ሣቂታ ሰፊታ። ሳቃዳው ፈሰሰ። ሣቅ ሲበዚ፥ ለቅሶ ይሆናል። ሣቅ ያበዚ ይቀላል፤ ዝምታ ያበዚ ይከብዳል። ሳቢውን ግረፈው። ሥሡ መ጑጑ቱን፤ ቆዳ መንጋጋቱን (አይተውም)። ሥሡ ሲበላ ይታነቃል፤ ሀሰተኛ ሲናገር ይታወቃል። (ሲናገር ~ በአነጋገሩ) ሥሡት፥ የእናቷን አትስት። ሥሡ አንድ ያንቀው፥ አንድ ይወድቀው። ሥሥታም ሲበላ ይታነቃል፤ ሀሰተኛ ሲናገር አፉ ሞቅ ሞቅ ይላል። ሥሥታም ሲበላ ይታነቃል፤ ሀሰተኛ ሲናገር ይታወቃል። ሥሩን የጠላ፥ ራሱን የጠላ። ሥራ ለሠሪው፤ ምርጫ ለመራጭ። ሥራ ለሠሪው፤ እሾህ ላጣሪው። ሥራ ለሠሪው፤ ወሬ ላውሪው። ሥራ ስፈታ፥ ልጄን ላፋታ። (ስፈታ ~ ከምፈታ) ሥራ ከመፍታት፥ ልጄን ላፋታት። ሥራ ከመፍታት፤ ምርጫ መወዳደር። ሥራ ከመፍታት፤ ፓርላማ መግባት። ሥራ ከሚፈቱ፥ አፍዎን ያፍታቱ። ሥራ ከአልሠራችኹ፥ የት ሉገኝ ምሳችኹ? ሥራ የፈታ ቄስ፥ በአህያ ፍታት ይውላል። ሥራ ያጣ ለማኝ፥ አፍሶ ይለቅማል። "ሥራ ያጣ መነኰሴ ""አደገኛ ቦ዗ኔ"" ተብል ታሰረ። ሥራ ያጣ መነኰሴ፥ የምርጫ ቅስቀሳ ጀመረ። ሥራ ያጣ፥ ሙቅ ያኝካል።" ሥራ ያጣ መነኰሴ፥ ቆቡን ቀድ ይሰፋል። ሥራ ያጣ መነኰሴ፥ አደገኛ ቦ዗ኔ ተባለ። ሥራ ያጣ ቄስ፥ ቆቡን ቀድ ይሰፋል። ሥራ ያጣ ገበሬ፥ በሠኔ ይሞታል። ሥራ ያጣ ገበሬ፥ ይሞታል በሠኔ። ሥራ ያጣ ገበሬ፤ ጨው የላለው በርበሬ። ሥራ ያጣ፥ ገንፎ ያላምጣል። ሥራ ያጣ ጢስ ይሞቃል። ስትሠራ ውላ፥ አበላሸችው ባተላ። ሥራ ያጣ፥ ሚስት ያወጣ። ሥራ ያጣ፥ ጢስ ይሞቃል። ሥራ ያጣች አፍ፥ ሞት ትጠራለች። ሥራ ጠፍቶ፥ ጢስ ይሞቃል። ሥራ ጣፋጭ ናት፥ ችግሩ ግን እኔ ስ኱ር በሽተኛ ነኝ። ሥራ ፈት ሲመለከት፥ ላም ነው። ሥራስ ጥሩ ነበር፥ ሥራችንን ይሻማብናል እንጂ። ሥራን ለዚሬ፤ መብልን ለነገ። ሥራን ሲፈልጉ፥ ጉልበትን አያባልጉ። ስርቆት የሚለመድ፥ ማጀት የገቡ ዕለት። ሥርአት ያናግራል፥ እርቅ ያፋቅራል። ሥብ ያርደ፤ ጉፋያ ይነደ። (ያርደ ~ ሉያርደ) ሥንቁን የተቀማ ነጋዳ፥ ዋግ የመታው ስንዳ። ሥንቃችን በልባችን፥ አለ አሞራ። ሥንቅ ሳይጎደ። ሥንቅ ያለው ጦም አያድር፤ ዋስ ያለው አይታሰር። ሥንቅ ያለው ጦም አያድርም፤ ዋስ ያለው አይታሰርም። ሥንቅህን በአህያ፤ አመልህን በጉያ። ሥንቅና ማሕላት እንደ ያዢው ነው። (ያዢው ~ ያዥው) ሥንቅና ውሸት እያደር ይቀላል። ሥጋ (ሰውነት)ከነፍስ፥ ልብስ ከምግብ ይበልጣሉ። ሥጋ ሰጥተው፥ ቢላዋ ነሡ። ሥጋ ለሥጋ ነው። ሥጋ ለአንበሳ፤ ወተት ለእንቦሳ። ሥጋ ለጥጋብ፤ አጥንት ለትካዛ። ሥጋ ምረጥ ቢሉት፥ ጣፊያ። ሥጋ ሲያመልጥህ፥ በቆዳው ታጠቅ። ሥጋ ቀረ፤ ዕዳ ቀረ። ሥጋ ቀርቦለት፥ አይኑ ወደ ፈርስ። ሥጋ ቁጠር ቢሉት ጣፊያ (አንድ አለ)። ሥጋ በአዋዛ፤ ቄስ ለኑዚዛ። ሥጋ በገበታ፤ ሹመት በተርታ። ሥጋ ቢወድቅ፥ አፈር ይዝ ይነሣል። ሥጋ ከመሬት ወድቆ፥ አፈር ሳይዝ አይነሣም። ሥጋ ከሥጋ ነው። ሥጋ ከነፍስ፤ ልብስ ከምግብ ይበልጣሉ። ሥጋ የአሳማ፥ እን኱ን ለበላው፥ የሰማው ገማ። (ለበላው ~ ከበላው) ሥጋ ያማረው፤ መረቅ የሸተተው ከበጎች መሀል ገብቶ ይተኛል። ሥጋ ያማረው፤ መረቅ የሸተተው በበጎች መካከል ዝግ ብል ይተኛል። ሥጋ ያማረውን ል኱ንዳ አትውሰደው። ሥጋ ያንገፈገፈው፥ ቀይ በሬ ሲያይ ይሸሻል። ሥጋም፥ እጅግ ፍርሀቱን አበዚው፥ በመንቀጥቀጥ። (በመንቀጥቀጥ ~ በመጠንቀቅ) ሥጋና ሴት፥ በባለጌ ቤት ይረክሳል። ሥጋን ከጥሬው፥ ነገርን ከወሬው። ሥጋው የአሳማ፥ እን኱ን ለበላው፥ ለሰማው ገማ። ሥጋው የአሳማ፥ ከበላው የሰማው ገማ። ሥጋውን እጦማለኹ፥ ከመረቁ አውጣልኝ። ሥጋውን ጠልቶ፥ መረቁን። ሥጋዬን ለአራዊት፤ ነፍሴን ለገነት። ስጋጃና ወላንሳ። ሦስት ጉልቻ ይስጥህ። ሦስት ጉልቻ ይቅጣሽ። ሦስት ጊዛ ለካ፥ አንድ ጊዛ ቅደድ። ሦስት ጊዛ ሰላምታ፥ አንደ ለነገር ነው። ሦስት ጊዛ እንዳት አደራችኹ፥ አንደ ለነገር ነው። (እንዳት አደራችኹ:_ ሰላምታ) ረመጥን የሚያውቃት፥ የረገጣት። ረባዳ ቤቱ፤ ገራም ሚስቱ። ረኃብ ይከላል ባቄላ፤ ቀን ያሳልፋል ነጠላ። ረኃብ ይከላል ባቄላ፤ ከመልካም ያደርሳል ነጠላ፤ ጠላት ይገፋል ዱቃላ። ረኃብ ይከላል ባቄላ፤ ከእጥፍ ያደርሳል ነጠላ። ረኃብ ይከላከላል ባቄላ፤ ከእጥፍ ያደርሳል ነጠላ። ረኃብ ይከላከላል ባቄላ፤ ጠላት ይገፋል ዱቃላ። ረኃብ ይከላከላል ባቄላ፤ ጥቃት ያወጣል ዱቃላ። ረኃብ ይከፍላል ባቄላ፥ ደም ያወጣል ዱቃላ። ረኃብን ባለቤቱ ያውቀዋል፥ ማን ይጠይቀዋል? ረኃብን የማያውቅ፥ ለተራበ አያዝንም። ረኃብን ያማርራል ሰው፥ ቁንጣንን ባይቀምሰው። (ባይቀምሰው ~ ያልቀመሰው) ረጂም እንትን፥ (የወንድ እቃ) ከአንድ ቀን በኋላ አይበልጥም። ረጅሙን ባላማ፤ አጭሩን በጫማ። ረጅም ባይፈራ፤ አጭር ባይኮራ። ረጅም ጦር፥ ባይወጉበት ያስፈራሩበት። ረጅም ጭራ፥ ከጎረቤት ያጣላ። ረጅምና ቀፋፋ፤ ገደልና ፈፋ። ሩቅ አሳቢ፤ ቅርብ አዳሪ። ሩቅ አገር፥ ለውሸት ይመቻል። ሪዝና ካባ ለግርማ። ራሔል፥ ኺጅ ቶል ቶል። ራሱ ጋባዥ፥ ራሱ ተጋባዥ። ራሱን ለተላጨ፤ ፊቱን ለተነጨ። ራሱን ከፍ ከፍ ያደረገ፥ ዝቅ ዝቅ ይላል። ራሱን የማይችል አንገት፥ ባለቤቱን የማያስገባ ቤት። ራሱን ዝቅ ዝቅ ያደረገ፥ ከፍ ከፍ ይላል። ራሴ ሸብቷል ወይ ቢለው፥ እፊትህ ስጥልልህ እኔን ምን ትጠይቀኛለህ አለው። ራሴን መተው፥ እግሬን ቢያሻሹኝ መች ይገባኛል። ራሴን መትቶ፥ እግሬን ቢያከኝ አይገባኝም። ራሴን ሲበላኝ፥ እግሬን ቢያኩኝ አይገባኝም። ራሴን እኔ፥ ከአላቆላመጥኹት ማን ያቆላምጥልኛል? ራስ ሲመለጥ፤ ነገር ሲያመልጥ (አይታወቅም)። ራስ ሳይጠና፥ ጉተና። ራስ ተላጭቶ ወለባ፥ ልባልባ ታጥቆ አዚባ። (ልባልባ ~ ልባልማ) ራስ ተከናንቦ፤ ሙርጥ ገልቦ። ራስ ከተመለጠ፤ ነገር ከአመለጠ። ራስ ከአለበት፥ እግር ይሰበሰባል። ራስ ከአዋለ፤ ለምድ አይገድም። ራስ ከዋለ፤ ለምድ አይገድም። ራስ ከዋለበት፥ እግር ይሰበሰባል። ራስ ወዳድ ባላባት፤ የጭሰኛውን ጋቢ (ለ)ሸንጎ ይለብሳል። ራስ ያለ አንገት፤ ጽድቅ ያለ እውነት። ራስ ይሸብታል እንጂ፥ ልብ አይሸብትም። ራስና ምላስ፥ ከዅሉ ይደርሳል። (ይደርሳል ~ ይደርስ) ራስን ሳይዙ፤ ወዳጅ አያበዙ። ራስን ተከናንቦ፤ ሙርጥን ገልቦ። ራስን አይችል በድጋፍ፥ ኋላም ለጉድፍ። (ለጉድፍ ~ በጉድፍ) ራስን ይዝ፤ ልጅን ልጅን ይዝ ወዳጅን። ራሷ ለኩሳ፥ ታይቶኛል ቤት ይቃጠላል አለች እብዱቷ። ራቁቱን ለተወለደ ልጅ፥ ለምድ አነሰው ወይ። ራቁቱን ለተወለደ (ልጅ)፥ ጥብቆ መች አነሰው። ራት ሲበሉ፥ የመጣ እንግዳ እራቱ ፍሪዳ። ራት ሲበሉ የመጣ፥ ይቆጠራል ፍሪዳን እንዳመጣ። ራት በዳረጎት አይለወጥም። ራት ቢንቁ አንድ እጅ ይለቃለቁ፤ ዳኛ ቢንቁ ከመከራ ይወድቁ። ራት ቢንቁ አንድ እጅ ይለቃለቁ፤ ዳኛ ቢንቁ የተያ዗ እህል ይወቁ። ራት የለህም ቢሉት፥ ከወጡ አውጡልኝ አለ። ራት የለው፤ ምሳ አማረው። ራት የላት፤ ምሳ አማራት። ራት የላለው ቄስ፥ እንደ ልቡ አይቀድስ። ራት የላለው ቄስ፥ ከልቡ አይቀድስ። (ከልቡ ~ ከልብ) ራት የላላት፤ ምሳ አማራት። ራት የላላት ደግሞ ምሳ አማራት። ራት፥ የሰማይ መብራት። ራትና መብራት፤ አማትና ምራት። (:_አይስማሙም) ራትን ቢንቁ፥ አንድ እጅ ይለቃለቁ። ራትን ቢንቁ፤ አንድ እጅን ይለቃለቁ ዳኛን ቢንቁ ከመከራ ይወድቁ። ራዚ የት ትኼዳለህ? ከአንተ ጋራ። ሥንቅህሳ? አንተሳ? ራድ ከቅምጥ ይፈነቅላል። ሬሳ በምኑ ይከበራል? በዝምታው። ሬሳ በምን ከበደ? ሀሳቡን በሰው ጥል። (በሰው ጥል ~ በሰው ላይ ጥል) ሬሳ በአልጋ፤ ጥሬ በመንጋጋ። ሬሳ በዝምታው ይፈራል። ሬሳ የሳመ ሰው ይመስል ልብህ ጠፍቷል። ሬት ለቀመሰው እንጂ፥ ላልቀመሰው አይመርም። ሬትን ያልቀመሰ፥ የማርን ጣዕም አያውቅም። ርስት በሺ ዓመቱ፥ ለባለቤቱ። ርስት በሺ ዓመቱ፥ ይመለሳል ለባለቤቱ። ርስት ያዳግማል፤ አቀበት ያደክማል። ርካብ ሳይረግጡ ኮር። ርጅና ብቻህን ና፥ የአንተ ተከታዮች ብዙ ናቸውና። ርጉዝ ላም ያለው ሰው፥ ደረቅም አያንቀው። ርጅና ብቻህን ና። ርጉዝ ሲያርደ፤ በወዳጅ ይፈርደ፤ ሆድ መርበድበደ። ርግማን ያነሰው፥ ገበያ ይፈሳል። ርግማንና ምርቃት፥ ከአንድ አፍ ይወጣሉ። ርግብን ስትበላት፥ ቆቅ ነች ብለህ ጥራት። ርጥቡ ሬሳ፥ ደረቁን አስነሣ። (አስነሣ ~ ያስነሣ) ርጥብ ቅል፥ ክብደቱ እስኪደርቅ ነው። ርጥብ ከደረቅ ይነዳል። ሮሮ የማይመረው፤ ኮሶ የማያሽረው የለም። ሮቃ የዝኆን አለቃ፥ ለምሳር አይበቃ። ሯጭ፥ መንገድ ቆራጭ። ሯጭና በራሪ፤ ንፉግና ፈሪ። ሰለሞን ሳባን ውሃ ባያስጠማት ኖሮ፥ የሱ ጥም ባልበረደ ነበር። ሠላ ብል ገብቶ፥ እቤቴ ቀረ ተንሰራፍቶ። ሰላላ መላላ። ሰላም ሰላም ለቅኔ ሰራቂ ናሁዳ፥ ዳር ዳሩን ኮርመም መሀሉን ሳይጎዳ። ሰላም ሰው፥ በርበሬ አይሰርቅም። ሰላምን ከፈለግህ ለውጊያ ተ዗ጋጅ። ሠላሳ ቢታለብ፥ እኔ በገላ አለች ድመት። ሰመረ ካሉ፥ ግብሩን ያሳያሉ። ሰሚ ልብ ነው፥ ጆሮማ ቅጠል ነው። ሰማኹት ያሻማል፤ አየኹት ያመሳክራል። ሰማህ? አልሰማኹም። አየህ? አላየኹም። ሰማንያ ለማገጃ፤ ስለት ለማረጃ። (ስለት ~ ብረት) ሰማንያ አንድ መጽሀፍ ከተማረው፥ መከራ የመከረው ይሻላል። ሰማንያ የጎሰመው። ሰማዩ ንጉሥ እስኪረዳ፥ የመሬቱ ንጉሥ ይጎዳ። ሰማይ ላይ፥ ጤፍ ይወቃል ቢሉት፥ እብቁ ዓይኔ ገባ አለ። ሰማይ ምን ይርቅ፥ መንገደኛ ምን ይጨነቅ። ሰማይ ሲጠና፤ ምድር ሲቀና። ሰማይ በመብረቅ ይታረሳል፤ ውሃ በምንቸት ይጠበሳል፤ አባት በወንጀል ይከሰሳል። ሰማይ ቢያኩ፤ ጤፍ ቢለኩ (አይደረስም ልኩ)። ሰማይ ብልጭ፤ ወፍ ጭጭ። ሰማይ ተቀደደ ቢሉት፥ ሽማግላ ይሰፋዋል አለ። ሰማይ አለ ደመና ብረት፤ ቤት አለ ሴት መሠረት። (አለ ~ ያለ) ሰማይ አትረስ፤ ንጉሥ አትክሰስ። ሰማይ አያርሱ፤ በአፍ አይለግሱ። ሰማይ አይላጥ፤ የሦስት ፍርድ አይለወጥ። ሰማይ አይታረስ፤ ንጉሥ አይከሰስ። ሰማይ አይታረስ፤ ንጉሥ አይከሰስ፤ ውሃ አይጠበስ፤ አባት አይከሰስ። ሰማይ አይታረስ፤ እርኩስ አይቀደስ። ሰማይ አገሬ፤ ምድር ወንበሬ። ሰማይ ከነዳመናው፤ ምድር ከነጉተናው። ሰማይ ከነጉሙ፤ ምድር ከነልብሱ። ሰማይ ከነግሱ፤ ምድር ከነልብሱ። ሰማይ ያለ ዳመና ብረት፤ ነገር ያለ ዳኛ ተረት። ሰማይ ይናዳል ብል፥ ባላ ተከለ። ሰማይ ይወድቃል ብላ፥ ምሰሶ ይዚ ቆመች። ሰማይን ያህል አገር ባገኘኹ ቢለው፥ ኮከብን ያህል ቀላዋጭ አለበት አለው። ሰማይን ያህል አገር ባገኘኹ ቢለው፥ ኮከብን ያህል በላተኛ ያዝብሀል ሰምቶ መቻል፥ ለእግዙሄር ይመቻል። ሰምቶ ዝም፥ አይቶ ዝም (በሆድ ያለ አይነቅዝም)። ሰምቶም ዝም፥ አይቶም ዝም፥ ወይ የምድር ሰው፥ በሆድ ያለ አይነቅዝም። ሰምና ወርቅ፤ እንጀራና መረቅ። ሰምና ፈትል ካልተዋሀደ፥ ብርሃን የላቸውም። ሰምና ፈትል ካልተዋሀደ፥ አያበሩ። ሰረቅህ የጉም ላባ፥ ጉም ሲለቅ የታባትህ ትገባ። ሰረቅህ የጉም ላባ፥ ጉም ሲለቅ የት ትገባ። ሰርቆ ከማሰብ፥ እጅን መሰብሰብ። ሰርቆ የጉም ላባ፥ ጉም ሲለቅ የት ሉገባ። ሰርገኛ መጣ፤ በርበሬ ቀንጥሱ። ሰርገኛ ሳይመጣ፤ ሙሽሪት ትመጣ። ሰርገኞች መጡ፤ ብቅል አስጡ። ሰርገኞች ደረሱ፤ በርበሬ ቀንጥሱ። ሰርጉን ተዝካር ትለዋለህ። ሰርግ አላፊ ነው፤ ቪዱዮ ቀሪ ነው። ሰሳ፥ የእናቷን አትረሳ። ሰባ ዓመት ከመደንቆር፥ ሰባት ዓመት መማር። ሰባ እንረደው፤ ጎፈየ እንስደደው። ሰባት ቀን አልችል፥ ያለ ሰባት ዓመት ተሸከመ። ሰባት ዓመት ባይማሩ፥ ሰባ ዓመት ይደንቁሩ። ሰባት ወልድ አቃቢትነት። (ወልድ ~ ወልዳ) ሰባት ጊዛ እንዳት ዋላችኹ? አንደ ለነገር ነው። ሰባት ዓመት እንዳይማሩ፥ ሰባ ዓመት ይደነቁሩ። (ይደነቁሩ ~ይደናቆሩ) ሰባት ዓመት የታወረ ሰው፥ ነገ ትድናለህ ቢሉት፥ ዚሬ እንደምን አድሬ አለ። ሰባት ዓመት የታወረ ዕውር፥ ነገ አይንህ ይበራል ቢሉት፥ ዚሬ እንደምን አድሬ አለ። ሰባኪ መፈለጉ ለሰሚ፥ መርፌ መፈለጉ ለጠቃሚ። ሰነፍ ሰው ሥራውን ትቶ፥ ነገር ሲያኝክ ይውላል። ሰነፍ ሰው ናቂ፥ ሞኝ ሰው ሣቂ። ሰነፍ ሲኮራ፥ ማጭድ ይታጠቃል። ሰነፍ ሳል ያበዚል። ሰነፍ ሳይከብር ይሞታል። ሰነፍ ሴት የአገባ፥ በሬው በሠኔ ገደል የገባ። ሰነፍ ሥራ ሲያይ፥ ወደ ጎን ይኼዳል። ሰነፍ በዓል ያበዚል። ሰነፍ ሴት፥ እድል የላትም ለንብረት። ሰነፍ ሴት ያገባ፥ በሬው በሠኔ ገደል ገባ። ሰነፍ ቢመክሩት፥ ውሃ ቢወቅጡት። ሰነፍ እረኛ ከሩቅ ይመልሳል። ሰነፍ ከመውለድ፤ ይሻላል መጨንገፍ። ሰነፍ ከመውለድ፤ ይሻል መጨንገፍ። ሰነፍ የድባ፤ ላም የጋለሞታ። ሰነፍ ይጸድቃል ቢለው፥ ገለባ ይበቅላል ወይ አለው። ሰነፍ ገበሬ በመስከረም ያርማል። ሰነፍ ገበሬ፥ በሠኔ ይሞታል። ሰነፍ ጸሀፊ፥ ከሙሴ ይገድፋል። ሰነፍ ገበሬ፥ ክረምት፥ በጋው ክረምቱ። ሰነፍ ገበሬ፥ ዱቪ ይሞላል። ሰነፍ፥ ሰው ያሰንፋል። ሰነፍና አጋራ፥ ራሱን ሲነቀንቅ ይኖራል። ሰነፍና ዋንጫ፥ ከወደ አፉ (ይሰፋ)። ሰነፍን ከመውለድ፥ ይሻላል ማስወረድ። ሰናፍጭ ትቀምሽ፥ ተልባ መስልሽ። ሰንበላጥ ለቤት፤ ቀሚስ ለባለቤት። ሰንበት ሲጠም፥ ከአርብ ረቡዕ ይብሳል። ሰንበት ከእለታት፤ ሰው ከፍጥረታት (ይበልጣሉ)። ሰኞ የወጣ ስም ማክሰኞ አይመለስም፤ (አንዳ የተተፋ ኹለተኛ አይላስም)። ሰአሉ በስዕሉ፤ ፈጣሪ በፍጡሩ። ሰካራም፥ ቤት አይሠራም። ሰካራም፥ ዋስ አያጣም። ሰክሮ ከጌታ መገናኘት፤ ከሹመት መለየት። ሰው ለአማኙ፤ እግዙአብሔር ለለማኙ። ሰው ለአማኙ፤ እግዛር ለለማኙ ሞኝ። ሰው ለወደደው፥ ዗ንጋዳ ጤፉ ነው። ሰው ለወዳጁ፤ መኮንን ለጠጁ። ሰው ለወዳጁ፥ ጫጩት ያርዳል። ሰው መሳይ በሸንጎ። ሰው መስልኝ፥ ድንጋይን ቆነጠጥኹ አለ የሰለቸው። ሰው መታፈሩ፥ በከንፈሩ፤ መሬት መከበሩ፥ በድንበሩ። ሰው መኖሩ ለመከበር፤ የመሬት ወሰኑ ድንበር። ሰው መስልኝ፥ ድንጋይን ቆነጠጥኹ። ሰው መጣ፤ ነገር መጣ ማለት ነው። ሰው መጣ፤ ነገር መጣ። ነገር ከመጣ አለ ጣጣ። ሰው መፈተኑ፥ በክፉ ቀን ነው። ሰው ማለት ሰው የሚሆን ነው፥ ሰው የጠፋ ዕለት። ሰው ማመን ቀብሮ ነው። ሰው ማመን ገደለኝ፥ የእኔ እየመሰለኝ። ሰው ማማት፥ የሰው ሥጋ መብላት። ሰው ማን ያህላል ቢሉት፥ የተናገረውን ያህል አለ። ሰው ማን ያህላል? የተናገረውን። ሰው ማንን ያህላል? የተናገረውን ያህል። ሰው ማጅራቱ አይታየውም። ሰው ምን ቢዋሽ፤ እግዛርን አያታልልም። ሰው፥ ምን በሠራ፥ መቅረቱ ይወራ። ሰው ምን ቢዋሽ፥ እውነትን ፈጽሞ አያጠፋም። ሰው ምን ይመስላል? ቢለው ኑሮውን። (ቢለው ~ ቢሉ) ሰው ሠራሽ፤ በአምላክ ሥራ ፈራሽ። ሰው ሰብስባ ~ በሰው ሥብሳብ ተደብቃ ትፀንሳለች፥ ሰው ጠርታ ትወልዳለች። ሰው ሲታጣ፤ ተመለመለ ጎባጣ። (ተመለመለ ~ ይመለመላል) ሰው ሲወድ፥ ልብ ሥር ይሰድ። ሰው ሲኼድ ለአገር፤ ንብ ሲኼድ ለአጥር። ሰው ሲያረጅ ከቤቱ፤ ባል ሲያረጅ ከሚስቱ። ሰው ሲያረጅ ወደ ምድጃ፤ በሬ ሲያረጅ ወደ ሙጃ። ሰው ሲጠላህ፤ ግንድ ይጫንህ። ሰው ሳይቸግረው፥ ከሰው ቤት ይኼዳል። ሰው ሥራ ሲፈታ፥ ወዳጁን ያማል። ሰው ስትውልበት፤ እምነት ይጥልብሀል። ሰው ቁመቱን አይቶ፥ ደጃፉን ይሠራል። ሰው በልብሱ ይከብራል። ሰው በሚስቱ፤ ገበሬ በርስቱ፤ ንጉሥ በመንግሥቱ። ሰው በምስል ይሞታል። ሰው በሰው ላይ፤ ቅቤ በጨው ላይ። ሰው በሰው፤ ቅቤ በጨው። ሰው በሰው የተጠጋ፥ ሰው ወጋ። ሰው በቦታው ይታወሳል፥ ቦታም በሰው። ሰው በትር ይዝ ቁሞ፥ እባብ ከምድር ተጋድሞ። ሰው በአንደበቱ፤ ውሻ በጅራቱ። ሰው በአገሩ ወይራ ነው፥ ያለ አገሩ ግን ጉል ነው። ሰው በአፉ፤ አሞራ በክንፉ። ሰው በአገሩ፤ ሰው ነው። ሰው በአገሩ፤ ቤት በበሩ። ሰው በአገሩ፤ አሣ በባሕሩ አንበሳ በደሩ። ሰው በአገሩ፤ አንበሳ በደሩ፤ አዝ በባሕሩ። ሰው በአገሩ፤ አውሬ በደሩ። ሰው በአገሩ፤ ወይራ ነው። ሰው በአገሩ፤ ዗ፈን በትብብሩ። ሰው በእህል፥ እህል በዝርዝር ያምራል። ሰው በከንቱ አይጎነበስም፥ ወይም እቃ ሉያነሣ፥ ወይም ሉፈሳ። ሰው በወሬ፤ ደቄት በሙሬ። ሰው በዝና፤ ዝናብ በደመና (ይታወቃል)። ሰው በየወንዙ፥ ብዙ ነው መ዗ዙ። ሰው በያ዗ው ከመታ፥ ፈሪ አይባልም። ሰው በደር፤ አይኑ ዝንጉርጉር። ሰው በጉደ አይሥቅም። ሰው ቢማር ቄስ እንጂ፥ መላክ አይሆንም። ሰው ቢሰባ ለመሬት፤ አህያ ቢሰባ ለአራዊት። ሰው ቢታጣ፤ ተመለመለ ጎባጣ። ሰው ባለው ይሰለፋል። ሰው ባላወቀው ይፈርዳል፥ እግዛር ባወቀው ይቀጣል። ሰው ብርቱ፤ ድመት ጠንካራ። ሰው ብጤውን፤ ድስት እፊያውን አያጣም። ሰው ብጤውን፤ ድስት ግጣሙን አያጣም። ሰው አለ ሀገሩ፥ ምነው መናገሩ? ሰው አለ ሀገሩ፥ ምነው መኖሩ? ሰው አለ ብልኀቱ ገደል መግባቱ፤ አለ ጉልበቱ ውሃ መግባቱ። ሰው አለ ወንዙ፤ ብዙ ነው መ዗ዙ። ሰው አለቀ፤ ምድር ተደባለቀ። ሰው አትመኑ፤ አብዶል ዗መኑ። ሰው አውቆን፤ ፀሓይ ሞቆን። ሰው አየ፤ እግዛር አየ። ሰው አይወድም፤ በደል ከብት አይወድም ገደል። ሰው እንደ ቤቱ፤ ልጅ እንደ አባቱ። ሰው እንደ ዕውቀቱ ነው። ሰው እንደቤቱ እንጂ፤ እንደ ጎረቤቱ አይበላም። (አይበላም~ አይተዳደርም~ አይኖርም ~ አያድርም) ሰው እንደብጤቱ ይኖራል። ሰው እንደነገሩት፤ በቅል እንዳሠሩት። ሰው እንደአቅሙ፤ እህል እንደ ቀርሙ። (ቀርሙ ~ ቃርሙ) ሰው እንዳነጋገሩ፤ በቅል እንዳሰጋገሩ። ሰው እንግዳ ቢሆን፥ እግዛር ባላገር ነው። ሰው ከሀሜት፤ ፋሲካ ከሰንበት ወጥቶ አያውቅም። ሰው ከመለመን፤ አምላክን ማመን። ሰው ከመከረው፤ መከራ የመከረው። ሰው ከመከረው፤ ዗መን የመከረው። ሰው ከሚጠላህ፤ ድንጋይ ይጫንህ። ሰው ከሞተ የለ ንስሓ፤ ከፈሰሰ አይታፈስ ውሃ። ሰው ከሞት ወዱያ ከወረደ አንጋዳ፥ ወዳጁን አይጠቅም ጠላቱን አይጎዳ። ሰው ከሞት፤ ከብት ከቢላ (አያመልጥምና ይታረዳል)። ሰው ከራበው፥ የሰይፉን ሰገባ ይበላል። ሰው ከቆየ መዚመድ፤ አህያን በገመድ። ሰው ከቆየ፤ ከሚስቱ ይወልዳል። ሰው ከተከተተ፤ ጅብ ከአኮተኮተ። ሰው ከኖረ፥ ከሚስቱ ይወልዳል። ሰው ከአለ ሀገሩ፥ ምነው መናገሩ? ሰው ከአላማ ጀንበር አይጠልቅም። ሰው ከአልሞተና፥ ከአልኼደ አይመሰገንም። ሰው ከአስታማሚው፤ እህል ከአራሚው። ሰው ከ዗መደ፤ ቀበሮ ተጉድ጑ደ። ሰው ከ዗መደ፤ አህያ ታመደ። ሰው ከ዗መደ፤ አህያ ከአመደ። ሰው ካለቤቱ፤ ልፋት ከንቱ። ሰው ወጣኒ፤ እግዛር ፈጻሚ። ሰው ሆኖ አይስት፤ ዕንጨት ሆኖ አይጨስ የለ(ም)። ሰው ሆኖ የማያስብ፤ ዕንጨት ሆኖ የማይጨስ። ሰው ሆኖ የማይበድል፤ ዕንጨት ሆኖ የማይጨስ። ሰው ለሰው፥ መድኀኒቱ ነው። ሰው ዅሉ ሲሰድብህ፥ ሲያማህ እሰማለኹ፥ እኔ ስደረድር ስክብ እኖራለኹ። ሰው ሆኖ አይስት፤ ዕንጨት ሆኖ አይነድ የለም። ሰው ዅሉ ገብቶ አገሩን፥ እህና እኔ (ብቻ) ቀረን። ሰው ዅሉ ገብቶ አገሩ፥ እህና እኔ ብቻ ቀረን። ሰው ወጣኝ፤ እግዙአብሔር ፈጻሚ። ሰው የልቡን ሲነግሩት፥ የኮረኮሩትን ያህል ይሥቃል። ሰው የሚበላ ቡዳ፥ እጉድ጑ድ ሆኖ ይጠብቃል። ሰው የሠራው፤ መሬት አወራው። ሰው፥ የሰው ጠላት የለውም። ሰው የተወለደበትን እንጂ፤ የሚሞትበትን አያውቅም። ሰው የተጠጋ፤ ሰው ወጋ። ሰው የወለደውን ቢስሙለት፥ የደገሰውን ቢበሉለት ይወዳል። ሰው ያለ ሀሳቡ፥ የሰው በቅል መሳቡ። ሰው ያለ ሀገሩ፥ ይበዚል ነውሩ። ሰው ያለ፤ ሀገር መሬት ያለ዗ር። ሰው ያለ ሥራው፥ የተሰረቀ አህያ ይነዳል። ሰው ያለ አገሩና፥ ሰው ያለ ቦታው፥ ብሳና ይሆናል ሸንኮራ አገዳው። ሰው ያለበት አገር፥ ሰው የላለበት ደር። ሰው ያለቤቱ፤ ያንሣል ጉልበቱ። ሰው ያለው፥ አርፍድ ይሞታል። ሰው ያመነ፤ ውሃ የ዗ገነ። ሰው ያስባል፤ እግዙአብሔር ይፈጽማል። ሰው ያስባል፤ እግዛር ይፈጽማል። ሰው ያስገድላል አባይ፤ ውሃ ያስጮሀል ድንጋይ። ሰው ይለፋል፤ እድል ይሠራል። ሰው ይኖራል እንጂ እንደቤቱ፥ አይኖርም እንደ ጎረቤቱ። ሰው ይውደድህ፤ ድንጋይ ይጫንህ። ሰው ይጥራል፤ እድል ይሠራል። ሰው ይጨርሳል እንጂ፥ ሀሳብ አያልቅም። ሰው ይጨነቃል፥ የሚሆነውን እግዛር ያውቃል። ሰው ይጫኑብህ ግንድ ቢሉት፥ ግንድ ከተጫነ ሰው ያነሣልኛል፥ ሰው ከተጫነኝ ግን ማን ያነሣልኛል አለ። ሰው ጊዛውን፤ እቃ ቦታውን ምን ጊዛም አያጣውም። ሰው ጠባቂና፤ ጾም ገዳፊ ለጥቂት ይሳሳታል። ሰው ጠባቂና፤ ጾም ገዳፊ አንድ ነው። ሰው ጥራ ቢሉት፥ መራራን ጠራት። ሰው ጥራ ቢሉት፥ እራሱ መጣ። ሰው ፊትን፤ እግዛር ግን ልብን ያያል። ሰው፥ በወደደው ይገድፋል። ሰው በዋለበት፤ ውሃ በወረደበት። ሰው በ዗መድ፤ አህያ በገመድ። ሰው በ዗መድ፤ ከብት በገመድ። ሰው በዛና፤ ውሃ በደመና። ሰው፥ ከጠመመ ይሰበራል እንጂ፥ አይቃናም። ሰው፥ ካለ እህል፥ ምን ያህል? ሰውነቱ ከንጽሕና፥ ልቡ ከትሕትና፥ ያልተለየ ደኅና። ሰውነቱን ቢንቁ፥ ልብሱን ይጠይቁ። ሰውነት ከነፍስ፥ ልብስ ከምግብ ይበልጣሉ። ሰውና አመሉ፥ ሳይተዋወቁ ይኖራሉ። ሰውና ዕንጨት ተሰባሪ ነው። ሰውና ጥሬ፥ ሆድ አሻካሪ ነው። ሰውን ማመን ቀብሮ ነው (አለች ቀበሮ)። ሰውን ማመን፥ ቀብድ ተቀብል ነው። ሰውን ማመን ገደለኝ፥ እኔን እየመሰለኝ። ሰውን ሰው ናቀው፥ የራሱን ሳያውቀው። ሰውን ሰው አማው፥ የራሱን ባይሰማው። ሰውን ሰው የሚበልጠው ለተወሰነ ጊዛ (ብቻ) ነው። ሰውን ሰው የሚያደርገው የራሱ ምግባር ነው። ሰውን ሰው ያሠኘው፥ ዕቁብ ነው። ሰውን ሲወደ፥ ከነንፍጡ እና ልጋጉ። ሰውን ሲያሙ፥ ጤፍ ቀድሚያ ለብልቦ ነው። ሰውን ሲያማ፥ ለእኔ ብለህ ስማ። ሰውን አትናቀው፤ እህልን አትራቀው። ሰውን እጎዳ ባይ፥ አመድ ተንከባላይ። ሰውን ከመለመን፤ ፈጣሪን ማመን። ሰውን ከነአመሉ፤ ድሪቶን ከነቅማሉ ወዱያ በሉ። ሰውን ከአልናቁ፥ አጥሩን አይነቀንቁ። ሰውን ውደደው፥ እንጂ አትመነው። ሰውን የሚያስረጅ ሀሳብ፥ ልብስን የሚያስረጅ ሥብሳብ። ሰውን ያመነ፤ ጉም የ዗ገነ አንድ ሆነ። ሰውን ፈላጊ፥ በምርጫ ይሸነፋል። ሰውየው ውሃ ሲወስደው፥ እኔም ወደ ቆላ እወርዳለዅ ብዬ ነበር አለ። ሰውየውን ከአልናቁ፥ አጥሩን አይነቀንቁ። ሰዎች ዅሉ አብደው፥ እኔ ጤነኛ ከሆንኩ፥ እብደ እኔ ነኝ። ሰዎች፥ በማያገባቸው ነገር፥ ለጋሾች ናቸው። ሰይጣን ለአመሉ፥ መጽሀፍ ቅደስ ይጠቅሳል አሉ። ሰይጣን ለወዳጁ ደርብ ነው። ሰይጣን ለወዳጁ ድሩግ፥ ለጠላው ደግሞ ጠላት ነው። ሰይጣን ለወዳጁ፥ ድርብ ነው አሉ። ሰይጣን ሲያረም፥ ባሕታዊ ያስንቃል። ሰይጣን ቢያረምም፥ ባሕታዊ ይመስላል። ሰይጣን ቢጠፋ፥ የመነኰሴ ቆብ አንሥተህ ፈልገው። ሰይጣን ባሸመቀው፤ መንፈስ ቅደስ ባወቀው። ሰይጣን ከመታው፤ ፓርቲ የመታው። ሰይጣን ጦመኛ ሲሆን፥ ዗ላለም ሰይጣን ነው። ሰድ ከማሳደድ፤ የያዙትን ማጥበቅ። ሰድ ማሳደድ ቢሻህ፥ ድሮህን ለቆቅ ለውጥ። ሰድ ማሳደድ ቢያምርህ፥ ድሮህን በቆቅ ለውጥ። (ቢያምርህ ~ ከአማረህ) ሰጋር በቅል ያለው፥ መንገድ አይፈራም። ሰድ ከማሳደድ፥ የያዙትን አለመስደድ። ሰጥቶ በእጅ፥ መለመን ከሰው ደጅ። ሰጥቶ ከእጁ፥ ለመነ ከደጁ። ሰፊ ሆድ ያለው፥ ከሰፊ አገር አይውጣ። ሰፊ ሜዳ፥ እንደ ወግዳ። ሰፌድና ወንፊት ያላት ሴት፥ ያልተነፋ ደቄት አታቦካም። (ደቄት ~ ደቄት) ሱሱ አይቀርም፥ እሱ ከነፈረሱ። ሱሪ በአንገት አውልቁ። (አውልቁ ~ አውልቅ) ሱሪ በጭንቅላት አውልቁ። ሱሪ አውሶ፥ አትቀመጥበት። ሱሪ አውሶ፥ አደራህን እንዳትቀመጥበት። ሲለቁት ሜዳ ሙሉ፤ ሲይዙት ጭብጥ ሙሉ። ሲሉ ሰምታ ድሮ ሞተች፥ እማጥ ገብታ። ሲሉ ሰምታ ድሮ ሞተች፥ ከጢስ ገብታ። ሲሉ ሰምታ ድሮ ሞተች፥ ዋና ገብታ። ሲል ነበር ደግሞ፥ ከወግ ይጨመር። ሲመሽ ወደ ቤቴ፤ ሳረጅ ወደ ርስቴ። ሲመትሩለት ይነጭ። ሲመች በእጅ፤ ሲፈጅ በማንኪያ። ሲመች የአማት ተዝካር ይወጣል፤ ሳይመች የአባት ይቀራል። ሲመክሩት ለማይሰማ፥ ሲያበሉት ለሚከሳ፥ ለዙያም ምክር፥ ለዙያም እህል ንሣ። ሲመክሩት አይመከር፥ በደም ይነከር። ሲመክሩት ያልሰማ፤ ሲያጮሉት ይሰማ። ሲመክሩት ያጠፋል ልጅ፤ ሲታጠቡት ያድፋል እጅ። ሲመክሩት ይረሳል፤ ሲከድኑት ይፈሳል። ሲመጣ መንጫጫት፤ ሲኼድ መረሳት። ሲምር ያስተምር። ሲሞላ ይፈሳል፤ ሲከር ይበጠሳል። ሲሞቱ ብታይ፥ አንቀላፋች። ሲሞቱ ቢያይ፥ ያንቀላፋል። ሲሞቱ ገመድ፤ ሲሾሙ ዗መድ አይታጣም። (ሲሾሙ ~ ሲገዙ) ሲሰማ የሞተውን፤ ሲያይ ቅበረው። ሲሠሩ ልላ መስል፤ ሲበሉ ጌታ መስል። ሲሠሩ ልላን፤ ሲበሉ ጌታን አህል። ሲሰርቀኝ ያየኹት፥ ሲሰጠኝ ጠላኹት። ሲረዝም ይጠር፤ ሲሰበር ይሰንጠር። ሲራክ በምግባሩ፥ ጠፋ መቃብሩ። ሲርበኝ ታነቅኹ፤ ሲጨንቀኝ ታረቅኹ። ሲሮጡ የታጠቁት፤ ሲሮጡ ይፈታል። ሲሮጡ የፈቱት፥ ሲቀመጡ ለማስተካከል ቀላል ነው። ሲሮጥ ልላ መስል፤ ሲበሉ ጌታ መስል። ሲሮጥ የመጣ አህያን፥ አጥብቀህ ጫነው። ሲሮጥ የመጣን አህያ፥ አጥብቀህ ጫነው። ሲሻሩ ከሳሽ፤ ሲሞቱ ወራሽ አይታጣም። ሲሻኝ ጢስ ወጋኝ። ሲሰርቀኝ ያየኹትን፥ ቢጨምርልኝ አላምነውም። (ቢጨምርልኝ ~ ቢመርቀኝ) ሲሰርቅ ያየኹት፥ ሲሰጠኝም አላመንኹት። ሲሰርቅ ያየኹትን፥ ቢሰጠኝ አላምነውም። ሲሰበር ይሰንጠር፤ ሲረዝም ይጠር። ሲሱ ሲበላ ይታነቃል፤ ሀሰተኛ ሲናገር ይታወቃል። ሲሳይ በርምጃ ይገባል፥ በሩጫ ይወጣል። ሲስሟት ቀርታ፥ ሲስቧት። ሲስሟት ትታ፥ ሲስቧት። ሲስሟት እንቢ፤ ብላ ሲስቧት። ሲስሟት እንቢ፤ ብላ ሲጎትቷት። ሲሾም ያልበላ፤ ሲሻር ይቆጨዋል። ሲሾም ያልጠጣ፤ ሲሻር ይሰክራል። ሲቀላውጡ አይን አፍጦ፤ ሲቆፍሩ አንፈራጦ። ሲቀላውጡ አይንን አፍጦ፤ ሲቆፍሩ እግርን አንፈራጦ። ሲቀመጡ አውቃለኹ፤ ሲነሡ አፍራለኹ። ሲቀርቡን እየገፋን፤ ሲርቁን እየከፋን። ሲቃ የቀስቀስው፥ ነቅቶ አይተኛም። ሲቅዚ፥ በራሷ አርግዚ። ሲበሉ መደንደን፤ ሲያጡ መቅጠን። ሲበሉ በሰዓት፤ ሲናገሩ በሥርአት። ሲበሉ አድርሰኝ፤ ሲጠሉ አርቀኝ። ሲበሉ አድርሱኝ፥ ሲጣሉ መልሱኝ። ሲበሉ የላኩት፥ ሲናገር ያሳስታል። ሲበሉ የላኩት። ሲበላ ለሚከሳ፥ ሲመክሩት ለሚረሳ፥ ለዙያ እህልን ለእዙህ ምክርን ንሣ። ሲበላ ለሚከሳ፥ ሲመክሩት ለሚረሳ፥ ለዚ እህል ንሣ፥ ለዙያም ምክር ንሣ። ሲበላ ለሚከሳ ሲነግሩት ለሚረሳ፥ ለዙያ እህልን ንሣ፥ ለዙያ ምክርን ንሣ። ሲበዚ ማር ይመራል። ሲበዚ ሲበዚ ይገነፍላል። ሲበዚ ይገነፍላል። ሲበደሉ ማሩኝታ፤ ቢበድሉ ይቅርታ። ሲተረጉሙ ይደረግሙ። ሲተባበር ግም፥ እን኱ን ያምራል። (አለቃ ገብረ ሀና አሉት የተባለው) ሲተኙ ነገር ያገኙ፤ ሲነሡ ነገር ይረሱ። ሲታሰር ያልተሰማው፥ ሲፈታ ጎረበጠው። ሲታረቁ ክሶ፤ ሲጸድቁ መንኰሶ። ሲታጠቡ ከክንድ፤ ሲታረቁ ከሆድ። ሲታጠቡ እስከ ክንድ፤ ሲታረቁ እስከሆድ። ሲታጠቡ እስከ ክንድ፤ ሲታረቁ ከሆድ። ሲቸኩሉ የታጠቁት፥ ለወሲብ አይመችም። ሲቸገሩ ያልሰጠ፥ ቸር አይባልም። ሲቸግር ጤፍ ብድር። ሲቻለው ማሪ፥ እግዛርና አሉ። ሲነግሩት የማይሰማ፥ ሲቀልቡት አይድንም። ሲነግሩት የሚ዗ነጋ፤ ሲያምኑት የሚሰጋ የለውም ዋጋ። ሲነግሩት ያጠፋል ልጅ፤ ሲታጠቡት ያድፋል እጅ። ሲናገሩት ያልሰማ፤ ሲመቱት ያልደማ። ሲኖሩ ለጠቅ፤ ሲኼደ መንጠቅ። ሲኖሩ ጥልቅ፤ ሲለዩም ንጥቅ። ሲከሱ ይከሰሱ፤ ሲኼደ ይመለሱ። ሲከር ይበጠሳል። ሲኼደ አገር፤ ሲተኙ ነገር። አወይ የዓለም ነገር። ሲሆን በውድ፤ ሳይሆን በግድ። ሲወለድ ያጠለቀው፥ ሲሞት አወለቀው። ሲወልደ አየኹ ብላ፥ በጠጧን ጣለች። ሲወርደ ይዋረደ። ሲወደ ከልብ ነው፤ ሲታጠቡ ከክንድ ነው። ሲወጡ እንደ ጦጣ፤ ሲወርደ አሣር መጣ። ሲወጣ ባቱን፤ ሲገባ ደረቱን። ሲወድቅ ~ ቢወድቅ ሀብታም በምጽዋቱ፤ ድሀ በጸልቱ። ሲዋቀር ያልበጀው፥ ሲማገር እሳት ፈጀው። ሲዋጥ በመረቅ። ሲዝሩ በመኖር ጽድቅ፤ ሲመኙ በመኖር ወርቅ አይገኝም። ሲዝር ውል፥ እራቱ ጥሬ። ሲያልቅ አያምር። ሲያልፍ ዋዚ። ሲያምረኝ ይቅርብኝ። ሲያምርህ ይቅር። ሲያምኑ መክዳት፤ ሲወደ መጥላት። ሲያምኑት የከዳ፥ አለበት ዕዳ። ሲያረጁ፥ አንባር ይዋጁ። ሲያርስ የዋለ ሞፈር፥ ግርግዳ ላይ ተሰቅል፥ ቤት የዋለ ማንኪያ ገንፎ ውስጥ ጥልቅ አለ። ሲያብል የተኛ፥ ሲጠሩት አይሰማ(ም)። ሲያንቀለቅለኝ አንበሳ ገድዬ፤ በየጠጅ ቤቱ ስሜን ያጠፉታል። ሲያከሩት ይበጠሳል። ሲያከብሩ ያላየ፥ አያከብርም። ሲያወላውል፥ ቀረ ባጉል። ሲያውቀኝ ናቀኝ። ሲያውቁ በድፍረት፤ ሳያውቁ በስሕተት። ሲያውቅ የሞተን፤ ሲሰማ ቅበረው። (የሞተን ~ የተኛን) ሲያውቅ የተኛ፥ ሲጠሩት አይሰማም። (ሲጠሩት ~ ቢጠሩት፥ አይሰማም ~ አይሰማ) ሲያውቅ ያሟግት ዳኛ። ሲያውቅ ያጠፋ ሰይጣን። ሲያዝሉት ይነክስ፤ ሲያወርደት ያለቅስ። ሲያዩም ዝም፤ ሲበሉም ጉርድም። ሲያዩት የማያምር፤ ሲበሉት ያቅር። ሲያዩት ያላማረ፤ ሲበሉት ያቅራል። ሲያዩት ያምራል፤ ሲይዙት ያደናግራል። (ያደናግራል ~ ያደናግር) ሲያዩት ያፈረ፤ ኋላም አላማረ። ሲያይ የገባን፥ ሲሰማ ቅበረው። ሲያደርጉ አይታ ድሮም ጡት መያዣ ገዚች። ሲያድጡት ይጥላል። ሲያጋድል ያልታየ፤ ሲወድቅ ታየ። ሲያጌጡ ይመላለጡ። ሲያጌጡ ይመላለጡ፤ ሲገዙ ይገዙ፤ ሲምሩ ያስተምሩ። ሲያጎርሡት የማያጎርሥ፥ በግርግዳ እንደ መለጠፍ ነው። ሲያጎርሡት የማያጎርሥ፥ ከቀማኛ አንድ ነው። ሲያጣ እጅ፥ ላፍ ይጠናል። ሲያጣጥር አውቆ ጭጭ፤ ሞተ ሲሉ ዗ጭ ዗ጭ። ሲያጣጥር አይቶ ጭጭ፤ ሞተ ሲሉ ዗ጭ ዗ጭ። ሲያጥቡት ያድፋል እጅ፤ ሲመክሩት ያጠፋል ልጅ። ሲደላኝ አቅፋታለኹ፤ ሲከፋኝ እገፋታለኹ። ሲገረገድ ያልበጀው፤ ሲዋቀር እሳት ፈጀው። (ሲገረገድ ~ ሲገደገድ) ሲገባ ደረቱን፤ ሲወጣ ባቱን (መመልከት)። ሲገዙ ይገዙ። ሲገደኝ ጥል የለም። ሲጎርሡ በልክ፤ ሲታጠቁ ጠበቅ። ሲጠላ ይጠና። ሲጠሩት ወዳት፤ ሲልኩት አቤት። ሲጠሩት የቀረ፥ ለምኖ ይኼዳል። ሲጠሩት ያልሰማ፥ ሲቀልቡት ይከሳል። ሲጠባ ያደገ ጥጃ፥ ቢይዙት ያ጑ራል። ሲጠባ ያደገ ጥጃ፥ ቢይዙት ይ጑ጉራል። ሲጠሩህ ዝም በል፤ ሳይጠሩህ እመት በል ነገሩ እንዱ዗ነበል። ሲጠሩት አቤት፤ ሲልኩት ወዳት። ሲጠግቡ ይደግሱ (ሲርብ ግን፥ ምን ልብላ ይላሉ)። ሲጥል እንጂ፤ ሲቆርጥ አይታይም። ሲጮህ እንደ አንበሳ ፤ ሲኼድ እንደሬሳ። ሲፈሩ አይከሱ፤ በጉጣ አያርሱ። (ጉጣ:_ ያለቀ ማረሻ) ሲፈራ ሲቸር፥ ተናገር። ሲፈራገጡ ይመላለጡ። ሲፈጭ ሲቦካ፤ ሲወለድ ሲተካ። ሲፈጭ የነበረ፤ ሲነፋ ከበረ። ሳለቅስ ሳነባ ስውል ሳሰማ፥ የሰጠኸኝ ሸማ ከደጅህ ተቀማ። ሳለቅስ ሳነባ ውል ሳሰማ፥ የሰጠኸኝ ሸማ በደጅህ ተቀማ። ሳለቅስ ሳነባ ውል ሳሰማ፥ የሰጠኸኝ ሸማ ከደጅህ ተቀማ። ሳለው የማያበድር ገዳይ፤ ተበድሮ የማይመልስ አባይ። ሳላም ሰው፥ በርበሬ አይሰርቅም። ሳላውቀው እኔ፥ ስንት ያመጣ ሠኔ? ሳላይ መ዗ዙን፥ አየኹ ሙዙን። ሳል ተይዝ ስርቆት፤ ቂም ይዝ ጸልት። ሳል ተይዝ፤ ስርቆት ቆል መዝራት። ሳል ያለበት ጎልማሳ፤ ዗ንጋዳ ያለበት ዳጉሳ አይጠቅምም። ሳል ይዝ ስርቆት፤ ሞት ይዝ ቅጥፈት። ሳል ያለበት ጎልማሳ፤ ዗ንጋዳ ያለበት ዳጉሳ። ሳል ይዝ ስርቆት፤ ቂም ይዝ ጸልት። ሳል ይዝ ስርቆት፤ ቆል መዝራት። ሳማና አለብላቢት፤ ውሽማና ሚስት። (አብላሉት ~ አለብላቢት) ሳብል ብሥቀው፥ የምር መሰለው። ሳታት በግርግርታ፤ ዳዊት በቀስታ። ሳታድፊ አጉራፊ። ሳትበጡ አግሙኝ፤ ሳትመክሩ አርሙኝ። (አርሙኝ ~ እርሙኝ ) ሳትበጡ እገሙኝ፤ ሳትመክሩ አርሙኝ። ሳትታመም ተፈወስ፤ ሳትረክስ ተቀደስ። ሳትቸገር ተበደረች፤ ሳትከፍል ሞተች። ሳትወልድ ብላ። ሳትዋጋ ንገሥ ቢሉት፥ ሳልዋጋ አልነግሥም አለ። ሳትዋጋ ንገሥ ቢሉት፥ ግድ ተዋግቼ አለ። ሳትጋደም፥ ፈሷ ቀደም። ሳትጠራ ምስክር፥ ልዅን አትበል። ሳንባ ፍየል ላሰባ። ሳንባ ፍየል ላረባ። (ላረባ ~ ላርባ) ሳንባ ለድመት፤ ገለባ ለከብት። ሳንነሣ ይነከር ነበር። ሳንፈራ በድፍረት፤ ሳናፍር በእውነት። ሳያስረግጡ ወሬ፤ ሳይገድሉ ጎፈሬ። ሳያረደ አይሰደደ። ሳያረጋግጡ ወሬ፤ ሳይገሉ ጎፈሬ ። (ሳይገሉ ~ ሳይገድሉ) ሳያርሱ ግርድ፤ አለዳኛ ፍርድ። ሳያሽ የበላ ኮሶኛ፤ ሳይፈርድ የበላ ዳኛ። ሳያሽ የበላ ዝንጀሮ፥ ሲስል ያድራል። ሳያሽረው የበላ ኮሶኛ፤ ሳይፈርድ የበላ ዳኛ። ሳያተርፍ ያበደረ፥ ሳይቀበል ተቀበረ። ሳያት የምታሥቀኝ ሚስት አገባኹ! አለ አስቀያሚ አግብቶ እኮ ነው። ሳያውቁ የቆረጡት አበባ፥ የፈለጉት ቀን ይደርቃል። ሳያውቅ የተረተ፤ ሳይ዗ራ ያመረተ። ሳያዝኑ ደስታ፤ ሳይጾሙ ፋሲካ። ሳያድጉ ማደግ፥ ያዳግማል። ሳያገቡ ማርገዝ፤ ሳያረጁ መፍ዗ዝ። ሳያጠፉ ምክር፤ ሳይሞቱ ተዝካር። ሳያጣሩ ወሬ፤ ሳይገሉ ጎፈሬ። ሳይሆን ሆነ፤ ሳይሰበር ተጠገነ። ሳይሆን ለብም፤ ሳይሰብር ጠግን። ሳይሆን ለጉም፤ ሳይሰበር ጠግን። ሳይለማ በደልማ፤ ሳይቃጠል በቅጠል። ሳይለግሙ ያግሙ። ሳይለፉ አያተርፉ። ሳይለፋ የአገኙት፥ ለቅጽበት። ሳይማሩ መተርጎም፤ ሳያም ማገም። (ማገም ~ ማከም) ሳይማሩ ማንበብ፤ ሳይበሉ መጥገብ። ሳይማሩ መተርጎም፤ ሳይበጡ ማገም አይቻልም። (አይቻልም ~ የለም) ሳይሞቅ ፈላ። ሳይሠሩ ማግኘት፤ ሳይጸድቁ ገነት (አይገኝም)። ሳይሰበር ጥግን። ሳይረቱ አይሞቱ፤ አለዳኛ አይሟገቱ። ሳይረቱ አይበረቱ። ሳይርቅ በቅርቡ፤ ሳይደርቅ በቅርቡ። ሳይርበው የሚበላ፥ ረኃብን አያውቅም። ሳይቀሱ መና዗ዝ፤ ሳይሾሙ ማ዗ዝ። ሳይቀሥሱ መምሬ፤ ሳይጠምደ ገበሬ። ሳይቀሥሱ አይናዝዙ፤ ሳይሾሙ አያዝዙ። ሳይቀቡ አይነግሱ፤ ሳይመነኰሱ አይጰጵሱ። ሳይቀድስ ያርዳል፤ ሳይታየው ይፈርዳል። ሳይቃጠል በቅጠል። ሳይሰሙ ወሬ፤ ሳይገድሉ ጎፈሬ። ሳይሰሙ ማውራት፥ መዋረድ አለበት። ሳይቃጠል ቸብቸብ በቅጠል። ሳይቆርሱ መጉረሥ። ሳይቆርጡ ምጣኔ፤ ሳይሰጡ ዝካሬ። ሳይቆጥር የሰጠ፥ ሰጭውም ላባ ተቀባዩም ላባ። ሳይቆጥር ያኖረ ላባ፤ ሳይቆጥር የተቀበለም ላባ። ሳይበሉ ማግሳት፤ ልከበር ብል መ጑጑ት። ሳይበሉ ማግሳት፥ ልክበር ብል መ጑጑ት። ሳይባርክ ያረደ፤ ሳይታየው የፈረደ። ሳይባርክ ያርዳል፤ ሳይታየው ይፈርዳል። ሳይተርፋት አበደረች፥ ሳትቀበል ሞተች። (አበደረች ~ ያበደረች) ሳይተርፋት አበድራ፥ ሳትቀበለው ሞተች። ሳይታለም የተፈታ። ሳይታደሉ አይገዙ፤ ሳይበሉ አይወዙ። ሳይታገል ጣይ፤ ሳይወጋ ገዳይ። ሳይታፈሩ መገላገል፥ እብድ ያሰኛል። ሳይቸገር የተበደረ፤ ሳይከፍለው ተቀበረ። ሳይቸግር ጤፍ ብድር። ሳይቸግር ጤፍ ብድር፤ በስተርጅና ሙሽርና። ሳይነገር ይፈርደታል፤ ሳይጻፍ ያነቡታል። ሳይነጋ ለከፈኝ። ሳይናገር ብልኀቱ፤ ሳይታረድ ስባቱ። ሳይከካ ተቦካ። ሳይሆን መርጃን ለቃልቻ፤ ሳይቀደሙ መታገል ለሙትቻ። (መርጃን ~ መረጃ) ሳይሆን ይመስላል፤ ሲሆን ይገርማል። ሳይወደ ቢያጎርሡ፥ አጥንት አስነከሱ። ሳይዋጉ ተን዗ራጉ። ሳይውሉ ያዋዋሉ፤ ይሰብሩ ላይጠግኑ። ሳይውሉ ይዋዋሉ፤ ሳይተማመኑ ይማማሉ። ሳይውል ሳያድር፥ የሰው ልጅ ብድር። ሳይ዗ሩ ማጨድ፤ ሳይራመደ መኼድ። ሳይ዗ራ ያመረተ፤ ሳያውቅ የተረተ። ሳይያዙ ገና፥ ዚር ልመና። ሳይደርሱባቸው እየደረሱ፤ ይመለሳሉ እየቀመሱ። ሳይደውል ቅደስ። ሳይደግስ አይጣላ(ም)። ሳይገድሉ ጎፈሬ፤ ሳያስረግጡ ወሬ። ሳይጠሩህ መጣህ፤ ሳትጠግብ ወጣህ። ሳይጠሩት አማካሪ፤ ሳይሾሙት ፊታውራሪ። ሳይጠሩት አቤት ባይ፤ ሳይሰጡት ተቀባይ። (አቤት ~ ወይ) ሳይጠሩት አቤት፤ የሰይጣን ጎረቤት። ሳይጠሩት አቤት፤ ሳይልኩት ወዳት። ሳይጠሩት የመሰከረ፤ ሳይጠጣ የሰከረ። ሳይጠሩት የመጣ፤ ሳይጠግብ ወጣ። ሳይጠሩት ይመጣል፤ ሳይ዗ሩት ይበቅላል። ሳይጠይቁ አያውቁ። ሳይጠጡ መስከር፤ ሳይሞቱ መቀበር። ሳይጣሉ መገላገል፥ እብድ ያሰኛል። ሳይጣሉት የተጣላ፤ ሲርብ ያበላ አይረሳም። (አይረሳም ~ አይረሱም) ሳይጾሙ ይጸድቃሉ፤ ሳይታመሙ ይጠይቃሉ። (ይጠይቃሉ ~ ይጠየቃሉ) ሳይፈሩ እውነት፤ ሳይጠራጠሩ እምነት። ሳይፈታ ሚስቱ፤ ሳይረታ ርስቱን። ሳይፈታ ሚስቱን፤ ሳይረታ ከብቱን። ሴቱ ሲበዚ፥ ጎመን ጠነዚ። (ሴቱ ~ ሴት) ሴቱ አለንጋ፤ ወንደ አምበልጋ። ሴቱን ዅሉ፤ ባላልቦ አደረጉት። ሴት ለቤት፤ ወፍጮ ለደቄት። ሴት (ልጅ) በማጀት፤ ወንድ (ልጅ) በችልት። ሴት ማገድ ሲቸግራት ምሰሶ ትነቅላለች። ሴት ምክንያት አታጣ። ሴት ልጅ ሲቸግራት ምሰሶ ትነቅላለች። ሴት ሲበዚ፥ ወንድች ይፈራሉ። ሴት ሲወዶት ጣራ፥ ሲጠሎት ጠንቋይ ትጠራ። ሴት ሲያፏጩላት፥ ያረሱላት ይመስላታል። ሴት ሦስቱ፥ የአህያ ሰባቱ ሀገር ያውላል። ሴት በማጀት፤ ወንድ በችልት። ሴት በወንድ ግራ ጎን መተኛቷ፥ ስለምንድነው ቢሉ? ከግራ ጎኑ፥ ከአዳም አጥንት ስለተፈጠረች ነው። ሴት በዚ፥ ሱሪ ተቀደደ። ሴት በዚ፥ ጎመን ጠነዚ። (በዚ ~ ከበዚ) ሴት በጳጳስ፤ ኱ደሬ በንጉሥ። ሴት ብታውቅ፤ በወንድ ያልቅ። (ብታውቅ ~ ታውቅ) ሴት ብትወልድ፥ መቼም ሴት ነው። ሴት ነጠላ ከአመቻት፥ የአህያ ልቅሶ ላይ ትውላለች። ሴት አሉሽ፥ ምን ይበሉሽ? ሴት አማት የመረ዗ው፤ ኮሶ ያነ዗዗ው (አንድ ነው)። ሴት አትኼድም ማለት፥ ተቀምጣ አትሸናም ማለት ነው። ሴት አዋቂ ትወልዳለች እንጂ፥ ራሷ አታውቅም። ሴት አግብተው ሴት ቢወልደ፥ የት አለ ንግደ። ሴት ከማማከር፥ ደግሶ መስከር። ሴት ከባሎ፤ እንጂ ከአባቷ አትወርስም። ሴት ከቤት፤ ወፍጮ ከደቄት። ሴት ከተማረች፤ በቅል ከጠገበች አመል አወጣች። ሴት ከአላበለች፥ ባሎን ትወልዳለች። ሴት ከአልወደደች፥ ቋንጣ አትጠብስም። ሴት ከአልዋሸች፥ ባሎን ትወልዳለች። ሴት ከአረጠረጠች፥ ቤት ቤት አይሆንም። ሴት ከወንድ፤ እህል ከሆድ። ሴት ከጠላች፤ በቅል ከበላች አመል ታወጣለች። (ታወጣለች ~ አወጣች) ሴት ኮር኱ሪ፥ ቀባጣሪ። ሴት የላለበት፥ ወንድ አይበቅልበት። ሴት የላከችው፥ ጅብ አይፈራም። ሴት የላከው፥ ምልክቱን አይረሳም። ሴት የላከው፥ ሞት አስፈራራው። (አስፈራራው ~ አይፈራም) ሴት የላከው፥ በር አያን኱኱ም። ሴት የላከው፥ ጅብ አይፈራም። ሴት የላከው፥ ፓርላማ ይገባል። ሴት የመጀመሪያዋ እንጂ፥ የመጨረሻዋ አያምርም። ሴት የወለደ፤ መቅ የወረደ። ሴት የወለደ፥ ተዋረደ። ሴት የወለደ፤ ጉድ የወለደ። ሴት የወለደና፥ ጉድ ያ዗ለ አንድ ነው። ሴት የወደደ፥ (ወደ) ገሃነመ እሳት ወረደ። ሴት የወደደ፤ ጉም የ዗ገነ። ሴት የገዚው አገር፤ በግ የጋጠው ድንበር። ሴት ያመነ፤ ጉም የ዗ገነ። ሴት ያመጣችው ጠብ ቶል አይበርድም። (ያመጣችው ~ ያመጣው ~ ያወጣው) ሴት ያመጣው ጠብ አይበርድም። ሴት ያማከረ፥ ደግሶ የሰከረ። ሴት ያሳደገው፥ ወሮታው ውርደት። ሴት ያወጣው ጠብ አይበርድም። ሴት ያሳደገው። ሴት ይወዶል፤ ማጀት ያንጎዳጉዶል። (ያንጎዳጉዶል ~ ይንጎዳጎዶል) ሴት ዳላዋ እንጂ፥ አእምሮዋ አይሰፋም። ሴት፥ ሞፈርና ቀንበር ሲወጣ ካየች የታረሰ ይመስላታል። ሴት ሲበዚ፥ ልማት ይፋጠናል። ሴት፥ ጅብ ትፈራለች፥ አጥር ትመዚለች። ሴትና መሬት የማይችሉት የለም። ሴትና ሥጋ በሰል ሲል ነው የሚጣፍጡት። ሴትና ስፌት፥ በሩቅ ሲያዩት ያምር። ሴትና ቄስ፥ ቀስ (በቀስ)። ሴትና በቅል እንደ ገሪዋ ነው። ሴትና በቅል ጊዛ አይታ ትጥላለች። ሴትና ቤት አይታመንም። ሴትና ቶፋ ወደ ማጀት። ሴትና አህያ በደላ። ሴትና አህያ በግፊያ አይቻልም። ሴትና አህያ ካልከበዳት አትኼድም። ሴትና አህያ ደላ ይወዳል። ሴትና አህያ ጭነት አይከብዳትም። ሴትና አሽከር አያሽበልብሉ። ሴትና እሳት ጥጋብ ያበዚል። ሴትና ኮርቻ ከአንድ አይረጋም። ሴትና ወደል ካልተደበደበ አይሆንም። ሴትና ወጪት ሲከናነቡ ይሻላል። ሴትና ውሻ የሚያመጣው መ዗ዝ አገር ያጠፋል። ሴትና ይሉኝታ ያከበራትን ነው የምታጠቃው። ሴትና ዳዊት በብብት። ሴትና ድመት ወደ ሞቀበት። ሴትና ድስት ወደ ማጀት። ሴትና ድሮ ሳያብደ አይውሉም። ሴትና ድሮ ሳያብድ አይውልም። (አይውልም ~ አይውል) ሴትና ድሮ ሳይጣላ አይውልም። ሴትና ድሮ ደር ሲኼደ፥ ቤታቸውን ከደ። (ከደ ~ ይከደ) ሴትና ድሮ ደር ከኼደ፥ ቤታቸውን ይክዳሉ። ሴትና ጊንጥ በቂጥ። ሴትና ፈረስ የሰጡትን ይቀምስ። (የሰጡትን ~ ያቀረቡለትን) ሴትና ፈረስ እንደ ኩሬ ውሃ፥ እያደር ማነስ። ሴትን ማመን፤ አይጥን በአቁማዳ መክተት ነው። ሴትን ሲታ዗ቧት፥ ሥጋ ቀቅይ አሎት። ሴትን አትቅደማት፥ አትድገማት። ሴትን ከቤት፤ ብርን ከማእድ ቤት። ሴትን ከአስተማረ፤ የዳረ ከበረ። ሴትን የወለደና ጉድን ያ዗ለ አንድ ነው። ሴትን ያመነ፤ ጉምን የ዗ገነ። ሴትን ያማከረ፤ ሸክሙን በሣር ያሰረ። ሴትየዋ፥ በገዚ አረሟ፥ እባብ ይዚ ታስፈራራ። ሴትየዋ፥ እንደፈራኹት ተቀደደብኝ አለች። ሴትየዋ የመጣችው ለጠብ ነው፥ ለጠብ ትሰፋለች። ሴቶች ሲበዙ፤ ጎመን አጠነዙ። ሴቶች በጆሯቸው፥ ወንድች በአይናቸው ይወዳሉ። ሴቶች ከሰከሩ፤ እንግድች ጦም አደሩ። ሴቶች ያለፈውን እንጂ፤ የሚመጣውን አይናገሩም። ስሕተትና አበባ፤ በትምህርትና በጥቅምት ይታረማል። ስሕተትና አበባ በጥቅምት ይታረማል። ስለ ላቁ፤ ውል አያውቁ። ስለ ልብስ፥ ይኮራል ነፍስ። ስለ ትዕግሥቱ ይጾሙ፤ ስለ ሥርአቱ ይቆሙ። ስለ ናቁ፤ መላ አያውቁ። ስለ ከሰሱ፥ አይፈወሱ። ስለ ጤሰ አይነድም፤ ስለ ዳመነ አይ዗ንብም። (ጤሰ ~ ጨሰ) ስለ ፍቅር፥ በስመ አብ ይቅር (አለ ሰይጣን)። ስለት ይቆርጣል፤ ምላስ ያስቆጣል። ስለት ድጉሱን፤ ደባ ራሱን። ስላንጋጠጡ አይገጡ። ስላጎረሥኹ፥ እጄን ተነከስኩ። ስልህ እንዳልልህ፥ አላገኝህ። ስልብ ልላ፥ በጌታው ምንትስ ይፎክራል። ስልቻ፥ ለሥጋ መክተቻ። ስልቻ ቀልቀል፥ ቀልቀልም ስልቻ። ስልቻ አሳሪ፤ እርቦ ሰፋሪ። ስልቻና አቁማዳ፤ ቆራጣና ጎማዳ። ሥልጡን እንግዳ፥ ይውላል እ጑ዳ። ሥልጣንና ኮት፥ ወላቂ ነው። ስመሰክርልህ (ስመሰክርልህ) ዋልኩ ቢለው፥ ስታ዗ብህ (ስታ዗ብህ) ዋልኩ አለው። ስሙ በካህን፥ በላተኛው መሃይምን። ስሙ ለባለቤት፥ ቤተሰብ ናኘበት። ስሙን ለሰው አወረሰው። ስሙን ጠርቶ፤ ራሱን ቆርጦ። ስም ከመቃብር በላይ ይውላል። ስም ያለው ሞኝ ነው። ስም ከመቃብር በላይ፥ ልብስ ያምራል በሰው ላይ። ስም ከመቃብር በላይ ይቆማል። ስም ይመራል፥ ጧፍ ያበራል። ይቀበላል ~ ይቀበል) ስም ይወጣል ከቤት፥ ይኼዳል ጎረቤት።          ዗ይኗ) ስም ይወጣል ከቤት፥ ይከተላል ጎረቤት። (ይከተላል ~ ስም ጥራ ቢሉት፥ ዓመተ ዗ይኑ። (዗ይኑ ~ ስምሽ ማነው ሲሎት፥ ቂጤ ትልቅ ነው አለች። ስምን መላክ ያወጣዋል። ስምንተኛ(ው) ሺ፤ ሰው አበላሺ። ስሞታ፥ የውርርድ እኩላታ። ስምህ ማነው? ለአገር አይመች፥ ማን አወጣልህ? አሮጋግቶች። ስምህ ማነው? ለአገር አይመች፥ ማን አወጣልህ? ጎረቤቶች። ስም እኩል፤ ሥራው ስንኩል። ስበላ ቢመሽብኝ፥ ጭንቅር ይበልብኝ። (ጭንቅር ~ ጥንቅር) ሥብ ሉያርደ፥ ጉፋያ ይነደ። (ሉያርደ ~ ሲያርደ) ስቦ ያስገቡት፥ ስቦ ያወጣል። ስታበዪው፥ በልተሽ ታዪው። ስታበጀው ውላ፥ ባተላ። ስታበጅ ውላ፥ አበላሸችው ባተላ። ስታቦካ ውላ፥ ባተላ። ስትታጭ ያጣላች፤ በሰር጑ ታጋድላለች። ስትኼድ ቀንጣ ቀንጣ፤ ስትበላ እንደ አንበጣ። ስትሞት የማያለቅስልህን፥ ታመህ እየው። ስትሠራ ሥራ፥ ስትጫወት ተጫወት። ስትወልድ የምትበላውን፥ በእርግዝናዋ ጨረሰችው። ስት዗ጋው አይሰማብህ፤ ስትከፍተው ኮሽ አይበልብህ። ስትግደረደሪ፥ ጦም አትደሪ። ስትግደረደር፥ ጦምህን አትደር። ስትግደረደሪ፥ ጦምሽን እንዳታድሪ። ስትግደረደሪ፥ ጦምሽን እደሪ። ስትጠጣ አይተህ፤ ስትፈርም አንብበህ። ስትፈጭ የነበረች፤ ማን጑ለል አቃታት። ስትፈጭ የነበረች፤ ሲፈጩላት ደከመች። ስትፈጭ የነበረች፤ ስትነፋ ከበረች። ስቸገር የረዳኝ፤ በጥፊ ይምታኝ። ስንተዋወቅ አንተናነቅ። ስንት ያመጣ? ሠኔ። ስንዝር ሲለቁለት፤ ክንድ ፈለገ። ስንዝር ሲስቡት ጋት። ስንዝርና ጋት፤ አባትና እናት። ስንዳ ለመቁረብ፤ ዋስ ለማቅረብ። ስንዳ ራቱ፥ ወይራ እሳቱ፥ ማለፊያ ሚስቱ፥ ለምን ሰርግ ይኼዳል? ሰርግ አለ በቤቱ። ስንዳ በማድ፥ ይመስላል በረድ። ስንዳ በጤና። ስንዳ በጭምቅ፤ ባለጌ በጥብቅ። ስንዳ በጭንቅ፤ ባለጌ በጥብቅ። ስንዳ ቢፈትጉት ይነጣል፤ ነገር ቢመረምሩት ይወጣል። ስንዳ ከአልተከተተ፤ መነኰሴ ከአልሞተ። ስንዳ ካለ፥ ፈታጊ አይታጣም። ስንዳና ጤፍ ገበታ ያሳሳል። ስንዳ፥ ምን አልኩ ዗መዳ? ምስር፥ እስኪ ቀሥር። አተር፥ እስኪ ተርትር። ባቄላ፥ አንተም እንደ ላላ። ስንዳውንም አልበላ፥ ከወጥመድም አልገባ። ስውተረተር፥ ደረሰልኝ ዓተር። ስን኱ን ረኃብ፥ ጥጋብንም እችላለኹ። ስን኱ን ከጦርነት፥ ከወሬም አልፈራ። ስንዝር ሲሉት፥ ክንድ። ስደቡኝ ባይ፥ ከመንገድ ያራል። ስደተኛ ሲሰነብት፥ ይሆናል ባላባት። ስደት ለወሬ ይመቻል። ስደት ከጨዋ ልጅ፥ መንገድ ከሀገር ልጅ። ስደት ከጨዋ ልጅ፥ መንገድ ከሹም ልጅ። ስደትና መንገድ አያልቅም። ስደትና አግዳሚ፥ ዅሉንም እኩል ያደርጋል። ስደትና አግዳሚ ወንበር፥ እኩል ያስቀምጣል። ስደትና እብደት፥ ከአረጁ በኋላ አያምርም። ስድ የለመደ ጥጃ፥ ሲይዙት ይ጑ጉራል። ስድብ በላይህ አይለጠፍብህም። ስድብ፥ በልጅ ያምራል። ስድብሽና ስድቤ እኩል ነው፥ ትርፉ ሰው መስማቱ ነው። ሥጋ ሆነብኝ። ስግብግብ አንደ ያንቀው፥ አንደ ይወድቀው። ስጡኝ አለማለት፥ ከወዳጅ መሰንበት። ስጣቸው፥ ለራስ በእጃቸው። ስጥ ለእኔ፥ ድገም ለእኔ። ስጥ ለእንግዳ፤ አንተም ጠጣ፤ ለእኔም አምጣ። ሦስቱን ቢጠጣቸው፥ ኹለቱን ጣላቸው። ሦስቴ ከመፍሳት፥ አንዳ መቅ዗ን። ሸማ ለብሶ ስልቻ፤ በቅል ጭኖ ለብቻ። ሸማ ማዋስ ለባላገር፤ በቅል ማዋስ ለወታደር። ሸማ በውሃ፤ ሰው በንስሓ። ሸማ በየፈርጁ ይለብሳል። ሸማና ምስጥ፥ ወደ ውስጥ። ሸማኔ በመኑ፤ ጠይብ በከሰሉ። ሸማኔ በድሩ፤ ጠይብ በመንደሩ። ሸማኔ ውሃ ሙላት ሲወስደው፥ እስከ አዅን አንድ እውረውር ነበር አለ። ሸማኔ ድውሩን፤ ባለ ሥልጣን ክብሩን። ሸማን በውሃ፤ ሰውነትን በንስሓ። ሸማን ጠምዝ ያሰጧል፤ እህልን አላምጦ ይበሎል። (ይበሎል ~ ይውጧል) ሸረኛ ጥጃ፥ ቢያርዶትም አትተኛ። ሸርሙጣ ስታረጅ፥ አቃጣሪ ትሆናለች። ሸርሙጣን የወደደ፤ ልብሱን ጥል ያበደ። ሸርደም ሸርደም ብትኼድ፤ ጎርደም ጎርደም መጣች። ሸንበቆ በመር዗ሙ፥ ምሰሶ አይሆንም። ሸንበቆ በመር዗ሙ፥ አይሆንም ምሰሶ። ሸኚ ቤት አያደርስም። ሸኚ እቤት አያገባም። ሸኚና ጥላ ቤት አይገባም። ሸኝ ቤት አይገባም። ሸክላ ሲሰበር ያው አፈር ነው። ሸክላ ቢጥሉት፥ ገለባ። ሸዋ ሲጥል እንጂ ሲተኩስ አይታይም። ሸዋ በአላመጠ በዓመቱ ይውጣል። ሸዋ በአኘከ በዓመቱ ይውጣል። ሸውራራ ብት኱ል፥ ለትዝብት። ሸፎ ገመዳ፥ ቢሞት አይጎዳ ቢሰበር ዕዳ። ሹመት ላወቀው ይከብደዋል፥ ላላወቀው ያሳብደዋል። ሹመት ሲገኝ፥ ዗መድ አይገድም። ሹመት የለመደ፥ ወንዝ ዳር ይወርዳል። ሹመትና ቁመት አይገኝም በምኞት። ሹመትና ቁመት ከልኩ አያልፍም። ሹም ለመነ። አ዗዗። ሹመት፥ ሺህ ሞት። (ሹመት ~ ሺመት) ሹመት በተርታ፥ ሥጋ በገበታ። ሹም ለሹም ያወርሳል፤ ጉም ተራራ ያለብሳል። ሹም ለሹም ይጎራረሣል፤ ድሀ ለድሀ ይለቃቀሳል። ሹም መክሰስ፤ ወጀድ ማረስ አይቸግርም። ሹም ሲቆጣ፥ ማር ይዝ እደጁ፥ ደስ ሲለው፥ ማር ይዝ እደጁ። ሹም ሳይለፈልፍ፥ ይደፈድፍ። ሹም ቢሞት ቀባሪው ኀምሳ፥ የሹም ልጅ ቢሞት መቶ ኀምሳ። ሹም ባይለፈልፍ፥ ይደፈድፍ። ሹም ቢሞት ኀምሳ፤ የሹም ልጅ ቢሞት መቶ ኀምሳ። ሹም ነገር ሲፈልግ፥ የድሮ ሻኛ አምጡልኝ ይላል። ሹም ከአ዗዗ው፤ ስሜት የወ዗ወ዗ው። ሹም ያዚል፤ ቄስ ይናዝዚል። ሹምና ማር እያደር ይከብዳል። ሹምና የጋማ ከብት፥ በጊዛ ይከተት። ሹምና ጥጥ እያደር ይከብዳል። ሹምና ጥጥ እያደር ይከዳል። ሹሩባ ልትሠራ ኼዳ፥ ተላጭታ መጣች። ሹሩባ ትሠራ ኼዳ፤ ጠጉሯን ተላጭታ መጣች። ሹክሹክታ፥ የጠብ ወለምታ። ሺ ሉበላ፥ አንድ ይጠላ። ሺ በመከረ፥ አንድ በወረወረ። ሺ በመከር፥ አንድ በወረወር። ሺ ቢታለቡ፥ ከገላ አላልፍም (አለች ድመት)። ሺ ቢያጩሽ፥ አንድ ያገባሽ። ሺ አውል፥ ከሚሞት ሺ ይሙት። ሺ ዝንብ፥ መሶብ አይከፍትም። ሺ ያጭሽ፥ አንድ ያገባሽ። ሺ ይሙቱ፥ ሺ አውል አይሙት። ሺ ጊዛ ቢፈጠር ግርግር፥ መች ይቀራል ግብር። ሺሕ ቢታለብ፥ አንድ በገላ አለች ድመት። ሺም ታለበ፥ አንድ ያው በገላ። ሺን አሸን። (ሺን በፈረንሳይኛ ቻይና። ሻማ ራሱ ነድ፥ ራሱ ብርሃን ይሰጣል። ሻማ ራሱ እየተቃጠለ፥ ለላልች ብርሃን ይሰጣል። ሻሽ ይደምቃል፥ ማቅ ይሞቃል፥ የሚበጀውን ባለቤቱ ያውቃል። ሻኛ ለጀግና። ሻጭ፥ ገዥ ሆኖ ይገምታል። (ሻጭ ~ ሽያጭ) ሼህ ሙልጭ፤ ሼህ ቁልጭ። ሽል እንደሆን ይገፋል፤ ቂጣም እንደሆን ይጠፋል። ሽል ከሆነ ይገፋል፤ ቂጣም ከሆነ ይጠፋል። ሽልና ዗ር፥ በሞፈር ቀዳዳ ያመልጣል። ሽመልና ዗ንግ፤ ቂልና በግ። ሽማግላ ሳለ ምክር አይጠፋም፤ ጎልማሳ ሳለ ላም አይነዳም። ሽማግላ በሀሰት ይፈርዳል፤ በእውነት ያስታርቃል። ሽማግላ በምክሩ፤ አርበኛ በሰናድሩ። ሽማግላ ከአለበት ሸንጎ፥ ነገር አይነጠቅበት። ሽማግላ ከአለበት፤ ነገር አይሰረቅ። ጎበዝ ከአለበት፤ በትር አይነጠቅ። ሽማግላ ከአለበት፤ ነገር አይናቅበት። ሽማግላ ከአልሞተ፤ ስንዳ ከአልመረተ። ሽማግላ ከአልሞተ፤ ስንዳ ከአልሸተ። ሽማግላ የላለበት፤ ሀገር ባድ ይቀር። ሽማግላ የተተወ ጌጥ። ሽማግላ ይገላግላል፤ የተጠቃ አቤት ይላል። ሽማግላና ስልቻ ሳይሞሉ አይቆሙም። ሽማግላና ጅብ በላላባት ይገባል። ሽማግላን ከምክር ከመለየት፤ ከምግብ መለየት። ሽሮን ሲሸውዶት፥ ፕሮቲን ነሽ አሎት። ሽሽት፥ ከኡኡታ በፊት። ሽበት ምን ታረግ መጣህ ቢሉት፥ እኖር ብዬ አለ። ሽታና ግማት፤ ላልሰማ ማውራት። ሽበት እኖር ብዬ፥ መጥቻለኹ አለ። ሽንብራ፥ መኖር በመከራ። ሽንኩርት አንድም በሉት ሽታ፥ ኹለትም በሉት ሽታ። ሽንኩርት አንድም በሉት ገማ፥ ደገሙትም ገማ። ሽንኩርት አንድም በሉት ገማ፥ ደገሙትም ገማ፥ የተባባልነውስ አልቀረም ተሰማ። ሽንኩርት የባሕሪውን ይሸታል። ሾላ በድፍን። (በድፍን በድፍኑ) ሾተልን ወደ ሰገባህ፤ ቁጣህን ወደ ትዕግሥት። ሾተልን ወደ አራዊት፤ ቁጣህን ወደ ትዕግሥት። ሾተልን ወደ አፎት፤ ቁጣን ወደ ትዕግሥት። ቀለም ሲበጠበጥ፤ ብዕር ሲቀረጥ። (ብዕር ~ ብርዕ) ቀለም ሲበጠበጥ፥ ብርዕ ቅረጹልኝ። ቀለበት ለቆማጣ፤ ሚድ ለመላጣ። ቀለብ የላለው ውሻ፥ ጣዱቅ አምጡልኝ ይላል። ቀሉል አማት፥ ሢሶ በትር አላት። ቀላዋጭ፥ ወጥ ያውቃል። ቀላጅ፥ የሰይጣን ወዳጅ። ቀልብ የላለው ውሻ፥ ጠዱቅ አምጡልኝ ይላል። ቀልደኛ፥ አልቅሶ ከአልተናገረ፥ የሚያምነው የለም። ቀልደኛ ገበሬ፥ ሲያሥቀን አደረ። ቀልደኛ ገበሬ፥ በሚሉኒየም ይሞታል። ቀልደኛ ገበሬ፥ ናይት ክለብ ከፈተ። ቀልደኛ ጎረምሳ፥ እያራ ያፏጫል። ቀልድና ቅ዗ን፥ ቤት ያበላሻል። (ያበላሻል ~ ያጠፋል ~ ይፈታል) ቀሙን ላይቀር፥ ከነጫማቸው። ቀማኛ ዋሻውን፤ ድሀ ስልቻውን። ቀማኛና ሽፍታ፤ ጨለማና ማታ። ቀስ በመቀስ። ቀርቀሬ ኼጄ ማር ስበላ፥ ማር ልክፈል። ቀርቀሬ ወርጄ ማር ስልስ፥ ማር ልክፈል። ቀበሮ ናት የገጠሯ፤ ሚዳቋ ናት የሰፈሯ። ቀስ በቀስ፥ አባይም ዝናብ ይሆናል። ቀስ በቀስ፥ እንቁላል በእግሩ ይኼዳል። ቀስ እንዳይደፈረስ። ቀስ እንዳይፈስ። ቀበሮ፥ የበሬ ቆለጥ ይወድቅልኛል ብላ ስትከተል ዋለች። ቀበሮ፥ የበሬ ቆለጥ ይወድቅልኛል ብል ሲከተል ዋለ። ቀበሮን ለማምለጥ፤ ጅብን እጉም አለች በግ። ቀበቶ ለማፈኛ፤ ሰንሰለት ለማቆራኛ። ቀበኛ ማሰሪያውን፥ በልቶ ያሳጥራል። (ያሳጥራል ~ ያሳጥረዋል) ቀበኛ ከብት፥ ማሰሪያውን በልቶ ያሳጥራል። ቀበኛ ከብት፥ ዋጋውን ያደርስ። ቀባሪ ሲገባ፥ እግዙአብሔር ይማርህ። ቀባሪ በፈጣሪ። ቀባሪ በፈጣሪ፤ ጠዋሪ ቀባሪ። ቀብረው ሲመለሱ፥ እግዛር ይማርዎ። ቀብሮ የሚመለስ፥ የሚመለስ አይመስለውም። ቀኑ ሳይመሽ፤ ብርሃን ሳይሸሽ። ቀኑ የጨለመበት፥ መንገደ ዗ንግ ነው። ቀና ሲታጣ፤ ይመለመላል ጎባጣ። (ሲታጣ ~ ቢታጣ) ቀናቸው ደርሶ እስከሚፋቱ፥ ይባላሉ አንቱ። ቀናውን ብነግራት፥ ውልግድግደን አለች። ቀን ለሰራዊት፤ ላሉት ለአራዊት። ቀን ለተባባሰው፥ ማጭድ አታውሰው። ቀን ሰው፤ መስል ማታ ጅራት አብቅል። ቀን ሲከፋ፥ በግ ይነክሳል። ቀን ሲደርስ፤ አምባ ሲፈርስ። ቀን ሲደርስ፥ የለበሱት ጋቢ ጠልፎ ይጥላል። ቀን ሲገለበጥ፥ ውሃ ወደ ላይ ይፈሳል። ቀን ሲጥለው፥ ዅሉ ይጠላው። ቀን ሳይቆጥሩ፤ ውሻ ሳይጠሩ ደረሰ በእግሩ። ቀን በቅል፤ ማታ ቆል። ቀን በበቅል፤ ማታ በቆል። ቀን በአጀብ፤ ላት በ዗ብ። ቀን ቢረዝም፥ ልብ ያደክም። ቀን ቢረዝም፥ ልብ ይደክም። ቀን ቢቆጥሩ፤ ውሻ ቢጠሩ ይደርሳል በእግሩ። ቀን ቢቆጥሩ፤ ውሻ ቢጠሩ ደረሰ በእግሩ። ቀን ቢደርስ፤ አምባ ይፈርስ። ቀን አይጥለው፤ ጠጅ አያሰክረው (የለም)። ቀን አይጥለው፥ የቀለም ሰረገላ አያሰናክለው። ቀን እስኪወጣ፥ የአባቴ ገበሬ ያግባኝ። ቀን እስኪያልፍ፥ የአባቴ ባሪያ ያግባኝ። ቀን እስኪያልፍ፥ የአባቴ ባሪያ ይግዚኝ። ቀን እስኪያልፍ፥ የአባትሽ ልላ ያግባሽ። ቀን እስኪያልፍ፥ የአባትህ ባሪያ ይግዚህ። ቀን እንደ ተራዳ፥ ላሉት እንደ ግርግዳ። ቀን ከሕዝብ፤ ላት ከጅብ። ቀን እስኪያልፍ፥ ያለፋል። ቀን ከጣለው፥ ኹሉ የጠላው። (የጠላው ~ ይጠላው) ቀን ከጣለው፥ ዅሉ ይጥለው። ቀን ካልለቀሙ፤ ላት አይቅሙ። ቀን ወጣ፤ መከር ነጣ። ቀን የሰጠው ቅል፥ ቅምጫና ይሆናል። (ቅምጫና፦ የሙሽራ ቅቤ ማስቀመጫ) ቀን የሰጠው ቅል፥ ድንጋይ ይሰብራል። ቀን የጎደለበት ጠገራ፥ አይጥ ይበላዋል። ቀን ያልፋል፥ እስከዙያው ግን ያለፋል። ቀን ይነዳ፥ እንደ ፍሪዳ። ቀን ደርሷል፤ አምባ ፈርሷል። ቀንበር ታርቆ፤ ጣውንት ታርቆ ምን ይሆናል። ቀንበር ታንቆ፤ ጣውንት ታርቆ ምን ይሆናል። ቀንና ጨርቅ፥ እንደምንም ያልቅ። ቀንና ጨርቅ ያልቃል፤ ብልኅ ያውቃል። ቀንደ ሰማይ ጠቀስ፤ ጭራው ምድር አበስ። ቀንዳምን በሬ፥ ቀንድ ቀንደን። ቀንድ ከአላት ላም፥ ጎዳ ትከፋለች። ቀንድ ከአላት ይልቅ፥ ጎዳ ትከፋለች። ቀንድ ውስጥ ገብቶ፥ ጅራት አይቀርም። ቀንድ የገባበት፤ ጅራት አይቀርም። (የገባበት ~ እገባበት) ቀንድና ጅራት፥ ለዋንጫ አለፉ። ቀንጠፋ ልጄን ይዝ ጠፋ። ቀኝም ሰረሩ፥ ግራም ሰረሩ፥ መገናኛው ኮሩ። ቀኝም ሰገሩ፥ ግራም ሰገሩ፥ መገናኛው ኮሩ። ቀኝና ግራ፤ ጭራና ደብተራ። ቀይ መላሱ፤ ጥቁር ራሱ። ቀይ፥ መልክ አይገፋም። ቀይ ሰው፥ መልክ አይፈጅም። ቀይ እና ወርቅ ሲብለጨለጭ ያልቅ። ቀይ እንደ በርበሬ፤ ጥሩ እንደ ብርላ። ቀዳ አላለበሰች፤ ቆርሳ አላጎረሠች። ቀዳሚ ተጠቃሚ። ቀዳዳ ያፈሳል፥ ግቢ ያፈርሳል። ቀድ ያለበሰ፤ ቆርሶ ያጎረሠ። ቀጣፊን ያመነ፤ ጉም የ዗ገነ። ቀጥኜ ቢያየኝ፥ ጅማት ለመነኝ። ቀጥኜ ቢያዩኝ፥ ጅማት ለመኑኝ። ቀድሞ ድሮ ቅድም ወይ ጌሾ፥ እንንም አውሬ አይጠጣሽ። ቀድሞ ማን ቢስምሽ? ታሞጠሙጫለሽ። ቀድሞ ሰኞን አለመሆን ነው። ቀድሞ ነበር እንጂ፥ መጥኖ መደቆስ፥ አኹን ምን ያደርጋል ድስት ጥድ ማልቀስ። ቀድሞ ነበር እንጂ፥ ተራምድ ማለፍ፥ አዅን ምን ይሆናል ተይዝ መለፍለፍ። ቀድሞ የሸተውን ወፍ ይበላዋል፤ ቀድሞ የሚናገረውን ሰው ይጠላዋል። ቀድሞ የተናገረን ሰው ይጠላዋል፤ ቀድሞ የወለደን ወፍ ይበላዋል። ቀድሞ ያሸተን አሞራ ይበላው፤ ቀድሞ የተናገረን ሰው ይጠላው። ቀድሞ ያሸተን ወፍ ይበላው፤ ቀድሞ የተናገረን ሰው ይጠላው። ቀድ አላለበሰ፤ ቆርሶ አላጎረሠ። ቀጥኜ ቢያዩኝ፥ ሞዳል ነሽ አሉኝ። ቁልቢጥ የላት፥ ቁና አማራት። ቁልቢጥ የላት፤ ድርጎ አማራት። ቁመቷ ቢያጥር እንደ ድንብላል፤ ውዶ ክፉ ነው ይደበልላል። ቁመህ ተናገር፤ ዙረህ ተመካከር። ቁመህ ተከራከር፤ ዙረህ ተመካከር። ቁም ነገረኛ መምሰል፥ የተለመደ አመል። ቁም ነገር ከዋዚ፤ ዋዚ ከቁም ነገር። ቁም ነገር ይዝ ተረት፤ ቂም ይዝ ጸልት። ቁም እንደ ማማ፤ ቁርጥ እንደ ጫማ። ቁም እንደ ሳማ፤ ቁርጥ እንደ ጫማ። ቁም እንደ አላማ፤ ቁርጥ እንደ ጫማ። ቁሞ የሰቀሉትን፥ ተቀምጦ ለማውረድ አይሆንም። ቁስሉን ትቶ፥ ንፍፊቱን። ቁራ ሲነጣ፥ አህያ ቀንድ ያወጣ(ል)። ቁራ፥ ስሙን የጠራ። ቁራ በልቷል። ቁርበት ምን ያንቋቋሀል ቢሉት፥ ባያድለኝ ነው እንጂ፥ የነጋሪት ወንድም ነበርኩ አለ። ቁርበት ምን ያን጑጑ሀል ቢሉት፥ ባያድለኝ ነው እንጂ፥ የነጋሪት ወንድም ነበርኩ አለ። ቁርጥ ያጠግባል፤ ተስፋ ያታልላል። ቁርጥማት ቢያብር፥ አልጋ ላይ ያማቅቃል። ቁቅም ከፈስ ተቆጠረች። ቁና ለመስፈሪያ፤ ብርብራ ለማስከሪያ። ቁንጥጫ፥ ይሻላል ከግልምጫ። ቁንጫ ሞኝ ናት፥ ቀን ትበራለች ተለቃቅማ ታልቃለች። ቁንጫ በበላ፤ ዳውላውን በደላ። ቁንጫ ውሃ ውረጂ ቢሎት፥ ስፈናጠር የሰው ድጮ አሰብር አለች። ቁንጫ የተጠረገ ዕለት፤ ባለጌ የተመከረ ዕለት። ቁንጫ፥ ለትልቅ ሰው ይበረታል ይባላል። ቁንጫ መኼድ ሳትማር፥ መዝለል ትማራለች። ቁጡና ብስጩ፤ አልማችኹ ፍጩ። ቁጥቋጦ፥ ያለዚፍ አይሆንም። ቁጥቋጦ(ም) ሲያድግ፥ ዚፍ ይሆናል። ቁጥቋጦና ታሪክ፥ ከመቃብር በላይ ነው። ቁጭትና መረቅ፥ ለጊዛው ይጣፍጣል። ቁጭትና መጠጥ፥ ለጊዛው ይጣፍጥ። ቁፍ ቁፍ አሰኘሽ እንደቄብ ድሮ፥ ለመከራ ላሣርሽ ኖሮ። ቂል ሲረግሙት፥ የመረቁት ይመስለዋል። ቁፍ ቁፍ አሰኘሽ እንደቄብ ድሮ፥ ለመከራ ላሣርሽ። ቂል ከጠገበበት፥ አይወጣም። ቂል ጠጉርህ አደገ ቢሉት፥ ጸደቅኹ አለ። ቂል ያገኘው ፈሉጥ፤ ውሻ የደፋው ሉጥ። ቂል ያገኘው ፈሉጥ፤ ውሻ ያየው ሉጥ። ቂልን ለብቻው ስደበው፥ ራሱን በአደባባይ እንዱሰደብ። ቂልን አንድ ጊዛ ስደበው፥ ሲሰደብ ይኖራል። ቂም ቂም ያሰኘሽ እንደ ድሮ፥ ለካስ ለመከራሽ ለአሣርሽ ኖሮ። ቂም ይዝ ጸልት፤ ሳል ይዝ ስርቆት። ቂም ይዝ ጸልት፤ ጭድ አዝል ወ዗ት። ቂምህን አትርሳ፤ የወደቀን አንሣ። ቂጡ የቆሰለ ውሻ፥ እንደልቡ አይጮህም። ቂጡን የተወጋ ውሻ፥ እንደልቡ አይጮህም። ቂጥ ቢወድል፥ ፈስ አያድን። ቂጥ ቢያብጥ፥ ልብ አይሆንም። ቂጥ ገልቦ ክንብንብ። ቂጥኛም ከውርዳ መጫወቱ፥ ድሮም የነበረ ነው። ቂጥኛም ከውርዳ ይማከራል። (ይማከራል ~ ይውላል) ቂፍ ቂፍ ያሰኘሽ እንደ ቄብ ድሮ፥ ለመከራሽ ለአሣርሽ ኖሮ። ቃል ያስገቡት፥ ቃል ከሚረሳ፥ የወደቀ አይነሣ። ቃልህ ሳይ዗ጋ፤ እግርህ ሳይ዗ረጋ። ቃልና ቅል ለየቅል። ቄሱም ዝም፤ መጽሀፉም ዝም። ቄስ ለኑዚዛ፤ ፍቅር ለሚዛ። ቄስ ምን ይሻል ጠላ፤ ነገር ምን ይሻል ችላ። ቄስ ዔርክሶን መምህሩ፥ እናት አያስቀብሩ። ቄስ እበር፤ አረመኔ ከማኅበር። ቄስ ከአና዗዗ው፤ ዕድሜ ያና዗዗ው። ቄስ ከአፈረሰ፤ ዱያቆን ከረከሰ። ቄስ ያ዗዗ህን አድርግ፤ እንጂ ቄስ ያደረገውን አታድርግ። ቄስና አሞራ፥ በበላበት ይጮሀል። ቄስና ንብ፥ እያዩ እሳት ይገባሉ። ቄስና ንብ፥ እያየ እሳት ይገባል። ቅል በአገሩ፥ ድንጋይ(ን) ይሰብራል። ቅልና ድንጋይ ተማትቶ፤ ልላና ጌታ ተሟግቶ (የማይሆን ነው ከቶ)። ቅልና ድንጋይ ተማትቶ፥ ጌታና ልላ ተሟግቶ፥ የማይሆን ነው ከቶ። ቅልውጥ አሳስቦ፥ ይጥላል ዗መቻ። ቅመሙ የበዚበት ወጥ፥ አይፋጅ አይኮመጥጥ። ቅማል በጥፍር ቢድጧት፥ ራስ ደኅና አለች። ቅማል እን኱ን ከአቅሟ፥ ጥብጣብ ታስፈታለች። ቅማል ከአከላት፤ ምሥጢር ከቤት። ቅማል ውሃ ውረጂ ቢሎት፥ ስንዳሰስ ለመቼ ልደርስ? ቁንጫ ውሃ ውረጂ ቢሎት ስፈናጠር የሰው ድጮ እሰብር አሉ። ቅምሙ የበዚበት ወጥ፥ አይፋጅ አይኮመጥጥ። ቅምዝምዝ ወዱያ፥ ፍየል ወዱህ። ቅርብ ያለ ጠበል፥ ልጥ ይነከርበታል። ቅርብ ያለ ጠበል፥ ቆዳ መንከሪያ ይሆናል። ቅርናታም ለቅርናታም፥ ሰንቡላ ሰንቡላ ይባባላል። ቅርንጫፉ እንደዚፉ። ቅርንጫፍ ከአበዚኹ፥ ወዱህ ነው የወደቅኹት አለ ቁልቋል። ቅቤ መዚኝ፥ ድርቅ ያወራል። ቅቤ ሲለግም፥ ወስፌ አይበሳውም። ቅቤ ሻጭ፥ ድርቅ ያወራል። ቅቤ ተነጥሮ ለመብላት፤ የአባት የእናት። ቅቤ ነጋዳ፥ (዗ወትር) ስለ አቧራ ያወራል። ቅቤ ይፍሰስ፥ ከገንፎ አይለፍ። ቅቤ ይፍሰስ፥ ከገንፎ አይተርፍ። ቅቤ፥ አናት ላይ የወጣኹት ተገፍቼ ነው፥ አለች አሉ። ቅቤ አንጣሪቱ እያለች፥ መቅመቆ ማሽቱን ምታት መታት። ቅቤ አንጣሪዋ እያለች፥ ጎመን ቀንጣሿን ምች መታት። ቅቤ ከመብላት፥ መቀባት። ቅቤና ቅልጥም፥ ወዳት ግጥምጥም። ቅብጥብጥ ያለች ሴት፥ ወይ ለወንድ ወይ ለወጥመድ። ቅኑት እንደ ገበሬ፤ ጥሙድ እንደ በሬ። ቅና ያለው፥ በአባቱ ከረባት ይቀናል። ቅና ያለው፥ በእናቱ ብልት ይቀናል። ቅናት እንዳያጠብቀው፥ ሆደን ይሸልጋል። (ይሸልጋል ~ ይነፋል) ቅናት ጥናት፥ አያገናኝ ከእናት ከአባት። ቅናት ጥናት፥ አያገናኝ ከአባት ከእናት። ቅናት ጥናት፥ አይገኝም ከእናት ከአባት። ቅናት፥ ያደርሳል ከሞት። ቅኔ ያልተማረ፤ ቄስ ሙቀጫ ያላሸው ገብስ። (አንድ ነው) ቅን ሬሳ፥ በደጀ ሰላም ኺድ ይሞታል። ቅን በቅን ከማገልገል፥ ፊት ለፊት ማውደልደል። ቅንቡርስ የት ትኼዳለህ? መተማ ትደርሳለህ? ልብማ። ቅንነት፥ ለነፍስ መድኀኒት። ቅንድብ፥ ለአይን ጥቅሻ አስተማረች። ቅዝምዝም ሲወረወር፥ ጎንበስ ብለህ አሳልፈው። ቅዝምዝም ወዱያ፥ ፍየል ወዱህ። ቅዟት ተፈርቶ፥ ሳይተኛ አይታደርም። ቅጡም የምንኩስና ነው። ቆላና ደጋ፤ እመቤትና አልጋ። ቆል ለ዗ር፤ እንድድ ለድግር አይሆንም። ቆልን ቢቆረጥሙት እንጂ፥ ቢያሹት አያልቅም። ቆመው የሰቀሉትን፥ ቁጭ ብለው ለማውረድ ይቸግራል። ቆማጣ ቤት፥ አንድ ጣት ብርቅ ናት። ቆማጣ ብለው፥ ያው ቁምጥና ነው፥ ላላ ምን ይመጣል አለ። ቆማጣን ቆማጣ ከአላሉት፥ ገብቶ ይፈተፍታል። ቆሩ መቀበሪያው፥ ያው ፈሩ። ቆሩ በማን፥ ምድር ትለፋ። ቆርሶ ያላጎረሡትን፤ ቀድ ያላለበሱትን ብላቴና ማ዗ዝ አይገባም። ቆቅ ማሪ አቦዬ። ቆቅ ወዱህ፥ ቅዝምዝም ወዱያ። ቆቅ የሰገረ፤ ወፍ የበረረ። ቆቅና ባላገር፥ በራሱ ያወራል። ቆቅና ባለጌ፥ በራሱ ያወራል። ቆቅና ባለጌ፥ በራሱ ይጮሀል። ቆብ በጫኑ ባመታቸው፥ ሹሩባ ከጀላቸው። ቆንጆ ሴት፥ ቆንጆ ጭንቅ ናት። ቆንጆና እሸት አይታለፍም። ቆንጆን ሳሚ እንጂ፥ አግቢ የለም። ቆዳ ሲወደድ፥ በሬህን እረድ። ቆዳ ማን጑጑ቱን፤ ሥሡ መ጑጑ቱን (አይተውም)። ቆዳን በእርጥብነቱ ያጥፏል። ቆጥ ሳይሠሩ ድሮ፤ አዝመራ አሳምሮ ለዝንጀሮ። ቆጥሮ የማይሰጥ ላባ፤ ቆጥሮ የማይቀበል ላባ። ቋሚ ለ጑ሚ። ቋንጣ፥ ሉወጋኝ መጣ። ቋንጣና ባለሟል፥ ሳያር አይቀርም። ቋያ፥ መጥፎ ቡቃያ። ቋግሚት፥ ተጠዋሪቷ ባልቴት። በሀምላ በነሀሴ፥ ቀረችልኝ ነፍሴ። በሀምላ ወጨፎ፤ በሠኔ ርክፍካፎ። በሀምላ ጎመንና አሞላ። በሀምላ፥ ጤፍ ይ዗ሩ፥ ቤት ይሠሩ። በሀሰት መሰከርኩልህ ቢለው፥ እኔም ታ዗ብኩህ አለው። በኹለት ሀሳብ፥ እስከ መቼ ታነክሳላችኹ። በለምለም ምላሴ ኮሸሽላ በላኹበት አለ(ች) አህያ። በለጠች እንዱሉኝ፥ አክሱም ጽዮን ቅበሩኝ። በለፈለፉ፥ በአፍ ይጠፉ። በሉት አለቀ፤ ፈጩት ደቀቀ። በሉቃውንቱ መሀል አትጥቀስ። በላይ በላዩ ያጎርሣታል፥ የበላችው ያገሳታል። በል በለውና በረጅም ሰልፋ፥ እንደ ወለደች እናቱ ትልፋ። በል በል ይላሉ ሲፈርደ፤ ጣል ጣል ይላሉ ሲያርደ። በል ያለው የበላላው፥ ተው ያለው ያተተው። በልብ አምኖ፤ በአፍ መንኖ። በልተው ከአልጠጡ አረር፤ ወልደው ካላኩ እነር። (እረር ~ አነር) በልተው ከጨረሱ፥ ከመኝታ ይነሡ። በልቶ መጠጥ ያጣ፤ ተበድል ፍርድ ያጣ። በልቶ እንደ እንሰሳ፤ ተኝቶ እንደ ሬሳ። በልቶ የማይመርቅ፥ ገበያ ወጥቶ የማይጠይቅ። በልቶ የማይበርደው፥ የሰው ነገር የማይከብደው ኹለቱ አንድ ነው። በልቶ የማይበርደው፥ የሰው ነገር የማይከብደው (አንድ ነው)። በልቶ የከሳ፤ የነገሩትን የረሳ። በልቼ እንደ እንሰሳ፤ ተኝቼ እንደ ሬሳ። በልኩ የሚበላ፥ ሰላማዊ እንቅልፍ ይተኛል። በልክ ዗ምር። በልጁ ቆዳ፥ (ተጠቅልል) የተቀበረ የለም። በልጅ አመሀኝቶ፥ ይበሎል አንጉቶ። በልጅነት ወደ ገዳም፤ በርጅና ወደ አለም። በልጅነት ያልተወለደ ልጅ፥ በአባቱ ተዝካር፥ ፊኛ ይለምናል። በመልካም አንገት፥ ዕንቅርት። በመልካም ዳኛ መሟገት፤ በመልካም ዋገምት መታገም። በመልክ ቢጠፉ፤ በስም ይደግፉ። በመረጡት ዳኛ ቢረቱ፤ በቆረጡት በትር ቢመቱ በማን ያጉመተምቱ? በመሰለው ይናገራል፥ ከበላው ይበላል። በመስተዋት ቤት የሚኖሩ፥ አይወራወሩ። በመስከረም ሉያብድ ያለ፥ ክረምቱ ላይ ጨርቁን ይጥላል። በመስከረም ሴት ያላጨ፤ ስንደድ ያልቀጨ (ዋጋ የለውም ይላሉ)። በመስከረም የሚቆስል እግር፥ በሠኔ ዝንብ ይወረዋል። በመስከረም የሚያብድ፥ በሠኔ ሱሪውን ከፍ ከፍ ያደርጋል። በመስከረም የሚጋገር፥ በሸንጎ የሚናገር (ልጅ ይስጥህ)። በመስከረም ጤዚ፥ እን኱ን አባቴ ጥጃ አልገዚ። በመሸታ ቤት የተገዚ ጦር፥ ቢወረውሩት ከድፍድፍ። በመሸታ የተገዚ ጦር፥ ቢወረውሩት ከድፍድፍ። በመቀንጠብ፥ ሸክም ሽንብራ ያልቅ። በመከሩት ምክር፤ በሸመቁት ጦር። በመ዗ንከው ሚዚን፤ በሰፈርከው ላዳን። በመጀመሪያ የመቀመጫዬን አለች ዝንጀሮ። በመጀመሪያና በኹለተኛው ሽሽ፤ በሦስተኛው ግን ተነሥተህ ተፋለም። በመጠቃቀም የቆመ፥ ፍቅር አይውል አያድር። በመጠቃቀም የተቋቋመ፥ ፍቅር አይውል አያድር። በሙቀጫ ያልተፈተገ ገብስ፤ በቅኔ ያልታሸ ቄስ አንድ ናቸው። በሙቅ ውሃ የታጠበ፤ በሰው ገን዗ብ የቸረ። (የቸረ ~ የተቸረ) በሚታረስበት ጊዛ የሣቀ፥ በመኸር ጊዛ ያለቅሳል። በሚያኝክ፥ ዋጭ አ዗዗በት። በሚያዙያ ጎመን ዗ራ፤ ክረምቱን ዅሉ በላ። በማሚቴ ክርስትና፤ እነሀብትሽን ምሥጋና። በማሰሮ ውስጥ የላለውን፥ መጭለፊያ አይሰጥም። በማር ላይ ወተት፥ ሲረባም ሲሰባም። (ሲሰባም ~ ቢሰባም) በማር አጠገብ፤ ውሃ(ን) ጥገብ። በማር ጠብታ፥ ሀገር ተረታ። በማታየው፥ እጅህን አታድርሰው። በማን ላይ ቆመሽ፥ እግዛርን ታሚያለሽ። በማን ላይ ተቀምጠሽ፥ እግዛርን ታሚያለሽ። በማያድሩበት ቤት፥ አያምሻሹበት። (አያምሻሹበት ~ አያመሹበት) በማፈር፥ ደጃዝማችነት ይቀራል። በምርጫ ከአልሆነ በርግጫ። (ነው እንዱህ አይነቱን) በምርጫ ወይስ በጡጫ። በምን በላህ? በሳማ፥ ባይፈጅህማ። በምን የተነሣ? ይህ ዅሉ ጠባሳ። በምን ተነሣ? በጣቁሳ፥ ምን በጣቁሳ? በዳጉሳ። በምንቸት ጠላ፤ ታፈላ ከጎረቤት ትጣላ። በምክራቸው ተጎደበት፤ በሰይፋቸው ተመቱበት። በምድር መጠቅጠቅ፤ በሰማይ መጠየቅ። በምድር ብሠራ እባቡ መከራ፥ በዚፍ ብሠራ እረኛው መከራ፥ በሰማይ ብሠራ አሞራው መከራ የት ውዬ የት ልደር ጌታዬ። በምድር ዓለም፥ አለ ገን዗ብ የለም። በምድር አይቀር፥ ብድር። በምድር ድንበር፤ በሴት ከንፈር። በምግባሩ፥ አይታወቅ ማማሩ። በምጥ ባጣሽ፥ በእንግዳ ልጅ አላጣሽ። በሞኝ ቁመት፤ መቃብር ይለካበት። በሞኝ ቢፈርደ፤ ሞኝ ይወልደ። በሞኝ እግር፤ ውሃ ሞክር። በሞኝ ክምር፥ ዝንጀሮ ልጇን ትድር። በሞኝ ክንድ፥ የ዗ንድ ጉድ጑ድ ይለኩበታል። (ይለኩበታል ~ ይለኩበት) በሰለ እንብላ፤ በለገ እንዝራ። በሠኔ ተጎልቶ፤ በጥቅምት ጑ጉቶ። በሠኔ ካል዗ሩ፤ በጥቅምት ካልለቀሙ፤ እህል የት ይገኛል በድንበር ቢቆሙ። በሠኔ ዗ርን ይ዗ሩ፥ ቤትን ይሠሩ። በሥራ የኮሰሱ፤ በመንፈስ የረከሱ። በሥራህ ድሀ አትበድል፥ ነጋሪት ባይኖረው እንባ አለው፥ ውሃ ሆኖ ቢኮል ያለ ሞረድ የተሳለ ነው። በረጂም ጦር፥ ባይወጉበት ያስፈራሩበት። በሩቅ ሲያዩት፥ አህያ ፈረስ ይመስላል። በሩጫ ባልንጀራህ፤ አይብለጥህ በጎመን ጉርሻ ባልንጀራህ ይብለጥህ። በራሱ ቤት ሰው የሞተበት፥ በጎረቤቱ ልቅሶ ለማልቀስ አይኼድም። በራት ዋዚ፥ ምሳ ይመስል። በራቸውን ከፍተው፥ ሰው ላባ ይላሉ። በራቸውን ክፍት ትተው፥ ሰውን ላባ ነው ብለው ያማሉ። በሬ ሆይ፥ ሣሩን አየህና ገደሉን ሳታይ። በሬ ሆይ በሬ ሆይ፥ ሣሩን አይተህ ገደሉን ሳታይ። በሬ ሆይ፥ እኔ ለአንተ ብዬ፥ ገለባ ቆልዬ፥ ውሃውን ደልድዬ። በሬ ለስበት፤ ጥገት ለወተት። በሬ ሲያረጅ፥ ከጥጃ ይውላል። በሬ ቅባቱን በቅልጥሙ ይዝ ይኖራል፥ ለምንህ ቢሉት ኋላ ለገዚ ቁርበቴ ማልፊያ ይሆነኛል አለ። በሬ በመቶ፥ ያውስ የት ተገኝቶ? ምድር በድሮ፥ ያውስ ማን ገብሮ። በሬ በአንጀቱ እንጂ፥ በአንገቱ አይሥብም። በሬ በጭብጦ ተገዚ ቢለው፤ ያላቦካ ከወዳት ያገኛል አለው። በሬ ቢጠፋ በድማ፤ ሥራ ቢጠፋ ድጎማ። በሬ ተሸካሽኮ ከቀንበር፤ ገበሬ ተሸካኝኮ ከድንበር። በሬ ተሸ኱ሽኮ ቀንበር፤ ገበሬ ተቸካችኮ ከድንበር። በሬ አርድ በስለት፤ ከብት አርብቶ በበረት። በሬ አጣማጁን፤ ላም ጥጃዋን ጠሩ። በሬ እን኱፥ ለወገኑ በፈርስ ያ጑ራል። በሬ፥ ከአራጁ ቢላ ተዋሰ። በሬ ከአራጁ ይውላል። በሬ ከአንጀቱ፥ እንጂ በአንገቱ አያበብም። (አያበብም ~ አይሥብም) በሬ ከጎለበተ፤ አሽከር ከሰነበተ። በሬ ወደ አገሩ ይስባል። በሬ ወደ አገሩ ይጎትታል። በሬ የሚጠምድ እህሉን፤ ጥጃ የሚጠምድ ሞፈሩን ተሸክሞ ይመለሳል። በሬ ያርሳል፥ ምርቱን አህያ ያፍሳል። በሬ የሚጠምድ እህሉን፤ ጥጃ የሚጠምድ ሞፈሩን። በሬ ያርሳል፥ ምርቱን ግን አህያ ያፍሳል። በሬ ያርሳል፤ አህያ ምርቱን ያፍሣል። በሬ ግዙ፥ ግዙ፥ አንድ ጨው ላይገዙ። (ጨው ~ አሞላ) በሬና ሴት ከአገርህ መሬት። በሬና በሬ መከሩ፥ ቀንበር ሉሰብሩ። (ሉሰብሩ ~ ሰበሩ) በሬዎች ተረት ለመደ፤ ዝም ብለው እንዳይጠመደ። በር የመለሰው፤ ማጀት የጎረሠው። በርስት ነው፥ በሚስት። በርቄ፥ እሞታለኹ ታንቄ። በርበሬ ታልፈጀ፤ ጠበቃ ታረጀ። በርበሬ አይሆን እጣን፤ ነገር አይሆን ሥልጣን። በርበሬ እጣን አይሆን፤ ነገር ሥልጣን አይሆን። በርበሬ፥ በገዚ እጅ ገብቶ ይፈጃል። (ይፈጃል ~ ይፋጃል) በርበሬና ሚጥሚጣ፤ ሥጋና ቋንጣ። በርበሬን ከላመ ከሞተ አግኝተሽው፥ ዋጥ ስልቅጥ አድርገሽ፥ ከምኔው ጨረሽው? በርኖስ ሳይገዙ፥ ካባ። በርግዝና ላይ ዕርዝና። በርጥብ አያቃጥሉ፤ በሰማንያ አይቀጥሉ። በርጥብ ይከላ፤ በደረቅ ያበላ። በሰለ እንብላ፤ ደረሰ እንዝራ። በሰላም ጊዛ አለኹልህ ያላሉት፥ በመከራ ጊዛ ቢጠብቁት አይገኝም። በሰላም ጊዛ ያልመከሩት፥ በመከራው ጊዛ ልምከርህ ቢሉት አይሆንም። በሰላም ጊዛ ያልሞከሩት፥ በመከራው ጊዛ ልሞክርህ ቢሉት አይሆንም። በሠላሳ እግርህን አታንሣ፤ በአርባ አገርህ ግባ። በሰማኸው ተማከር፤ በሳልከው ተመተር። በሰማንያ አይቀጥሉ፤ በርጥብ አያቃጥሉ። በሰማንያ የተረታ፤ መሀል አገዳውን የተመታ። በሰማንያ ያለቀ፤ በፀሓይ የደረቀ። በሰማይ ቢዝር አንበጣ፤ በምድር ወገቡን ይይዚል ፌንጣ። በሰማይ ቢዝር ዗መደ አንበጣ፤ በምድር ወገቡን ይይዚል ፌንጣ። በሰማይ የለ ደር፤ በቄስ የለ ግብር። በሰማይ የለ ጸጸት፤ በአባት የለ(ም)ቅጣት። በሰማይ የለም ደር፤ በቄስ የለም ግብር። በሰማይ የለም ጸጸት፤ በአባት የለም ቅጣት። በሰማይ የጸደቀ በምድር ይታወቃል፥ ከከንፈሩ ወጥቶ ጥርሱ ጣይ ይሞቃል። በሰማይ ደመና የለ፥ በእግሬ ጭቃ። በሰም የተጣበቀ ጥርስ:_ ቢሥቁበት አያደምቅ፥ ቢበሉበት አያደቅ። በሰም የተጣበቀ ጥርስ:_ ቢሥቁበት አያደምቅ፥ ቢያኝኩበት አያደቅ። በሰም የተጣበቀ ጥርስ:_ ቢበሉበት አያደቅ፥ ቢሥቁበት አያደምቅ። በሰም የተጣበቀ ጥርስ:_ ቢያኝኩበት አያደቅ፥ ቢሥቁበት አያደምቅ ያጣበቁት። በሰም ያጣበቁት ጥርስ:_ ቢሥቁበት አያደምቅ፥ ቢበሉበት አያደቅ። በሰበቡ፥ መምሬ ተሳቡ። በሰባት አመታቸው እንዳይማሩ፥ ሰባ ዓመት ይደናቆሩ። በሰባት አመቷ ብታሠራ፥ አንገት ልብስ። በሰንበት ላይ ደብረ ዗ይት፤ በሥጋ ላይ አሞት። በሰንበት ላይ ደብረ ዗ይት፤ በእራት ላይ ዳረጎት እንዱሉ። በሰው ላይ ቄስ። በሰው ልጅ ይሥቁ፤ በራስ ልጅ ያፍሩ። በሰው ምድር፥ ልጇን ትድር። በሰው ሰርግ ገብቶ ጉሮ ወሸባ፤ እናቷን ገድል ልጁዋን ሉያገባ። በሰው ቍስል፥ ዕንጨት ስደድበት። በሰው ቁስል፥ ዕንጨት ቀርቅርበት። በሰው ቂማ፥ እጇን ትቃማ። በሰው ቂጣ፥ እጅህን አትቃጣ። በሰው ቂጣ፥ ልጇን ትቀጣ። በሰው ቡሀቃ (ያቦካ) አሟጦ አይጋግርም። በሰው ብድር፥ ልጇን ትድር። በሰው አገር ማግኘት፤ ደር ገብቶ ዗ፈን። በሰው አገር፥ አለመናገር። በሰው እጅ እሳት (አይፋጅም)። በሰው ፊት አይበሉ፤ በፀሓይ አይኮበልሉ። በሰው ፊት አያብሉ፥ ሲታይ አይኮበልሉ። በሰጡህ አትስነፍ፤ ከሰጡህ አትለፍ። በሰጡበት አገር፥ ለምኖ ማደር የማይመች ነገር። በሰፈሩበት ላዳን፤ በመ዗ኑበት ሚዚን። በሰፈሩበት ቁና፥ መሰፈር አይቀርም። በሰፈሩት ቁና፥ መሰፈር አይቀርም። በሰፈሩበት ቁና፥ ሳይሰፈሩ አይቀሩም። በሰፌድ ያሰጣ፤ በእንቅብም ያሰጣ እኩል ለእኩል ወጣ። በሳልከው ተመተር። በሴት የከበረ፤ ከእግዛር ተማከረ። (ተማከረ ~ የተማከረ) በሴት የከበረ፤ ከእግዛር የተማከረ። (የከበረ ~ የቆረበ) በሴትና በላሉት፥ እማይደርስ የለም። በሴትና በውሃ፥ የማይደርስ የለም። በሴትና በዳገት አይሮጡም። በስለት ከሚቆረጥ አንገት፤ በምላስ የሚቆረጥ አንጀት። በስለት የተመተረ፤ በአጤ ይሙቱ የተከተረ። በስሙ፥ ቤተ ክርስቲያን ይስሙ። በስማም ወልድ ሲያዙኝ አልወድ ሲሰጡኝ መጉመድ። በሥራ የኮሰሰ፤ በመንፈስ ረከሰ። በስርቆት ከመክበር፥ ይሻላል ደህይቶ መኖር። በስተእርጅና ሙሽርና። በስተእርጅና ድቁና። በስንቱ ልቃጠል አለች፥ ብረት ምጣድ። በስንቱ ልበጥበጥ አለች፥ በሶ። በስንዝር አልሰጥ ያለ፥ ከንድቶ ይሰጥ። በሥጋው ጠንካራ፤ በሥራውም ኀይለኛ። በሶ ጥረሾ፥ አ጑ት አፈሾ፥ ጥንስስ ያልፈላ፥ ባላን ይዝት ደላ። በረት ከአልፈላ፥ አይላላ። በሸንጎ ቢረታ፥ ከቤት ሚስቱን መታ። በሸንጎ ተግደርዳሪ፤ በቤት ውስጥ ጦም አዳሪ። በሺ ሰርገኛ፤ በሥሉስ ዳኛ (ሚስት አመጣ)። በሺ ዓመቱ፥ ርስቱ ለባለቤቱ። በሻሽ ገንዙኝ፥ ጎንደር ቅበሩኝ። በሽማግላ የታረቀ፤ በፀሓይ የደረቀ። (አለቀ ደቀቀ) በሽሮ ላይ ቅቤ ተጨምሮ፥ አማረ በእሐድ ላይ በዓል ተጨምሮ፥ ከበረ። በሽበት አይደለም፤ በማስተዋል እንጅ። በሽተኛ፥ ያድርቅህ መጋኛ። በሽታውን የደበቀ፥ መድኀኒት አይገኝለትም። (አይገኝለትም ~ የለውም) በሽታውን የደበቀ፥ መፍትሔ አያገኝም። በሽታውን የደበቀ፥ ሬሳው ይ዗ልቃል። በሽታውን የደበቀ፥ ተፋተሽ። በሽታውን የደበቀ፥ ቫይረሱ አለበት። በሽንብራውም፥ ትል አለበት። በሾተል የገደሉ፤ በሾተል ይሞታሉ። በቀና ልቦና፤ በንጹሕ ህሉና። በቀን ብዚት፥ እንቁላል በእግሩ ይኼዳል። በቀኝ ቁሜ እንደ ክርስቶስ፤ በግራ ቆመህ እንደ ዱያብልስ። በቀኝም ቀጥ፤ በግራም ቀጥ። በቁርበትም ያሰጣ፤ በደላጎም ያሰጣ እኩል ቀን ወጣ። በቂል ክምር፥ ዝንጀሮ ይማታበታል። በቃል ያለ ይረሳል፥ በመጽሀፍ ያለ ይወሳል። በቃል ያለ ይረሳል፥ በመጽሀፍ ያለ ይወረሳል። በቃሪያ የሚበላና፤ አጥንት የሚግጥ ይሉኝታ የለውም። በቄስ ተናዚዥ፤ በመነኰሴ ገናዥ። በቄስ ተና዗ዝ፤ በ዗መድ ተገነዝ። በቄስና በሴት የመጣ ፀብ አይበርድም። በቆል እያረረ ይሥቃል። በቅል ማሰሪያዋን በጠሰች ቢለው፥ አሳጠረች አለ። በቅል ማን አባትህ ቢሉት፥ ፈረስ አጎቴ አለ። በቅል ሳይገዙ ኮርቻ። በቅል ማሰሪያዋን በጠሰች፥ ለራሷ አሳጠረች። (ማሰሪያዋን ~ ገመዶን) በቅል ማሰሪያዋን በጠሰች፥ ለራሷ አባሰች። (ለራሷ ~ በራሷ) በቅል ሽንቷን አጠራ ብላ፥ ሀፍረቷን አሳየች። በቅል በኮርቻ፤ ሥንቅ በስልቻ። በቅል ቢወልዶት እንጂ፥ አትወልድ። በቅል አባትህ ማን ነው ቢሉት፥ በቅል አባትህ ማን? ቢሉት፥ ፈረስ አጎቴ አለ። በቅል አትወልድም፤ የሚወልድም አትወድም። በቅል እንደ ሰገሩት፤ ልላ እንደ ነገሩት። በቅል እንደ ሰገሩት፤ ዕውር እንደ መሩት። በቅል እንደ አሰጋገሩ፤ ልላ እንደ አስተዳደሩ። በቅል እንደ ገሪው፤ ሕዝብ እንደ መሪው። በቅል ከሸጠ፥ የሸመጠጠ (በለጠ)። በቅል ያለ ኮርቻ፥ ለማኝ ያለ ስልቻ። በቅል ገመዶን በጠሰች፤ በራሷ አሳጠረች። በቅል ጌታዋን እንጂ፥ የጌታዋን ጌታ አታውቅም። በቅል ግዙ፥ ግዙ፥ አንድ አሞላ (ጨው) ላያግዙ። በቅል ግዙ፥ ግዙ፥ አንድ ጨው ላያግዙ። በቅል ጭኖ፥ መጭ መጭ፤ ሚስት አግብቶ፥ ምሳዬን አምጭ። በቅልን አባትሽ ማነው ቢሎት፥ እናቴ ፈረስ ነች አለች። በቅርብ የወደቀ፥ ብዙም አይጎዳ። በቅርብ ያለ ጠበል፥ ልጥ መንከሪያ ይሆናል። በቅናት የቀላ ፊት፥ በቫዝሉን አይወዚም። በቅጣት፥ ይመለሳል ጥፋት። በቅጥ የኖረ፥ በቅጥ ያገኛል። በቆማጣ ቤት፥ አንድ ጣት ብርቅ ነው። በቆረጡት ብትር ቢመቱ፤ ባወጡት ዳኛ ቢረቱ፤ የእግዛር ግቡ ከብቱ። በቆፈሩት ጉድ጑ድ ይገቡበታል። በቆብ ላይ አብርጣም፤ በመስቀል ላይ ውዥሞ። በበላህ ገብር፤ በሰማህ መስክር። በቆፈሩት ጉድ጑ድ መቀበር አይቀርም። በቅል አንገት ይገባል። በበርበሬ የተገዚ ፈረስ፥ መደቆሻ አይ዗ልም። በበሽታ(ው) የተጎዳ፤ በጥንሥሱ የተቀዳ። በበትሩ አይመታ፤ በ዗መደ አይረታ። በበትሩ እማይማታ፤ በ዗መደ እማይረታ። በበዚብህ ጊዛ የደነቆረ፥ በበዚብህ አምላክ ሲል ይኖራል። በበጋ የማይነድ የለም። በበጋ እሞኝ ቤት ተንጋጋ፤ በክረምት እንደ ጭልፊት እየቤትህ ግባ። በቡሀ ላይ ቆረቆር። በበጋ ከሞኝ ቤት ተንጋጋ፤ በሀምላ ደጅህን ዝጋ። በበጋ እሞኝ ቤት ተንጋጋ፤ በክረምት እቤትህ ተከተት። በቢላዋ ያርዶል፤ በውል ይሟገቷል። በባለቤት፥ ባቄላ ኮሽ አይልበት። በባዕድ ቢቆጡ፤ በጨለማ ቢያፈጡ (ምን ያመጡ)? በባዕድ ቢቆጡ፤ በጨለማ ቢያፈጡ ከመድከም በስተቀር ምንም አያመጡ። በባዳ ቢቆጡ፤ በጨለማ ቢያፈጡ (ምን ያመጡ)? በባዳ ቢያኮርፉ፤ በጨለማ ቢያፈጡ ምን ሉያመጡ? በቤተ ዗መድ ገራዥ፤ በቄስ አናዚዥ። በቤተ ዗መድ ገናዥ፤ በቄስ ናዚዥ። (ናዚዥ ~ ተናዚዥ ~ አናዚዥ) በቤት ይለምደታል፤ በአደባባይ ይደግሙታል። በቤቷ ቀጋ፤ ለውጭ አልጋ። (ለውጭ ~ በውጪ) በብረት ከመመርኮዝ፥ በእህል መተከዝ። በብርሃን ካለቀሙ፥ በጨለማ አይቅሙ። (አይቅሙ ~ አይለቅሙ) በብዙ ከማረስ፥ ከተቀላቢው ማሳነስ። በቦላ ነው፥ በሞያላ። በቦላ ነው፥ በባላ። በተለሙ ያርሷል፤ በጀመሩ ይጨርሷል። በተለይ ንዳ፤ በጠራ ቅዳ። በተረታ፥ የለውም ቅሬታ። (በተረታ ~ በተርታ) በተረገ዗ በዓመት፤ በተወለደ በዕለት። በተራራ ላይ የተሠራች ሀገር፥ መሰወር አትችልም። በተሾመ ይሟገቷል፤ በተሻረ ይመሰክሩበታል። በተሾመ ይከራከሩበታል፤ በተሻሩ ይመሰክሩበታል። በተተከለ(ው) ግንድ፤ በተፈተለ(ው) ገመድ። በተናጋሪ ዗ንድ፥ ሰሚ ይደነቃል። በተሳለ ያርዶል፤ በታየ ይፈርዶል። በተወረሱበት ዗መናት፥ አይረጠጡበት። (አይረጠጡበት ~አይረጫጩበት) በተድላ ጊዛ የደነቆረ፥ ደንቆሮ እስከ ዚሬ ድረስ፥ ተድላ ይሙት ይላል። በተጀመረው ነገር፤ በተጣበቀው ማገር። በትር ለገና፤ ነገር ለዋና። በትር ለገና፤ ውሃ ለዋና። በትር ከእጅህ፤ እባብ ከእግርህ። በትር ፈሪ፤ ጑ሮ ወዳጅ። በትንሽ መንገድ፤ ንጉሥም አይኼድ። በትንሽ ማረሻ፤ ትልቅ ዕርሻ። በትንሽ ያልታመነ፤ በብዙ አይታመንም። በትንባሆ የተገዚ ጦር፥ ቢወረውሩት ጋያ(ን) ይወጋል። (የተገዚ ~ የገዙት) በትኩስ ሥጋ፤ በርጥብ ፍለጋ። በችኮላ ቅቤ ያንቃል፤ ቀስ በቀስ ድንጋይ ይዋጣል። በችኮላ ያፈቀሩት፥ በኋላ ይጠሉት። በችኮላ ያፈቀሩት፤ በችኮላ ተጣሉት። (ተጣሉት ~ ይጠሉት) በነሀሴ ባቄላ፤ በግንቦት አተላ። በኅዳር አትበል፥ ዳር ዳር። በኋላ የመጣ፥ አይን አወጣ። በኋላ የመጣ፥ እጅ ይዝ አስወጣ። በኋላ የበቀለ ቀንድ፥ ጆሮን በለጠው። በለምለም ምላሱ፤ በሠላሳ ጥርሱ። በለምለም ምላሴ፥ ኮሸሽላ በላኹ። በነፋስ አውታር ወጥሮ፤ በእሳት ዝንጀሮ አስሮ። በንሳ የከበረ፤ በአ጑ት የሰከረ የለም። (ንሳ ~ ጉማ) በንብ ጊዛ፥ ዝንብ ይነክሳል። በንጉሥ ሞት አይ዗በት፤ በዝኆን ሀሞት አይፈተፈትበት። በንጉሥ ሰው አይፈርድ፤ በውሃ ላይ እሳት አይነድ። በንጉሥ ፍርድ የተቆረጠ እጅ፥ ካለ እኩል ነው። በንጹሕ እቃ ላይ ዝንብ የምትቀምሰው አታገኝም። በአህያ ላይ ሞፈር፤ በፈረስ ላይ ቀንበር እኛም የፈራነው ይህንኑ ነበር። በአህያ ማገር የተሠራ ቤት፥ ይበጣጠሳል ጅብ የጮኸ ዕለት። በአህያ ቆዳ የተሠራ ቤት ሲፈርስ ያድራል፥ ጅብ የጮኸ ዕለት። (ቆዳ ~ ጠፍር) በአህያ ቆዳ የተሠራ ቤት ብትንትን ይላል፥ ጅብ የጮኸ ዕለት። በአህያ ቆዳ የተሠራ ቤት፥ ይበታተናል ጅብ የጮኸ ዕለት። (ይበታተናል ~ ይፈራርሳል) በአህያ ቆዳ የተሠራ ድን኱ን፥ ጅብ ሲጮህ ይፈርሳል። በአለፈ ክረምት፥ ቤት አይሠራም። በአላወቀው ፈርድ፥ አደረገው ባድ። በአላዋቂ ቤት፥ እንግዳ ናኘበት። በአልጋ የሚለያይ፥ በፍቅር ይራራቃል። በአመልህ፥ በጥፊ ይበልህ። በአመጣሽው ዳኛ፥ ትሆኝ አሣረኛ። በአመጣኸው ዳኛ፥ ትሆን እስረኛ። በአሥብ በአሥብ እግሬን ቆርጦ፥ በራሴ አሸከመኝ። በአስተጋባ፥ (ከ)ባሕር ሆዳ ገባ። በአረገ዗ች፥ ክታቡን ያ዗ች። (ክታቡን ~ ክታብ) በአሸዋ ላይ የተሠራ ቤት፥ መሠረቱ ድቡሽት። በአቅጣጫ ውበት፤ መልክ በአፍንጫ። በአሰበችው ቀርቶ ባሰበው ከአዋላት፥ እኔ ምን እላለኹ እናንተው ቅበሯት። በአሥር ጣቱ፤ በሰፊው ደረቱ። በአስበው ላሉት፥ ባል ነው መድኀኒት። በአበደሩበት አገር ተበድሮ፤ በሰጡበት ተቀባጥሮ። (በሰጡበት ~ በሰጡት) በአባቱ ከተማ፤ ልጁ ተቀማ። በአባቱ ፊት የሚናገር፥ አፉ ለምጣም (ነው)። በአባትህ አገር አትቀማ፤ በእናትህ አገር ጦም አትደር። በአባቶች ፈንታ ልጆች ተተኩልሽ። በአባያ የተ዗ራ፥ ዗ንጋዳ እንደታሰበው አይረዳ። በአንበሳ በረት፤ የፍየል ጭፈራ። በአንበሳ አፍ፥ ሣር አይገባም። በአንቺ ኑሮ በአንቺ ንብረት፥ ውሻ ድመት። በአንቺ ኑሮ፥ በአንቺ ንብረት፤ 7 ውሻ፥ 7 ድመት። በአንደ ታ዗ብ፤ በአንደ ተለ዗ብ። በአንደ ፍቅር ላላው ይሳባል። በአንድ ኹለት፤ በጥሬ ደቄት። በአንድ ምስክር፤ አይረታ በኹለት አለንጋ አይመታ። በአንድ ራስ፥ ኹለት መላስ። በአንድ ቀበላ፤ ኹለት ምስለኔ። በአንድ ቀን ስሕተቱ፥ ዗ላለም ይጸጸቱ። በአንድ ቀን ስሕተት፥ ዓመት ጸጸት። በአንድ ቅል፤ ጀንበር ጥልቅ። በአንድ ነፍስ፤ ኹለት ንጉሥ ይቻላልን? በአንድ አልጋ፤ ኹለት አራስ። በአንድ አይን ጉድፍ። በአንድ አጉራ፤ ኹለት አውራ። በአንድ አፍ፥ ኹለት ምላስ። በአንድ አፍ፤ ተናጋሪ በአንድ ምላስ መስካሪ። በአንድ አፍ ተናጋሪ፤ በአንድ በቅል ሰጋሪ። በአንድ እጅ ማጨብጨብ፥ ሆነና ቀረ። በአንድ ከበሉ፥ የለም ዳረጎት። በአንድ ከተማ ኹለት ንጉሥ፤ በአንድ አልጋ ኹለት አራስ፤ በአንድ ራስ ኹለት ምላስ። በአንድ ከፈጩ፥ የለም እመቤት። በአንድ ወናፍ፤ ኹለት አፍ። በአንድ ዙፋን፥ ኹለት ንጉሥ። በአንድ ዙፋን ኹለት ንጉሥ፥ በአንድ አፍ ኹለት መላስ። በአንድ ደብር፥ ኹለት መምህር። በአንድ ጉድ጑ድ፥ ኹለቴ ጅብ አይነክስም። በአንድ ጎራ፥ ኹለት አውራ። በአንድ ጠጠር፥ ኹለት ወፍ። በአንድ ጣት፥ ፊት አይታጠብም። በአወጡት ዳኛ መረታት፤ በያዙት በትር መመታት። በአወጡት ዳኛ ቢረቱ፤ በቆረጡት በትር ቢመቱ። በአወጡት ዳኛ ቢረቱ፤ በቆረጡት በትር ቢመቱ የእግዛር ግቡ ከብቱ። (በትር ~ ጨንገር) በአወጣኸው ዳኛ ትሆን፤ አሳረኛ። በአወጣው ዳኛ ተረታ፤ በያ዗ው በትር ተመታ። በአዋቂ ፊት መናገር፥ መታገም። በአይብ እንጂ፤ በቅቤ አያወፍሩ። በአይብ እንጂ፥ በቅቤ አይወፍሩም። በአይኑ ሰው አይሞላ። በአይኑ የተኮሰ፥ የልቡ ደረሰ። በአይኔ መጣህብኝ። በአይኔ አልቅሼ፤ በእጄ አልብሼ። በአይኔ አልቅሼ፤ በእጄ አብሼ። በአይን ተቀምለው፤ በጣት ተጠንቁለው። በአይን ጥቅሻ፤ በከንፈር ንክሻ። በአይጥ ሽንት የተሠራ ቤት ድመት ሲጮህ ይፈርሳል። በአደባባይ ወተት፤ በቤት ውስጥ ጉጠት። በአደጉበት ያረጁበት፤ በአረጁበት ይሞቱበት። በአዳመጠች አረገ዗ች። በአድላዊ ያድላበት፤ በአመጸኛ ሰይፍ ይ዗ዝበት። በአገባቡ፥ በደጃፉ ይገቡ። በአገኘህ ቀን ቅቤ ዋጥ፥ ባጣህ ቀን ድንጋይ ዋጥ። በአጉራ ጠናኝ የተረታ፥ መሀል አገዳውን የተመታ። በአግባቡ፥ በደጃፍ ይገቡ። በአጎረሥኩት እጄ፥ ምነው መነከሴ? በአጎረሥኹኝ፥ (ጣቴን) ተነከስኩኝ። (ጣቴን ~ እጄን) በአጎረሥኩ፥ እጄን ተነከስኩ። በአጎራህ ጠናኝ የተረታ፤ መሀል አገዳውን የተመታ። በአ጑ት አይሰክሩ፤ በካሳ አይከብሩ። በአጠሩ፥ በነጠሩ ቃላት። በአጠፋ ወታደር፥ ይክሳል ባላገር። በአጤ ሞት የተከተረ፤ በስለት የተመተረ ። (ሞት ~ ይሙቱ) በአጭር ታጥቆ፥ ጋሻ ነጥቆ፥ ዗ገር ነቅንቆ፥ ይዋ጑ል አጥብቆ። በአፈሳ ይታፈሳል፤ በነጠር ይመለሳል። (በነጠር ~ በንጥጥር) በአፈሳ ይወረሳል፤ በነጠር ይመለሳል። በአፉ በጎራዳ ትደነቃላችኹ፤ ወገብ ቆርጦ እሚጥል ቅናት አለላችኹ። በአፉ ቅቤ አይሟሟም። በአፉ ያመነ፤ ከሥሩ የመነመነ። በአፉ ይወደድ ሽመላ፤ በአፉ ይጠላ ቁራ። በአፌ፥ ማን በላበት አለ እርኩም። በአፍ ላይ ይረሳል፤ በመጣፍ ላይ ይወሳል። በአፍ ስሕተት፤ በእግር መንሻተት። በአፍ በለፈለፉ፥ በነገር ይጠፉ። በአፍ እህል ብሉበት፥ ጡር አትናገሩበት። በአፍ ወይም በወናፍ። በአፍ ይበሉበታል እንጂ፥ ክፉ አይናገሩበትም። በአፍ ይጠፉ፥ በለፈለፉ። በአፍህ ነባቢ፤ በልሳንህ ቆራቢ። በአፍጢሙ፥ በግንባሩ ወደቀ። በእሪያ አፍንጫ፥ የወርቅ ቀለበት። በእርቦ ያበድራል፥ በቁና ይከፈላል። (ይከፈላል ~ ያስከፍላል) በእርጅና የተወለደ ልጅ፥ ከነአባቱ አንድ ሰው ያጠቃዋል። በእርጅና፥ ይመጣል ምንኩስና። በእርጅና፥ ይመጣል ጣጣ። በዕርጎ ላይ ጠላ፥ እግዛር ሲጣላ። በእናት ላይ አክስት፤ በሰንበት ላይ ደብረ዗ይት። በእናትና በልጅ መሀል መርፌ ጠፋ። በእኔ ሲያዩብኝ፥ በአንቺ ይዩብሽ። በእኔውም ጥርስ አልተሣቀበት። በዕንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ። በእንቅብም ያሰጣ፤ በሰፌድም ያሰጣ እኩል ቀን ወጣ። በዕውር ቢፈርደ፤ ዕውር ይወልደ። በእህል የተከ዗፤ በ዗ንግ የተመረኮ዗ ቶል አይወድቅም። በዕለቱ፥ ይወርዳል መዓቱ። በእጅ ስጥ፤ በእግር ፈልግ። በእጅ አግብቶ ቁንጣን። በእጅ አግብቶ ቁጣ። በእጅ የያዙት ወርቅ ስለ መዳብ አንድ ነው። (ስለመዳብ ~ ከመዳብ) በእጅ የያዙት ወርቅ ከመዳብ እኩል ነው። (እኩል ~ አንድ) በእጅ የያዙት ወርቅ ከብረት እኩል ነው። (ከብረት ~ ከመዳብ) በእጅ ያለ ወርቅ እንደ መዳብ ነው። በእጅ የ኱ሉት ኩል አይን ያጠፋል። በእጅ ያገኘሽ አያጣሽ፥ ያጣሽ አያገኝሽ። በእጅ ገብቶ፥ ቁንጣን። በእግዛር ቢቆጡ፤ በጨለማ ቢያፈጡ ምን ያመጡ። (በእግዙሔር ~ በእግዛር) በእፉኝት የተመረ዗፤ በቄስ የተና዗዗። በከብቱ የለገሰ፤ በወለደ የከሰሰ። በከብቱ የለገሰ፤ በፈረሱ የገሠገሠ። (ከአሰበው ደረሰ) በካሳ የከበረ፤ በአ጑ት ሰከረ። በካሳ የከበረ፤ በአ጑ት የሰከረ የለም። በካብ ላይ ብሠራ እባቡ መከራ፥ በዚፍ ላይ ብሠራ አሞራው መከራ፥ በምድር ብሠራ እረኛው መከራ የት ውዬ የት ልደር አለች። በካፊያ የሚርስ። በክረምት፥ በርኖስህን አታውል እቤት። በክረምት ከአረሰ፤ እናቱን ያስመነኮሰ። በክፉዎች አትቅና። በኹለት በትር አይማቱ፤ በኹለት ዳኛ አይሟገቱ። በኹለት ቢላዋ መብላት። በወለደ የከሰሰ፤ በከብቱ የለገሰ። በወላ ደጃዝማች ነው ባላ። በወሬ አትጥላኝ፥ በስመ ጅብ አትውጋኝ። በወሬ፥ እኔም አለኝ ቁስል ያንተን የሚመስል። በወሬ አይነግሱ፤ በእጅ አይካሱ። (በቁንጫ አያርሱ) በወር ልቅ፥ በዓመት ቀሚስ ጥልቅ። በወሰኑት ፍልሚያ ተረቱ፤ በቆረጡት አርጩሜ ተመቱ። በወረት፥ ኮሶ ይጣፍጣል። በወበራ የተሠራ፤ በወበራ ይፈርሳል። በወተት ላይ ውሃ መጠጣት፥ ያበዚዋል ያነጣዋል። በወንድሜ ግንባር ደም አልይበት። በወንፊት ላይ፤ ውሃ መጨመር። በወደሉ የለገሰ፤ ከአሰበው ደረሰ። (የለገሰ ~ የገሠገሠ) በወደቀ ግንድ፥ ምሳር ይበዚበታል። (ምሳር ~ መጥረቢያ) በዋስ ያለ ከብት፤ በጣት ያለ ቀለበት። በዋዚ ያልረዳ፤ በቁም ነገር አይረዳ። በዋጋ፥ ከእናትህ ልጅ ተዋጋ። በውሃ የለመደች፥ መረቅ ውስጥ ገባች። በውላ፥ ደጃዝማች (ነው) ባላ። በውል ከኼደች በቅልዬ፤ ያለ ውል የተበላች ቆልዬ። (የተበላች ~ የኼደች) በውርርድ ላይ ውርርድ፤ ከነብር ላይ ስማርድ። በውሻ ሆድ ቅቤ አያድርም። በውሻ ራት፤ ውሻ ቆሞባት። በውሽማ ሞት፥ ፊት አይነጭም። በውሽማዋ ዳኝነት፥ ባሎን ኹለት ጊዛ ረታችው። በውዳታ ከተወሰደብኝ ወርቄ፥ በግዳታ የተወሰደብኝ ጨርቄ። በውድ ሽጥልኝ፤ በሀቅ መዝንልኝ። በዓል ሽሮ የከበረ፤ ጦም ገድፎ የወፈረ (የለም)። በዓመት እንደ ርገት። በዕርሻ ጊዛ ያል዗ራ፥ በመከር ጊዛ አይሰበስብም። በዕርጎ በአይብ የለመደች ዝንብ፥ በትኩስ ሽሮ ትገባለች። በእናት ላይ ሞግዙት፤ በራት ላይ ዳረጎት። በዕውር ቤት፥ አንድ አይና ብርቅ ነው። (ብርቅ ~ ንጉሥ) በዕውር አገር፤ ጠንባራ ንጉሥ ነው። በዕውር ይጠቃቀሱበታል፤ በደንቆሮ ይሾካሾኩበታል። በዕውር ይጠቃቀሷል፤ በደንቆሮ ይሾ኱ሸ኱ል። በዕውር ጎዳና፥ ብርቅ ነው አንድ አይና። በዕውሮች ከተማ፥ አንድ አይና ንጉሥ ነው። በዕውቀት የጎለመሰ፥ ብቻውን ነገሠ። በዕድሜህ እወቅበት፤ ሠርተህ ክበርበት። በእጅ ሰጥቶ፤ በእግር መፈለግ። በዙህ ዓለም ሥራ የማይሠራ ሰው፤ አፈር ልብሱ ድንጋይ ትራሱ። በዙህም አዳርህ፥ ግብር አለብህ። በዝምታ ይገኛል ከበሬታ። በዝና የለም ጤና። በዝኆን አፍ፥ ቅርፊት። በዝኆን ጆሮ ትንኝ፤ በዝኆን አፍ ቅርፊት። በዝምታ የለበት ሀሜታ። በዝኆን ጠብ፥ የሚጎዳው ሣሩ ነው። በዝኆን ጆሮ፥ ትንኝ። በዝናብ መሮጥ ምንድር ነው፤ ቢሉት ከአንድ ለአንደ ማዳላት ነው። በዝንጋታ፥ ብዙ ጊዛ ይረታ። በየት አልፈሽ፤ ድ጑ ተማርሽ። በየዕለቱ፥ ይወርዳል መዓቱ። በየወንዙ ሃላ። በየወንዙ፥ ብዙ ነው መ዗ዙ። በየዋህ እጅ፥ የ዗ንድ አፍ ይለካል። በየገደሉ መቀደስ፥ የተኛውን ሰይጣን መቀስቀስ። በያ዗ው ብትር አይመታ፤ በወንድምና በአጎቱ አይረታ። በዮሀንስ እረስ፤ በማቴዎስ እፈስ። (እንዱሉ) በደመና ጊዛ፥ ስለ መብረቅ አይወራም። በደረቅ አበሳ፤ እርጥብ ይነዳል። በደረቅ ይበላ፤ በእርጥብ ይከላ። በደባ፥ ሞት ይገባ፥ አለች ግራጫ። በደባስ፥ ሞት ይግባ፥ አለች ጃርት። በዳቦ ላይ ሙልሙል። በደቦ የተሠራ፤ በደቦ ይፈርሳል። በደኅና መንገድ፥ ዓመት ዙር። በደል፥ ዋና አጥታ ትኖራለች። በደንቆሮ ይሾካሾኩበት፤ በዕውር ይጠቃቀሱበት። በደንባሪ በቅል፥ ቃጭል ተጨምሮ። በደግነቱ ተቆረጠ አንገቱ። በደግነት ተቆረጠ አንገት። በደላ ሳይሆን፥ በመላ። በደር ጥገት፤ በጥሬ ደቄት። በደሮ በሬ አይታረስም። በዳኛ ፊት አይናገሩም ዋዚ፤ ልጅ ፊት አይበሉም አምዚ። በድል ማሩኝታ፤ ተበድል ይቅርታ። (ማሩኝት ~ ማሩኝ) በድመት አፍንጫ አልፎ ጫን ጫን ይሸመታል ቢሎት ለአይጥ፥ ለምን ትቀልድብኛለህ በየት አልፎ አለች። በድመት አፍንጫ አልፎ፤ ያለ መጠን ጠግቦ ጫን ጫን ይሸመታል ቢሎት ለአይጥ፥ በየት አልፎ አለች። በድምፅ ይወደድ አሞራ፤ በድምፅ ይጠላ አሞራ። በድሮ በሬ ያረሰ የለም። በድቡሽት ላይ የተሠራ ቤት ዕድሜ የለውም። በድንገት፥ አህያ ገባ፥ እጅብ ቤት። በድህነት ላይ ስንፍና፤ በቂጥኝ ላይ ቁምጥና። በድሮ ፊንጢጣ፤ በሽንብራ ቂጣ። በጅብ ሆዳምነት፤ በእህል ጣፋጭነት ሳይተዋወቁ ይኖራሉ። በጅብ ቆዳ የተሠራ ከበሮ ሲመቱት፥ እንብላው እንብላው ይላል። በጅብ ቆዳ የተሠራ ከበሮ ቅኝቱ፥ እንብላው እንብላው ነው። በጆሮ ከሰሙት፥ በአይን ያዩት። በጆሮ ጠቢ መንደር፥ ሣር ቅጠሉ አድማጭ ነው። በገቡበት አያወጡበት። በገና ጨዋታ፥ አይቆጡም ጌታ። በገን዗ቡ የለገሰ፤ በወደሉ የገሠገሠ። በገና፥ በሰው እጅ ያምር፥ ሲይዙት ያደናግር። (ያደናግር ~ ድንግርግር) በገና ወተሩ ቢላላ፥ ቃናው ይጠፋል። በገን዗ብ የተገኘ ወዳጅ፥ ለመከራ አይበጅ። በገዚ ሀገራችን በገዚ ወንዚችን፥ ማዕ዗ኑ እንደሆነ ሞልቷል ባገራችን። በገዚ ራሱ እባብ ጠመጠመ። በገዚ አረሟ፥ እባብ ይዚ ታስፈራራ። በገዚ ዳቦዬ፥ ልብ ልቡን አጣኹት። በገዚ ጌታ፥ እግሩን ይመታ። በገዚ ጥይቱ፥ ይቆስላል ብልቱ። በገዚ ፈሴ፥ አስሜን መቀስቀሴ። በገደል ያለ ዝንጀሮ ይኖራል ተከብሮ። በጉጣ ያረሰ፤ ሲፈራ የከሰሰ። በጊዛ የመጣ እንግዳ፥ እራቱ ፍሪዳ። (የመጣ ~ የገባ) በጊዛ የጮኸ ጅብ አያሳድረኝም። በጊዛ ያልታሸ ለምርኩዝ ያበቃል። በጊደር ጥገት፤ በጥሬ ደቄት። (ደቄት ~ ደቄት) በጋ ቢዳምን ይ዗ንብ ይመስላል፤ ሽማግላ ቢያጎብብ ይወጋ ይመስላል። በጋ ትታ፤ ክረምት ቧገታ። በጋለሞታ ቤት፥ ዅሉ ይጣላበታል። (ይጣላበታል ~ ይጣላበት) በጋሻው ዕንብርት፤ በጦሩ አንደበት፤ በፈረሱ አንገት። በግ ባልበላሽ ትበዪኝ አለ ጅብ። በግ ከበረረ፤ ሞኝ ከአመረረ፤ መመለሻ የለውም፤ ነገሩ ከረረ። በግ ከበረረ፤ ሞኝ ከአመረረ (አይመለስም)። በግ ከበረረ፤ የሰው ልጅ ከአመረረ። በግ ከደነበረ፤ ሞኝ ከአመረረ አይመለስም። በግ የላለው፥ ቀበሮን አውሬ አይላትም። በግምገማ እርማት፥ በግለ ሂስ እድሳት። በግራግል አንድ ወልደህ አግል። በግብሩ ተጠልቶ በድምፁ ይወደድ አሞራ፥ በመልኩ ተጠልቶ በግብሩ ይወደድ ጨ጑ራ። በግንቦት፥ አንድ ዋንጫ ወተት። በግድ፥ አ጑ት ጠጡ የፋሲካ ዕለት። በጎ ለራሱ፥ ክፉ ለራሱ። በግድ። በጎ አማጭ መጦር፤ ክፉ አማጭ በጦር። በጎ አማጭን መጦር፤ ክፉ አማጭን በጦር። በጎመን ያበጠ ሆድ፥ በድንች ይፈተናል። በጎመን ጥላ ተጠልል ይታያል ዝኆን ተንጋል። በጎውን አማጭ መጦር፤ ክፉውን አማጭ በጦር። በጎደል ቀን የገዚኹት ጋሻ፥ ሳያስገድለኝ አይቀርማ አለ ፈሪ። በጠላ ላይ ወተት፥ የእግዛር ቸርነት። በጠረጠሩ ድንጋይ ፥ ይጥሉ። (ድንጋይ ~ ጠጠር) በጠራ ተሻገር፤ በተሳለ ምተር። በጠብ ጊዛ፥ አሥር እንጀራ ለኹለት አይበቃም። በጠብመንጃ የመጣን፥ በጠብመንጃ። በጠይቆ ዕውቀት፥ ይገኛል ክብረት። በጠጅ ተጀምሮ፥ በጠላ ያልቅ ድግስ። በጠገብኹ ጠብ የለም። በጠፍር የተሠራ ቤት፥ ጅብ ሲጮህ ይፈርሳል። በጣም ሀብታም፤ በጣም ድሀም። በጣይ በጉባይ። (በጣይ በጉባይ ~ በፀሓይ በጉባኤ) በጥምቀት ያልተወረወረ፤ ልሚ ሀገሩን የከዳ ተሿሚ። (ሀገሩን ~ ወገኑን) በጥር ሰርግ፤ በግንቦት በልግ። በጥቂት በጥቂት፥ ይሞላል ልቃቂት። በጥቂት የታመነ፥ በብዙ ይሾማል። በጥቅምት፥ አንድ አጥንት። በጥበብ መብዚት፥ ትካዛ ይበዚል። በጥባጭ ካለ፥ ጥሩ አይጠጣም። በጥባጭ ሳለ፥ ማን ጥሩ ይጠጣል?( ሳለ ~ ካለ) በጥንሥሱ የተቀዳ፤ በጨርቋው የተጎዳ። በጥጃዬ ባላረሳችኹ፤ የእንቆቅልሼን ፍች ባላወቃችኹ። በጦም ቆል፤ በዳገት በቅል፤ ቆልው ይከካል፤ በቅልውም ይነካል። በጦም ቆል፤ በዳገት በቅል፤ በቅልው ይነካል፤ ቆልው ይከካል። በጦሩ ቅብጭ፤ በጠላው ቁጭ። በጦር አንደበት፤ በፈረስ አንገት። በጨለማ እየኼደ፥ ጅብን ነገረኛ ያደርጋሉ። በጨለማ እሳት ወርዋሪ፥ ለጠላቱ መንገድ ያሳያል። በጨረቃ፥ ልጅ ይድሩ ወይንስ ይኮበልሉ። በጨረቃ ጅብ ያስደነገጣት ውሻ በቀን ፀሓይ አትሞቅም። በጨዋታ ያልረታ፤ ታጥቆ ያልመታ ይናደዳል ወደ ማታ። በጨው ደንደስ፤ በርበሬ ተወደስ። (ተወደስ ~ ይወደስ) በጫማ የሚኼድና በቃሪያ የሚበላ ሰውን አይጠብቅም። በጫጩት ፊት ስለ ፈንግል አይወራም። በጭቃ የተመራ፤ በቅቤ የተሠራ። በፀሓይ ቅቤ አያበሩበትም። በፀሓይ በጉባኤ። በፈሉጥ ካልገባው በፍልጥ። በፈረስ የፈለጉት፥ በእግር ይገኛል። በፊት ዕወቁኝ፥ በኋላ ደብቁኝ። (ዕወቁኝ ~ ዕወቁኝ ዕወቁኝ) በፊት ዕወቁኝ ዕወቁኝ፥ በኋላ ደብቁኝ ደብቁኝን ያስከትላል። በፊት የወጣን ጆሮ፥ በኋላ የወጣ ቀንድ በለጠው። በፊት የደረሰን ወፍ ይበላዋል፤ በፊት የተናገረውን ሰው ይጠላዋል። በፋሲካ የተቀጠረች ገረድ፥ ኹል ጊዛ ፋሲካ ይመስላታል። በፋሲካ የተገዚች ባሪያ፥ ኹል ጊዛ ፋሲካ ይመስላታል። በፋሲካ የተገዚ ባሪያ፥ ኹል ጊዛ ፋሲካ ይመስለዋል። በፍርድ ከኼደች በቅልዬ፤ ያለ ፍርድ የኼደ ጭብጦዬ። (የኼደ ~ የኼደች) በፍርድ ከኼደች በቅልዬ፤ ያለ ፍርድ የተበላች ጭብጦዬ። በ዗መኔ፥ ይድላው ለወገኔ። በ዗ር የላኩ በዝርዝር፥ በጠዋት የላኩ በቀትር። (የላኩ ~ የላኩት) በ዗ር የላ኱ት፥ በዝርዝር። በ዗ነበበት ቦታ ያባራ። በ዗ጠና፥ የለም ጤና። በ዗ጠና ገዝቶ በ዗ጠና መሸጥ፥ ትርፉ እን዗ጥ እን዗ጥ። በዙህ ሥራሽ፥ ወጥተሽ ወድቀሽ። ቡሄ ከዋለ የለም ክረምት፤ ከጮኸ የለም ላሉት። ቡሉኮና ጋቢ፤ አቢላምና አላቢ። ቡቃያ አይታጨድ፤ አንበሳ አይጠመድ። ቡቃያው አንድ ማሳ፥ አራሚው ኀምሳ። ቡና በአቦሉ፤ ስጦታ ከአቀባበሉ። ቡና እና ማሽላ፥ እየሣቀ ያራል። ቡናና ፍቅር በትኩሱ ነው። ቡናና ፍቅር (ትኩስ) ትኩሱን። ቡዳ ቤት፤ ሰላቢ ገባ። ቡዳ በወዳጁ ይጠናል። ቢሰቀል ስፍራው ይታወቃል። ቢራቢሮ ቂጧን የምትሸፍነው የላት፤ ምድር ታለብሳለች። ቢርበኝ ሰረቅኹ፤ ቢጨንቀኝ ታረቅኹ። ቢሰጡን እንነዳ፤ ቢነሡን እናረዳ። ቢሰጡኝ እነዳ፤ ቢነሡኝ እረዳ። ቢሰጡኝ ዕዳ፤ ቢነሡኝ አረዳ። ቢስ የቢስ ዕለት፤ ክፉ የክፉ ዕለት። ቢቆጡት የማይፈራ፥ ቢናገሩት አይሰማ። ቢቆጡት ያልሰማ፥ ቢመቱትም ያው ነው። ቢበሉትም ነጭ ሽንኩርት፤ ቢነኩትም ነጭ ሽንኩርት። ቢበላ ገዓት፤ ቢኖር ዓመት። (ቢኖር ~ ቢኖሩ) ቢበርድ በእጅ፤ ቢተኩስ በማንኪያ። ቢበይኑለት ቀጠነኝ፤ ቢፈርደለት ይግባኝ። ቢተኙ ነገር፤ ቢኼደ አገር። (አይታጣም) ቢተኙ ነገር ያገኙ፥ ቢነሱ ነገር ይረሱ። ቢተኙ ነገር ያገኙ። ቢተኙ ነገር፤ ቢኼደ አገር፤ ቢቆፍሩ አፈር። (አይታጣም)። ቢታ዗ዝ ነው እንጂ፥ ከላይ ከጀመደ እሾህ ይወጋል ወይ? በጫማ ከኼደ። ቢቸግረን፥ ሾጤ ሆንን። ቢቸግር ነው እንጂ፥ ዗ሚሀዬል ስም ነው። ቢነሡ፥ ነገር ይረሱ። ቢነግሩሽ ትናገሪብኝ፤ ቢያጠጡሽ ትሰክሪብኝ። ቢነግሩሽ ትነግሪብኝ፤ ቢያጠጡሽ ትጠጪብኝ። ቢናገሩ አፈኛ ዝም ቢሉ ሞኝ፥ ተነገሩ ዅሉ ይህ ገረመኝ። ቢናገር የማያምር፥ ሲቀመጥ አይከበር። (ሲቀመጥ ~ ቢቀመጥ) ቢናገር የማያምር፤ ቢቀመጥ የማይከመር። ቢከማች፥ ዕዳው ለአንቺ። (ዕዳው ~ እጣው) ቢከማች፥ ዕዳው የአንቺ። ቢከፍቱት ተልባ። ቢኼደ አገር፤ ቢቆፍሩ አፈር፤ ቢተኙ ነገር አይጠፋም። ቢኼደ አገር፤ ቢተኙ ነገር። ቢወቅሩ አይፈጭም። ቢወደኝ ብል ሞት፤ ቢጠሉት ምን ሉመጣበት። ቢወደኝ ብል የሞተ፤ ቢጠሉትስ፥ ምን ይመጣበት ነበር? ቢዋደደ ጾም ገደፉ፤ ቢጣሉ ተዋረፉ። ቢያብደም ቢሞቱም፥ የአንደን ነገር አያጫውቱም። ቢያብደም ቢጨምቱም፤ የአንደን ነገር ለአንደ አያወጡም። ቢያብደም ቢጨምቱም፤ የአንደን ነገር ለአንደ አያጫውቱም። ቢያንጋልሎት ጡት የላት፤ ቢደፏት ቂጥ የላት። ቢያዝሉት ያለቅስ፤ ቢስሙት ይነክስ። ቢያዝኑለት ያለቅስ፤ ቢስሙት ይነክስ። ቢያዩኝ አሰርግ፤ ባያዩኝ እሰርቅ። ቢያዩኝ እሥቅ፤ ባያዩኝ እሰርቅ። ቢያዩኝ እሥቃለኹ፤ ባያዩኝ እሰርቃለኹ (አለ ላባ)። ቢያድጥ ቢያድጥ ቁልቁል ያድጣል እንጂ፥ ሽቅብን ያድጣል። ቢያጎርሧት ተኮሳት። ቢደፏት ቂጥ የላት፥ ቢገለብጧት ጡት የላት። ቢጠሉት አይሆን፥ ሞትና ሴት መሆን። ቢጠረጥሩ ጠጠር ይጥሉ። ቢጠሩሽ አትሰሚ፤ ቢጠቅሱሽ አታዪ፤ ረጋ ብለሽ ኺጂ፤ ብር ብር አትበዪ። ቢጠሩት ያልሰማ፤ ቢወቅሱት አያይም። ቢጠሩት ያልሰማ፤ ቢጠቅሱት አያይም። ቢጠሩኝ አቤት፤ ቢልኩኝ ወዳት። ቢጠናባት ጠናች፥ የልጇን ባል ቀማች። ቢጨብጧት ትሞታለች፤ ቢለቋት ትበራለች። ቢጨንቀነ፥ ሾጤ ሆንነ። ቢጨንቀኝ፥ ሾጤ ሆንኩኝ። ቢፈሩት አይቀር፤ ሞትና ነገር። ቢፈትጉት ይነጣል፤ ቢመረምሩት ይወጣል። ቢፈጀኝ በማንኪያዬ፥ ባይፈጀኝ በእጄ። ቢ዗ል ማጀት፤ ቢወጋ ምንቸት። ቢ዗ረዝሩት መቋጫ፤ ቢቆጥሩት ማለቂያ። ቢያስቀምጥም፥ ጮማ ይሻላል። ባለ መድኀኒት ሆይ! ራስህን ፈውስ። ባለ ርስት፥ የርስቱን ያህል ይከበራል። ባለ ቁርጥ አትደንግጥ። ባለ ቁርጥ አትደንግጥ፤ ባለ አንቀልባ አታግጥ። ባለ ነገር፥ ከቤት ጠርቶ ከችልት። ባለ ነገር ከቤት፤ ጠበቃ ከችልት። ባለ ንብረት አያደርስ ከበረት። ባለ አደራ፥ ጩህ በተራራ። (በተራራ ~ ከተራራ) ባለ አደራ፥ ጮኸ ከተራራ። ባለ ካባ ከባለ ካባ፤ ባለ ዳባ ከባለ ዳባ። ባለ ጋሪ መንገድ አስቸጋሪ። ባለማ ፍረደኝ፤ ባጠፋ ስደደኝ። ባለሞያ ሴት የሰፋችውን ውራንታ፥ ጅል ትተረትረዋለች። ባለቤቱ በኩበት የመታውን በሬ፥ ባዕድ በድንጋይ ይመታዋል። ባለቤቱ ባጥላላው ውሻ፥ ዅሉም እጁን ይሰነዝርበታል። ባለቤቱ ከአልጮኸ፤ ጎረቤት አይረዳም። (ባለቤቱ ~ ባለቤት) ባለቤቱ ያልተቻለውን ምሥጢር፥ ማን ይችልልኛል ብል ይናገራል። ባለቤቱ ያቀለለውን፥ ባለዕዳ አይቀበለውም። ባለቤቱ ያቃለለውን አሞላ፥ ባለዕዳ(ው) አይቀበለውም። ባለቤቱ ያከበረው አህያ፥ በቅል ይላውጣል። ባለቤቱን እፊቱ ማመስገን፥ ከማማት እኩል ነው። (ከማማት እኩል ነው ~ የማማት ያህል ነው) ባለቤቱን ከአልናቁ፥ አጥሩን አይነቀንቁ። ባለቤቱን ከአልናቁ፥ ውሻውን አይመቱ። (አይመቱ ~ አይነኩ) ባለቤቱን ከአልናቁ፥ ሚስኮል አያደርጉ። ባለቤቱን ከፊቱ ማመስገን፥ ከሀሜት እኩል ይቆጠራል። ባለቤት ሲተዋወቅ፥ የሰርገኛ ልብስ ይደርቅ። ባለቤት ሲያፍር፥ እንግዳ ይጋብዚል። ባለቤት ቢያፍር፤ እንግዳ ይጋብዝ። ባለቤት የወደደው አህያ፥ ፈረስ ያላውጣል። ባለቤት የወደደው አሞላ፥ በሬ ይለውጣል። ባለቤት ያቀለለውን አሞላ፥ ባለዕዳ አይሸከመውም። ባለቤት ያከበረው አህያ፥ በቅል ይለውጣል። ባለቤቷን ያመነች በግ ላቷን ውጭ ታሳድራለች። ባለኩል ያሰናክል። ባለጋራ ሲገፋ፥ ወዳጅ ይጎትታል። ባለጋራ ያለው፥ እንቅልፍ የለው(ም)። ባለጌ መንገድ ይፈጃል፤ ነገር አይፈጅም። ባለጌ ማማቱን፥ ቆዳ መን጑጑ቱን፥ አይተውም። ባለጌ ሲሞት፤ ሬሳውን በሽመል። ባለጌ ሲቀመጥ፥ ቂጡን ገልቦ ነው። ባለጌ ሲወደት፥ ከልጅ እኩል አድርጉኝ ይላል። ባለጌ ሲጫወት በእጁ ነው፤ አዋቂ ግን በምላሱ። ባለጌ፥ ቁም ነገሩን ቧልት ያደርገዋል። ባለጌ ቢወልድ ጌታውን፥ ጌታ ቢወልድ ባሪያውን። ባለጌ ባለሟል፥ ልብስ ገልቤ ልይ ይላል። ባለጌ ተለጣጭ፥ ከድንጋይ ላይ ተቀማጭ። ባለጌ ተጣሪ፥ ወይ ባዩን ያባልጋል። ባለጌ ታዋረደው፥ ደኅና ሰው የመታው። ባለጌ አያዝንም ለገበረ፤ ያዝናል ባልንጀራው ለቀረ። ባለጌ አፉን እንጂ፥ እግሩን አያዳልጠውም። ባለጌ ከበቅል የወጣ እንደሆን፥ ከሰማይ የደረሰ ይመስለዋል። ባለጌ ከተጠነቀቀበት፥ አዋቂ የፏጨረ(ው) ይሻላል። ባለጌ ከአወራው፤ የሰው ልጅ የገመተው። ባለጌ ከአወራው፤ የጨዋ ልጅ ያሰበው። ባለጌ የተመከረ ዕለት፤ ቁንጫ የተጠረገ ዕለት (ይብሳል)። ባለጌ የጠገበ ዕለት፥ ይርበው አይመስለውም። ባለጌ ያለበት ሸንጎ፤ ዝንብ የገባበት ዕርጎ። ባለጌ ጆሮ ከለበሰ፤ አዋሽ ከደፈረሰ። ባለጌ ጆሮው ከለበሰ፤ አዋሽ ከደፈረሰ። ባለጌ፥ ገን዗ብ አያከብርም። ባለጌና ውሻ በቤቱ ይኮራል። ባለጌና ቆቅ፥ በራሱ ያወራ። ባለጌና የቆቅ አውራ፥ በራሱ ያወራ። (በራሱ ~ ያለበትን) ባለጌን ተነሥ አይሉትም። ባለጌን አንድ ጊዛ ስደበው፥ ከዙያ በኋላ እራሱ ሲሰደብ ይኖራል። ባለጌን ከአሳደገ፥ የገደለ ይሻላል። (ይሻላል ~ ይጸድቃል ~ ጸደቀ) ባለጌን ከአሳደገው፥ የገደለው ይጽድቃል። ባለጌን አንድ ጊዛ ስደበው፥ ኹል ጊዛ ራሱን ይሰድባል። ባለጌን ከወለደ፤ የገደለ ጸደቀ። ባለጌን ገን዗ቡ አያኮራውም። ባለፀጋ ሉሰጥ፥ የድሀ ሙርጥ ዓበጥ። ባለፀጋ ሲቀናጣ፤ የድሀ ልጅ ይሞታል። ባለፀጋ በሀብቱ፤ ድሀ በጉልበቱ። (በሀብቱ ~ በከብቱ) ባለፀጋ በድል ይቆጣል፤ ድሀ ተበድል ይለማመጣል። ባላ ቢታመም፥ የጎረቤቷን በሬ ተሳለች። ባላ መታኝ አለች፥ ወይስ ፈታኝ። ባላና ጉለላ። ባላና ተራዳ። ባላን ጎዳኹ ብላ፥ መንታ ልጅ ወለደች። ባላን ጎዳኹ ብላ፥ እንትኗን በዕንጨት ወጋች። ባላገር ሆደ ገር፤ ክፉ አይናገር። ባላገር የሚበላው ቢያጣ፥ የሚከፍለው አጥቶ አያውቅም። ባላጋራ ያለው፥ እንቅልፍ የለው። ባል ሳይኖር ውሽማ። ባል ከአላጎረሠ፤ በሬ ከአላረሰ። ባል የላላት ሴት፤ የመንገድ ላይ እሸት። ባል የአማት ልጅ፤ ልጅ የእናት ልጅ። ባል የአማት ልጅ ነው። ባልሞገትክበት ተፈረድ፤ ባልወጣህበት ውረድ። ባልሽ ማነው? አውራ ድሮ፥ ምን ሉያበላሽ? መሬት ጭሮ። ባልሽ ቆላ ወርድ፥ ሰማይ ሰማይ ሲያይ፥ አንቺ ከእኔ ጋራ ሰበር ሰካ በዪ። ባልበላ፥ ጭሬ አላፈሰውም ወይ፥ አለ ድሮ። (አለ ~ አለች) ባልነቃ ሠንጥቆ፤ ባል዗ነበ በርቆ። (ባል዗ነበ ~ ባልደመነ) ባልነበር፥ ይሻላል ነበር። (ይሻላል ~ ይሻል ~ ይቻል) ባልና ሚስት ሉተዋወቅ፥ የሰርገኛ ልብ ይውለቅ። ባልና ሚስት ከአንድ ባሕር ይቀዳሉ። (ይቀዳሉ ~ ይቀዳል) ባልና ሚስት፥ ከፈንና ገላ (ናቸው)። ባልና ሚስት፤ ፍትሕና መንግሥት። ባልና ጉንፋን፥ በሩቁ ነው። ባልና ሚስት፥ ልሚ ከኹለት። ባልን ወድ፤ ምጥን ፈርቶ። ባልንጀራህ ሲላጭ፥ አንተም አብረህ ቅረብ። ባልንጀራህ ሲበልጥህ፤ ቁንጣን ይምለጥህ። ባልንጀራህ ሲበልጥህ፥ የጎመን ቁንጣን ይግደልህ። ባልንጀራህ ሲታማ፥ ለእኔም ብለህ ስማ። (ለእኔም ~ የእኔ) ባልንጀራህ ከሚበልጥህ፤ ቁንጣን ይግደልህ። ባልንጀራው ቢያጠቃው፥ ወደ ሚስቱ ሮጠ። ባልንጀራዬ ሲበልጠኝ፥ ቁንጣን ይፍለጠኝ። (ሲበልጠኝ ~ ከሚበልጠኝ) ባልወልድልሽ ታከትኹልሽ። ባልዋጁበት ጣት፥ የ዗ንድ ጉድ጑ድ ይለኩበት። ባልፈጨሽ በኖብሽ፤ ባልነበርሽ በርቆብሽ። ባሎ ቢታመም፥ የጎረቤቷን በሬ ተሳለች። ባሎን ጎዳኹ ብላ፥ መንታ ልጅ ወለደች። ባሎን ጎዳኹ ብላ፥ ትምህርት ቤት ገባች። ባል዗ፈንሽ፥ ከ዗ፈንሽም ባላሳፈርሽ። (ባላሳፈርሽ ~ ባላፈርሽ) ባልፈሱበት ቂጥ አያፍሩበት። ባሎን ጎዳኹ ብላ፥ እንትኗን በማጭድ አቃጠለችው። ባሎን ጎዳኹ ብላ፥ እንትኗን በዕንጨት ወጋች። ባሩደ በከምሱር ይነሣል፤ አንበሳ በደር ያገሳል። ባሪያ ሲኮራ፥ መድኀኒቱ ደላ። ባሕር ዚፍ ከተከሉት ይጸድቃል፥ ገን዗ብ ከአላኖሩት ያልቃል። ባሕታዊ እንደናፈቀ ይሞታል። ባሪያ ሲኮራ፥ ራሱን በደላ። ባሪያ ሲኮራ፥ በደላ። ባሪያ ሲጠግብ ሸንጎ፤ አህያ ሲጠግብ አምቦ። ባሪያ፥ ረዳት ቢያመጡላት፥ መጇን ደበቀች። ባሪያ ቅቤ ለምድ፥ እንግዱህ ማን ሉሸከም ነድ። ባሪያ ቅቤ ወድ፥ ማን ሉሸከም ነድ? ባሪያ በአንደበቱ፤ ውሻ በጅራቱ። ባሪያ ቢያግዞት፥ መጁን ደበቀች። ባሪያ አጋዥ ብታገኝ፥ መጅ ደበቀች። (መጅ ~ መጇን) ባሪያ ከአልሰረቀ፤ ሰማይ ከአልፈለቀ። ባሪያና ቃርያ፥ ጌታውን እንዳቃጠለ ይኖራል። ባሪያና ውላጅ፤ ሸራቢና ገማጅ። ባሪያና ጨ጑ራ፥ ቢያጥቡትም አይጠራ። ባሮች አግዙ ለአህዮች፤ አህዮች አግዙ ለባሮች። ባቄላ ሳይሰበር፤ መነኰሴ ሳይቀበር። ባቄላ ቀረ ቢሉት፥ ፈስ ቀለለ አለ። ባቄላ አለቀ ቢለው፥ ፈስ ቀለለ። (ቢለው ~ ቢሉ) ባቄላ፥ የረኃብ ደላ። ባተ_ መልካም ሲሆን፥ ለመሮጥ ሳይሆን ለጌጥ። ባትዋጋ እን኱ን፥ ተሰለፍ ከመልካ። (ትሰለፍ) ባንዳ፥ አደረገን ባዳ። ባዕድ ሥር የለውም። ባዕድ ቂሙን አይረሳ፤ ቂም በቀል ሲወሳ። ባዕድ ከሳመው፤ ዗መድ የነከሰው። ባዕድ ከሳመው፥ ዗መድ ያቆሰለው ይሻላል። ባዕድና ጨለማ አንድ ነው። ባዝራ እናቴ፤ ድንጉላ አጎቴ። (በቅል እን኱ን አባቷን ስትክድ) ባዝራ ከድንጉላ (ወለደ)። ባይሰጡት ፈገጡት። (ፈገጡት ~ ፈግጡት) ባይቆጭ ያንገበግባል። ባይቸኩል እንቁላል፥ ይኼዳል በእግሩ። ባዳና ጨለማ አንድ ነው። ባድ ኮረብታ፥ በችፍርግ ያዋዚል። ባፉ በጎራዳ ትደነቃላችኹ፥ ወገብ ቆርጦ እሚጥል ቅናት አለላችኹ። ቤተ ሠሪ፥ በኋላ ይመጣል። ቤተ ሠሪ፥ የተሰረቀ ቦታ አይገዚም። ቤተ ክርስቲያን ለማላጅ፤ ገበያ ለአርፋጅ። ቤተ ክርስቲያን ተ኱ሽ፥ ዕርቅ አፍራሽ። ቤተ ክርስቲያን አቃጥል ቢሉት፥ ደጀ ሰላም አቃጠለ። ቤተ ክርስቲያን የገባ ውሻ። ቤቱ ገነነ፤ እሳቱ ገነነ። ቤታቸውን እየከፈቱ፥ ሰው ላባ ይላሉ አለች ውሻ። ቤቴ፥ ከባለሥልጣኖች እንድቀድም አደረግሽኝ። ቤቴን ሞቅ ሞቅ አድርጉልኝ፥ በከሰል ነው ወይስ በነገር? ቤት ሆኖ ከአሰበ፥ ኼድ ያልሰጠ በለጠ። ቤት ለላለው፥ ቤት ይሰጠው ችግሩን እንዱቀምሰው። (እንዱቀምሰው ~ እንዱያውቀው) ቤት ለላለው፥ ቤት ይስጠው እንዱቃወሰው። ቤት ለእንቦሳ፥ እንቦሳ እሰሩ። ቤት ሠርቶ ያለመውጫ፤ ፊት ያለ አፍንጫ። ቤት ሲሰፋ፥ የሰው ዅሉ ተስፋ። ቤት በማገር፤ ንጉሥ በባላገር። ቤት ቢሰፋ፥ ደልሰ ተስፋ። ቤት አለ አጥር፤ ቤተ ክርስቲያን ያለ ቅጥር። ቤት አለ ክዳን፥ ከምንም አያድን። ቤት አባይ፤ ቤት አባባይ። ቤት ያለ መውጫ፤ ፊት ያለ አፍንጫ፤ ያ መፈንጫ፤ ያ ሙገጫ። ቤት ያለ ሴት፤ ከብት ያለ በረት። (አይሆን ለንብረት)። ቤት ያለ ቁልፍ፤ አልጋ ያለ ምንጣፍ። ቤት ያለ በር፤ ፊት ያለ አፍንጫ፤ ያ መውጫ፤ ያ ማጌጫ አይኖረው። ቤት ያለ አጥር፤ ሰው ያለ ልብስ። ቤት ያለ አጥር፤ ሬሳ ያለ መቃብር። ቤት ያለ አጥር፤ ቤተ ክርስቲያን ያለ ቅጥር። ቤት ድሮ ሲታረድ፥ እደር ቆቅ ይይዚል። ቤት ዗ግተው የደበደቡት ውሻ፥ ባለቤቱን ይነክሳል። ቤት፥ እስኪፈርስ ድረስ ይሠራል። ቤት ከነጉልላቱ፤ ምድጃ ከነማዕ዗ንቱ። ቤት ካሉት መቃብር ይሞቃል። ቤት፥ ጨለማና፥ ሴት የሚወልደት አይታወቅም። ቤትን መመሥረት፥ በባላገር አንጀት። ብለው ግዚኝ፥ ግዚኝ፥ ሉሸጠኝ አስማማኝ። ብላ ለከርስህ፤ ፍረድ ለነፍስህ። ብላ ቢለኝ፥ እንደ አባቴ በቆመጠኝ። ብላ የበሰለ፤ ተናገር የመሰለ። ብላ ያለው ቀርቦ፥ ተሸከም ያለው ተሰብስቦ (ይቆየዋል)። ብላ ያለው ቀርቦ፥ ተሸከም ያለው ተከማችቶ ይጠብቀዋል። ብልኀተኛ ነጋዳን፥ ጉም ለብሶ ይቀሙት። ብል ብል፥ የድሮ አንገት በምሳር። ብል ብል፥ የድሮ አንገት ከማሰሮ። ብልኀትን ከሴት፤ ትዕግሥትን ከጉንዳን። ብልኅ ሚስት፥ ለባሎ አክሉል ናት። ብልኅ ሲናገር፤ ሞኝ አድምጥ። ብልኅ ሴትና፤ ቀንድ ያላት አህያ የሉም። ብልኅ በልቶ፥ በሞኝ አፉን አበሰ። ብልኅ በልቶ፥ በሞኝ አፍ አበሰ። ብልኅ በ጑ዳ ያወራውን፥ ሞኝ በአደባባይ ይናገራል። ብልኅ አይረቱ፤ ከአጥፊ አይ዗ምቱ። ብልኅ የሸረበውን፥ ሞኝ ሥቆ ይፈታዋል። ብልኅ ያመቱን፤ ሞኝ የዕለቱን። (ያስባል) ብልኅና ቅባት፤ ብርሃንና መብራት። ብልኅን ማሞኘት፥ ቂም(ን) ማቆየት። ብልኅን አይረቱ፤ ከአጥፊ አይ዗ምቱ። ብልጥ ለብልጥ አይበላለጥ። ብልጥ ለብልጥ፥ አይን ብልጥጥ። ብልጥ ለብልጥ፥ ይተያያል ካብ ለካብ። ብልጥ ሰው በከንፈሩ ይሥቃል። ብልጥ ሰው ይታወቅበት አይመስለው(ም)። ብልጥ ሲለግም፥ አመድ በደቄት ይለውጣል። ብልጥ አይን አስቀድሞ ያለቅሳል። ብልጥ አይጥ፤ ከባለቤት እኩል ስትበላ ትኖራለች። ብልጥ እስኪያስብ፤ ሞኝ ይወልዳል። ብልጥ ጑ደኛ፥ የሰዎቹን የጋራዬ፥ የራሱን የብቻዬ። ብልጥና ምስጥ፥ ውስጥ ለውስጥ። ብመታው ሰደበኝ፤ (ብጥለው ገለበጠኝ)። ብሳሳትም እታረማለኹ፤ ብዳከምም አጠነክራለኹ። ብሳናም በአገሩ ወይራ ነው። ብረት ለብረት ሲፋጭ፥ ስለት ይወጣዋል። ብረት ሲግል ቀጥቅጠው፤ ንፉግ ሲወድ መጥምጠው። ብረት በብረት ይሠራል፥ ዕውር በሰው ይመራል። (ይሠራል ~ ይስላል) ብረት ብረትን ይስለዋል። (ይስለዋል ~ ይስላል) ብረት ከአልፈላ፥ አይላላ። (አይላላ ~ አይሣሣ) ብረት ያልታጠቀ፤ ጥል ያልወደቀ። ብረትን መቀጥቀጥ፥ እንደጋለ ነው። ብር ለሰጠ ጠጠር፤ እህል ለሰጠ አፈር። ብር ትምህርቱ፤ ጽሕፈት ነቀል ዕውቀቱ። ብር እጀታው፤ አለንጋ ጉማሬው። ብር ያየች ሴትና ጥንብ ያየ ጅብ (አንድ ናቸው)። ብርላ ከነቃ፥ አይሆንም ዕቃ። ብርቅና ድንቅ፥ አለ ሳምንት አይደንቅ። ብርቅና ድንቅ፥ አለ አንድ ቀን አይደምቅ። ብርቅና ድንቅ፥ አላንድ ቀን አይደምቅ። ብርቅና ድንቅ፥ አንድ ሰሞን ይደምቅ። ብርቅና ድንቅ፥ ያለ አንድ ጊዛ አይደምቅ። ብርቱ በአመረተ፥ የሰነፍ ሆድ ተነረተ። ብርና ወርቅ ያምራሉ፥ ግን ሰውን ያጣላሉ። ብርንድው ሲገኝ፥ ቢላዋው አይገኝ። ብርድ ምን ያመጣል? ከማንቀጥቀጥ በቀር። ብርድ ቆላ ወረደ፤ ልጅ አባቱን ወደደ። ብርድ ቢያብር፥ ለቁርጥማት ይዳርጋል። ብርድ ከማንቀጥቀጥ በቀር፥ ምን ያመጣል? ብርድ ፈሪ ያሞቃል፤ ረኃብ ፈሪ ያበላል። ብርድና ረኃብ ጸልትን ያስረሳል። ብርጉድ ሲያውድ (ነው)። ብርጭቆ ከነቃ፥ አይሆንም እቃ። ብቀጥንም ጠጅ ነኝ። ብስጭት፥ ትርፉ ሽበት። ብቅል አት዗ናነቅ። (ብቅል ~ ጠላ) ብቅል፥ እንደ ሰቀሉት ይሰቅላል። (ይሰቅላል ~ ይሰቅል) ብትር አይሉት ግትር። ብቆጣም እመታሻለኹ፤ ብትቆጪም እመታሻለኹ። ብቅ ብቅ፥ እንደ ስንዳ ምርቅ። ብቸኩል ያንቺንም፥ የእኔንም በላኹት። (በላኹት ~ በላኹ) ብቻ የበሉት ሽታ፥ ከሰው የበሉት እሸት። ብቻ የበሉት ይሸታል፥ ከሰው የበሉት ይሸታል። ብቻውን የሚሟገት፥ የሚረታው የለም። ብቻውን የሚሮጥ አይቀደምም፥ ብቻውን የሚሟገት አይረታም። ብቻውን የሚሮጥ የሚቀድመው፥ ብቻውን የሚሟገት የሚረታው የለም። ብቻውን የሚሮጥ የሚቀድመው የለ፤ ብቻውን የሚሟገት የሚረታው የለ። ብቻውን የሚሮጥ፥ የሚቀድመው የለም። ብቻውን የበላ፥ ብቻውን ያለቅሳል። (ያለቅሳል ~ ይሞታል) ብነጨው ፊቴን፤ ብመታው ደረቴን። (ብመታው ~ ብደግመው) ብናሥር እናጠብቃለን፤ ብንመታም እናደቃለን። ብንከባለል መንገዳ፤ ጣለኝ ከወንበዳ። ብኖር ዓመት፤ ብበላ ገአት እንዱያው መታከት። (ገአት ~ ጋት) (ገአት:_ በልተውት የማያጠግብ ደረቅ ዳቦ) ብዙ ሀብት ያመጣል ብዙ ጠላት። ብዙ መላ፥ እምብዚም አይበጅ። ብዙ መሳም፥ ልብ አይነካም። ብዙ መናገር ምላስን ያላሻል። (ያላሻል ~ ያሰለቻል) ብዙ ሰው ሉበላ፥ አንድ ሰው ይጠላ። ብዙ ሥንቅ የሚሸከም፥ ሳይበላ ይወድቃል። (ሳይበላ ~ ሳይበላው) ብዙ ቢተቹ ይሰለቹ። ብዙ ቢወልደ፥ ሙያውን አይተው አንደን ይወደ። ብዙ ቢወልደ፥ ግብሩን አይተው አንደን ይወደ። ብዙ ቢያወጉ ይ዗ነጉ፤ (ብዙ ቢተቹ ይሰለቹ)። ብዙ ቧልት ያፈርሳል ንብረት። ብዙ ቸርነት ያመጣል ድህነት። ብዙ ከመናገር፥ አንድ ያመልጣል። ብዙ ከማውራት፥ ጥቂት መሥራት። ብዙ ከማዳመጥ፤ ጥቂት መናገር። ብዙ ከመናገር፤ ጥቂት ማሰብ ይበልጣል። ብዙ ከብት ለማርባት፥ አልቅትን ጠብቆ፥ ውሃ ማጠጣት። ብዙ ውሃ ፍቅርን አያጠፋትም። ብዙ ዝምታ፥ ይሆናል በሽታ። ብዙ ዕውር አየኹ፥ እንዳንቺስ የፈሰሰ የለም። ብዙ ዕውር አየኹ፥ እንዳንቺስ ፈረስ የለም። ብዙ ከመናገር፥ ማዳመጥ ይበልጣል። ብዙ የሚያወራ፥ ጥቂት ይሠራ። ብዙ የተናገረና፤ ቆሞ የ዗ራ አንድ ነው። ብዙ ያለው አልተረፈውም፥ ትንሽ ያለው አልጎደለበትም። ብዙ ያይሻል፥ አንደ ይወድሻል። ብዙ ገን዗ብ ያለው ይደፈራል፥ ብዙ ወንድም ያለው ይታፈራል። ብዙዎች ይስጡህ፤ ብዙዎች አይቆጡህ። ብዙዎች ለብዙ ሲያውቁ፥ የራሳቸውን አይጠነቀቁ። ብዚት አይደለም፥ ጥራት። ብዙዎች ይስጡህ፤ ብዙዎች አይጥሉህ። ብድሩን የማይመልስ ልጅ አይወለድ። ብጤ ከብጤው። ብጥለው ገለበጠኝ። ቦይ ለውሃ፤ ጎመን ለድሀ። ቧልተኛ ሽማግላ፥ አንቱ ሳይባል ያረጃል። ቧልትና ቅ዗ን ቤት ያስፈታል። (ያስፈታል ~ ያጠፋል) ተለመደና ድሮ መከሽከሽ፤ እኝህ እናትሽ ሀሙስ ከች። ተለማማጭ አልማጭ። ተለጣጭ፥ የጎረቤቷን ድልህ ሟጣጭ። (ሟጣጭ ~ አሟጣጭ) ተላጭቶ ወለባ፤ ልባልባ ታጥቆ አዚባ። ተልባ መስልሽ፤ ሰናፍጭ ትቀምሽ። ተልባ በቅባ ኑግ ለሰሚው ግራ፥ ለበዪው መልካም ነው። ተልባ በጥባጭ ሳለች፥ ጎመን ቀንጣሿን ምች መታት። ተልባ ቢንጫጫ፥ በአንድ ሙቀጫ። (ሙቀጫ ~ ሙገጭ) ተመልከት አላማህን፤ ተከተል አለቃህን። ተመርቄያለኹ ብለህ፤ ከተረገመ አትዋል። ተመቶ ከመካስ፤ መትቶ መካስ። ተመስገን ጌታዬ፤ ከሞላ ጎታዬ (አለ ገበሬ)። ተመረቅኹ ብለህ፤ ተተረገመ አትዋል። ተመክሮ ልብ፤ ተሸምቶ ድልብ አይሆንም። ተማሪ ሲለግም አንድ መርፌ ለኀምሳ ይሸከማል። ተማሪ፥ ውሻ ቀባሪ። ተማሪ፥ ዗ኬ ለቃሚ። (ለቃሚ ~ ቆጣሪ) ተማሪና ድሮ በሞቱ ክብር ነው፥ በቁመናው እራቱ ጥሬ ነው። ተማክረው የፈሱት፥ ፈስ አይሸትም። ተማክሮ የፈሱት፥ ፈስ አይገማም። ተምሮ የማይጽፍ፤ አክፍል የማይገድፍ። ተምሮ ያላስተማረ፤ ዗ርቶ ያላጠረ። ተሟጋች እኔ እረታ ይመስለኛል ሰውም ይመለከተኛል። ተረታን እንዳይሉ፥ ይግባኝ ይላሉ። ተረቴን መልስ፤ አፌን በዳቦ አብስ። (በዳቦ ~ በጨው) ተረት ለነገር፥ ይሆናል መሠረት። ተረት በምሳላ፤ ዛማ በሃላ። ተረት ይሆናል፥ ለነገር መሠረት። ተራራ ለጥናት፤ ውሃ ለጥማት። ተራራም ከአነባ፥ ሰንበር ይሠራል። ተራጋሚ፥ ራሱን ደርጋሚ። ተርቦ ያወጡት ደሞዝ፥ ለመዳኛ አይሆንም። ተሸፋፍኖ ቢተኙ፥ ሳይገልጥ የሚያይ ጌታ አለ። ተሸፋፍኖ ቢተኙ፥ ገልጦ የሚወጋ ጌታ አለ። ተሰቅል የቆየህን አታውርድ፤ ከመሬት ያገኘኸውንም አትስቀል። ተሰብሮ ቢጠገን፥ እንደ ቀድሞው አይሆን። (እንደ ቀድሞው ~ እንደ ነበረ ~ እንደ ድሮው) ተሰዳቢ፥ ጥርሱ ነጭ ነው። ተሴትን ትብሱ፥ ትመለሱ። ተስማምቶ የፈሱት፥ ፈስ አይገማም። ተስፋ መስጠት፥ (እያዩ) ዕዳ መግባት። ተስፋ ርቆ፥ የተሰቀለ ዳቦ ነው። ተስፋ ቆርጦ አንድ ላይ ከመቆም፥ ይሻላል በተስፋ ሲ጑ዙ መክረም። ተስፋ የተሰቀለ ዳቦ ነው። ተስፋ ያልቆረጠ መነኰሴ ምናኔ ሲኼድ፥ ሴቲቱን ይሰናበታል። ተስፋ ያድናል፤ ክህደት ያመነምናል። ተሸፋፍኖ ቢተኙ፥ ገልጦ የሚያይ አምላክ አለ። ተሸፍኖ ቢተኙ፥ ገልጦ የሚያወጣ ጌታ አለ። ተሹሞ ከመታለል፤ ጥል መኮብለል። ተሹሞ ያልበላ፥ ተጠንስሶ ያልፈላ፥ ሹሙም ሹም፥ ጥንሥሱም ጥንስስ አይደለም። ተሻገር ከወንዙ፤ ጉድ እንዳያበዙ። ተቀመጥ በወንበሬ፤ ተናገር በከንፈሬ። ተቀማጭ የላለው ተሟጋች፥ ስልቻ የላለው ቧጋች። (ቧጋች ~ አንጋች) ተቀማጭ ገን዗ብ፥ ፍቱን መድኀኒት ነው። ተቀማጭ፥ አፉ ምላጭ። ተቀምጠው የሰቀሉት፥ ቆመው ለማውረድ ያስቸግራል። ተቀምጦ ከመላክ፥ ተነሥቶ መሥራት። ተቀምጦ የሰቀሉት ቁሞ ለማውረድ ይቸግራል። (ቁሞ ~ ቆሞ) ተቀምጦ የሰቀሉት፥ ቆሞ ማውረደ ይቸግራል። ተቀምጦ የሰቀሉት፥ ቁሞ ለማድረግ ይቸግራል። ተበድሬ ተቀድሜ። ተበድሬ ተለቅቼ። ተበድሮ ጋሬዳ። ተበድሮ ቅቤ፤ ታርዝ ጎፈሬ። ተነጠፈስ ቀረ፥ የኬሻ ምንጣፍ ... አለ የአገሬ ሰው። ተናካሽ ውሻ፥ የጅብ መቋደሻ። (መቋደሻ ~ መደገሻ) ተናካሽ ውሻህን፤ ተዋጊ በሬህን እሰር። ተናዝ ይሞቷል፤ አምኖ ይሟገቷል። ተናዝ ይሞቷል፤ አስይዝ ይሟገቷል። ተናድ መቅረት፤ ሴት የሆኑለት። ተናገር በከንፈሬ፤ ተቀመጥ በወንበሬ። ተናገር በከንፈር፤ ተቀመጥ በወንበር። ተናጋሪ ሲያመርት፥ ሰሚ ያከማቻል። ተናግሮ አናግሮ የሆድን ጨርሶ፥ ጠላት ይሆናል ወዳጅ ተመልሶ። ተናግሮ አናገረኝ ይወደኝ ይመስል፤ ኼድ ተናገረ የላክኹት ይመስል። ተንከትክተሽ ስትሥቂ፥ የጥርስሽ ወገብ እንዳይቀጭ። ተናግሮ ከማሰብ፥ ከከንፈር መሰብሰብ። (ከከንፈር ~ ከንፈርን) ተናግሮ ከመጨነቅ፤ የቀልቀልዬን አፉን እንቅ። ተናግሮ ያጣ ሰው፥ ሦስት ጊዛ ሞቱ ነው። ተንኮለኛ መበለት፤ በጦም ድሮ በፋሲካ እልበት። ተንኮለኛ ገደል፥ ዝንጀሮ ይጥላል፥ በሬ ያሳልፋል። ተንኮለኛ፥ ተሰባብሮ ተኛ። ተንኮለኛ ናቸው፥ አርቃችኹ ቅበሯቸው። ተንኮለኛ፥ የሰይጣን አርበኛ። ተንኮል መነሻዬ ለግፍ፤ መኖር መድረሻዬ እያለ። ተንጋለው ቢተፉ፤ ተመልሶ ከአፉ። ተንጋል ቢተፉ፤ ተመልሶ በአፉ። (በአፉ ~ ከአፉ) ተንጋል የተፋ፤ ለራሱ ከፋ። (ለራሱ ~ ከራሱ) ተንፈስ! የአሮጊት ነፍስ። ተኚ ብልሽ፥ አትነሺ አልኩሽ(ን) ተኛ ወዱያ ጎራሽ፤ እህል አበላሽ። ተከብሬ ሳበቃ፥ ተዋረድኹ። ተከብሮ፥ ያደርጋል ደንቆሮ። ተከናንቦ የሚበላውን፥ ተጎንብሰህ ግባበት። (ተጎንብሰህ ~ አጎንብሰህ) ተከፈት ያለው ጐረሮ፥ ጦም አያድርም። ተኩላ እንደ አንበሳ እጮህ ብላ ተተረተረች። ተኩሶ ጣለ፤ ወጋ ነቀለ። ተኩላ ፍየል በላ። ተክሶ የበለጸገ፤ ጑ያ በልቶ ያደገ። ተኮሰ ጣለ፤ ወጋ ነቀለ። ተዋሰኝ:_ ግዝት ይሆነኝ፤ አበድረኝ አይማረኝ። ተዋርድ ቢያሳዩት፥ ሀብት የጌታ ያድራል። ተዋርድ ከማግኘት፤ ኮርቶ ማጣት። ተዋቅሶ ወዳጅነት፤ የቂም ጠባሳ በአንገት። ተዋዚንና ቆል ተ጑ረሥን። ተዋጊ በሬ ከጭድ ይጣላል። ተዋጊ በሬህን፤ ተናካሽ ውሻህን (ያዝ)። ተው አትርሳ፤ ተሠርቶልሀል የእሳት ገሳ። ተው ፈረሴን ለጉም፤ አይ዗ነጉም ለሴትና ለጉም። ተዝካር ያየ ተማሪ፤ ሸቀጥ ያየ አጣሪ (አይን የለውም)። ተይዚ ት዗ፍን ጦጣ። ተይዝ ከመለማመጥ፥ አርፎ መቀመጥ። ተደርቦ መጣላት ሥራ ማጣት። ተደብቀው ያረግዙታል፥ ሰው ሰብስበው ይወልደታል። ተደብቃ ትፀንሳለች፥ ሰው ሰብስባ ትወልዳለች። ተድረው ቢመለሱ፥ የውሃ(ን) መንገድ ረሱ። ተድራ ብትመለስ፥ የውሃው መንገድ ጠፋት። ተገናኝተናል መሳ ለመሳ፥ አንቺም ዕውር ነሽ፥ እኔም አንካሳ። ተገናኝተው ሳሉ፥ ምን ጊዛ እንገናኝ ይላሉ? ተገደው የዋጡት ማር፥ ከሬት ይመር። ተገዳዩ(ም)፥ ሟቹ ይጣደፋል። ተገፍቶ ተገፍቶ በታላቅ ለቃቃ፥ ካሳ ሽፍታ ሆነ ለራስ የሚበቃ። ተጋበዙና ብሉ፤ ሀይ በሉ ከልክሉ። ተጋፊ ውሃ ሽቅብ ይኼዳል። ተጋፊ ውሃ አሻቅቦ ይፈሳል። ተግደርዳሪ ቀላዋጭ፥ ቀባጣሪ። ተግደርዳሪ:_ በለጠብ ሽሮ ተበዳሪ። ተግደርዳሪ:_ በልቶ ሽሮ ተበዳሪ። ተግደርዳሪ፥ ጦም አዳሪ። (ቀላዋጭ ቀበጣሪ) ተጎንብሶ የሚበላን፥ ተኝተህ ቀላውጠው። ተጠማኝ ቢሰነብት፥ ባለርስት ይሆናል። (ቢሰነብት ~ ሲሰነብት) ተጠንቀቅ ወደል፥ እንዳትገባ ገደል። ተጥድ አይፈላ፤ ተሹሞ አይበላ። ተጥድ የማይፈላ፤ ተሹሞ የማይበላ (የለም)። ተጨንቆ ኩራት፤ ተንጠራርቶ ራት። ተጫውቶ መማረር፤ አለ ጉዳይ መብረር። ተፈጥሮ ሞት፤ ተሾሞ ሽረት። ተፈጥሮን ተመክሮ አያድነውም። ተፈጥሮን፥ ተመክሮ አይመልሰውም። (ተመክሮ ~ ተገብሮ) ተፈጭቶ ያልተነፋ ደቄት፤ ተበራይቶ ያልተመረተ ምርት። ቱ አለች፥ ወለቱ። ተ኱ሽ በኹለት አይኑ አያነጣጥርም። ተወኝ ተወኝ፥ አዱስ ግልብጥ ነኝ። ቱሪናፋ:_ በጦር ሜዳ አትገኝ፥ ከቀለቡ አትጠፋ። (ቱሪናፋ:_ ሰነፍ ወታደር) ታላቁን ነገር እየተመኘኹ፤ ቢከፍቱት ተልባ ኹኘ ቀረኹ። ቱስ ያለ፥ ዗ረጥ ሳይል አይቀርም። ታላቅ ነው ብለው አይፈሩም፤ ታናሽ ነው ብለው አይደፍሩም። ታላቅየው ሲመቸው፥ ታናሽየው ሳይድህ በእግሩ ይኼዳል። ታልመሱ አያነሡ። ታላቅ ጦር፥ ባይወጉበት ያስፈራሩበት። ታላቅ ወንድም፥ እንደ አባት ይቆጠራል። ታሞ መመንመን፤ ሞቶ መኮነን። ታሞ ከመማቀቅ፥ አስቀድሞ መጠንቀቅ። ታሞ የተነሣ፥ እግዙአብሔርን ረሳ። (እግዛርን) ታስሮ ከመማቀቅ፥ ይሻላል መጠንቀቅ። ታርቄ ተመርቄ፤ ታጥቤ ተለቃልቄ። ታርቆ ሙግት፤ በልቶ ሥሥት። ታስሮ የማያውቅ ጥጃ፥ ቢይዙት ይ጑ጉራል። ታሪኩን የማያውቅ፥ ለአባቱ ገዳይ ይ዗ፍናል። ታሪክ አይሙት፥ እንዱያጫውት። ታቦተ መልካም፤ አፀደ ክፉ። (አጸድ:_ ቤተሰብ) ታቦተ ክፉ፤ አፀደ መልካም። ታቦቱን ከመንበሩ፤ ካህኑን ከደብሩ (አይለይብን)። ታቦት በራሱ፤ ቃጭል በጥርሱ። ታቦትን ከመንበሩ፤ ሰውንም ከአገሩ (አታውጣው)። ታ዗ብኩሽ ማይ጑጑፤ ማድጋ ዗ርቼ ማድጋ። ታዝበው ሲጠሉህ፤ ታዝበው ይወደደህ። ታየው ትመለከተው፤ ትታነቀው ትሞተው። ታይቶ የመጣውን በበር፤ ተሰውሮ የመጣውን በድር ይመልሱታል። (በድር ~ በዱር ~ በጥሩር) ታዳጊ ያለው በግ፥ ላቱን በውጭ ያሳድራል። ታድያስ? (ጠያቂ) አለን በአዱዳስ ያውም ሳንዋስ። (መላሽ)። ታጥቀህ ታገል እንዳትንገላታ፤ አስተውለህ ተሟገት እንዳትረታ። ታጥቦ ጭቃ። ትሁት በሠራው፥ ብልጥ ይሾማል። ትለብሰው የላት፤ ትከናነበው አማራት። (ትከናነበው ~ የምትከናነበው) ትላንት ልጄን ዚሬ እናቴን፥ ምን ይበጃል ዗ንድሮ አለ አውራ ድሮ። ትላንት የበላናት ሲሳይ ሀ ባይ፤ አመድ ላይ ተንከባላይ፥ ዳውላን አዚይ። ትልቁ ዳቦ ሉጥ ሆነ። ትልቁ አሣ ትንሹን አሣ ይውጣል። ትልቁ አውራ ድሮ እንቁላል ነበር። (አንድ ጊዛ) ትልቅ ብልኀት፥ ለትምህርት መትጋት። ትልቅ ብልኀት፥ ለንጉሥ መገዚት። ትልቅ ጥቃት፥ ለምኖ ማጣት። ትልቅ ጦር፥ ባይወጉበት ያስፈራሩበት። ትልና መጋዝ፤ በሽተኛና ጑ዝ። ትምህርት በልጅነት፤ አበባ በጥቅምት። ትምህርት ከሚሉት ነቀርሳ፤ ኤድስ ከሚሉት በሽታ (ያውጣን)። ትምህርት፥ የማያልቅ ሀብት። ትምህርት፥ የማያልቅ ምርት። ትምህርትም እንደ ኮት፥ ፋሺኑ አለፈበት። ትምህርትን ለፈጠረ ጥይት፤ በርጫን ላገኘ ገነት። ትራሱን ከፍ አድርጎ ተኛ። ትሞታለች። ትርፉን ገልጸህ፤ መከራውን ሳትነግረኝ። ትርፍ ከአላማረ፥ መከራ አይገኝም። ትሻልን ፈትቼ፤ ትብስን አገባኹ። ትበያለሽ ግን አትጠግቢም። ትተውት የማይኼደትን፥ ባልንጀራ አይቀድሙትም። (አይቀድሙትም ~ አይቅደሙት) ትናንሽ ልጆች፤ ትናንሽ ሀብቶች። ትንሳዔ ትንሳዔ ቢሉኝ፥ ጸልተ ሀሙስ መሰልኝ። ትንሽ ወጠጤ፤ ቀንደ ሠላጤ። ትንሽ ልጅ ከሠራው፤ ሽማግላ የጎበኘው። ትንሽ ምላጭ፤ አገር ትላጭ። ትንሽ በመናገር፤ እውነት ትከበር። ትንሽ ሥንቅ ይ዗ህ፥ ከባለ ብዙ ተጠጋ። ትንሽ ጥንቸል በአገሯ፥ ለጎሽ ታገዳለች። ትንሽ ሥጋ፥ እንደ መርፌ ትወጋ። ትንሽ ሰው፥ ትንሽ ነው። ትንሽ ሽሮ ባገኝ፥ ጨው የለኝም እንጂ፥ ተበድሬ ወጥ እሠራ ነበር። ትንቢት ይመራል፤ ል጑ም ይገራል። ትንሽ ቆል ይዝ፥ ከአሻሮ ተጠጋ። (ተጠጋ ~ ጠጋ) ትንሽ ቆል ይዝ፥ ከአሻሮ ጋ ትጠጋ። ትንሽ ቆል፥ ያደርሳል ከአሻሮ። ትንሽ ጭላንጭል፥ ታስይዚለች ምንጭር። ትንሽ ጎልማሳ፥ ትቢያ ታነሣ። ትንባሆ ለምን ይበጃል? ያስተዋውቃል። ትንተና ነው ወይስ ቅንቀና (ያጠናው)? ትንኝም ለሆደ ዝኆንም ለሆደ ተያይ዗ው (ወደ) ወንዝ ወረደ። ትንኝም ለሆደ ዝኆንም ለሆደ፥ ወደ ወንዝ ወረደ። ትእቢትን ከሥሥት፥ ምን አገናኝቶት። ትዕግሥተኛ ከፈለገበት ይደርሳል። ትዕግሥት ፍራቻ አይደለም። ትከሻው ከአበጠ፥ ዝንጀሮም አንበሳ ይሆናል። ትኩሱ ሬሳ፥ ደረቁን አስረሳ። ትኩስ ሬሳ፥ የቀድሞውን ያስነሣ። ትኩስ ሬሳ፥ ደረቁን አስነሣ። ትኩስ በድቁስ። ትካዛ ሲመጣ፥ መከፋት ጑ዝ ይሆናል። ትክ ብል ላያት፥ ሽንብራም አፍንጫ አላት። ትወልዳለች ሲሎት፥ ከነደሙ ከለከላት። ትወልዳለች ብዬ ባገባት፥ ከነደሙም ከለከላት። ትዳርና ጫማ እያደር ይመቻል። ትዳርና እንቅፋት፥ ድንገት (ነው)። ትገርም ሻሸመኔ፤ ትብስ ኮፈላ። ትጉህ፥ ከአንድ እንጀራ ይጠግባል። ትግል አይሉት ልፊያ (ይሆናልና)። ትጸድቅ ትኮነን ቢለው፥ ቆይ መክሬ አስታውቅሀለኹ አለ። ትፈጭ የነበረች፥ ለአመልማል ኮራች። ትፈጭ የነበረች፥ መከካት አቃታት። ትፈጭ የነበረች፥ ማን጑ለል ተሣናት። (ተሣናት ~ አቃታት) ቶል ቶል ቢቆጡ፥ አብረው አይቀመጡ። ቶፋ፥ መቀበሪያው ያው ፈፋ። ቶፋ፥ በማን ምድር ትለፋ? ቸር ሚስት ያገኘ፥ በረከትን አገኘ። ቸር ይመፀውታል፤ ጠላት ያጠፋል። ቸር ተመኝ፥ ቸር እንድታገኝ። ቸርን ቢያጠብቁት፥ ቢስ ይሆናል። (ቢስ ~ ንፉግ) ቸርን ቢያጠቁት፥ ቢስ ይሆናል። ቸኩለው ያፈሱታል፤ ተቀምጠው ይለቅሙታል። ቸኩል ከተጠቀመ፥ ዝግ ብል የተጎዳ ይሻላል። ቻቻታ የለመደ ሰው፥ አባይ ዳር ቅበሩኝ ይላል። ችችችች ያመኑት ፈረስ፥ ጣለ በደንደስ። ችኩል ሰው፥ ጠንቋይ ይጠይቃል። ችኩል፥ ቅቤ ያንቀዋል። ችኩል አደን጑ሬ፥ ሳይበሉት ሆድ ያማል። ችኩል አፍ፥ ሞትን ይጠራል። ችኩል እግር፥ ከ዗ንድ ጉድ጑ድ ይገባል። ችኮ የጦም ሥጋ። ችግረኛ:_ ሲናገር ውሸት፤ ሲደነፋ እውነት። ችግር ለወዳጅ ሲያዋዩት ይቀላል። ችግር የገረፈው፥ ውጤቱ ያማረ ካልተንቀባረረ። ችግር፥ በቅቤ ያስበላል አለች ውሻ። ችግር ነው ጌትነት፥ (በቅቤ ያስበላል)። ኀለፈ ክረምት፤ ቆመ በረከት። ኀምሳ ልሚ፥ ለኀምሳ ሰው ሽቱ ነው፥ ለአንድ ሰው ሸክሙ ነው። ኀምሳ ልሚ፥ ለኀምሳ ሰው ጌጡ፥ ለአንድ ሰው ሸክሙ። ኀምሳ ልሚ፥ ለኀምሳ ሰው ጌጡ ነው፥ ለአንድ ሰው ሸክሙ ነው። ኀምሳ ልሚ፥ ለአንድ ሰው ሸክሙ፥ ለኀምሳ ሰው ጌጡ። ኀምሳ ልሚ፥ ለአንድ ሰው ሸክም፥ ለኀምሳ ሰው ጌጥ ነው። ኀምሳ ልሚ፥ ለአንድ ሸክም ነው፥ ለኀምሳ ሰው ጌጥ ነው። ኀምሳ ሰማ፤ ጆሮ ገማ። ኀምሳ ሆነው፥ ኀምሳ በግ ፈጁ። ኀምሳ ዳቦ ከመላስ፥ አንደን መቅመስ። (መቅመስ ~ መግመጥ ~ መጉረሥ) ሀሰተኛ ምስክር፥ ጉልበት ይሰብር። ኀይለኛ ደቄት ከነፋስ ይጣላል። (ይጣላል ~ ይጠጋል) ሃይማኖቱ ከጅማት፥ ጉልበቱ ከብረት የጠና። ሃይማኖት ከግብር፤ ጸልት ከፍቅር። ኀጢአት ሳያበዙ፥ በጊዛ ይ጑ዙ። ኀጢአት በንስሓ፤ እድፍ በውሃ። ኀጢአትና ሸክላ የሚገሥጸውን ይጠላል። ኀጢአት(ን) በንስሓ፤ በደል(ን) በካሳ። ኀፍረተ ሥጋውን፥ የጠበቀ ህይወቱን ጠበቀ። ኀፍረት ያከሳል፥ ያመነምናል። ኀ዗ንሽ ቅጥ አጣ፥ ከቤትሽ አልወጣ። ኀ዗ንሽ ቅጥ አጣ፥ ከቤትሽም አልወጣ፤ የገደለው ባልሽ የሞተው ወንድምሽ። ኀ዗ንና ደስታ በአንድ ገበታ። ኀ዗ንና ደስታ ጎን ለጎን ናቸው። ኀ዗ንን የፈራ፤ በደስታ የተጣራ። (የተጣራ ~ የተጠራ) ኀይለኛ ውሃ አሻቅቦ ይፈሳል። ነቅናቂ ሳለ፥ ማን ጥሩ ይጠጣል? ነበረ እንጂ፥ ይኖራል የሚባል ፍጡር የለም። ነበር ባይሰበር። ነበር፥ እንዱህ ቅርብ ነበር አሉ እቴጌ ጣይቱ። ነበርንበት አትኩሩበት። ነቢያት በመደመደ፤ ሀዋርያት ገደገደ። ነቢያት በቀየሱ፤ ሀዋርያት ገሠገሡ። ነቢይ በአገሩ አይከበርም። ነቢይ ቢኖር፥ በከበረ ነበር። ነብር ሳይገድል፥ ቆዳውን ያስማማል። ነብር ቢያንቀላፋ፥ ዝንጀሮ ጎበኘው። ነብር ባየለበት ዗መን፥ ድመት ይበረታል። (ይበረታል ~ ይኮርታል) ነብር አየኝ በል። ነብር አይኑን ታመመ፤ ፍየል መሪ ሆነ። ነብር የሞተ ዕለት፥ ፍየል ልጇን ትድራለች። ነብርን ካልነኩት አይነካም። ነብርን ሲይዙ ተጠንቅቆ፤ ጎመሮ ሲገቡ ደኮ ታጥቆ። ነዋሪ ለ዗ለአለም፥ አለ አምላክ የለም። ነውረኛ፥ ታሞ አይተኛ። ነውሩን የማያውቅ ወላቃ፥ ሲሥቁ ይሥቃል። ነውር ለባለቤቱ፥ እንግዳ ነው። ነውን ለማወቅ፤ ነበርን ጠይቅ። ነገረ ሠሪ፤ ጆሮ አጋሚ። ነገረኛ ሰው፥ በቤቱ አይሞትም። (በቤቱ ~ ከቤቱ) ነገረኛ፥ ታሞ አይተኛ። ነገረኛ ናቸው፥ በጣም ፍሯቸው። ነገረኛ ናቸው፥ በጦም ቅበሯቸው፥ የተነሡ እንደሆን ብዙ ነው ጣጣቸው። ነገረኛ ናቸው፥ አርቃችኹ ቅበሯቸው። ነገረኛ ናቸው፥ አጥልቃችኹ ቅበሯቸው፥ የተነሡ እንደሆን ብዙ ነው ጣጣቸው። ነገረኛ ዝንጀሮ፥ ውሻ ታረባለች። ነገረኛ ገለባ፥ ከእሳት ጋር ይጣላል። ነገረኛ ገደል፥ በሬ ያሳልፋል ዝንጀሮ ይጠልፋል። ነገሩ ነው እንጅ፥ ቢላዋ ሰው አይጎዳም። (ቢላዋ ~ ጩቤ) ነገሩ ነገር ነው፤ ውስጡ ጉራንጉር ነው። (ጉራንጉር ~ ጥቅንጥቅ) ነገሩን በልጥ አሰረው። ነገሬ በሆዳ፤ መንገዳ በአመዳ። ነገሬ በከንፈሬ። ነገር ለሰሚ፤ ውሃ ለተጠሚ። ነገር ለበለጥ፤ ውድማ ለመለጠ። (ለመለጠ ~ ለመለጥ) ነገር ለጀማሪው፤ እሳት ለጫሪው። ነገር ላምጫ ይግደደው። ነገር ሲበዚ ጥፋት፤ አጀብ ሲበዚ ሥጋት አይቀርም ይባል የለ። ነገር ሲያመልጥ፤ ራስ ሲመለጥ። ነገር ሲበዚ፥ በአህያ አይጫንም። ነገር ሲበዚ፥ ይሆናል ዋዚ። ነገር ሲያመልጥ፤ ራስ ሲመለጥ አያስታውቅም። ነገር ሲጀመር፤ እህል ሲከመር። ነገር ሳያውቁ ሙግት፤ ሳይጎለብቱ ትእቢት። ነገር ሳያውቁ ሙግት፤ አቅም ሳይኖር ትእቢት። ነገር ስንት ነው? ኹለት፤ ምን ያበዚዋል? ውሸት። ነገር በሆዳ፤ መንገድ በአመዳ። ነገር በሆዳ እየተመኘኹ፤ ቢከፍቱት ተልባ ሆኜ ተገኘኹ። ነገር በለዚው፤ ጥሬ በለዚዚው። ነገር በልክ፤ ሙያ በልብ። ነገር በመልከኛ፤ ጠላ በመክደኛ። ነገር በምሳላ፤ ቅኔ በሃላ። ነገር በምሳላ፤ ጠጅ በብርላ፤ መዝሙር በሃላ። (መዝሙር ~ ዛማ) ነገር በቀጠሮ፤ ዗ፈን በከበሮ። ነገር በምሳላ፤ ጠጅ በብርላ። ነገር በተርታ፤ ሥጋ በገበታ። ነገር በትኩሱ፤ ጨዋታ በወዙ። ነገር በነገር ይወቀሣል፤ እሾህ በእሾህ ይነቀሳል። (ይነቀሳል ~ ይጠቀሳል) ነገር በአዋቂ፤ ብረት በጠራቂ። ነገር በአይን ይገባል። ነገር በእርቅ፤ መንገድ በድርቅ። ነገር በእርቅ፤ ወይፈንን በድርቅ። ነገር በወቀሣ፤ በደል በካሳ። ነገር በዋስ፤ እህል በነፋስ። ነገር በዋና፤ ሚድ በእረኛ። ነገር በዋና፤ ሜዳ በእረኛ። ነገር በዋና፤ ዗ፈን በገና። ነገር በዋናው፤ ንብ በአውራው። ነገር በዳኛ፤ ሚድ በእረኛ። ነገር በጀማሪው፤ ውሃ ከማሻገሪያው። ነገር በፈሉጥ፤ ካልሆነ በፍልጥ። ነገር ቢሳሳት ከጠዋቱ፤ ጥጃ ቢሳሳት ከእናቱ። ነገር ቢሳሳት ከጥንቱ፤ ሰይፍ ቢመ዗ዝ ከአፎቱ። (ቢመ዗ዝ ~ ቢመለስ) ነገር ቢበዚ፥ በአህያ አይጫን(ም) ነገር ቢኖራችኹ ነው እንጂ፥ የማለዳ መንገድ ጠፍቷችኹ ነወይ። ነገር ተሥሩ፤ ውሃ ከጥሩ። (ተሥሩ ~ ከሥሩ) ነገር ነገርን ያመጣል፤ ድግር አፈር(ን)ያወጣል። ነገር ነገርን ያነሣል፤ ጥጋብ ሞትን ያስረሳል። ነገር ነገርን ይወልዳል። ነገር አለኝ ከማለት፤ ሥራ አለኝ ማለት። ነገር አለዳኛ፤ ነድ አለመጫኛ። ነገር አንሺውን፤ እሾህ አጣሪውን (ይወጋል)። ነገር አዳምጦ፤ እህል አላምጦ። ነገር እንደዚፉ፤ ዚፉ እንደ ቅርንጫፉ። ነገር እንዱጠፋ፥ ዳኛውን ግደል። ነገር እንዳገቡት፤ ሙክት እንዳሰቡት። ነገር እንዳፉ፤ ዚፉ እንደ ቅርንጫፉ። ነገር ከመጀመሪያ፤ ፍለጋ ከመሸጋገሪያ። ነገር ከመጀመሪያ፤ ፍለጋ ከመሻገሪያ። ነገር ከመጀመሪያው፤ ውሃ ከመሻገሪያው። ነገር ከመጀመሪያው፤ እህል ከመከመሪያው። ነገር ከመፈለግ፤ ይቻላል ነግ ፈረግ። ነገር ከሥሩ፤ ውሃ(ን) ከጥሩ። ነገር ከአምጩ፤ ውሃ ከምንጩ። ነገር ከአንሹ፤ ሥጋ ከጠባሹ። ነገር ከሰነበተ፤ ቅራሪ ከሆመጠጠ። ነገር ከአንሺው፤ ሥጋ ከጠባሺው። ነገር ከአዋቂ፤ ብረት ከጠራቂ። ነገር ከአጀማመሩ፤ እህል ከአከማመሩ። ነገር፥ ከእብድ ይገኛል። ነገር ከዋስ፤ ምላስ ከጥርስ (አያልፍም)። ነገር ከግቡ፤ ጋሻ ከእንግቡ። ነገር ከፊቱ፤ ደቄት ከወንፊቱ። ነገር ዅሉ በመጀመሪያ ይከብዳል፥ በኋላ እየቀለለ ይኼዳል። ነገር ለሰሚ፤ ውሃ ለልሚ። ነገር ዅሉ በኹለትና በሦስት ምስክሮች ይጸናል። ነገር ወዳት ትኼዳለህ? ጎንደር፤ መጨረሻህ? ከአገር። ነገር የሚከረው፥ ጎን጑ኙን ሲያገኝ ነው። ነገር ወዳድ ሰው፥ ከመንገድ ዳር ቅበሩኝ ይላል። ነገር ወዳጅ፤ ነገር ያነጉታል። ነገር ወዳጅ፥ ከቤቱ አይሞትም። ነገር ወዳት ትኼዳለህ? ወዳገር። ነገር የሻ ዳኛ፥ አምጡ ይላል የድሮ ሻኛ። ነገር የዋለበት ዳኛ፤ ከብት የዋለበት እረኛ። ነገር የዋለበት ዳኛ ያውቃል፥ ከብት የዋለበት እረኛ ያውቃል። ነገር የፈራ ይቃጠራል፤ አውሬ የፈራ ያጥራል። ነገር ያለ ዳኛ ተረት፤ ሰማይ ያለ ደመና ብረት። ነገር ያለ ዳኛ፤ ትብትብ ያለ መጫኛ። ነገር ፈጣሪውን፤ እሾህ አጣሪውን። ነገር፥ ከእጅ ይገኛል። ነገር፥ ይጸናል በሦስት። ነገርም ይበረክታል፤ ባለጋራም ይታክታል። ነገርና መጫኛ እንዳሳጠሩት ወይም እንዳስረ዗ሙት ነው። ነገርና ገመድ፥ አለውሉ አይፈታም። ነገርን በእርቅ፤ ወይፈንን በድርቅ። ነገርን አዳምጦ፤ እህልን አላምጦ። ነገርን ከሥሩ፤ ውሃን ከጥሩ። ነገርኩት መስዬ፥ እንዱመስለው ብዬ። ነገርህና ነግሬ ልክ ነው፤ ሰው መስማቱ ትርፍ ነው። ነገርህን በጠጄ፤ ርስትህን በልጄ። ነገደ አበደ፤ ተሾመ ሰለመ፤ አረሰ ነገሠ። ነጋ ላሉቱ፤ ሰጋ ላማቱ። ነጋሪ የላለው፥ ይታማ አይመስለው። ነጋሪት ገሣ፥ ውቤ ገሠገሠ፥ ወዳት ትገባለህ ሰባጋድስ ካሳ። ነጋዳ ባያፍር ጨው አበሰልኩ ይላል። ነጋዳ ወረቱን፤ ዗ላን ከብቱን፤ ገበሬ ምርቱን። ነጋዳን ከ዗ማች፥ ምን አቀላቀለው? ነጎድ጑ድ የማያሰማ ዝናብ አይምታን። ነጠላ ፍቅር፥ በአንድ እጅ ማጨብጨብ። ነጩ አሸልቶ፤ ጠጁ ጠርቶ፤ ወጡ ሰልቶ። ነጭ ሽንኩርት በመሽተቱ፥ ራሱን ቀብሮ ይኖራል። ነጭ ሽንኩርት የበላ፥ እንደ ልቡ አይናገርም። ነጭ እንደሸማ፤ ትክል እንደ ትርሽማ። (ትርሽማ ~ አክርማ) ነጭ ከመጣ፤ ነገር መጣ። ነጭ ድሀ፥ ነጭ ማር ይከፍላል። ነጻነት ያኮራል፤ ሥራ ያስከብራል። ነፋስ ሲነሣ፥ እሳት አይጫርም። ነፋስ በተነሣበት ጊዛ እሳት አይጭሩም። ነፍስ በደም ታድራለች። ነፍስ በፈጣሪዋ፤ ሴት በአሳዳሪዋ። ነፍስ ካለ መንቀሣቀስ አይገድም። ነፍጥ ቢያ጑ራ፥ የጌታውን ጎን ይሰብር። (ጎን ~ ጎድን) ኑ ባይ ከባሪ፥ እንቢ ባይ ቀላይ። ኑር በአገር፤ ጥፋ ከአገር። ኑሮ በ዗ዳ አቶ ዗ወልዳ። ኑሮ በ዗ዳ፤ ጾም በሐዳዳ። ኑሮ በደጋ፤ መቀመጥ በአልጋ ታላቅ አደጋ። ኑሮ በደጋ፤ መተኛት በአልጋ። ኑሮ ቢያምርህ ችላ፤ ጥጋብ ቢያምርህ ባቄላ። ኑሮ ኑሮ ከመሬት፤ ውል ውል ከቤት። ኑሮ ኑሮ ከመሬት፤ ዙሮ ዙሮ ከቤት (አይቀርም)። ኑሮ ኑሮ ከሞት፤ ውል ውል ከቤት። ኑሮ ከማናደድ፥ ኼድ መመስገን። (መመስገን ~ መናፈቅ) ኑሮ ካሉት መቃብር(ም) ይሞቃል። ኑሮ ካሉት፥ የጤፍ ቅጠል ኹለት ሰው ያስተኛል። ኑሮ ካሉት፥ ፍሪጅ ይሞቃል። ኑሮ ካሉት፥ ፍሪጅ ይሞቃል የቢራ ጠርሙስ። ኑሮ ካሉት፥ ፍሪጅም ይሞቃል አለ ቅቤ። ኑሮ ያኗኑራል፥ ሕግ ያከባብራል። ና ብላኝ፥ የት ኼደች? ና ባይ አክባሪ፤ እንቢ ባይ (ተ)ቃላይ (ነው)። ና ባይ አክባሪ፤ እንቢ ባይ አቃላይ ነው። ና ብላ ሳይሉት፥ ከወጡ አውጡልኝ። ና ያሉት፥ እንግዳ እራቱ ፍሪዳ። ናቂ ወዳቂ። ናዳ መጣልህ፥ ቢሉት ተከናንቤአለኹ (ልቀቀው) አለ። ንቅ ያለበት፥ ዕንጨት ታቦት አይሆንም። ንቡን አባሮ፥ ማሩን። ንባቡን በማጉላት፥ ምሥጢሩን በማርቀቅ። ንብ ለባለቤት፥ ሳያረዳ አይኼድም። (ሳያረዳ ~ ሳያርፍ) ንብ ለአጥር፥ ሳያረዳ አይኼድም። ንብ ሲሰማራ፤ አጥሩን ተመልከት። ንብ በአውራው፤ ገበሬ በአዝመራው (ይታወቃል)። ንብ ቢኼድ ከአጥር፤ ሰው ቢሰደድ ከአገር። ንብ ያለ አውራው፥ መርከብ ያለ ካፒቴኑ ማረፊያ አያገኙም። ንብረቴ አትውጪ ከቤቴ፤ እንዳታጣዪኝ ከጎረቤቴ። ንብና ምን፥ ትከሻ ይወዳል። ንብን አይተህ፥ ተገዚ ብሎል እግዛር። ንካ ያለው አይቀርም። ንዳማ ቢያጭደት፥ ክምር አይሞላም። ንገሥ ቢሉት፥ ሳልዋጋ አልነግሥ(ም) አለ። ንገረው ንገረው፥ እምቢ ካለ መከራ ይምከረው። ንገሩኝ ባይ፤ የሽንብራ ቆል ያሻል። ንጉሡ በድን኱ናቸው፥ እኔ በጎጆዬ (ንጉሥ ነን አለ ድሀ)። ንጉሡ ቢሞቱ፥ ከማን ይሟገቱ። ንጉሡ ከሾመው፤ ማረሻ የሾመው። ንጉሥ ለብያኔ፤ አቡን ለኩነኔ። ንጉሥ ሲሞት ግንቡን፤ ብልኅ ሲሞት ልቡን። ንጉሥ ሲቆጡ፥ ቀስ ብላችኹ ውጡ። ንጉሥ ሳይ፥ ክሰስ ክሰስ ይለኛል። ንጉሥ በመንግሥቱ፤ እግዛር በመለኮቱ፤ ጎልማሳ በሚስቱ። ንጉሥ በመንግሥቱ፤ ወንድ ልጅ በሚስቱ፤ መልከኛ በርስቱ። ንጉሥ በመንግሥቱ፤ ጎልማሳ በሚስቱ፤ አምላክ በአምላክነቱ። ንጉሥ በ዗ውደ፤ ድሀ ባመደ። ንጉሥ በግንቡ፤ ገበሬ በርስቱ ቢገቡባቸው ቀናተኞች ናቸው። ንጉሥ በግንቡ ይታማል። ንጉሥ ቢቆጣ፥ ቀስ ብለህ ውጣ። ንጉሥ ቢያርፍ፥ ዅሉ ይተርፍ። (ቢያርፍ ~ ቢያተርፍ) ንጉሥ አንጋሹን፤ ቤተክርስቲያን ቀዳሹን። ንጉሥ አይከሰስ፤ ሰማይ አይታረስ (አባት አይወቀስ)። ንጉሥ ከሠየመው፤ ማረሻ የሾመው። ንጉሥ ከሾመው፤ ማረሻ የሾመው። ንጉሥ ከተነፈሰ፤ አይን ከፈሰሰ። ንጉሥ ከተነፈሰ፤ ውሃ ከፈሰሰ። ንጉሥ ከግንቡ፥ ውጭ ይታማል። ንጉሥ የሰቀለው፤ አንበሳ የሰበረው። ንጉሥ የቆረጠው እጅ፥ ካለ ይቆጠራል። ንጉሥ የወደደው፤ ዗መን የወለደው። ንጉሥ የፈረደበት፤ መርከብ የተሰበረበት (አንድ ነው)። ንጉሥ ያላቸው ንቦች ማር ይበላሉ፤ ንጉሥ የላላቸው ዝንቦች ጥንብን ይልሳሉ። ንጉሥ ይሞግትልህ፤ ንጉሥ አይሞግትህ። ንጉሥ ይተክላል፤ ንጉሥ ይነቅላል። ንጋትና ጥራት እያደር ይታያል። ንጋትን አውራ ድሮ ያውቃል፥ ወፍ ያረጋግጣል። ንጋትን ድሮ ያውቃል፥ ወፍ ያረጋግጣል። ንግርና ግግር፥ ሳይደርስ አይቀር። ንግዳ ዳር ዳሩን ያነጥንጥ፤ ሣህለ ሥላሴም ከአልጋው አይናወጥ። ንግድ ለወረት፤ ወዳጅ ለችግር ዕለት። ንግግር ሲበዚ ያጠፋል፤ ማር ሲበዚ ያስተፋል። ንጣት ይገድለው ነበር። ንፅህና ለሥጋ፤ ለነፍስ ጤና። ንፉግ ለግሶ ቢሰጥ፥ እጁ ይንቀጠቀጥ። ንፍጥ ለባለቤቱ፥ ቅቤ ነው። ኖረሽ አልጠቀምሽን፥ ሞተሽ አለቀቅሽን። ኖር በዪው ልብሱን፥ ሰውየውስ የቅድሙ ነው። ኖር ከአንገት፤ ወገብ ሥራ አለበት። ኖሮ ኖሮ ከሞት፥ ዝሮ ዝሮ ከቤት። አህያ ለማኝን፥ አህያ ለማኝ ቀደመው። አህያ ለሰርድ፤ ሰው ለመርድ። (ሰው ~ ባላገር ~ ድሀ) አህያ ለአህያ ቢራገጥ፥ ጥርስ አይሳበር። አህያ ለአህያ፥ ጥርስ አይሳበርም። አህያ ልጆቿን ይዚ ብትጠፋ፥ ጅብ የሚደፍራት አይመስላትም። አህያ ሞተች ተብል፥ ከጉዝ አይቀርም። አህያ ሞተች ተብል፥ ጉዝ አይቀር። አህያ ሰባ፤ ምን ረባ? አህያ ሰባ፥ አልታረደም ምን ረባ? አህያ ሰባ፥ ካልታረደ ምን ረባ? (ካልታረደ ~ ካልተበላ) አህያ ሲረግጥህ መልሰህ ብትረግጠው፥ አንተም አህያ ነህ። አህያ ሲግጥ፤ ደብተራ ሲያላግጥ ይሞታል። አህያ ሲጠግብ አምቦ፤ ልጅ ሲጠግብ ሸንጎ። አህያ ሲጠግብ፥ ከጅብ ይጫወታል። አህያ ሲጭኑ ሦስት ኹኖ፤ ከሰው ሲኖሩ ሞኝ ኹኖ። አህያ ሲጭኑ(ት) ሦስት ሆኖ፤ መንገድ ሲኼደ ኹለት ሆኖ። አህያ ቀንድ ቢያወጣ፤ ቁራ እንዳት በነጣ። አህያ በለስላሳ ምላሷ፥ እሾህ ትበላለች። አህያ በሞተች በዓመቷ፥ ኩር ኩር። አህያ በወለደች ታርፋለች። አህያ ቢሞት ጉዝ አይቀሩም፥ ገዥ ቢጠፋ ተገዥ አይጠፋም። አህያ ቢረግጥህ መልሰህ ብትረግጠው፥ አህያው አንተ እንጂ፥ እሱ አይደለም። አህያ ቢያጋድል በመጫኛ፤ ዳኛ ቢያዳላ በዳኛ። አህያ ተማላ፤ ጅብ አወረደች። አህያ ተማል፥ (ተማምል) ጅብን አወረደ። (ተማምል:_ ለምኖ) አህያ፥ አህያን አረደበት። አህያ አረደበት። አህያ አትመሀኝብኝ፥ ትበላኝ እንደሆነ እንዱያው ብላኝ (አለች)። አህያ እን኱ን፥ በወለደች ታርፋለች። አህያ እንደ አባቱ ይፈርጥጥ፤ ጅብም እንደ አባቱ ይ዗ርጥጥ። አህያ እንደምትታለብ፥ ከላሞች ፊት (ለፊት) ትቅለበለብ። አህያ ከመሞቷ፥ መጎተቷ። አህያ ከአመደ፤ ሰው ከ዗መደ። አህያ ወደ ሜዳ፥ ጅብ ወደ ጑ዳ። አህያ የለኝም፥ ከጅብ አልጣላም። አህያ የላለው፥ በቅል ያን኱ስሳል። (ያን኱ስሳል ~ ያነውራል ~ ይንቃል) አህያ የላለው፥ ቤቢ ፊያት ይንቃል። አህያ የተጫነችውን አትበላም። አህያ ያለ ዕውቀት፥ እጅብ ቤት ገባች። አህያ ጅብ፥ ለቅሶ ኼደች። አህያ ፈሳች ብል፥ ማን አፍንጫ ይይዚል? አህያ ፈረሱን፥ አንተ አህያ ብል ሰደበው። አህያም እንደ አባቱ ይፈርጥጥ። አህያም እንደ አባቱ ይፈርጥጥ፤ ጅብም እንደ አባቱ ይ዗ርጥጥ። አህያም የለኝ፥ እርግጫም አልፈራ። አህያም የለኝ፥ ከጅብ አልጣላ። አህያና አቁማዳ ልመና፤ ያለ መጫኛ ዅሉ መና። አህያና ጑ያ፥ በምስያ። አህያና ፋንድያ፤ አራዳና ገበያ። አህያና ጑ያ፥ በአምሳያ። አህያን ሥጋ ጭነህ፤ ጅብን ንዳ ብለህ እንጃ ይሆን(ን) ብለህ። አህያን በመንገድ፤ ካህንን በማርገድ። አህያን በአመድ፤ ካህንን በማእድ። አህያን አባትህ ማን ነው ቢሉት፥ አህያን ከላም ነዶት። አህያው ፈረሱን፥ አህያ ነህ ብል ሰደበው። አህያውን ቢፈሩ፥ መደላድሉን ሰበሩ። አህያውን ቢፈሩ፥ ዳውላውን መቱ። አህያውን አመሰግን ብል፥ ፈረሱን አዋረደ። አህያውን ፈርቶ፥ ዳውላውን። አህያዬ ነች እያልክ ንዳ፤ ዗መዳ ነች እያልክ **። አለ መባ፥ ቤተ ክርስቲያን አትገባ። (አትገባ ~ አትግባ ) አለ መንገድ እየኼደ፥ ጅብን ነገረኛ ያደርጉታል አሉ። አለ ሲል ባለቤት፤ ሞተ ይላል ጎረቤት። አለ ራቱ አይቆርስ፤ አለ ረጀቱ አይወርስ። አለ በለኝ ቀለቤን፤ ሞተ በለኝ ከፈኔን። አለ በል ቀለቤን፤ ሞተ በል ከፈኔን። አለ ባለቤቱ፥ አይነድም እሳቱ። አለ ባል ሴት ወይ዗ሮ፥ አለ ማንገቻ ከበሮ። አለ ብልኀት ገደል መግባት፤ አለ ጉልበት ውሃ መግባት። አለ ነገር፥ ፒያሳን ስንሻገር። አለ ንጉሥ ሰላም፤ አለ ደመና ዝናብ የለም። አለ ንጉሥ ዗ውድ፤ አለ ምሳር ግንድ። አለ አሽከር በቅል፤ አለ ወንድም አንባ ጑ሮ። (ወንድም ~ ወንድማማች) አለ አቁማዳ መጫኛ፤ አለ ከብት እረኛ። አለ አቅሙ፥ ጥሬ መቃሙ። አለ አቅማቸው እንዋጋ ቢሉ፥ ጀግኖችን አስገደሉ። አለ አቡን ቄስ፤ አለ ዗ውድ ንጉሥ። አለ አቡን ክህነት፤ አለ ንጉሥ ሹመት። አለ አባት ቢዚቁን፥ ይባክን። አለ አባት ነገር፤ ዝንጀሮን ከባሕር አሣን ከገደል። አለ አባት፤ ጎመን በአ጑ት። አለ አባት፥ ጆሮ በጡጫ። አለ አቻ ጋብቻ፥ ቆይ ብቻ ቆይ ብቻ። አለ አንኮበር፥ ሾላ ሜዳ አይገኝም። አለ አንድ የላት፥ በ዗ነ዗ና ትነቀስ። አለ አንድ የላት ጥርስ፥ በ዗ነ዗ና ትነቀስ። አለ አንድ የላት፥ እንቅልፍ የላት። አለ አዋቂ ሳሚ፥ ንፍጥ ይለቀልቃል። አለ እህል አቁማዳውን ይሞላሉ፥ አለ ዗ር ይቀራሉ። አለ እኩያ ጋብቻ፥ ቆይ ብቻ። አለ ካሉት አይርብም። አለ ወንድም ጋሻ፤ አለ ድግር ዕርሻ። አለ ዋንጫ አይስማት፤ አለ ቀንጠፋ አይስባት። አለ ዋዚው ዋዚ፥ ማቄን ትቀጃለሽ። አለ ዋዚው ዋዚ፥ ቅቤም አያወዚ። አለ ውድ በግድ። አለ ዳኛ ሙግት፤ አለ ገመድ እክት። አለ ዳኛ ቀጠሮ፤ አለ ቅቤ ድሮ። አለ ዳኛ አይካሱ፤ አለ ጥርስ አይነክሱ። አለ ድሀ ዗ውድ፤ አለ ገበሬ ማእድ (አይገኝም)። አለ ጉልበት ሰኮና፤ አለ ራስ ጉተና። አለ ጨለማ ፍራት፤ አለ዗መድ ኩራት። አለ ፊቱ አይቆርሱ፤ አለረጃቱ አይወርሱ። አለኹ ባይ፥ አስ዗ላይ። አለላን በጉማሬ፤ መንገድን በወሬ። አለመታደል ነው፥ ቀላውጦ ማስመለስ። አለመንገድ እየኼደ፥ ጅብን ነገረኛ ያደርጉታል አሉ። አለመኛ እንትን፥ ቅቤ ቀቡኝ አለች። አለማረፌ፥ አንተን ማንከርፈፌ። አለማረፍ፥ የተርብ ቤት መቀስቀስ። አለማወቄ፥ በላኹ ተጨንቄ። አለማወቄ፥ ከ዗መድ መራቄ። ዓለም ኀላፊ፤ መልክ ረጋፊ። አለሥራ አይበላ እንጀራ፤ አለባል ቆጥ አይሠራ። አለቃ፥ ለራሱ አይበቃ። አለቃ ቢለቅ ለሻለቃ፤ ምንዝር ቢለቅ ላለቃ። አለቃ የላለው ሕዝብ፥ አውራ የላለው ንብ። አለቃ የሰጠው፤ አጣሪ የሸጠው። አለቃ ያውቃል፤ ድሀ ይጠይቃል። አለቅትና ድሀ፥ ውሃ ለውሃ። አለቃ፥ ለራሱም አልበቃ። አለቅን! አለቅን! አለች፥ የእንትን ቅማል። አለባብሰው ቢያርሱ፥ በኹለት እጅ አይጎርሡ። አለባብሰው ቢያርሱ፥ በአረም ይመለሳሉ። (ይመለሳሉ ~ ይመለሱ) አለባብሰው ከአረሱ፤ አይቀርም አረም ማፈሡ። አለት ለረገጠ ፍለጋ የለው፤ ውሃ ለጠጣ ሽታ የለውም። አለንጋ ለፈረስ፤ ጅራፍ ለሰነፍ። አለንጋ እስኪመጣ፥ በክርን ይተክዙ። (እስኪመጣ ~ እስኪገዙ) አለኝ ብል ከማፈር፤ የለኝም ብል መድፈር። አለንጋ፥ ባይገርፉበት ያስፈራሩበት። አለንጋ እስኪመጣ፥ በክርን ያዝግሙብኝ። አለኝ እንጂ፤ ነበረኝ አይጠቅምም። አለአቻ ጋብቻ፥ ቆይ ብቻ ቆይ ብቻ። አለኩያ ጋብቻ፥ ቆይ ብቻ (ቆይ ብቻ)። አለፈ በዋዚ፥ ልብ(ን) ሳልገዚ። አለው። አሉ ባሉ ዕዳ፥ አዎን ባለ ሜዳ። አሉ ብለህ፥ ከአላሉህ አትገኝ። አሉ ብል የተረታ፤ መሀል አገዳውን የተመታ። አሉባልተኛ፥ ላት ተቀን አይተኛ። አሉን ያህል ነገር፥ ማሉን ያህል ምስክር። አላህ ሞኝ ቢያገኝ፥ ምን ባደረገ? አላ ብል የተረታ፤ መሀል አገዳውን የተመታ። አልመህ ፍጭ፥ አልመህ ተኩስ። አላህ፥ ተሸካሚ ብለምነው፥ ሸክም አ዗዗ብኝ። አላህ፥ ወይ ውረድ፥ ወይ ፍረድ። አላህንም አምናለኹ፤ አህያየንም አስራለኹ። አላምን ያለች አራሽ፥ ታገነፋ ለራስ። አላምጠህ አላምጠህ፥ ወደ ወገንህ ዋጥ። አላረፈች ጣት፥ አር ጠንቅላ ትመጣለች። (ትመጣለች ~ ትወጣለች ~ ወጣች) አላረፈች ጣት፥ አር ጠንቅላ ትመጣለች። (ጠንቅላ ~ ጠንቁላ) አላርፍ ያለ ውሻ፥ ላፉ ሉጥ፥ ለጀርባው ልጥ አያጣም። አላርፍ ያለች ጊደር፥ ጅቦች ሰፈር ታነጅባለች። አላርፍ ያለች ጣት፥ ስትጠነቁል ትያዚለች። አላርፍ ያለች ጣት፥ አር ትጠነቁላለች። አላርፍ ያለች ጣት፥ አር ጠንቁላ መጣች። (መጣች ~ መጣች) አላርፍ ያለች ጣት፥ ክስ ተመሠረተባት። አላቻ ጋብቻ፥ ቆይ ብቻ ቆይ ብቻ። አላዋቂ ለባሽ፥ ልብስ አበላሽ። አላዋቂ ሳሚ፥ ንፍጥ ይለቀልቃል። አላዋቂ ቤት፥ እንግዳ ናኘበት። አላዋቂ አጉራሽ፥ አፍ ያበላሻል። አላዋቂ አጉራሽ፤ አፍ ያበላሽ። አላዋቂ ከአረደው፥ አዋቂ ያወራረደው። አላዋቂ ከአረዳው፥ አዋቂ ያወራረደው። አላዋቂ፥ ወሬ፥ ጠያቂ። አላዋቂ ጎራሽ፥ ማእድ ያበላሽ። አላዋቂነትን ምላስ፥ ቁስልን ልብስ ይሸፍነዋል። አላውቅም፥ አስገድል አያውቅም። አላየናት እንዱየው ገበያ ናት፥ እንዱየው ገበየናት። አላጋጭ አልማጭ። አላጋጭ ገበሬ፥ ይሞታል በሠኔ። አል ብል የተረታ፤ መሀል አገዳውን የተመታ። አመለኛ ውሻ፥ የጅብ መቋደሻ ይሆናል። አመሉ ከከፋ፥ ላከው ጎሙ ጎፋ። አልሞት ባይ ተጋዳይ። አልሞትም ብል ኼድ፥ ከማይቀርበት አገር ደረሰ። አልሰሜ የእናቱን፥ ተዝካር ይበላል። አልሰሜን ግባ በለው። አልሸሹም፥ ዗ወር አሉ። አልቀባም ብትል፥ ትመሰክር። አልቅትና መዥገር፥ ከላም ጡት ተጣብቆ ይገኛል። አልቅትና ድሀ፥ ውሃ ለውሃ። አልበላ አልጠጣ፥ ጎንደር ኺድ ቀረ፥ እንደወጣ። አልባሽ ብል ገፋፊ፥ ደጋፊ መስል ገፊ። (ይሰውረን) አልተጋበ዗ ገንፎውን፥ ላይበላ ይምላል። አልነገርኩሽም ወይ በአጥር ተንጠልጥዬ፣ ውሻ በቀደደው ጅብ ይገባል ብዬ። አልኹ ባይ፥ ይቅር ባይ። አልጋ ሲሉት አመድ። አልጋ ቢያብር፥ ለሆቴል ይጠቅማል። አልጋው ሲገኝ፥ ባሉ አይገኝ። አልጠግብ ባይ፥ ሆደ አይሞላም። አልጠግብ ባይ፥ ሲተፋ ያድራል። አልፎ አልፎ፥ በዋልድባም ይ዗ፈናል። አመላ፥ አወጣኝ ከማኅበሬ። አመል ላይቀር ቅጣት፥ ሞት ላይቀር ፍራት። አመል፥ ቤት አይጠብቅ። አመል ያላት አገልጋይ ከእመቤቷ እኩል ትቀባለች። አመል ያስወጣል፥ ከመሀል። አመል፥ ያገባል እመሀል። አመልህ፥ በጥፊ ይበልህ። አመልህ(ን) በጉያ፥ ሥንቅህ(ን) በአህያ። አመልና መልክ፥ አብሮ አያረጅም። አመልና ጅራት፥ በስተኋላ ይበቅላል። አመልና ጅራት፥ ከወደኋላ ነው። አመሥጋኝ አማሳኝ። አመራር ያጣ ትግል፤ ተቀባይ ያጣ ድል። ዓመት ላያበላ፥ ዓመት ያጣላ። አመንዝራ ስታረጅ፥ አቃጣሪ ትሆናለች። አመንዝራ ካሎት፤ ብትቆርብም አያምኗት። አመንዝራን ሳሚ እንጂ፥ አግቢ የለም። አመካከት፥ ዝንጀሮን ተመልከት። አመድ በደቄት ሲሥቅ፥ ልቡ በነፋስ ውልቅ። አመድ በደቄት ይሥቃል። አመድ ባለበት በስመአብ ማለት፥ የተኛ ጋኔን መቀስቀስ ነው። አመድ ያጠለቀው፤ ጉልቻ የላቀው። አመግል ብላ አሳበጠች። አመጸኛ ልላህን፥ በሰው ፊት አት዗዗ው። አሙኝ ብለህ፥ ከአሙህ አትገኝ። አማሪት በመብለጥለጥዋ፥ መንግሥተ ሰማያት በገባች። አማሪት እንደ መብለጥለጥዋ፥ መንግሥተ ሰማያት በገባች። አማሪት ገንቦኛ። አማርኛ እንዳበጁሽ ትሳሚያለሽ። አማቱን ምታ ቢለው፥ ሚስቴን በየት አልፌ (አለ)። አማትና ምራት፥ ሳይስማሙ መሬት። አማትና ምራት፤ እሳትና ራት ሳይስማሙ መሬት። አማቻችን አፈኛ፥ ቢመለስ ወደእኛ፥ ወይ እኛ እንሆን አሣረኛ። (እንሆን ~ እንኹን) አማቻችን አፈኛ፥ ይመለስ ወደእኛ። አማች ቆቁ፥ አንተ ተወልደህ ላልች ይለቁ። አማች አሟች። አማች አስታርቆ፤ ቀንበር አርቆ። አማች የበላው፤ እሳት የበላው። አማችና ቂጥ ትርፍ ነው። አማችና ጋሻ፥ ከአልሰጎደት አይወድም። አማጪን መጦር፤ አማጪን በጦር። (ክፉና ደግ) አማጭ ለልማደ፤ የበቅል ክበድ፤ የሀር ገመድ አለኝ ይላል። አማጭ ለአመሉ:_ የበቅል ክበድ፥ የሀር ገመድ ይላል። አማጭ ረማጭ። አማጭን መጦር፤ አማጭን በጦር። (ክፉና ደግ) አምላክ ሲሰጥ፥ ምክንያት ያዚል። አምላክ በአወቀ፥ ሰማዩን አራቀ። አምላክ የተቆጣው በረድ፥ ከድንጋይ ላይ ወርድ። አምራለኹ ብላ ተኩላ፥ አይኗን አጠፋች ቸኩላ። አምባ ያለው ፈሳሽ፤ ወንዝ ያለው መላሽ። አምቦ ወርድ፥ ጭቃ አይንካኝ አይባልም። አምነው የሞገቱት አያስረታ፥ ዝግ ብለው የታጠቁት አይፈታ። አምና ላሞቹ፤ ዗ንድሮ ጥጆቹ። አምና እረኞቹ፤ ዗ንድሮ በጎቹ። አምና ከላሞቹ፤ ዗ንድሮ ከጥጆቹ። አምና የሞተውን፥ ጥጃ ስደደ። አምኖ ለሚሟገት ረቺ የለው፤ ብቻውን ለሚሮጥ ቀዳሚ የለው። አምኖ ይሟገቷል፤ እጠገቡበት ይሸምቷል። አምዬ ጣጣሽ በዚዬ። አሞላ ሲወፍር፥ እወንዝ አውርዳችኹ እጠቡኝ ይላል። አሞራ ሲበሉ፥ ስሙን ጅግራ ይሉ። አሞራ በበላ፤ ጥፍጥሬን በደላ። አሞራ በዚፍ፤ ውርርድ በጫፍ። አሞራና ቅል ተጋቡ፥ አሞራው በረረ ቅሉም ተሰበረ። አሞራን ሲበሉ፥ ጅግራ ነው ይሉ። አሞራን ሲበሉ፥ ስሙን ጅግራ ይሉ። አሞራውም በረረ፥ ቅሉም ተሰበረ። አሠሩት ተበተቡት፥ በኋላ ሉፈቱት። አሰድ፥ የያ዗ውን አይሰድ። አሣ ለወጋሪ፤ ነገር ለጀማሪ። አሣ መብላት፥ በብልኀት። (አሣ ~ አሣን) አሣ በልቶ ውሃ መጠጣት፥ መልሶ ከነበረው ማግባት። አሣ በባሕሩ፤ ዝንጀሮ በገደሉ። አሣ በወንዙ ይታረዳል፤ የጨዋ ልጅ በቤቱ ይፈርዳል። (ይፈርዳል ~ ይፋረዳል) አሣ ብለምነው ዗ንድ፥ ዝናብ ብለምነው በረድ። አሣ አሣን ይበላዋል፥ ወንድም ወንድሙን ይጠላዋል። አሣ ከውሃ ወጥተህ ኑር ቢሉት፥ ምነው የምልሰው ድንጋይ፥ የምቅመው አሸዋ ነው አለ። አሣ ወጋሪ፤ ልብደ ሠሪ። አሣ ያለበት ባሕር፥ ዕውር ያለበት ደብር፥ ሳይበጠበጥ አያድር። አሣ ጎር጑ሪ፥ ዗ንድ አወጣ። (አወጣ ~ ያወጣል) አሣ ጎር጑ሪ፥ ዗ንድ ያወጣል፥ የሰው ፈላጊ የራሱን ያጣል። አሳማ በበላ፤ ጉፍጠራን በደላ። አሣ፥ የጌቶች ምሳ፥ የገረድ አበሳ። አሣው እንዳይሞት፥ ውሃው እንዳይደርቅ አድርጎ ነው እርቅ። አሣውም እንዳያልቅ፥ ውሃውም እንዳይደርቅ። አሥራ ኹለት ሆኖ፥ አንድ ነብር ፈጃት። አሥራው ከአሉ፥ አዕጹቁ ይገዳሉ። አሥር ቡልኮ፥ ፈስ አይደብቅም። አሥር የሚመኝ፥ አንድም አያገኝ። አሥር ያባረረ፥ አንድ አይዝም። አሥር ጊዛ ለካ፥ አንድ ጊዛ ቁረጥ። አስቀድመህ ሰኞን አትዅን። አሥብ ያለው፥ የመገ዗ዝ አይጥ ምን ትበላለች? እያለ እንቅልፍ ያጣል። አስተማሪ፥ ችጋር ጠሪ። አረመኔ በጭካኔ፤ ሙግት በውጣኔ። አረምና ጥላት ሳይ዗ሩት ይበቅላል። አረምን መንቀል፥ ሥር ሳይሰድ (ነው)። አረረም መረረም፥ ማኅበሬን ከፈልኩ። አረብ አንቀልባ፤ የሱፍ አበባ። አረጉን ሲስቡት፥ ዚፍ ይወዚወዚል። አረፉ ጀጀባውን። (:_የሆነ ያልሆነውን) አራምባና ቆቦ። አራስ የእጅዋን፤ ድመት የልጇን (ትበላለች)። አራሪ ለማራሪ፥ ማራሪ ለበራሪ ይተው። አራት ቀን መታመም ቸግሮት፥ አርባ ቀን ይታመማል። አራት ቁና አጃ ቢጠፋት፥ ኹለት ቁና ስንዳ ይዚ ከጠንቋይ ቤት። አራጅ ሆኖ፤ ጾም አይፈሩም። አር ላይ ተቀምጦ፥ ፈስ ገማኝ። አር ሲቀብጥ፥ እንግላል ይወድቃል። አር ቢሰበሰብ፥ ግርግዳ ይሆናል። አር የነካች ጣት፥ ገማች ተብላ ተቆርጣ አትጣልም። አርሶ ያልበላ፥ ሆነ ነኹላላ። አርሶ ያልጠገበ፥ ነግድ (አይሆንለትም)። አርሼ በበላኹ በቀንጃ በሬ፥ የ዗ንድሮን አሉን አክርሞት ጌታዬ። አርባ ኹነህ ና፥ አጪርና በራ ሰው አታምጣብኝ ብቻ። አርባ ዓመት ቢቀመጥ፥ በደል አያረጅም። አርባ ዓመት ከሆነው ጋር ምከር፥ ከሠላሳ ዓመት ልጅ ጋር መክት። አርባህ ሲደርስ፥ አርባ ቀን ዙር። አርጂ ጥኑ ነው። አሮም መሮም፤ ማኅበሬን ከፈልኹ። አሮጌ መጥረጊያ፥ ቤት አያጠራም። አሮጌ ማሳ ያረሰ፥ ለእንጀራ ልጅ ያጎረሠ። አሮጌ ቢታጠቅ ይዋጋ ይመስል፤ ግንቦት ቢዳምን ይ዗ንብ ይመስላል። አሮጌ ውሻ፥ በከንቱ አይጮህም። አሳማ ዝሮ ዝሮ ወደ ጭቃው አለ። አሳም በበላ፤ ጎፍናኔን በደላ። አሳምር ያሉት አያክፋ፤ ጠብቅ ያሉት አያጥፋ። አሳሳች፥ ከላይ ሲሉት ከታች። አሳብ የለሽ፥ ወጧ ጣፋጭ ነው። አሳብ የላለው ሰው፥ ሽንብራ ነቀላ ሲኼድ፥ ምሳዬን ይላል። አሣን ወደ ተራራ፤ ዝንጀሮን ወደ ባሕር። አሳይ ብላ፥ ታየባት። አሳይቶ መሳሳት፤ የሰጭ ቅላት። አሳይቶ መሳሳት፤ የሻጭ ቅላት። አሳዳጊ ለበደለው፤ ፊትህን አትስጠው። አሳዳጊ የበደለው፥ ለክፋት ያደለው። አሳግርቶች፥ እንመናተፍ ከአላችኹ እንመናተፍ። አሳፋሪ ልላህን፥ እሰው ፊት አት዗዗ው። አስመሳይ ወንድ፥ በረንዳ ያድራል። አስሰሽ አስሰሽ ምጣደ ሲደራ፥ አንቺ ወደ መሬት በላተኛው ላላ። አስረዝመው ያሰሯት ድሮ፥ የተፈታች ይመስላታል። አስቀድሞ ማመስገን፥ ለሀሜት ያስቸግራል። አስቀድሞ ማመስገን፥ ለማማት ያስቸግራል። (ያስቸግራል ~ ይቸግራል) አስቀድሞ ነበር መጥኖ መደቆስ፥ አዅን ምን ይሠራል ድስት ጥድ ማልቀስ። አስቀድሞ የተናገረን ሰው ይጠላዋል፤ አስቀድሞ ያሸተን ወፍ ይበላዋል። አሥብ ኹለቴ፥ ከመናገር አንዳ። አስተካክል ይቀዶል፥ ለእግዙአብሔር ብል ይፈርዶል። አስተዋይ ሰው፥ ያዝንበት አያጣም። አስተዋይነት ያነሰው ሰው፥ ከሚጎርሠው በላይ ይቆርሳል። አስተውል ላየው፥ የሽንብራ አፍንጫ አለው። አስቸጋሪ እንግዳ፥ ተ዗ቅዝቆ ይተኛል። አስጨነቀኝ ገንፎ፤ ከራቴ ተርፎ። አስፍቶ ከማረስ፥ ከበላተኛው መቀነስ። (ከበላተኛው ~ ከተቀላቢው) አሻሮ የበላ፤ አሻሮ ያገሳል። አሻሺኝና፥ ጠቁሚኝና፥ ልስጥሽ አንድ ቁና። አሻቅቦ ቢተፉ፤ ተመልሶ ባፉ። አሽሟጣጭ ዝናብ፥ ወንዝ ዳር ያካፋል። (አሽሟጣጭ ~ አሽቃባጭ) አሽቶ ቃመው። (:_ጣለው ከመሬት ደባለቀው) አሽከሩን አይዳኝ፤ በገናውን አይቃኝ። አሽከር በአንደበቱ፤ ውሻ በጅራቱ (ይታወቃል)። አሾክሻኪ አነካኪ። አቀማመጥ ያላወቀ፥ ከባልና ሚስት መሀል ይቀመጣል። አቀበት ያደክማል፤ ዕርሻ ያዳግማል። አቀፈ አ዗ለ፥ ለባለቤቱ ያም ይኸም ሸህም ነው። አቃቢ በተልባ በበላች፥ ገበዙን ተጋረፈው። አቃቢ ኮሶ ቢጠጡ፥ ቄሰ_ገበዙን አሻራቸው። አቅለው ብለው፥ ቆለለው። አቅሙን አያውቅ፤ ቶል አይታረቅ። አቅሙን አያውቅ ፎናና፥ ሲሥቁ ይሥቃል። አቋራጭ ነው ብለህ፥ በገደል አትግባ። አበልጄ፥ አትቁም ከደጄ። አበልጅ፥ አትቁም ከደጅ። አበልጄ፥ አትድረስ ከደጄ። አበሻና ጉንዳን፥ ክፋቱ እንጂ ደግነቱ አይወራም። አበበን ጥራ ቢሉት፥ እራሱ መጣ። አበቢላ፥ የመስከረም ጠላ። አበባ፥ እየአገርህ ግባ። አበው ሲያልፉ፤ ውሉድ ሲተርፉ የሚተረጉሙላቸው አጥተው። አበው ጮርቃ በበሉ፤ የውሉድ ጥርስ ጠረሰ። አበድረኝ አይማረኝ፤ ተዋሰኝ ግዝት ነኝ። (ነኝ ~ ይኹነኝ) አቡን ቄስ ናቸው ወይ ቢሉት፥ ተርፏቸው ይናኛሉ አለ። አቡክቶ ሀሳብ። አበጠ ያብጣል ሀብታም ለሰጠ፥ ድሀ ምንጭሩ አበጠ። አበጠ ያብጥ ሀብታም ሉሰጥ፥ የድሀ ቂጥ ያብጥ። አቡጊዳ፥ የተማሪ ዕዳ። አባ ልብሱ ዳባ፤ ውስጡ ደባ። አባ በላሉበት፥ ተዝካር ተበላ። አባ ቢ዗ሉ፥ እስከ ንፍሮ። አባ በጠጡ፥ አቃቢቷን አሻራቸው አሉ። አባ ላዩ ካባ፤ ውስጡ ዳባ። አባ ከበሉ፥ እመን አነሣቸው። አባ በበሉ፥ እማን አገሳቸው። አባ ገምናኔ የለውም ቤትህ፥ ወረን ይላል ለመሸበትህ። አባም ሰው ሆኑና ፋኖ ገደላቸው። አባሪ ተነባባሪ። አባቱ ሲላጨው፤ እናቱም ስታቅፈው። አባቱ ዳኛ፤ ልጁ ቀማኛ። አባቱ ያልበላውን ኑግ፥ ልጁ አማረው ቅባ ኑግ። አባቱን አያውቅ፤ አያቱን ናፈቅ። አባቱ ዳኛ፤ ልጁ ተጫዋች። አባቱን ረስቶ ለአማቱ ይነጭ፤ አማቱን ጋርድ እናቱን ያስፈጭ። አባቱን የጠላ፥ የሰው አባት ይሰድባል። አባቱን ሳይመስል የተወለደ ልጅ፥ ከጎረቤት ያሳማል። አባቱን ያላወቀ፤ አያቱን ናፈቀ። አባቱን ገድል ለአማቹ ይነጭ፤ አማቱን ጋርድ እናቱን ያስፈጭ። አባታቸውን አይጦሩበት፤ ልጃቸውን አይድሩበት። (አለቃ ገብረ ሀና) አባቴ ሲሞት፥ እናቴን የአገባ ዅሉ አባቴ ነው። አባቴ ትንሽ ነው፥ ብልቴ ትልቅ ነው የሚል የለም። አባት ላም ይሰጣል፤ ልጅ አ጑ት ይነሣል። አባት ሲታማ፥ ልጅ አይስማ። አባት ሲያማ ቢሰማ፤ ልጅ ያያል በጠማማ። አባት ሳለ አጊጥ፤ ጀንበር ሳለ ሩጥ። አባት ቀፎ ቢያበጅ፥ ልጅ ማንጉዚ ገዚ። (ማንጉዚ:_ ቀፎ ደፊ) አባት በነውሩ ይከሰሳል፤ ሰማይ በመብረቅ ይታረሳል፤ ውሃ በምንቸት ይጠበሳል። አባት አይከሰስ፤ ሰማይ አይታረስ፤ ውሃ አይጠበስ። አባት እያለ አጎት፤ እናት እያለች አክስት (አይታጡም)። አባት ከነሣው፤ ምግባር ያነሰው። አባት ከአልሞተ፥ ልጅ አዋቂ አይባልም። አባት ከአነሰው፤ ምግባር ያነሰው። አባት ካለ አጊጥ፤ ጀንበር ካለ ሩጥ። አባት የላት፥ አያት አማራት። አባት የላለው ልጅ፤ መዝጊያ የላለው ደጅ። አባት የያ዗ውን ልጅ ይወርሳል፥ እጅ የያ዗ውን አፍ ይጎርሣል። አባት ያርስ፥ ልጅ ግን ያፈርስ። አባት ያቆየው፥ ለልጅ ይበጀው። አባት ያበጀው፥ (ለ)ልጅ ይበጀው። አባት ያጠፋው፥ ልጁን ያለፋው። አባት ጨርቋን በጎረሠ፤ የልጁ ጥርስ አጠረሰ። አባትና ጋሻ፥ ምስክር(ም) አያሻ። አባትና ጋሻ፥ በውጭ ያስታውቃል። አባትና ጋሻ አይሸሸግም። አባቶች፥ ልጆቻችኹን አታስቆጡ። አባቷን አታውቅ፤ አያቷን ናፈቀች። አባያ ቢቀና፥ ቤት ያቀና። አባያ ከሰው፥ ዅሉ ፊት ይተኛል። አባይ ለዕለቱ፤ ደስ ማሰኘቱ። (ማሰኘቱ ~ ያሰኛል) አባይ በቃሉ ያስታውቃል፥ በእጁ ሲበላ ይታነቃል። አባይ፥ ነፍስ አስገዳይ። አባይ ማደሪያ የለው(ም)፥ ግንድ ይዝ ይዝራል። አባይ ማደሪያውን ሳያውቅ፥ ግንድ ተሸክሞ ይዝራል። አባይ ቢሞላ፥ ተሻገር በመላ። አባይ ቢሸፍት ተከዛን በፍልጥ። አባይ አንተ የምታየኝ ከጉልበት፤ እኔ እማይህ በአንገት። አባይ አንተ አየኸኝ ከደረት፤ እኔ(ም) አየኹህ ከጉልበት። አባይ ጠንቋይ ቤት ያስፈታል። (ያስፈታል ~ ያፈርሳል) አባይና ሥንቅ፥ እያደር ይቀላል። አባይን በምን፥ ይረቱ? በሚስቱ በእኅቱ። አባድር፥ ጾም አታሳድር። አባይን በጭልፋ። አባይን ያላየ፥ ምንጭ ያመሰግናል። አባይን ያላየ፥ ምንጭ (አይቶ) ያደንቃል። አባይን ያላየ፥ ምንጭን ያመሰግናል። አባይን ያላየ፥ ቁርጡሜን ያደንቃል። አባይን ያላየ፥ ባይራራ ያደንቃል። አቤት ሲወርደ ማስጠላቱ፥ የረገጡትን ሲጨብጡ። አብ ሲነካ፤ ወልድ ይነካ። አብረህ ብላ ቢሉት፥ ቆሞ አጉርሡኝ አለ። አብረው የበሉ፤ አብረው ይሙቱ። አብረው የተጠመደ፥ አብረው ይፈቱ። አብራ ቅዳ፥ ሲል አደረ። አብራ የተኛችው እያለች፥ በቀዳዳ ያየችው አረገ዗ች። አብሮ መብላት፥ ያናንቃል። አብሮ ማደግ ያሳሥቃል። አብሮ ማደግ፥ ያናንቃል። አብሮ የበላን፥ ቅደስ ዮሀንስ አይሽረውም። አብን ያየ፤ ወልድን አየ። አብሮ የበላን፥ ጳጉሜ አይሽረውም። አብሲት ጥዬ፤ ጎመን ቀቅዬ። አብስል መብላት፥ በእሳት። አብዝቶ ከማረስ፥ ከተቀላቢ(ው) መቀነስ። አብጅር ቀብዥር። አቦ ተረጋጋ፥ ሰው አታ዗ናጋ። አቦን አይጠምቅ፤ ወር አይጸድቅ የለም። አቦን አይጠምቅ፤ ፍልሰታን አይጥድ የለም። አቧራው እንዳይነሣ፤ ጉፋያው አንበሳ እንዳያገሳ በመፍራት። አተላ በሠኔ፥ ለእኔ ለእኔ። አተር መዝራት፤ አቦ ብልኀት። አተር ቢጎድል፥ ሽንብራ ይበረክትልናል። (ይበረክትልናል ~ ይበረክታል) አተርፍ ባይ አጉዳይ፤ (አልሞት ባይ ተጋዳይ)። አታላይ ለጊዛው ያመልጣል፥ በኋላ ይሰምጣል። አታላይ ባለሟል፥ ባቄላ አሽቶ ይበላል። አታላይ እታች፥ ሲሉት እላይ። አታላይ ከላይ ሲሉት፥ ከታች ይላል። አታላይ ከታች፥ ሲሉት ከላይ። አታላይ ወደ ታች ሲሉት፥ ወደ ላይ። አታላይ፥ ጉድባ ዗ላይ። (ጉድባ ~ ጉድ጑ድ) አታላይን ማታለል አጠፊታ ያለው ደስታ ነው። አታማርጭው፥ አንደን አምጭው። አታምጣው ሲለው፥ ቆለለው አሉ። አታስለምዳቸው አትከልክላቸው። አታርፍ አትሠራ፤ አትጾም አትበላ። አታበድር እንዳትቸገር። አታበድር፥ ከአበደርክም አታስቸግር። አታንቀላፋ ነቅተህ ተኛ፥ ይህ ዅሉ መንገደኛ። አታውላውል፥ እንዳትቀር ከመሀል። አታይን ማታለል አጠፊታ ያለው ደስታ ነው። አታግባና ስት዗ል ኑር። አታግባና የሰው አጥር ዝለል። አትመላለስ ትሰለቻለህ፤ አትጥፋ ትረሳለህ። አትማታ በበትር፥ ተከራከር ባጤ ሥር። አትስረቁ ትላለህ፥ አንተ ግን ት዗ርፋለህ። አትረፊ ያላት ወፍ፥ በጥቅምት ትሞታለች። አትረፍ ያለው መነኰሴ፥ መቁጠሪያውን ሸጦ፥ ፍየል ይገዚል። አትረፍ ያለው በሬ፥ ቆዳው ከበሮ ይሆናል። አትሩጥ አንጋጥ። አትቁም ያሉት ለማኝ፥ ከሰጡት አንድ ነው። አትቁም ያሉት ለማኝ፥ የሰጡት እኩል ነው። አትበደር ባለህ ዕደር። አትብዪ ያላት ወፍ፥ በጥቅምት አይኗ ይጠፋል። አትትረፊ ያላት ወፍ፥ በጥቅምት ትሞታለች። አትናገረው፥ ምሰህ ቅበረው። አትንገር ብየ ብነግረው፥ እንዳትነግር ብል ነገረው። አትኩራ ገብስ፤ ጎመን ባቆየው ነፍስ። (ባቆየው ~ ባወጣው) አትክልት በውሃ ይለመልማል፥ እህል ከፈጩት ይልማል። አትዋልባቸው ይዋሉብህ፤ አትምከርባቸው ይምከሩብህ። አትግደርደሪ፥ ጦምሽን እንዳታድሪ። አትጥላኝ በወሬ፥ ሳታጣራ ነገሬ። አትፍራ ጋብ዗ኝ፤ አትናገር ሸኘኝ። አነር ጉድባ መዝለል ስላቃተው፥ ከእናቱ ከነብር ተለየ። አነሰ ሲሉት፥ ተቀነሰ። (ተቀነሰ ~ ተቆረሰ) አነሰ ስትዪ ሽሮ ስትጨምሪ፥ ወፈረ ስትዪ ውሃ ስትጨምሪ፥ ሞላ ገነፈለ ወዳት ታማስዪ። አነክስ ብዬ በቅል ገዚኹ፥ አይኔ ጠፋ ብዬ መሪ አበጀኹ፥ ያላሰብኹት ጆሮዬ ደነቆረ። አነጋገሩ ባሕታዊ፥ አወሳሰደ እንደነአባይ። አነጋገራችን፥ እንደ ጠባያችን። አነጋገር ቢያምር፥ አሟሟት ይከፋል። አነጋገር አያውቅ፥ ምርቃት ያበዚል። አናውቅም፥ አስገድል አያውቅም። አንቃ፥ ለራሱ አይበቃ። አንቃ ለአንቃ ቢደጋገፍ፥ ተያይዝ ዗ፍ። አንበሳ ለአንበሳ፥ ቢያገሳ ሞቱ ለኮሳሳ። አንበሳ ምን ይበላል? ተበድሮ ምን ይከፍላል? ማን ተናግሮ? አንበሳ ሰባሪ፤ አሞራ በራሪ። አንበሳ ሲያረጅ ኮሳሳ፤ ምሥጢር ሲያረጅ አፈሳ። አንበሳ ሲያረጅ፥ የዝንብ መጫወቻ ይሆናል። (የዝንብ ~ የጅብ) አንበሳ ሳይገድሉ፥ ቆዳውን ያስማማሉ። አንበሳ ቢለምድ ድመት፤ ድመት ቢያመር አንበሳ። አንበሳ የሰበረው፥ ለጅብ ይተርፋል። አንበሳ የሰበረው፥ ንጉሥ የገደለው አንድ ነው። አንበጣና ፌንጣ፤ ሰንጠረዥና ገበታ። አንተ ለእኔ፥ እኔ ለአንተ። አንተ ሰው፥ ና ግንቡን ጣሰው። አንተ ቀውላላ፤ መኖህ ባቄላ። አንተ አስበሀል፥ ሥላሴ ያውቁልሀል። አንተ አብጀው፥ አስቤም አልፈጀው። አንተ አብጀው፥ ጌትዬ አንተ አብጀው፥ እኔማ አስቤም አልፈጀው። አንተ ውለታ ቆጣሪ ቢለው፥ አንተ(ውለታ) አስቆጣሪ አለው። አንተ ግፋኝ እሥጋ ላይ፥ እኔም እውድቃለኹ ከላይ። አንተ ግፋኝ ከላይ፥ እኔ እወድቃለኹ ከሥጋ ላይ። አንተ ግፋኝና፥ እኔ ሥጋ ላይ እወድቃለኹ። አንተም ላባ፥ እኔም ላባ፥ ምን ያጣላናል? በሰው ገለባ። አንተም አራዳ፥ እኔም አራዳ፥ ምን ያጣላናል? በሰው በረንዳ። አንተን ብዬ መጣኹ፥ አንተን አጣኹ። አንተን ያመነ፥ ዅሉ ዳነ። አንተን ያመነ፤ ጉም የ዗ገነ። አንተንም መሬት ይበላሀላ፥ እንደ ሞኝ ሰው፥ እንደ ተላላ። አንቱ ትራገሙ፤ አንቱ ትደረግሙ። አንቱ ትተረጉሙ፤ አንቱ ትደረግሙ። አንቱም አንቱም አትዋሹ፤ ወደ ጑ሮ ልትሸሹ። አንቱው ትተረጉሙ፤ አንቱው ትደረግሙ። አንቺ ምን ቸገረሽ? ኹለት አባት አለሽ፥ አንደ ቢሞትብሽ ባንደ ትምያለሽ። አንቺ ምን አለብሽ? ኹለት ባል አለሽ፥ አንደ ቢሞትብሽ ባንደ ትምያለሽ። አንቺ ስትጎተቺ፥ አህያ ቀንድ ታወጣለች። አንቺ ክምር አለኹ ብለሻል፥ ተበልተሽ አልቀሻል። አንቺማ ታቦኪያለሽ፥ ውሻ ይደፋብሻል። አንቺም ማመን፤ ጉም መዝገን። አንቺን ቢጠሉሽ፥ አጥመዝም዗ው ጣሉሽ አለቻት ትኋን ለቁንጫ። አንቺን ጣመሽ እንጂ፥ እኛንስ አስረጀን። አንቺው ሲሳይ፥ የተጫንሽው ሲሳይ አለ ጅብ። አንቺው ታመጪው፥ አንቺው ታሮጪው። አንችም አበዚሽው፥ ዕርጎውን በቅቤ ፈትፍተሽ በላሽው። አንችው ታመጭው፥ አንችው ታሮጭው። አንካሳ በልቡ፥ ኢየሩሳላም አሳቡ። አንካሳ በእውሩ እግር ኼደ። አንካሳ ያለው ደብር፥ አዝ ያለው ባሕር ሳይበጠበጥም አያድር። አንካሳን ማገም፥ ድንጋይ መቆርጠም። አንደ ሉበላ፥ አንደ ያገበግባል። (ያገበግባል ~ ያጎበጉባል) አንደ ልብ፤ መካሪ አንደ ቃል ተናጋሪ። አንደ መውጫ፥ ለማምለጫ። አንደ ሲሻር፥ አንደ ይሾማል። አንደ ሥራት፥ ያሉትን መስማት። አንደ በአንደ ሲሥቅ፤ ጀንበር ጥልቅ። አንደ ሲናገር ያፈዝ፥ አንደ ሲናገር ያደነዝዝ። (ያደነዝዝ ~ ያደንግዝ) አንደ ሲያልፍ፤ አንደ ሲተርፍ። አንደ ታቦት፤ አንደ ጣዖት (ሆነው ኖሩ)። አንደን ለእሾህ፥ አንደንም በእሾህ። አንደን ሳይ዗ው፤ ደረሰ ጊዛው። አንደበቱ ሰውን ከመበደል፥ እጁ ሰውን ከመግደል። አንደበቱ ከጸልት፤ እጁ ከምጽዋት (ያልተለየ)። አንደን ጥላ፤ አንደን አንጠልጥላ። አንደን ጥል፤ አንደን አንጠልጥል። አንደኛው ልብ አብርድ፥ ኹለተኛው ልብ አንድድ፥ ሦስተኛው ነገር ቀስቅስ፥ አራተኛው ጎራዳ ም዗ዝ። አንደኛውን ሲሰሙት፤ ያፈዚል ላላው ያደነግዚል። አንዱት ሴት ከመጠበቅ፥ አንድ ጆንያ ቁንጫ መጠበቅ ይሻላል። አንዳንድ ጊዛ ከሞኝና ከእብድ ነገር ይገኛል። አንዳ ያበደረ፥ ኹላ ተከበረ። አንድ ኹለት ተባባሉ። አንዳንድ ጊዛም፥ በዋልድባ ይ዗ፈናል። (ጊዛም ~ ቀን) አንዳ ላባ ካሉት፥ ቢቆርብም አያምኑት። አንድ ለ዗ጠኝ፥ እንዱያውም ስጠኝ። አንድ ልብ አንድድ፤ ኹለት ልብ አብርድ። አንድ ልላ፥ ለኹለት ጌታ አይገዚም። አንድ መሀለቅ የላለው፥ የግመል ጭነት አመለጠው። አንድ ማጭድ ወደቀ። አንድ ምስክር አያስደነግጥ፤ አንድ አይን አያስረግጥ። አንድ ሠኔ የተከለው፥ ከዓመት አተረፈው። (ከዓመት አተረፈው ~ ከዓመት ዓመት አተረፈው) አንድ ሠኔ የገደለውን፥ ሦስት ሠኔ አያድነውም። (አያድነውም ~ አያነሣውም) አንድ ሠኔ የጣለውን፤ አምስት ሠኔ አያድነውም። አንድ ሲሻር፥ አንድ ይሾማል። አንድ ሲናገር ዅሉ ይሰማል፤ ዅሉ ቢናገር ማን ይሰማል? አንድ ሳይሉ፥ ኹለት አይሉ። አንድ ቀን ስትሰርቅ ካዩዋት፥ ብትቆርብም አያምኗት። አንድ ቀን በሳቱ፥ ዓመት ይጸጸቱ። (በሳቱ ~ ቢስቱ ~ ቢሳሳቱ) አንድ ቀን ቢሳሳቱ፥ ዗ላለም ይጸጸቱ። አንድ ቅማል ሱሪ ያስፈታል። (ያስፈታል ~ ታስፈታለች) አንድ በሬ ስቦ፤ አንድ ሰው አስቦ። (አስቦ ~ አሳቦ) አንድ በቀል፤ አብሮ በቀል። አንድ ቢናገር ዅሉ ይሰማል፤ ዅሉ ቢናገር ማን ይሰማል። አንድ ባይሞት፥ ሺ አይጎለት። አንድ ትኋን ገድዬ፥ ጣቴ ገማ ብደግምም ገማ። አንድ አረግ ቢስቡ፥ ደር ይሰበስቡ። አንድ አይነድ፤ አንድ አይፈርድ። አንድ አይና ሰው፥ በአፈር አይጫወትም። አንድ አይና በግ ኼደች፥ በአንድ አይኗ እንቅልፏን ትፈጃለች በአንድ አይኗ አንድ አይና፥ በዕንጨት አይጫወትም። አንድ አይናና አንድ አይና ተጋብተው ኹለት አይና ወለደ፥ አንደን ከእናቱ አንደን ከአባቱ። አንድ አይፈርድ፤ አንድ አይነድ፤ (አንድ አይቀድ)። አንድ እንጀራ በእኔ ምነው ትኮራለህ? በጌቶቹማ ፊት ትነባበራለህ። አንድ እንጀራ ቢጠፋት፥ ቁና ጤፍ ይዚ እጠንቋይ ጋ ኼደች። አንድ እንጀራ የጣለው፤ አምስት እንጀራ አያነሣውም። አንድ እጅ እድፍ አያወጣም። አንድ እግረኛ ያወራውን፤ አንድ ፈረሰኛ አይመልሰውም። አንድ እግር ያለው፥ በከና አይማታም። አንድ ከደግ ተወለድ፤ አንድ ከደግ ተጠጋ። አንድ ወሬኛ አገር ይፈታል፤ አንድ ቅማል ሱሪ ያስፈታል። አንድ ወር የማይጸድቅ፣ ኋላ የማይደርቅ የለ። አንድ ወናፍ፤ ኹለት አፍ። አንድ ወንድ ለ዗ጠኝ፥ ያውም እግዛር ሰጠኝ። አንድ ወይፈን የቀላቀለ፥ ከብቶቻችን ይላል። አንድ ዓመት ሰርተት፤ አንድ ዓመት ሸርተት። (ሸርተት ~ ከርተት) አንድ ዓመት በወዝ፤ አንድ ዓመት በደመወዝ። አንድ ዓመት በደመወዝ፤ አንድ ዓመት በወዝ። አንድ ዓመት እንዳይማሩ፥ ሰባት ዓመት ያፍሩ። አንድ ዓመት እንዳይማሩ፥ ዕድሜ ልክ ይደነቁሩ። አንድ ዓመት ወር፥ ድንጋይ ጠጠር (አይሆንም)። አንድ ዓይን ያለው፥ በአፈር አይጫወትም። አንድ የላት፥ እንቅልፍ የላት። አንድ ያላት፥ እንቅልፍ የላት። አንድ ይበርድ፤ አንድ ይነድ። አንድ ግንድ፥ ለሺሕ አይከብድም። አንድ ጣት፥ ቁንጫ አይገድልም። አንድ ጣት፥ በቆማጣ ቤት ብርቅ ናት። አንድ ጥርስ ያላት፥ በ዗ነ዗ና ልትነቀስ አማራት። አንድ ፋሲል ነበረ፤ እሱም ተመተረ። አንድ ዗መን አለ የተልወሰወሰ፥ ወይ ጠርቶ አላረፈ ወይ አልደፈረሰ። አንድ የላላት፤ ኹለት አማራት። አንድም ምረጥ፤ አንድም ቁረጥ። አንድም ሣር፥ አንድም አሣር (ይጠብቀዋል)። (ስደተኛው ዗ላን በኼደበት ዅሉ) አንድም ሆነ ሺ ጊዛ ቢንጡት፥ የቁልቋል ወተት ቅቤ አይወጣውም። አንድም ለንግሥ፤ አንድም ለኪስ። አንድም ገዳይ፤ አንድም ሰናይ። አንድነት ኀይል ይሰጣል፥ ነጻነት ዕውቀት ያሰፋል። (ያሰፋል ~ ይሰጣል) አንድነት ያለው፥ ጠላቱን ያሸንፋል። አንድነት፥ ያገባል ገነት። አንጀት ዳብሣ የማታበላ ሴት፥ በክረምት የሚያፈስ ቤት፥ ሴቷንም መፍታት፥ ቤቱንም ለእሳት። አንገት ለምን ተሠራ? ዝሮ ለማየት። አንገት ለምን ተፈጠረ? አዙሮ ለማየት። አንገት ሳይጠና፥ ጉተና። አንገት የት ትቀናለህ ቢሉት፥ በራስ አገር አለ። አንገት ደፊ፤ አገር አጥፊ። አንገቷን ደግፈው ቢያ዗ፍኗት፥ ያለች መሰላት። አንጋጣጭ ደላ ዋጭ። አንጣሪያ ላንጣሪያ ቢደጋገፍ፥ ተያይዝ እ዗ፍ። (እ዗ፍ ~ ዗ፍ) አኝከህ አኝከህ፥ ወደ ዗መድህ ዋጥ። አእምሮ ባልገመተው፥ ልቡና ባልጠበቀው። አከራክሬ እውላለኹ፤ አ዗ራዝሬ አሳድራለኹ። አከፋፈል ለዕለት፤ አሰባሰብ ለጥንት። (አሰባሰብ ~ አሳሳብ) አካኼደ እባበኛ፤ አኮራኮሩ ድንገተኛ። አካልና አምሳል። አካልና ከብት፤ ሚስትና ቁርበት። አክ ቢሉም ደም፥ ቢተፉም ደም። አካኼደን አይተህ፥ ጭብጦውን ቀማው። (አይተህ ~ አይቶ) አካል የወለደው፤ ዗መድ የወደደው። አክ እንትፍ አክ እንትፍ ምኑን በላኹት? አያበቅለው የለ ሠኔና ግንቦት። አክንባልና ዕዳ፥ ተሸራርፎ ያልቃል። አኹን ሉደርቅ ውሃ፥ አደረገኝ ድሀ። አዅን እዩኝ እዩኝ፥ ኋላ ደብቁኝ ደብቁኝ። አኹን ወጣች ጀንበር፤ ተሸሸገ የነበር። (ተሸሸገ ~ ጨረቃ) አዅን የሚያልፍ ውሃ፥ አደረገኝ ድሀ። አኹን ዱዝዱዝ፥ አኹን ብዝብዝ። አሃደ ሳቡሬ፤ አጠገበኝ ወሬ። አወላለድ ያለው፥ አከፋፈል አይቸግረው። አወቅኹሽ ናቅኹሽ። አወቅሽ አወቅሽ ቢሎት፥ መጽሀፍ አጠበች። አወቅሽ አወቅሽ ቢሎት፥ መጽሀፍ አጥባ ቆየች። አወቅሽ አወቅሽ ቢሎት፥ የባሎን መጽሀፍ አጠበች። አወን ባይ፤ ዕዳ ከፋይ። አወይ ልጅ፤ በማን እጅ? አለች ቆማጣ። አወይ ብልኀት፤ ለንጉሥ መገዚት። አወይ የእኔ ኑሮ፥ እንዱያው ተለባብሶ መስቀል ተሰላጢን፥ ኀ዗ንና ለቅሶ። አወድማ ሙሉ እብቅ፥ ቢያበጥሩት ልብ ውልቅ። አዋቂ ሲበዚ፥ በሽተኛ ይሞታል። (በሽተኛ ~ አስታራቂ) አዋቂ አስታራቂ። አዋቂ ከጠመመ፥ ይሰበራል እንጂ፥ አይቃናም። አዋቂ ይርዳኝ፤ ሸንጎ ይፍረደኝ። አዋጁን በጆሮ። አዋጅ በአዋጅ፤ የደበል ቅዳጅ። አዋጅ ቢነግሩ፥ ልዩ ነው ምክሩ። (ቢነግሩ ~ ቢያስነግሩ) አውልቢኝን መብላት፥ በብልኀት። (አውልቢኝ:_የማሽላ አይነት) አውራ ለአውራ ቢጋፋ፥ ሞቱ ለጎፋፋ። አውራ የላለው ንብ፥ አለቃ የላለው ሕዝብ። አውራ ድሮን አውራ መንገድ ላይ መኪና ገጨው። አውሬ ከዋሻ፤ በሬ ከዕርሻ። አውሬ ከዋሻው፤ ገበሬ ከዕርሻው። አውቀሽ ከተደፋሽ፥ ቢረግጡሽ አይክፋሽ። አውቀሽ ከተደፋሽ፥ ቶል ተነሽ። አውቀው በድፍረት፤ ሳያውቁ በስሕተት። አውቃለኹ ሳትል፥ ያውቃልን ጠብቅ። አውቆ መተው፥ ለእግዛር ይመቸው። አውቆ መተው፤ ነገሬን ከተተው። አውቆ የሚያጠፋ፥ ኑሮው ምን ይከፋ? አውቆ የተሸሸገ፥ ቢጠሩት አቤት አይልም። አውቆ የተሸሸገ፥ ቢጠሩት አይሰማም። አውቆ የተኛን፥ ቢቀሰቅሱት አይሰማም። አውቆ የተኛን፥ ቢጠሩ አይሰማም። (ቢጠሩ ~ ቢጠሩት) አውድማ ላመለጥ፤ ምስክር ላበለጥ። አውድማ እንደ ነፋስ፤ አገር እንደ ንጉሥ። አውጣን አውርደን (ነው)። አዎን ማለት መረታት፤ አለመመከት መመታት። አዎን ባይ ዕዳ ከፋይ፤ አሉ ባይ ሞት ተቀባይ። አዎን ብለህ ተሟገት፤ ከተጠገበ ሸምት። (ከተጠገበ ~ ከጠገበ ~ ከጠገበበት) አዎን ብል የተረታ፤ መሀል አገዳውን የተመታ። አዎን ብል የተረታ ባላጋራ፤ ከሥሩ እንደተነቀለ ወይራ። አዎን ያለ አያሟግቱ፥ እሺ ያለን አይመቱ አይሟገቱ። አዎን ያለች ምላስ፥ እናት የላላት አራስ። አዚውንት ዳዊት ሲደግም እንጂ፥ ሲያስፈራራ ተሰምቶም አያውቅ። አዚዩን ነካሽ። አዝ ያለው ባሕር፥ አንካሳ ያለው ደብር፥ ሳይበጠበጥ ውል አያድር። አየኹ ያለ ጣጣ ያመጣል፤ አላየኹም ያለ ከጣጣ ያመልጣል። አዝመራ በቁንጥጫ፤ ሰማይ በጡጫ። አዝመራ ካልተከተተ፤ መነኰሴ ከአልሞተ። አዝኜ በአሳድረው፥ ሰርቆኝ ኼደ። አዝኜ ባቅፋት፥ እንቅልፍ ወሰዳት። አዝ ሲውጥ ያለቅሳል። አየኹህ ~ ያየኹህ አያ ተዋሰኝ፥ ስትኼድ አሳንሰኝ። አያ ጅቦ፥ ሳታመካኝ ብላኝ። አያ ጅቦ፥ እን኱ን ድ጑ በልተህ? ድሮም ጯኺ ነህ!። አያልቅበት፥ ምን አለበት? አለ ቅማል፥ አለ ድህነት። አያስብ ቀበኛ፥ ተንኮለኛ። አያምርም) አያስብ፥ ወጥ ይሥራ። አያስገባ ኮሶ፥ የታባቱ ደርሶ። (የታባቱ ~ የት) አያርም አራሽ፥ አያጥብ ለባሽ፥ አይረታ ከሳሽ። አያርስ አይነግድ፤ አይተች አይፈርድ። አያበቅለው የለ ሠኔና ግንቦት፥ አክ እንትፍ አክ እንትፍ፥ ምኑን በላኹት? አያወዚው ተቀብቶ ይሆንብሀል። አያውቅ ቢዳኝ፥ ከቤቱ ይናኝ። አያውቅ እንደኛ፤ የበግ እረኛ። አያ዗ልቅ ጸልት፥ ለቅስፈት። አያያዙን አይቶ፥ ገን዗ብ አበደረው። አያያዙን አይቶ፥ ጭብጦውን ቀማው። አያድሩበት ቤት፥ አያምሻሹ(በት)። አያድሩበት ከተማ፥ አያምሻሹበት። አያድርስ፥ የባል ቢስ። አያድርስ የባል ቢስ፥ አያቅፍ አያንተርስ። አያድን አግሬ፥ ጎድን ያሰብራል። (ያሰብራል ~ ያሰብር) አያድን ጋሻ፥ ቂጥ ያስወጋ። አያገቡት ገብቶ፤ ችግርን ጎትቶ። አያገባት ገብታ፤ አያወዚት ተቀብታ። አያገባው ገብቶ፤ አያወዚው ተቀብቶ። አያጥብ ለባሽ፤ አይረታ ከሳሽ። አያጥብ ለባሽ፤ አይረታ ከሳሽ፤ አያርም አራሽ። አዬ ላላ፤ ወዬ ላላ። አዬ ጉና፥ ትመስላለች መና። አዬ ጉዳን አታበላሽ፥ ለባሰ ቀን ይሆናል። አዬ ጉዳ፥ ባላ ሰው ገደለ በጎራዳ። አዬና ወዬ፥ ምን አገናኘው?( ወዬ ~ ወዬን) አይ ልጅነት፥ አይ ሞኝነት። አይ ሰው? ሞት አነሰው አለች ዝንጀሮ። አይ ነድ፥ የሰው ሚስት ወድ። አይመረው አይተኩሰው፤ ውጦ ውጦ ጨረሰው። አይመጣምን ትተሽ፥ ይመጣል ባሰብሽ። አይመጣምን ትተሽ፥ ይመጣልን በያዝሽ። (በያዝሽ ~ ያዥ) አይሞቀው አይበርደው። አይሰጥ አዚኝ፥ ከነፍሰ ገዳይ አንድ ነው። አይሱዙ፥ ተበድረው ይግዙ፥ ተኝተው ይ዗ዙ። አይረቢትን አረቧት። አይቅርብኝ ያለ፤ እመንገድ ቀረ። አይበሉት እህል፥ ከአፈር አንድ ነው። አይበላ የለ፤ አይጠጣ የለ። አይበላ ዳኛ፥ በሙግት ይመረር። (በሙግት ~ በእግት) አይቡ ዳኛ፤ ቅቤው መልከኛ። አይቡን ሲያዩ፥ አ጑ቱን ጨለጡ። አይቡን ሲያዩት፥ አ጑ቱን ጨለጡት። አይብ ሲያድር፥ አጥንት ይሆናል። አይብ ከአ጑ቱ፤ ልጅ ከእናቱ። አይብ የጠላ፥ ጎመን ይበላ። (ይበላ ~ የበላ) አይቦ የሚባል በሬ:_ ጭራው ምድር አበስ፥ ቀንደ ሰማይ ጠቀስ። አይተህ ቁረስ፥ ከጥርስህ እንዱደርስ። አይተህ ተቀጣ፥ በጉድህ እንዳትወጣ። (አለ ላባ) አይተፋሽ ማር ነሽ፥ አይውጡሽ ምርቅ ነሽ። አይታ የማታውቀው(ን) የሰው ጃኖ ለብሳ፥ ተመለሺ ቢሎት ወዳት ተመልሳ። አይታይም ሲወረወር ሲመታ እንጂ፥ የአንተ በትር። አይታፈሩበት ቤት፥ ገላጋይ አይሆንም። (አይኹኑ ~ አይሆኑም) አይቴ ቁርጠቴ፥ ደፋ በይ ከፊቴ። አይቶ አያቅ፥ ዳቦ ፍሪዳው። አይቶ አጣ ቤት፥ ጎመን የተቀቀለ፥ ሲያጨበጭብ ሲጨፍር ያድራል። አይቶ አጣ ቤት፥ ጎመን የተቀቀለ ዕለት፥ ሲጨበጨብ ያድራል። አይቶ አጣ፤ ጠምድ ፈታ። አይችሉት ድንጋይ ቢሸከሙት፥ ከፍ ብል ደረት ይመታል፥ ዝቅ ብል እግር ይቆርጣል። አይችል ቢዳኝ፥ ከቤቱ ይናኝ። አይችል ዳኛ፥ በቤቱ ይናኝ። አይነ ስውር ቤት፥ ፊልም መሥራት ተጀመረ። አይነ አፋር ልጃገረድ፥ ከወንድሟ ታረግዚለች። አይነ ደረቅ ላባ፥ ከነቃጭሉ ይገባ። አይነ ደረቅ፥ መልሶ ልብ ያደርቅ። አይነት አይነቱን ለነፍሴ፥ ግርድ ግርደን ለፈረሴ። አይነኩን ቢነኩ፥ ያድሯል ሲታወኩ። አይነጋ መስሎት፤ ቁርሷን ማታ በላች። አይነጋ መስሎት፥ በቋት አራች። (በቋት ~ እቋት) አይነጋማ መስሎት፥ ደጋገመች በቋት። አይነጋም ብላ፥ በቋት አራች። አይኔ ነው? ባላ ነው? አለች ሴትየዋ። አይኔ እያየ፤ ጆሮዬ እየሰማ፤ የተባለውን እምቢ ብለሽ፤ የጸጸት ለቅሶ ታለቅሻለሽ። አይኔን ሲያመው፥ ጥርሴን አሣቀው። አይኔን ሲያመው፥ ጥርሴን አታስቆጣው። አይኔን አታሥቀው፤ ጥርሴስ ልማደ ነው። አይኔን ጨፍኜ፤ ጆሮዬን ደፍኜ። አይን ሕመም ክሱት ነው፤ የሆድ ሕመም ስውር ነው። አይን ሲያይ ብረቱ፤ ጆሮ ሲሰማ መስኮቱ። አይን አይቶ፥ ልብ ይፈርዳል። አይን አይቶ፤ ልብ ደም ይረጫል። አይን አይፈስ፤ ዕርቅ አይፈርስ። አይን አፋር ልጃገረድ፥ ከወንድሟ ታረግዚለች። አይን አፋር ልጃገረድ፥ ከወንድሟ ትወልድ። አይን አፋሮች የበዙበት፥ ቀባሪዎች የናኙበት ሀቅ። አይን እና አሞራ፥ ማረፊያ ይወዳል። አይን ከማየት፥ ጆሮ ከመስማት አይጠግቡም። አይን ከአላዩበት፥ ግንባር ነው። አይን ኹል ጊዛ ከምታለቅስ፥ አንድ ቀን ብቻ ታልቅስ። አይን ሕመም፥ ልግም ይወዳል። አይን ግጥጥ፤ ጥርስ ፍጥጥ። አይን ፈሪ ቄስና ዕውር አህያ አንድ ናቸው። አይንህና አገርህ አይጠግቡም። አይን፥ ከጥርኝ አፈር በቀር የሚያጠግባት የለም። አይን የማያየው፤ ልብ የማይስተው (እውነት አለ)። አይን ያጣ፤ ጠምድ የፈታ። አይንህን ያምሀል አንተ ገመምተኛ፥ እንዳይቆረቁርህ ተው ተመለስ ተኛ። አይኗን ሲያጠፏት፥ ቅንድቤን አደራ አለች። አይኗን ቢያጠፉት፥ ቅንድቤን አደራ (አለች)። አይወርደው ሸጥ፤ አያቋርጠው ድንበር የለውም። አይወጋ ብላቴና፤ አይ዗ንብ ደመና። አይዋስ ቢዋሰኝ፥ ከባለዳው ባሰኝ። አይዋጥ አይተፋ፤ መላው የጠፋ። አይውጥ ጎራሽ፥ እህል ያበላሽ። አይ዗ልቅ ጸልት፥ ለቅስፈት። አይዝህ (አይዝህ) ማለት፥ ከመውደቅ ያድናል። አይዝህ ካሉት፥ ውሃ አይወስድም። አይዝህ ወንድሜ፤ ተሠራው ጋሜ። አይጠቅም ጠላ፥ ባልና ሚስት ያጣላ። አይጠቅም ጠላ፥ ከጎረቤት ያጣላ። አይጣል ነው እንጂ፥ ከጣለ ምን ይሎል። አይጥ ለሞቷ፥ የድመት አፍንጫ(ን) ማሽተቷ። (ማሽተቷ ~ ታሸታለች) አይጥ ለሞቷ፥ የድመት አፍንጫ ታሸት። አይጥ ሞቷን ስትሻ፥ ኼዳ ታሸታለች የድመት አፍንጫ። አይጥ በበላ፤ ዳዋን በደላ። አይጥ በበላ፤ ዳዋ ተመታ። አይጥ በድመት አፍንጫ ወርድ፥ አህያ ታስሮ ከሰርድ። አይጥ በጉድ጑ደ፤ ሰው በ዗መደ። አይጥ ቢበላ፤ ዳዋ ተመታ። አይጥ ቤት፥ ብቅል። አይጥ ነሽ? እዩት ክንፌን፥ ወፍ ነሽ? እዩት ጥርሴን። አይጥ ወልዳ ወልዳ፥ ከጅራቷ ሲደርስ ሲጥ አለች። አይጥ ወልዳ ወልዳ፥ የድመት ሲሳይ አደረገቻቸው። አይጥ ወልዳ ወልዳ፥ ዱቪ ደረሳቸው። አይጥ ወልዳ ወልዳ፥ ጅራቷ ሲቀር ሲጥ። አይጥ ዝኆን አክል ብላ ፈንድታ ሞተች። አይጥ ጣረ ሞት ይዞት፥ ትጫወታለች ድመት። አይጥም ጠላ፥ ባልና ሚስት ያጣላ። አይጥም ጠላ፥ ከጎረቤት ያጣላ። አይጥና ዝኆን ቢዋደደ፥ አሣ ወለደ። አይጥና ድመት፥ ታገሉ ማናቸው ጣሉ? አይጥና ፍልፈል፤ ሸክላና ገል። አይጥን ከማገር፤ ሰላቢን ከአገር (አጥፋ)። አይጥፍ ደብተራ፤ ክንፍ የለው አሞራ። አይጧ ጣረ ሞት ይዞት፥ ድመቷ ትጫወታለች። አይጽፍ ደብተራ፤ ክንፍ የላለው አሞራ። አይፈስ ውሃ፤ አይሰደድ ድሀ የለም። አዮ ላላ፤ ወዮ ላላ። አደራ ቢሎቸው፥ ይብሳሉ እሳቸው። አደራ ጥብቅ፤ ሰማይ ሩቅ። አደራ፥ ጅብም አይበላ። አደባባይ አይወድም፥ አባይ። (አይወድም ~ አይውል(ም)) አደባባይ ወጥቶ ወሬ የማይጠይቅ፤ በልቶ የማይመርቅ ኹለቱ አንድ ናቸው። አደናግር፥ እንደ ነብር። አደን፥ ያስረሳል ኀ዗ን። አደን጑ሬ ቀቀሉ፥ በሰለና ብሉ። አደን጑ሬ፥ የእህል አውሬ። አዱስ ሚስት፥ የሙገጫ ክዳን ትሰፋለች። አዱስ አበባ ልትኼድ፥ ወደ ጎንደር ተሸኘች። አዱስ ወጠ ሠሪ፥ ዝንጅብል ታበዚለች። አዳም በበደለ፥ መድኀኒ አለም ካሰ። አዳራሹ ተመላሽ፥ ቀበና ድንጋይ ላሽ። አዳኝ ውሻ ጠጉር በአፏ በትር ትርፏ። (ጠጉር ~ ጭገር) አድል አልኩህ እንጂ፥ ጨልጥ አልኩህ። አድላ ወርቅ በየወንዚ ወንዙ፥ እንደ ድመት ግልገል ሹሞቹ ባይበዙ። አጀብ እና ጃል። አድሎዊ ዳኛ፥ አምጡ ይላል የድሮ ሻኛ። አድመው ቢነሡ፥ አፈረሰው እሱ። አድረው ሉለዩ፥ አመል አያሳዩ። (አያሳዩ ~ ያሳዩ) አድረው ሉለያዩ፥ አመልን አያሳዩ። አድሩስ፥ የባሕር ንጉሥ። አድራሽ ተመላሽ፥ ቀበኛ ድንጋይ ላሽ። አድሮ ቃሪያ። አጀብ፥ እየወለደ ማጀብ። አጃ ወቅጦ ቢ዗ሩ፥ ተመልሶ ከ዗ሩ። አጃ ፈልፍለው ቢ዗ሩ፥ ተመልሶ ከ዗ሩ። አገሩ ሩቅ፤ ሥንቁ ደረቅ። አገራችን ቆላ፥ ዕርሻው በደጃችን፥ ያ ቢሾም፥ ያ ቢሻር፥ እኛ ምን ተዳችን። አገሬ ሩቅ፤ ጭብጦዬ ደረቅ። አገሬን ያለ ወገሬን። አገር ላጣ ስሜን፤ ምግብ ላጣ ጎመን። አገር ሲበላሽ፥ ጑ጉንቸር ያፈላል። አገር ሲያከር፥ ለንጉሥ ያስቸግር። አገር ሲጠፋ፥ ጃርት ያፈራል። አገር ቀሚስ ናት። አገር በጤና፤ ለማኝ በጭራ። አገር ቢያብር፥ ለንጉሥ ያስቸግር። (ለንጉሥ ~ ንጉሥ) አገር ቢጠላህ፥ አልፈህ አልፈህ ታረቅ። አገር አላት ይበሉኝ፥ ማህደረ ማርያም ቅበሩኝ። አገር የላለው፥ ለጌታ አዳሪ፤ ማጭድ የላለው፥ መስክ ሰፋሪ። አገር የጋራ ነው፤ ሃይማኖት የግል ነው። አገር የላለው፥ ለጌታ አዳሪ፤ ማጭድ የላለው፥ ወራሪ። አገር ያለ ምክር፥ ቤት ያለ ማገር። አገር ያደረው፤ ዗ንድ የወደረው። አገር ያጣ መቄት፥ ሥንቅ ያጣ ዗ንጋዳ ደቄት። አገር ጥል፤ ቁርበት ጠቅል። አገር ያጣ ስሜን፤ ምግብ ያጣ ጎመን። አገርህ ወዳት ነው? ማርያም ውሃ፥ እንግዱያው ዗መዳ ነሀ። አገርህ ወዳት ነው? ማርያም ውሃ፥ ዗መዳ ነሀ። አገርህ ወዳት፤ ነገርህ እንዳት። አገባሻለኹ ያለሽ ላያገባሽ፥ ከባልሽ ሆድ አትባባሽ። አገኘ በላ፤ ተናገረ ረሳ። አገኘኹ ብልኀት፥ አርሶ መብላት። አገኝ ባይ፥ ልብ የለህም ወይ። አገዳ ለማያውቅ ሥር፥ ሥጋ ለማያውቅ ሳንባ ይሰጧል። አጉሉንጥ ባልንጀራ፥ እንብላ ሲሉት እንራ። አጉል ልጅ ከመውለድ፥ ነጉላ ልጅ ከመውለድ፥ ይሻላል ማስወረድ ደግሞም ከማስወረድ ይሻላል ሴት መውለድ። አጉል መንጠራራቱ፥ ለመፈንዳቱ። አጉል መንፈራገጥ፥ ለመላላጥ። አጉል መጋባት፥ መጋማት። አጉል ባልንጀራ፥ እንብላ ሲሉት እንራ። አጉል ትውልድ፥ ያባቱን መቃብር ይንድ። (አጉል ~ አ጑ጉል) አጉል ንግግር ያደናግር። አጉል ፈሉጥ:_ ውሻ ወደ ሰርድ፥ አህያ ወደ ሉጥ። አጉል ፌዝ ያመጣል መ዗ዝ። አጉል ፍቅር ያመናቅር። አጉራሹን ነካሽ፥ የበላበትን ወጪት ሰባሪ። አጋም ተደግፎ፥ ይዋጋል እንባጮ። (ተደግፎ ~ ተጠግቶ) አጋምን የተጠጋ ቁልቋል፥ ሲያለቅስ ይኖራል። አጋሮ፥ ላባው በ጑ሮ። አጋሮ፥ ስሙኒ ከ጑ሮ። አጋሰስ በጭነት፤ ወገብ በመቀነት። አጋሰስ ቢያጋድል፤ መደላድሉን በክርን። አጋሰስ ያገባች፤ ዕዳ ገባች። አጋፋሪያችን፥ ዗ርዚራ ወንፊት፥ እብቅ እብቁን ያስገባል በፊት። አግባኝ አግባኝ ብለው፥ ሉሸጠኝ አሰበ። አጋ዗ን ሲጠግብ የነፍጠኛ ጎጆ ይታከካል። አጋጨው፥ እንደ ነጋዳ ጨው። አግኝቶ ከመዋረድ፤ አጥቶ መኩራት። አጎንብሶ በላን፥ ተኝተህ ቀላውጠው። አጎንብሶ የሚበላን፥ ተኝተህ ቀላውጠው። አ጑ቱን ሲያዩት፥ አይቡን ጨለጡት። አጣሪ እንደ ለጋስ፤ ከመንገድ ዳር ትቀመጣለች። አጣቢ ነበርን፤ አለቅላቂ አ዗዗ብን። አጣቢ ነበርኩኝ፥ አለቅላቂ ላከብኝ። አጤ ከሞቱ፥ በማን ይሟገቱ?( በማን ~ በምን) አጤን መደብ፤ እቴጌን ገደብ። (እቴጌን ~ ይተጌን) አጤን ይሻል፥ ቀላጤ። አጤን ይበልጡ ቀላጤ፤ ሙክትን ይሻል ወጠጤ። አጥልቆ የሚያርስ፤ ከብሮ የማይጨርስ። አጥልቆ የማያርስ፤ አጥርቶ የማይጨርስ። አጥልቆ የማያርስ፤ ጀምሮ የማይጨርስ። አጥር ቆስቋሽ፤ ነገርን አመላላሽ አያድርግሽ። አጥር ጥሶ፤ ቅጥር አፍርሶ። አጥር ጥሶ፤ ግርግዳ ምሶ። አጥቃ ያሉት ኮርማ፥ ተንበርክኮ ጠባ። አጥባቂ፥ ደን ጠባቂ። አጥባቂ ፈረስ፥ ከገደል ያደርስ። አጥብቀህ ጉረሥ፥ ወደ ዗መድችህ ተመለስ። አጥብቀህ ጉርሥ፥ ወደ ዗መድችህ ምልስ። አጥብቀህ ጎርሠህ፥ ወደ ዗መድህ ተመለስ። (ተመለስ ~ ዙር) አጥብቆ ያሰረ፥ ዗ቅዝቆ ይሸከማል። አጥብቆ ጠያቂ፥ እናቱን ይረዳል። አጥብቆ ጠያቂ፥ የእናቱን ሞት ይረዳል። አጥንት ከሚግጡ፥ መቅኒን ወደ ሚመጡ። (አጥንት ~ ሥጋን) አጥንት የሚያለመልም ወሬ፥ ሰማኹላችኹ ዚሬ። (የሚያለመልም ~ አጥፊው፥ አልሚ መስል፥ ይታየዋል ለሰው። አጥፍቶ ይርቋል፤ አልምቶ ይሞቋል። አጩለው በለው። አጭር ሰው ለምክር፤ ረጅም ሰው ለጦር። አጭር ባይኮራ፥ ማን ያውቀው ነበር? አጭር ባይኮራ፤ ረጅም ባይፈራ። አጭር ባይኮራ፥ ነፋስ በወሰደው ነበር። አጭር አህያ፥ ኹል ጊዛ ውርንጭላ። አጮላቂ ሰራቂ። አጮላቂ አጭላጊ። አፄ ከሞቱ፥ በማን ይሟገቱ። አፈ ምላጭ፤ በደረቅ ይላጭ። አፈ ቅቤ፤ ልበ ጩቤ። አፈ ቅቤ ልብ ይሰብር፤ አፈ ጩቤ አጥንት ይሰብር። አፈ ድዳ፤ ቀንደ ጎዳ። አፈ ድዳ፤ ግንባረ ጎዳ። አፈረ ፈጭ፤ ዝርዝረ ቀጭ። አፈረች፥ ድብኝት አከለች። አፈር ማሽ፥ በአንድ እጁ አፈር መላሽ። አፈር ብለው አያፈሱህ፤ እህል ብለው አያፍሱህ። አፈር ፈጭ፤ ዝርዝር ቁጭ። አፈርጣለኹ ብል፥ አደማ። (:_ሆነሳ?) አፈኛ በአፉ፤ ኀይለኛ በመዳፉ። አፉ ለምጣም። አፉ ቅቤ፤ ሆደ ጩቤ። አፉ ቅቤ፤ ልቡ ጩቤ። አፉ ከእኛ፤ ልቡ ከእነኛ። አፉ ከእኛ፤ ልቡ ከወሬኛ። አፉ ከእኛው፤ ልቡ ከወሬኛው። አፉን የረቱ፤ እጁን የመቱ። አፉን ጠቅሞ፤ ወርቁን ቅሞ። አፋሽ አጎንባሽ። አፌን አበላኹ፤ አንደበቴን አሰላኹ። አፍ ላላ፤ ልብ ላላ። አፍ ሲናገር፥ ልብ ይንቃል። አፍ ሲናገር፥ አፍንጫ ያሽሟጥጣል። አፍ ሲከዳ፥ ከልላ ይብሳል። አፍ ሲከፈት፥ ጭንቅላት አብሮ ይከፈታል። አፍ ሲከፈት፥ ጭንቅላት ይታያል። አፍ ሲዋሽ፥ ሆድ ይታ዗ባል። አፍ ሲያመልጥ፤ ራስ ሲመለጥ አይታወቅም። አፍ ሲያመልጥ፤ ብዕር ሲያዳልጥ። አፍ ሲያመልጥ፤ ጠጉር ሲመለጥ አይታወቅም። አፍ ሲያርፍ፥ ወዳጁን ያማል። አፍ ሲያብል፥ ልብ ዳኛ ነው። አፍ ሲድጥ ከዕዳ፤ እግር ሲድጥ ከአንጋዳ። አፍ ቀለም ሲነዳ፥ ልብ ዕቃ ያሰናዳ። አፍ ቢሳሳት ዕዳ፤ እግር ቢሳሳት አንጋዳ። አፍ ቢስት ዕዳ፤ እግር ቢስት አንጋዳ። አፍ ነገር፥ አይን አገር አያጣም። አፍ እላፊ፥ ያስከትላል ጥፊ። አፍ እኩል፤ ጉልበት ስንኩል። አፍ ከአልተናገሩበት፥ ዕዳሪ ነው። አፍ ወድቆ አይሰበር። አፍ የለው ዱዳ፤ ቀንድ የለው ጎዳ። አፍ የሚጎርሠውን፥ እጅ ይመጥነዋል። አፍ ያለው ያግባሽ ከብት ያለው ቢሎት፥ አፍ ያለው አለች። (:_ከብት ያለውን አፍ ያለው ይወስድበታል) አፍ ያለው ያግባሽ፥ ከብት ያለው። አፍ ያለው፥ ጤፍ ይቆላል። አፍ ያለው፥ ጤፍ ይቆላል፤ ራሱ ተናግሮ፥ ሰውን ያናግራል። አፍ ያበዚ፤ ጥበቡ ዋዚ። አፍ ዳገት አይፈራም። አፍ፥ ሞትን ይጠራል። አፍ ሲነድ፤ ሆድ ይንደድ። አፍልተው ቢጠጡት፥ ወተት አይፋጅም። አፍም ልብም፥ በአንድነት ይሙት። አፍራ ያለው ማሽላ፥ ተኝቶ ያፈራል። አፍና ቅብቅብ፥ ኹላ አያበላም። አፍና ቅብቅብ፥ ኹል ጊዛ አያበላም። አፍና እጅ አይተጣጣም። አፍና እጅ አይን የላቸው፥ ምነው አለመሳሳታቸው? አፍና ደጃፍ፥ እኩል ይከፈታል። አፍና እጅ፤ እጅና ፍንጅ። አፍና እጅ፤ እግርና ፍንጅ። አፍንጫ ሲመታ፥ አይን ያለቅሳል። (ሲመታ ~ ሲነካ) አፍንጫን ሲመቱት፥ አይን ያለቅሳል። (ሲመቱት ~ ቢመቱት) አፍንጫው የገማ ጎበዝ፥ አፍንጫ የላላት ሴት እስቲያገኝ ይጠብቃል። አፍኣው ሰንሰለት፥ ውስጡ አውደ ነገሥት። አፍህን ዝጋ፥ ደጅህን አይደለም። አፍላ ያለ፤ ወጉ ፈላ። አፍጣኝና አቅጣኝ፥ እመዳሮ(ው) እንገናኝ። (እመዳሮው:_ የድር ስፍራ) ዓይቡን ሲያዩት፤ አ጑ቱን ጠገቡት። አ዗ለም አሟቀለም፥ ያው ተሸከመ ነው። አ዗ለም አቀፈም፥ (ያው) ተሸከመ ነው። አ዗ለም አንጠለጠለም፥ ያው ተሸከመ ነው። አ዗ኑ ላይለቅህ፤ ድግሱ አያምልጥህ። (አያምልጥህ ~ አይራቅህ) አ዗ንሽ ቅጥ አጣ ከቤትሽም አልወጣ፥ የገደለው ባልሽ የሞተው ወንድምሽ። አ዗ንጊ ወጥ፥ ከእንጀራ ይተርፋል። አ዗ዝ አንድም ተናዝ፥ አንድም ሥንቅ(ን) ይዝ። አ዗ዝ፥ ጠላ በሜዝ። (ሜዝ ~ ሳንቲም) አዙሮ ላየው፥ ብላም ነገር ነው። አዚኝ ቅቤ አን጑ች። አ጑ት ጠጥቶ የሰከረ፤ ካሳ በልቶ የከበረ የለም። አጠደ ክፉ፥ ታቦተ ደግ። ኤሉ ሀጂ እኼዳለኹ ብላ፥ እሰገራ ተገኘች። (ሀጂ ~ መካ) ዕለት ቆይቶ፥ ለዓመት። እልልታ ደስታ። እልክ ምላጭ ያስውጣል። እልፍ ሲሉ፥ እልፍ ይገኛል። እልፍ ሲሉ እልፍ ይገኛል፥ ድሀ ሞኝ ነው ሞቱን ይመኛል። እመት ጎርፍነሽ፥ ነገር አያልቅብሽ። እመዬቴ ጎፈጎፍ፥ ወረደች እጉድፍ። እመጫት፥ ሆዶ ቅርጫት። እማን ላይ ቆመሽ፥ እግዛርን ታሚያለሽ። እማኝ ሲገዙ፥ ነገር አያበዙ። እማይችል ቢዳኝ፥ ከቤቱ ይናኝ። እሜቴን ከማዝገም፥ አዝል መሮጥ ይሻል። እምም አለ አያ ጅቦ። እምቅ በቅምጤ፤ ሳይነሣ ቂጤ። እምበላው ሳጣ፥ ልጄ ጥርስ አወጣ። እምተረፈ ልብ፥ ይነበብ አፍ። እምትበላው የላት፥ እምታበራየው አማራት። እምነት እስከ ሞት። እምነት ሲታመም፥ ሺ ወረቀት መፈራረም። እምን ላይ ቆመሽ፥ እግዛር ታሚያለሽ። እምዬ ኢትዮጵያ ሞኝ ነሽ ተላላ፥ የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ። እምዬ ጣጣሽ በዚዬ። እምድር የወደቀ ሥጋ፥ አፈር ሳይዝ አይነሣም። እምጥ ይግባ፥ ስምጥ። እሠራለኹ ብላ ኺዳ፥ ተላጭታ መጣች። እሠራለኹ ብላ፥ ተላጭታ መጣች። እሥሩ ባርፍ ደክሞኝ፥ ዋርካ በፍሬው ፈነከተኝ። እስራኤልና ፀሓይ፥ የማይደርሱበት የለም። እረኛ ቢያኮርፍ፥ ራቱ ምሳው ይሆናል። እረፍታቸው ማመስገናቸው፥ ማመስገናቸው እረፍታቸው ነው። እሩቅ አሳቢ፥ እቅርብ አዳሪ። እሪ በከንቱ፥ ማን ሉሰማ ነው ጩኸቱ(ን)? እሪ በከንቱ፥ ማን ሉሰማው ነው ጩኸቱን? እራሱ ጋባዥ፥ እራሱ ተጋባዥ። እራሱን የማይችል አንገት፥ ባለቤቱን የማያስገባ ቤት። እራሴን መተው፥ እግሬን ቢያሻሹኝ መች ይገባኛል። እራስ ተላጭቶ ወለባ፥ ልባልማ ታጥቆ አዚባ። እራስ ከተመለጠ፤ ነገር ከአመለጠ። እራስን ሳይዙ፥ ወዳጅ አያበዙ። እራሪ ለማራሪ፥ ማራሪ ለበራሪ። እራቁቱን ለተወለደ ልጅ፥ ለምድ አነሰው ወይ። እራቁቱን ለተወለደ ልጅ፥ ጥብቆ መች አነሰው። እራቴ ድሮ፤ እልሄ ሽሮ። እራት ሲበሉ የመጣ እንግዳ፥ እራቱ ፍሪዳ። እራት ሲበሉ የመጣ፥ ይቆጠራል ፍሪዳን እንዳመጣ። እራት ቢንቁ አንድ እጅ ይለቃልቁ፥ ዳኛ ቢንቁ የተያ዗ እህል ይወቁ። እራት የላለው ቄስ፥ እንደ ልቡ አይቀድስ። እራት የላለው ቄስ፥ ከልብ አይቀድስ። እራት የላላት፥ ምሳ አማራት። እራት የላላት ደግሞ፥ ምሳ አማራት። እራት፥ የሰማይ መብራት። እራትና መብራት፤ አማትና ምራት ሳይስማሙ መሬት። እራትና እሳት፤ አማትና ምራት ሳይስማሙ መሬት። እራትን ቢንቁ፥ አንድ እጅ ይለቃለቁ። እራትን ቢንቁ አንድ እጅን ይለቃለቁ፥ ዳኛን ቢንቁ ከመከራ ይወድቁ። እርም ለትሕትና። እርሟን ብታፈላ፥ አንድ ቁና አተላ። እርሟን ብታፈላ፥ ጀበናው ሙሉ አተላ። እርሟን ብታፈላ፥ ጋን ሙሉ አተላ። እርሟን ዚሬ ጠምቃ፥ ፈጀችው ጠልቃ ጠልቃ። እርሟን ጠምቃ፥ ፈጀችው ጠልቃ። እርሱ ራሱ ጊዛ መሆኑን ባያውቀው፥ ጊዛ ጊዛ ይላል ሞኝ ሰው። እርሱ አይወደኝም፤ መከራው አይለቀኝም። እርሱ ካለው ላያልፍ፥ ምነው በሽተኛው ባይለፈልፍ። እርሱ ካለው ላያልፍ፥ በሽተኛው ባይለፈለፍ። እርስ በእርሱ ያልተደጋገፈ ግርግዳ አይቆምም። እርስ በእርሱ፥ ሥጋን በኩበት ጠበሱ። እርስ በእርሱ የተከፋፈለ፥ ቤት አይቆምም። እርሷ ሰንፋ፥ ራቷን ገንፎ አድርጋ ቢያጎርሧት ተኮሳት። እርሷ ወልዳው አልመሰለም፥ እርሷው ጋግራ አልበሰለም። ዕርሻ ለባለ ከብት፤ ርስት ለባለ ርስት። እርሾው ቢያምር፥ ዳቦውም ያምር ነበር። (ያምር ነበር ~ ያምራል) እርቅ ቢፈርስ፥ ከአስታራቂ(ው) ድረስ። እርቅ አይፈርስ፤ አይን አይፈስ። እርቅ አፍራሽ፤ ቤተክርስትያን ተ኱ሽ። እርቅ ከወርቅ፤ ዚላ ከምርቅ። እርቅ የሰው፤ ደም ያደርቅ። እርቅ የፈለገ ንጉሥን ገበሬ ያስታርቀዋል፥ እርቅ ያልፈለገ ገበሬን ንጉሥ አያስታርቀውም። እርቅ፥ ደም ያደርቅ። እርቅና ሥንቅ፥ ከቤትህ ሳለህ ይጠላል። እርቦ ሰፋሪ፤ ስልቻ አሳሪ። እርኩም በልቷል። እርኩም ብትጠቃ፥ ጉጉት ሆነ ጠበቃ። እርኩም፥ ይህን እስክበላ ዕድሜ ስጠኝ ይላል። እርኩም ጉድ ባይ፥ ጦጣ አታላይ። እርካብ ሳይረግጡ ኮር። እርያ በሬ አይደለም። እርጅና ብቻህን ና። እርጅና ብቻህን ና፥ የአንተ ተከታዮች ብዙ ናቸውና። እርጉዝ ላም ያለው ሰው፥ ደረቅም አያንቀው። እርጉዝ ሲያርደ፤ በወዳጅ ይፈርደ፤ ሆድ መርበድበደ። እርጉዝን ያቅፉ፥ ይደግፉ። እርግማን ያነሰው፥ ገበያ ይፈሳል። (ገበያ ~ ገባያ) እርግማንና ምርቃት ከአንድ አፍ ይወጣሉ። እርግዝና ያምርብሻል፥ አትውለጂው። እርጥብ ቅል ክብደቱ እስኪደርቅ ነው። ዕርፍ ይዝ ወደ ኋላ የሚያርስ የለም። እሸት በወረት፤ እህል መውቃት በከብት። እሺ ቢል በምክር፤ እምቢ ቢል በጦር። እሺ ባይ አክባሪ፤ እምቢ ባይ አሳፋሪ። እሺ ከተባለ፥ ምን አለ? እሰር በፍንጅ፥ ጣል በደጅ። እሱ ርጥብ፤ ነገሩ ደረቅ። እሱ ቀርቶ፥ ላላ ዗ፈን መጥቶ። እሱ በእሱ፥ ሥጋ(ን) በኩበት ጠበሱ። እሱ አይወደኝ፤ መከራው አይለቀኝ። እሱ እርጥብ፤ ነገሩ ደረቅ። እሱ የከፈተውን ጐረሮ፥ ሳይ዗ጋው አያድርም። እሱሱሱሱስ አለ ጎማ፥ መነፋቱን ሳያውቀው። እሳት ለብሶ፤ እሳት ጎርሦ። እሳት ለፈጀው፥ ምን ይብጀው? እሳት መጣብህ ቢሉት፥ እሣር ውስጥ ገብቻለኹ አለ። እሳት በላለበት፤ ጢስ አይኖርም። እሳት በገል፤ ውሃ በቅል። እሳት ቢቀርቡት ያሳክካል፤ መነኰሴ ቢቀርቡት ይልካል። እሳት ቢቀርቡት ያሳክካል፥ ባለጠጋ ቢቀርቡት ይልካል። እሳት ቢተኛ፥ ገለባን ሰደደ ገበኛ። እሳት ቢያንቀላፋ፥ ገለባ ጎበኘው። እሳት ቢዳፈን፥ የጠፋ ይመስላል። እሳት ቢዳፈን የጠፋ ይመስላል፤ ሞት ቢ዗ገይ የቀረ ይመስላል። እሳት ቢፈጃት፥ ወደ ልጇ ጣለች። እሳት ተበረበረው፤ ሴት የበረበረው። እሳት አለ ዕንጨት አይለማ፥ ጆሮ ዕዳውን አይሰማ። እሳት አመድ ወለደ እንዱሉ። እሳት አመድ ይወልዳል። እሳት እና ጌታ ብርቁ ነው። እሳት ከበረበረው፤ ሴት የመከረው። እሳት ከበረበረው፤ ሴት የበረበረው። እሳት ከአየው፥ ምን ለየው? እሳት ከጠሉ፥ ከምጣደ ይርቁ። እሳት የላለበት ቤት፥ ጭስ አይወጣውም። እሳት የገባ ቅቤ። እሳት ያለ ዕንጨት አይለማ፥ ጆሮ ዕዳውን አይሰማ። እሳት ጭሮ፥ ከነፋስ ላይ። እሳት፥ ከአልነደደ አያበራም። (አያበራም ~ አይበራም) እሳት ከአባረረው፤ ሴት የመከረው። እሳት፥ ዕንጨት ከአልነሡት አይጠፋም። እሳት ከበላው፤ ወራሪ የ዗ረፈው። እሳትና ነገር፥ ትንሽ ይበቃዋል። እሳትና ነገር፥ ቢያጋንኑት ይጋነናል። እሳትና ነፋስ፥ ማርና መላስ። እሳትና ውሃ አቀረብኩልህ፥ እጅህን ወደምትሻው ስደድ። እሳትና ድሀ፥ ሲነካኩት አይወድም። እሳትና ጌታ፥ ብርቁ ነው። እሳትና ጥል የቀረበውን ያቃጥል። እሳትና ጭድ ናቸው። እሳትን ምን ብትወደው፥ ከጉያ አይሸጎጥ፥ ወይ ጣራ አታወጣው። እሳትን በጭኑ፥ ማን ይሸከማል። እሳትን ወይ አንድድ ይሞቋል፤ ወይ አጥፍቶ ይርቋል። እሳትን የሚያውቀው፥ ያቃጠለው። እስቲ ይኹና፥ እናያለን፥ አለች ዕውር። እስኪያልፍ ያለፋል። እስክትመጣ፥ አህያ ቀንድ ታበቅላለች። እሷ ሰንፋ፥ ራቷን ገንፎ አድርጋ ቢያጎርሧት፥ ተኮሳት። እሷ ሳትነሣ ፥ ልታቋቁም ኼደች። እሷ በፈሳችው፥ በእኔ አላከከችው። እሷ ነፍጋ፥ ራቷን ገንፎ አድርጋ ቢያጎርሧት፥ ተኮሳት። እሷ ክርስትና ሳትነሣ፥ ልታቋቁም ኼደች። እሷ ኼዳ አንጀት ጉበት የነሧት፥ እቤቷ ኼዳ ታናሽ ታላቅ ስደደ ብላ ላከች። እሷ ሠርታ፥ እሷው ታፈርሰዋለች። እሷ ወልዳ አልመሰለም፤ እሷ ጋግራ አልበሰለም። እሷ ጣፋጭ፤ ልጅቷ ቆንጣጭ። እሷን ቢያቃጥላት፥ ከልጇ ላይ ጣለች። እሷው ሞታ፥ እሷው መርድ ጠርታ። እረባዳ ቤቱ፤ ገራም ሚስቱ። እሺ፥ ይበልጣል ከሺ። እሺና ገለባ አይከብድም። እሻ እሻ፥ ልጅ አያሳድግም። እሽ አትበሉኝ፥ የሹም ድሮ ነኝ። እሽት አድርገህ ቅዳው፥ እንዳይጎሽ ጠላው። እሾህ ለረጋጩ፤ ነገር ላምጪው። እሾህ ለአጣሪው፤ ሥራ ለሠሪው። እሾህ በእሾህ ይወጣል፤ ሰው በሰው ይመጣል። እሾህ በእሾህ ይነቀላል፤ ገን዗ብ በገን዗ብ ይመለሳል። እሾህ አጣሪውን፤ ነገር ፈጣሪውን (ይጎዳል)። እሾህ ያለው አሣ፥ ልዋጥህ ቢሉት እሺ አይልም። እሾህን ሳያስወግደ፥ እንደ ልብ አይራመደ። እሾህን በእሾህ። እቃ ብናጣ፤ አብረን በላን። እቃ፥ እንደመጣ ይውጣ። እቅድ ድሮ፤ ክንውን ሽሮ። እበላ ባይ፤ ቃል አቀባይ። እበላ ብዬ ተበላኹ። እበላ ብዬ ተበላኹ፥ ምነው ሳልበላ በቀረኹ። እበላ ያለ ዳኛ፤ እገድል ያለ መጋኛ። (መጋኛ ~ ደመኛ) እበላለሁ ብለህ መሬት አታዚጋ፤ ጠርጥሮ ጠርጥሮ ጨርሶታል አልጋ። እበት ትል ይወልዳል። እበት ትል ይወልዳል፤ ድሀ እብለት ይወዳል። እበትም ትል ይወልዳል። እበትና ኩበት፤ ወገንና ከብት። እባብ ለእባብ፥ ይተያያሉ ካብ ለካብ። (ይተያያሉ ~ ይተያያል) እባብ ላይበላው፥ አብላላው። እባብ ልቡን፤ አይቶ እግር ነሣው። እባብ ሲያዩት ይለሰልሳል፥ ጌታ ቢጫወት ባልንጀራ ይመስላል። እባብ ስለሆደ ይኼዳል በሆደ። እባብ ቀጭን ነው ተብል ራሱ አይረገጥም። እባብ በመርዙ፤ መሬት በወንዙ። እባብ በምድር ተጋድሞ፥ ሰው በትር ይዝ ቆሞ። እባብ በራሱ ጠመጠመ፤ ከሰይፍ ላይ እግሩን አቆመ። እባብ በራሱ ላይ የጠመጠመ፤ ከሰይፍ ላይ እግሩ የቆመ። እባብ በእግርህ፤ በትር በእጅህ። እባብ በእግርህ፤ በትር በእጅህ አለች ቀበሮ። እባብ፥ አፈር ያልቅብኛል ብል፥ ሲሰስት ይኖራል። እባብ እንደ መለስለሱ፥ መታጠቂያ በሆነ እሱ። እባብ እንደ መለስለስሽ፤ ቅናተ ዮሀንስ በሆንሽ። እባብ ከምድር ተጋድሞ፥ ሰው በትር ይዝ ቆሞ። እባብ ከእግርህ፤ ብትር ከእጅህ። እባብ የልቡን አይቶ፥ እግር ነሣው። እባብ የሚገድለው፥ በምላሱ እኮ ነው። እባብ የረገጠ፤ በልጥ ደነገጠ። እባብ ያየ፤ በልጥ በረየ። እባብ ጉድ጑ደን አይስት። እባብ ጉድ጑ደን፤ ውሻ ጌታውን። እባብ ጥበስልኝ፥ ይብረድልኝ። እባብ(ን) ግደል፥ ከነበትሩ ገደል። እባብና ጑ጉንቸር በአንድ ይኖራሉ። እባብን ልቡን አይቶ፥ እግር ነሣው። እባብን ሞተ ብል፥ እራሱን መርገጥ መቅበጥ። እባብን ያየ፤ በልጥ በረየ። እባክህ አታጋልጠኝ፤ ለጠላት አትስጠኝ። እባክሽ ያሎት ጎረቤት፥ ትሆን እመቤት። እቤተ ክርስቲያን ሲደርስ የጠላቴ ሬሳ፤ የእኔ ከቤት ይነሣ። እቤት ተኛ ቢሉት፥ መንገድ እኼዳለኹ፥ እጨቡማለኹ ብል በደጃፍ ተኛ። እብድ ለእብድ ቀን ይበጃል። (ይበጃል ~ ይባጅ) እብድ ለእብድ፤ አብሮ ይነጉድ። እብድ ቀን አይመሽ(ም)። እብድ ቢጨምት ለጥቂት። እብድ ቢጨምት፥ እስከ እኩለ ቀን (ብቻ ነው)። እብድ ቢጨምት፥ እስከ እኩለ ቀን ድረስ ነው። እብድ አሞራ፤ ሲላ ደንገጡራ። እብድ አይሙት፥ እንዱያጫውት። እብድ እህል ገዝቼ፥ ሚስቴን አሳበድ኱ት። እብድ ከመጨመት በቀር፥ ምን ይቀረዋል? እብድ፥ ከወፈፍተኛ ቤት ያድራል። እብድ የያ዗ው፥ መልክ አይበረክትም። እብድና ሰካራም፥ የልቡን ይናገራል። እብድና ብርድ፥ ያስቃል በግድ። እብድና ዗መናይ፥ የልብን ይናገራል። እብድና ዗በናይ፥ የልቡን ይናገራል። እብድና ጅኒ(ጂን) አያግኘን። እብድና ገር፥ የታየውን ይናገር። (ይናገር ~ ይጫወት) እብድና ፖሉስ ሕግ አያቅም (የ዗መኑ) ። እብድን በርቀት፤ ወሬን በንቀት። እተካከል ተግመል። እታከል ተግመል። እታ዗ዝክበት አውለሀቸው፥ ሽፍታ በወሰዳቸው። እቴ ከሆንሽ፥ ካለስሜ አታልቅሽ። እቺ እንጣጥ እንጣጥ፥ አምፖል ለማውለቅ ነው። እቺም ቂጥ ሆና፥ ስንጥቅ ተበጀላት። እቺውም ቂጥ ሆና፥ ተፈሳባት አሉ የኔታ። እነ ጨዋ ሰው ቢውረገረጉ፥ ምን ሉያደርጉ?( ምን ሉያደርጉ ~ ምን ያርጉ) እኒህ ሥሡ፥ ለዝናብ ጌታ ውሃ ነሡ። እናቱ ውሃ የኼደችበትና የሞተችበት እኩል ያለቅሳሉ። እናቱ የሞተችበትና ውሃ የወረደችበት እኩል ያለቅሳሉ። እናቱ የሞተችበትና ገበያ የኼደችበት እኩል አለቀሱ። እናቲቱ ድሮ ልጇን ይዚ ጑ሮ ለ጑ሮ። እናቲቱን አይተህ፤ ልጅቷን አግባ። እናቴ ቤት፥ ጠላ እጠጣለኹ ብላ፥ የቤቷን ውሃ ትታ ወጣች። እናቴን ላክል ዗ጠኝ ወር ቀረኝ አለች። እናቴ የዕለቱን፤ አባቴ የዓመቱን። እናቴን ሳይ ሴት ማግባቴን፤ ቤቴን ሳይ ትንባሆ መጠጣቴ። እናቴን የአገባ፥ ዅሉ(ም) አባቴ ነው። እናት ለልጄ፥ ልጅ ለነገዬ። እናት የላለው ልጅ፥ ቀላል እንደ ጌሾ፥ ሳይበላ የበላ፥ ሳይናገር ዋሾ። እናት የላለው ተ጑ዳጅ፥ ዕርሻ የላለው ጠላ ወዳጅ። እናት የዕለቱን፤ አባት የዓመቱን። እናትህ ማን ነች? ሳልወለድ ሞተች። እናት፥ ለልጇ ሙት ናት። (ሙት ~ ነቢይ ~ ጠንቋይ) እናት ሳለች፤ ሞግዙት ታንቃ ልሙት አለች። እናት፥ ትረገጣለች እንደ መሬት። እናት እንደ ጡቷ፤ ኹለት አትሆንም። እናትና ልጅ፥ ቃል ተባሉ። እናትና አባት፥ ሳሉ ቀሉል። እናትህ ምን ታደርጋለች ቢሉት፥ እያፈሰሰች ትለቅማለች አለ አሉ ልጅ። እናትህ፥ ውሃ ትጋትህ አለ። (:_ የድካምን ዋጋ ነሣ) እናትዋን አይተህ፤ ልጅቷን አግባ። እናትዋን ጥላቻ፥ የልጇን ስም አጎደፈ። እናትየዋን ሲከጅሉ፥ ልጅቷን ይስማሉ። እናቷ ዗ንድ ኼዳ ከመጣች፥ ከእንብላው በቀር ሥራ አጣች። እናቷን አይተህ፤ ልጂቱን አግባ። (ልጂቱን ~ ልጇን) እናንተ ቤት ያለው እሳት፥ እኛ ጋርም አለ። እናያለን ሲሉ ይታያሉ፥ እናማለን ሲሉ ይታማሉ። እኔ ልብላ፥ አንተ ጦም ዕደር። እኔ ሳጣ፥ ልጄ ጥርስ አወጣ። እኔ በልጄ ሳዝን፥ ልጄ በልጁ ያዝን። እኔ አለኝ ቁስል፥ ያንቱን የሚመስል። እኔ አውቃለኹ የቆቅን መላ፥ ወይ በራለች ወይ ደፍጣለች። እኔ አይገባኝ አር ላይ ቁጭ ብል፥ ፈስ ገማኝ። እኔ እውነት እናገራለኹ፥ ላላውን አስኮንናለኹ። እኔ ከሞትኩ፥ ሀብቴ ለከዝኔ። እኔ ከሞትኩ፤ ማ዗ር ታብዳለች። እኔ ከሞትኩ፥ ምርጫው ይሰረዚል። እኔ ከሞትኩ፤ ሰርድ አይብቀል። እኔ ከሞትኩ፤ እቃ እንዳታውሽ። እኔ ዗ንድ ሆነህ ባየኸው። እኔ የምሞተው በዕለት፥ ሕልሜ የሚደርስው በዓመት። እኔ የምሞተው ዚሬ ማታ፥ ገብስ የሚደርሰው ለፍልሰታ። እኔ የምሞት ዚሬ ማታ፥ እህል የሚደርሰው በፍልሰታ። እኔ የምሞት ዚሬ ማታ፥ ገብስ የሚደርስ በፍልሰታ። እኔ የምበላው ሳጣ፥ ልጄ ጥርስ አወጣ። እኔም አለኝ ቁስል፥ ያንተን የሚመስል። እኔም አራዳ አንቺም አራዳ፥ ምን ያጣላናል በሰው በረንዳ። እኔም ፈጣጣ፥ አንቺም ፈጣጣ፥ ምን ያጣላናል? በሰው ሰላጣ። እኔስ የሚገርመኝ የዙህ አብነቱ፥ ባልልቦ ወለደች ልጃገረዱቱ። እኔን ለቀቅ፤ ሱሪህን ጠበቅ። እኔን መሳይ ዗ካሪ፤ አንቺን መሳይ ጋጋሪ አያጥፋ ፈጣሪ። እኔን ሲፈጀኝ፥ ልጄን ያቃጥለው። እኔን ቢወደኝ ወደ አፍንጫቸው ወሰደኝ፥ አንቺን ቢጠሉሽ አጥመዝም዗ው ጣሉሽ አለቻት ትዃን ቁንጫን። እኔን አይተህ ተቀጣ፤ በጉድህ እንዳትወጣ። እኔን እኔን ይጠሉ፤ አሬን አሬን ይረመርሙ። (አይጥ ያለችው) እኔን የሚደፍረኝ፤ ወጤን የቀመሰ ነው። እኔን የወደደ ከአንጀት፥ ልጄን የወደደ ከአንገት። እኔን ያለ ከአንገቱ፥ ልጄን ያለ ከአንጀቱ። እኔን ያርሙ፤ አር አሬን ይረመርሙ። እኔው ሞቼ፤ እኔው ቄስ ጠርቼ አለች ሴትዮ ቢመራት። እኔው ሞቼ፤ እኔው ቄስ ጠርቼ። (እኔው ~ እኔ) እኔው ተቀርድጄ እኔው ተቀቅዬ ባወጣኹት ነፍስ፥ ተንጎራደደብኝ ባለ ዗ጠኝ ልብስ። (ጎመን በቆልን) እኔውም እብድ ነኝ፥ ከወፍ የገበየኹ መቀመጧን እንጂ፥ መብረሯን መች አየኹ። እንስራዋን ረስታ ውሃ ወረደች። (ውሃ ~ ወንዝ) እንስራዋን ትታ ውሃ ወረደች። (ረስታ ~ ጥላ) እንቀት አንቅቼ፤ ገንፎ አገንፍቼ። እንቁላል ቀስ በቀስ በብር አንድ ይሆናል። እንቅልፍ ታበዢ፤ ከነብር ትፋ዗ዢ። እንቅልፍ ታበዥ፤ ከነብር ትፋ዗ዥ። እንቅልፍ የጠላ፥ ውሻ ያሳድጋል። እንቅልፍ የገረ዗዗ው፥ ውሃ ያወረዚው ቤት ነው። እንቅልፍና ሞት፤ ሬትና ሀሞት። እንቅልፍና ሞት አንድ ነው። ዕንቅርቱን ትተው፥ ንቅሳቱን። እንቅፋት አይፈራ፤ ሥንቅ አያሰላ፤ ከመውጣቱ ዓለምን ዝሮ መግባቱ። እንቆቆ ሲጠጡ ስቅጥጥ፤ ወተት ሲጠጡ ጭልጥ። እንበለ ገን዗ብ መዝናናት፥ ያመጣል ውርደት። እንባ ሲሻኝ፥ አይኔን ጢስ ወጋኝ። እንብላም ከአላችኹ እንብላ፥ አንብላም ከአላችኹ እንብላ አለች አያ ጅቦ። እንብዚም ስለት፥ ይቀዳል አፎት። እንብዚም ብልኀት ያደርሳል፥ ከሞት እንብዚም ስለት፥ ይቆርጣል አፎት። እንትኑን በእንትን፥ አደረገው ብትንትን። እንብዚም ብልኀት፥ ያደርሳል ከሞት። እንትን አልንበት እንትን ገባበት፥ እንትን አምጪልኝ እንትን እልበት፥ አንቺም ነዪልኝ እንትን ትዪልኝ። እንትኗን ~ ብልቷን ~ አይኗን ባል ሲጠግብ፥ ውሃ ቀጠነ ይላል። እንናገራለን እንጂ፥ አንማታም። እንኩን የማያውቅ፥ ስጡኝን ማን አስተማረው? እንካ ሲሉት እምቢ፤ ቁጭ ሲያደርጉ ሥርቅ። እንካ ብላ አለችኝ ደረቁን እንጀራ፥ እሷ በነካካው በራሰው ልትበላ። እን኱ን ለሉጥ፥ ለገንፎም አልደነግጥ። እንኺድ ዗ገዩ ይሉናል፥ ግድ የለም ስንገባ ያምኑናል። እንሳሣቅ ካልሽ ነድዬን ጥለሽ። እንደ መስቀሉ ይበሳሳኝ፤ እንደ ወንጀሉ ይደምስሰኝ። እንደ መረብ ሸፍኖ፤ እንደ እንቁላል ደፍኖ። እንደ ሚስቴ፤ እንጂ እንደ እናቴ ሀሳብ አታውለኝ። እንደ ምላጭ ስለት፤ እንደ ጉንዳን ጉልበት፤ እንደ ሴት ብልኅት ይስጥህ። እንደ ሠኔ ቧጋች፥ እርቡድ እርቡድ። እንደ ርግብ የዋህነት፤ እንደ እባብ ብልኅነት። እንደ ሸሸ ተነጥፎ፤ እንደ ቅጠል ረግፎ። እንደ ሰው በከተማ፤ እንደ አውሬ በጨለማ። እንደ ሰው ትመጪ፤ እንደ አውሬ ትሮጪ። እንደ ሣር ነጭቶ፤ እንደ ውሃ ተጎንጭቶ። እንደ ሥራቸው፥ በተዋረድ ክፈላቸው። እንደ ሽመላ፥ በኹለት ይበላ። እንደ ቆጫት ተነሥታ፤ የሰው ለቅሶ አጥፍታ። (አጥፍታ ~ አጠፋች) እንደ ቆጫት ተነሥታ፥ የሰው ልቅሶ አጠፋች። እንደ በሶ አንቆ፤ እንደ ርጉዝ አስጨንቆ። እንደ ተተከለ ትርሽማ፤ እንደ ተሰጣ ሸማ። እንደ ነደደች ተነሥታ፤ የሰው ለቅሶ አጠፋች። እንደ ንብ ቀስሞ፤ እንደ ወጥ ቀምሞ። እንደ በሶ፥ በእጁ ነግሦ። እንደ ንጉሡ አጎንብሱ። (አጎንብሱ ~ ያጎንብሱ) እንደ ንጉሡ፥ ይንገሡ። እንደ አህያ ጆሮ፤ እንደ ጦር ጐረሮ ተካክለው በደሉ አለ። እንደ አማሩ መሞት (አይገኝም)። እንደ አባት ሥቆ፤ እንደ ንጉሥ አውቆ። እንደ አንበሳ በድሱ፤ እንደ ጅብ በደንደሱ። እንደ አንድ ልብ መካሪ፤ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ። እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ፤ እንዳንድ ሰው መስካሪ። እንደ አውሬ ባፋፍ፤ እንደ ጦጣ በዚፍ። እንደ አይን ፈሪ፤ እንደ እግር ደፋር የለም። እንደ አገሩ፤ ጅብ ይገሩ። እንደ አገሩ ይናገሩ። እንደ አገሩ ይኖሩ፥ እንደ ወንዙ ይሻገሩ። እንደ አጤ ሥርአት፤ እንደ አብርሃም እራት። እንደ አጥር፤ እንደ ቅጥር። እንደ እርገት፥ በዓመት (የሙሴ ድግስ)። እንደ እሸት ፈልፍል፤ እንደ ዗ንግ መልምል። እንደ እሸት ፈልፍዬ፤ እንደ ዗ንግ መልምዬ። እንደ እንቁላል ድፍን፤ እንደ መረብ ሽፍን። (መረብ ~ ባር ማሽላ) እንደ እንቁላል ደፍኖ፤ እንደ መረብ ሸፍኖ። እንደ እንግዳ ጥልቅ፤ እንደ ውሃ ፍልቅ። እንደ እንግዳ ደራሽ፤ እንደ ውሃ ፈሳሽ። እንደ ዕውር አፍጣጭ፤ እንደ ጎግ ቀላዋጭ። እንደ ካህን ናዝዝ፤ እንደ ንጉሥ አዝዝ። እንደ ወርቅ አንከብል፤ እንደ ሸማ ጠቅል። እንደ ወናፍ፥ ኹለት አፍ። እንደ ወንድማማች ተበዳደሩ፤ እንደ ባእድች ተቆጣጠሩ። እንደ ወይን መልምዬ፤ እንደ ዕንጨት ተክዬ። እንደ ውሃ ይፍሰስ፤ እንደ ጋጃ ይፈስ። እንደ ውላ፥ ደጃዝማች ባላ። እንደ ዝንጀሮ በአፋፍ፤ እንደ ጦጣ በዚፍ። እንደ የለም፥ በጎ የለም። እንደ የቤቱ፥ ብዙ ነው ብልኀቱ። እንደ የቦ ሰልቶ፤ እንደ ቆንጆ ደርቶ። እንደ ዳኛ በውል፤ እንደ ምሰሶ በመሀል። እንደ ድመት በወተት፤ እንደ ልጅ በቀለበት (ልመና)። እንደ ጆሮ ትልቅ፤ እንደ ዓይን ትንሽ የለም። እንደ ገና፥ ይመታል በገና። እንደ ጉም በኖ፤ እንደ ጢስ ተንኖ። እንደ ጥጥ ዳጠው፤ እንደ ቀሚስ አጠለቀው። እንደ ፀሓይ የሞቀ፤ እንደ ጨረቃ የደመቀ፤ እንደ አበባ ያሸበረቀ። እንደ ፈረስ ጆሮ፤ እንደ ሰላጢን ጐረሮ። እንደ ፈታሂነቱ ኹላችን፤ እንደ መሀሪነቱ ኹላችን እንማራለን። እንደ ፈንታላ ትቀልጣለህ። እንደሚባለው ዅሉ፥ አምላክ ሲሰጥ ምክንያት ያዚል። እንደምን ይኖራል ጎጃሜ ሳያርስ? በሬ ሳላይ መጣኹ፥ ከዙያ እስከዙህ ድረስ። እንደገና፥ ይሞታል በገና። እንዱህ ሉታረፈን፥ ለሚስቴ ነፈግኋት። እንዱህ ልጠግብ፥ በሬዬን አረድኩት። እንዱህ ነድጄ ልሙት፥ የፊቱን በኋላ አድርጎት። እንዱህ ንገሩ፤ እንዱህ ሥሩ። እንዱህ እንዱህ እየተባለ፥ የኔም ቀን ይደርሳል አለች አልቃሽ። (አልቃሽ ~ አስለቃሽ) እንዱህ ያለ ዳኛ፥ የዳኛ ቄናጣ። እንዱህ ያለ ዗መን ዗መነ ግልምቢጥ፥ ውሻ ወደ ሰርድ አህያ ወደ ሉጥ። እንዱያው በደረቅ፥ አላህም አይታረቅ። እንዱያው ብትመለሺ፥ የገንፎ ዕንጨት ላሺ። እንዱያው ተመሆን፥ ማቅ ይሻላል። እንዱያው ከምትቀሪ፤ ምንቸቱን አንቅሪ። እንዱያው ከተመለሽ፥ የገንፎ ዕንጨት ላሽ። እንዱያውም በመላ፥ ፈስ ዳለቻ ነው። እንዳልበላ በአፌ፤ እንዳልበር በክንፌ። እንዳልተወው ወለድኩ፤ እንዳልሰው ነደድኩ (አለች ላም)። እንዳልውጠው አርብ ነው፤ እንዳልተፋው እህል ነው። እንዳትኼድ ቀየዳት፤ እንዳትበላ ለጎማት። እንዳትበላ ለጎሟት፤ እንዳትኼድ ቀየዶት። እንዳንኼድ ፍቅር፥ እንዳንተው ችግር። እንዳንራብ ጀአል፤ እንዳንሠራ በዓል። እንዳንድ ቃል ተናጋሪ፤ እንዳንድ ሰው መስካሪ። እንዳየን፥ ጤፍ አጋየን። እንዳዩ መብላት፥ ሆድ ያሰፋል። እንዳዩ መብላት፥ ቤት ያስፈታል። እንዳዩ መጉረሥ፥ እድህነት ያደርስ። እንዳያማህ ጥራው፤ እንዳይበላ ግፋው። እንዳይለቁት እሳት፤ እንዳይዙት መዓት። እንዳይወልደ ይመነኩሱ፤ እንዳይጸድቁ ይልከሰከሱ። እንዳት ዋልሽ ለእኅቱ፤ ግንድ ለሚስቱ። እንድድ በሞኝነቱ፥ ወንዝ ወረደ። እንድድ በገርነቱ፥ ውሃ ወሰደው። እንድድ በገርነቷ፥ ውሃ ወሰዳት። እንድድ በገርነቷ፥ እወንዝ ወረደች። እንጀራ ለረኃብ፤ ድንጋይ ለካብ። እንጀራ ለባዕድ፤ መከራ ለ዗መድ። እንጀራ፥ በማየት አያጠግብም። እንጀራ በሰፌድ፤ አሞላ በገመድ። እንጀራ እንጀራ ከባዕድ፥ መከራ መከራው ከ዗መድ። እንጀራ ከባዕድ፤ መከራ ከ዗መድ። እንጀራ የለም እንጂ፥ በወተት አምገህ ትበላ ነበር። እንጀራ ያለ ወጥ፤ ቤት ያለ ሴት፤ ከብት ያለ በረት። እንጀራ ያለው ክቡድ፤ እንጀራ የላለው ዕብድ። እንጀራ ይጋግሯል እማድ ቤት፤ መላ ያማክሯል ለሴት። እንጀራስ ወጡ ረኃብ ነው። እንጀራን ምን፥ ይጨርሰዋል? መጉረሥ። እንጀራን ከባዕድ፤ መከራን ከ዗መድ። እንጀራን ከባድ፤ ዋይን ከ዗መድ። እንጀራው ሳይኖር፥ ከወጡ አስነኩልኝ። እንጀራው ሳይገኝ፥ ከወጡ አስነኩልኝ። እንጀራው ቢሳሳ፥ ከወጡ አለው ካሳ። እንጀራውን ሳይሰጡት፥ ከወጡ አስነኩልኝ አለ። እንጃ በሰማያት፥ በምድርስ የለም ምክንያት። እንጃ፥ ባፍህ ሙሉ ጅብ ይንጃጃ። እንግዱህ ልሩጥ፤ አምርቼ ቁርጥ። እንግዱህ ነገሬን በከንፈሬ። እንግዳና ሞት በድንገት። እንግዳ ሲወደስ፥ ባለቤቱን ያጎርሥ። እንግዳ ሲያ዗ወትር፥ ቤተሰብ ይሆናል። እንግዳ ሲያፍር፥ ባለቤቱን ይጋብዚል። እንግዳ ሲያፍር፥ ባለቤት ይጋብዚል። እንግዳ ሳይመጣ ዅሉ ሴት፤ ዝናብ ሳይጥል ዅሉ ቤት። እንግዳ ባይመጣ ዅሉ ሴት፤ ክረምት ባይመጣ ዅሉ ቤት። እንግዳ ሆነህ ብትመጣ፥ ሳይሰለቹህ ውጣ። እንግዳ ይጋብዚል፥ ባለቤት ሲያፍር። እንግዳ ደራሽ፤ ውሃ ፈሳሽ። እንግዳ ፊት ወርቅ፥ ኋላ ብር፥ ኋላ ብረት፥ (ኋላ ጨርቅ)። እንግዳና ሞት፥ በድንገት ይመጣል። እንግዳህ ለርጥ፤ አምሮቴ ቍርጥ። እንጎቻ የበላ፥ ከእራት ይታገሣል። እንጣጥ እንደ፤ ፌቆ ሙልጭ እንደ ሥብቆ። እንጥስ ቢሉ፥ ቅንጥስ። እን኱ን ለሞት፥ ለእርጅና ይቆዩታል። እን኱ን ለራሱ፥ ለሰው ይተርፋል እሱ። እን኱ን ለቤቱ፥ ያተርፋል ለጎረቤቱ። (ያተርፋል ~ ይተርፋል) እን኱ን ለእኅቱ፥ ለላላውም ይ዗ፍናል አንገቱ። (ለእኅቱ ~ ለእኅቴ) እን኱ን ለገንፎ፥ ለሙቅም አልደነግጥ። እን኱ን ልመነኩስ፥ አልከናነብም። እን኱ን መሞት፥ ማርጀት አለ። እን኱ን መብረር፥ አይነሡም። እን኱ን ሞት፥ እርጅና እን኱ አለ። እን኱ን ሲሸጡኝ፥ ሲያስማሙኝ አውቃለኹ። እን኱ን በ዗ንድሮው፥ በአምናውም አልዳሩኝ። እን኱ን ባሩድ ሸቶሽ፥ እንዱያውም ጠርሙስ አረቄ ትጨርሻለሽ። እን኱ን ተልባ ሸቶሽ፥ እንዱያም ዗ጠኝ ቂጣ ትፈጃለሽ። እን኱ን እመነኩስ፥ አልከናነብም። እን኱ን እስቀው፥ አንጋጥጠው የለኝ። እን኱ን እስቀው፥ አገጠው የለኝ። እን኱ን እስቀው፥ አገጠውም የለኝ። እን኱ን እናቴ ሞታ፥ እንዱያውም አልቅስ አልቅስ ይለኛል። እን኱ን ከፎከረ፥ ያድናል አምላክ ከወረወረ። እን኱ን ከፎከረ፥ ያድናል ከወረወረ። እን኱ን ዋሽተን፥ በእውነትም እየጮህን ዕውር ነው የምንወልደው አለች ውሻ። እን኱ን ይችን፥ የዝንብ ጠንጋራ እናውቃለን። እን኱ን ድሮ፥ የለም ሽሮ። እን኱ን ዗ንቦብሽ፥ ድሮም ጤዚ ነሽ። እን኱ን የሸመተ፥ ያረሰም አይችልሽ። እን኱ን(ስ) ዗ንቦብሽ፥ እንዱያውም ጤዚ ነሽ። እን኱ንስ ለእኔ ለሰው፥ ለእሳት እራት አለው። እን኱ንስ ነጠላ አግኝታ፥ ደሮም ዗ዋሪ እግር አላት። እንወራረድ፥ አህያ እንረድ፥ እኔ ጠባሽ፥ አንተ ቀማሽ። እንደ ልብ የለም ነዳጅ፤ እንደ ልብ የለም በራጅ። እንደ ልጅ በቀለበት፤ እንደ ድመት በወተት። እኖራለኹ ብለህ እጅግ አትበርታ፥ እሞታለኹ ብለህ ሥራ አትፍታ። እኖር ባይ ተጋዳይ። እኖር ባይ ተጋዳይ፥ እድን ባይ ተከላካይ። እኛ ምን አገባን በሰው ፖለቲካ፥ እኛንም አይንኩን እኛም ሰው አንነካ። እኛ በአገራችን፤ ዳቦ ፍሪዳችን። እኛ ካልለመድናት፥ ጅላለች እንላለን። እኛ ያልፈሳንበት ዳገት የለም፥ አለች አሉ አህያ። እኛን ተወት፤ መቀነትን ጠበቅ። እኝኝ ሲል ችግኝ። እከሉት ስለሞተች፥ ሰዎች ይገምጧት ወጡ። እከላ ተናገረ፤ እግዛር ተናገረ። እከላ እባብ ነው፥ መኼጃው አይታወቅም። እከላ፥ ዗ር ስትወልድ ቢያይ ያማምጣል። እከላ የዋለበት ሸንጎ፥ አይጥ የገባበት ዕርጎ። (የዋለበት ~ የገባበት) እከከኝ ልከክህ። እከክ የሰጠ ጌታ፥ ጥፍሩን አይነሣም። እከክ የሰጠ፥ ጥፍር አይነሣም። እከክን ያመጣ፥ ጥፍርንም አላሳጣ። እኩሉ በድሮ፤ እኩሉ በሽሮ። እኩሉን ተላጭታ፤ እኩሉን ተቀብታ። እካስ ያለ ታግሦ፤ እጸድቅ ያለ መንኵሶ። እክ እንትፍ በጅል ቤት ድሮ ሲከተፍ። (ሲከተፍ ~ ሲቀጠፍ) ዕወቁኝ (ያለ)፥ ደብቁኝ። እኼድ ባይ፥ ሥንቅ ፈጅ። እህ ትበል እናትሽ፥ እኔን አይታ የዳረችሽ አለ ቆማጣ። እህሉ አንድ፤ ሴቱ አሥራ ኹለት። እህሉ አንድ፤ ሴቱ አሥር ነው። እህላን የሚበላ፥ ተረከዙን አነሣብኝ። እህል ለቀጠና፤ ወርቅ ለዝና። እህል ለአራሽ፤ ርስት ለወራሽ። እህል ላበደረ አፈር፤ ወርቅ ላበደረ ጠጠር። እህል መጣፈጡን፤ ጐረሮ መዋጡን አይተውም። እህል ሲያጡ፥ የእናት ልጅ ያጡ። እህል ሲገኝ፥ ወፍጮ ይሟልጣል። እህል ሲጠፋ ወፍጮ ይሰላል፤ እህል ሲገኝ ወፍጮ ይደንዚል። እህል ሲጠፋ፥ ወፍጮ ይቀራል። እህል በቀርበቦ፤ እንቁላል በወታቦ። እህል በጥቅምት፤ ልጅ በጡት። እህል ባሳደገ፤ ደመኛ አይደለም። እህል አላምጦ፤ ነገር አዳምጦ። እህል አይገፋም። እህል ከባድ፤ ልጅ ከአጎድ። እህል ከበዩ፤ ሰው ከገዳዩ። እህል ከአልተዋጠ፤ ነገር ከአልተደመጠ። እህል ከአራሚው፤ ሰው ከአስታማሚው። እህል ከአባድ፤ ልጅ ከጎድ። እህል ከውድማ ብቻውን ዋለ፥ አያላ ሰዎችን እንዳልገደለ። እህል ከ዗ባጣ፤ ልጅ ከአርጣጣ። እህል ከደር፤ ልጅ ከአጉል። እህል ኪያጡ፥ የእናት ልጅ ይጡ። (ኪያጡ ~ ሲያጡ) እህል ወዳጁን ይጎዳል። እህል የበቀለበት ያስታውቃል። እህል የያ዗ ፈርዚዚ፤ ወርቅ የያ዗ ቀበዝባዚ። እህል ያለ ውሃ፤ ንጉሥ ያለድሀ። እህልና መሬት፤ ሴትና ባለቤት። እህልን በጥቅምት፤ ልጅን በጡት። እህልን አላምጦ፤ ነገርን አዳምጦ። እህልህን ስትወቃ፤ የሚያበራየውን በሬ አፍ አትለጉመው። እልልታ ለደስታ፤ እሪታ ለርዳታ። እወተቱ ላይ ውሃ ጨምሩበት፥ እንዱያበዚውም እንዱያናጣውም። እወይ የኔ ኑሮ፥ እንዱያው ተለባብሶ፥ መስቀል ተሰላጢን፥ ኀ዗ንና ለቅሶ። እወደዋለኹ በል እንጂ፥ ይወደኛል አትበል። እወዳለኹ እያለ የሚጠላ፤ እጾማለኹ እያለ የሚበላ። ዕውር ምን ይሻሀል ቢሉት፥ ማየት አለ። እውነተኛ ሚስት፥ ባሎን ትወዳለች። እውነቱን ተናግሮ፥ እመሸበት ያድራል። እውነቱን ተናግሮ፥ ከአመሹበት ማደር። እውነት ለእግዛር፤ ውሸት ለሳጥናኤል። እውነት ትቀጥናለች እንጂ፥ አትበጠስም። እውነት ትከሳለች እንጂ፥ አትሞትም። እውነት ትገያለች እንጂ፥ አትቀርም። እውነት የተናገረ፤ በመርከብ የተሻገረ። እውነት፥ የሀሰት ባሕር ብትሰምጥ ትሟሟለች እንጂ፥ አትጠፋም። እውነት ይመስላል፥ ልብን ያቆስላል። እውነትና ሀቅ እያደር ይጠራል እንደ ወርቅ። እውነትና ርግዝና፥ ቶል አይገለጡም። እውነትና ንጋት፥ እያደር ይታያል። (ይታያል ~ ይገለፃል ~ ይጠራል) እውነትና ንጋት፥ እያደር ይጠራል (እንደወርቅ)። እውነትና ዕብለት፤ ውሃና እሳት። እውነትና ጢስ የሚወጣበት አያጣም። (የሚወጣበት ~ ይወጣበት) እውነትን የሚያሥንቅ ውሸት፤ መውጋትን የሚያሥንቅ መሳት አለ። እዙያ ማድ ጠብ ብታደርሰኝ፥ አሞላ ጨው አገባለኹ። እዙያም ኼደሽ በላሽ፥ እዙህም መጥተሽ በላሽ፥ ሰው ታ዗በሽ እንጂ ሆድሽን አልሞላሽ። እዙያው ሞላ፤ እዙያው ፈላ። እዙያው ዗ንቦ፤ እዙያው ያባራ። እዚም ቤት እሳት አለ። እየሰለሉ፥ ዕድሜ መቁጠር። እየሰማ የሞተ፥ እያየ ይቀበራል። እየቆሉ ጥሬ። እየቆረጣችኹ አንበሳውም ኼደ፤ ነብሩም ሞተላችኹ። እየቆራረጣችኹ አንበሳ ኼደ፤ ነብሩም ሞተላችኹ። እየበለቱ ሳይሆን፥ እየቧለቱ ቅኝት። እየቤትህ ግባ፤ እየራስህ ተቀባ። እየተፈጨ እየተቦካ፤ እየሞተ እየተከካ። እየታጠቡት ያድፋል፤ እየመከሩት ያጠፋል። እየነገርናቸው እያረጉት ዋዚ፤ ከተለበለበው የተላጠው በዚ። እየወገንህ ቢሉት፥ አክንባል ጋጥ ገባ። እየወገንህ ቢሉት፥ የመቶ ዓመት ቆዳ ከብት ተራ ቆመ። እየጠላኹት መጣኹ። እየጠጡ ዝም፥ የጋን ወንድም። እየፈለገው፥ ዕወቀኝ ብል መጣ። እየፈለገው፥ ዕወቀኝ ዕወቀኝ ብል መጣ። እየፈጩ ጥሬ። እዩኝ እዩኝ ያለች፥ ደብቁኝ ደብቁኝ ታመጣለች። እዩኝ እዩኝ ያለ፥ ደብቁኝ ደብቁኝ ይላል። እያለው የማይከፍል፤ ጭኖ የማያደላድል። እያንጎራጎረ፥ ጋራውን ዝረ። እያወቀ የገባን፥ አብረህ ቅበረው። እያወቁ ቢስቱ፥ ምንድር ነው መድኀኒቱ? እያየኋት የምታሥቀኝ፥ ሚስት አገባኹ። እያየህ ተናገር፤ እየዋኘህ ተሻገር። እያደር ይቃቃር። እያደረ እያደር ሀሰትና እውነት፥ የቱ ይረታ ጠዋት። እያደፈ በእንድድ፤ እየጎለደፈ በሞረድ። እያጫወት኱ት ታንቀላፋለች። እዬዬ(ም) ሲደላ ነው። (ሲደላ ~ ሲዳላ ~ ቢዳላ) እደ ልቡና ለጸልት፥ እደ ሰብእና ለመሥዋዕት። ዕደር ያሉት፥ እንግዳ እራቱ ፍሪዳ። እደን ወርድ፥ አምሳያውን ቆርጦ መጣ። እደን ገብተህ፤ አምሳያህን ቁረጥ። እድለ ቢስ አሞራ አሸን ሲመጣ፥ አይኑ ይጠፋል። (አሸን ~ አንበጣ) እድላም አሞላ፥ በቅል ይለውጣል። እድላም አሞላ፥ በድላር ይሸጣል። እድላም አሞላ፥ የምርጫ ምልክት ነው። እድል ተርታውን፤ ዕጣ ፈንታውን። (ፈንታውን ~ ፋንታውን) እድል የላለው፥ የሚለፋው ለሰው። እድል ፈንታ፤ ጥዋ ተርታ። ዕድሜ ለንስሓ፤ ዗መን ለፍስሓ። እጀ ለስላሳ፥ ብርላ ለመጨበጥ ያቅተዋል። እጁ ከበትር፤ አፉ ከነገር። እጁን በሰንሰለት፤ እግሩን በብረት። እጄ ከበትር፤ አፌ ከነገር። እጄን በእጄ ቆረጥኩት። (ቆረጥኩት ~ ቆረጥኹት) እጅ ለነገር ያግዚል፥ ልብ እንደ ንጉሥ ያዚል። እጅ ለአፍ ሚዚኑ ነው፤ በአፍ የገባ ለእጅ ኀይሉ ነው። እጅ ሲነድ፤ ልብ ይነድ። እጅ ለአፍ፤ አሳብ ለልብ ያህል ነው። እጅ ሲያጥቡት ያድፋል፥ ልጅ ሲመክሩት ይጠፋል። እጅ አፍን አይስትም። እጅ እሾህን ይነቅሰዋል፤ ጥጋብ ሞትን ያስረሳዋል። እጅ እየታጠቡት ያድፋል፥ ልጅ እየነገሩት ያጠፋል። እጅ እያጠቡት ያድፋል፥ ልጅ እየነገሩት ያጠፋል። እጅ ከልብስ፤ ምላስ ከጥርስ። እጅ ከበትር፤ አፍ ከነገር (ይቆጠብ)። እጅ ይ዗ው ያስገቡት፤ እጅ ይዝ ያስወጣል። እጅ ይዝ ያገቡት፤ እጅ ይዝ ያስወጣል። እጅና አፍ፥ አይተጣጡም። (አይተጣጡም ~ አይተጣጣም) እጅና ጭራ፤ ሥጋና አሞራ። እጅና ጭራ፤ አፍና እንጀራ። እጅና ፍንጅ፥ አፍና እጅ። እጅን በሰንሰለት፤ እግርን በእግር ብረት። እጅግ መሠልጠን፥ መስረቅ ያመጣል። እጅግ መብሰል፥ ማረር ይጠቅሳል። እጅግ ማግኘት፥ ያመጣል ትእቢት። እጅግ ሞኝነት፥ ያደርሳል ከሞት። እጅህን ከባሕር አግባ፤ ብታገኝ ዓሣን ታወጣለህ ባታገኝ ታጥበህ ትወጣለህ። እጅግ ስለት ይቀዳል አፎት፥ እጅግ ብልኀት ያደርሳል ከሞት። እጅግ(ም) ብልኀት፥ ያደርሳል ከሞት። እጅግ ስለት፥ ይቀዳል አፎት። እጅግም ስለት፥ ይቀዳል አፎት። እገላ የዋለበት ሸንጎ፥ አይጥ የገባበት እርጎ። እርጎውንም ለውሻ እርሱንም ለውርሻ። እገላን ሲያማ፥ ለእኔ ብለህ ስማ። እገድል ያለ መጋኛ፥ እበላ ያለ ዳኛ። እግረ መንገዳቸውን፥ ይሸጣሉ በሬያቸውን። እግረ ቀላል አማት፤ ያለ አንድ ኖር አይሎት። እግረ ቀላል አማት፤ ያለ አንድ ጊዛ አይነሡላት። እግረ ቀጭን እንደ ሰሳ፤ ልበ ሙሉ እንደ አንበሳ። እግረ ቀጭን ይሞታል ሲሉ፥ እግረ ወፍራም ይሞታል። (ወፍራም ~ ደንዳና) እግሩን ለጠጠር፤ ግንባሩን ለጦር። እግር ሲደርስ፥ እግት ይመለስ። እግር በደረሰው፥ ሆድ ይቆጠራል። እግር ቢሳሳት ከአንጋዳ፥ አፍ ቢሳሳት ከዕዳ። እግር ቢያሳስት፤ ከአንጋዳ አፍ ቢያሳስት ከዕዳ። እግር ከርካብ፤ እጅ ከዚብ። እግር ከሸሸ፤ ልብ ሸሸ። እግር ኼዳ ኼዳ፥ ሰገራ ጉድ጑ድ ትገባለች። (ሰገራ ~ ከአር) እግር ዛጋ ነው። እግር የላት፥ ክንፍ አማራት። እግር ይብሳል፥ ያበሰብሳል። እግር ይብሳል፥ ያንከላውሳል። እግርና እራስ፥ እኔ እለብስ እኔ እለብስ ይጣላሉ። እግርን ለጠጠር፤ ደረትን ለጦር። እግርህን ለጠጠር፤ ደረትን ለጦር። እግርህን በፍራሽህ ልክ ዗ርጋ። እግዙሔር ያመነውን፥ ማን ይችለዋል? ንጉሥ የተከለውን፥ ማን ይነቅለዋል? እግዙአብሔር ለፍጥረቱ፤ ሰው ለሰውነቱ (ያስባል)። እግዙአብሔር የተቆጣው በዝናብ አር መጣው። እግዙአብሔር የተናገረውን አያስቀር፤ የማያደርገውን አይናገር። እግዙአብሔርን ከማይፈራ ወዳጅ፥ እግዙአብሔርን የሚፈራ ጠላት። እግዙአብሔርን ያህል ጌታ፤ ገነትን ያህል ቦታ። እግዙእ አእምሮ በጠጅ፥ እንደ ወላቡ በደጅ። እግዛር ሰጠ፤ እግዛር ነሣ። እግዛር ሲሰጥ፥ እንጀራ በወጥ። እግዛር ሲቆጣ፤ በዝናብ አር ያመጣ። እግዛር ሲጥል፤ እናት አታነሣም። እግዛር ሳይደግስ አይጣላም። እግዛር በመለኮቱ፤ ጎልማሳ በሚስቱ። እግዛር በትር ሲቆርጥ፥ ቆላ አይወርድም። (ሲቆርጥ ~ ሉቆርጥ) እግዛር ባወቀ ሰማይን አራቀ። እግዛር እባብን ልቡን አይቶ፥ እግር ነሣው። እግዛር ከእኔ ጋራ እንታገል አለኝ፥ ኧረ እንዳት? ፈጥሮ ሉጥለኝ። እግዛር የተናገረውን አያስቀር፤ የማያደርገውን አይናገር። እግዛር የከፈተውን ጐረሮ፥ ሳይ዗ጋው አይድርም። እግዛር ያለ እሳት አነደደ፤ ያለ ውሃ አበረደ። እግዛር ያመነውን፥ ማን ይችለዋል? ንጉሥ የተከለውን፥ ማን ይነቅለዋል? እግዛር ያውቃል፥ ሰው (በከንቱ) ይጨነቃል። እግዛርን ሳይጨምር የቆጠረ፥ ኹል ጊዛ ሲቆጥር ይኖራል። እጠድቅ ብዬ ባዝላት፥ ተንጠልጥላ ቀረች። እጠጣ ሲል ይዋኛል፥ እበላ ሲል ይዳኛል። እጣ በድግጣ። እጣ ያስታርቃል፤ ሙግት ያዳርቃል። እጣ ያስታርቃል፥ እንጂ አይፈርድም። እጣ፥ በጉያ ይጣላል። እጣት ገማ ብለው፥ ቆርጠው አይጥሉት። ዕጥ የሆነ ስምጥ። (ዕጥ:_ ሩቅ የማይታይ) እጨለማው ውስጥ አግብተህ፥ ለምን ትልሳታለህ? እጨጌነት ከሳደላ። እጭን ያለ ኮርቻውን፤ እለምን ያለ ስልቻውን። እጸድቅ ብየ፥ ባቅፋት አንቀላፋች። እጸድቅ ብዬ ባዝላት፥ ተንጠልጥላ ቀረች። (ተንጠልጥላ ~ ተኝታ) እጸድቅ ብዬ ባዝላት፥ አንቀልባውን በጥርሷ በጠሰችው። እጸድቅ ያለ መንኰሶ፥ እካስ ያለ ታግሦ። እፍረት ያከሳል፥ ያመነምናል። ኧ ኧ አንጠራራኝ፥ እኔንም ሰው ጠራኝ። (ነብርና ዝንጀሮ)) ኧረ ሰውን ና ሰው። ኧረ ሣቄ ናልኝ፥ ጥርሴስ አመሉ ነው። ኧረ ጉዳ፥ ባላ ገደለ በጎራዳ። ከሀብታም ተወለድ፤ ወይ ከአለው ተጠጋ። ከኀይለኛ፥ ይሻላል ትዕግሥተኛ። ከሃዱ፥ ያጎረሠውን እጅ ይነክሳል። ከሀገር ተስፋ፤ ውሃ ጠፋ። ከሆደ የሚማከር፥ በአባት አገር አይቀበር። ከሆድ ያኖሩት ያድናል፥ የተናገሩት ያስገድላል። ከሆድ የመጣን ትፋት፥ የጥርስ መግጠም አያድነውም። ከሆድ የገባውን፥ የእናት ልጅ እን኱ አያገኘውም። ከኋላ ጸጸት፥ ፊት መጠንቀቅ። ከለመደበት የተጋባበት። (ከለመደበት ~ ከለማበት) ከለማበት የተጋባበት። ከለማኝ ለማኝ፥ ቁረንጮዬን ቀማኝ። (ቁረንጮዬን ~ ቆሮንጮዬን) ከለከርሞ ድሮ፥ እንቁላል ዗ንድሮ። ከሉቃውንት ሉቅ:_ የሰማዩን በመጣፍ፥ የምድሩን በአፍ የሚያውቅ። ከሉጥ ሙጣጭ፥ ትንሽ እንጀራ ጋግር። ከላለ ባለቤት፤ አይረዳም ጎረቤት። ከላለ ባካፋ፥ የለኝም ተስፋ። ከላም የዋለ በሬ፥ ከሴት የዋለ ገበሬ። ከላም የዋለ በሬ፥ ከጋለሞታ የዋለ ገበሬ። ከላይ እንዳያፈስ፥ ከታች እንዳይተነፍስ። ከላባ ላባ ቢሰርቀው፥ ምን ይደንቀው። ከል የገባ አይነጣ፥ ክልል የገባ አይወጣ። ከልብ ከሞላ፥ በአፍ ይተርፋል። ከላይ ከደፈረሰ፥ ከታች አይጠራም። (ከደፈረሰ ~ ካልደፈረሰ) ከላይኛው መቀመጫ አትቀመጥ። ከልብ ከአለቀሱ፤ ነጻ ምርጫ ይካኼዳል። ከልብ ከአለቀሱ፥ እንባ አይገድም። ከልጄ ሆዳ፤ ከባዕድ ዗መዳ። ከልጅ አትጫወት፥ ንፍጥ ይለቀልቅሀል። ከልጅ አትጫወት፥ ያወጣሀል በዕንጨት። (ያወጣሀል ~ ይወጋሀል) ከልጅ ልጅ ቢለዩ፥ ዓመትም አይቆዩ። ከልጅ ጋር አትጫወት፥ አይንህን ያወጣዋል በዕንጨት። ከልጅ ክፉ ዱቃላ፤ ከልብስ መጥፎ ነጠላ። ከሕመሜ ይበልጥ፥ መርፌው ጎዳኝ። ከኅዳር ዝናብ፥ የኅዳር አንበጣ (ይሻላል)። ከሕፃን አይዋዋሉ፤ ከጠላት አይበሉ። ከሕፃን ጋር አትብላ፥ ድንች ድንቹን ይለቅምብሀል። ከሆነ ወዱያ፥ ንዳት ለሽበት። ከመሀል አይደርስ፤ ከዳር አይመለስ። (አይመለስ ~ አይመልስ) ከመሀል ደርሶ አይደርስ፤ ከዳር አይመለስ። (አይመለስ ~ አይመልስ) ከመሆን ፋቂ፥ ይሻላል ነጣቂ። ከመሃይም ጎረምሳ፤ የተማረ ሽማግላ ይሻላል። ከመሃይም(ን) ጎረምሳ፤ የተማረ አሮጌ። ከመላሰኛ፥ ድዳ ታድል ተፈጥሮአል። ከመልከኛ ዳኛ፤ መልካም ፈራጅ። ከመልካም ሽቶ፥ መልካም ስም ይሻላል። ከመልካም ሽቱ፥ መልካም ስም ይበልጣል። ከመልካም ጠላ ክፉ ጠጅ፤ ከመልካም ጎረቤት ክፉ ልጅ። ከመመላለስ፥ ይሻላል ማረስ። ከመመራመር፥ ይገኛል ቁም ነገር። ከመመርመር፥ ይገኛል ነገር። ከመማር መነገድ። ከመመስከር ማስመስከር። ከመምህሩ ደቀ መዝሙሩ። ከመሞቱ ያሟሟቱ። ከመሞት (ይሻላል) መሰንበት። ከመሠረት አትጣላ ለጥንት እንዱሆንህ፤ ከግርግዳ አትፋቀር ተንድ እንዳይጫንህ። ከመሠረት ጋር አትጣላ፥ ለኹል ጊዛ ይሆንልሀል። ካብ ጋ አትጠጋ፥ እላይህ ላይ ይፈርሳል። ከመረቁ አውጡልኝ፥ ከሥጋው ጦመኛ ነኝ። ከመሬት የወደቀ ሥጋ፥ አፈር ሳይዝ አይነሣም። ከመርመር፥ ይገኛል ነገር። ከመሮጥ ማንጋጠጥ (ይሻላል)። ከመሮጥ ወደ እግዙአብሔር ማንጋጠጥ። ከመሸም፥ ጋዝ አለ። ከመሳሳም፥ ዝምድና ይቀራል። ከመቀመጥ መኼድ፤ ከመሞት መሰንበት። ከመቀመጥ መቀላወጥ። ከመቀመጥ፥ በእግሬ መኼድ እወዳለኹ። ከመቃለል መጠቃለል። (መጠቃለል ~ ማጠቃለል) ከመቅረት፥ ማዝገም ይሻላል። ከመቅናት መፍታት፤ ከመፍታት አለማግባት። ከመቆም መቀመጥ፤ ከመቀመጥ ማላመጥ። ከመቆም መቀመጥ፥ ከመቀመጥም መተኛት ይሻላል። ከመቆም መቀመጥ ይሻላል፥ ከመቀመጥም መተኛት ይሻላል። ከመታማት ይሻላል መሥራት። ከመታገል መታደል። ከመቶ ቅል፤ አንድ እርኮት። (እርኮት ~ አርኮት) ከመቶ ውሸት፤ አንድ እውነት። ከመቶ ኀምሳ ዳዊት፥ የልብ ቅንነት (ይጠቅማል)። ከመቸገር፥ ለእግዛር መንገር። ከመቸገር፥ ሰርቆ ማደር። ከመነሻው መድረሻው ይታወቃል። ከመነቃቀፍ፥ ይሻላል መተቃቀፍ። ከመነኮሰች ባሰች፤ ከቆረበች አፈረሰች። ከመነኮሰች ባሰች፤ ከተተኮሰች አነከሰች። ከመናገሩ ይሻላል፥ ጦም ማደሩ። ከመናገር ማዳመጥ፤ ከመዋጥ ማላመጥ። ከመናገር፥ ደጃዝማችነት ይቀራል። ከመናፍቅ ትር጑ሜ፤ ከትንባሆ ልምላሜ። ከመነኰሴ ቤት ሥሥት፤ ከሸማኔ ቤት ቁቲት። (ቁቲት ~ ቁጢት) ከመነኮሰች ባሰች። ከመንታ ቅርንጫፍ የተንጠለጠለች ወፍ፥ ኹለት ክንፏን ትነደፍ። ከመንቻካ ተሰናባች፤ ደኅና ከዳተኛ ይሻላል። ከመንታ የተንጠለጠለች ወፍ፥ ኹለት ክንፏን ትነደፍ። ከመንደር አደባባይ፤ ከነጋሪት ደባይ። ከመንግሥት አመልጣለኹ፥ ከሞት እድናለኹ ማለት ዗በት። ከመንግሥት፥ ልብ ያዚል። ከመወለድ መዚመድ፥ ከመዚመድ መላመድ። ከመዋረድ፥ ጌታን መውደድ። ከመውለደ በፊት ሸመገለ። ከመውለድ ሰነፍ፤ ይሻላል መጨንገፍ። ከመውደቅ በፊት መጠንቀቅ፥ ከሞት በፊት ጽድቅ። ከመውጣቱ ዓለምን፥ ዝሮ መምጣቱ። ከመደብደብ፥ ይሻላል ማደብ። ከመድረሷ፥ ጎመን መቀንጠሷ። ከመጋደም መጋደል። ከመግፋት፥ ይሻላል መገፋት። ከመጠምጠም፥ መማር ይቅደም። ከመጠን በላይ ሣቅ፥ ልብ ያደርቅ። ከመጠን በላይ ደግነት፥ ሙልጭ ያስወጣል። ከመጣ ምጣቱ፤ ከወረደ መዓቱ ያድነን። ከመጣሽ፥ ማርያም ታምጣሽ። ከመጣህ፥ ኀ዗ን ልንገርህ። ከመጣፍ ይበልጣል፤ የመምር አፍ። ከመጥፎ የተጋባ፤ ገደል ገባ። ከመጫን ከመተብተብ፥ ምናለኝ መሸከም። ከመጫን ከመተብተብ፥ ይሻላል መሸከም። ከሚለፈልፍ ጎበዝ፥ ዝምተኛ ፈሪ ይበልጣል። ከሚስቱ ጋር የቆረበ፥ ከእግዙአብሔር ተማከረ። ከሚስቱ ጋር የቆረበ፥ ከእግዛር የተማከረ። ከሚበጀው የሚፈጀው። ከሚያስፈልገው በላይ የሚለማመጥህ፥ ሉያታልልህ ወይም ሉገድልህ። ከማርከኝ፥ ሞቴን አታሳየኝ። ከማሽላ ገንጠል፤ ከአገዳ ጠልጠል። ከማሽላ ቢያስወጧት፥ ከ዗ንጋዳ ገባች። ከማትረባ ጉልበት፥ በሕግ አምላክ ይሻላል። ከማን ጋር እንደምትውል ንገረኝ፥ አንተ ማን እንደሆንክ እነግርሀለኹ። ከማያውቁት መልአክ፥ የሚያውቁት ሰይጣን ይሻላል። ከማያውቁት መልአክ፥ ያወቁት ሰይጣን ይሻላል። ከማያውቁት መንፈስ ቅደስ፥ የሚያውቁት ሰይጣን ይሻላል። ከማያውቁት ወዳጅ፥ የሚያቁት ጠላት ይሻላል። ከማይም ጎረምሳ፤ የተማረ ሽማግላ ይሻላል። ከማይረባ ቁርስ፥ የጠዋት ፀሓይ ይሻላል። ከማይረባ ጉልበት፥ እዩልኝ ስሙልኝ ይሻላል። ከማይራገጥ ወተቱን፤ ከማይናገር ከብቱን። ከማይችለው አይድረስ። ከማይሰማህ ደብር አትማለል፤ ከአቅምህ በላይ አትዝለል። ከማይረባ ልላ፤ ወደል ውሻ ይሻላል። ከማይናገር ከብቱን፤ ከማይራገጥ ወተቱን። ከማይጠቅም ኑሮ፥ መቃብር ይሻላል። ከማደር ማስተዳደር። ከማጠቢያ ዅሉ ሳሙና፥ ከሥራ ዅሉ ትሕትና። (ከሥራ ~ ከምግባር) ከሜዳ ወዱያ ፈረስ፤ ከአርባ ወዱያ ቄስ። ከምርት ላይ ከታሰረ ወፍ፤ ከጭራሮ የሚዚለል ድንቢጥ። ከምኔው ሞትሽና፥ አፈር አፈር ሸተትሽ። ከምሳ የለዩት ደብተራ፤ ከውቅር ይገባ። ከምሳ የለዩት ደብተራ፤ ውቅር ይሠራ። ከምሳ የተለየ ደብተራ፥ ያደርጋል ሤራ። ከምን ላይ፥ ቁመሽ እግዛርን ታሚያለሽ። ከምክር የለዩት ደብተራ፤ ነገር ይሠራ። ከምድር አብሶ፥ ከሰማይ ዳብሶ ሳይሰጥ። ከምድር፥ አይሰጡም ስንዝር። ከምድር አደላድል ለአህያ፥ ከቡላድ አደላድል ከቋያ። ከምድር ውስጥ፥ ልቃቂት አይወጣም። ከሞተ ንጉሥ፤ የቆመ ባላምበራስ። (ባላምበራስ ~ አምባራስ) ከሞተ አቴተ፤ ምን አለኝ ከአማቴ። ከሞተ አንበሳ፥ ያለ እንሰሳ። ከሞተ ወዱያ ማልቀስ፥ ድንጋይ(ን) መንከስ። ከሞተ ደጃዝማች፤ የቆመ ባላምባራስ። ከሞተ፥ ድመት ይገማ። ከሞተች ሚስቴ፥ ምን አለኝ ከአማቴ?( ሚስቴ ~ ምሽቴ) ከሞተች እቴቴ፥ ምን አለኝ ከአማቴ? ከሞቱ በኋላ መድኀኒት፤ ከአረጁ በኋላ አቤት አቤት። ከሞቱ በኋላ ማልቀስ፥ ድንጋይ መንከስ። ከሞቱ አሟሟቱ። ከሞት ቀጥል፤ ማጣት በደለኝ። ከሞት ወዱያ ሀኪም አይጠየቅም። ከሞት የተረፈ፤ ከጥላ ያረፈ። ከሞት የተረፉ፤ ከጥላ ያረፉ። ከሞኝ ሸክም፥ ሞፈር ቀንበር ይቆረጥለታል። (ይቆረጥለታል ~ ይቆረጥበታል) ከሞኝ ትከሻ ወይን ይለቀማል። ከሞኝ ክብረት፤ የብልኅ ድህነት። ከሞኝ ደጃፍ፥ ሞፈር ይቆረጣል። (ደጃፍ ~ ደጅ) ከሞኝ ጋር ከመናገር፥ ከብልኅ ጋር መቸገር። ከሠላሳ ምላስ የወጣ፤ ከሠላሳ ደጃፍ ይደርሳል። ከሠላሳ ብር በቅል፤ አር ያሠገረው ይበልጣል። ከሠላሳ ጥርስ የወጣ፥ ከሠላሳ በር ደርሶ ያድራል። (በር ~ ደጅ) ከሰማ የነበረ፤ ከአለቀሰ የቀበረ። ከሠሪው አሠሪው። ከሰቀላ ወደ ጥላ። ከሣቅ በፊት ፈገግታ፤ ከ዗ፈን በፊት እስክስታ። ከሥሥታም አንድ ያንቀው፥ አንድ ይወድቀው። ከሥሥታም፥ አንድ ይወድቀው፥ አንድ ያንቀው። ከሥሥታም፥ አፈር ይጠግባል። ከሥሩ የተነቀለ ወይራ፥ አለ ብል የተረታ ባላጋራ። ከሥራ ክፉ፥ መኪና ግፉ። (አራድኛ) ከሥብ፥ ስም ይሸታል። ከሥጋ ብስና፤ ጎመን በጤና። ከሥጋው ጦመኛ ነኝ፥ ከመረቁ አውጡልኝ። ከሶ ነገር ያጣ፤ ቀብቅቦ ዗ር ያጣ። ከሦስት ዱግሪ፤ አንድ ግሮሠሪ። ከረኃብ ጦር ይሻላል። ከረጅም ጋር ሲኼድ የዋለ አጭር፥ ሲያቃስት አደረ። ከረጠበው ላይ ሸናችበት። ከሩቁ በቅርቡ፤ ከደረቁ በርጥቡ። ከሩቅ ዗መድ፤ የቅርብ ጎረቤት። ከራሳቸው ይጠፋል፥ መድኀኒታቸው። ከራስ በላይ ነፋስ። ከራስ ወዱያ መስካሪ፤ ከአምላክ ወዱያ ፈጣሪ ከጠጅ ወዱያ አስካሪ። ከራስ ጠጉር እስከ እግር ጥፍር። ከርሞ ጥጃ አድሮ፤ ቃሪያ ታጥቦ ጭቃ። ከርሞም ነገ ነው። ከርስት፥ መልክ ይበልጣል። ከርቀት የሚታይ አህያ፥ በቅል ይመስላል። ከርዚት ክፉ:_ ሱሪ ማጣት፤ ከአካላት ክፉ:_ የሆድ ጂማት። ከርጅናና ከሞት ቢሸሹ፥ አያመልጡ። ከሮጠ፥ ያንጋጠጠ (በለጠ)። ከሰማይ የወረደ፥ ለምድር አይከብደውም። (አይከብደውም ~ አይከብድም) ከሠሩ የማይገኝ፤ ከለፉ የማይሰናኝ። ከሰባት አያት፥ አንድ መከራ የመከረው ይበልጣል። ከሰነበተ፥ እንቁላል በእግሩ ይኼዳል። ከሰነፍ ንጉሥ፥ ብልኅ አገልጋይ ይሻላል። ከሰነፍ ገበሬ ማሳ፥ ሞፈር ይቆረጣል። ከሰው ለስላሳ፤ የራስ አንካሳ። (አንካሳ ~ ከርካሳ) ከሰው መልካም ገበሬ፤ ከእህል መልካም ፍሬ። ከሰው መርጦ ለሹመት፤ ከዕንጨት መርጦ ለታቦት። ከሰው ምቀኛ፤ ይሻላል የእባብ መር዗ኛ። ከሰው ሲያድሩ፥ አንድ ጥፊ ተበልጦ ነው። ከሰው ስሕተት፤ ከብረት ዝገት (አይጠፋም)። ከሰው ቀለብላባ፤ ከመሬት ገብጋባ። ከሰው በፊት ይጠግቧል፤ ከሰው በኋላ ይናገሯል። ከሰው ቡዳ፤ ከከብት ጎዳ። ከሰው ተመርጦ ለሹመት፤ ከዕንጨት ተመርጦ ለታቦት። ከሰው አለኹ ብዬ፤ ከጅብ (ጋር)ተዳብዬ። ከሰው አድር ብዬ፥ ቀረኹ ተታልዬ። ከሰው አገር መልከኛ፤ የአገር ምንደኛ። ከሰው እንደ ረአይት፤ ከዚፍ እንደ በቀልት። ከሰው እንደ ቡዳ፤ ከከብት እንደ ጎዳ። ከሰው ክፉ የሚያማ፥ ከዕንጨት ክፉ ጠማማ። ከሰው ክፉ ደባል፤ ከዕንጨት ክፉ አላል። (አላል ~ ደራል) ከሰው ክፉ ደባል፤ ከጭነት ክፉ አላል። (አላል:_ መጣያ) ከሰው ክፉ ደብተራ፤ ከአውሬ ክፉ ዳሞትራ። ከሰው ክፉ ዱቃላ፤ ከእህል ክፉ ባቄላ፤ ከልብስ ክፉ ነጠላ። ከሰው ያልወሰድከው፥ ምን አለህ? ከሰው ጋር ሲኖሩ ሞኝ ሆኖ፥ አህያን ሲጭኑ ሦስት ሆኖ። ከሰው ጠማማ፤ ከጎመን ሳማ። ከሰው ጥፋት፥ ከዕንጨት ንቅ዗ት አይጠፋም። ከሰው ፊት አይበሉ፥ ሥጋን አይበድሉ። ከሰው ፊት፥ ውሃ በወንፊት። ከሰግዳዳ ቦታ፤ ታዳጊ ጌታ። ከሰጡህ አትለፍ፤ በሰጡህ አትስነፍ። ከሰጡህ አትለፍ፤ ከአልሰጡህ አትስነፍ። ከሰጪ ድሀ፥ ተቀባዩ ባሰ። ከሰጪው አስጪው። ከሰጭ አሰጭ፥ ከሰቀላ ወደ ጥላ። ከሰጭው አሳጭው። ከሱሪ የተሸሸገ ብልት፤ እንቅልፍ የላለበት ላሉት። ከሳልስትና ይሻላል ትናንትና። ከሳሽ ከእሳት ጠባሽ። ከሳሽ፥ የተከሳሽን ልብ ቢያውቀው፥ ከቤቱ አይነሣም ነበር። ከሳሽ፥ የተከሳሽን ልብ ቢያውቅ፥ ከቤቱም አይነሣ። ከሳሽ፥ የተከሳሽን ልብ ቢያውቅ፥ ከቤቱም አይነሣ (ነበር)። (አይነሣ ~ ባልተነሣ) ከሳሽና ጠባሽ፥ የወደደውን ያሻል። (ያሻል ~ ያሽ) ከሳሽና ተከሳሽ፥ የመረጠን ያሽ። ከሳቱ ወዱያ ይገኛል ምክር፤ ያ ከአመለጠ ይሰበሰባል እግር። ከሴት ሆዳም፥ የአንድ ዓመት በረድ ይሻላል። ከሴት ሆዳም፥ ያመት በረድ ይሻላል። ከሴት መምከር፤ ደግሶ መስከር። ከሴት ብልኅ፤ ከገብረ ጉንዳን ጉልበት አውጣኝ። ከሴት ነገር፤ ከበቅል መደንበር (አይታጣም)። ከሴት፥ አይጠፋም ብልኀት። ከሴት ወይ዗ሮ፤ ከመረቅ ድሮ። ከሴት ወይ዗ሮ፥ ገጣባ አህያ ይሻላል። ከሴት ወይ዗ሮ፥ ገጣባ አህያ ይሻላል፥ ስለምን ሠርቶ ይበላልና። ከሴት የመከረ፤ በሣር ያሰረ። ከሴት ጎበዝ፤ የወንድ ደካማ። ከስቼ ቢያዩኝ፥ ቁግ ለመኑኝ። (ቁግ ~ ጅማት) ከስድብ ክፉ፥ አቅሙን አያውቅ። ከሸማኔ ቤት ቁቲት፥ ከመነኰሴ ቤት ሥሥት አይጠፋም። (ቁቲት ~ ቁጢት) ከሸማኔ ቤት ቁጢት፥ ከመነኰሴ ቤት ዝተት አይጠፋም። ከሸንጎ ቢረታ፥ ሚስቱን ከቤት መታ። ከሸንጎ ቢረታ፥ ከቤት ገብቶ ሚስቱን መታ። ከሹመት ግብዝና፤ ከሕመም ቁምጥና። ከሹመት ክፉ ግብዝና፤ ከበሽታ ክፉ ቁምጥና። ከሹም አይጣሉም፤ ከግንብ አይታገሉም። ከሹም ፊትና፥ ከመጥረቢያ ፊት አይቆሙም። ከሹምና ከእሳት፥ እጅግም ሳይቀርቡ እጅግም ሳይርቁ። ከሺ ልላ፤ አንድ በሬ። ከሺ ልላ፤ አንድ ወሬ። ከሺ መካሪ፥ አንድ ቋጣሪ። ከሺ ምስክር፤ ዋና በከናፍር። ከሺ ምስክር፤ የታቦት እግር። ከሺ ሴት፥ አንድ ወንድ ይበዚል። ከሺ በቅልኛ፤ አንድ ፈረሰኛ። ከሺ ነፍጠኛ፤ አንድ መልከኛ። ከሺ ነፍጠኛ፤ አንድ ወሬኛ። ከሺ አባራሪ፤ አንድ አምራሪ። ከሺ እብለት፤ አንድ እውነት። ከሺ ወሬኛ፤ አንድ ልበኛ። ከሺ ወርዋሪ፤ አንድ መካሪ። ከሺ ወቄት ወርቅ፤ አንድ ወቄት ፍቅር ሥንቅ። ከሺ ወንድ፤ አንድ ሴት ይበዚል። ከሺ ዋስ፥ ራስ ቀራቢ። ከሺ ደብተራ፤ አንድ ቄስ መን጑ላ። ከሺ ደብተራ፤ የቄስ ደንካራ። ከሺ ገበና፤ አንድ ቀጣፊ ልበኛ። ከሽማግላ ምከር፤ ከረጅም ውረር። ከሽማግላ ምከር ከሽበታም፤ ከጎበዝ ውረር ከጉልበታም። ከሽማግላ ምከር፤ ከጉልበታም ውረር። (ከጉልበታም ~ ከጎበዝ) ከሾህ ወጥቶ፥ እጋሬጣ። ከቀሽም ዱፕልማ፥ እግዛር ይስጥልኝ ይሻላል። ከቀበጡ ሞት አይቀርም። ከቀባሪ ወዱያ፥ ማን ያርዳ። ከቀኑ ያለፈ ሥጋ፥ መግማቱ አይቀርም። ከቀናተኛ ሰው፥ ሽሽ እንዳትበላሽ። ከቀዳዳ፥ ይሻላል ጨምዳዳ። ከቀጥቃጭ ያረፈደ፥ ቀጥቃጭነት ለመደ። ከቁመቱ ማጠር፤ የልቡ መጠርጠር። (መጠርጠር ~ መጠጠር) ከቁመትህ ማጠሩ፤ ሆድህ መጠጠሩ። ከቁም የሚጥል፤ ከቅምጥ የሚፈነቅል (ፍርሀት)። ከቁም ድሮ፤ ከሸክላ ማሰሮ። ከቁራ ጋር የዋለች እርግብ፥ ላባዋ ባይጠቁርም ውስጧ ጠቁሮ ትመለሳለች። ከቁርባን ውጭ፥ ክርስትና። ከቁንጫ፥ ለምድ ያወጣል። ከቁንጫ፥ ላጦ ያወጣል። ከቁንጫ መላላጫ። ከቁንጫ፥ መላላጫ ያወጣሉ። (ያወጣሉ ~ ያወጣል) ከቁንጫ ባመልጥ፥ በቡጥጫ። ከቂል አትጫወት፥ አይንህን ያወጣል በዕንጨት። ከቂል ፈገግታ፤ የወዳጅ ቁጣ። ከቂጡ ላይ ቁስል ያለበት ውሻ፥ እንደልቡ አይጮህም። ከቂጥ እከክ፤ ጥፍረ መጥምጥ ይሻላል። ከቃጫ ወዱያ ገመድ፤ ከእናት ወዱያ ዗መድ። ከቆሉበት፥ የጋፉበት የመሰለ። ከቅርብ የወደቀ፥ ከቁስል ይድናል። ከቅበላ ጥጋብ፥ የስቅለት ጦም ማደር ይሻላል። ከቅደሳን አፍ ምሥጋና፤ ከሰማይ ደመና። ከቆብ ላይ ሚድ። ከቆረሰ የጎረሠ። ከቆረበች ባሰች። ከቆረበች አፈረሰች፤ ከመነኮሰች ባሰች። ከቆረጠ አትምከር። ከቆጥ የሰቀለ፤ ከማገር የተንጠለጠለ። ከቆፈሩት ጉድ጑ድ፥ ሳይገቡም አይቀሩ። ከቆፈሩት ጉድ጑ድ፥ ሳይገቡ አይቀሩ(ም)። ከቅርቡ የወደቀ፥ መሰበሩ አልታወቀ። ከቅርብ የወደቀ፥ ከስብራት ይድናል። ከቅርብ የወደቀ፥ ከቁስል ዳነ። ከቋት የሚ዗ገንለት፤ ከምርት የሚነፈግለት አለ። ከበሉ አይቀር እንክት፤ ከገሙ አይቀር ጥንብት። ከበላ ብላ፥ ከሰው አትጣላ። ከበላተኛ መብል ወጣ፥ ከብርቱካንም ውስጥ ጥፍጥ ወጣ። ከበላህ ብላ፥ ከሰው አትጣላ። ከበላዩ የተገፋ፥ እጅግም አይፋፋ። ከበሬ በሮች፤ ከአህዮች አህያ። ከበሬ ፊት መቆፈር። ከበሬ ፊት የምትገኝ ጥጃ፥ የሣር በሽታ ይገላታል። ከበሮ በሰው ላይ ታምሪያለሽ፥ ሲይዙሽ ታደናግሪያለሽ። ከበሮ፥ በሰው እጅ ታምር፥ ሲይዞት ታደናገር። ከበሮ፥ በሰው እጅ ያምር፥ ሲይዙት ያደናግር። ከበሽታ ላይ ችግር፤ መሪ የላለው ዕውር። ከበሽታ ክፉ ቁምጥና፤ ከሹመት ክፉ ግብዝና። ከበሽታው መድኀኒቱ። ከበስመ አቡ የሚገድፉ፤ የቁርባኑን ለፍትሀት የሚደግሙ። ከበረት ያመለጠ ከብት። ከበቀለ ያልተነቀለ፤ ከተነቀለ ያልተተከለ። ከበቀለ ያልተነቀለ። ከበግ ቆዳ የተሠራ መስገጃ አይበቃ አይብቃቃ። ከቡሀቃ መስተዋት፥ ያድንሽ። ከቡቃያየ ሲገባ አፈላማ። ከባለቀትር አትቀታተር፤ ከባለጊዛ አትፎካከር፤ ከነገረኛ አትነጋገር። ከባለቀትር አትቀታተር፤ ከነገረኛ አትነጋገር። (ከባለቀትር ~ ከባለ ጊዛ) ከባለቤቱ (በላይ) የአወቀ፥ ቡዳ ነው። ከባለቤቱ እጅ የዋለ እንቁላል አይሰበርም። ከባለቤቱ የአወቀ ቡዳ ነው። ከባለቤቱ የዋለ እንቁላል አይሰበርም። ከባለቤት የዋለ እንቁላል አይሰበርም። ከባለቤት ወዱያ መስካሪ፤ ከአምላክ ወዱያ ፈጣሪ። ከባለጊዛ አትፎካከር፤ ከነገረኛ አትነጋገር። ከባለጌ መጋባት፥ የጨዋ ልጅ መፋታት። ከባለጌ ክቡር፤ የድሀ ሥልጡን ይሻላል። ከባለጌ ጡጫ፤ ከዳገት ሩጫ (ያድናችኹ)። ከባለጌ ፍቅር፤ የንጉሥ ቁጣ ይሻላል። ከባላገር ንብ፤ የከተማ ዝንብ ትበልጣለች። ከባል በፊት ልጅ ይስጥሽ። ከባለጌ ጡጫ፤ ከዳገት ሩጫ፤ ከዕውር ግልምጫ፤ ከሴት ነገረኛ፤ ከወንድ ቡጢኛ ያድናችኹ። ከባልሽ ባላ ይበልጣል፥ ማይክሮዌቭ አበድሪኝ። ከባልሽ ባላ ይበልጣል፥ ሽሮ አበድሪኝ። ከባልሽ ታረቂ ቢሎት፥ ልመና መሰላት። ከባልሽ ጋር ኹኚ ቢሎት፥ የተለመነች መሰላት። ከባልንጀሮቿ ከፍ ያለች ማሽላ፥ ወይ ለወፍ ወይ ለወንጭፍ። ከባሪያ ጥቁሩ፤ ከነገር አጭሩ። ከባሕር አይቀዳ፤ ለንጉሥ አይረዳ የለም። ከባሕር ወጥታ፥ ጤዚ ላሰች። ከባሕር ጠልቆ፤ ከገደል ወድቆ። ከባለ ቀትር፥ አትቀታተር። ከባቄላ አይጠፋም ዱቃላ፤ ከጠላ አይታጣም አተላ። ከባዕድ ለስላሳ፤ የራስ ከርካሳ። ከባቄላ አይጠፋም ዱቃላ። ከባዕድ እየጎረሥክ ወደ ዗መድህ ዋጥ። ከባዕድ ወደ ዗መድ፤ ከጫካ ወደ መንገድ። ከባዕድ የጠጡት ኮሶ፥ ይወጣል ደም ጎርሦ። ከባዕድ ጋር የበሉት በሶ፥ ይወጣል ደም ጎርሦ። ከባድ ሬሳ ትሆናለች። ከቤተ ቀሉል፤ ቤተ ቆማጣ ይሻላል። ከቤት ድሮ ሲታረድ፥ ከዕዳሪ ቆቅ ይያዚል። ከቤት ድሮ ሲገኝ፥ ከውጪ ቆቅ ይያዚል። ከቤት ድሮ ካለ፥ ከበረሓ ቆቅ ይያዚል። ከቤትህ ረኃብተኛ እያለ ውጭ አውጥተህ አትስጥ። ከብልኅ የሚወጣ ስሕተት ተራራ ያህላል። ከብልኅ ያለ ሞኝነት ተራራ ያህላል። ከብልኅ ጠበቃ፥ ሞኝ ራሱ ያውቃል። ከብልጥ ተበላለጥ፥ ከሞኝ አትበላለጥ፤ ከጠብጣቢ አትሯሯጥ፥ ልብህ እንዳያመልጥ። ከብልጥ አትወዳጅ፤ ከላባ አትዋጃጅ። ከብስል ጠበቃ፥ ሞኝ ለራሱ ያውቃል። ከብርቱ ሯጭ፥ ኤሉ ትቀድማለች። ከብቱን በእግት፤ እጁን በሰንሰለት። ከብት ሰማይ ይከፍት። ከብት ቢወፍር፤ ለልደት ሰው ቢወፍር ለመሬት። ከብት አይቶ ክፉ ማግባት፥ ከብቱ ቢያልቅ ኹለት ጥፋት። ከብት አይቶ፥ ፈፋ ማግባት፤ ከብቱ ቢያልቅ፥ ኹለት ጥፋት። ከብት አይወድም፤ ገደል ሰው አይወደም በደል። ከብት ከተከተተ፤ ጅብ ከአኮተኮተ። ከብት ያለ እረኛ፤ ሕዝብ ያለ ዳኛ። ከብዙ ሀሰት፤ አንድ እውነት (ይበልጣል)። ከብዙ ራስ፥ አንድ ራስ። ከብዙ ሺ፥ ይበልጣል አንድ እሺ። ከብዙ አህዮች፥ አንድ ፈረስ። ከብዙ ጉልበት፥ ጥቂት ብልኀት። (ጥቂት ~ ትንሽ) ከብዙ ጉልበት፤ ጥቂት ብልኀት ይበልጣል። ከብዙ ጸልት፥ የልብ ቅንነት። ከቦሆር እና ከሚዳቋ ማን ይሮጣል ቢለው፥ አሣ ያሙለጨልጫል። ከተመቱ መጠርጠር፤ ከወሰደ አጥር ማጠር። ከተመቱ መጠርጠር፤ ጅብ ከኼደ አጥር ማጠር። ከተመቱ መጠርጠር፤ ጅብ ከወሰደ አጥር ማጠር። ከተመቱ ማንጠራጠር፤ ጅብ ከወሰደ አጥር ማጠር። ከተመቱ ማንጠርጠር፤ ጅብ ከኼደ ማጠር። ከተመቱ ማንጠርጠር፤ ጅብ ከኼደ አጥር ማጠር። ከተመከርሽ ባስሽ፤ ከተቀደስሽ ረከስሽ። ከተማረ የላላ ሰፈር ልጅ፥ በቅርብ ቀን የሞተ የመርካቶ ልጅ ይበልጣል። ከተማረ የተመረመረ። ከተማረ የተመራመረ፤ ከወረወረ ያማከረ። ከተማረ የተመራመረ። ከተሜ አይጦም፥ አይበላ። ከተሟጋች ታራቂ፤ ከአጣቢ አድራቂ። ከተሰቀለ አይወርድ፤ ከተሳለ አይበርድ። ከተሳለ የማይበርድ፤ ከታ዗ለ የማይወርድ። ከተረገመ በቅል፥ የተባረከ አህያ ይሻላል። ከተራራ፥ ሞኝ ያደክማል። ከተራበ ይልቅ፥ ለጠገበ (አዝናለኹ)። ከተቆረበ ይበላዋል፤ ሳይወድቅ ይታገለዋል። ከተባሉ ብየኛ፤ ከተጋደሉ ደመኛ። ከተራበ፥ ለጠገበ አዝናለኹ። ከተራበ አዝናለኹ፥ ለጠገበ ከተባሉ የእኛ፤ ከታገሉት ደመኛ። ከተናገረ እያባራ አፋቸው፤ ከያ዗ አይለቅ ምንቸታቸው። ከተናገረ አያባራ አፋቸው፤ ከያ዗ አይለቅ እጃቸው። ከተናገረው የደገመው። ከተናጋሪ ሰሚ፥ ከሰሚ ተር጑ሚ። ከተናጋሪ፥ ዝምተኛ ያስቆጣል። ከተናጋሪ ዝምተኛ፥ ያስቆጣል ያሥቆጫል። ከተናጋሪው ደጋሚው፤ ከተር጑ሚው ደርጋሚው። ከተንኮለኛ የዋህ አይወጣውም። ከተኛ አንበሳ፤ ዝርዝር ያለ ቀበሮ ይሻላል። ከተወለደበት፥ ያራበት ገነነ። ከተወጉ በኋላ፥ ጋሻ ምከታ። ከተዚመደ፥ የተዋለደ። (የተዋለደ ~ የተወለደ) ከተያዙ ወዱያ ቄስ ጥሩልኝ ማለት። ከተያዙ ወዱያ ቄስ ጥሩልኝ ማለት፤ ላያደላድሉ በሺ ብር ጭነት። ከተያዙ፥ ብዙ ነው መ዗ዙ። ከተጋደሉ ደመኛ፤ ከተማማሉ ማለኛ። ከተጋገዙ፥ ጠላትና፥ ችጋር ባጠገብ አይደርስም። ከተጠራ ውሻ፥ ያልጠሩት ቀን ይፈጥናል። ከታመሙ መክሳት፤ ከአጡ መንጣት። ከተ዗ጋ ቤቴ፤ ከተዳፈነ እሳቱ። (እሳቱ ~ እሳቴ ~ እሳት) ከተዚመደ የተዋደደ። ከታዳጊ ጌታ ሰግደድ፤ ያለ ቦታ። ከታዳጊ ጌታ፤ ሰግዳዳ ቦታ። ከታገልህ፥ አባትህ አይጣልህ። ከታጠቡ እስከ ክንድ፤ ከተጫወቱ እስከ ሆድ። ከታፈሩ እንደ አንበሳ፤ ከተፈሩ እንደ ሬሳ። ከትንሽ በላተኛ፥ ይሻላል ጦመኛ። ከታ዗ለ የማይወርድ፤ ከሞቀ የማይበርድ። ከታ዗ዝህበት አውለሀቸው፥ ጠላት በወሰዳቸው። ከታዳጊ ጌታ፤ ሰዋራ ቦታ። ከትንባሆ ልምላሜ፤ ከመናፍቅ ትር጑ሜ (አይታጣም)። ከቶ ለምን ይሆን? ፈሪ ማጦንጦኑ፥ ቅጠል አይበጠስ ከአልደረሰ ቀኑ። ከነአበሳሽ፥ ማን ይግዚሽ? ከነጂው የተጣላ በሬ፥ ቀንደ ቁርፍርፌ። ከነገረ ቀደሙ፥ ይሻላል አፈ_ገራሙ። ከነገረኛ፥ ላባ ይሻላል። ከነገረኛ ሰው፥ ሥንቅ አይደባልቁ(ም)። ከነገሩ ጦም ዕደሩ። (ዕደሩ ~ ይደሩ) ከነገሩት አያጎርሥ። ከነገር ተው ባይ፥ ከጦር አግባ ባይ። ከነገር እንጃ፤ ከእህል አጃ። ከነገር ክፉ ቁጭት፤ ከአውሬ ክፉ ድርጭት። ከነገር ክፉ ቁጭት፤ ከወፍ አስደንጋጭ ድርጭት። ከነፋስ መውጫ፥ በመፈርጠጫ። ከኑግ የተገኘህ ሰሉጥ፥ አብረህ ተወቀጥ። ከኑግ የተገኘሽ፥ መጭ አብረሽ ተወቀጭ። ከኑግ የተገኘን ሰሉጥ፥ አብረህ ወቀጥ። ከኑግ ጋር የተገኘ ሰሉጥ፥ በጣም ይጣፍጣል። ከኑግ ጋር የተገኘህ ሰሉጥ፥ አብረህ ተወቀጥ። ከንጉሥ ላይ ሰው አይፈርድ፤ ከባሕር ላይ እሳት አይነድ። ከንጉሥ በላይ ሰው አይፈርደ፤ ከባሕር ላይ እሳት አያነደ። ከንጉሥ በላይ ሰው አይፈርድ፤ ከባሕር በላይ እሳት አይነድ። ከንፉግ አንድ ያንቀው፥ አንድ ይወድቀው። ከአህያ ባልነት፤ የፈረስ ውሽማነት። (ውሽማነት ~ ውሽምነት) ከአህያ አፍለኛ፤ የጅብ አሮጌ ይበልጣል። ከአህያ የዋለች ጊደር፥ ፈስ ተምራ ትመጣለች። (ትመጣለች ~ መጣች) ከአህያ የዋለች ጊደር፥ ፈስ ተምራ ትገባለች። (ትገባለች ~ ገባች) ከአህያ (ጋር) ያረፈደ፥ የአህያን አመል ለመደ። ከአህያ የዋለች፥ ሣር መጋጥ ትማራለች። ከአህያ የዋለች ጊደር፥ ለከፋ ጀመረች። ከአለ ከርሞ፤ ድሮ እንቁላል ለ዗ንድሮ። ከአለ ፈጣሪ፥ አሟጠሽ ጋግሪ። ከአለ ፈጣሪ፥ ጨልጠሽ ጋጋሪ። ከአለህ ስጥ፤ ከላለህ እ዗ን። ከአለቀ መቆጠብ፤ ከመሸ መጠብጠብ። ከአለቀ መቆጠብ፤ ከሞተ መንጠብጠብ። ከአለቀሰ አይቀር በደንብ ምታው። ከአለቃና ከጠገራ ፊት ዝር በል። (ትርጉም ነው) ከአለው ተዚመድ፥ ወይም ተወለድ። ከአለፈ ወዱያ ነገር ይቆጫል። ከአለፈ ጌትነት፥ የቆየ ድህነት። ከአላህ አልሆንኹ፥ ከነቢ። ከአላት ከፍላ፥ ኑ ቅመሱ የምትል ናት ተቃመሱ። ከአመሱበት የጋፉበት። ከአማራሪ፥ አባራሪ ይሻላል። ከአማት መኖር፥ መጋማት። ከአምና፥ ይሻላል ዗ንድሮ። ከአምናው ቢሻላት፤ ቁንጣን ገደላት። ከአሟጋች አስታራቂ፤ ከአጣቢ አድራቂ። ከአሰብሽው አልተውሽው። ከአሥር ኤም ኤ፥ አንድ ኤም ዋን። ከአስተዋይ ይልቅ፥ እብድ በጤናው ይኖራል። ከአረጁ መንገድ፤ ከመነኮሱ መውለድ። ከአረጁ፥ አንባር ይዋጁ። ከአረጁ አይበጁ። ከአረጁ አይባጁ። ከአረጁ አፈጁ። ከአረጁ ወዱያ ጎፈሬ፤ አዝመራ የሳተው ገበሬ። ከአረገ዗ች፥ ክታብ ያ዗ች። ከአረገ዗ች ክታብ ያ዗ች፤ ፈሷን ፈስታ ቂጧን ያ዗ች። ከአረጋዊ ምከር፤ ከጉልበታም ውረር። ከአር ላይ የጠገበና፤ ከዕዳ ላይ የከበረ አንድ ነው። ከአር ዗ል፥ ከቅ዗ን። ከአርባ ዓመት አትመክት፤ ከኀምሳ ዓመት አትሟገት፤ ከስልሳ አትድልት። ከአርባ ከአለፉ፥ አይገኝም ቢለፉ። ከአሮጌ ልጅ ወገኛ፤ ከጀግና ልጅ አርበኛ። ከአሽከር ገበየሁ፤ ከነፍጥ ጎበዝአየኹ። ከአቀበት በረድ፤ ከቁልቁለት ዗ንድ። ከአበሳ፥ ትሩፋት አፈሳ። ከአሳጭ፥ መካሪ ይሻላል። ከአሥር ዱግሪ፤ አንድ ግሮሠሪ። ከአሥር ቡልኮ፥ ግማሽ እንጀራ። ከአበደው፥ የአገረገረው ይበዚል። ከአቡ ቁፍር፥ እሸት ተበልቶለት። ከአባቱ የተረፈ፥ ተከሸፈ። ከአባቱ የተረፈ፥ ተጠለፈ። ከአባቱ ፊት የሚናገር ልጅ፥ አፈ ለምጣም ይሆናል። ከአባቱ ፊት የሚናገር፤ አፍ ለምጽ ይሆናል። ከአባት ልጅ አይበልጡ፤ ከሞት አያመልጡ። ከአባያ ቤት እህል፤ ከአይጥ ቤት ብቅል። ከአብሮ አደግህ አትሰደድ። ከአብሮ አደግህ ጋር፥ አብረህ አትሰደድ። ከአብነት ዅሉ ኮሶ፤ ለቤት መቋሚያ ምሰሶ። ከአትክልት መጥፎ ጎመን፤ ከሰው መጥፎ **መን። ከአነጋገር ይፈረዳል፤ ከአያያዝ ይቀደዳል። ከአነጠፈ፥ የተኛ ያውቀዋል። ከአንበሳ መንጋጋ፥ ማን ያወጣል ሥጋ? ከአንበሳ ቤት፥ አይጠፋም አጥንት። ከአንበሳ ቤት፥ አጥንት አይጠፋም። ከአንበሳና ከዝኆን ማን ያሸንፋል ቢለው፥ ከዅሉም ከዅሉም አሣ ሙልጭልጭ ነው አለ። ከአንተ አፍ ወሬ፤ ከዝንጀሮ አፍ ጥሬ። ከአንተ ጋር ጉዝ የማይኼድ፥ አህያ አያጫጭንህ። ከአንቺ የተሻለች ሴት ባላገኝ፥ ላላ እንዳታገቢ ጠብቂኝ። ከአንድ ልጃገረድ ይገኛል፥ ኹለት ዗መድ። ከአንድ ብርቱ፤ (የ)ኹለት መድኀኒቱ። ከአንጀት በላይ ፍቅር፥ እያደር ያቃቅር። ከአንጀት ነው፥ ከአንገት። ከአንጀት ከአለቀሱ፥ እንባ አይገድም። (አይገድም ~ አይቸግርም) ከአንጀት ከአ዗ኑ፤ እንባ አይጠፋም። ከአንገት በላይ ፍቅር፥ እያደር ያቃቅር። ከአከረሩት ይበጠሳል። ከአዋቂ ጠራቂ፤ ከአጣቢ አድራቂ ከኺያጅ ጠያቂ። ከአዋቂ ጠያቂ። ከአዋቂ ጠራቂ፤ ከኺያጅ ጠያቂ። ከአዋቂ ጠያቂ፤ ከጠያቂ አጥባቂ፤ ከአጣቢ አድራቂ። ከአውሬ ክፉ ዗ንድ፤ ከዝናብ ክፉ በረድ። ከአ዗ንሽልኝ ባማርሽልኝ። ከአያያዝ ይቀደዳል፤ ከአነጋገር ይፈረዳል። ከአይን ማየት፤ የልብ ብልኀት። ከአይን ማየት፤ የልብ ዕውቀት። ከአይን የራቀ፥ ከልብ ራቀ። (ራቀ ~ ይርቃል) ከአይን የፈጠነ፤ ከውሃ የቀጠነ (የለም)። ከአይጥ ሸሽቶ ከእባብ፤ ከቤት ወጥቶ ከጠብ። ከአይጥ ቤት፥ ብቅል። ከአይጥ ቤት ብቅል፤ ከውሻ ቤት ጠፍር (አይጠፋም)። ከአድራጊ አስደራጊ፤ ከአስደራጊ አደራራጊ። ከአድራጎቱ፥ በለጠ ቃላቱ። ከአገለገለ ያውደለደለ፤ ከአማከረ ያገለለ። ከአገሩ የወጣ አገሩ እስኪመለስ፥ ቢጭኑት አህያ ሲለጉሙት ፈረስ። (ሲለጉሙት ~ ቢለጉሙት) ከአገሩ የወጣ አገሩ እስኪመለስ፥ ቢጭኑት አህያ ቢጋልቡት ፈረስ። ከአገር ሆድ ይሰፋል። ከአገር ንጉሥ፤ የጎንደር ባላምበራስ። ከአገር ወይና፤ ደጋ ከመኝታ አልጋ። ከአገር ደጋ፤ ከመኝታ አልጋ። ከአገር ደጋ፤ ከመኝታ አልጋ ታላቅ ጸጋ። ከአጉል ብልኀት፥ አርሶ መብላት። ከአጉል ጉልበት፥ በሕግ አምላክ ማለት። ከአጉል ጉልበት፥ እዩልኝ ስሙልኝ ማለት። ከአጉል ጥንቆላ፥ የሰው ልጅ መላ። (የሰው ~ የጨዋ) ከአጋም የተጠጋ ቁልቋል፥ እንዳለቀሰ ይኖራል። ከአጋም የተጠጋ ቁልቋል፥ (዗ላለም) ሲያለቅስ ይኖራል። ከአ጑጑ ዗መድ፤ ቁርጡን ያሳወቀ ዗መድ። ከአጣቢ አድራቂ፤ ከተሟጋች ታራቂ። ከአጣቢ ሳሙና፤ ከምግባር ትሕትና። ከአጤ ቃል በላይ፤ አወቅ አታላይ። ከአጤ ቃል በላይ፤ ዋና አታላይ። ከአጨደ የሰበሰበ። ከአጭር ምከር፤ ከረጅም ውረር። (ከረዥም ~ ከረጅም) ከአፈር ላይ ነፋስ፤ ከአፍ ላይ እስትንፋስ (አያቋርጥም)። ከአፈር በላይ ተንጋል፥ ይህን ማን ተቀብል? ከአጭር ምከር፤ ከኀይለኛ ውረር። ከአፈር በላይ ተንጋል፤ ድሀን ማን ተቀብል። ከአፈርኩ አይመልሰኝ። ከአፍ ከአመለጠ፥ በሺ ፈረስ ቢያባርሩት አይያዝም። ከአፍ ከወጣ፥ አፋፍ (ነው)። ከአፍ ካመለጠ፥ በሺ ፈረስ ቢያባርሩት አይያዝም። (ካመለጠ ~ ያመለጠውን) ከአፍ ወለምታ፤ የእግር ወለምታ ይሻላል። ከአፍ የወደቀ ጥሬ። ከአፍ የወጣ ቃል፥ ከእጅ የወደቀ እንቁላል። ከአፍ የወጣ፥ አፋፍ (ነው)። ከአፍ የወጣ፤ ከልብ የመጣ። ከአፍ የወጣ፤ ከጥርስ የነጣ። ከአፍ ያመለጠውን፥ በሺህ ፈረስ ቢያባርሩት አይያዝም። ከአፍሽ ይለቡልሽ፤ አይግባ ከሆድሽ። ከአፍሽ ያረጉልሽ፥ አይገባስ ከሆድሽ። ከዓመት ልፋት፥ የአንድ ቀን የአይን ጥራት። ከዓመት ልፋት፥ የአንድ ቀን ጥፋት። ከዓመት በሽታ፥ የአንድ ቀን ድንጋጤ። ከእባብ አምልጦ፤ ወደ እፉኝት ሮጦ። ከእባብ እንቁላል፥ እርግብ አይፈለፈልም። ከእናቱ ያደረ እንቁላል አይሰበርም። ከእናቲቱ ሞግዙቱ። ከእናት ልጅ አያበልጡ፤ ከሞት አያመልጡ። ከእናት ቀን ይሻላል። ከእናት ትሻል ሞግዙት። (ትሻል ~ ታቀርብ) ከእናት አትሻል፥ ሞግዙት። ከእናት አጭር፤ የሰው አጭር። ከእናት ወዱያ ዗መድ፤ ከቃጫ ወዱያ ገመድ። ከእናቷ ልጇ ትብስ፥ ባቄላ አሮባት እጅዋን ትልስ። ከእናቷ ጉልበት የደረሰች ልጃገረድ፥ የማትችለው የለም። ከእኔ በላይ፥ አዋቂ ላሣር። ከእኔ ከወሰድሽው፥ ተቀምጠሽ ልበሺው። ከእንጀራው ቆርሶ፤ ከወጡ አጥቅሶ የሚያጎርሥ። ከእንጀራው የለሽ፤ ከወጡ የለሽ እንዱያው በላይነሽ። ከእንግዱው ማቅ፥ ይሻላል። (ከእንግዱው~ ከእንዱያው) ከዕንጨት አጥር፤ የሰው አጥር። ከእኛ ወዱያ ፉጨት፥ አፍ ለማሞጥሞጥ። ከእህል ክፉ ባቄላ፤ ከልብስ ክፉ ነጠላ፤ ከሰው ክፉ ዱቃላ። ከእህል ክፉ አጃ፤ ከሣር መጥፎ ሙጃ፤ ከነገር ክፉ እንጃ። ከእህል ክፉ አጃ፤ ከሣር ክፉ ሙጃ፤ ከነገር ክፉ አንጃ። ከእህል ክፉ አጃ፤ ከነገር ክፉ እንጃ፤ ከሣር ክፉ ሙጃ። ከዕውር ቤት፥ አንድ አይና ብርቅ ነው። ከእውነት መስክሮ ከማስኮነን፤ በሀሰት መስክሮ ማጽደቅ ያጸድቃል። ከእውነት የሚሻል ሀሰት፤ ከመውጋት የሚሻል መሳት። ከእውነት የተሻለ ሀሰት፤ ከመውጋት የተሻለ መሳት። ከዕዳ ገላግለኝ ቢለው፥ ገድል ደበቀው። ከእጄ በጉንጬ (አለች ዝንጀሮ)። ከእጄ በጉንጬ። ከእጅ አይሻል ድማ። ከእግር ነጣ ነጣ፥ ከእጅ ነጣ ነጣ፥ እንዱህ አይደለም ወይ ቁምጥና ሲመጣ። ከእግዙአብሔር ወዱያ ፈጣሪ፤ ከባለቤት ወዱያ መስካሪ። ከእግዙአብሔር ወዱያ ፈጣሪ፤ ከዳኛ ወዱያ መርማሪ። ከእግዛር ወዱያ ፈጣሪ፤ ከባለቤት ወዱያ መስካሪ፤ ከጠጅ ወዱያ አስካሪ። ከእግዛር ወዱያ ፈጣሪ፤ ከአባት ወዱያ መካሪ፤ ከእናት ወዱያ መስካሪ። ከኦና ቤት፤ ኦና ሚስት። ከኦና ቤት፤ ኦና ሴት። ከከበሩ፥ ሰው አይፈሩ። ከከብት እንስት፤ ከሀብት ርስት። ከከተማ ቅሬ፥ ትሻለኝ ያገሬ። ከከተማ ወደ፤ ደር ከአልጋ ወደ ምድር። ከኩተት እስከ ሽበት፤ ከልጅነት እስከ ዕውቀት። ከካህን ይዋደዶል፤ ከላም ይሳደዶል። ከካራ ይፎከፉካል። ከክፉ ልላ፤ ጌታው ኮበለለ(ው)። ከክፉ በቅል፥ የተባረከ አህያ ይሻላል። ከክፉ ባለዕዳ፥ ተልባም አይጎዳ። ከክፉ ባለዕዳ፥ ጎመን ዗ር ተቀበል። ከክፉ ባለዕዳ፥ ጎመን ዗ር ይቀበሎል። ከክፉ ተወልጄ፥ ስፈጭ አደርኩ። ከክፉ ጎረቤት፥ አይሠሩም ደኅና ቤት። ከወሰን ቢያልፉ ይቀሰፉ። ከኹለት ቅርንጫፍ ያረፈች ወፍ፥ ኹለት ክንፏን ትነደፍ። ከኹለት አይነ ደረቅ፤ አንድ አይነ አፋር። ከኹለት አይነ ፍርቅርቅ፤ አንድ አይነ ምሩቅ። ከኹለት ዚፍ የወደቀ። ከኹለት ዚፍ ያለች ወፍ፥ ኹለት ክንፏን ትነደፍ። ከኹለት ዚፍ ያረፈች ወፍ፥ ኹለት ክንፏን ትነደፍ። ከኹለት ያጣ ጎመን። ከኹለት ዱግሪ፤ አንድ ጋሪ። ከኹለት ጥዋ ወተት፥ አንደን ምረጥለት። ከዅሉ ልብ ይበርድ፥ ከዅሉ ልብ ይነድ። ከዅሉ መጣላት፤ ቀባሪ ማጣት። ከሆነ ወዱያ፥ ንዳት መሸበት። ከዅሉ ምን ይጠላል ቢለው፥ ያበደረ ሰው በመንገድ ሲገጥም አለ። ከዅሉ ክፉ፤ የመበለት አራስ። ከዅሉ የሚነጣ ውሃ ነው፥ ከዅሉ የሚጣፍጥ ዋጋ ያላወጡበት ሥጋ ነው። ከዅሉም ምን ይብሳል? የጉልቻ ውሰት፥ የቢላ ደነዝ፥ ከሸንጎ ሲመለስ ከዅሉም ያው ወንድም፥ ቢከፋም ቢበጅም። ከኼደ አይቀር፤ ጥርግ ነው። ከወረወረ የመከረ፤ ከመከረ የሰነ዗ረ። ከወረወረ ያማከረ። ከወረወረ የመከረ። ከወንድ ሆዳም፥ ከልጅ አመዳም ይሰውረን። ከወንድ ፈሪ፤ ከባል አስደፋሪ አድነን። ከወንድሜ ደም አልይበት። ከወንድም ደረቅ፤ ከወጥ መረቅ። ከወደቁ በኋላ፥ መንፈራገጥ መላላጥ። ከወደቁ በኋላ መንፈራፈር፥ ጀርባን መምለጥ ነው። ከወደቁ ወዱያ፥ መንፈራገጥ ለመመለጥ። ከወደቁ ወዱያ፥ መንፈራገጥ መላላጥ። ከወደቁ ወዱያ፥ መንፈራገጥ ወገብ ለመምለጥ። ከወደቁ ወዱያ፥ መንፈራገጥ ወገብን መምለጥ። ከወደደ ወዱያ፥ ገደሉ ሜዳ። ከወዳጅ መሰንበት፥ አንጡ አለማለት። ከወዳጅ የቀደመ፤ ከጠጅ የከረመ። ከወገብ በላይ ታቦት፤ ከወገብ በታች ጣዖት። ከወገብ በላይ ጥጋብ፤ ከወገብ በታች ረኃብ። ከወገብ በታች ጣዖት፤ ከወገብ በላይ ታቦት። ከወገኑ የተለየ አንበጣ፥ ይባላል ፌንጣ። ከወገኑ የተለየ አንበጣ፥ ይሆናል ፌንጣ። ከወገንዎቿ የረ዗መች ማሽላ፥ ወይም ለወፍ ወይም ለወንጭፍ። ከወገኗ የረ዗መች ማሽላ፥ አንድም ለወፍ አንድም ለወንጭፍ። ከወጭት አፍ፤ ከወንጭት አፋፍ። ከወጭት አፍ፤ የወንጭት አፋፍ። ከወፈሩ አያፍሩ። ከወፈሩ:_ ፈጣሪን አይፈሩ፥ ሰውን አያፍሩ። ከዋለች አደረች፥ ከአደረች ለመደች። ከዋናው ግርሻቱ። ከወፈሩ፥ ሰው አይፈሩ። ከውሃ የቀጠነ፤ ከአይን የፈጠነ። ከውሃ ዳር ያለች ንብ፥ ማር አትሠራም። ከውሻና ከዝንጀሮ ማን ይሮጣል ቢለው፥ ጦጣ ዚፍ ይወጣል። ከውትር ውትር፥ ይነሣል በትር። ከዓርብና ሮብ በፊት፥ ይህም ይጹም ክፋ ነገር ከአፍ አያወጡም። ከእሾህ በለስን አይለቅሙም፤ ከደንድርም ወይንን አይቆርጡም። ከዕንጨት መርጦ ለታቦት፤ ከሰው መርጦ ለሹመት። ከእኛ ወዱያ ጎራሽ፥ እህል አበላሽ። ከዕንጨት አጥር፤ የሰው አጭር። ከዕውር ቤት፥ አንድ አይና ሩጦ ገባ። ከዕውር፥ አንድ አይና ሩጦ ገባ። ከዙህ የወደቀን፥ ሬሳ፥ ማን ያንሣ? ከዚር፥ እካህን አለ። ከዚፍ ስንወጣ፥ እንሰፍራለን። (ከዚፍ ~ ተዚፍ) ከዝምታ ያለ ደስታ፤ ከፍቅር ያለ ጨዋታ። ከዝንብ ማር አይገኝም። ከዝንጀሮ ቆንጆ፥ ምን ይመራርጡ?( ይመራርጡ ~ ይመራርጧል) ከዝንጀሮ ቆንጆ፥ አንዶ ውድድሩን አሸነፈች። ከዝንጀሮ ጋሜ፥ ያንበሳ መላጣ። ከየዚ፥ አንደም ሲበዚ። ከይሉኝ አይል አይብ አትብላ፤ አይመረው አይተኩሰው፤ ውጦ ውጦ ይጨርሰው። ከይሉኝ አይል አይብ አትብላ። ከይሉኝ አይል አይብ አትብላ። (ከይበሉኝ ~ ከይሉኝ ) ከደኅና ቢደርሱ፥ ያደርጋል እንደርሱ። ከደስ ደስ፤ ይሻላል ማረስ። ከደረቅ ደር፤ ከጎደጎደ ምድር። ከደባል፥ ሆድ ቁርጠት ይሻላል። ከደብረ ታቦር ወዱያ ክረምት፤ ከድሮ ጩኸት ወዱያ ላት የለም። ከደብረ ታቦር ወዱያ የለ ክረምት፤ ከድሮ ጩኸት ወዱያ የለ ላት። ከደጃዝማች፥ ማን ተሟጋች? ከደግ ተወለድ፥ ወይም ከደግ ተጠጋ። ከደላ መላ። ከዱዳ፥ ላም ንዳ። (ከዱዳ ~ ከድዳ) ከዳቦ፥ ወጥ ጨምረህ ግመጥ። ከዳቦ የተገኘህ ወጥ፥ አብረህ ግመጥ። ከዳቦ የተገኘ ወጥ፥ አብረህ ግመጥ። ከዳኛ ተሟግቶ፤ ላያደማ ተዋግቶ። (ላያደማ ~ ታዱያማ) ከዳኛ የደረሰ፤ ከልቡ የጎረሠ። ከዳኛ ፊት አይተነፍሱ፤ አምዚ ከሰው ፊት አይቆርሱ። ከዳኛ ፊት አይናገሩም ዋዚ፤ ከልጅ ፊት አይቆርሱም አሚዚ። (አሚዚ ~ አምዚ ከዳገት ሩጫ፤ ከባለጌ ጡጫ ሰውረኝ። (ሰውረኝ ~ አድነኝ) ከድስት አፍላል፤ ከቅመም ድንብላል። ከድሀ ቤት ጎመን ሲቀቀል፥ ከበሮ ይመታል። ከድሀ ቤት ጥቅስ፤ ከሀብታም ቤት ጥብስ አይጠፋም። ከድሀ ቤት ሰርግ፥ የባለጠጋ ቤት ኀ዗ን ይደምቃል። ከድሀ ከመበደር፤ ከባለ ፀጋ መለመን። ከድሀ ከመበደር፤ ከባለ ጸጋ መስረቅ ይቀላል። ከድጡ ወደ ማጡ። ከጀመሩ መጨረስ፤ ከአረገደ ማልቀስ። ከጀርባ ሆድ ይሞቃል። ከጀርባ ሆድ ይቀርባል። ከጃጁ፥ አማራቸው ሉቆናጁ። ከጅብ ዋሻ ሲሸሹ፥ እጅብ ዋሻ። ከጅብ የተጠጋ ፈረስ፥ ኋላውን አያይም። ከጅብ ጎሬ ሲሸሹ፥ እጅብ ጎሬ። ከጅብ ጎሬ ሸሽቶ፥ ጅብ ዋሻ። ከጅብ ጎፈሬያም፥ የአንበሳ መላጣ። ከገሙ አይቀር መጠንባት ነው። (መጠንባት ~ ቅርንት) ከገበያ ኺድ ማንቀላፋት፥ በአፋፍ ላይ ኹኖ መንጠራራት። ከገን዗ብ ርስት፤ ከከብት እንስት። ከገን዗ብ ዋና ርስት፤ ከከብት ዋና እንስት። ከገጠር መሪ ጌታ፤ የደብር አቃቢት። ከገጠር ቄስ፤ የደብር እመበለት ትሻላለች። ከገጠር ንብ፤ የከተማ ዝንብ። ከጉሽ አተላ፤ ከዕንጨት ሽበት አይታጣም። ከጌታ ግልምጫ፤ ከዳገት ሩጫ፤ ከባለጌ ጡጫ (ሰውረኝ)። ከጌታህ አትፎካከር፤ ከውሻህ አትቀዳደም። ከጌታህ ጋር አትከራከር፥ ከልጅ ጋር አትማከር። ከጌታው የሚበልጥ አገልጋይ። ከግቡ የተጎዳ፤ ከጥንሥሱ የተቀዳ። ከጎሽ እበት፤ ከዕንጨት ሽበት። ከጎተት እስከ ሽበት፤ ከልጅነት እስከ ዕውቀት። ከጎንደር ንጉሥ፤ የአገር አምባ ራስ። ከጎጃምና ከዳሞት ማናቸው ይልቃል በስፋት? ተወው አየነው ለየነው ታላቁ ዳሞት ነው። ከጠላቱ የሚዋደድ፤ እያደረ ይናደድ። ከጠላቴ እኔ እጠብቃለኹ፥ ከወዳጄ ጠላት አንተ ጠብቀኝ። ከጠላት መሳም፥ የወዳጅ መንከስ። ከጠላት መሳም፥ የወዳጅ መግመጥ ይሻላል። ከጠላት ምክር፥ ፊተኛውን ትተህ፥ ኋለኛውን ያዝ። ከጠላት ስሞሽ፤ የወዳጅ ንክሻ። ከጠላት አሳሳም፥ የጠላት መግመስ ይሻላል። ከጠላት ጉረሥ፥ ወደ ወገንህ ተመለስ። ከጠማኝ ቢሰነብት፥ ባለ ርስት ይሆን ኖሮአል። ከጠንካራ ጦር፤ ጠንካራ ምሽግ። ከጠጅ ወዱያ አስካሪ፤ ከባለቤት ወዱያ መስካሪ ከእግዛር ወዱያ መስካሪ። ከጠጅ ወዱያ አስካሪ፤ ከዋና ወዱያ መስካሪ ከእግዛር ወዱያ ፈጣሪ። ከጡጫ የዳነ፥ በርግጫ። ከጠጅ ወዱያ አስካሪ፤ ከባለቤት ወዱያ መስካሪ። ከጢስ የተቀመጠን፥ ልጅ አትንካው። ከጣልያን ነጻነት፤ ከእግዛር ቁምጥና አይለመንም። ከጤፍ የደቀቀ፤ ከመርፌ የረቀቀ። ከጥላ ያረፈ፤ ከሞት የተረፈ። ከጥላ ያረፉ፤ ከሞት የተረፉ። ከጥቅምት ማለዳ፤ የጊደር ዕዳ። ከጥቅምት ማለዳ፤ ይሻላል የጊደር ዕዳ። ከጥንት እስከ አጥንት። ከጦረኛ ሥንቅ አይደባልቁ። ከጦረኛ ሰው፥ ሥንቅ አይደባልቁም። ከጦጣ የዋለ ጉሬዚ። ከጦጣ የዋለ ጉሬዚ፥ እህል ፈጅቶ ገባ። ከጨለመ ደር፤ ከጎደጎደ ምድር። ከጨረቃ ነጩ፤ ከቡሀ ልጩ። ከጨረቃ የደመቀ፤ ከፀሓይ የሞቀ። ከጨርቅ ነጩ፤ ከበሀ ልጩ። ከጨርቅ ነጩ፤ ከበራ ልጩ። ከጫጩት ፊት፥ ፈንግል አይወራም። ከጭቅጭቁ ከንዝንዙ፥ የላባ ገን዗ብ ምነው ባይገዙ? ከጮማ ብስና፤ ጎመን በጤና። ከጳጳሱ ቄሱ። ከጸደቁ አይቀር፥ ይንጋለሉ(በት)። ከፈሳም ቤት፥ ቅ዗ናም ገባበት። ከፈታኋት ሚስቴ የተወለደ፥ ዅሉም የእኔ ናቸው። ከፈን ኪስ የለውም። ከፈጣሪ የወረደ፥ ለመሬትም አልከበደ። ከፈጣሪ ይበልጣል፤ ቂጥ ጫሪ። ከፊቱ ፍትፍቱ። ከፈጣሪ፥ ሙርጥ ጫሪ። ከፊት ከወጣ ጆሮ፥ በኋላ የወጣ ቀንድ በለጠው። ከፋ፥ ምን ይከፋ? ከፋ ከረፋ። ከፋም ለማም፥ አሩቴን ተወጣኹ። ከፍ ብል ከአንገት፤ ዝቅ ብል ከባት። ከፍላት እጅ ጥልቅ፤ ሙልቅቅ። ከፍታቱ መሻማቱ። ከፍትፍቱ አጉርሡኝ፥ ከመረቁ ጾመኛ ነኝ። ከፍትፍቱ ፊቱ። ከፍትፍቱ አጉርሡኝ። ከፍትፍቱ ፊቱ፤ ከጠላው ማቶቱ። ከፍትፍቱ ፊቱ፤ ከፊቱ ፍትፍቱ። ከፎከረ፥ የጠረጠረ (ይሻላል)። ኩላሉት ከአላየ፥ አይን አያይም። ኩላሉት ያጤሰው፤ ልቦና ያሰበው። ከ዗ላለም ጥናት፥ የአንድ ቀን አይን ጥራት። ከ዗ላለም ፈስ፥ የአንድ ቀን ቅ዗ን ይሻላል። ከ዗መድ ባዳ፤ ከአገር ምድረ በዳ። ከ዗መድ አጠገብ የተዳረች ልጅ፥ ትዳር አትይዝም። ከ዗ራ እስኪይዙ፥ በክርን ይተክዙ። ከ዗ር የሚሰጡ፤ ከአውድማ የሚነፍጉ። ከ዗ር የሚሰጡት አለ፥ ከአውድማ የሚነፍጉት አለ። ከ዗ር የሚሰጡት፤ ከአውድማ የሚነፍጉት። ከ዗ጋኹት ቤቴ፤ ከአዳፈንኹት እሳቴ። ከ዗ፈን፥ ይሻላል ማ዗ን። ከዙሁ ብሶ፥ አጎንብሶ። ኩላሉት ያጨሰውን፥ ልብ ያመላለሰውን መርምሮ የሚያውቅ የለም። ኩሎን ተ኱ኩላ፥ ትመስላለች ድኩላ። ኩሩ ሰው አይሸሽም፥ አይዋሽም፥ ቢሸሽም አያመልጥም። ኩራት ለጎንደሬ፤ ዕድር ለበጌምድሬ። ኩራት ራት (ነው)። ኩራት፥ አይሆን ራት። ኩራትና ሀብት አይገኙም አንድነት። ኩራትና ድህነት ይኖራሉ አንድነት። ኩር ኩር አለ አህያ፥ በቅል ለመጥራት የሚባል? ኩሸት ያማራት፥ ወታደር ታገባለች። ኩበት ሰማይ ይከፍት። ኩት አትበሉኝ፥ የሹም ድሮ ነኝ። ኩይሳ ቢያድግ፤ እቦታው ይወድቅ። ካህን በንጉሥ ቀኝ ይቀመጣል። ካህን ቢመንን፥ ከርስቱ ይለምን። ካህንና ሽመላ፥ ያል዗ራውን ይበላ። ካለ መናገር፥ ደጃዝማችነት ይቀራል። (ይቀራል ~ ይቀር) ካለ መናገር፥ ደጃዝማችነት። ካለ ማስተዋል የተነሣ፥ ይመጣል አበሳ። ካለ ሥራው፥ ምን አገባው? ካለ ሥራዎ፥ ምን አገባዎ? ካለ ሥንቅ መንገድ፥ ካለ ገን዗ብ ንግድ። ካለ አባት፥ ድሮ ባ጑ት። ካለ ፊቱ አይቆርሱ፤ ካለርስት አይወርሱ። ካላስተዋሉ፥ አይገኝ ዅሉ። ካለ ጑ደኛ መጋፋት፥ ከንቱ ልፋት። ካላረሱ አይጎርሡ፤ ካልፈተሉ አይለብሱ። ካላረፉ፥ መከራ ነው ትርፉ። ካላበበ አያፈራ፤ ካልሰማ አያወራ። ካላወቀ ዗ዳ፥ በለው በጎራዳ። ካላወቁት መንፈስ ቅደስ፥ ያወቁት ሰይጣን። ካላዋቂ ቤት፥ እንግዳ ይዋኝበታል። ካላዩ አያሳዩ። ካላዩ አይቆጩ፤ ካልሰሙ አይበሳጩ። ካላየ አይቆጭ፤ ካልሰማ አይበሳጭ። ካላዩ አይነድ፤ ካልሰሙ አይቆጭ። ካላዩም አይነድ፤ ከአልሰሙም አይቆጭ። ካላጎነበሱ አይረገጡ። ካላጡት አውሬ፥ ነብር አደን። ካልሠሩ በጣም፥ ገን዗ብ አይመጣም። ካልሠሩ፥ አይገኝ መከሩ። ካልለቀሙ ~ ካላረሙ በሠኔ የገለገለ፤ ለአማቱ ያገለገለ። ካልሠሩ፥ አይገኝ(ም) ብሩ። ካልሰጡ አይሰደቡም። ካልረባ ጎበዝ፥ ይሻላል ቀበሮ፥ ግልገል ያመጣል ተራራ ዝሮ። ካልቀመሰ፥ የቀመሰ ባሰ። ካልሰጡ አይጸድቁ፤ ከአልተማሩ አያውቁ። ካልረባ አዝማሪ፥ ጥሬ ቃሚ ይሻላል። ካልረባ ጉልበት፥ እዩልኝ ስሙልኝ ማለት። ካልረባ ግብር፥ ይሻላል ጦም አዳር። ካልቀመሰ፥ የደገመ(ው) ባሰ። ካልቀበጡ አይ዗ሉ፤ ካል዗ለሉ አይሰበሩ። ካልበሉ ሬሳ፤ ካልለበሱ እንስሳ። ካልበሉበት ደጀ ሰላም፤ ከበሉበት ቤት ነው። ካልተማሩ አያውቁ፤ ከአልመጸወቱ አይጸድቁ። ካልተናገሩ፥ አይከብድም ነገሩ። ካልተናገሩ፥ አይከፈት በሩ። ካልተዋጋ፥ አይገኝም አልጋ። ካልተዋጋኹ፥ አልነግሥም አለ። ካልተገለባበጠ ያራል። ካልታረደ ስባቱ፤ ከአልተሞከረ ብልኀቱ። ካልታረደ አይታይ ስባቱ፤ ከአልተናገረ አይታይ ብልኀቱ። ካልታ዗ልኩ አላምንም፥ አለች ሙሽራ። ካልታጣ ቡሆር፥ ነብር አደና። ካልታጣ እህል፥ ጑ያ ሸመታ። ካልታጣ ገበያ፥ ጑ያ ሸመታ። ካልቸኮሉ፥ እንቁላል ይኼዳል በእግሩ። ካልቸኮሉ፥ ቀስ በቀስ ይገኛል ዅሉ። ካልወደቀ አይሰበር፤ ካልሞተ አይቀበር። ካል዗ለሉ አይሰበሩ። ካልደፈረሰ አይጠራም፤ ካልጠራ አይጠጣም። ካልጠበቁ አይጠይቁ። ካልደፈረሰ አይጠራም። ካልጠየቁ አያውቁ፤ ካላወቁ አይጸድቁ። ካልጠገቡ አይ዗ሉ። ካልጠገቡ አይ዗ሉ፤ ከአል዗ለሉ አይሰበሩ። ካልጠፋ መንገድ ጉራንጉሩን፤ ካልጠፋ ማረፊያ ጢሻውን። (ጢሻውን ~ ዋሻውን) ካልጠፋ ገላ፥ አይን ጥንቆላ። ካልጨከኑ፥ እናት አትቀበርም። ካልፈላ አይገነፍል፤ ካልተጣደ አይበስል። ካሳ በልቶ የከበረ፤ አ጑ት ጠጥቶ የሰከረ። ካራ ከስለቱ፤ ጨዋታ ከእውነቱ። ካራ ያፎከፉካል። ካብ አይገባ ድንጋይ። ካካ እያደረገች፥ ፈስ ገማኝ ትላለች። ክሕደትና እምነት፤ ሸፍጥና እውነት። ክስ በክሱ፤ ሥጋን በኩበት ጠበሱ። ክረምቱን የፈጀ በጋ፤ ዕዳውን የፈጀ ዛጋ። (ክረምቱን ~ ክረምት ~ ክረምትን) ክረምት ሲጠሉት፥ ያከብራል። ክረምት እንደ ግርግዳ፤ በጋ እንደ ተራዳ። ክረምት ከጭቃ፤ በጋ ከግጫ። ክረምትና ልጅ፥ ሲጠሉት ያከብራል። ክረምትና በጋ፤ ቆላና ደጋ። ክረምትና ኮሶ፤ ቤት በምሰሶ። ክረምትና ወላድ፥ ሲጠሉት ያከብራል። ክረምትና ጊዛ፥ የማያወጡት ምሥጢር የለም። ክራር የቅኝቱን ይጫወታል። ክርስትናም እነሣለኹ፤ ፋጡማንም አገባለኹ። (አገባለኹ ~ እወዳለኹ) ክርስትናም እነሣለኹ፤ ፋጡማንም እወዳለኹ። ክርና መርፌ አገኘኹ፤ ጠቃሚ ሰው አጣኹ። ክርክር በመሀላ፥ ይ዗ጋል። ክርና መርፌ፥ ስንደድና ወስፌ። ክርና ነገር በአጭር። ክበድ ላም ያለው፥ ጠረሾ አያንቀው። (ጠረሾ ~ ጥረሾ) ክብረት ከስምረት፤ ነጻነት ከአንድነት ነው። ክብር መስተዋት ነው፥ ይጠብቁት ይሻል። ክብር ከአልሳሳ፤ ድሀ አይኖርም። ክንፉ የተሰበረ አሞራ፥ ከሥሩ የተነቀለ ወይራ። ክንፍ የላለው አሞራ፤ ቀንድ የላለው አውራ። ክክ ነው ልዝብ? ክድ ከመሟገት፤ አምኖ መረታት። ክፉ ሆድ፥ ጌታውን አስገዳይ። ክፉ ለመናገር፤ ቂጣ ለመጋገር። ክፉ ለራሱ፥ ደግ ለራሱ። ክፉ ልማድ፥ ያሰርቃል ከማእድ። ክፉ ልላ፥ ከሰው ፊት ያሳፍራል። ክፉ መልስ፥ ይሰብራል ራስ። ክፉ መንፈስ፥ በሣቅ፥ በስላቅ ይገባል። ክፉ ሰው፥ ለክፉ ቀን ይሆናል። ክፉ ሰው፥ በከንፈሩ ያለቅሳል። ክፉ ሰው ከመሬት፥ በግን ከበረት። ክፉ ሰው፥ ከክፉ ልቡ ክፋትን ያወጣታል። ክፉ ሰው ከፍቶ ያስከፋል፤ አተላ ያስተፋል። ክፉ ሰው፥ ከፍቶ ያከፋል አተላ ያስተፋል። ክፉ ሰውን፤ እመሬት በግን እበረት። ክፉ ሳይናገር፤ ሞት ይፈታል አገር። ክፉ ሴት፤ ጧት ወተት ማታ ሬት። ክፉ ሴት፥ በኑሮ ላይ ከባድ ሬሳ ትሆናለች። ክፉ ሴት፥ ጠዋት ወተት፥ ማታ ሬት። ክፉ ቀን አይምጣ፥ ዗መድ እንዳላጣ። (዗መድ ~ ወዳጅ) ክፉ በሬ ያስቸግራል ለገበሬ፤ ክፉ ገበሬ ያስቸግራል ለበሬ። ክፉ፥ በትር ነው ትርፉ። ክፉ ባይኖር፥ የመልካም ዋጋ አይታወቅም። ክፉ ነገር ለከርስ፤ ክፉ ሥጋ ለጥርስ። ክፉ አሽከር፤ እሰው ቤት ሲደርስ ወደ ኋላ ይቀራል። ክፉ አሽከር፥ ከመንደር ሲደርስ ይቀራል። ክፉ አውሬ አይልመድ፥ ከለመደም አይውለድ። ክፉ እንደ አፉ፤ ዚፍ እንደ ቅርንጫፉ። ክፉ ከማድረጋቸው፥ ክፉ(ን) ማስለመዳቸው። ክፉ የከፋ ዕለት፥ ቢስ የባሰ ዕለት። ክፉ ያስከፋል፤ ጎሽ ያገለግላል። ክፉ ያከፋል፤ ጉሽ ያስገሳል። ክፉ፥ ይነካል በክንፉ። ክፉ ጌታ፥ ከዳገት ያሰግራል። ክፉ ጎረቤት፥ ድሮና ፍየል ያረባል። ክፉ ጎረቤት፥ ገቢውን እንጂ ወጭውን አያይም። ክፉን አይረሱም፥ አይነሡም። ክፉን፥ እስከ ክንፉ። ክፋት እላለበት፥ የለም ኀጢአት። ክፍልህ መቃብር ነው። ኮሶ ለማላጅ፤ ገበያ ላርፋጅ። ኮሶ ለአፍ ይመራል፥ በኋላ ይገድላል። ኮሶ ለአፍ ይመራል፥ በኋላ ጠላት ይገድላል። ኮሶ ላልቀመሰው፥ ይመር አይመስለው። ኮሶ ሲጠጣ ሰቅጥጥ፤ ወተት ሲጠጣ ሸምጥጥ። ኮሶ ሳይመር፥ አያሽር። ኮሶ ያለበት፥ አይ዗ልም ከዳገት። ኮሶ ያነ዗዗ው፤ ሴት አማት የመረ዗ው። ኮሶ፥ በኮሶ ይሞታል። ኹለተኛ ግፌ፦ ጫንቃዬን ተገርፌ፥ ልብሴን መገፈፌ። ኹለተኛ ግፍ፦፤ ልብሴን ይገፍ፥ ጀርባዬን ይገርፍ። ኹለተኛ ጥፋት፥ ቆሞ ማንቀላፋት። ኹለተኛ ጥፋት ፦ ከገበያ ማንቀላፋት፥ በአፋፍ ላይ ኹኖ መንጠራራት። ኹለተኛ ጥፋት፥ ከገበያ ቆሞ ማንቀላፋት። ኹለተኛ ጥፋት፥ ከገበያ ማንቀላፋት። ኹለተኛ፥ ደሞ ለ዗በኛ! ኹለቱ፥ ሺሕዎቹን ያሳድዶቸዋል። ኹለቱን ወንበዳ በአንድ ዗ዳ። ኹለቱን የተመኘ፥ አንደንም አላገኝ። (አንደንም ~ አንድም) ኹለቴ ሰላምታ፥ አንደ ለነገር ነው። ኹለት ሞግዙት ያለው ሕፃን፥ ያለጥርጥር በእሳት ይቃጠላል። ኹለት ሰላምታ፥ አንደ ለነገር ነው። ኹለት ቍና ሰጥቼ፥ አንድ ጥንቅል። ኹለት በትር አይማቱ፤ በኹለት ዳኛ አይሟገቱ። ኹለት ባላ ትከል፥ አንደ ከአንደ ተንጠልጠል። (ሲነቀል ~ ቢነቀል) ኹለት ባላ ትከል፥ አንደ ሲሰበር ባንደ ተንጠልጠል። (ሲሰበር ~ ቢሰበር) ኹለት ብልጥ ኑግ አያደቅ(ም)። ኹለት ነድ ይዝ፥ ወደ ክምር ጠጋ። ኹለት አርጩሜ ያዝ፥ አንደ አስማት አንደ ማርከሻ መድኀኒት። ኹለት አውራ ድሮ በአንድ ቤት አያድርም። ኹለት አይወደ፤ ከመነኰሴ አይወልደ። ኹለት አይወደም፤ ከመነኮሱ አይወልደም። ኹለት አገር አራሽ፥ ለባልንጀራው አውራሽ። ኹለት አፎች ባይናከሱ ይናቀሱ። ኹለት እግር አለኝ ብል፥ ከኹለት ዚፍ አይወጡም። ኹለት እግር አለኝ ተብል፥ ኹለት ዚፍ አይወጣም። ኹለት ወፎች ባይናከሱ ይናቀሱ። ኹለት እግር አለኝ ብል፥ ኹለት ዚፍ አይወጡም። ኹለት እግር አለኝ ብል፥ እኹለት ዚፍ አይወጣም። ኹለት ሆነው የተናገሩት፥ በመሬት የቀበሩት። ኹለት ሞት መጣ ቢለው፥ አንደን ግባ በለው አለ። ኹለት የተመኘ አንድም አላገኘ። ኹለት የወደደ አንድ ያጣል። ኹለት የወደደ አንደን ሳያገኝ ኼደ። ኹለት ያማረው ከአንደ ያጣል። ኹለት ያባረረ አንድም ሳይዝ ቀረ። ኹለት ጉድ጑ድ ያላት አይጥ አትሞትም። ኹለት ጉድ጑ድ ያላት አይጥ አንደን አከራየችው። ኹለት ጊዛ ተናገርህ ከፋህ፥ ኹለት ጊዛ በላህ ተፋህ። ኹለት ጊዛ ነው የድሮ ልደት፥ አንደ በእንቁላል አንደ በጫጩት። ኹለት ጊዛ ይፈርደ፥ ጉድ ይወልደ። ኹለት ጥፉ፥ ከአገር ይጠፉ። ኹለት ጥፉ፥ ከአገር ይጥፉ። (ይጥፉ ~ ይጠፉ) ኹለት ጥፉ፥ ከአገር ጥፉ። ኹል ጊዛ በአሬራ ትበያለሽ ወይ፥ አንዳንድ ጊዛ እን኱ ወጥ አትይሞይ። ኹል ጊዛ ከመደንገጥ፥ አንድ ጊዛ መሸጥ። ኺደ ይሎቸዋል፥ እንሰት ይተክላሉ። ኺዳ ጉበት ቢነሧት፥ ታናሽ ታላቅ ስደደልኝ አለች። ኺዳ ጉበት የነሧት፥ ታናሽ ታላቅ ስደደልኝ አለች። ኺዳ ጉበት የነሧት፥ እቤቷ ኺዳ፥ ታናሽ ታላቅ ስደደልኝ አለች። ኺዳ ጉበት ይነሧታል፤ ታናሽ ታላቅ ላኩልኝ አለች። ኺዳ ጉበት ይነሧታል፤ ታናሽ ታላቅ ስደደልኝ አለች። (ኺዳ ~ ኼዳ) ኺድ አትበለው፤ እንዱኼድ አድርገው። ኺድ አትበለው፤ እንደሚኼድ አርገው። ኺድ እንዳልልህ ቀኑ ገና፥ ግባ እንዳልልህ ሚስቴ ገናና። (ገናና ~ ኀይለኛ) ኺድ ከአገር፤ ኑር ከአገር። ዅሉ በእጄ፥ ዅሉ በደጄ። ዅሉ ቢናገር፥ ማን ይሰማል? ዅሉ ተፈቅድልኛል፥ ዅሉ ግን አይጠቅመኝም። ዅሉ አማረሽን፥ ዱስኮ አታውጧት። ዅሉ አማረሽን፥ ገበያ አታውጧት። ዅሉ አማረኝን፥ ገበያ አታውጣት። ዅሉ አረሰ፥ ማን ይሸምት? ዅሉ አንድ ሳሉ፥ ባለመስማት ተጣሉ። ዅሉ ኼደ ተበተነ፥ እህና እኔ ቀረነ አለ ያ዗ነ። ዅሉ ኼድ ተበተነ፥ እህና እኔ ቀረነ አለ እያ዗ነ። ዅሉ (ሆነ) ቃልቻ፥ ማን ይሸከም ስልቻ? ዅሉ የሚገኝ ከእሱ፥ የሚገኝ የለም ያለእርሱ። ዅሉ ያልፋል፥ እስኪያልፍ ያለፋል። ዅሉ ያልፋል ግን፥ እስኪያልፍ ያለፋል። ዅሉ ያልፋል፥ እውነት ብቻ ይተርፋል። ዅሉም ለሰው፥ ቤዚው ነው። ዅሉም ለራሱ፥ አሪቲ ነው ፈሱ። ዅሉም ለቤቱ ያስባል። ዅሉም ሰው መምሰሉ፥ ባይታይ አመሉ። ዅሉም ሸክሙን፤ ፍቅርም ያዥውን። ዅሉም በየ዗መድህ ቢሉት፥ አክንባል ጋጥ ገባ። (ጋጥ ~ በረት) ዅሉም በየ዗ርህ ቢሉት፥ አከንባል ጋጣ ገባ። ዅሉም ተባብሮ ከፋ። ዅሉም አካል ነው ግን፥ እንደ አይን አይሆንም። ዅሉም ከኋላው፥ ያገኘዋል እንደ ሥራው። ዅሉም ከልኩ አያልፍም። ዅሉም ወንፈሉን፤ ፈታይም ድውሩን። ዅሉም ያልፋል፥ እስኪያልፍ ያለፋል። ዅሉም ያልፋል፥ እስኪያልፍ ያለፋል፤ ድሀ ሞኝ ነው ሞቱን ይመኛል። ዅሉም ያልፋል፤ እውነት ብቻ ይተርፋል። ዅሉም ያልፋል፥ የሚኮርጅም ቢሆን። ዅሉም ያልፋል ግን፥ እስኪያልፍ ያለፋል። ዅሉን ለእኔ አትበል። ዅሉን ቢናገሩት፥ ሆድ ባድ ይቀራል። ዅሉን ቢናገሩት፥ ማን ይሰማል? ዅሉን አውቆ፥ አሣውን እሾህ ከሥጋው ለይቶ። ዅሉን አውቆ፥ አሣውን እሾህ ከሥጋው ለይቶ ይዅን። ዅሉን አይወደ፤ ከመነኮሱ አይወልደ። ወለባ ለሹሩባ። ወላድ ትጮሀለች፤ መሀን ትተኛለች። ወላድና ክረምት፥ ሲጠሉት ያከብር። ወላጇ እያለች፤ አዋላጇ አማጠች። ወልደው ሳያበቁ፥ በሰው ልጅ አይሥቁ። ወልደው ሳይጨርሱ፥ በሰው ልጅ አይሥቁ። ወልደውት ያላሳረፈ፤ ነግድ ያላተረፈ። ወልዳ የገዚው አገር፤ አህያ ያደረችበት ማገር፤ አገሩም አገር አይሆን፤ ማገሩም ማገር አይሆን። ወልድ አይሳምለት፤ ተናግሮ አይሰማለት። ወልድ አይሳምለት፤ ተናግሮ አይሳቅለት። ወልድ አይስም፤ ዗ርቶ አይቅም (የለም)። ወልድ አይስም፤ ዗ርቶ አይከምር የለም። ወልድ የማይሳምለት፤ ተናግሮ የማይሰማለት። ወልጄ አልላክኹ፤ መንኰሼ አልጸደቅኹ። ወረቀትና ሞኝ የያ዗ውን አይለቅም። ወረቱን የተቀማ ነጋዳ፥ ዋግ የመታው ስንዳ (አንድ) ነው። ወራሽ የላለው ባለጸጋ፤ ፍራሽ የላለው አልጋ። ወራት ይገፋል ባቄላ፤ ጠላት ያጠፋል ዱቃላ። ወራጅ ውሃ አይውሰድህ፥ ሟች ሽማግላ አይርገምህ። ወሬ ለጠያቂ፤ ገበጣ ላዋቂ። ወሬ ሲሞቅ፥ እናቴ ባሪያ ናት አለች አሉ። ወሬ ሲነግሩህ፥ መላ ጨምር። ወሬ ሲደራ፥ እናቴ ቡዳ ነች ይመጣል። ወሬ ሲዳራ፥ ራስን መወንጀል ይጀመራል። ወሬ ቢቆለል፥ በአህያ አይጫንም። (ቢቆለል ~ ቢበዚ) ወሬ ቢነግሩህ፥ መላ ጨምር። ወሬ ቢነግርህ፥ አሳብ ጨምር አለ። ወሬ ቢያምርህ በየልላህ። ወሬ ቢያበዙት፥ በአህያ አይጫንም። ወሬ ብነግርህ በሚስጥር፥ መላ ጨምር። ወሬ ታሽቶ አይቆረጠም፤ ነገር ተ዗ግኖ አይቃም። ወሬ ካለ እብለት፤ ቀሚስ ካለ ጥለት አያምርም። ወሬን ከባላገር፤ ጦርነትን ከወታደር። ወሬኛ ሚስት፤ ዗ርዚራ ወንፊት። ወር አይጸድቅ፤ አቦን አይጠምቅ የለም። ወርቁ ቢጠፋ፥ ሚዚኑ አይጠፋ። ወርቁ፥ ከዳኛ ፊት ይቅረብ፤ መጻፉ፥ ከቄስ ፊት ይነበብ። ወርቁን በሚዚን፤ እህሉን በላዳን። ወርቁን ይዝ፥ ሚዚኑን። ወርቅ ለማግኘት፥ ወርቅ ይዝ መነሣት። ወርቅ ለአበደረ፥ አፈር። ወርቅ ለአበደረ ጠጠር፤ እህል ለአበደረ አፈር። ወርቅ ለአንጣሪ፤ በቅል ለሰጋሪ። ወርቅ በእሳት፤ መሬት በጣት። ወርቅ በእሳት ይፈተናል። ወርቅ ቢጠፋ፥ የወርቅ ሚዚን አይጠፋ። ወርቅ የተጫነች አህያ፥ ምሽግ ታፈርሳለች። ወርቅ የተጫነች አህያ፥ የማትገባበት የለም። ወርቅ የያ዗ ሳጥን፥ በወርቅ አልተለበጠም። ወርቅ የያ዗ ሳጥን፥ በወርቅ አይለበጥም። ወርቅ የያ዗ ቀበዝባዚ፥ እህል የያ዗ ፈዚዚ። (ፈዚዚ ~ ፈርዚዚ) ወርቅ የጫነች አህያ ስትገባ፥ የማይፈርስ ግርግዳ የለም። ወርቅ ያለው ቀበዝባዚ፤ እህል ያለው ፈርዚዚ። ወርቅ ይረክሳል፤ መዳብ ይነግሣል። ወርቅና ሰም፤ ፈትልና ቀለም። ወርቅና ጨዋ አስታራቂ ነው። ወርቅና ጨው አስታራቂ ነው። ወርቅን ለማግኘት፥ ወርቅ ይዝ መነሣት። ወርቅን በጭቃ፤ ነብርን በጫንቃ። ወርች አሳልፎ ገራፊ፤ ዳኛ ሳለ ዗ራፊ። (ሳለ ~ ካለ) ወርች የረገጠው፥ እግር አይስተው። ወርውረው ቢስቱት፥ ያልወጉት ይመስለዋል። ወቃሉሞ፥ ያየኛል አግድሞ። ወስፌ መግቢያዋን እንጂ፥ መውጪያዋን አታይም። ወስፌ ሰርቆ ማረሻ ቢተኩ፥ ልብ አይሞላም። ወስፌ ሲለግም፥ ቅቤ አይወጋም። ወስፌ ቢሰበሰብ፥ ማረሻ አይሆንም። ወስፌ የራሷን ቀዳዳ ሳታይ፥ ለብዙ ሰው ትጠቅማለች። ወስፌ የራሷን ቀዳዳ ሳታይ፥ የላላውን ቀዳዳ ትጠቅማለች። ወስፌ የጠፋው፥ ጋን ይፈነቅላል። ወባና ፍቅር ከአገረሸ ይገድላል። ወተት ለእንቦሳ፤ ሥጋ ለአንበሳ። ወተት ተበድሮ ለእንግዳ፤ ቅቤ ተበድሮ ላቁማዳ። ወተት ተበድሮ ለእንግዳ፤ ፈረስ ተውሶ ለሜዳ። ወተት ያጠጧት ውሻ፥ ቅቤ ሳትቀቡኝ አልኼድም አለች። ወተት ያጣ፥ አሬራ ይጠጣ። ወተት ጠጥቶ ጠላ፤ እግዙሄር ሲጣላ፤ ጠላ ጠጥቶ ወተት፤ የእግዙሄር ስጦታ። ወተቷንም አለቅ፤ ጥጃዬም አይከሳ። ወታደር ሲያረጅ አቃቢ ይሆናል፥ ጋለሞታ ብታረጅ አማጭ ትሆናለች። ወታደር ሲደኸይ፥ ጃኖ ያ዗ወትራል። ወታደር ሲያረጅ፥ አቃቢ ይሆናል። ወታደር ቢበድል፥ ባላገር ይካስ። ወታደር ቢያገኝ ስምንት፤ ቢያጣ ሳምንት። ወታደር ባለቃው፤ ባላገር በጭቃው። ወታደር፥ ዋቶ አደር። ወንዝ ለወንዝ መቀደስ፤ ያረፈ ሰይጣን መቀስቀስ። ወንዝ ለወንዝ ሯጭ፤ የሰው በግ አራጅ። ወንደ ዅሉ፥ ሴት ሆነ። ወንድ ለግርግርታ፤ ጋሻ ለመከታ። ወንድ ሉበላ፤ የሴት ላባ። ወንድ ልጅ ለፈረስ፤ ሴት ልጅ ለበርኖስ። ወንድ ልጅ በበላበት፤ አንበሳ በሰበረበት። ወንድ ልጅ በተሾመበት፤ ሴት ልጅ ባገባችበት። ወንድ ልጅ ተወልድ ከአልሆነ እንደ አባቱ፥ ስጡት አመልማል ይፍተል እንደ እናቱ። ወንድ ልጅ እግር እንጂ፥ ሀገር የለውም። ወንድ ልጅ ከጃን ሜዳ፥ ሴት ልጅ ከመሀል ሜዳ። ወንድ ልጅና ቢላዋ ሥጋ ይወዳል። ወንድ ልጅ፥ አንዳ እንደ አባቱ፥ አንዳ እንደ እናቱ። ወንድ ልጅ፥ አንድ ቀን እንደ አባቱ፥ አንድ ቀን እንደ እናቱ። ወንድ ልጅ፥ አንድ ቀን እንደ እናቱ፥ አንድ ቀን እንደ አባቱ። ወንድ ልጅ እና ቢላዋ፥ ጮማ ይወዳሉ። ወንድ ሲርበው ይተኛል፤ ሴት ሲርባት ታለቅሳለች። ወንድ ባለ በዕለቱ፤ ሴት ባለች በዓመቱ። ወንድ ባለ በዕለት፤ ሴት ባለች በዓመት። ወንድ ተወልድ ከአልሆነ እንደ አባቱ፥ አመልማል ስጡት ይፍተል እንደ እናቱ። (ስጡት ~ ይስጡት) ወንድ እንደ ያዙት ነው። ወንድ ከቤላ፤ ሴት ልጅ ከኬላ። ወንድ ከዋለበት፤ ከብት ከተሰማራበት። ወንድ ወንደ ለሞት፤ ሴት ሴቱ ለድልት። ወንድ ወደሽ፤ ጺሙን ፈርተሽ (እንዳት ይሆናል)? ወንድ የሞተበት፥ ወንድ አይሻገርበት። ወንድ የወለደ፥ እንደ እግዙአብሔር ከበደ። ወንድም ለግርግርታ፤ ጋሻ ለመከታ። ወንድም ወንድሙን አይበልጠው፤ ምላጭ ምላጭን አይቆርጠው። ወንድምና ወጥ፥ ማስፈራሪያ ነው፡። ወንድምን አስቀይሞ ከመጾም፥ ይሻላል ሥጋን መኮምኮም። ወንድና ወደል አህያ አንድ ነው። ወንድና ፍየል ወዳየው ይሮጣል። ወንጌል ያለ ኦሪት፤ ጥምቀት ያለ ግዝረት። ወንጌልን ከተማዋ፤ መስቀልን አላማዋ። ወንጠፍቷን ላትሰጠኝ፤ ድፍድፌን ነገር኱ት። ወንጭፉ ባልነበረ፥ የማሽላ እሸት ደግ ነበረ አለች ወፍ። ወዚም ይገማል ቢለው፥ የነጭ ወሬ ነው አለ። ወዚም ገማ ቢለው፥ የነጭ ወሬ ነው አለው። ወዬው ጉድ፥ ስ኱ርና ብርጉድ። ወዬው ጉድ አይገርምም፥ ጂል ሰው አያሳዝንም። ወየው ጉድ፥ ያሰቡት አይገድ። ወይ ልጅ፤ በማን እጅ አለች ቆማጣ። ወይ መሮጫ ሜዳ፤ ወይ መውጫ ቀዳዳ። ወይ በኮረት፤ ወይ በጸጸት። ወይ ልጅ፤ በማን እጅ። ወይ ባል዗ፈንሽ፥ ከ዗ፈንሽም ባላሳፈርሽ። ወይ ባይ፥ እንደ ጠሪው ነው። ወይ ተሸከመኝ፤ ወይ ግፋ ለደገፋ። ወይ ነድ፤ ወይ ቀንድ። (አለ እናትና ልጅ የናፈቀው ዋርካ) ወይ ንቀፈው፤ ወይ እቀፈው። ወይ ነድ፥ በእሳት ተማግድ። (አለ ያገሬ ገበሬ) ወይ ነድ፥ አለች ስንደድ። ወይ አለማወቅሽ፥ መራቁ አገርሽ። ወይ አበዳሪ፤ ወይ ተበዳሪ ይሞታል። ወይ አታምር፤ ወይ አታፍር። ወይ አገርሽ መራቁ፥ ልቤን አለማወቁ። ወይ አገርሽ መራቁ፥ ልብ አለማወቁ። ወይ አጥፍቶ ይርቋል፤ ወይ አንድድ ይሞቋል። ወይ ከአለው ተወለድ፤ ወይ ከአለው ተዚመድ። ወይ ዗ንድሮ፥ አለች ቀበሮ። ወይ የምድር ሰው፥ እኔ ዗ንድ ሆነህ ባየኸው። (ሆነህ ~ መጥተህ) ወይ የምድር ሰው፥ የሰማዩን ባይቀምሰው። ወይ ይውቀሩት፤ ወይ ይንቀሉት። (መነሻው ለወፍጮ ይመስለኛል = ለሰው) ወይ ጉዳ፥ ላግባሽ አለኝ ነጋዳ። ወይ ጋሻ፥ ቀድሞ ቀረሻ። ወይ ጣዖቱን፤ ወይ ታቦቱን። ወይ ጣጣ፥ ምን ነገር መጣ? ወይ ጣጣ፥ በዙህም አያስወጣ። ወይ ጣጣ፥ ዝሮ መጣ። ወይ ዗ንድሮ፥ አያልቅም ተነግሮ። ወይ የማይሟሽ፤ ወይ የማይሟሽሽ። ወይም አጥፍቶ ይርቋል፥ ወይም አንድድ ይሞቋል። ወይንና ማሕላት ልብን ያስደስታሉ። ወይኖ አረሰው፤ ወይኖ ጎረሠው። ወይኖን ግረፈው፤ ለቡላ እንዱሰማው። ወይኖን ግረፈው፤ ፈንዝን እንዱሰማው። (:_ለአግቦ) ወይ዗ሪትነት፥ የአንድ ቀን ርቀት። ወይፈን ለገራፊ፤ አሣ ለጠላፊ። ወይፈን ለገፋፊ፤ አሣ ለጠላፊ። ወይፈን ሲቦርቅ፥ ድንበር ያፈርሳል። ወይፈን ከአረሰው፤ በሬ ያንከላወሰው። ወይፈን ከአረሰው፤ አባት በሬ የዳሰሰው። ወይፈን ከአረሰው፤ አባት በሬ ያበላሸው። ወደእኔ የመጣውን፥ ወደ ውጭ አላወጣውም። ወደ ዗ማ ቤት መዝለቅ፥ መጥፎ ጠንቅ። ወይፈን ከአሳመረው፥ በሬ ያበላሸው ይሻላል። ወይ዗ሮ ስመኝ፤ ለማያውቁሽ ታጠኝ። (ስለ ቅርናታም ሴት) ወይ዗ሮና ሚድ፤ ገበሬና ምሳር። ወደ ጎሬ መኼድ፥ መጥፎ አካኼድ። ወደሽ ነው ቆማጢት፥ ንጉሥ ትመርቂ። ወደሽ ነው ገጣቢት፥ ንጉሥ ትመርቂ። ወደሽ ከተደፋሽ፥ ቢረግጡሽ አይክፋሽ። ወደሽን ቆማጢት፥ ንጉሥን ታከብሪ። ወደሽን ገጣቢት፥ ንጉሥ ትመርቂ። ወደቀ ሲሉ፥ ተሰበረ (ነው)። ወደቀ ሲሉ፥ ደቀቀ። ወደው አይሥቁ አሉ፥ አበው። ወደው የዋጡት ቅልጥም፥ ከብርንድ ይጥም። (ከብርንድ ~ ከፍርንባ) ወዳጁን የሚበድል፥ ለወንድሙ አይሳሳም። ወዳት ትኼዳለህ? ወደ በለሳ፥ ሰላን የለህምሳ? ወድቀህ ተነሥ የሚለው የለም። ወዳጄ ስለው በለጠኝ፥ ስለቴ ስለው ቆረጠኝ። ወዳጄ ቢጠላኝ፥ ሸክሙ ቀለለኝ። ወዳጅ ለችግር ዕለት። ወዳጅ ሲበዚ፥ ጠላት ይቀንሳል። ወዳጅ ሲከዳ፥ ይቀላል ዕዳ። ወዳጅ ሲያረጅ በደጅ ያልፋል። ወዳጅ ሲጠላ ያረካክሳል። ወዳጅ በአንደበቱ፤ ውሻ በጅራቱ። ወዳጅ ወዳጁን አይከዳም፤ ከጅብ ወዱያ ሆዳም። ወዳጅ ይመጣል ከሩቅ፤ ጠላት ይነሣል ከጉያ። ወዳጅና ሥዕል በሩቅ ያምራል። ወዳጅና ጠላት:_፥ አንድነት ይስሙሀል አንድነት ይጠይቁሀል። ወዳጅህ ማር ቢሆን፥ ጨርሰህ አትላሰው። ወዳጅህ ሲታማ፥ ለእኔ ብለህ ስማ። ወዳጅህ ቢሰክር ይስምሀል፤ ጠላትህ ቢሰክር ይነክስሀል። ወዳጅህን ስታማ፥ እሜዳ ላይ ሆነህ እማ። ወዳጅህን በሰው ፊት አታሳጣው። ወዳጅህን ጥራ ውሻዬን፤ ጠላትህን ጥራ ሚስቴን። ወዳጅህን ጥራ ውሻዬን፤ ጠላትህን ጥራ ምሽቴን። ወዳጇን ብታይ፥ ባሎን ጠላች። ወድ ገባ ውሻ፥ ባለቤቱን አትግባ ይላል። ወገነ ብዙ፤ ኀ዗ነ ብዙ። ወድቀው ይነሣሉ በእጅ፤ ዗ግይተው ይቀበሯል በልጅ። ወድቆ ይነሧል በእጅ፤ ዗ግይቶ ይከብሯል በልጅ። ወድደህ ከተደፋህ፥ ቢረግጡህ አይክፋህ። ወድደው የዋጡት፥ ቅልጥም ከብርንድ ይጥም። ወድ የዋጡት ቅልጥም፥ ከብርንድ ይጥም። ወድ ገባ፥ ልብሱ ዳባ። ወገን ያለው ማንም አይታገለው። ወገኛ ቀበላ፥ ወረዳ (ከፍተኛ) መሆን ያምራታል። ወገኛ፥ በባዳ ምድር ልኹን ይላል ሰርገኛ። ወግ ነው፤ ሲዳሩ ማልቀስ። ወግ አይቀርም ብል፥ ይሸታል እንኩሮ። ወግ አድራሽ ገበሬ፥ ይሞታል በሠኔ። ወግ የጎደለው፥ ከፈን የለውም። ወጠጤ ለወጠጤ፥ ቢመካከሩ እንዳይታረደ። (ቢመካከሩ ~ ቢማከሩ) ወጠጤ ለወጠጤ፥ ቢፈርደ እንዳይታረደ። ወጡ ሳይወጠወጥ፥ ወስከንባዩ ቂጢጥ። (ቂጢጥ ~ ቂጥ ~ ቁጥጥ) ወጡ ሳይወጠወጥ፤ የወስከንባዩ መሯሯጥ። ወጣ ወጣና እንደ ሸንበቆ፥ ተገነደሰ እንደ ሙቀጫ። ወጣት፥ የነብር ጣት። ወጣኹ ልጅ ነኝ፤ ፈላኹ ጠጅ ነኝ። ወጤን አገኘኹት፥ በማማሰያዬ። ወጥ ለእኛ፥ በርበሬ አይደቅልንም እንጂ። ወጥ ሲታጣ፥ ይበላል በደባ። ወጥ ቢጣፍጥ፥ እጅ ያስመጥጥ። ወጥ ያጣ፥ ደባ። ወጥ ያጣ ደባ፤ ልብስ ያጣ ዳባ። ወጥ ያጣ ጎመን፤ አገር ያጣ ስሜን። ወጥ ይሉሻል፥ በርበሬ ነው። ወጥ(ን) ማን፥ ያውቃል? ቀላዋጭ። ወጥቶ አደር፥ ይ጑ዚል ከገደል። ወጥና ዗መድ ማስፈራሪያ ነው። ወጥን ማን ያውቃል? ቢሉ ቀላዋጭ። ወጥን የሚጨርስ መጎራረሥ፤ ሴትን የሚያስመታት መመላለስ። ወጪ ያ዗዗ባት ጥቁር ሴት፥ አንገቷን ትነቀሳለች። ወጭትና ሴት፥ ሲከናነቡ ይሻላል። ወጮ ቢገለብጡት ወጮ። ወፌ ቆመች፥ አልለገመች። ወፍ፥ እንደ አገሯ ትጮሀለች። ወፍ እውሃ ላይ ቆማ፥ አፏን ከፍታ ዝናብ ትለምናለች። ወፍ ከበረረን ይያዚል? እንግዳህ ወዮ ምን ያግዚል? ወፍ ከድንጋይ ላይ አርፋ፥ ፍለጋዋ ጠፋ። ወፍ ዚፍ አይቶ፤ ወታደር ቤት አይቶ አይራመድም ከቶ። ወፍ የሚፈራ፥ ዗ንጋዳ አይ዗ራም። ወፍ ዚፍ አይቶ፤ ወታደር ቤት አይቶ። ወፍ ጠባቂ ቢያደር጑ት፥ ድንጋይ ለቀማ አማራት። ወፍ ጠባቂ ቢያደር጑ት፥ ድንጋይ ለቃሚ ቀጠረች። ወፍ ጠባቂ ቢያደር጑ት፥ ድንጋይ ለቃሚ አገባች። ወፍራም ቢከሳ ይቀጥናል፤ ቀጭን ቢከሳ ይመነምናል። ወፍጮና ሴት መቼም አይሞላለት። ወፍጮው እንደ አ጑ራ መስከረም ዗ለቀ። ዋ ቅል፥ ከአንተ በኋላ ገደል። ዋ ትላለች አሞራ። ዋልድባ ገብቶ፤ ልጩህን ፈልጎ። ዋሱን የሚያወጣ፤ ጢም አያወጣ። ዋስ አያወሳውስ። ዋርሳ አታርክሱ፤ ድንበር አታፍርሱ። ዋርካ በላለበት፥ ብሳናም አድባር ነው። (ብሳናም ~ ብሳናው) ዋስ አይሞግት፤ ቆማጣ አይፈተፍት። ዋስ አይወሳወስ፤ በግ አይናከስ። ዋስ ከአለህ፥ ደቄትክን ለነፋስ አበድረው። ዋስ ያለው ያመልጣል፤ ዋስ የላለው ይሰምጣል። ዋስ ጠርቼ ሹልክ ብዬ ወጣኹ። ዋሽ ቢሉኝ እዋሻለኹ፤ ነፋስ በወጥመድ እይዚለኹ። (እይዚለኹ ~ ይዣለኹ) ዋሽቶ ከማጣላት፥ ዋሽቶ ማስታረቅ ይበልጣል። ዋሾና ሥንቅ እያደር ይቀላል። ዋቢ ተሸሸ፤ ጠላ ከጎሸ። ዋቢ ያለው በአጤ በቅል ይቀመጣል። ዋቢ ያለው ያመልጣል፤ ዋቢ የላለው ይሰምጣል። ዋቢ ያለው ያመልጣል፤ ዋቢ የላለው ይሰጥማል። ዋቢ ያለው ያመልጣል፤ ዋቢ ያጣ ይሰምጣል። ዋቢ ያለው ይወጣል፥ ዋቢ የላለው ይቀጣል። (ይቀጣል ~ ይሰምጣል) ዋና ከቤት፤ ጠበቃ ከደለት። ዋንዚ በልታ፤ ብሳና መረቀች። ዋንጫ በተርታ፤ ሹመት በገበታ። ዋንጫ በገበታ፤ ሹመት በተርታ። ዋዚ፥ ለቁም ነገር ብላቴን ጌታው ነው። ዋዚ ይወ዗ውዚል። ዋዚና ጨዋታ ለባለጌ ባዛቃው ነው። ዋዚና ፈዚዚ የለውም ለዚ። ዋጪው ብላት ትጎርሥበት፤ ተዪው ብላት ትጨምርበት። ውሃ ለሚወስደው ሰው፥ በትርህን እንጂ እጅህን አትስጠው። ውሃ ለቀደመ፤ ግዳይ ለፈለመ። ውሃ ለወሰደው፥ ካሳ አይከፍልም። ውሃ ለወሰደው፥ ፍለጋ የለውም። ውሃ ሉያንስ ሲል ይገማል፥ ሰው ሉያንስ ሲል ይኮራል። ውሃ ላነቀው፤ ባለቤት ላላወቀው መድኀኒት የለውም። ውሃ ልትቀዳ ኺዳ፥ እንስራዋን ረስታ መጣች። ውሃ መልስ፥ ውሃ ቀልስ። ውሃ መመለስ፥ ወደ ላላ ማፍሰስ። ውሃ ምን ያገሳ፤ ድሀ ምን ያነሣ። ውሃ ሲወስድ፥ እያሳሣቀ ነው። ውሃ ሲያልቅ፤ አሣ ያልቅ። ውሃ ሲደርቅ ይሸታል፤ ሰው ሲከዳ ይወሸክታል። ውሃ ሲጎድል ተሻገር፤ ዳኛ ሲገኝ ተናገር። ውሃ ሳለ ጥጋብ፤ በሬዬን ሸጥኹት ብራብ። ውሃ በለ዗ብታ፥ ድንጋይ ይፈነቅላል። ውሃ በብልኀት፥ ይቆላል በእሳት። ውሃ በእሳት፤ ሰሳ በዳገት። ውሃ ቢወቅጡ፥ እንቦጭ። ውሃ ቢወቅጡት፥ መልሶ እንቦጭ ነው። ውሃ ቢወቅጡት፥ እንቦጭ። ውሃ ቢደርቅ፤ አሣ ያልቅ። ውሃ ቢጠቅምህም፥ ማእበሉን አትመኝ። ውሃ ብረት ያጠናል። ውሃ ብቻ አትጠጣ ስለ ሆድህ ሕመም፥ ትንሽ ወይን ጨምር እንጅ። ውሃ አያንቅ፤ አገር አያልቅ። ውሃ እድፍን ያጠራል፤ ትምህርት ልብን ያጠራል። ውሃ ከነቁ፤ አባባ ከአጽቁ። ውሃ ከፈሰሰ፥ አልታፈሰ። ውሃ የሚወስደው ሰው፥ አረፋ ይጨብጣል። ውሃ የናጠና፥ ሴት ያመነ አንድ ነው። ውሃ የጥቅምት ነበርሽ፥ (ታዱያ) ማን ይጠጣሽ። ውሃ የጥቅምት ነበርህ፥ ማን በጠጣህ? ውሃ ጠፍቶ፥ በአረር ይለቀሳል። (አረር:_ድርቅ~ ደረቅ~ ቦና) ውሃ፥ ጭስ(ና)፥ ክፉ ሴት፥ ሰውን ያባርራሉ ከቤት። (ያባርራሉ ~ ያበራሉ) ውሃና ገደል እያሳሣቀ ይወስዳል። ውሃና ጠጅ እኩል ይጠጣሉ። ውሃን መመለስ፥ ወደ ላላ ማፍሰስ። ውሃን ምን ያስጮኸዋል? ድንጋይ። ውሃን የሚያናግረው፤ ድንጋይ ነው። ውሃውም እንዳይደርቅ አሣውም እንዳያልቅ፥ አድርጎ ነው እርቅ። ውሃዬ በቀጠነ፥ ቆልዬ በአረረ (ማሩኝ)። ውለታ እስከ ትዝታ፤ ፍቅር እስከ ዝምታ። ውለታ፥ የልብ ትዝታ። ውላ ከመጣች፤ ነገር አመጣች። ውላ ውላ፥ ባሎ ሲመጣ ትበላ። ውላ ያዋውላል፤ ታን኱ ያሻግራል፤ አቧራ ያስላል። ውል አያናግር፤ የተከዛ ምላት አያሻግር። ውል አያወላውል፤ ምላት አያሻግር። ውል አይፈርስ፤ አይን አይፈስ። ውል ውል ከቤት፥ ኖሮ ኖሮ ከመሬት። (ኖሮ ኖሮ ~ ኑሮ ኑሮ) ውል የበሉት፥ ምል የበሉት አይጠቅምም። (:_አለጊዛው) ውስጡን ለቄስ። ውል የለው ሸንጎ፥ ለፈራጅ ያስቸግራል። ውል ያዋለ፥ ሰንበት ያከበረ። ውል ያዋውላል፤ ታን኱ ያሻግራል፤ (አቧራ ያስላል)። ውል ውል፥ አህያ ለጅብ። ውል ያዋውላል፤ ትንባሆ ያስላል። ውል ያዋውላል። ውረድ ባላ፥ ታች በላ። ውረድ ከማማ፤ ውጣ ከጫማ። ውርርድ ቁም ነገር ይጋርድ። ውርርድ እንደ ጫፉ፤ ዚፍ እንደ ቅርንጫፉ። ውርርድ ከጫፉ፤ አሞራ ከክንፉ። ውርደት ከአር ይገማል። ውርጃ የሚበዚባት ሴት፥ ልጆቿን ውሃ ይወስዳቸዋል። ውሸታም ሰው፥ ማስታወሻው ጣቃ ነው። ውስጡን ሲያጥቡት፥ ላዩ ይጠራል። ውስጥ ውስጡን፤ ድመትም አውሬ ነች። ውረድ ሲዋረድ። ውሸታም፥ ቁም ነገር ቢናገርም ተቀባይነት አያገኝም። ውሸት መልካም ነበር፥ ጣጣው ባልነበር። (መልካም ~ ደግ) ውሸት ተናግረህ፤ እውነትን አግኝ። ውሸት አገር ይፈታል፤ ቅማል ሱሪ ያስፈታል። ውሸት፥ ይዳርጋል ለሞት። ውሸትና ሥንቅ እያደር ይቀላል። ውሸትና ቅራሪ፥ ሽምጥጥ ነው። (ቅራሪ ~ ቅራሬን) ውሻ መጣ፤ ሰው መጣ። ሰው መጣ፤ ነገር መጣ። ውሻ፥ ምሳ በማጣት ያረጃል። ውሻ ፦ ምን አገባሽ በዕርሻ? ውሻ ምን ትበያለሽ? አለ ጌኛ፥ ቢበልግም እላቴን ባይበልግም አንቺን። ውሻ ሳይቸግረው ገበያ ወጥቶ ይደበደባል። ውሻ ሥጋ ክምር፥ የወተት ባሕር፥ አለ ቢሉት ወዳት ነው ሳይጠይቅ መሮጥ ጀመረ። ውሻ ቀንድ ልታወጣ ኺዳ፥ ጆሮዋን ተቆርጣ ተመለሰች። ውሻ በሰፈሩ ጅብ ነው። ውሻ በርግጫ ማለት፥ ዕንካ ሥጋ ማለት ነው። ውሻ በቀደደው፤ ድመት ተከተለች። ውሻ በቀደደው፤ ጅብ ይገባ(ል)። ውሻ በቀደደው፤ ጅብ ገብቶ ለመደው። ውሻ በበላበት ይጮሀል። ውሻ በእግር መምታት፥ እንካ ብል ሥጋን መስጠት። ውሻ በጅራቱ፤ ባሪያ ባንደበቱ። ውሻ ቢመላለስ፥ የልቡን አያደርስ። (ቢመላለስ ~ ሲመላለስ) ውሻ ቢጠራ፥ ቀን ቢቀጥሩ፥ ደረሰ በእግሩ። ውሻ አይበላሽ ጥል። ውሻ አጥንትን የሚቆረጥመው፥ መዋጥ ቢያቅተው። ውሻ እበላበት ይጮሀል። ውሻ እንቅልፉ፥ ከደጃፉ። ውሻ እንዳትጮህብህ፥ ልፋጭ ጣልላት። ውሻ ከሉጥ፤ ጦጣ ከጥጥ። ውሻ ከሸሹለት፤ ልጅ ከሣቁለት፤ ያ አይመለስ ያ አይታገሥ። ውሻ ከሸሹለት፤ ልጅ ከሣቁለት፤ ያም አይመለስ ያም አይታገሥ። ውሻ ከአልቀበጠ፤ ጅብ አይበላውም። ውሻ ከሸሹለት፤ ልጅ ከሣቁለት። ውሻ ወደ ሰርድ፤ አህያ ወደ ሉጥ። ውሻ የለከፈው ገበታ አታድርገን። ውሻ የሚበላውን እንጂ፥ የተቃጣበትን ደላ አያይም። ውሻ ጌታዋን በለጠች። ውሻ ጌታዋን እንጂ፥ የጌታዋን ጌታ አታውቅም። ውሻ ጌታውን እንጂ፥ የጌታውን ጌታ አያውቅም። ውሻህ ምን አገባት ዕርሻ? ውሻም በላው፥ አንቺም በላሽው ካልከደንሽው። ውሻና ውሻ በአጥንት ይጣላል፥ በአውሬ ይስማማል። ውሻና ድመት፥ አይንና አፈር፥ ድሮና ሙጭጭላ፥ ነብርና ፍየል እንዳይስማሙ ሰውና ሰይጣን አይስማሙ። ውሻን በእርግጫ ማለት እንካ ሥጋ ማለት (ነው)። ውሻን በእግር መምታት፥ እንካ ብል ሥጋን መስጠት። ውሽማ ሲቆይ፥ ባል ይሆናል። ውሽማዋን ብታይ፥ ባሎን ጠላች። ውሾች ምንጊዛ ነው የሚናከሱ? ጅብ አባረው ሲመለሱ። ውሾን ያነሣ፥ ውሾ ይኹን። ውቤ በረሓ፥ (በ 3 ቀን) አደረግሽን ድሀ። ውትር ወትር፥ ያነሣል በትር። ውዝፍ ለሹም፤ ጥንብ ለጅብ። ውዳሴ ከንቱን፥ ዝሙት ይልካታል። ውድሽና ውዳ፥ የለቀሙት ስንዳ። ውግ዗ት በኪሴ፥ አለማወቅ በመቅደሴ። ውጣ ከቤት፤ ተነቀል ከመሬት። ውጣ ውጣ ከሚሉት በሬ፤ ድማ ይሻላል። ውጣ ያለው ብር፥ ግርግዳ ሲፍቅ ያድራል። ውጣ ያለው ገን዗ብ፥ ግርግዳ ሲቧጥጥ ያድራል። (ሲቧጥጥ ~ ሲጭር) ውጦ ውጦ ጨረሰው፤ አይመረው አይተኩሰው። ዓለም ሳይፈጠር፤ ፈጣሪ ነበር። ዓለም ተልባ ነው፥ ይሸትብሀል። ዓለም ተልባ ነው፥ ይንሸራተታል። ዓለም አላፊ፤ መልክ ረጋፊ። ዓለም አታላይ፥ እንደ በቅል ኮብላይ። ዓመት ሙሉ የማቀቀ፥ በእናቱ መርድ ተጠናቀቀ። ዓመት በደመወዝ፤ ኹለት ዓመት በወዝ። ዓመት አርሶ አያጎርሥ፤ ዓመት ፈትላ አትለብስ። ዓመት ከማጥናት፤ ከአጠናው መቅዳት። ዓመት አስቦ ለልደት። ዓመት ከማጥናት፥ የአንድ ቀን ያይን ጥራት። ዓመት ዗መን፤ መክሳት መመንመን። ዓመት የማያበላ፥ ዓመት ያጣላ። ዓጸድ የላለው ደብር፤ ጺም የላለው መምህር። ዕርሻ ለአጥማጅ፤ መሬት ለተወላጅ። ዕርሻ ሲሉ፥ ሞፈር ቁረጡ። (ቁረጡ ~ ቆረጣ) ዕርሻ ቢያለሰልሱት እህል ያሳምራል፥ ገን዗ብ ቢያከማቹት ያኮራል። ዕርሻ ቢያርሱ፥ እንደልብ ያጎርሡ። ዕርሻ ያውቋል፥ ያጠብቋል። ዕርሻ ደጉ፥ ሳያደገድጉ። ዕርሻ ጋራ ዝሮ፥ የጎረቤት ድሮ። እርሾው ሲያምር፤ ዳቦው ያምር። ዕርጎ መስልሽ፤ እርሾ ጥልቅ። ዕርጎውን ለውሻ፤ እርሱን ለውርሻ። እርጥብ ሬሳ፤ ደረቁን አስነሣ። ዕቡይ ጉልቻ ልቆት፥ አመድ አጥልቆት ሳለ የሚኮራ ነው። እባብ ለሆደ ሲል በሆደ ይኼዳል። ዕንቁራሪት ዝኆን አህል ብላ፥ ተሰንጥቃ ሞተች። እንቁጣጣሽ፥ የማታ የጋለሞታ። ዕንቅርት በቆላ ይይዚል፥ ደጋ ሲወጣ ይጠፋል ይሟሽሻል። ዕንጨት ሞልቶ፤ ዚቢያ አይገኝበት። ዕንጨት ቢያነደት አመድ፤ ቃጫ ቢፈትሉት ገመድ። ዕንጨት ቢጠርቡት፤ ይቀጥናል ሰው ቢበልጡት ይቀናል። ዕንጨት አይሸከሙ ላመድ፤ አሮጊት አያገቡም ላትወልድ። ዕንጨት አይሸከሙም ላመድ፤ አሮጊት አያገቡም ላትወልድ። ዕንጨት ካልነሡት፥ እሳት አይጠፋም። (ካልነሡት ~ ካልነፈጉት) ዕንጨት ካልነሡት፤ አይጠፋም እሳት። ዕንጨት ኹኖ የማይጨስ፤ ሰው ኹኖ የማይበድል የለም። ዕወቅ ያለው ባርባ ቀኑ ያውቃል፥ አትወቅ ያለው ባርባ ዓመት አያውቅም። ዕወቅ ያለው ባርባ ቀኑ ያውቃል፥ አትወቅ ያለው ባርባ ዗መኑ። ዕውር ምን አይቶ፤ ደንቆሮ ምን ሰምቶ። ዕውር ምን ይሻል? ብርሃን፤ በሽተኛ ምን ይሻል መዳን። ዕውር ምን ይሻል? ብርሃን፤ ነጋዳ ምን ይሻል መድን። ዕውር ሲቀናጣ፥ ምርኩዙን ወርውሮ ይፈልጋል። ዕውር ሲቀናጣ፥ ዗ንጉን ወርውሮ ፍለጋ ይገባል። ዕውር ሲወበራ፥ በትሩን ይጥላል። ዕውር ሲጠግብ፥ ከመሪው ይጣላል። ዕውር ሲወበራ፥ ከመሪው ይጣላ። (ሲወበራ ~ ቢወበራ) ዕውር ሲወበራ፥ በሸማው ላይ አራ። ዕውር ሲጠግብ፥ ዗ንጉን ይወረውር። (ሲጠግብ ~ ቢጠግብ) ዕውር በበዚበት፥ አንድ አይና ይነግሣል። ዕውር በ዗ንጉ፤ ነጋዳ በወርቁ። ዕውር ቢሸፍት፥ ከ጑ሮ አያመልጥ። ዕውር ቢፈርደ፤ ዕውር ይወልደ። ዕውር ዕውርን ቢከተል፥ ተያይ዗ው ገደል። ዕውር ከመሪው፤ ሞኝ ከመካሪው (ይጣላል)። ዕውር ያለበት ደብር፥ አሣ ያለበት ባሕር ሳይበጠበጥ አያድር። ዕውር ይወልደ፤ ዕውር ቢፈርደ። ዕውር፥ ነገ አይንሽ ይበራል ቢሎት፥ ዚሬን እንዳት አድሬ አለች። ዕውር አያፍር፤ ፈሪ አይደፍር። ዕውር፥ አይንህ ነገ ይበራል ቢሉት፥ ዚሬ እንደምን አድሬ አለ። ዕውር አይ዗ም፤ መላጣ ጋሜ አይሠራ። ዕውርን ዕውር ሲከተል፥ ተያይ዗ው ገደል። እውሻ ሆድ፥ ቅቤ አያድርም። ዕውቀት ኀይል ነው፤ ሰላም ጤና ነው። ዕውቀት ከአለህ፥ ጻፍ። ዕውቀት ያኮራል፤ ሥራ ያስከብራል። ዕውቀትና ፍጥረት አንድ ቀን ነው። ዕዳ ለቤት፤ ምሥጢር ለጎረቤት። ዕዳ ልቦና ለጸልት፤ ዕዳ ሰብዕና ለመሥዋዕት። (ሰብዕና~ ለብዕና) ዕዳ ሰርጉ፤ ነውር ማዕረጉ። ዕዳ በድግጣ። ዕዳ ቢያምርህ ዋስትና፤ ኩነኔ ቢያምርህ ግብዝና። ዕዳ አለብኝ ብለህ አትቸገር፤ ዕዳ የለብኝም ብለህ አትከበር፤ አይታወቅም የአምላክ ነገር። ዕዳ ከሜዳ፥ ሲለኝ አደረ። ዕዳ ከፋይ አሉ ባይ፤ ሞት ተቀባይ አዎን ባይ። ዕዳ ወዳጅ መነኰሴ፥ መጻፉን ሸጦ፥ ፍየል ይገዚል። ዕዳሪ ሳያወጣ የበላ፤ ዕዳውን ሳይከፍል ጎታውን የሞላ። ዕዳሪ ያረሰ፥ ለልጁ አጎረሠ። ዕዳና ደም፥ ደብ ዕዳ። ዕዳው ድሮ፤ መጋቢያው ዳወሮ። ዕዳውን ከፍል የከተተ፤ ጌታውን የተሰናበተ። እድለ ቢስ ሲዳር፥ ውሃ ይሞላል በጥር። ዕድሜ ከአላነሰው፥ ጊዛ አለው ለሰው። ዕድሜ የጠገበ፤ ለሞት የቀረበ። ዕድሜ ያልመከረው ሽማግላ፤ ከውሃ የገባ አሞላ። ዕድሜና መስተዋት አይጠገብም። ዕድሜ ያስታርቃል፤ ሙግት ያደርቃል። ዕድሜና ቁረንጮ፥ ተበጣጥሶ ያልቃል። ዕድሜና ጨርቅ፥ ሲበጣጠስ ያልቅ። (ሲበጣጠስ ~ እንደ ምንም) ዕድሜና ጨርቅ፥ በደኅና አያልቅ። ዕድር እስከ በጌምድር። ዕፍኝ ቆል ይ዗ህ፥ ከአሻሮ ተጠጋ። ዚሬ የትላንት ነገ ነበረች፥ ዚሬ ደግሞ የነገ ትላንት ትሆናለች። ዚሬ ጠምቃ፥ ፈጀችው ጠልቃ ጠልቃ። ዚሬም ውስኪ ነገም ውስኪ፥ ተነገ ወዱያ እስኪ። ዚር ልመና፤ ሳይያዙ ገና። ዚር ልመና፤ ሳይያዙ ገና። ከተያዙ፤ ብዙ ነው መ዗ዙ። ዚብ አይጨብጥ፤ ርካብ አይረግጥ። ዚብ የላለው ፈረሰኛ፥ ምሳ የላለው ኮሰኛ። ዚፍ ሲወድቅ ከግንደ፤ ሰው ሲቸገር ከ዗መደ። ዚፍ በላለበት፥ እንቧጮ አድባር ይሆናል። ዚፍ ዝናብ ያስጥላል፥ ትልቅ ሰው ከዕዳ ያስጥላል። ዚፍ የራሱን ፍሬ ያፈራል። ዚፍ ያለቅርንጫፍ አይደምቅም፤ ሰው ያለሰው አይከበርም። ዚፍ ያጣ ጉሬዚ። ዚፍና ወፍ፤ ገደልና አፋፍ። ዚፎች ቢጠፉ፥ ቁጥቋጦች ተሰለፉ። ዚፎች ቢጠፉ ቁጥቋጦች ዚፎች ነን አሉ። ዚፎች አለቁ እና ግራሮች ዚፍ ሆኑ። ዛማ በሃላ፤ ነገር በምሳላ። ዝኆኑ ሳለ ደካውን። ዝሙተኛ ሴት ሰባት ቆብ ታሰፋለች። ዝም ማለት ከሞኝ ያስቆጥራል። ዝም በማለቱ ብልኅ ይመስላል። ዝም ባለ አፍ ዝንብ አይገባበትም። ዝም ብትል፥ ባትከበርም፥ ችላ ትባልበታለህ። ዝም አይነቅዝም። ዝም ያለ ተንኮለኛ ይመስላል፤ እንብላ ያለ ስስታም ይመስላል። ዝምታ ለበግም አልበጃት፥ አሥራ ኹለት ሆና አንድ ነብር ፈጃት። ዝምታ፥ ራሱ መልስ ነው። ዝምታ ወርቅ ነው፤ መናገር ብር ነው። ዝርክርክ፥ ከወንፊት የባሰ ዝክዝክ። ዝምታ ወርቅ፤ መናገር መዳብ፤ መጣላት ነሀስ። ዝምታ ወርቅ ነው። ዝምታ፥ ራሱን የቻለ መልስ ነው። ዝር አሉ፥ አልሸሹም። ዝሮ ከቤት፤ ኖሮ ከመሬት። ዝሮ ዝሮ፤ መዝጊያው ጭራሮ። ዝሮ ዝሮ፥ አለም የዝንጀሮ። ዝሮ ዝሮ ከቤት፥ ኑሮ ኑሮ አላህ ፊት (ይመለሷል)። ዝሮ ዝሮ ወደቤት፥ ኖሮ ኖሮ ወደ መሬት። ዝሮ ዝሮ፥ እራቱ ጥሬ። (ጥሬ ~ ጥፊ) ዝሮ ዝሮ፥ የድሮ አንገት ከማሰሮ። ዝቅ ቢል ከገብርዬ፤ ከፍ ቢል ከዙያ ሰውዬ። ዝባድን ከውሻ፤ እምነትን ከባለጌ አትሻ። ዝኆን ለቀንድ፤ ባላባት ለትውልድ። ዝኆን ማለት ከሞኝ ያስቆጥራል። ዝኆን ቂጡን ተማምኖ፥ ግንድ ይውጣል። ዝኆን ቢያንቀላፋ፥ ዚፍ ተደግፎ ነው። ዝኆን ተሰብስቦ ሲጫወት ገበጣ፤ የኢትዮጵያ ጀግና ጅም አፍራሹ መጣ። ዝኆን አምጣ አምጣ፥ አይጥ ወለደች። ዝኆን እንሆ(ት)፥ ፍለጋው ወዳት? ዝኆን የቂጡን ልክ አውቆ፥ ግንድ አይውጥም። ዝኆን የዋለችበትን ትመስላለች። ዝኆን ይሣቅ፥ አንድ ጥርሱ ሺ የሚያወጣ። ዝኆን ጥርሱን፤ አዝመራ ገብሱን። ዝኆንም ለሆደ ድንቢጥም ለሆደ፥ ወደ ወንዝ ወረደ። ዝኆንና ዝኆን ቢጣሉ፥ የሚጎዳው ሣሩ። ዝናር የላለው ነፍጠኛ፥ አለንጋ የላለው ፈረሰኛ። ዝናብ ለምኖ፥ ጎርፍ አመጣ። ዝናብ ለ዗ር፤ ጠል ለመኸር። ዝናብ ሉጥል ሲል ይነፋፍሳል። (ይነፋፍሳል ~ ይነፍሳል) ዝናብ ሲያባራ፥ ከዋሻ። ዝናብ ሲያባራ ዋሻ፥ ምን ያሻ?( ያሻ ~ ሉሻ) ዝናብ ሳይመጣ ዅሉ ቤት፥ እንግዳ ባይመጣ ዅሉ ሴት። (ሳይመጣ ~ ባይመጣ ~ ከአልጣለ) ዝናብ ሳይመጣ ገና፤ የውሃን መንገድ መጥረግ ደኅና። ዝናብ ከአባራ፥ ወደ ዋሻ። ዝናብ ከደመና፤ ነገር ከዋና። ዝናብ ካለ ዝራ፥ እናት ሳለች ኩራ። ዝናብ ዗ነበ ቢለው፥ ከደጅህ እየው። ዝናብ ዗ነበ ወይ ቢለው፥ በየደጅህ እየው አለው። ዝናብ የመታው አንበሳ፥ ቀበሮን መሰለ። ዝናብና ልጅ ሲጠሉ(ት) ያከብር። ዝንብ ሳይቅሙ፥ ዝግን አይቅሙ። ዝንብ ሩቅ አይበር፥ ሜዳ አደግ ደር አይደፍር። (ሜዳ አደግ ~ የሜዳ ልጅ) ዝንብ ቢሰበሰብ መግላሉት አይከፍትም። (መግላሉት ~ ጋን) ዝንብ ቢሰበሰብ መግላሉት አይከፍት። (አይከፍት ~ አይከፍትም) ዝንብ ቢሰበሰብ ጋን አይከፍትም። (ጋን ~ መግላሉት) ዝንብ ባትገድል ታስታውክ። ዝንብ ከአይን፤ ጭራ ከ዗ባን። (ከ዗ባን ~ ከዝንብ) ዝንጀሮ፥ መቀመጫዬ ይብሳል አለች። ዝንጀሮ ሰው ነበር ይላሉ ድሮ። ዝንጀሮ ሲበዚ ይወረዚል ገደል፤ ወተት ይሸፍታል እን኱ን ሰው ሲበደል። ዝንጀሮ ቂጧንና እግሯን እሾህ ቢወጋት፥ የትኛውን እንንቀልልሽ ቢሎት ዝንጀሮ እንሳሣቅ ካልሽ፥ ነድዬን መልሽ። ዝንጀሮ የመቀመጫዋ አይታያትም። ዝንጀሮ፥ የመቀመጫዬ ይቅደምልኝ አለች። ዝንጀሮ፥ የራሷን ጠባሳ ሳታይ፥ በባልንጀራዋ ሣቀች። ዝንጀሮ የቂጧን መላጣ ሳታይ፥ በባልንጀራዋ ትስቃለች። ዝንጀሮና ጥዋ ከአፉ ነው የሚያዝ። ዝንጀሮን በበግ ለውጠኝ ቢለው፤ ጣፋጩን ትቼ አልማጪን። ዝንጅብል ማን ቢሉህ፥ ማነኝ ትል። የሀምላ ጭቃ፥ ቅቤ ለጋ። የሀምላን ውሃ ጥም፤ የኅዳርን ረኃብ። የሀቀኛ ሥንቁ እውነቱ ነው። የሀብታም ልጅ ሲጫወት፥ የድሀ ልጅ ይሞታል። (ይሞታል ~ ይሞት) የሀብታም ልጅ ወደ ቦላ፤ የድሀ ልጅ ወደ ባላ። የሀብታም ሣቅ ክፋቱ፥ ርዝመቱ። የሀብታም ንግግር ባይጥምም ይደመጣል። የሀናን ለወለተ ሀና። የሀገር ርቀት፤ ፍቅርን አያስቀራት። የኀጢአት ክፉ ጉቦ፤ የበሽታ ክፉ ተስቦ። የሆድ ብልኀት፤ የጋን መብራት። የሆድ ነገር ሆድ ይቆርጣል። የሆድ ጠላቱ አፍ፥ የአይን ጠላቱ እጅ። የኋላ ኋላ፥ አይቀርም ደላ። የለመነ መነመነ። የለመነ ያገኛል፤ የነገደ ያተርፋል። የለመኑትን የማይረሳ፤ የነገሩትን የማይረሳ። የለመደ ለማኝ፥ ቁርንጮዬን ቀማኝ። የለመደ ልማድ፥ ያሰርቃል ከማእድ። (ያሰርቃል ~ ያሰድዳል) የለመደ ልማድ፥ ያሰርቃል ከአመድ። (ከአመድ ~ ከማእድ) የለመደ መደመደ። የለመደ እጅ፥ ጆሮ ግንድ ያስመታል። የለመደ ፈረሰኛ ዚብ(ም) አይጨብጥ፥ ርካብ(ም) አይረግጥ። የለመደ ፈረሰኛ ዚብን አይጨብጥ፥ እርካብን አይረግጥ። የለመደች ጦጣ ኹል ጊዛ ሸምጥጣ። የለመደው ቢያሥሩት በመጫኛ ኼደ እየጎመደው። የለማኝ ለማኝ ቁርንጮዬን ቀማኝ። (ቁርንጮዬን ~ ቁረንጮዬን) የለማኝ ስልቻ ሲንከባለል፤ ከለማኝ እጅ ይወድቃል። የለማኝ ቅንጡ፥ ይላል በወጥ አምጡ። የለም ቀሪ፤ ካለ ፈጣሪ። የለቅሶ ዳር ዳሩ፥ እዬዬ ነው። የለበሰ፥ የማንንም ጎረሠ። የለበሱት ያልቃል፤ የሰጡት ያጸድቃል። የለጋስ ምስክሩ፥ መስጠቱ። የላለው፥ ልብም የለው። የላለው፥ መዳኛም የለው። የላለው፥ ሚስት የለው፥ ወዳጅ የለው። የላሉት ጉድፍ፥ ከመንካቱ የማነካካቱ። የላሉት ግስገሳ፤ የቀን ዗ለሳ። የላላት ራት ደግሞ፥ ምሳ አማራት። የላመ የጣመ። የላሜ ልጅ፤ የአውራዬ ውላጅ። የላም መንጃ፤ የሸማ መከንጃ፤ የማር መቅጃ። የላም ወተቱን፤ የጌታ ከብቱን። የላባ መኝታው (ከ)አመድ፥ መታሰሪያው ገመድ። (መኝታው ~ ምኝታው) የላባ ሞኝ፥ በጎታ ሥር ይገኝ። (በጎታ ~ ከጎታ) የላባ ሞኝ፥ በጎተራ ሥር ይገኝ። የላባ ሞኝ፥ ከጎተራ ሥር ይገኝ። (ይገኝ ~ ይገኛል) የላባ ዋሻ፥ የቀማኛ መሸሻ። (መሸሻ ~ ዋሻ) የላባ አይነ ደረቅ፥ መልሶ ልብ ያደርቅ። የላባና የድመት ዓይን፥ ከቀኑ ይልቅ በጨለማ ያስተውላል። የላባን ጠበቃ፥ አደባልቀህ ውቃ። የላባን ገን዗ብ ባልገዙ፥ ተገዙም መድን ባበዙ። የልመና በሬ ትክክል አይኼድም። የላባን ጠበቃ፥ ደርበህ ውቃ። የላከ እንደ አፉ፤ ያከከ እንደ እጁ አይሆንለትም። የላይ ለምጡን፤ የውስጥ እብጡን ባለቤቱ ያውቀዋል። የላይ አልጋ፤ የውስጥ ቀጋ። የላይኛው ከንፈር ለክርክር፥ የታችኛው ከንፈር ለምስክር። የላጪን ልጅ፥ ቅማል በላት። የላጭ ልጅ፥ ጸጉሩ ድሬድ ሆነ። የላጭን ልጅ፥ ቅማል። የላጭን ልጅ ቅማል በላው፤ የአናጢን ልጅ ጅብ በላው። የላለው፥ ልብ የለው፥ ወዳጅ የለው። የላጭን ልጅ፥ ቅማል በላት። (በላት ~ በላው) የልላ አልቃሽ፤ የሴት ቀዳሽ (የቄስ አውደሽዳሽ)። የመል኱ን ሲሎት፥ የጠባዩዋን። የልመና በሬ ወደ ሀገሩ ይስባል። የልመና እንጀራ ምንጊዛም ከልመና አያወጣም። የልቡን ሲነግሩት፥ የኮረኮሩት(ን) ያህል ይሥቃል። የልቡን አድራጊ አይናደድም። የልብ ሳይደርስ፤ ሞት ይደርስ። (ሞት ~ ዕድሜ) የልብ ቅንነት፥ ይሰጣል ክብረት። የልብስ ሰፊ ልብስ፥ ጠርዙ ትርትር። የልብስ ቀላል፥ ባለቤቱን ያቀላል። የልብህን ቢያናግሩህ፤ አለ ዕዳ ቢለቁህ። (ቢያናግሩህ ~ ቢነግሩህ) የልብህን ቢያናግሩህ፤ አለ ዕዳ ቢሰደህ። የልደት ድግስ በዅሉም ነው፥ ላላ ቀን ቅጠሩኝ። የልጁን ነገር ምን አደረጋችኹት አለ፥ አያ ጅቦ። የልጃገረድ አፋራም፤ ከወንድሟ ታረግዚለች። የልጅ ልጅ፥ እህል ፈጅ ኋላም ጅብ ያስፈጅ። የልጅ ልጅ፥ እህል ፈጅ በኋላም ጅብ አስፈጅ። የልጅ ልጅ፤ ጅብ አስፈጅ። የልጅ መልከ ጥፉ፥ በስም ይደግፉ። የልጅ ማደጊያ፥ በመስክ ያድራል። የልጅ ሞት፤ የእግር እሳት። የልጅ ሞኝ ተቀምጦ፥ የአባቱን ክብረት ሲያወጋ ይውላል። የልጅ ሥጋ፤ በእናቷ ቅቤ። የልጅ ቀላቢ፤ የአህያ ጋላቢ። የልጅ ብልጥ፥ የሰጡትን። የልጅ ብልጥ፥ እየቀደመ ይውጥ። የልጅ ብልጥ፥ የፊት የፊቱን። የልጅ ብልጥ፥ የፊት የፊቱን እየቀደመ ይውጥ። የልጅ ተሟጋች፥ በፊት ሰማይ ያያል ኋላ መሬት። የልጅ ተሟጋች፥ በፊት ሰማይ ያያል ኋላ ምድር ያያል። የልጅ ተሟጋች፥ ጠዋት ሰማይ፥ ማታ ምድር ምድር ያይ። የልጅ ተሟጋች፥ ጠዋት ሰማይ ሰማይ፥ ማታ ምድር ምድር ያይ። የልጅ ነገር ኹለት ፍሬ፤ አንደ ብስል አንደ ጥሬ። የልጅ ነገር፤ ጥሬ በገል። የልጅ እናት፥ አባይ ናት። የልጅ እንግዳ፥ ማንን ይጎዳ። የልጅ ክፉ ዱቃላ፤ የቤት ክፉ ሰቀላ፤ የልብስ ክፉ ነጠላ። የልጅ ክፉ ዱቃላ፤ የእህል ክፉ ባቄላ፤ የልብስ ክፉ ነጠላ፤ የቤት ክፉ ሰቀላ። የልጅ ክፋቱ፥ አለመከማቸቱ። የልጅ ደፋር፥ ምጥ ለእናቷ ታስተምር። የልጅ ጥፉ፥ በስም ይደግፉ። የልጅ ፍሬ፥ አንደ ብስል አንደ ጥሬ። የልጅ ፍቅር፥ የሴት ከንፈር እናትን አያስቀብር። የልጅቷን ሥጋ፤ በእናቷ ቅቤ። የሕልም ሩጫ፤ የጨለማ ፍጥጫ። የሕዝብ ሀብቱ፥ አንድነቱ። የመምሬን ጠላት፥ አንጠልጥል ወደ ጉድፍ፥ እንዳይመለስ በብረት ቁልፍ። የመስከረም ውስጡ በጋ፤ የአረመኔ ልቡ ቀጋ። የመሬት ርጥብ እሸቱን፤ ደረቅ ምርቱን። የመቀናጆ በሬ ሲመሽ፥ ወደ ቤቱ ይስባል። የመበደሪያ አፍ፥ መክፈያ አይሆንም። የመስከረም ውስጡ፤ የንጉሥ ፍርደ አይታወቅም። የመሬት ሴሰኛ፥ ከመንገድ ዳር ይተኛ። የመብል ይደር ያገለግላል፤ የሥራ ይደር ያገነድራል። የመተማን ትተን፥ የቦሩን እናውጋ፤ 3 ቀን ጨልሞ፥ በ4 ኛው ነጋ። የመተሩበት እጅ ይወዚል፤ የተማከሩት ዳኛ ያግዚል። የመታሰር ምልክቱ መያዝ፤ የመሻር ምልክቱ መጋዝ። የመታሰር ምልክቱ መጋዝ፤ የመዳኘት ምልክቱ መያዝ። የመነነ ከደር፤ የሞተ ከመቃብር (አይወጣም)። የመነኰሴ ልላ፤ የክረምት አሞላ። የመነኰሴ ፈራጅ። የመንማና፥ የለው ገናና። የመንታ እናት፥ ተንጋላ ትሞት። የመንገድ ክፉ፥ ገደል። የመንገድ ዳር እሸት፤ ባል የላላት ሴት (ለማንም ናት)። የመከሩበት ሞተ፤ የወረወሩበት ተሳተ። የመከራ ላሉት አያልቅም። የመከራ ልጅ፥ ኹል ጊዛ መከራ መስል ይታያል። የመከራ ልላ፥ መከራ መስል ይታያል። የመከራ አካኼድ፥ የበግ ይመስላል። የመከራ ውዝፍ ያለበት ነጋዳ፥ ከሚወረር አገር ይደርሳል። የመከራን ጉድ጑ድ፥ ሚዳቋ አት዗ለውም። የመኮንን ልጅ፥ ኀ዗ን ቢነግሩት አደን። የመኮንን ልጅ በከተማ፤ የድሀ ልጅ በውድማ። የመውጊያውን ብረት ብትረግጥ፥ ለአንተው ይብስብሀል። የመዝሙር መጀመሪያ ሃላታ፤ የ዗ፈን መጀመሪያ እስክስታ። የመጀመሪያ እይታ፥ የ዗ለቄታ ትዝታ (ያተርፋል)። የመጀመሪያው ስሕተት፥ የኋለኛው እብደት። የመጠጡት ቅልጥም፥ ከብርንድ ይጥም። የመጣ ሳይመጣ፥ የውሃ ቦይ ጥረግ። የመጣ ቢመጣ፥ ከቤቴም አልወጣ። የመጣው ቢመጣ፥ ወይ ፍንክች ያባ ቢላዋ ልጅ። የመጥረቢያ ልጅ፥ መ዗ለፊያ። የመጥረቢያ ልጅ፥ ጥልቆ። የሙር ገላጋይ፥ ሾተል አቀባይ። የሙሽራ ዕድሜ ቢያጥር፥ የሰርጉ ድግስ ሆነ ለተዝካር። የሙቀጫ ልጅ፥ መውቀጫ። የሙት ምቀኛ፥ ሚስቴን አደራ ይላል። የሙት አልቃሹ፤ የቁም ወራሹ። የሙት፥ የለውም መብት። የሚመክተው ጋሻ፤ የሚጠጋበት ዋሻ። (የለውም) የሚመጣውን እንድታውቅ፥ ያለፈውን እወቅ። የሚሞት ልጅ፥ አንገቱ ረጅም ነው። የሚሞት ሲሞት፤ ሳይሞት አይሞትም። የሚሞት ሽማግላ አይርገምህ፤ የሚያልፍ ዝናብ አይምታህ፤ የሚያድግ ልጅ አይጥላህ። የሚሠራ፥ ምንም አያወራ። የሚሮጡበት ሜዳ፤ የሚወጡበት ቀዳዳ። የሚሮጥበት ሜዳ፥ የሚመጣበት ቀዳዳ የለውም። የሚሸሹበት አንባ፥ ሲሸሽ ተገኘ። የሚሰርቀውን ያጣ ላባ፥ ሰላማዊ መስል ይገባ(ል)። የሚሰርቅ ሰው፥ አደራ ቢያስቀምጡት፥ እጅ ይነሣል። የሚሰጥም እሾህ ይጨብጣል። (እሾህ ~ ገለባ) የሚስት መናኝ፤ የእናት አገር ለማኝ። የሚስት አሳቢ፤ የጥንድ በሬ ሳቢ ይስጥህ። የሚስት አንባሻ፤ የጎረቤት ውሻ፤ የደጅ ዕርሻ። የሚስት ወይ዗ሮ፥ ዕርሻው ጋራ ዝሮ። የሚስት ዗መድ፥ የማር አንገት። የሚስት ዗መድ፥ የማር እንጎቻ። የሚበላው ከአጣ፥ ይበላለት ያጣ። (ይበላለት ~ ይበላበት) የሚበጀውን ባለቤት ያውቃል። የሚነቃነቅ ግንድና፥ የምትሥቅ ሴት ልብ ሩቅ ነው። የሚከርመውም የማይከርመውም፥ በአንድነት ዝናብ ይለምናል። የሚካኤል ስለት፥ ለገብርኤል ምኑ ነው? የሚናገረውን ~ የተናገረውን የሚክድ ሰው፥ አደራ ሲያስቀምጡበት፥ እጅ ይነሣል። (ሲያስቀምጡበት ~ ቢያስቀምጡት) የሚኼድ ተማሪ፥ ምክንያት ይሻል። የሚሆን ቢሆን፥ ዝኆን ይበላ ቢሆን። የሚሉሽን በሰማሽ፥ ገበያም ሳልወጣሽ። የሚወደትን ሲያጡ፥ የጠሉትን ይቀላውጡ። የሚወደትን አቅፎ፤ የሚጠሉትን ነቅፎ። የሚወጋ ጦር፥ ከእጅ ሲወጣ ያስታውቃል። የሚወጡበት ገደል፤ የሚንጠለጠሉበት ቅጠል። የሚውል ሆድ፥ ማለዳ ይርበዋል። (ይርበዋል ~ ያረግዳል) የሚዚንን አባይ ለእሳት፤ የዳኛን አባይ ለሰንሰለት። የሚያልቅ እህል፥ ከማያልቅ ዗መድ ያጣላል። የሚያለሰልስ) አጥንትና ጅማት፥ በአከላት። አጥፊ ለጥፋት፤ ስካር ለትፋት። አጥፊና ጠፊ፤ ወናፍና አናፊ። የሚያልፍ ረኃብ፥ የማያልፍ ስም አወረሰ። የሚያልፍ ቀን፥ የማያልፈውን ስም ያወርሳል። የሚያልፍ ቀን፥ የማያልፍ ስም ያወርሳል። የሚያልፍ ነገር፥ የማያልፍ ስም ይሰጣል። የሚያልፍ ውሃ፥ አደረገኝ ድሀ። የሚያልፍ ዝናብ አይምታህ፤ የሚሞት ሽማግላ አይርገምህ። (አይምታህ ~ አይደብድብህ) የሚያልፍ ዝናብ አይምታህ፤ የሚያድግ ልጅ አይጥላህ። የሚያማ ጠበኛ፥ ዗ወር ይበል ከእኛ። የሚያስፈሳውን ለሚነግርህ፤ የሚያስቀዝነውን ንገረው። የሚያብረቀርቅ ዅሉ፥ ወርቅ አይደለም። የሚያወጣ እያወጣ። የሚያድግ ልጅ፥ በእናቱ እጅ። የሚያድግ ልጅ አይጥላህ። የሚያውቅ ያውቀዋል የሀምላን ውሃ ጥምና የታኅሣሥን ረኃብ እናት አታውቀውም። የሀር ገመድ፤ የበቅል ክበድ። የሚያድግ ልጅ አትበድል፤ የሚሞት ሽማግላ አታቃልል። (አታቃልል ~ አታቅል) የሚያድግ ልጅ አይጥላህ፤ የሚሞት ሽማግላ አይርገምህ። የሚያድግ ልጅ አይጥላህ፤ የሚያልፍ ዝናብ አይምታህ። የሚያድግ ዚፍ፥ ከቁጥቋጦው ያስታውቃል። የሚያጠግብ ቂጣ ከምጣደ፤ የሚወጣ ጥጃ ከገመደ (ያስታውቃል)። የሚያጠግብ እንጀራ፥ ከምጣደ ያስታውቃል። (ከምጣደ ~ በምጣድ) የሚያፈስ ቤት፤ ጨቅጫቃ ሚስት። የሚዳቋ ብዚት፥ ለነአቶ ውሻ ሰርግ ነው። የሚዳቋ ብዚት፥ ለውሻ ሰርግ ነው። የሚዳቋ ግርግር(ታ)፥ ለውሻ ሰርጉ ነው። የሚገነፍል ድስት፥ ራሱን ያቆሽሻል። የሚጠጉበት ገደል፤ የሚንጠለጠሉበት ቅጠል። የሚጠፋ ከተማ፥ ነጋሪት ቢመቱበት አይሰማ(ም)። የሚጣፍጥ ምግብ፥ ሲርብ የበሉት ነው። የሚጣፍጥ ምግብ ምንድር ነው ቢሉት፥ ሲርብ የበሉት (አለ)። የሚጣፍጥ ምግብ ምንድን ነው ቢሉት፥ ሲርብ የበሉት ነው። የሚጮኸው ቁራ፤ የሚበላው አሞራ። የሚጮህ ውሻ አይናከስም። የሚፈልግ ያገኛል፤ የሚተኛ ያልማል። የሚፈርስ ከተማ፥ ነጋሪት ቢመታ አይሰማ። (ቢመታ ~ ቢጎሰም) የሚፈታ ከተማ፥ ነጋሪት ቢመቱ አይሰማ። የሚፈታ ከተማ፥ አዋጅ ቢነግሩበት አይሰማ። የማረተ ማጭድ ሸክም፤ በሀቅ ጭብጥ ይፈታል። የማር ብጥብጥ፤ የተልባ ድርጥ። የማርያም ልጅና፥ የጥቅምት ልጃገረድ አትጭ። የማሽላ ዗ር፤ ከነአገዳው ቸር። የማሳና የሰው ንጹሕ የለውም። የማታ ማታ፥ እውነት ይረታ። የማታ ማታ፥ ጭምት ይረታ። የማታ ምግብ ለእንግዳ፤ የጠዋት ምግብ ለአገዳ፤ የጠዋት መጠጥ ለዕዳ። የማታ ሩጫ፥ እንቅፋት (ነው) ትርፉ። የማታ አፍ አይረጋም። የማታ አፍ፥ ከበረት ይሰፋል። የማታ አፍ፥ ከጋን ይሰፋል። የማታርፍ ጣት፥ አር ጠንቁላ ወጣች። የማታውቅበትን የሰው ግምጃ ለብሳ፥ ተመለሺም ቢሎት ወዳት ተመልሳ። የማታድግ ውርንጫ፥ እናቷን ትመራለች። የማታድግ ጥጃ፤ እናቷን በእርግጫ። (በእርግጫ ~ ትመራለች) የማታድግ ፍየል አምስት ትወልዳለች፥ ልጆቿም ያልቃሉ እሷም ትሞታለች። የማታፍር ድመት፥ ስሜ ገብረማሪያም ነው ትላለች። የማትረባ ፍየል ዗ጠኝ ትወልዳለች፥ ዗ጠኙም ያልቁና እሷም ትሞታለች። የማትሸሸውን ባልንጀራ፥ ዙረህ ዙረህ አትየው። የማትኼድ መበለት፥ ዝራ ዝራ ትሰናበት። የማትሰማው ስድብ፥ ከቀረርቶ ይቆጠራል። የማትረባ ፍየል አምስት ትወልዳለች። የማኅበር አሽከር፤ በልቶም አይጠገን ታሞም አይድን። የማሚቴን እጅ ያላየ፥ በእሳት ይጫወታል። የማነው እህል? ያሰኝሀል ክምር። የማነው ቤት? ያሰኝሀል አጥር። የማናቃት ክምር፥ አድዮ ለበሰ አለች አሉ ዝንጀሮ። የማን ነው ፈረስ ያሰኛል ገብስ፤ የማን ነው ልጅ ያሰኛል ፈረስ። የማን ዕርሻ ብለህ እረስ፤ የማን ሚስት ብለህ ውረስ። የማን ዗ር፤ ጎመን ዗ር። የማንኮሪያ ልጅ፥ መላፊያ። የማያለቅስ ልጅ፥ በእናቱ ጀርባ ይሞታል። የማያልፍ ነገር የለም፥ ምሽትም በማለዳ ይተካል። የማያልፍለት ዗በኛ፥ ከዋርካ ሥር አይጠፋም። የማያመሽ ባል፥ ቅንድብ ይስማል። የማያምኑበት ተ዗ግቶ፥ ይተውታል ተከፍቶ። የማያስተኛ ነግረውህ፥ ተኝተው ያድራሉ። የማያስተኛ ነግረውት፥ ሳይተኛ አደረ። የማያበላ ቢገላምጥ፥ አያስደነግጥ። የማያበድር ደመኛ፤ የማይመልስ ቀማኛ። የማያበድር ገዳይ፤ የማይመልስ አባይ። የማያባራ አይ዗ንብም፤ የማይሞት አይወለድም። የማያዋጣ ማኅበር፥ በጠጅ ይጀመራል። የማያዋጣ ባል፥ ቅንድብ ይስማል። የማያውቁት፥ ምን ያውቅ? የማያውቁት ስድብ፥ ከ዗ፈን ይቆጠራል። የማያውቁት አገር አይናፍቅም። የማያውቁትን መሥራት፥ ከጥቅሙ ጉዳቱ ይብስ። የማያውቅ፥ ምን ያውቅ? የማያዚልቅ ጸልት፥ ለቅስፈት። የማያደርሱበትን አያኩም። የማያድሩበት ቤት፥ አያመሻሹበት። የማያድግ ልጅ ቅ዗ን ይበዚዋል፤ የማያጠግብ እንጀራ ከምጣደ ያስታውቃል። የማያድግ ልጅ፥ በአራስ ቤቱ ዳንኪራ ይመታል። የማያድግ ልጅ፥ ታዝል ያፏጫል። የማያድግ ጥጃ፥ ከበሬ ፊት ይነጫል። የማያግዙ በፈር፥ ያግዚሉ በከንፈር። የማያጠግብ እንጀራ፥ ከምጣደ ያስታውቃል። የማያፍር እንግዳ፥ ባለቤቱን ይጋብዚል። የማያፍር ያሳፍራል። የማይመስል ነገር፥ ለሚስትህ አትንገር። የማይመስል ነገር፥ ለሴት አትንገር። የማይመቱት ልጅ፥ ሲቆጡት ያለቅሳል። (ሲቆጡት ~ ቢቆጡት) የማይሞት የማይበርድ፤ የድንጋይ ምጣድ። የማይሠራ አይብላ፤ የማይረዳ አይጥላ። የማይሰማ ሰው፥ ልቤን አፈረሰው። የማይሰማ ጆሮ፥ ከጎረቤት ያጣላል። የማይስማሙ ዝንቦች ጥንብ ይልሳሉ፤ የሚስማሙ ንቦች ማር ይጎርሣሉ። የማይረባ ገንፎ፥ በጥድ ይጠበሳል። የማይቀርልህን እንግዳ፥ አጥበቀህ ሳመው። የማይቀና ባይወልድ፥ የማያስብ ባይነግድ (ይሻላል)። የማይበሉት እህል፥ ከአፈር እኩል ነው። የማይበላ የለም፥ የማይጠግብ ባሰ። የማይተማመኑ ባልንጀሮች፥ በየወንዙ ይማማላሉ። (በየወንዙ ~ እየወንዙ) የማይተማመን ባልንጀራ፥ በየወንዙ ይማማላል። የማይተች አይፍረድ፤ የማያተርፍ አይነግድ። የማይታ዗ዝ ልላ፤ የማያስታርቅ ሽማግላ፤ ታስሮ እንደሚጮህ አለላ። የማይቻል ጠላት፥ ስለ ወዳጅ ይቆጠራል። (ስለ ወዳጅ ~ ከወዳጅ) የማይችሉት ድንጋይ፥ ሲያወጡት ደረት ሲያወርደት ጉልበት ይመታል። የማይችሉትን ሰው አይታገሉትም። የማይችል ቢዳኝ፥ ከቤቱ ይናኝ። የማይነጋ መስሎት፥ እቋቱ ላይ አራች። የማይከፍል ባለ ዕዳ፥ የሰጡትን ይቀበላል። የማይ዗ልቅ ማኅበር፥ በጠጅ ይጀመራል። የማይ዗ልቅ ማኅበር፥ አሜሪካ ይጀመራል። የማይ዗ልቅ ባል፥ ቅንድብ ይስማል። የማይ዗ልቅ ጸልት፥ ለቅስፈት። የማይደርሱበትን አያኩም። የማይሆን ነገር የተገላቢጦሽ፥ ያችን ለአንቺ ማን አለሽ? የማይመለስ ማር፥ ሹመኛ ይበደረዋል። የማይድን በሽተኛ በበጋ፥ እሸት አምጡልኝ ይላል። የማይድን በሽተኛ በጥር፥ እሸት አምጡ ይላል። የማይድን በሽተኛ፤ የማይመለስ ኀጢአተኛ። የማይድን ባሕታዊ ወተት አምጡ፤ የማይድን ፉቅራ ጠላ ስጡ። የማይገለጥ ሽሽግ፤ የማይታይ ስውር የለም። የማይገባ ሱሪ፤ የማይበቅል ዗ር። የማይገባችኹን ልብስ፥ አትልበሱ። የማይገባውን የሚናገር፥ የማይወደውን ይሰማል። የማይጠረጥር፥ ቤቱን አያጥር። የማይጣሉ መላእክት፤ የማይታረቁ አጋንንት። የማይጮህ ጅብ አያግኘን። የማይጽፍ ደብተራ፤ ክንፍ የላለው አሞራ። የማይፈርስ ምሽግ የለም። የማይፈነቅለው ድንጋይ የለም። የማይፈወስ ድውይ፤ የማይመለስ ጊጉይ። የማይፈጭ ማስጣት፥ ለድሮ ማስበላት። የማድ ሰው፥ አንድ ይወ጑ል አንድ ይወ጑ል፥ ከቤት ኺድ ምን ያወ጑ል። የማጀቱን በአደባባይ። የማድ ቤት አንድ ያወራል፥ የጠጅ ቤት አንድ ያወራል። የማጥ መድኀኒት ምንድነው ቢለው፥ ላላውን ማስቀደም ነው አለው። የሜዳ ንስንሱን፤ የቤት ጉስጉሱን። (ጉስጉሱን ~ ጉዝ጑ዙን) የምሕረት ጎደል፤ የባሪያ ወይ዗ሮ። የምላስ ወለምታ፥ በቅቤ አይታሽም። የምላስ ጦር፥ ቢታከም አይድንም። የምመክተው ጋሻ፤ የምጠጋበት ዋሻ። የምሮጥበት ሜዳ፤ የምሾልክበት ቀዳዳ። የምሮጥበት ሜዳ፤ የምወጣበት ቀዳዳ የለም። የምሽት ጨምጫማ፤ የበትር ቆልማማ። የምበላው ሳጣ፥ ልጄ ጥርስ አወጣ። የምበላው ሳጣ፥ ማዕቀብ ሉጣል ነው። የምሳር ማውለቂያ አደረገን። (:_ያሾፍብኛል) የምሥራች፥ በቃሎ መላች። የምስር ወጥ፤ ብኩርናን የሚያሸጥ። የምሥጢረኛ ምላስ የለውም። የምርጫ ወይስ የበርጫ። የምታሸንፈውን ምታ ቢሉት፥ ወደ ሚስቱ ሮጠ። የምታቦካው የላት፥ የምትጋግረው አማራት። የምታደርጉኝን አርጉኝና፥ እወፍጮዬ ልመለስ። የምትኼድ መበለት፥ ዙራ ዙራ ትሰናበት። የምትለብሰው የላት፥ ሻንጣ ቆለፈች። የምትለብሰው የላት፥ የምትከናነበው አማራት። የምትመክተው ጋሻ፤ የምትሰወርበት ዋሻ። የምትሮጥበት ሜዳ፤ የምትገባበት ቀዳዳ። የምትበላው እህል፥ ከማታየው መሬት ይበቅላል። የምትነቃነቅ ግንድና፥ የምትሥቅ ሴት ልብ ሩቅ ነው። የምትኮነን ነፍስ፥ ጎረቤት ያውቃታል። (ያውቃታል ~ ያውቃል) የምትጠላው ሰው፥ ፈሱ እሆደ ውስጥ ሳለ ይሸታል። (እሆደ ~ ሆደ) የምትጠላውን የምትወደውን፥ ሰጥተህ ሸኘው። የምትጠባ ጥጃ አትጮህም፤ የማይደርሱበትን አያኩም። የምናውቃትን ክምር፥ በድባብ ሸፈኗት። የምናውቃትን ክምር፥ ገለባ አለበሷት። የምን ባል ነው፥ ይበልብለውና። የምኞት ፈረስ፥ ል጑ም አይገታውም። የምድሩን በአፍ፤ የሰማዩን በመጽሀፍ። የምጣደ ሳለ፤ የዕንቅቡ ተንጣጣ። (ሳለ ~ እያለ) የምጥ መድኀኒቱ አንድ እግር ማስቀደም ነው። የሞላለት ድመት፥ ሳንባ ያማርጣል። የሞላለት ድመት፥ በሞዝቮልድ ይተኛል። የሞተ ልጅ፥ አንገቱ ረጅም ነው። የሞተ ሳገኝ እሱን አያርገኝ! የቆመ ባገኝ ፈሴም አይገኝ! የሞተ ቢሞት፥ ያለን እንጫወት። የሞተ አይወቀስ፤ የፈሰሰ አይታፈስ። የሞተ ያልነበረ ይመስላል፤ ያለ የማይሞት ይመስላል። የሞተን አትርሳ፤ የወደቀን አንሣ። የሞተን ውሻ፥ የሚመታው የለም። የሞተው ባልሽ፤ የገደለው ውሽማሽ። የሞተው ወንድምሽ፤ የገደለው ባልሽ። የሞተው ወንድምሽ፤ የገደለው ባልሽ፤ አ዗ንሽ ቅጥ አጣ ከቤትሽም አልወጣ። የሞተውን፥ አያ ይለዋል። የሞት በደለኛ፤ አያይዝ በዳኛ። የሞት ሰርጉ፥ እስከ ሣልስት። የሞቷን ምክንያት ምን አመራመራችሁ፤ እንዱያው ቅበሩ እንጂ እየደመማችሁ። የሞኝ ለቅሶ፥ መልሶ መላልሶ። (መልሶ መላልሶ ~ መልሶ) የሞኝ ልጅ በአባቱ ምን ይጫወታል አሉ። የሞኝ መንገደ፥ አንድ ነው። የሞኝ ሚስት በምልክት። የሞኝ ምሥጋና፤ የግንቦት ደመና። የሞኝ ምሥጢር፥ ሲጣሉ ይወጣል። የሞኝ ምሽት፥ በምልክት። የሞኝ ሞኝ፥ አያውቁብኝም ባይ። የሞኝ ቄስ ጸልት፥ ዗ወትር አቡነ ዗በሰማያት። የሞኝ በትር፥ ሆድ ይቀትር። የሞኝ ተናጋሪ፤ የመከር ጋጋሪ ኹለቱ አንድ ናቸው። የሞኝ አሳላፊ፥ ለ዗መድ አይሰጥም። የሞኝ እጁን፥ ኹለት ጊዛ (እባብ) ነከሰው፤ አንድ ጊዛ ሳያይ፥ ኹለተኛው ሲያሳይ። የሞኝ ጀርባ ሲመታ፥ ለአዋቂ ይስማማል። የሞኝ ገበሬ፥ ዕርሻ በሠኔ። የሞኝ ጠላ፥ በጣሳ። የሞኝ ፍልጥ፥ ካለአንድ ቀን አይበልጥ። የሞኝን ጥርስ ብርድ ፈጀው። የሞኝ ዗መድ ያፍራል። የሞኝ ዗ፈን፥ ኹል ጊዛ አበባዬ። የሞኝን ጠላ፥ በለው በአንኮላ። የሞኝን ጠላ፥ በለው በጣሳ። የሞኝን ቂጥ፥ ድሮ ይጠቀጥቀዋል። የሰለጠነ ሰየጠነ። የሠራው ቢረሳ፥ የተሠራው አይረሳ። የሰርድ ምስክር፥ እንግጫ። የሥራ መንታ መልካም ነው እንጂ፥ የሀሳብ መንታ መልካም አይደለም። የሥራ ቅላት፥ ያስለምዳል ላብነት። የሥራት መቋሚያው ፈጠም፤ የሥጋ መቋሚያው ቅልጥም። የሥብስቴ ዕርሻ፥ የጠብ መነሻ። የሥጋ መድኀኒት ላም፤ የነፍስ መድኀኒት ማርያም። የሥጋ መጨረሻ አጥንት፤ የነፍስ መጨረሻ ግዝት። (ግዝት:_ የእግዙአብሔር መንግሥት) የሥጋ ራስ፥ ሰንበርና ምላስ። የነገር ራስ፥ አጥፍቻለኹ ልካስ። የሥጋ ቁራጭ፤ የብርላ ጭላጭ። የሥጋ ትል፤ የ዗መድ ጥል። የሥጋዬ ቁራጭ፤ የአጥንቴ ፍላጭ። የስጦታ ፈረስ፥ ጥርሱ አይታይም። የረከሰ አይወደድ፤ የመነነ አይሰደድ። የረከበው ቀሉል። የረገመ ተረገመ። የረጋ ወተት ቅቤ ያወጣል፥ የረጋ ሰው ከዅሉ ይበልጣል። የረጋ ወተት ቅቤ ይወጣዋል። የረጋ ሰው ማለፊያ ይሆናል። የረጋ ውሃ ይበሰብሳል። የረጋ ወተት፥ ምርጫ ይደገምለታል። የረጋ ወተት፥ ቅቤ ይወጣዋል። የረጋ ውሃ ይበጠብጣል። የረ዗መውን በገመድ፤ ያጠረውን በክንድ (ለካ)። የረ዗መውን በጠፍር፤ ያጠረውን በድግር። የረ዗መውን በጦር፤ ያጠረውን በድግር። የሩቁን የሚመለከት፥ የፊቱን ያፈሳል። የራሱ ውልጮ፥ ያስቀምጣል ድጮ። የራሱን ትቶ፤ የሰው አክባሪ፤ የበላበትን ወጭት ሰባሪ። የራሱን እንዳይበላ ገን዗ብ የለው። የሰው እንዳይበላ አመል የለው። የራሱን የሚበላ ዕዳ የለው። የመሰለውን የሚናገር በደል የለው። የራሱን ጥል፤ የሰው አንጠልጥል። የራስ ናቂ፤ የሰው አድናቂ። የራስ ገን዗ብ፥ በጥፊ ያስመታል። የራስ ጌጥ፥ ስለ ጨርቅ፥ የላላው ያስጨንቅ። የራስህን አትበላ ገን዗ብ የለህ፤ የሰው አትበላ አመል የለህ። የራስሺን አትበይ ገን዗ብ የለሽ፤ የሰው አትበይ አመል የለሽ። የራስን ሳያውቁ፤ ለሰው አይጨነቁ። የራሷ ሲያርባት፥ የሰው ታማስላለች። (ሲያርባት ~ ቢያርባት) የራሷ አሮባት የሰው ታማስላለች። (አሮባት ~ እያረረባት) የራሷ ጊዛ ተንሰቀሰቀች፤ የሰው ጊዛ ሣቀች። (ተንሰቀሰቀች ~ አለቀሰች) የራሷን ስታወርድ፥ የብብቷ ወደቀ። የራሷን አበሳ፤ በላላው አብሳ። የራሷን አበሳ፥ በሰው (ላይ) አብሳ። የራሷን አታውቅ፤ የሰው ትንቅ። የራበው (ሰው)፥ ይጠግብ አይመስለው። የራበውን፥ ገበያ አታውጣው። የሬሳ ቋንጣ፥ ቀባሪ ሲያጣ። የሬሳ ጎረቤት፥ እሳት አያጫጭር፥ ቢሞቱ አይቀብር። የሬትን ምሬት ያልቀመሰ፤ የማርን ጣዕም አያውቅም። የሮጠ አመለጠኝ፤ የበላ ገለበጠኝ። የሮጠ አመለጠ፤ የቆመ ቀለጠ። የሮጠ አመለጠ፤ የ዗ገየ ተለየ። የሰማ ይስማ፤ ያልሰማ ይግማማ። የሰማ ያውራ፥ ያየ ይናገር። የሰማ ገማ። የሰማው ሲኼድ፥ ያልሰማው ሲመጣ። የሰማዩ ንጉሥ እስኪረዳ፤ የመሬቱ ንጉሥ ይጎዳ። የሰማዩን ያህል እንጀራ ይስጥህ ቢለው፥ የኮከቡን ያህል በላተኛ አለበት አለ። የሰማይ እርቀቱን፥ የምድር ስፋቱን፥ የፀሓይ ድምቀቱን። የሰቆጣ ሰው፥ ሺህ ብር ሲቀረው ከቤቱ፥ ስደት ይኼዳል። የሰባ አርድ፤ የጠራው አውርድ። የሰባራ ድስት ቅያሪ ቀዳዳ ጣሳ። የሰባን አርድ፤ የጠራውን አውርድ። የሰነፍ ለቅሶ፥ መልሶ መላልሶ። የሰነፍ ልቡ፥ ዓይኑ ነው። የሰነፍ መላሰኛ፤ የበሽተኛ በላተኛ። የሰነፍ ሰው ተዝካር፤ ውሃ ያስወስዳል በኅዳር። የሰነፍ አባባል ይብረድልኝ፤ የሰነፍ ምስክር ይማልልኝ። የሰከረ ሰው፥ አወዳደቁ አያምርም። የሰከረ ሲተፋ፤ የገደለ ሲደነፋ። የሰከረ፥ አወዳደቁ አያምር። የሰከረ ይተፋል፤ የገደለ ይደነፋል። የሰካራም ግጥም፥ ኹል ጊዛ ቅዳ ቅዳ። የሰው ሆደን፥ የወፍ መንገደን የሚያውቅ የለም። (መንገደን ~ ወንደን) የሰው ልጅ ሀገሩ፥ ምግባሩ። የሰው ልጅ መከራው፥ እንጀራው ያልቅና ወጡ ይተርፍና። የሰው ልጅ ሲፋታ፥ ያገባ ይመስላል። የሰው ልጅ ሥሱ፥ መደቆሻ ሲልስ ተሰበረ ጥርሱ። (:_ ስስታም) የሰው ልጅ በምን ይታፈራል? አይደለም በወንበር፥ በከንፈር። የሰው ልጅ ቢወልድ ልላውን፤ ባለጌ ቢወልድ ጌታውን። የሰው ልጅ ተነሣ አይሉም፥ እስኪነሣ ይጠብቋል። የሰው ልጅ ከማሳደግ፤ የውሻ ልጅ ማሳደግ። የሰው ልጅ ኩራቱ፥ ራቱ ነው። የሰው ልጅ ካለ አገሩ፥ ጎራዳ ካለ ሰፈሩ። የሰው ልጅነት አያኮራም፤ ጊዛ ነው እንጂ፣ ቁምነገራም። የሰው ልጅና ምስማር አጥብቀው ከአልመቱት አይፀናም። የሰው መሠረቱ፥ እናትና አባቱ። የሰው ሕይወት ሽንብራ እሸት፥ በሽንብራውም ትል አለበት። የሰው ሆደ፤ የወፍ ወንደ አይታወቅም። የሰው መዋደደ፥ መዋለደ። የሰው መዋደጃው፥ በየምድጃው። የሰው ማስጠንቀቂያ አታርገኝ። የሰው ማስጠንቀቂያ፤ የመዝጊያ ማጥበቂያ። የሰው ማጣፈጫው፥ ሃይማኖቱና ምግባሩ። የሰው ምላስ መንታ፥ ለሙገሳና ለሀሜታ። የሰው ምላስ መንታ፥ አንደ ለሙገሳ አንደ ለሀሜታ። የሰው ምላስ እን኱ን ሰው፥ ዕንጨት ያደርቃል። የሰው ምላስ፥ ዕንጨት ይሰብራል። የሰው ሞኝ፥ አንድ ዕንጨት ያሥራል። የሰው ሞኝ፥ ከሦስት ወር ጎበዝ ጋር ይታገላል። የሰው ሞኝ፤ የአባቱን ሀብት ያወራል። የሰው ሥጋ፥ ቢበሉት ይመራል ቢጠብሱት ያራል። የሰው ሥጋ፥ ቢጠብሱት ያራል ቢበሉት ይመራል። የሰው ርስት ከማልማት፥ አይሻልም ወይ የአባት። የሰው ቀላል ለራሱ ይቀላል፤ የልብስ ቀላል ባለቤቱን ያቀላል። የሰው ቀላል ራሱ ይቀላል፤ የልብስ ቀላል ለባሹን ያቀላል። የሰው ቁስል አይነዝርም። የሰው ቁስል፥ የግንድ ይመስል። የሰው ቃሪያ፥ እስኪሞት ድረስ አይበስልም። የሰው በልቶ፥ አያድሩም ተኝቶ። የሰው ባሕርይ ሳይደርሱ፥ የድንጋይ ሥር ሳይምሱ። የሰው ቤት ሲቃጠል፥ ቋያ ይመስላል። የሰው ብልኀቱ፥ ለፈጣሪ መንገር ነው መድኀኒቱ። የሰው ብድር፥ አይቀር(ም) በምድር። የሰው ታናሽ፥ ያደርጋል ትንሽ። የሰው ታናሽ፥ ይገዚል በግማሽ። የሰው ታናሽ፤ ይጥላል ጭራሽ። የሰው ነገር፥ አለመናገር። የሰው አመሉ ዳውላ ሙሉ፥ መቼ ያስታውቃል አብረው ከአልዋሉ። (ካልዋሉ የሰው አባቱ ሸማ፥ የሸማ አባቱ እዱያት። (እዱያት ~ ጥለት) የሰው አባት የሚሰድብ፥ አባቱን የጠላ ነው። የሰው አባት የሚሰድብ፥ አባቱን ያሰድብ። የሰው አትበዪ ምግባር የለሽ፤ የራስሽን አትበዪ ገን዗ብ የለሽ። የሰው አገሩ፥ ምግባሩ። የሰው አገሩ ምግባሩ፤ የከብት አገሩ ሣሩ። የሰው አገሩ ምግባሩ፤ የከብት አገሩ ጌታው። የሰው አገር ዝናብና፥ የእንጀራ አባት አይምታህ። የሰው አፍ እንደ ተሳለ ጦር ነው። የሰው እረኛ ጥቁር ነው። የሰው እንጂ፥ የቃል ውሸት የለም። የሰው እንግዳ፤ የአገር ባዳ። የሰው እጅ፤ የእግዛር ደጅ። የሰው ከማየት፥ የራስን መብላት። የሰው ከርፋፋ፥ ሲሰድቡት አይከፋው። የሰው ኩራቱ፥ በእናትና በአባቱ። የሰው ክብረቱ፥ ያሰኘዋል አንቱ። የሰው ክፉ ዋሾ፤ የእፅ ክፉ አብሾ። የሰው ክፉ፥ ጠማማ ነው አፉ። የሰው ክፋቱ፥ ሲያምኑት መክዳቱ። የሰው ወርቅ፥ አያደምቅ። የሰው ደኅናው፤ መቃብር የተኛው። የሰው ገላ፥ ርጥብ ሸክላ፥ ያልተተኮሰ ያልተኮላ። የሰው ገሚስ፥ ግማሽ እንጀራ ግማሽ አሞላ። የሰው ገን዗ብ ተበድሮ፥ በዕዳ ተወጥሮ። የሰው ገን዗ብ አይጠገብም። የሰው ግብሩ አይለየው፥ እስከ መቃብሩ። የሰው ግብር ቢመለከቱ፤ ድሀ ይሆኗል በዓመቱ። የሰው ግብር፥ እስከ መቃብር። የሰው ጠላቱ፥ ቤተሰቡ። የሰው ጠላቱ፥ ይወጣል ከቤቱ። የሰው ጠማማ፥ እንብላ ሲሉት እንራ። የሰው ፈላጊ፥ የራሱን ያጣል። የሰው ፈላጊ፥ የራሱን ያጣል፤ አሣ ጎር጑ሪ፥ ዗ንድ ያወጣል። የሰው ፊት አይቆረስ፤ የሰው ገን዗ብ አይወረስ። የሰው ፊት የሚያፍር፥ በቅል አይቀመጥ። የሰው ፊት፥ ደግነቱ አለመፋጀቱ። የሰውን ሞኝ አቆይልኝ፤ የራሴን ሞኝ ግደልልኝ። የሰውን በአህያ፤ የራስን በጉያ። የሰውን ነገር፥ ስንቱን ልናገር?( ስንቱን ልናገር ~ አለመናገር) የሰውን አባት የሚሰድብ፥ አባቱን ያሰድብ። የሰይጣን ክፋቱ፥ ያለ መታየቱ። የሰይጣን ገን዗ብ የተበደረ፥ ሳይበላው ተቀበረ። የሰይጣንን አመጣጥ፥ የማያውቅ አይመንኩስ። (አይመንኩስ ~ አይመነኩስም) የሰዳጅ ለወዳጅ። የሰጋ ቤቱን ዗ጋ፤ የ዗ነጋ ተወጋ። የሰጠ ቢነሣ፤ የለበት ወቀሣ። የሰጠኸኝ መሬት ለእኔ መች ባነሰኝ፥ አስቸገረኝ እንጂ መጭ እየወረሰኝ። የሰጠኸኝ ሸማ፤ ከደጅህ ተቀማ። የሰጠውን አላህ፤ ማን አልችል ይላል። የሰጡህን ተቀበል፤ ያደረጉህን ቸል አትበል። የሰጡህን ተቀበል፤ ያደረጉልህን ቸል አትበል። የሰጡን ይሰጧል፤ የገዙን ይነዶል። የሰጡን ይሰጧል፤ ያጠቡን ያሰጧል። የሰጪ ሆድ ሳያስብ፤ የበይ ሆድ ያስብ። የሣር ክምር፤ የጭሰኛ ክብር። የሰጡህን አትንሣ፤ ያደረጉህን ቸል አትበል። (ቸል አትበል ~ አትርሳ) የሰጡህን አትንሣ፤ ያደረጉልህን አትርሳ። (አትርሳ ~ ቸል አትበል) የሳተ ይምከርህ፤ የዋለ ይንገርህ። የሳንቲም ድቃቂ፤ የልብስ እላቂ። የሴት ሀሳብና የፈረስ ጋማ፥ አንድ አቅጣጫ ብቻ ይኼዳል። የሴት ሆዳም፥ (ታማ) አትተኛም። የሴት ሆድና፥ የወፍ ወንድ አይታወቅም። የሴት ላጪ፤ የወንድ ነጪ። የሴት ላባ፤ ወንድ ሉበላ። የሴት ልባም፤ የአህያ ቀንዳም። የሴት ልብ መርፌ ታህላለች፤ የነ኱ት ዕለት ትጠፋለች። የሴት ልብና የክረምት ነፋስ ዗ወትር ተለዋዋጭ። የሴት ልቧ እንጂ፥ ሆዶ አይመርጥም። የሴት ልጅ ልብ ከከንፈሯ ላይ ነው። የሴት ልጅ መብቷ፥ ማጀቷ። የሴት መላ፤ የጉንዳን ጎዳና። የሴት መል኱ ምንድን ነው? እጇን ታጥባ እንኩ ስትል ነው። የሴት መጠጥ ደፋር፤ የወንድ አይን አፋር። የሴት ምላስ የለው መላ። የሴት ምራቋ ወፍራም ነው(ምግብ ባትበላም)። የሴት ምክር፤ ማሰሪያው አሽከቴ። የሴት ምክር፤ የሾህ አጥር። የሴት ሞቷ፥ በማጀቷ። የሴት ሥብሰባ፤ በአንድ አይጥ ይበተናል። የሴት ስካር፤ ያጭር ስው ኩራት አይታይም። የሴት ረጅም፤ የማቅ ውዥምዥም አያስጎመጂም። የሴት ረጅም፤ የማቅ ውዥምዥም እንብዚም አያስጎመጂም። (አያስጎመጂም የሴት ረጅም፤ የእባብ ቅዝምዝም እንብዚም አያስጎመጅም። የሴት ሩጫ፥ ከአፍ እስከ አፍንጫ። የሴት ሰካራም፥ ቤት አይሠራም። የሴት ቀበጥ የበቅል መድን ለመሆን፥ ገበያ ትወጣለች። የሴት ቀበጥ፥ ትታጠቃለች ካራ። የሴት ቀዳሽ፤ የልላ አልቃሽ። የሴት በራ፤ የበቅል ቦራ። የሴት በራ፤ የበቅል ደንባራ። የሴት ብልኀት፥ እንደ ጋን መብራት። የሴት ብልኀት፤ የጉንዳን ጉልበት። የሴት ብቻዋን ኺያጅ፤ የቄስ አርፋጅ ኹለቱም ነገር ወዳጅ። የሴት ትልቅ፤ የ጑ያ ክምር የለም ። የሴት ትንሽ የለውም። የሴት ኑሮ (ሕይወት)፤ ከቤት እስከ ማጀት። የሴት አመዳም፤ የአህያ ሆዳም። የሴት አስተዳዳሪ፤ የጦጣ አስታራቂ የለውም። የሴት አቤተሆን፥ የበቅል መድን ትሆን። የሴት አንዳሻ፤ የ጑ሮ ዕርሻ፤ የጎረቤት ውሻ። የሴት አእምሮ፥ እንደጡቷ የተንጠለጠለ ነው። የሴት አገሯ ባሎ፤ (ማደሪያዋ አመሎ)። የሴት አገሯ፥ ቤቷና ትዳሯ። የሴት አጭር ወይ዗ሮ፤ የወንድ አጭር አውራ ድሮ። የሴት አፈኛ፥ የበቅል መድን ትሆናለች። የሴት እንግዳ፤ የመርፌ ጎዳ። የሴት ከርፋፋ ዕቃውን በእቃ ደጋግፋ፥ አንደን ስታነሣ ዅሉም ይደፋ። የሴት ክፉ ምላሰኛ፤ የበሽታ ክፉ መጋኛ። የሴት ክፉ አፈኛ፤ የጎረቤት ክፉ ምቀኛ። የሴት ወበራ፥ ትታጠቃለች ካራ። (ወበራ ~ ቀበጥ) የሴት ወገን በ጑ዳ፤ የወንድ ወገን በበረንዳ። የሴት ወፍራም፥ እንጂ ታላቅ የለውም። የሴት ዗በናይ የፊቷን እንጂ፥ የኋላዋን አታይ። የሴት ዗ንገኛ፤ የእናት ምቀኛ። የሴት ደንደሁራ፥ ከባሎ ሆዶን ትፈራ። የሴት ድሮ ኩኩሉ፤ ለባለጌ ኩሩ። የሴት ጉልበቷ፥ ምላሷ። የሴት ጎረምሳ፥ መጣች አጥር ጥሳ። የሴት ጠጪ፤ የግመል ፈንጪ። የሴት ጠጭና፥ የአህያ ፈንጪ አያድርስ ነው። የሴት ጥፋት፤ የጤፍ ጥራት አይታወቅም። የሴት ጥፋትና ጤፍ ሲፈስ አይታወቅም። የሴት ፀባይ፥ የትኩስ ገንፎ ያህል ነው። የሴትና የበሬ፥ እንግዳ የለውም። የሴትና የአህያ፥ ልብ አንድ ነው። የሴትን ልብ፥ ሰይጣን እራሱ አያውቀውም። የሴትን ብልኀት፤ የጉንዳንን ጉልበት ይስጥህ። የሥሡ ልጅ ሥሡ፥ መደቆሻ ሲልስ ተሰበረ ጥርሱ። የሥሥታም፥ አንድ ያንቀው፥ አንድ ይወድቀው። የሥራ ሥሩ መራራ፥ ፍሬው ግን ጣፋጭ። የስንዳ ንፍሮ፤ ያተር ድብልቅ፤ ከዙያችው ወጥተው፥ እዙያችው ጥልቅ። የስንዳው ዚላ፥ ዕፍኝ ይመላ። የስንዳ አራራ፤ የሴት መራራ። የስንዳ አራራ፤ የቆንጆ መራራ። የስድብ እበጥ የለው(ም)። የስድብ ክፉ አባት፤ የብትር ክፉ እናት። የሥጋ ልል ጭቅና፤ ያመት ባል ትልቅ ገና። የሸሁ ቃል ንቁፍ፤ የዋነኛው ቃል ጽሐፍ። የሸማ ጥቅል፤ የወርቅ እንክብል። የሸማኔ የቀጥቃጭ፤ የመጣፍ ገላጭ። (:_አሥራት) የሸሸ ንጉሥ፤ ያፈረሰ ቄስ። የሸሸ አይነግሥም፤ ያፈረሰ አይቀድስም። የሸንበቆ በትር ቢመረኮዙት ይሰበራል፥ ቢመቱበት እጅ ያቆስላል። የሸንጎ አይን፥ ጉልበትን ይሰብራል። የሹም ልል፥ በጥፊ ያወላውል። የሹም መጋዣ ሰብሬ፥ ባዝራ ልከፍል። የሹም ሰነፍ፥ ባይለፈልፍ። የሹም ሰነፍ፤ ባይደፈድፍ ይለፋልፍ። የሹም ሰነፍ፥ አንደን ሳይጨርስ አንደን ይወዝፍ። የሹም ሰነፍ፤ አይለፍ አይለፈልፍ። የሹም ከርፋፋ አገር ያጠፋ(ል)፤ የአህያ ጀላፋ መስክ ያጠፋ(ል)። የሹም ዗ፋፋ፥ አገር ያጠፋ። (዗ፋፋ ~ ከርፋፋ) የሹም ድሮ ነኝ፤ እሽ አትበሉኝ አለች። የሹም ገፋፋ አገር ያጠፋ፤ የአህያ ጀላፋ መስክ ያጠፋ። የሹም ጦሩ፥ እቅፍ ሙሉ። የሹክሹክታ ግቢ፥ ለፍች ያስቸግራል ገርጋሪ በቅል ይደነብራል። (ግቢ ~ ጋብቻ) የሺ ሞት ሰርግ ነው፤ የአንድ ሞት ጉዳት ነው። የሺ ቃል ንቁፍ፤ የዋና ቃል ጽሐፍ። የሺ አከላት፥ መሰብሰቢያው አናት። የሺ ከብቱን፤ የአንድ ሚስቱን። የሺ ገን዗ብ ብላ፥ ወንድሙን አትንካ። የሺ ገን዗ብ ብላ፥ ከሺ ወንድም አትጣላ። የሺ ገን዗ብ ተቀበል፤ የሺ ወንድም አትግደል። የሺ ፍልጥ፥ ማሰሪያው ልጥ። የሺን ገን዗ቡን ብላ፥ ወንድሙን አትንካ። የሽሮ ድንፋታ፥ እንጀራ እስኪመጣ። የሽማግላ አቃጣሪ፤ የቆማጣ መታሪ። የሽማግላ አገር አይወረርም። የሽማግላ እጁ ክት (የተሰበሰበ)፥ አንደበቱ ነገር አያሳስት። የሽማግላ ፍቅር እና የክረምት አበባ አንድ ነው። የሽሮ ድንፋታ፥ እንጀራ እስኪገባበት ድረስ ነው። የሽሮ ድንፋታ፥ እንጀራው እስኪመጣ (ነው)። የሽሮ ድንፋታ፥ ከእሳት እስኪወጣ። የሽሮ ፉከራ፥ ከምጣደ እስኪወጣ እንጀራ። የሽንኩርት ላባ አታላይነቱ፥ ልሽተት ማለቱ። የሽኮኮ ዳቦ ለመስበኪያ፤ ቀጭን ቋሬ ለማረግረጊያ። የሽኩሹኩታ ግቢ፥ ለፍች ያስቸግራል። የሽኮኮ ጸልት:_ መጨረሻው የማያምር፥ ማደናገሪያ፥ ማታለያ። የሾተላይን ልጅ፥ የገበታ ውሃ ይወስደዋል። የሽኮኮ ጸልት። የሿዳ ፍየል፥ እናቲቱ አሞላ፥ ልጅቱ አሞላ። የቀማኛ የለው እጅ፤ የበቅል የለው ልጅ። የቀረ ይቀራል እንጂ፥ ቀርቅር ብዬ አልጣራም። የቀበረ ተቀበረ። የቀበሮ ባሕታዊ፥ ከበግ መሀል (ገብቶ) ይፀልያል። የቀበሮ ባሕታዊ የለም። የቀበሮ ብልጥ፥ የበግ ደበል ይለብሳል። የቀበሮ ጻድቅ፥ በበግ መሀል ትሰግዳለች። የቀበጠ ሸክላ፥ ከብረት ይላፋል። የቀበጠች አይጥ፥ በድመት ጭራ ዗ፈን ት዗ፍናለች። የቀበጠች አይጥ፥ የድመት አፍንጫ ታሸታለች። የቀበጡ ዕለት፥ ሞት አይገኝም። የቀበጡ ዕለት፥ አይገኝም ሞት። የቀባጣሪ፥ አፉ ጠማማ ነው። የቀና ቢታጣ፤ ይመለመላል ጎባጣ። የቀን እንጂ፥ የሰው ደግ የለውም። የቀን ወራሪ፤ የላሉት ስባሪ። የቀን ጠማማን፥ ሚዳቋ አት዗ለውም። የቀን ጨዋታ፥ አይገኝም ማታ። የቀደመን ሞት ይወስደዋል። የቀደመው ያገሳታል፤ ደግሞ ደግሞ ያጎርሣታል። የቀድሞ አርበኛ፥ የቅምጥ ይዋጋል። የቀድሞ ወዳጅህን በምን ቀበርከው? በሻሽ የኋለኛው እንዳይሸሽ። የቀጂ ልጅ፥ ጠጪ። የቀጣፊ ቃል፤ የገማ እንቁላል ካልተሰበረ አይሸትም። የቀጣፊ እንባ፥ ባቄላ ያክላል። (ባቄላ ~ እንቧይ) የቁልቋል ሳንቃ፥ በቃ ሲሉት ነቃ። የቁልቋል ወተት፥ አንዳም ናጡት ሺ ጊዛ፥ ቅቤ አይወጣውም። የቁማር ገበያ እጅግ ተፋፍሞ፥ ሀገሬ ተበላች ሕዝቧ ከዳር ቆሞ። የቁም ነገር፥ ስልቻ ለብቻ። የቁርበቶችን ተግባር እኛ እናውቃለን አለ ጅብ። የቁጡና የዕብድ ስካር አይታወቅም። የቁጣ ሩጫ ባለቤቱን ገደለ። የቁጥር መጨረሻ ዝም። የቂል በትር፥ ሆድ ይቀትር። የቂል ዗መድ፥ ከገበያም አይገድ። የቂል ጑ደኛው፥ ቂል። የቂጣ እንደኹ ይጠፋል፤ የማርገዝ እንደኹ ይገፋል። የቂጥ አጋሚ፥ ፈስ ነው፥ ወሮታው። የቃላት ሙሽራ፥ ሰርግ አያደምቅም (ነውና)። የቃል ዗መድ፤ ከገበያም አይገድ። የቃመ ተጠቀመ፤ ያልቃመ ተለቀመ። የቃርያ እልክ፥ አወፈረኝ። የቄስ ልጅ በአገባ፥ በሜሮን ፈትፍቼ እበላ ነበር አለ። የቄስ ልጅ፥ እግዛር አጎቱ ይመስለዋል። የቄስ ሚስት አወቅሽ ቢሎት መጣፍ አጠበች። የቄስ ምንደኛ፤ የሴት በትረኛ። የቄስ ሞገደኛ፤ የሴት በትረኛ አያድርስ ከእኛ። የቄስ ሹመት፤ የመሪ ሽሽት(አይዋጥልኝም)። የቄስ ቀማኛ፤ የዳኛ ምቀኛ። የቄስ ቃል፥ አንድ ይበቃል። የቄስ ነጋዳ ቢያረጅ አቃቢ ይሆናል፤ ጋለሞታ ብታረጅ አማጭ ትሆናለች። የቄስ ነጋዳ፥ ይመስላል ወንበዳ። (ይመስላል ~ ይሆናል) የቄስ አባይ፤ የደበል ተባይ። የቄስ ጠበቃ ዳዊት ይጠቅሳል። የቅል ውሃ አያኮራም። የቅማል ስደት፤ ከራስ ወርድ ከአንገት። የቅማል ስደት፤ ከጭንቅላት ወርድ ከአንገት። የቅሬ ከናፍር፤ የኩሸት መደብር። የቅርቡን በደጅ፤ የሩቁን በአዋጅ። የቅርብ አራሽ፤ በእንቅብ አፋሽ። የቅርብ አዝመራ፥ ለጤና። የቅርብ ጠበል የልጥ መንከሪያ ይሆናል። የቅድሙ በዚ፤ የአኹኑ ተንዚዚ። የቆለኛ ምስክር፥ ከጥይት ይፈጥናል። የቆመ ቀለጠ፤ የሮጠ አመለጠ። የቆመ ላባ፥ የተቀመጠውን ይቀማ። የቆመው እግር ቢሆን፥ አሳቢው ራስ ነው። የቆመው ግንድ ተቆርጦ፤ የወደቀው ተፈልጦ። የቆሰለ አራዊት፤ የተከበበ ሰራዊት። የቆሰለ አውሬ፥ በቅጡ ማሰብ አይችልም፥ የአገኘውን ዅሉ ይነክሳል። የቆረጠ አመለጠ። የቆቅ አውራ፥ ይውላል ተራራ። የቆቅ ጋጋታ፥ ለውሻ ሰርጉ ነው። የቆየ ከሚስቱ ይወልዳል። የቆዳ ጑጑ታ ለውሻ ሰርጉ ነው። የቆጡን ስታይ፥ የብብቷን ጣለች። የቆጡን አወርዳለኹ ብላ፥ የብብቷን ጣለች። የቆጡን አወርድ ብላ፥ የብብቷን ጣለች። (ጣለች ~ ጥላ) የቋመጡትን ሲያጡ፥ የጠሉትን ይቀላውጡ። የበለጠ ቢመጣ፥ የቀድሞውን ያስረሳ። የበላ በለጠኝ፤ የሮጠ አመለጠ(ኝ)። የበላ ቢሮጥ፥ አያመልጥ። የበላ ቢያብል፥ ገላው ይነግር። (ይነግር ~ ይናገር) የበላ ቢያብል፥ ፊቱ ይመሰክራል። የበላ ባይማታም፥ ደላ ይችላል። የበላ ዳኛ፤ የወጋ መጋኛ። የበላበትን ወጭት ሰባሪ። የበላች ብት዗ፍን፤ ያልበላች ታዝን። የበላችው ያስታውካታል፥ በላይ በላዩ ያጎርሧታል። የበላችው ያገሳታል፥ በላይ በላዩ ያጎርሣታል። የበላና የተደገፈ፥ ወድቆ አይወድቅም። የበላን ሆድ ያውቃል፤ የወጋን ክንድ ያውቃል። የበላው አብላላው። የበላን ሆድ፤ የወጋን ክንድ ያውቃል። የበላውን ያብላላዋል፥ የለበሰ(ው)ን ይበርደዋል። የበላይ አዳባይ። የበረታ ከራሱ፤ የሰነፈ ከዋሱ። የበረደውን አሙቆ፤ የረጠበውን አድርቆ። የበራ ሻማ፥ ላላውን ያበራል። የበሬ ሆዳም፥ ቢሞት(ም) አይጎዳም። የበሬ ሆዳም፥ ቢታረድም አይጎዳም። የበሬ ሳቢ፤ የቤት አሳቢ ይስጥህ። የበሬ ሻኛማ፤ የላም ግታማ። የበሬ ቀንደ(ን)፤ የወይራ ግንደ(ን)። የበሬ እቃ፤ እየራሱ አለቃ። የበሬ ዳተኛ፤ የሴት ምላሰኛ አታምጣ ወደኛ። የበሬ ድሰኛ፤ የሴት ምላሰኛ አያድርስ ወደኛ። የበሬ ዳተኛ፥ በመሀል ይተኛ። የበሬም ዋይ ይውላል ገበያ፥ ሥጋው ለመብል ቆዳው ለጠፍር። የበሬን ምሥጋና፥ አህያ ወሰደው። የበሬን ውለታ፥ አህያ ወሰደች። የበሰለ ሥጋ(ን)፥ የሚበላው አያጣም። የበሰለ ይበላል፤ ጥሬ በምጣድ ይቆላል። የበሰበሰ ዕንጨት አይጠረብም። የበሰበሰ፥ ዝናብ አይፈራም። የበሶ አቅማዳ ተፈትቶ፤ የላባ አፍ ነጥቶ። የበሶ አቅማዳ ተፈትቶ፤ የተሸካሚው አፍ ነጥቶ (ይመስላል?)። የበሶው ስልቻ አፉ ተፈትቶ፤ ሰውየው አፉ ነጥቶ። የበሽታ ክፉ ቁርጥማት፤ የኀጢአት ክፉ ቅናት። የበሽታ ክፉ፥ እህል ያስወድዳል። የበቀለውን እየነቀለ፤ የታጨደውን እየበተነ። የበቅል እቃ፤ እየራሱ አለቃ። የበቅል ክበድ፤ የሀር ገመድ (አለኝ ይላል አማጭ ለልማደ)። የበቅል ክበድ፤ የሀር ገመድ ይዤ ምን አጥቼ። የበዚ ቢመጣ፥ የቀድሞውን ያስረሳ። የበደለ ይካስ፥ የቀማ ይመልስ። የበደለ ይካስ፤ የወለድ ይላስ። የበደል በደል፥ በቦሀ ላይ ቆረቆር። የበጌምድር ደቄት ክፉ ነው ብያ ሽርንክት፤ እኛስ አስልመን በላነው ይብላን ለቀረ ሰው። የቡሄ ዕለት የደነቆረ፥ ሆያ ሆዬ ሲል ያረጃል። የቡሄ ዕለት ያበደ፥ ሆ እንዳለ ይኖራል። የቡሬ ጥጃ አባቱ ኹለት፤ ከአንደ ይጠጋል አንደኛው ሲሞት። የቡና ስባቱ፥ መፋጀቱ። የቡና ቀዝቃዚ፤ የሹም ፈዚዚ። የቡዳ ድሀ፤ የፈረንጅ ወረኃ የለውም። የባለቤት ልጅ፥ ቤት ሉሠራልህ ነው ያሉት እንደሆነ፥ ከስቶ ያድራል። የባለቤት ሰነፍ፥ ቤቱን ያዋርዳል። የባለቤት አዳይ፥ ጦም ያሳድራል። የባለቤት ዕውር፥ እቃውን ያነሣል። የባለጌ ልጅ እያደር ይጋጃል፤ የጨዋ ልጅ እያደር ይበጃል። (ይጋጃል ~ ይጃጃል) የባለጌ ልጅ:_ ከመብል ይደፍር፥ ከነገር ያፍር። የባለጌ ልጅ:_ ከመንገድ ይፈጃል፥ ከነገር ይጃጃል። የባለጌ ባለሟል ቂጥ ገልቤ ልይ ይላል። (ልይ ይላል ~ ያያል) የባለጌ ባለሟል ከአፍ አታውጡኝ ይላል። (አታውጡኝ ~ አትለዩኝ) የባለጌ ተለጣጭ፥ ከድንጋይ ላይ ተቀማጭ። የባለጌ ኀይለ ቃል፥ እንደ ሽመል ይወቃል። የባለጌ ሃይማኖት፥ ከጅማት ይከራል። የባለጌ ልጅ መብል ያፍር፥ ነገር ይደፍር። የባለጌ ልጅ:_ መንገድ ይፈጅ፥ ነገር አይፈጅ። የባለጌ እምነት፥ ሳይገድል አይለቅም። የባለጌ ኩራቱ፥ እንዱያው (ነው) በከንቱ። የባለጌን ጠበቃ፥ አብረህ ውቃ። የባላገር ሥልጡን፥ እሰው ፊት ይቆርሳል። የባላገር ሥልጡን፥ እጅ ይዝ ይጫወታል። የባላገር እንግዳ ሞት፤ የባልቴት ሳደላ መሬት። የባላገር ደለት፤ ይፈታል በኩበት። የባል ደግነቱ፥ ውሽሜን መርሳቱ። (ውሽሜን ~ ውሽምን) የባል ደግነቱ፥ ባትናገር ሚስቱ። የባል ዗መድ እዳርቻ፤ ሲከስም ቆይ ብቻ። የባል ዗መድ፥ በአይኑ አመድ። የባልቴት ወብራ፤ የክረምት ብራ። (ወብራ:_ ቀበጥ) የባሰ አለ፥ ሚስትህን አትፍታ። የባሕር ዳር ሲታረስ፥ ጑ጉንቸር ሆድ ይብሳታል። የባለሥር፥ ምላሱ አሥር። የባሪያ አሳላፊ፤ ደሞዙ ትራፊ። የባሪያ እረፍቱ፥ ኮሶ የቀመሰ ቀን ነው። (የቀመሰ ~ የጠጣ) የባሪያ ንጉሥ፥ ደኅና ሥጋ ቢያሳዩት፥ ዓይኑ ወደ ፈርስ። የባቄላ ማሳ፥ ከገደል አይነሣ። የባሰ አለና፥ አገርህን አትልቀቅ። የባሰበት እመጫት ያገባል። የባሰበት፥ አህያ ፈሳበት። የባዕድ ሞኝ ከ዗መድ አስተካክሉኝ ይላል፤ የ዗መድ ሞኝ ከልጅ አስተካክሉኝ ይላል። የባዕድ ሞኝ ከ዗መድህ እኩል አድርገኝ፤ የ዗መድ ሞኝ ከልጅህ እኩል አድርገኝ። የባዕድ ፍቅር፥ የውሃ ጌጥ አንድ ነው። የባዕድ ፍቅርና፥ የገለባ እሳት አንድ ነው። የባዳ ሞኝ፥ ከልጅህ እኩል አድርገኝ ይላል። የባዳ ሞኝ ከ዗መድ እኩል፤ የ዗መድ ሞኝ ከልጅህ እኩል አርገኝ ይላል። የቤቴ መቃጠል፥ ለትኋኑ በጀኝ። የቤት ቀጋ፤ የሜዳ አልጋ። (የሜዳ ~ የውጭ ~ የደጅ ~ የደር) የቤት ቤት አለው ማጀት፤ የሆድ ሆድ አለው አንጀት። የቤት አመል፥ (አብሮ) ገበያ ይወጣል። የቤት ጣጅ፤ የደር ጠማጅ። የቤት ጥጋብ፥ ያለ ሥንቅ ያ዗ምታል። የብልጥ አይን፥ ቶል ያለቅሳል። የብልጥ አይን፥ አስቀድሞ ያለቅሳል። የብረት ቆል፤ የድንጋይ ንፍሮ። የብርቱካን ውሃውን፤ የሽማግላ ምክሩን። የብትር ትሕትና ያስመታል፤ የነገር ትሕትና ያስረታል። የብዙ ሕዋሳት፥ መሰብሰቢያው አናት። የብድር ሽሮ፥ ምን ሲል ተጀምሮ? የቧልተኛ ልላ፥ ሳይሰለፍ ያረጃል። የተለጎመ በሬ፥ ከቀንበሩ ቢያመልጥ ቢላዋ ይጠብቀዋል። የተለፋን ቆዳ ላልተለፋ መለወጥ፥ ለ዗ጥ ዗ጥ። የተላከ፥ አፉን ለከከ። የተላጠ ዕንጨት ዳግም አይላጥም፤ ሰው አለ አንድ ጊዛ አይበለጥም። የተልባ ስፍር፤ የሕልም እንጀራ። የተላጠ ዕንጨት፥ ኹለተኛ አይላጥም። የተልባ ድጥ ነው። የተመረቀ፥ ከሰይጣን ራቀ። የተመረጠ ዕንጨት ለታቦት፤ የተመረጠ ሰው ለሹመት። የተመታ ዳነ፥ ደም የተፈናጠቀበት ሞተ። የተመሰከረ ይፈረዳል፤ የሰባ ይታረዳል። የተመረረ ድሀ፥ ይገባል ከውሃ። የተመቸው፥ ገንፎ ያላምጣል። የተመኘነውን አገኘነው። የተመክሮ ሙግት፥ ቢያልቅ አይተኩበት። የተማመኑት ቢላዋ፥ በጉበት ይሰበራል። የተማማሉት ማለኛ፤ የተጋደሉት ጠበኛ። የተማረ፥ ለፍቶ ቀረ። የተማረ መልካም፥ ጥቃት አያስነካም። የተማረ ተናቆረ። የተማረ፥ ነፍሱን የመረመረ። የተማረ፥ ክብሩን መረመረ። የተማረ (የ)ተሟረ። የተማረና ታጥቦ የተቀመጠ ብርጭቆ፥ ፈላጊ አያጣም። የተማሪ ቤት ያላየ፥ ሳንቃ ያልመታው ልጅ መልካም አይሆንም። የተማሪ ደረጃው፥ እንደ መምህሩ ነው። የተማሪ ጋፍ፥ መልክ ያጋፍፍ። (ያጋፍፍ ~ ይጋፍፍ:_ይሰበሥብ) የተማሪ ጋፍ፥ መልክ ይገፍ። የተማከሩት ዳኛ ያግዚል፥ የመተሩበት እጅ ይወዚል። የተሟጋች ሚስቱ፥ ቧጋች። የተረገ዗ በሆድ፤ የታ዗ለ በለምድ። የተራሰ ገመዳ፤ የተቆፈረ ጉድ጑ዳ። የተራበ አይ዗ፍንም፤ የጠገበ አያርፍም። የተራበ ከባቄላ፤ የተበደለ ከሰቀላ። የተራጋጭ ወተት፤ ያንጎራ጑ሪ ጉልበት። የተሸሸገ ምግብ፥ ሆድ አይጠፋለትም። የተሸሸገ ምግብ፥ የተሸሸገ ሆድ አያጣም። የተሳለ ብረት፥ አንገትን ከደረት ሥጋን ከጅማት (ይለያያል)። የተረታ ሉከፍል፥ ዳኛ ምን አስጨነቀው። የተሸከመው ከብድታል፥ እንደገና ይጨምርበታል። የተሾመ ወደ ግምጃ፤ የተሻረ ወደ ሙጃ። የተሾመ ይሟገቱለታል፥ በተሻረ ይመሰክርበታል። የተሾመን ይሟገቱበታል፤ የተሻረን ይመሰክሩበታል። የተቀመጠ ማርና ልጃገረድ፥ የሚሆኑት አያጡም። የተቀመጡ ማዕረግና ልጃገረድ፥ የሚሆኑት አያጡም። የተቀማጭ፥ ምላሱ ምላጭ። (ምላሱ ~ አፍ) የተቀቀለ ባቄላ፥ ዗ር አይሆንም። የተቃቃ ገመድ፤ የተቆፈረ ጉድ጑ድ። የተቆለፈ ወርቅ፤ ያልተቆለፈ ጨርቅ። የተቆረጠው እጅሽ፥ የቆረጠው እጅሽ፥ እንግዱህ ምን ይበጅሽ። የተበደለ ከነጋሽ፤ የተጠማ ከፈሳሽ። የተበደለ ይማጠናል፤ የተሰበረ ይታጠናል። የተታታ ገመዳ፤ የተቆፈረ ጉድ጑ዳ። የተነቃነቀ ጥርስ ሳይወልቅ አያርፍም። የተነቃነቀ ጥርስ ሳይወልቅ አይቀርም። የተናቀ መንደር በአህያ ይወረራል። (መንደር ~ ሰፈር) የተናቀ ብዕር ይገነፍላል። የተናቀ እንትን፥ ሆድ ይጎጥራል። የተናቀ (እንትን) ያስረግዚል። የተናካሽ ውሻ፥ የጅብ መቋደሻ። የተናገሩት ሲጠፋ፥ የወለደት ይጥፋ። የተናገሩት ከሚጠፋ፥ የወለደት ይጥፋ። (ይጥፋ ~ ቢጠፋ) የተናጠ ወተት፥ ቅቤ ይወጣዋል። የተንቀለቀለች፥ አፍሳ ለቀመች። የተንቀጀቀጀች ውሻ፥ ለአፏ ሉጥ፥ ለወገቧ ፍልጥ አታጣም። የተኛችው ሳለች፤ ያዳመጠችው አረገ዗ች። የተኛውን አንበሳ፥ አስነሣችው ላም ልሳ (ልሳ)። የተከፋ፥ (ጨርሶ) ተደፋ። የተኩላ ባሕታዊ፥ እበጎች መሀል ይሰግዳል። የተ኱ሉትም ባል አጥተዋል። የተወለደት ይራባሉ፥ እንደገና ይወልዳሉ። የተውሶ ይመለሳል፥ ታጥቦ ተተኩሶ። የተ዗ጋ ተጠበቀ፥ ያልተ዗ጋ ተሰረቀ። የተደረገ ተደርጎ፥ እንዳለ መስማት በጎ የለም። የተደረገላትን ረድኤት ትታ፤ የተሠራላትን ውለታ ዗ንግታ። የተደፋ ሬሳ፤ የተጠበሰ አሣ። የተገነ዗ች ነፍስ፤ የተለጎመች ፈረስ። የተገኘ ጥበብ፥ ከድሮና ከንብ። የተገ዗ተች ነፍስ፤ የተለጎመች ፈረስ። የተግደረደረ፥ ጦሙን አደረ። የተጠማ ከፈሳሽ፤ የተበደለ ከነጋሽ። (የተበደለ ~ የተጠቃ) የተጠረጠሩበት፥ ድንጋይ ይጥሉበት። የተጠገነ በትር፥ እንደ ልብ አያሰነዝር። የተጠገነ እጅ፥ እንደ ቀድሞው አይሆንም። የተጣደፈን፥ ቅቤ ያንቀዋል። የተጻፈ ይወረሳል፤ በቃል ያለ ይረሳል። የተጻፈ ይወሳል፤ ያልተጻፈ ይረሳል። የተጻፈው ዅሉ፥ እኛ እንድንመከርበት ተጻፈ። የተፈተለ ከኹለት፤ የተታታ ከሦስት። የተፈተለ ይለበሳል፤ የተጀመረ ይጨረሳል። የተፈጠመ አይናገር፤ አንካሳ አይሻገር። የተፈጠመ ያርፋል፤ የተኛ ያኮርፋል። የተፉትን ነገር መልሰው ቢውጡት፥ ተራራ ያህላል። የታለህ ያላሉት፥ እዙህ አለኹ ይላል። የታመመውን፥ ሙት፥ ጠየቀው። የታመነ ልላ፥ ጠጅ የመላበት ብርላ። የታቀፈችው እናቲቱ፤ የሚላጨው አባቱ። የታነቀ የልቡን ይናገራል፥ ግን የሚያምነው የለም። የታናሽ ልጅ አሳናሽ፥ የ዗ንጋዳ ወጥ እህል አበላሽ። የታ዗ለ በለምድ፤ የተረገ዗ በሆድ። የታደለ ተደላደለ። የታደለች ሴት፥ በፊት ትወልዳለች ሴት። የታደለች ቤት፥ አሮጌ ታያለች። የታገሠ አፈሰ። የታጠበ እጅ፤ ያልባለቀ ልጅ። የት ላይ ተቀምጠሽ፥ እግዛርን ታሚያለሽ። የት ትኼዳለህ? እሐዳዳቸው፤ ምን ያሮጥሀል? ውቃቢያቸው። የት ትኼጃለሽ ቢላት፥ በታክሲ አለች። የት ነው አገርህ? አህያ ፈጅ ከማዝር ከመጠምጠም፥ እንዱያው ጅብ ነኝ አትልምን። (ከመጠምጠም ~ ከማጠምጠሙ) የት አውቅሽ ብል፥ አጥብቆ ሳመኝ። የት ይደርሳል ያሉት ጥጃ፥ ል኱ንዳ ተገኘ። የት ይደርሳል የተባለ ዚፍ፥ ቀበላ ቆረጠው። የትሕትና በትር ያስመታል። የትልቅ ሰው ቤት፥ መግቢያው ቁልቁለት መውጫው ግን ዳገት ነው። የትም ተከሰስ፤ አለቃህ ድረስ። የትሕትና በትር ያስመታል፥ የትሕትና ሙግት ያስረታል። የትም ተወለድ፥ አንኮበር እደግ። የትም ፍጪው፥ ደቄቱን አምጪው። (ደቄቱን ~ ደጬቱን) የትምህርት ሙግት፥ አንድ ተናግሮ ጉልት። የትንሽ ሰው ፍቅር፤ (በ)መቀምቀሚያው ጥቁር። የትእቢት መድኀኒቱ፥ ጭንቀት። የትእቢትና የብርድ፥ ክንብንብ ይታወቃል። የትውልድ ጉልበቱ ሕብረቱ፤ የሕዝብ ሀብቱ አንድነቱ። የቸኮለ፥ አፍስሶ ለቀመ። የቸኮለች፥ አፍስሳ ለቀመች። የቸኮለች፥ እየሮጠች ኼደች። የቸገረው ርጉዝ ያገባል። የቸገረው ርጉዝ ያገባል፤ ስትወልድበት ገደል ይገባል፤ የባሰበት እመጫቷን። የቸገረው ርጉዝ ያገባል፥ የባሰበት እመጫት (ያገባል)። የቸገረው ሽማግላ፥ ገልብጦ ይፈርዳል። የቸገረው ደቄት፥ ከነፋስ ይጠጋ። የቸገረው ደቄት፥ ከነፋስ ይጠጋል። የቻለ በቦላ፥ ያልቻለ በባላ። የችግር ክፉ:_ እህል ማጣት፤ የኀጢአት ክፉ:_ ነፍስ ማጥፋት። የነ ቶል ቶል ቤት፥ ግርግዳው ሰንበላጥ። የኀጥኡ ዳፋ፤ ጻድቁን ያዳፋ። (ያዳፋ ~ አዳፋ) የኀጥኡ ዳፋ፥ ጻድቁን ይደፋ። የኅዳር ዝናብ፤ የታኅሣሥ ጀንበር። የሕግ ጣጣ፤ የባንክ ዕዳ። የነ ቶል ቶል ቤት፥ ግርግዳው ኖራ ነው። የነሀሴ ውሃ ጥሩ ነው የሚጠጣው የለም፤ የድሀ ነገር ፍሬ ነው የሚሰማው የለም። የነቂሉ ቤት፥ ግርግዳው ሰንበላጥ። የነበረ ይናገር፥ ያየ ይመስክር። የነበረ፤ ገብርኤል ተወገረ። የነብር ልጅ አይታቀፍ፤ የጨዋ ልጅ አይነቀፍ። የነብር አይን ከፍየል፤ የፍየል አይን ከቅጠል። የነብር አይን ወደ ፍየል፤ የፍየል አይን ወደ ቅጠል። የነብርን ጅራት አይዙም፥ ከያዙም አይለቁም። የነብርን ጅራት አይጨብጡም፥ ከጨበጡም አይለቁም። የነብርን ጭራ አይዙም፥ ከያዙም አይለቁም። የነቶል ቶል ቤት፥ ግርግዳው ጭራሮ ነው። የነገሩትን የማይረሳ፤ የለመኑትን የማይነሣ እግዛርን አትርሳ። የነገር ቅራቅንቦ፥ የእጅ መንሻ እንጂ፥ ጸሀፊ አያሰኝም። የነገር ትሕትና ያስረታል፤ የብትር ትሕትና ያስመታል (ያስረታል ~ ያስታል) የነገር አባቱ፤ የፈትል አይነቱ። የነገር ወጡ፥ መደመጡ። (መደመጡ ~ ማዳመጡ) የነገር ደበል፥ ጉኒና አይሆንም፥ ቢሆንም አያሞቅም። የነገር ጠማማ፥ በሽማግላ ይታረቃል። የነገር ጠማማ፥ ያስከትላል ሳማ። የነገር ጣዕሙ ዝግታ፤ የአዋቂ ጣዕሙ ዝምታ። የነገር ጣዕም በጆሮ፤ የእህል ጣዕም በጉረሮ። የነገን ነገ ይፍረደው። የነገደ አበደ፤ የአረሰ ነገሠ። የነገደ አተረፈ፤ ያለፈ ተራገፈ። የነጋሪት በቅል፥ ከላይሽ ማን ወርድ? የነጭ አጣጭ እንጂ፥ አማች የለውም። የነፉክክር ቤት፥ ሳይ዗ጋ ያድራል። የነፍሰ ገዳይ ምልክቱ፥ ደም በጣቱ። የነፍስ ትቶ፥ የገብስ። የኑሮ ክፉ ደባል፤ የመንገድ ክፉ ገደል። የኑግ ገለባ፥ እያገርህ ግባ። የኑሮ ክፉ፥ ደባል። የናቀ ወደቀ። የናቁት፥ ያስቀራል ራቁት። የንጉሥ መቃብር፥ ንጉሥ ይወልዳል። የንጉሥ ሞት፤ የፀሓይ እርበት። የንጉሥ ቁጣ፥ የመልአከ ሞት ያህል ያስፈራል። የንጉሥ ቃል:_ አነሰ ብል አይጨመር፥ በዚ ብል አይቀነስ። የንጉሥ ቃል፥ አንድ ይበቃል። የንጉሥ ቃል:_ አጠረ ብለው አያስረዝሙት፥ ረ዗መ ብለው አያሳጥሩት። የንጉሥ አሽከር:_ ስሙ ወርቅ፥ ልብሱ ጨርቅ። የንጉሥ አዋጅ፥ ለዅሉ ይበጅ። የንጉሥ እንግዳ፥ አያድር(ም) ምድረ በዳ። የንጉሥ ዕድር፥ አናት አያስቀብር። የንጉሥ የእጨጌ ከብት፥ በየወገኑ ይከተት። የንጉሥ ግንቡን፥ የሹም ልቡን። (የሹም ~ የብልኅ) የንፉግ ለጋስ፥ የሰጠውን ይወርስ። (ይወርስ ~ ይመልስ) የንጉሥ ልጅ:_ አ዗ን ቢነግሩት አደን። የንፉግ ገን዗ብ በለጋስ እጅ ይገኛል፥ የጠላት ገን዗ብ በወዳጅ እጅ ይገኛል። የንፍጣም፥ ነገሩ አይጥም። የንፉግ ገን዗ብ በለጋስ እጅ፥ የጠላት ገን዗ብ በወዳጅ። "የአህያ ""እቃው""፥ ሆደ ውስጥ ነው። የአህያ እንግዳ፥ የጅብ እራት ነው። የአህያ ከአልጋ፥ ሲሉት እምድር።" የአህያ ልጅ ጥል ይረግጣል፤ የፈረስ ልጅ ጥል ይደነግጣል። የአህያ ሥጋ፥ መደብ ሲሉት አመድ። የአህያ ሥጋ፥ አልጋ ሲሉት መሬት። (መሬት ~ ከምድር ~ ከአመድ) የአህያ ሥጋ፥ አልጋ ቢሉት አመድ። የአህያ ሥጋ፥ ውርደተኛ፥ አልጋ ላይ ቢያኖሩት፥ እመሬት ይተኛ። የአህያ ቀበጥ፥ ከጅብ ጡት ይጣባል። የአህያ ባል ለሚስቱ ስጦታ ገዚ። የአህያ ባል፥ ሲስም ያሳምማል። የአህያ ባል፥ ቀለበት አያሥርም። የአህያ ባል፥ ከጅብ አያስጥል(ም)። የአህያ ባል፥ ከጅብ ጉቦ በላ። የአህያ ውሃ ጠጭ፥ ሳይታወቅ መጣጭ። የአህያ ደግነት፥ ጭነት ማብዚት። የአህያ ጀላፋ መስክ ያጠፋ፤ የሹም ዗ፋፋ አገር ያጠፋ። የአህያ ፍለጋና፤ የጥሬ እራት በጊዛ ነው። የአህያ ፍሪዳ፤ የእባብ ለማዳ (የለውም)። የአለህ ም዗ዝ፤ የላለህ ፍ዗ዝ። የአለው ማማሩ፥ ምን ቢበዚ ነውሩ? የአለው ማማሩ፥ የላለው መልክ የለው። የአለው ይመዚል፥ የላለው ይፈዚል። የአለው ይም዗ዝ፤ የላለው ይፍ዗ዝ። የአለው ይበላል፥ የላለው ያፈጣል። የአለው ደገሰና የአለውን ጠቀሰው፥ ድሀው እንዳት ይሆን የማይጠነስሰው። የአለው ግንብ ቤት፥ የላለው ሣር ቤት፥ ይህንንም ያጣ ኪራይ ቤት። የአለውን ከአልሰጡ፥ በስም አይበሉ። የአለውን የሰጠ፥ ንፉግ አይባልም። (የሰጠ ~ የወረወረ) የአሉሽን በሰማሽ፥ ኖርዌይ ባልመጣሽ። የአላህን ነገር ምኑን አውቀሽው? ወይ እኔ እበላው አንቺ አርመሽው። የአላማረ ሰርግ፥ ጉልቻው ይሸርፋል። የአላረፈች እግር፥ ከ዗ንድ ጉድ጑ድ ትገባለች። የአላረፈች ጣት፥ አር ጠንቅላ ትመጣለች። የአላባቱ ቢዚቁን፤ አባክኖ ያባክን። የአላሰብከውን አግኝ፥ መረገመም ምርቃን አይደል። የአላሳደጉት ውሻ ቤት ዗ግተው ቢመቱት፥ ዝሮ ይናከሳል። የአላረፈች ምላስ፤ ሸማ ትልስ። የአላወቀ አለቀ። የአላወቁህ ይታጠኑህ። የአላዋቂ ሳሚ፥ ምላስ ይነክሳል። የአላዋቂ ሳሚ፥ ንፍጥ ይለቀልቃል። የአላዋቂ ቆራሽ፤ ማእድ አበላሽ። የአላዋቂ አስተናናቂ። የአላዋጣ ይውጣ። የአልኮል ፍቅር፥ እስከ መቃብር። የአልጋ ሴሰኛ፤ ሦስት ያስተኛ። የአልጫ ድንፋታ፥ እንጀራ እስኪቀርብ (ነው)። የአመላን ብተው ያወላግደኝ። የአመል ትንሽ፥ ይጥላል በጭራሽ። የአመሰገኗት ቅል፥ በአፍዋ ታፈሳለች። የአመነታ ተመታ። የአመኑት ሲከዳ፥ ይቀላል ዕዳ። የአመጣኹት ውሻ ነከሰኝ፤ ያነደድኹት እሳት ጠበሰኝ። የአማከሩት ዳኛ ያግዚል፤ የመተሩበት እጅ ይወዚል። የአምላክ ነገር አይመረመር። የአምላክን ነገር ምኑን አውቀሽው? ወይ እኔ እበላው፥ አንቺ አርመሽው። (ምኑን ~ ስንቱን) የአምና ሞኝ፥ ዗ንድሮም ደገመኝ። የአምናውን ዗ንድሮ፤ የአዋጁን በጆሮ። የአሞላ ጥጃ፥ በወንዞ ትናፋ። የአሞገሱት ሰፌድ፥ ቆል አፈሰሰ። የአሣ ግማቱ፥ (ከወደ) ጭንቅላቱ። (ጭንቅላቱ ~ አናቱ) የአሳር ጠመንጃ፥ ማንገቻው ብረት። የአሣ ግማቱ፥ ከወደ ጭንቅላቱ። የአሥር አለቃዬ ምክትላ ሆይ፥ አንተም እንደ መቶ ትኮራለህ ወይ። የአሥር(ን) እናት፥ ጅብ በላት። የአረሮ ልጅ፥ ጠለፋ። የአረሰ እንደ፥ ልቡ ጎረሠ። የአረሰማ ጎበዝ፥ ዕርፍ የነቀነቀ፥ ወፍጮው እንደ አ጑ራ መስከረም ዗ለቀ። የአረረበት ያማስል። (ያማስል ~ ያማስላል) የአረጀን ሹም ገባር ይከሰዋል፤ የአረጀን ጅብ አህያ ይጥለዋል። የአረገ዗ች ታስታውቅ፥ ከደረቷ ትታጠቅ። የአረገ዗ችውን ታስታውቅ፥ በጡቷ ትታጠቅ። የአረፋውን ሲሎት፥ የጀጀባውን። የአራስ ክፉ መበለት፤ የአደጋ ክፉ እሳት። የአራሷን በእርጉዞ። የአራሷን ገንፎ፥ እርጉዞ ውጣ ሞተች። የአራኝ ልጅ አጥባቂ፤ (የሴሰኛ ልጅ ሣቂ)፤ የአባያ ልጅ ወዳቂ። የአራኝ ልጅ አጥባቂ፤ የአባያ ልጅ ወዳቂ። የአርበኛ ልጅ ይወጋል፤ የአሮጌ ልጅ ያወጋል። የአርጋጅ አናጋጅ። የአሰረ ይፈታል፤ የሰጠ ይረታል። የአሰቡት አይገድ(ም)። የአሰቡት አይገድም፤ ጎኔን ላድርገው ጋደም። የአሣ ግማቱ፥ ከወደ አናቱ። የአሳደኩት ውሻ ነከሰኝ፤ ያነደድኩት እሳት ጠበሰኝ። የአሳደግኋት ጥጃ፥ አለችኝ በርግጫ። የአስለመደት ሰው፥ ኹል ጊዛ እጅ ያያል። የአስተማሪ ትርፉ፥ ሴትና የኹለት ወር እረፍቱ። የአስተማሪ ንብረት፥ ባትሪና ጃንጥላ ነው። የአስተማሪ ደሞዝ፥ ከልደታ እስከ ባታ። የአሽከኮ ዳቦ ለመስበኪያ፥ ቀጭን ሸማ ለማረግረጊያ። የአቀረቡልህን ጉረሥ፥ የተረፈህን መልስ። የአበረ፥ ወገኑን አስከበረ። የአበራሽን ጠባሳ ያየ፥ በእሳት አይጫወትም። የአበሻ መኪና አነዳድ፥ በላላው መንገድ መገድገድ (እንዳይሆን)። የአበሻ ንግድ፥ የላላውን ሥራ ማሽመድመድ። የአበደ ለኑሮው፤ የፈረደ ለጐረሮው። የአበደች ጋለሞታ፥ እናቷን ትመታ። የአበደና የወደደ፥ አንድ ነው። የአበደውን በሬ፥ ቀንደን ይ዗ው አሸንፈው። የአበጠው ይፈንዳ። የአቡነ ዗በሰማያት ጦር፥ ሲወጋ እንጂ አይታይም ሲወረወር። የአቡን የእጨጌ ከብት፥ በየወገኑ ይከተት። የአባ ሆይ መቋሚያ፥ ላዩ ባላ ታቹ ደላ። የአባ ደባደቦ ስልቻ፥ ጤፍ ይቋጥራል ባቄላ ያፈሳል። የአባ ጎፍናኔ፥ ቤቱ በሪድ። የአባበለሽ (ዅሉ) ላያገባሽ፥ ከባልሽ ሆድ አትባባሽ። የአባቱን ቢሰጡት ህይወቱ፤ የአባቱን ቢነሱት ሞቱ። የአባቱን የአገኘ ህይወቱ፤ የአባቱን ያጣ ሞቱ። የአባት ልጅ፥ የማድጋ ድሮ (አንድ) ነው። የአባት ልጅ፥ የደንደስ ሥጋ። የአባት ልጅና ጆሮ አንድ ነው። የአባት ምርቃት አያስገባም ጥቃት። የአባት ሞቱን አይወደ፤ ረድኤቱን አይሰደ። (ረድኤቱን ~ ረጃቱን ~ ረጀቱን) የአባት ሲቀር፤ ምሰህ ቅበር። የአባት ርግማን፤ ሲዳሩ ማልቀስ። የአባት ርግማን፥ ስብራት ነው። የአባት አገር፥ ሞት አያስቀር ሞት አያስፈር። የአባት አገር፥ ከሞት አያስጥልም። የአባት እርግማን፤ ሲዳሩ ማልቀስ። የአባት ወዳጅ፤ የድንጋይ ገድጋጅ። የአባት ያምራል፤ የባዕድ ያናግራል። የአባት ያምራል፤ የባዕድ ያኖራል። የአባት ዕዳ ለልጅ፤ የአፍንጫ እድፍ ለእጅ፤ የወፍጮ ዕዳ ለመጅ። የአባት ወርቅ ባለዝና፤ እህል ለቀጠና። የአባት ዕዳ ለልጅ፤ የአፍንጫ እድፍ ለእጅ። የአባት ደግ ይደልላል፤ የአባት ክፉ ለእንጀራ ልጅ ያደላል። የአባትህ ላም ሲበ዗በዝ፥ ጭራዋን ያዝ። የአባትህ ቤት ሲበ዗በዝ፥ አብረህ ዝረፍ። (ሲበ዗በዝ ~ ሲ዗ረፍ) የአባትህ ቤት ቢበ዗በዝ፥ አብረህ በዝብዝ። የአባትህ አገር ሲ዗ረፍ፥ የድርሻህን መንትፍ። የአባትህና የእናትህ ወገኖች ሲጣሉ፥ ጥግህን ያዝ። የአባትን ሞት አይወደ፤ ረጃቱን አይሰደ። የአባያ ልጅ ወዳቂ፤ ያራኝ ልጅ አጥባቂ። የአባያ እናት አትታረድም። የአባያ ወንድሙ አይታረድም። የአባይ ልጅ፥ ኩሬ። የአባይ ምልክቱ አንደበቱ፤ የጀግና ምልክቱ ሽልማቱ። የአባይ ምሽት፥ እውነት ሳታውቅ ትሞት። የአባይ እንባ አይታገድም። የአባይ ውሃ ተለያየ፥ ሲሉ ተገናኘ። የአባይን ልጅ ኩሬ። የአባይን ልጅ ወዳቂ፤ የዝማ ልጅ ሣቂ። የአባይን ልጅ ውሃ ጠማው፥ የላጭን ልጅ ቅማል በላው። የአባይን እናት፥ ውሃ ጠማት። የአብሮ አደግ ልብ፥ በቁና ይሰፈራል። የአብዬን እከክ፥ ለእምዬ ልክክ። የአብዬን እከክ፥ ወደ እምዬ ላከከ። (ላከከ ~ ልክክ ~ ለከክ) የአቦን መገበሪያ፥ የበላ ይለፈልፋል። የአቦን ፍየል የበላ ይለፈልፋል። የአተር ክምር፤ የጪሰኛ ክብር። የአነበብኩትን ጠቅሼ፤ የሰማኹትን ገምሼ። የአናጢን ልጅ ጅብ በላው፤ የላጭን ልጅ ቅማል ፈጀው። የአንበሳ ልመና፥ ጋማ ይዝ ነው። የአንበሳ ልመና ጋማ ይዝ፤ የቄስ ልመና አናዝ። የአንበሳ ልጅ ሲሞት ቅበር፥ አንበሳ ሲሞት እቤትህ ዋል። የአንበሳ ማላጅ ጋማ ይዝ፤ ጅብን መውጋት አህያን ተገን ይዝ። የአንበሳ ማላጅ ጋማ ይዝ፤ ጅብን መውጋት አህያን ተጎዝጉዝ። የአንበሳ አማላጅ ጋማ ይዝ፤ ጅብን መውጋት አህያን ተገን ይዝ። የአንበሳ አማላጅ ጋማ ይዝ፤ ጅብን መውጋት አህያን ተጎዝጉዝ። የአንበሳ ኮርዱዳና የጨዋ ልጅ ሞግዙት ከመሆን ይሰውርህ። የአንበሳ ገራም፥ የአንተን የሚመስል፥ የእኔም አለኝ ቁስል። የአንቺ ሀሳብ፥ ዗ር እንቁላ ነው። የአንችን አትበዪ ገን዗ብ የለሽ፥ የሰው አትበዪ ምግባር የለሽ። የአንካሳ ልብ ኢየሩሳላም። የአንደ ሀገር ዗ፈን፥ ለአንደ ሀገር ለቅሶ ነው። የአንደ በሬ ሲሞት፥ ለአንደ አጋ዗ኑ ፍስሓው፥ ለአንደ ኀ዗ኑ። የአንደ ቤት ሲቃጠል፥ ለአንደ ቋያው ነው። የአንደ ቤት ሳይጠፋ፥ የአንደ ቤት አይለማ። (አይለማ ~ አይለማም) የአንደ ቤት ከአልጠፋ፥ የአንደ ቤት አይለማም። የአንደ ነገር ለአንደ፥ የእንጀራ ልጁ ነው። የአንደ አገር መልከኛ፥ ለአንደ አገር ገባር ነው። የአንደን ነገር፥ ሰምተህ አትፍረድ። (የአንደን ~ የአንድን) የአንድ ላም ወተት፤ የአንድ ዕርሻ እሸት። የአንድ ሚስቱን፤ የሺ ከብቱን። የአንድ ሰው ነገር፥ ሰምተህ አትፍረድ። የአንድ ሰው፥ ፍቅር በአንድ እጅ እንደማጨብጨብ ያለ ነው። የአንድ ቀን መ዗ዝ፥ ያለ አሥራ ስምንት አይመ዗ዝ። የአንድ ቀን መ዗ዝ፥ ያለ ዗ጠኝ ወር አይመ዗ዝ። የአንድ ቀን ሰርግ፥ ልጅ አላሳደገም። የአንድ ቀን ስሕተት፥ የ዗ላለም ጸጸት ነው። የአንድ ቀን ስሕተት፥ ለ዗ለአለም ዕውቀት ነው። የአንድ በሬ እሸት፤ የአንድ ላም ወተት። የአንድ ዕርሻ እሸት፤ የአንድ ላም ወተት። የአንዶ ዕለት፤ አንዶ ባልቴት። የአንጎር጑ሪ ጉልበት፤ የተራጋጭ ወተት። የአኖሩት ዕንቅርት፥ መለያ ይሆናል። የአኖሩት ዕንቅርት ያገለግላል። የአኖሩት እንክርት ይጠቅማል። የአኩራፊ ምሳ፥ ራት ይሆነዋል። የአኵራፊ ምሳ፥ ራት ይሆናል። የአኩራፊ፥ ምሳው የነበረ ራት ይሆነዋል። የአኮረፈ ምሳው፥ እራቱ ነው። የአኮረፈ፥ ልብሱን አራገፈ። የአወረደ መዓቱን፤ ያመጣ ምሕረቱን። የአወሩ ከሠሩ፤ የሠሩ ከበሩ። የአወቀ ተጠነቀቀ፤ የ዗ነጋ ተነጠቀ። (ተነጠቀ ~ ተወጋ) የአወቀ ናቀ። የአወቀ ተጠነቀቀ፤ ያላወቀ ተነጠቀ። የአወቀ ዗ለቀ፤ ያላወቀ አለቀ። የአወቁ ሲታጠቁ፥ ያላወቁ ተሣቀቁ። (ተሣቀቁ ~ ተሳሣቁ) የአወቁት ጠላት፥ ከወዳጅ እኩል ነው። የአዋቂ ሴት ቤት፥ አለው ውበት። የአዋቂ አጥፊ፥ የእስራኤል ጣፊ። የአዋቂ አጥፊ፤ የጾመኛ ገዳፊ። የአዋጁን በጆሮ። የአዋጁን በጆሮ፤ የዕለቱን በቀጠሮ። የአዋጁን በጆሮ፤ የውኑን በሕልም። የአውሬ ምንነቱ፥ በግብሩ እንጂ፥ በልምደ። የአውሬ ሥጋ፥ ለወሬ። የአዚዥ ቤተ ክርስቲያን ሳሚ፥ የአጋፋሪ ራስጌ ቋሚ። የአዝማሪ ሚስት፥ አልቅሶ ታልነገሯት አታምንም። የአዝማሪ ሚስት፥ አልቅሰው ከአልነገሯት አይገባትም። የአዝማሪ ምሽት አልቅሶ ከአልነገሯት፥ ዗ወትር ቀልድ ይመስላታል። የአዝማሪ ሰርጉ፤ የአስለቃሽ ቀብሩ (አለመድመቁ)። የአየ ላውራ ቢል፥ የሰማ አወራ። (የሰማ ~ ያልሰማ) የአየ ልናገር ቢል፥ የሰማ ላውራ አለ። የአየ ቢኼድ፥ የሰማ ይመጣል። (የሰማ ~ ያልሰማ) የአየ ቢኼድ፥ ያልሰማ ይመጣል። የአየ ይናገራል፥ የተወለደ ይወርሳል። የአየኹ ላውራ ቢል፥ የሰማኹ ላውራ አለ። የአይነ ምድር ስለት፥ አይበሳ መሬት። የአይን ሕመም ክሱት ነው፤ የሆድ ሕመም ልግም ነው። የአይን መጠንቆልን፤ የጉረሮ ማነቅ ያስጥለዋል። የአይን በሽታዋ፥ ጠላትን ማየቷ። የአይን ጨንቋራ ዅሉ ያየዋል። የአይን ጨንቋራ ሰው ያየዋል፤ የልብን ጨንቋራ እግዛር ያየዋል። የአይንን ጨንቋራ ሰው ያየዋል፤ የልብን ጨንቋራ ማን ያየዋል። የአይ዗ጌን ቤት፥ ቡች ታውቀዋለች። የአይጢቱ እላፊ፥ ለምጣድ። የአይጥ ምስክሯ፥ ድንቢጥ። የአይጥ ሞት፥ ለድመት ሰር጑ ነው። (ሰር጑ ~ ሰርግ) የአይጥ ሞቷ፤ የድመት ጨዋታ። የአይጥ ባል፤ የድመት ምሽት ውሃ በወንፊት። የአይጥ እርዳታ፥ በጭራንፎ ያልቃል። የአይጥ እርጉቄ፤ የድመት ወቄ። የአይጥ እርጉዞ፤ የድመት ወዞ። የአይጥ እንግዳ፥ ከስልቻ ውስጥ ጎዝጉዙልኝ ይላል። የአይጥ ጣረሞቷ፤ የድመት ጨዋታዋ። የአይጥ ፉከራ ለመከራ፤ ድመት ምን ሉበላ። የአይጦች መሰናድና አድማ፥ ድመት እስኪደርስ። የአይጦች አድማ፥ ምርጫ ሲደርስ ነው። የአይጦች ዝላይ፥ ለነአቶ ውሮ ሲሳይ። የአደረገችውን ታስታውቅ፥ ከደረቷ ትታጠቅ። የአደረገችውን አውቃ፥ በደረቷ ታጥቃ። የአደሩበት ጭቃ፥ ከጭድ ይሞቃል። የአደን ዕለት ውሻ፤ የሽብር ዕለት ጋሻ። የአደፈ በእንድድ፤ የጎለደፈ በሞረድ። የአደፈውን በእንድድ፤ የጎለደፈውን በሞረድ። የአዱስ አበባ ሰው፥ አይጾም አይበላ፤ አያርፍ አይሠራ። የአዳም ዳፋ፥ ክርስቶስን አዳፋ። የአዳቆነ ሰይጣን፥ ሳያቀስ አይለቅም። የአዳቆነ ሰይጣን፥ የግል ኮላጅ ከፈተ። የአዳኝ ውሻ መነጽሩ፥ ከአፍንጫው ነው። የአዳኝ ውሻ ትርፉ፥ ጠጉር በአፉ። የአዳኝ ውሻ ጠጉር በአፉ፥ ብትር ትርፉ። የአዳይ ጠጪ፤ የግመል ፈንጪ። የአገሩን ሰርድ፥ በአገሩ በሬ። የአገሩን ሰርድ፥ የአገሩ በሬ ያወጣዋል። የአገሬ ሰዎች ተጠንቀቁ፥ የሰረቁት ሥጋ ያስይዚል መረቁ። የአገር ልማት፤ የገበሬ ሀብት። የአገር ልጅ በምን ይመታል? በኩበት፥ ያም እንዳይኼድ ያም እንዳይሞት። የአገር ልጅ በምን ይማታል? በኩበት፥ ያ እንዳይኼድ ያ እንዳይሞት። የአገር ልጅ፤ የማር ጠጅ። የአገር ልጅ፤ የቂጥ እከክ። የአገር ዕድር፥ ለንጉሥ ያስቸግር። የአገር ዕድር፥ ጦም ያሳድር። የአገር ጠላት ሽፍታ፤ የገን዗ብ ጠላት መሸታ። የአገር ልጅ፤ የማር እጅ። የአገርህ ልጅ፥ ብታገባት ሚስትህ ብትፈታት እኅትህ። የአገርህ ደር፥ ፍራትን ያስወግዳል እንጂ፥ ከሞት አያድንም። የአገርሽን ልጅ፥ ብታገቢው ባልሽ ብትፈቺው ወንድምሽ። የአገርን ሰርድ፥ የአገር በሬ ያወጣዋል። የአገባሽ ይፈታሻል፥ ወዮለት ለወለደሽ። የአገባሽስ ይፈታሻል፥ ይብላኝ ለወለደሽ። የአገኘ ከራሱ፥ ያጣ ከዋሱ። የአገኘና የሞተ፥ ዗መድ አያጣም። የአገኘው የሚበላ፥ ድሀ ይበልጣል። የአጣ ለማኝ፥ ተሳድቦ ይኼዳል። የአጣ ሰው፥ ያገኝ አይመስለውም። የአጣቢ ልጅ፥ አለቅላቂ ነው። የአጣጣመ የቆረጠመ። የአጣጣመች ዝንጀሮ፥ (አ)ውድማ ላይ ትንከባለላለች። የአጥንት ፍላጭ፤ የሥጋ ቁራጭ። የአጨሽ ላያገባሽ፥ ከባልሽ ሆድ አትባባሽ። የአጭር ኩራት፤ የሴት ስካር አያዋጣም። የአጭር ኩራት፤ የሴት ስካር አይታይም። የአጸጸውን ሞልቶ፤ የጠበበውን አስፍቶ (ከልዕልና ወደ ልዕልና)። የአፈና በሬ፥ ጠቀራ ይመዚል። የአፌን እስክውጥ ዕድሜ ይስጠኝ ይላል እርኩም። የአፍ ብልኀት ጌትነት፤ የእጅ ብልኀት ባርነት። የአፍ አማኝ፥ ያደርጋል ለማኝ። (ያደርጋል ~ አደረገኝ) የአፍ ዕውቀት ለሹመት፤ የእጅ ዕውቀት ለውርደት። የአፍ ወለምታ፥ በቅቤ አይታሽም። የአፍ ወለምታ፥ በፖሉስ ይታሻል። የአፍ ዗መድ፥ በመንገድ(ም) አይገድ። የአፍ ዗መድ፥ በገበያም አይገድ። (በገበያም ~ ከገበያም) የአፍላ ለማኝ፥ አደረገኝ ለማኝ። የአፍላ፥ የለው ቀርፋፋ። (ቀርፋፋ ~ ቀፋፋ) የአፍላ አማኝ፥ አደረገኝ ለማኝ። የአፍንጫ እድፍ፥ ለእጅ ይተርፋል። የአፍንጫን ንፍጥ፥ አፍ አያስገቡም። የአ጑ኑት ድንጋይ፥ ተመልሶ ራስ(ን) (ይመታል)። የአ጑ኑት ድንጋይ፥ ተመልሶ ይገምሳል። የእሬትን ምሬት ያልቀመሰ፥ የማርን ጣዕም አያውቅም። የእርኩስ መውጊያ አደረገኝ። የእሳት ልጅ አመድ። የእሳት ራት፥ አያውቅም መብራት። የእሷ ጊዛ ተንሰቀሰቀች፥ የሰው ጊዛ ሣቀች። የእረኛ፥ ፈሱ መር዗ኛ። የእሾህ መሀል አበባ። የእባብ ልጅ እፉኝት። የእባብ ደካ ሆነ። የእባብና የሴት ፍለጋ፥ ማነው የሚያወጋ? የእብድ ቀን አያልፍም። የእብድ ቅል፥ ማንጠልጠያው ክር። የእብድ በሶ። የእብድ አሞራ፥ ሲላ ገንደጡሯ። የእብድ አሞራ፥ ሲላ ደንገጡሯ። የእብድ አጫዋች፥ ሙር ነው። የእብድ ዗መድ፥ ሳያማስን አይሰድ። የእብድ ገላጋይ፥ ያቀብላል ድንጋይ። የእብድ ገላጋይ፥ ሾተል አቀባይ። የእብድ ገላጋይ፥ ጎራዳ አቀባይ። የእብድ ገላጋይ፥ ድንጋይ ያቀብላል። የእናት ሆድ፥ ዥንጉርጉር (ነው)። የእናት ሆድ ዝንጉርጉር፥ (ወላጅ ቀይና ጥቁር) (እንደ ነብር ጠጉር)። የእናት ልመና፥ ፊት አያስመልስ፥ አንገት አያስቀልስ፥ ሲሆን በውድ፥ አለዙያ የእናት ሆድ ዥንጉርጉር፥ ወላጅ ቀይና ጥቁር። የእናት ልጅ ቢጣላ እውነት ይመስላል (ለላላ)። የእናት ልጅ አይበላ፤ ሽሮ የላለው ምንቸት አይፈላ። የእናት ልጅ የላለው አይስላ፤ ጆሮ የላለው ምንቸት አይፈላ። (አይስላ ~ አይበላ) የእናት ልጅ፥ የጎን አሳጅ። (አሳጅ ~ አሳጭ) የእናት ልጅ፤ የጎን እጅ። የእናት ሞትና የእግር እሳት እያደር ያቃጥላል። የእናት ሞትና የድንጋይ መቀመጫ እያደር ይቆረቁራል። የእናት ርግማን፥ ወለምታ ነው። የእናት አማላጅ፥ አንገት አያስቀልስ ፊት አያስመልስ። የእናት ድሀ የለውም። የእናትን ክፋት፤ የደመናን ውሃ ጥማት ባለቤቱ ያውቀዋል። (ያውቀዋል ~ ያውቃል) የእኔ ነው የማይል የሞተ፥ የራሱን የማይተው የሞተ። የእኔነህ በለኝ፥ ደስ እንዱለኝ። የእኔነው የማይል የሞተ፥ የራሱን የማይተው የሞተ። የእኔን ችግር፥ ለማን ልንገር? የእኔን ነጭ ጥርስ አይታ፥ ከባሎ ተቆራርጣ ቀረች። የእኔን ወጥ በቀመስሽው፥ የአንቺን በደፋሽው። የእኔው ጠማማ ነው ያስቸገረኝ አለ ዚፍ። የእንሹክሹክታ ግቢ፥ ለፍች ያስቸግራል። የእንቢተኛ መድኀኒቱ፥ ዳኛ። የእንቧይ ካብ። የእንጀራ ሉጥ ይበላል። የእንጀራ ቀንጣቢ፤ የድመት አላቢ። የእንጀራ አብራጃውን፤ የወጥ ለብታውን። የእንጀራ እናቴን እማማ ስላት፥ እውነት መሰላት። የእንጀራ እናት ምን አጠናሽ እንደ ጅማት። የእንጀራ እናት አትሆን እናት፤ ቆል አይሆን እራት። የእንጀራ እናት አንጀት፥ ጠንካራ እንደ ጅማት። የእንጀራ ወጡ፥ ረኃብ ነው። የእንግዳ ለማዳ፥ ያመጣል ብዙ ዕዳ። የእንግዳ ለማዳ፥ ይገባል ከ጑ዳ። የእንግዳ ቅብጢ፥ ባለቤት ያጎርሣል። (ቅብጢ ~ ቀበጥ) የእንግዳ ችኩል፥ ባለቤትን ያጎርሣል። (ባለቤትን ~ ባለቤቱን) የእንግዳ አይን አፋር፥ ባለቤቱን ይጋብዚል። የእንጦጦ መምህር ቢናገር በዓመት፥ ያውም ሬት። የእንጦጦ መምህር አይናገር፥ ቢናገር በዓመት ያውም ሬት። የእከክ መድኀኒቱ፥ አለመቅረብ አለመቀራረብ ነው። የዕውር ልቡ፥ ኢየሩሳላም ነው አሳቡ። የእህል ክፉ አጃ፤ የሣር ክፉ ሙጃ፤ የነገር ክፉ እንጃ። የእህል ክፉ፥ ክርትፉ። የእህል ጌታ ፈርዚዚ፤ የወርቅ ጌታ ቀበዝባዚ። የእህል ጣዕም በጐረሮ፤ የነገር ጣዕም በጆሮ። የእኅት ልጅ፥ ባይወልደት(ም) ልጅ። የእውነት በትር ትቀጥናለች እንጂ አትሰበርም። የእውነት ዗ንግ ትመነምናለች እንጂ፥ አትሰበርም። የዕዳ ጎደል ይንቦጫቦጫል። የእጄን ለልጄ። የእጅ ላባ ይያዚል፤ የአፍ ላባ ያስገርፋል። የእጅ ብልኀት ባርነት፤ የአፍ ብልኀት ጌትነት። የእግር ጌጡ፥ መረገጡ። የእጨጌ ከብት፥ በየወገኑ ይከተት። የከሳ እሪያ ይገራል። የከረረ ይበጠሳል፤ የበደለ ይወቀሣል። የከረረ ይበጠሳል፤ የተበደለ ይካሳል። የከረዩ በሬ፥ ድባ አውሬ። የከርቤ ጥርስ አያደቅም። የከርቤ ጥርስ፥ ጥርስ አይሆንም። የከብት አገሩ ባለቤቱ፤ የሰው አገሩ ምግባሩ። የከተማ ዳንዳ፤ የበረሃ ወንበዳ። የከተማን ወሬ መስማት፤ ትልቅ አዳራሽ መሥራት። የከፈተውን ጐረሮ፥ ሳይ዗ጋው አያድርም። የከፋ እውነት፥ የተፈጠረ ነው ከውሸት። የከፋው ሰው፥ ሲኼድ አይሰናበትም። የከፋው ይትፋው። የከፋውን፥ ጋሞ ጎፋ። (ይልኩ ነበር) የካህን አይነ አፋር፤ የአህያ ዕውር፤ የሴት ደፋር አይረባም። (አይረባም ~ አይረቡም) የካህን አፋር፤ የአህያ ዕውር። የካህንና የሴት እንግዳ የለውም። የካባን ረኃብ፤ የዳባን ጥጋብ የሚያውቅ የለም። የክረምት መሻገሪያውን፥ በጋ ተመልከተው። የክረምት አሻቦ፤ የበጋ ቅቤ። የክረምት ጥማትና፥ የመከር ረኃብ፥ አለ ባለቤቱ የሚያውቀው የለም። የክረምት ጥማትና፥ የመከር ጊዛ ረኃብ፥ አለ ባለቤቱ የሚያውቀው የለም። የክብር አወዳሽ፤ የሽንብራ ቆል ያሽ። የክፉ ልጅ እናት፥ ኹለት ጊዛ ታዝናለች። የክፉ ልጅ እናት፥ ኹል ጊዛ ታለቅስ። (ታለቅስ ~ ታዝናለች) የክፉ ሰው ተዝካር፥ ውሃ ያስወስዳል በኅዳር። የክፉ ሰው፥ ተዝካር ያቅራል። (ተዝካር ~ ተዝካሩ) የክፉ ሰው ፈስ፥ አይን ያፈስ። የኮሶ ማግስት፥ እናት በሆነች አራት (አምስት)። የኮራ ተጎዳ፤ አይዋጋም የበሬ ቆዳ። የኮዳ ውሃ አያኮራም። የኹለት ሴቶች ባል፥ ይሞታል ይበላል ሲባል። የኹለት ላም ጭራ የያ዗፥ ወንዝ አይሻገርም። የኹለት ብልጦች ሥንቅ፥ ነጭ አመድ ነው። የሀምላ ብራ፤ የባልቴት ወብራ። የኹለት አገር ስደተኛ። የኹለት ዕዳ ከፋይ። የሆነ አይመለስ፤ እሳት አይጎረሥ። የሆድ ማበድ ያስቃል በግድ። የሆድ ምቀኛ(ው) አፍ ነው። የወለደ ይላስ፤ የበደለ ይካስ። የወለደ ይልሳል፤ የበደለ ይክሳል። የወለደ፥ መልኩ ተለወጠ እንጂ፥ አልሞተም። የወለደ አበደ። የወለደትን እየገደሉ፥ ላላ ለመውለድ ጠንቋይ ቤት ይኼዳሉ። የወለፌንድ ስልቻ፥ ጤፍ ይቋጥራል፥ ባቄላን ያፈሳል። የወለፌንድ ኑሮ፦ በሐዳዳ ቋንጣ፥ በፋሲካ ሽሮ። የወለደውን ሲስሙለት፤ የደገሰውን ሲበሉለት ደስ ይለዋል። የወለደውን ቢስሙለት፤ ያቀረበውን ቢበሉለት (ደስ ይለዋል)። የወለደት ዅሉ ከአደገ፤ የ዗ሩት ዅሉ ከፀደቀ። የወላጅ ሆድ ቀጥቀጥ፤ የልጅ ሆድ ቀጥ። የወላጅ ገን዗ብ ለልጅ ቁልቁለት፤ የልጅ ገን዗ብ ለወላጅ አቀበት (ነው)። የወሰን ላይ ሰዎች፥ ላቦች ወይም ሽፍቶች። የወረቀት ላይ ነብር፤ የተግባር ስንኩል (አንዅን)። የወረት ኮሶ ይጣፍጣል። የወረት ውሻ ስሟ ወለተ ጴጥሮስ። (ወለተ ጴጥሮስ ~ ወለተ ኪሮስ ~ ወለተየስ) የወረወርኩት አንካሴ፥ ተመልሶ በራሴ። የወረደ መዓቱን፤ የመጣ ምጣቱን። የወራት ራስ፤ ኅዳርና ታኅሣሥ። የወሬ ቆርፋዳ፥ ዋንጫ ቅቤ አያርሰውም። የወርቅ እንክብል፤ የሸማ ንቅል። የወታደር ቁም ነገረኛ፥ በዓመቱ ድሀ። የወታደር ወዳጅ፥ እህለ ፈጅ። የወታደር ፈዚዚ፤ የእናት ነዝናዚ የለውም። የወታደር ፈዚዚ፤ የእናት ነዝናዚ፤ የሴት ቀበዝባዚ (አይረቡም)። የወንበዳ ዋሻ፥ የላባ መሸሻ። የወንዝ ውሃ፥ የጠማውን አይጠብቅም። የወንድ ልጅ ሀብቱ ልቡ፥ የሴት ልጅ ሀብቷ ውበቷ። የወንድ ልጅ ልብ፥ አይኑ ሥር ነው። የወንድ ልጅ ሞት፥ ያደረገውን የ዗ነጋ ዕለት። የወንድ ነጪ፤ የሴት ላጪ። የወንድ አልጫ፤ የእንድድ ሙቀጫ። የወንድ አጭር ዝንጀሮ፤ የሴት አጭር ወይ዗ሮ። (ወይ዗ሮ ~ አውራ ድሮ) የወንድማችኹን በደል ተውለት። የወንድም ልጅ፥ ባይወልደትም ልጅ። የወንድም ልጆች፥ ጥንብ አሞሮች። የወንድምህ ጢም ሲላጭ፥ ጢምህን ውሃ አርስ። የወንድች ባል፥ አይተህ ማር። የወንጭፍ ድንጋይ ባልነበር፥ የማሽላ እሸት መልካም ነበር አለች ወፍ። የወይን ዗ለላ ጋን ይሞላ፤ የስንዳ ዚላ ዕፍኝ ይመላ ። (ይመላ ~ ይሞላ) የወይ዗ሮ ምሥጢር ማጌጥና መሸለም ነው። የወይፈን ሥልቻ፥ ጤፍ ይቋጥራል፥ ባቄላ ያፈሳል። የወደቀ ተነጠቀ። የወደቀ ዚፍ፥ መንገደን ዗ጋ። የወደቀ ዚፍ፥ ምሳር ይበዚበታል። (ዚፍ ~ ግንድ) የወደቀን አንሣ፤ የሞተን አትርሳ። የወደደ ሰው፥ ምን አይን አለው? የወደደ ሰው፥ አይንም የለው። የወደደ ነደደ። የወደደ አበደ። የወደደትን ሲያጡ፥ የጠሉትን ይለማመጡ። የወደደትን ቢያጡ፥ የጠሉትን ይቀላውጡ። የወደድኸው ቂጣ፥ ሰተት ብል ወጣ። የወዳጅ ሚዚኑ፥ መከራ ነው። የወደደና የአበደ፥ አንድ ነው። የወደደውን አቅፎ፤ የጠላውን ነቅፎ። የወዳጅ ስልቻው፥ እየብቻው። (እየብቻው ~ ለየብቻው) የወዳጅ ተጋፊ፤ የጠላት ደጋፊ። የወዳጅ ከዳተኛ፥ አደኛ። የወዳጅ ወዳጅ፥ ወዳጅ ነው። የወዳጅ ወዳጅ፥ ወንዝ ያሻግራል። የወዳጅ ጅብ፤ ልጄን ከዱብ። የወዳጅና የኮርቻ፥ አለመንካቱ ብቻ። የወዳጅን ነገር አያወጡም፥ ከደን እንዱያው ከደን ከደን። የወጋ ቢረሳ፥ የተወጋ አይረሳ(ም)። የወጋ መጋኛ፤ መቅቡጥ የለመደ ዳኛ። (መቅቡጥ ~ ጉቦ) የወጌሻ ልጅ፥ ዚፍ ላይ ያድራል። የወጋ ቢረሳ፥ ፖሉስ ያስታውሳል። (዗መነኛ) የወጣ ሰው፦ አንደን ጥል፥ አንደን አንጠልጥል። የወጣ ቢገባ፥ የገባ ይወጣል። የወጣበትን መሰላል የወረወረ፥ የሚወርድበት ያጣል። የወጣት ልብ በደረቱ። የወጥ ማጣፈጫው፥ ጨውና ቅቤ። የወጥ ምሥጢር በጭልፋ ከድስት መውጣት ነው። የወጥ ቅመም ብዙ እንደሆነ፥ የኦሪት ስልቷ ብዙ ነው። የወፍ ወንደ፤ የሰው ሆደ (አይታወቅም)። የወፍ ወንደን፤ የሰው ሆደን የሚያውቅ የለም። የወፍ ዝላ:_ ከቤት ይውላል፥ አሸን ሲፈላ። የወፍጮ እንጉርጉሮ፥ አይሆንም ለሰርግ። የዋለች ውላ፥ ባሎ ሲመጣ ትበላ። የዋልንበትን፥ አረም በላው። የዋስ ተሟጋች፤ የቆማጣ ፈትፋች። (የቆማጣ ~ የድውይ) የዋስ ወንድም አይታገት፤ የአባያ ወንድም አይጎተት። የዋርካ ልጅ ሳንቃ፤ የአለቃ ልጅ አለቃ። (ሳንቃ ~ ዋርካ) የዋኘ ይሻገራል፤ የሠራ ይከብራል። የዋህ ፊቱን ቢመልስ፥ ማጅራቱ ጋራ ይመስለዋል። የዋለ፥ ያደረ ነገር አትጥላ። የዋጋ ብልጥ ልብ ይግጥ፤ የልጅ ብልጥ እየቀደመ ይውጥ። የውሃ ሽታ፤ የእባብ ፍለጋ የለውም። የዋ዗ኛ ልላ፥ መሰለፍ አያውቅም። የዋጋ ብልጥ፥ ልብ ይግጥ። የውሃ ውሃ፥ ምን አለኝ ቀሀ? የውሃ ድምፅ ቀረበ ብለህ አትኺድ፤ የጨለማ እሳት ራቀ ብለህ አትቅር። የውሃ ድምፅ፤ የጨለማ እሳት። የውሃ ጡር፥ በእድፍ ያስታጥባል። የውል መንገድ፥ በሩጫ። የውስጥ አንጀቴን፤ የላይ ቁርበቴን። የውሻ ትሕትና፤ የካህን እብድና መቼ ይጋጠምና። የውሻን ጥርስ፥ በአጥንት ይፈሯል። የውሽማ ሞት፥ ፊት አይነጭለት። የውሾን ነገር ያነሣ ውሾ። የውድማ ዗ንድ፥ ይቀጠቀጣል እንደ በረድ። የውጭ አልጋ፤ የቤት ቀጋ። (የቤት ~ የውስጥ) የ዗ላን ቤት፥ ኹል ጊዛ ስደት። የዕቡይ ልጅ ወዳቂ፤ የ዗ማ ልጅ ሣቂ። የእባብ ለማዳ፤ የአህያ ፍሪዳ የለውም። የእባብ ልጅ በቅንብቻ፤ (ሥንቅ በስልቻ)። የእባብ ልጅ እባብ። የዕንጨት ምንቸት:_ ራሱ አይድን፥ ላላ አያድን። (ላላ ~ ሰው ~ ላላውን) የዕንጨት ኩስኩስት:_ ራሱ አይድን፥ ሰው አያድን። የዕንጨት ክፉ አባል፤ የዳኛ ክፉ መድል። የዕንጨት ወልጋዳ፤ የመንገድ አንጋዳ (አይታወቅም)። የእኛ ነገር፥ እያደሩ ማጠር። የዕውር ሞቱ፤ የጨረቃ ንጋቱ (አይታወቅም)። የዕውር ቀበጥ፥ ከመሪው ጋር ይጣላል። የዕውር ነፍጠኛ፤ የወንበር ፈረሰኛ። የዕውር አስተናባሪ፥ የድውይ አጋፋሪ። የዕውር አዝማሪ፤ የደንቆሮ ተጣሪ። (ተጣሪ ~ ተጠሪ) የዕውር አፍጣጭ፤ የንጉሥ ቀላዋጭ። የዕውር ግልምጫ፤ ያንካሳ ሩጫ። የዙህ ዓለም ፍቅር፥ ሰኞ ቅዱስ ማክሰኞ ልብስ ረቡዕ ብጥስጥስ። የዚሬ ዗መን ጫጩት ከአውራ እኩል ትውጣለች፤ ወይ ያንቃታል ወይ የዚሬን ለቀባሪ፤ የነገን ለፈጣሪ። የዝኆን ክሳት፤ የባለጸጋ ድህነት አይታወቅም። የዝኆን ጆሮ ይስጠኝ። የዝንብ ሽውታ፥ የነገር ስልት ይበጥሳል። የዝንብ ተላላ፥ ከአንድ በሬ ደም ይቀርባታል። የዝንብ ተባቱ፤ የሴት ጭምቱ ሳይታወቁ ሞቱ። የዝንጀሪትዬ ዝንጀሪት፥ ባላ ገደለ በነጋሪት። የዝንጀሮ ለቅሶ፥ መልሶ መላልሶ። የዝንጀሮ ልጅ ከዚፍ፤ የመምህር ልጅ ከመጽሀፍ። የዝንጀሮ መነኰሴ፤ የሰንበላጥ አንካሴ። የዝንጀሮ መንገድ፥ ቢከተሉት ገደል። የዝንጀሮ መንገድ ከገደል ያደርሳል። የዝንጀሮ ሰነፍ፥ የአባቱን ዋሻ ይጠየፍ። የዝንጀሮ ንጉሥ:_ ራሱ ይከምር፥ ራሱ ያፈርስ። የዝንጀሮ ንጉሥ:_ እሱ(ው) ይከምር፥ እሱ(ው) ያፈርስ። የዝንጀሮ አንካሳ፥ የውሻ ራት ይሆናል። የዝንጀሮ ጎልማሳ፥ የውሻ ራት ይሆናል። የዝረ ምን ያመጣ? ፌራና ፈንጣጣ። የየቤቱ ጥንስስ፥ ጋን ይሰብራል። የየጁ ቄስ፥ ቅኔው ቢጎድልበት፥ ቀረርቶ ሞላበት። የየጁ ቄስ፥ አንደዛ ቅኔው ቢጎድልበት ቀረርቶ ሞላበት። የየጁ ደብተራ፥ ቅኔ ቢያልቅበት፥ ቀረርቶ ጨመረበት። የያ዗ውን ከወረወረ፥ ፈሪ አይባልም። የያዙት ወርቅ፥ ከብረት እኩል ነው። የያዙትን ከወረወሩ፥ ፈሪም አይባሉ። የደላው ****፥ ወርቅ ያስራል። የደላው፥ ሙቅ ያኝካል። የደላው ውሻ፥ ማር ይቀላውጣል። የደመና ውሃ ጥምና የእናት በደል አይታወቅም። የደረሰ ልጅህን፤ የሚያርስ በሬህን አያሳጣህ። የደረቀ ወንዝ ተሻጋሪ፤ የሞተ ጅብ ወጋሪ። የደሮ አርበኛ፥ የቅምጥ ይዋጋል። የደባ ጥጋብ፥ ያለ ሥንቅ ያ዗ምታል። የዳባ ገበያ፥ ሸማ በአሥር ዳባ በሀያ። የደበል ተባይ፤ የዳኛ አባይ ቢገልጡት አይታይም። የደባ ገበያ፥ በሬው በአሥር ቆዳው በሀያ። የደንቆሮ ለቅሶ፥ መልሶ መላልሶ። (መልሶ መላልሶ ~ መልሶ) የደንቆሮ ሰርግ፥ በሽብሸባ ያልቃል። የደንቆሮ ተጣሪ፤ የዕውር አዝማሪ ዞሪ። የደንቆሮ ዗ፈኑ ያው አንድ ብቻ ነው። የደጃዝማች ሚስት አይቼ፥ ሚስቴን ጠላኹ። የደጅ ጠበል የቆዳ መንከሪያ ነው። የደገመ ተረገመ። የደግ ጊዛ ባዕድ፤ የክፉ ጊዛ ዗መድ። የደፉት ሬሳ፤ የጠበሱት አሣ። የዳባ ገበያ፥ በሬው በአሥር ቆዳው በሀያ። የዳቦ ልብ ልቡ፤ የዳገት ጥግ ጥጉ። የዳኛ ልል ያማታል፤ የአባል ልል ያፋታል። የዳኛ አባይ፤ የደበል ተባይ ቢገልጡት አይታይ። የዳኛ ጅሉ ያማታል፤ የአመል ክፉ ያፋታል። የዳኛ ጅል ያማታል፤ አባይ ምስክር ያስረታል። የዳገት ሩጫ፤ የባለጌ ጡጫ። የዳገት በረድ፤ የቆላ ዗ንድ። የዳጉሳ እንጀራ በትኩሱ፤ የባዕድ ፍቅር በአዱሱ። (እንጀራ ~ እንጌራ) የድመት ልጅ፥ መቧጨሯን አትረሳም። የድሀ ልጅ በአውድማ፤ የመኮንን ልጅ በከተማ። የድሀ መድኀኒቱ፥ የድንገቱ። የድሀ ማጀት፥ (ቃጢ) ማር ለማስቀመጥ አይችልም። የድሀ ምኞት ቁንጣን፤ የሀብታም ምኞት ሥልጣን። የድሀ ቁም ነገሩ፥ ገብስ እስከ አሠሩ። የድሀ ቅንጡ እንጀራ ሲሰጡት፥ ይላል ድልህ አምጡ። የድሀ ብድር፥ አይውል አያድር። የድሀ ተዝካር፤ የጎባጣ ስካር። የድሀ ነገር፥ ማንገቻ የለው(ም)። የድሀ አውድማና የሀብታም ሕመም አንድ ነው። የድሀ ጉልበቱ፥ በገበያ ያልቃል። የድሀ ጉልበት በገለባ ያልቃል። የድሀ ጉልበት በገበያ ያልቃል። የድሀ ግርግር፥ ሀብታም ይጋብዚል። የድሀ ግድርድር፥ ሀብታም ይጋብዚል። የድሀ ጠላ:_ ጧት አልፈላ፥ ማታ አተላ። የድሀ ጮማ፥ የደባ ሰንጋ ነው። የድሀን ድሀ ይቸግረዋል፥ እንጨትና ውሃ። የድህነት አሽከር፥ ድህነትን መስል ይታያል። የድመት ማንቀላፋት፥ አይጦችን ለማጥፋት። የድመት ትዕግሥት፥ አይጥ እስክትይዝ ድረስ ነው። የድሮው ኮንጎዬ፥ ከአኹኑ ስቶኪንጌ ተሻለኝ። የድንጋዩ ተራ የማዕ዗ኑ ሥራ፥ አለ አድማስ አይቃናም። የድንጋይ ልብ፤ የኩበት ግንብ (የለም)። የድንጋይ መቀመጥና፤ የባዕድ ፍቅር እያደር ይቆረቁር። የድንጋይ ንፍሮ፤ የብረት ቆል። የድንጋይ ጦርነት፤ የሽሮን ቀለብነት፤ የሚስትን ባርነት። የድሀ ሀብቱ፥ እንቅልፉ። የድፍድፍ ኩራቱ፥ ውሃ እስኪገባበት (ነው)። የድፍድፍ ኩራቱ፥ ውሃ እስኪገባበት (ድረስ) ነው። የድሮ አንገት ከምንቸት። የጀመረኝ ጅብ ይጨርሰኝ። የጀመሩትን መጨረስ፤ የቆረሱትን መጉረሥ። የጁ እሳት፤ ይዞል በእጁ። የጁ ቄስ:_ ቅኔው ቢጎድልበት፥ ቀረርቶ ሞላበት። የጃርት ሕልሟ፥ ደባ ነው። የጁ በእጁ። የጅል በትር፥ ሆድ ይቀትር። የጅብ ችኩል፥ ቶል ያፏጫል። የጅብ ችኩል፥ ቀንድ ይነክሳል። የጅብ ችኩል ቀንድ ይነክሳል፤ የአይጥ ችኩል የድመትን አፍንጫ ይልሳል። የጅብ ችኩል፥ ክንድ ይነክሳል። የጅብ ችኩል፥ ፍርድ ቤት ይቀርባል። የጅብ እንግዳ፥ ቁርበት አንጥፉልኝ ይላል። የጅብ ኹለት ስብሩ፤ የባለጌ ወታደሩ አስቸጋሪ ነው። የጅብ ለማዳ፤ የአህያ ፍሪዳ የለውም። የጅብ ገበሬ፤ የአህያ በሬ፤ የጦጣ ዗ር አቀባይ፤ የዝንጀሮ ጎል጑ይ ዅሉም በየበኩሉ እበላ ባይ። የጅብ ገበሬ፤ የአህያ በሬ፤ የጦጣ ዗ር አቀባይ፤ የዝንጀሮ ጎል጑ይ ዅሉም እበላ ባይ። የጅብ ፍቅር፥ እስኪቸግር። የጅብ ፍቅር እስኪርበው ነው። የጆሮ አጥር የለውም። የጅብ ጑ደኛ፥ ከጥንብ ያደርሳል። የጅብ ፈሪ፤ የሞት ቀሪ። የጆሮ ደግነቱ፥ ያለመሙላቱ። የገላጋይ ትዕግሥት፤ የባለቤት መጠቃት። የገላጋይ ደም የለውም። የገመገሙ ተገመገሙ። የገማ ሰው ሰውን አይሸሽም፤ ሰው እርሱን ይሸሻል እንጂ። የገርማሜን ምክር የሰማህ እንደሆን፤ እን኱ን ንጉሥና አምባ ራስም አትሆን። የገበያ ግርግር፥ ለላባ ይመቻል። (ይመቻል ~ ይበጃል) የገበያ ሽብር፥ ለቀጣፊ በጀው። (በጀው ~ ይመቻል) የገበያ ወንድና፤ የታሰረ አንበሳ በብላሽ ያገሳ። የገባ ወንድና፤ የታሰረ አንበሳ በብላሽ ያገሳ። የገበያ ግርግር፥ ለቀጣፊ ይመቻል። የገባር ልጅና የአጋሰስ ልጅ፥ ቢጭኑት ዝም ይላል። የገባያ ግርግርታ፥ ለቀጣፊ ተመቸው። የገብስ ብዙ ነድ፤ የጤፍ ሥሱ ነድ። የገብያ ሽብር፥ ለላባ ሰርጉ ነው። የገና ዕለት የተገዚች ባሪያ፥ ዗ወትር ገና ይመስላታል። የገንቦ ጠላ፥ ባልና ሚስት አጣላ። የገን዗ብ አሮጌ፤ የአባት ባለጌ (የለውም)። የገን዗ብ ወዳጅ፥ ፍቅር አያውቅም። የገን዗ብን ነገር ከአሰላሰሉት፤ አባ ሀናም ሞቱ እንደጨበጡት። የገዚ ምሥጢሩን አውጥቶ አደራ ማለት፥ ግመል ሰርቆ አጎንብሶ መኼድ ነው። የገዚ ጌታ፥ እግር ይዝ ይመታ(ል)። የገዚ ፈስ አይሸትም። የገደለ ባልሽ፤ የሞተ ወንድምሽ፤ አ዗ንሽ ቅጥ አጣ ከቤትሽ አልወጣ። የገደል ማሚቶ፥ ዳቦ ልስጥሽ ድፎ። የገዳይ ምልክቱ፥ ደም በጣቱ። የገጣጣ ሚስት፥ ችግሩን አልቅሶ ከአልነገራት አይገባትም። የገጣጣ ሚስት፥ አልቅሶ ከአልነገራት አታምነውም። የጉልበት ገሚሱ፥ ምላስ ነው። የጉልበት ግማሹ፥ አፍ ነው። የጉልቻ መለዋወጥ፥ ወጥ አያጣፍጥም። የጉም ላባ፥ ጉሙ ሲለቅ የት ትገባ?( ሲለቅ ~ ሲጠፋ) የጉም ላባ፥ ጉሙ ሲጠፋ ወዳት ትገባ። የጉድ አገር ገንፎ እያደር ይፋጃል፤ ተበልቶም ያፋጃል። (አድሮም ~ እያደር) የጊዛ ምስቅልቅል፥ እግር ራስ ያካል። (ራስ ~ ሰውነት ~ ራሱን) የጋራ ቤት፥ በግርግር ሳይ዗ጋ ያድራል። የጋራ ዕርሻ፤ ፍቅር መጨረሻ። የጋራ ወንጋራ። የጋራ ወጥ አይፈላም። የጋኑን በምንቸት። የጋን እጣቢ፥ ገንቦ ይሞላል። የጌታ ሆድ፥ ጠዋት ከባድ፥ ማታ ወላድ። የጌታውን ልብ የያ዗ ውሻ፥ ላም ሲታረድ ወንዝ ይወርድ። (ላም ~ ሰደቃ ~ ፍሪዳ) የጌታውን አመካከት፥ ልላው ይመልከት። የግልገል ስልቻ፥ ኹለት ቃጤ ብቻ። የግመል መጫኛ ቢበጠስ፥ ለአህያ ይበቃል። የግመል ሽንት ይመስል፥ ኹላ ወደኋላ። የግንቦት ልደታን፤ የታኅሣሥ ባዕታን ያልተ዗ከረልኝ እኔም አልለምንህ አንተም አትማርልኝ። የግፍ ግፍ፥ በዕንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ። የጎመን ምንቸት ውጣ፤ የገንፎ ምንቸት ግባ። የጎረምሳ መልኩ እንጂ፥ አነጋገሩ አያምርም። የጎረቤት ሀሳብ፥ ከገበያ አይወጣም። (ሀሳብ ~ አሳብ) የጎረቤት ላባ ሲመቸው ይሰርቃል፤ ሲደርሱበት ይሥቃል ሆኖ ነው ነገሩ። የጎረቤት ላባ:_ ቢያውቁት ይሥቃል፤ ባያውቁት ያሰጋል። የጎረቤት ላባ:_ ቢያዩት ይሥቃል፤ ባያውቁት ይሰርቃል። የጎረቤት ላባ:_ ቢያዩት ይሥቅ፤ ባያዩት ያጠልቅ። የጎሹን ገዳይ አበጀኹ ቢላችኹ፤ ይህን ባለ ጊዛ ምን ትሉታላችኹ። የጎበዝ ልብ፥ ከደረቱ። የጎበዝ ልቡ ከደረቱ ነው፤ የጉልበት ግማሹ አፍ ነው። የጎበዝ ልቡ ከደረቱ፤ የፈሪ ልቡ ከፊቱ። የጎበዝ ሹም፤ የኅዳር ጉም አገር ይደረግም። የጎበዝ ሹም፤ የጎንደር ጉም አገር ይደረግም። የጎበዝ አሰሳ፤ የወሬ አፈሳ ይደርሳል እግር ሳይነሣ። የጎበዝ ክምር፤ እያደር ይጨምር። የጎበዝ ደዳ፥ በዓመቱ ምድረ በዳ። የጎበዝ ጉልበቱ፥ ከደረቱ። የጎባጣ ባሪያ፥ አጎንብሶ ይኼዳል። የጎደለው ሉሞላ፤ የተረፈው ሉከላ። የጎጃም አዝመራ ሽንብራ ነው አሉ፤ እኛም እንዳንበላ ተነቀለ አሉ። የ጑ደኛ ምቀኛ፤ የከብት ቀበኛ። የጐረሮን መታነቅ፤ ያይን መደንቆል ያስጥለዋል። የጉብል ደላ፥ በክርከማ ያልቃል። የጠላ ክፋቱ አለመገኘቱ፤ የልጅ ክፋቱ አለመስማቱ። (አለመስማቱ ~ አለመከማቸቱ) የጠላ ክፋቱ፥ አለመገኘቱ። የጠላቴ ጠላት፥ ወዳጄ ነው። የጠመመውን አቅንቶ፤ የጎደለውን ሞልቶ። የጠመጠመ ዅሉ አይቀድስ፤ የጮኸ ዅሉ አይነክስ። የጠረጠረ፥ ሥንቁን ቋጠረ። የጠረጠረ፥ ቤቱን አጠረ። የጠረጠረ ተስፈነጠረ። የጠረጠረ፥ እሾህ አጠረ። የጠረጠሩበት፥ ድንጋይ ይጥሉበት። የጠሩት እንግዳ፤ እራቱ ፍሪዳ። የጠበቀ ከራራ፤ ባጥና ጣራ። የጠበኛ ፈስ፥ አይን ያፈስ። የጠብ መነሻ፤ የሥብስቴ ዕርሻ። የጠብ መነሾ፤ አበድሪኝ እርሾ። የጠንቀኛ ፈስ፥ አይን ያፈስ። የጠዋት መጠጥ ለዕዳ፤ የጠዋት ምግብ ለአገዳ፤ የማታ ምግብ ለእንግዳ። የጠዋት አር እንደመጣ፤ የማታ አር ደም እስኪ መጣ። የጠዋት ፀሓይ ለልጄ፤ የማታ ፀሓይ ለምራቴ። የጠይብ ጂል፥ ትበላለች በገል። የጠጅ ቤት አዝማሪ፥ አሉ ቆራጥ። የጠጅ ቤት አዚዥ፥ አተላ አጋዥ። የጠገራ ላም ባደረችበት በረት፥ እበት አይገኝም። የጠገበ ሰው፥ ራሱን አያስብም። (ራሱን ~ ረኃብን ~ ራቡን) የጠገበ ሰው፥ የተራበ ያለ አይመስለውም። የጠገበ አበደ። የጠገበ እንግዳ፥ ሳይተች አይወጣም። (ሳይተች ~ ሳይተኙ) የጠገበ ዕውር፥ ዗ንጉን ይወረውራል። (ይወረውራል ~ ይወረውር) የጠገበ ፍየል ካራ ይልሳል። የጠገበች ነፍስ፥ የማር ወለላ ትረግጣለች። የጠገበች ድሮ፥ ከነጭልፊት ማኅበር ትገባ። የጠጉር ጥቁሩ፤ የነገር አጭሩ። የጠፋ አደር፥ ከለማ አንድ ነው። የጠፋ ከብት፥ አንገቱ ረጅም ነው። የጠፍ ከብት ናት። የጢስና የልጅ፥ መውጫ(ው) አይታወቅም። የጣመው ቀለጠመው። የጣረ አንድ፥ ነገር አያጣም። የጣታ በሬ፥ ለነገ ብል ይጠጣል ዚሬ። የጣት ላይ ቅቤ ሆነች። የጣት ቁስልና፤ የጎረቤት ምቀኛ እንቅልፍ አያስተኛም። የጣውንት ደግ፤ የእንቧጮ ዗ንግ የለውም። የጥር በልግ፤ የብር ዗ንግ። የጥርስ ደም ሆነባት። የጥርስን እድፍ፤ የራስን ጉድፍ። የጥቁር ሴት ንቅሳት የምንድነው ቢለው፥ የእግዛር ቁጣ ነው አለው። የጥቅምት ዕርሻ፤ የአባት ውርሻ። (ውርሻ ~ ጉርሻ) የጥቅምት ዕርሻ፤ የእናት ጉርሻ። (የእናት ~ የአባት) የጥቅምት ቀን እና የቆንጆ ሣቅ አያታልልህ። የጥቅምት በረድ፤ የጫካ ላይ ዗ንድ። የጥበብ አያት ማለት፥ ማስተዋል ነው። የጥንት ወዳጅክን በምን ሸኘኸው? በሻሽ፥ አዱሱ እንዳይሸሽ። የጥጃ ሣሩ፤ መምሬ ማምሻ ወዱህ በዳዊት ወዱህ በጋሻ። የጥጋብ ዕለት ዅሉ አንበሳ፤ የረኃብ ዕለት ዅሉ ሬሳ። የጦመኛ ምቀኛ። የጦም ቆል፤ የቁልቁለት በቅል። የጦም ቆል፤ የበዓል ድሮ። የጦሰኛ ሰው ፈስ፥ አይን ያፈስ። የጦር ስለቱ፥ መዋጋቱ። የጦርነትን ነገር፥ ከፈሪ ጋራ አትምከር። የጦጣ ልጅ በዚፍ፤ የመናፍቅ ልጅ በመጻፍ (አይቻሉም)። የጦጣ ሞኛሞኝ፤ የዝንጀሮ ብልጣብልጥ የለውም። የጦጣ ብልጣ ብልጥ፤ የዝንጀሮ ቅልጣ ቅልጥ። የጦጣ ዗ር አቀባይ፤ የዝንጀሮ ጎል጑ይ (ዅሉም እንብላው ባይ)። የጦጣ ዗ር አቀባይ፤ የዝንጀሮ ጎል጑ይ የለውም። የጦጣን ልጅ በዚፍ፤ የጸጋን ልጅ በመጽሀፍ ማን ይችላል። የጧት ለማኝ፥ ለማታ። የጧት መጠጥ ለዕዳ፤ የጧት ምግብ ለአገዳ፤ የማታ ምግብ ለእንግዳ። የጨለመም ይነጋል፤ የተናጠም ይረጋል። የጨለማ አፍጣጭ፤ የዕውር ገልማጭ (አይረባም)። የጨለማ ገልማጭ፤ የዕውር አፍጣጭ አይረባም። የጨለማ ዗ፈን፥ ለዕንቅርታም ይመቻል። የጨረቃ ንጋትና፤ የዕውር ሞት አይታወቅም። የጨርቅ ነጩ፤ የበራ ልጩ። የጨሰ የጨሰውን ከወረወርሽው፥ ምኑን ማገድሽው? የጨረቃ ኺያጅ፤ የምስክር ፈራጅ። የጨነቀው ርጉዝ ያገባል፤ ስትወልድበት ገደል ይገባል። የጨነቀው ርጉዝ ያገባል፥ (የባሰበት እመጫት)። የጨነቀው ይዋጋል፤ የደረሰበት ያወጋል። (የደረሰበት ~ ያልደረሰበት) የጨዋ ልጅ ዅሉ፥ አርግዞል ሆደ። (ሆደ ~ በሆደ) የጨነቀው፥ ሙቅ አነቀው። የጨዋ ልጅ ሲያዝን፤ አሣ በወንዝ ይመክን። የጨዋ ልጅ ሲፋታ፥ ይጋባ ይመስላል። የጨዋ ልጅ በከተማ፤ የባለጌ ልጅ በውድማ። (በከተማ ~ የድሀ) የጨዋ ልጅ ከከተማ፥ ልጅ ከውድማ። የጨዋ ልጅና፥ ቅል ተሰባሪ ነው። የጨዋ ምክሩ አ዗ቅት፥ ማሰሪያው አሽክት ነው። የጨዋ አሮጌ ከደጀ ሰላም፤ የባለጌ አሮጌ ከላም። የጨው ተራራ ሲናድ፥ ባለጌ ይሥቃል፥ አዋቂ ያለቅሳል። የጨው ካብ ሲናድ፥ ሞኝ ይልሳል ብልኅ ያለቅሳል። የጨው ካብ ሲናድ፥ የአወቀ አለቀሰ፥ ያላወቀ ላሰ። (ካብ ~ ኮኛ) የጨው ገደል ሲናድ፥ ሞኝ ይሥቃል ብልኅ ያለቅሳል። የጨው ገደል ሲናድ፥ ብልኅ ያለቅሳል ሞኝ ይልሳል። የጨውን ባለዕዳ በጨው ቢያባብሉት፥ ጨዌን ማለቱ አይቀርም። የጨጌ ከብት፥ በየወገኑ ይከተት። የጫማ ጠጠርና፥ የእንጀራ እናት እያደር መቆርቆሩ አይቀርም። የጫሩት እሳት ይፋጃል። የፈላ ጠጅ፤ የደረሰ ልጅ። የፈሰሰ አልታፈሰ። የፈረሰኛ ማቅ ለባሽ፥ የሴት ትንባሆ ቀማሽ። (ቀማሽ ~ ጎራሽ) የፈረንጅ አስታራቂ እና የእህል አረቄ፥ ራስ ከማዝር በስተቀር ዋጋ የለውም። የፈረንጅ አሽከር ነጭ ለባሽ፥ ሳህን አመላላሽ። የፈሩት መድረሱ፤ የጠሉት መውረሱ አይቀርምና። የፈሩት ይደርሳል፤ የጠሉት ይወርሳል (የናቁት ያሳፍራል)። የፈሪ ልቡ፥ ከፊቱ። የፈሪ በትር፥ ሆድ ይቀትር። የፈሪ ደላ አያዳግምም። የፈሪ ደላ፥ ሠላሳ ነው። የፈሪ ደላው፥ ረጅም ነው። የፈሪ ገዳይነት፥ ለማታ። የፈሪ በትር፥ አሥር። የፈራ ወንድ ነው፤ የቆመ ግንድ ነው። የፈርስ ላይ እንጉዳይ። የፈሰሰ አይታፈስ፤ የሞተ አይመለስ። የፈሰሰ ውሃ፥ አይታፈስ(ም)። የፈሰሰ ውሃን፥ ማቆር ይጠቅማል። የፈሲታ ተቆጢታ። የፈሳ የጥጋብም አይደል ሲረሳ። የፈስ ማደናገሪያው፥ ዳቦ። የፈረሰ አልጋ፤ የተሸበረ ዛጋ። የፈቷት ሴት፤ ያጠቡት ወጪት፤ የወጡበት ቤት አንድ ነው። (ነው ~ ናቸው) የፉክክር በር፤ ሳይ዗ጋ አደረ። (አደረ ~ ያድራል) የፊተኛውን አሳረርሽ ቢሎት፤ የኋለኛውን ጥሬ አወጣች። የፊቱን ወደ ኋላ፤ የበክሩን ዱቃላ። የፊት መሪ፥ የኋላ ቀሪ። የፊት ምሥጋና፥ ለኋላ ሀሜት ያስቸግራል። የፊት እድፍ በመስተዋት፤ የኀጢአት እድፍ በካህናት። የፊት ከብት፤ የእጅ ወረት። የፊት ወዳጅህን በምን ቀበርኸው? በሻሽ የኋለኛው እንዳይሸሽ። የፊት የፊቱን አለ፥ ጑ያ ነቃይ። የፋቂ ሰነፍ፥ አንደን ሳይፍቅ፥ አንደን ይወዝፍ። (ይወዝፍ ~ ይ዗ፍቅ) የፋቂ ቆንጆ፥ ቡድነቱን አይተውም። የፋክክር ቤት፥ ሳይ዗ጋ ያድር። (ያድር ~ አደረ) የፌጦ መስልሽ፥ ሰናፍጭ ትቀምሽ። የፌጦ ብቅል፤ የብሳና ጌሾ፤ የተልባ አሻሮ፤ ይህን ጠምቆ ለማ? የሰው ነገር ለማይሰማ። የፍቅር ጣዕሙ፥ በመሳለሙ። የፍየል ልጁን፤ የላባ እጁን። የፍየል አይን ወደ ቅጠል፥ የነብር አይን ወደ ፍየል። የፍየል ጅራት፥ ቂጥ አይከድን፥ ከብርድ አያድን። (ቂጥ ~ ብልት) የፍየል ጅራት፥ ከብርድ አያድን ብልት አይከድን። (ብልት ~ እፍረት) የፍየል ጭራና የሰው ሀሳብ ኹል ጊዛ ወደ ላይ ነው። የፍጅት ወራት፤ እሳት በወንፊት። የፖለቲከኛ ገንፎ፥ ከፓልቶከኞች ተርፎ። የፖሉስ ዗መድ፤ የቤንዙን አመድ (የለውም)። የ዗ላን ወዳጅ፥ ሣረ ፈጅ። የ዗ላን ጦመኛ፥ ከጥጃ ጑ዳ አታስገቡኝ ይላል። የ዗መተ ይመለስ፤ የገደለ ይንገሥ። የ዗መኑ ሰው፥ ምላሱ መንታ አንደ ለፍቅር፥ አንደ ለሀሜታ። የ዗መኑ ሰው፦ ሲያቀርቡት ይርቃል ሲወደት ይጠላል። የ዗መኑ ወሬ፥ ይቀዳል ባቦሬ። የ዗መኑ ጫጩት፥ ከአውራ እኩል ልዋጥ ይላል። የ዗መድ ለማኝ:_ ከዝምድናው ወጥቶ፥ የለመነውንም አጥቶ። የ዗መድ ልፊያ፥ ልብስ ለመቅደድ። የ዗መድ ልላ፤ የፈረስ ጮላ ሲወጣ ወጥቶ ነው። የ዗መድ ቄስ፥ እየፈታ ያለቅስ። የ዗መድ አዳይ፥ ጦም ያሳድራል። የ዗መድ ዗መድ፥ ወንዝ ያሻግራል። የ዗መድ ጥል ለዓመት፤ የባዕድ ጥል ለ዗ለአለም። የ዗ማ ልጅ ሣቂ፤ የአባያ ልጅ ወዳቂ። የ዗መድ ጥል፤ የሥጋ ትል። የ዗መድ ጥል፤ የጎመን ትል። የ዗ማ ልጅ ሣቂ፤ የዕቡይ ልጅ ወዳቂ። የ዗ሩት ዅሉ አይበቅልም፤ የወለደት ዅሉ አያድግም። የ዗ራ ምን ያመጣ? ፍሬና ፈንጣጣ። የ዗ሬን ብለቅ ይቆማምጠኝ፥ አለ ቆማጣ። የ዗ሬን፥ ብተው ያን዗ርዝረኝ። የ዗ነበችን ፊት ያየ፥ በእሳት አይጫወት። የ዗ነጋ፥ በሩን ዗ጋ። (በሩን ~ ቤቱን) የ዗ነጋ ተወጋ፤ (የአወቀ ተነጠቀቀ)። የ዗ንጋዳ ስልቅ፥ ከሰው ጑ዳ ጥልቅ። የ዗ገነም አ዗ነ፤ ያል዗ገነም አ዗ነ። የ዗ገየው መጣ። የ዗ገዩ ተለዩ። የ዗ፈን መጀመሪያው፥ እስክስታ ነው። የ዗ፈን እንጂ፥ የጽሐፍ አዝማች የለውም። የ዗ፋኝ እጅ ከመሰንቆ፤ የሰካራም እጅ ከብርጭቆ። የ጑ደኛ ወሮ፥ ያጠነግር ዝሮ። የ጑ጉንቸር ልጅ መኼድ ሳታውቅ፥ መዝለል (ተማረች)። የጠሉት ሰው ቢቀር፤ ጠላ ማለቁ አይቀር። ያ ለ዗ር የተባለ፥ ወዳት አለ? ላመትስ እግዛር አለ። ያ በሬ ባላገደደ፥ ያ በሬ ገደል ባልገባ። ያ በሬ ባገደደ፥ ያ በሬ ገደል ገባ። ያለ መሠረት ቤት፤ ያለ ትምህርት ዕውቀት የለም። ያለ መባ፥ ቤተ ክርስቲያን አትግባ። ያለ መከራ ጸጋ፤ ያለ ድካም ዋጋ አይገኝም። ያለ መከራ፥ አይገኝም እንጀራ። ያለ መጥረቢያ ዕንጨት ሰባሪ፥ የቆማጣ ዗ንግ ወርዋሪ። ያለ ምቀኛ፥ አይገኝ ፍቅረኛ። ያለ ሥራ መብል፤ ያለዳኛ ውል (አይቻልም)። ያለ ሥራ አይበላ እንጀራ፤ (አለባላ ቆጥ አይሠራ)። ያለ በሬ፥ ምን ያደርጋል ገበሬ? ያለ ሴት፥ ምን ያደርጋል ቤት? ያለ ሴት ቤት፤ ያለ በሬ መሬት። ያለ በሬ መሬት፤ ያለ ሴት ቤት። ያለ ባለቤቱ፥ አይነድም እሳቱ። ያለ ቦታ የተሰበረ፥ ሉጠግኑት አስቸገረ። ያለ አቁማዳ ልመና፥ ዅሉ መና። ያለ አባቱ ቢዚቁን፥ አባክኖ ያባክን። ያለ አባቱ ቢዚቁን፥ አባክኖ ይባክን። ያለ አባት፤ ዕርጎ በአ጑ት። ያለ አቻ ጋብቻ፥ ቆይ ብቻ ብቻ። ያለ አንድ የላት (ጥርስ)፥ በ዗ነ዗ና ትነቀስ። ያለ አዋቂ ተራች፥ የራሱን አመልካች። ያለ ወንድም ጋሻ፤ ያለ ድግር ዕርሻ። ያለ ወጉ፥ አህዮች ተዋጉ። ያለ ዋጋ የበላችኹትን፤ ያለ ዋጋ ስጡ። ያለ ዕዳው መዝመት፥ ዋ ብል መቅረት። (መዝመት ~ ዗ማች) ያለ ክንፍ መብረር፤ ያለ ሥራ መክበር። ያለ ዝናብ ደመና፤ ያለ ንጽሕና ምንኩስና። ያለ ዝናብ ነጎዳ፤ ያለ ብድር ዕዳ። ያለ የሚኖር ይመስላል፥ የሞተ ያልነበረ ይመስላል። ያለ ይበዚል (አለ ወፍጮ)። ያለ ዳኛ ቀጠሮ፤ ያለ ቅቤ ድሮ። ያለ ድሀ ዗ውድ፤ ያለ ገበሬ ማእድ (አይገኝም)። ያለ ድካም ዋጋ፤ ያለ መከራ ጸጋ አይገኝም። ያለ ጊዛው የተወለደ ልጅ፥ አባቱን ጥል አያቱን ያስረጅ። ያለ ጊዛው ጊዛ፥ ማን እሸት አምጥቷል? በዙህ በቤታችሁ ጥርጣሪ ሞልቷል። ያለ ጎረቤት ቡና፤ ያለ ሙያ ዝና። ያለ ጎተራ ደረባ፤ ያለ ልብስ ካባ። ያለ ጎታ ደረባ(ው) ምንድነው። ያለ ጎታ ደረባ፤ ያለ ልብስ ካባ። ያለ ጥርስ ቆል፤ ያለ ጑ድ አንባ጑ሮ። ያለ ጨው በርበሬ፤ ያለ ሞፈር በሬ። ያለ ፊቱ አይቆርስ፤ ያለቤቱ አይወርስ። (ያለቤቱ ~ ያለባለቤቱ) ያለ ፍርድ ማሰር፥ በፈጣሪ ማማረር። ያለ ፍቅር ሰላም፤ ያለ ደመና ዝናብ። ያለ ፍቅር ጸልት፤ ያለ ዕንጨት እሳት። ያለ ዗መድ ነግሦ፤ ያለ አቡን ቀስሶ። ያለ ዗ዳ፥ ጋሻ እንቅብ ነው። ያለስፍራው የተሰበረ፥ ሲጠግኑት አስቸገረ። (አስቸገረ ~ አስቸጋሪ ~ ያስቸግራል) ያለቀ ደቀቀ። ያለበት ይበንበት ይሉሀል፥ ይህ ነው። ያለበት ይብላላበት። ያለቦታ የተሰበረ፥ ሉጠግኑት አስቸገረ። ያለአቻ ጋብቻ፥ ቆይ ብቻ ብቻ። ያለአዋቂ ተራች፥ የራሱን ለመልካች። ያለወጉ፥ አህዮች ተዋጉ። ያለው ሉሆን፥ አሳብ አደቀቀው ጎኔን። ያለጎታ፥ ደረባው ምንድነው? ያለፊቱ አይቆርስ፤ ያለቤቱ አይወርስ። ያሉሽን በሰማሽ፥ ኖርዌይ ባልመጣሽ። ያሉሽን በሰማሽ፥ ገበያ ባልወጣሽ። ያላማረ ሰርግ፥ ጉልቻው ይሸረፋል። ያላረፈች እግር፥ ከ዗ንድ ጉድ጑ድ ትገባለች። ያላረፈች ጣት፥ አር ጠንቅላ ትመጣለች። ያላዝረ፥ ሲዝር አደረ። ያላሳደጉት ውሻ ቤት ዗ግተው ቢመቱት፥ ዝሮ ይናከሳል። ያላረፈች ምላስ፥ ሸማ ትልስ። ያላየ ልጅ፥ ዳቦ ፍሪዳው። ያላዩት ነገር:_ ክፉ አይደለም፥ መልካምም አይደለም። ያላዩት አገር አይናፍቅም። ያልሞላ፥ ተርፎ አይፈስም። ያልሞተና ያልተኛ፥ ብዙ ይሰማል። ያልሟል ይተረጉሟል። ያልሰሙት ነገር፥ ክፉም መልካምም አይደለም። ያልሰማ ጥኑ ነው፤ ባልሽ ወዳጄ ነው። ያልሰማ ጆሮ፥ ከጎረቤት ያጣላል። ያልሰጡት ተቀባይ፤ ያልጠሩት አቤት ባይ። ያልሳሉት አይላጭ፤ ያላዩት አይቆጭ። ያልቆመ አንገት፥ ራስን አይሸከምም። ያልቆረጠ፥ እግብ አይደርስም። ያልበሉት ዕዳ፤ ያልጠሩት እንግዳ። ያልበላ ሬሳ፤ ያልለበሰ እንሰሳ። ያልበላ ዳኛ አያሟግት፤ ያልጠጣ እንግዳ አያጫውት። ያልበላህን አትከክ። ያልበላነውን ሥጋ፥ ከጥርሳችን እናውጣ። ያልበላኝን ቢያከኝ፥ አይገባኝ። ያልበላኝን ቢያኩኝ፥ አይገባኝም። ያልበጀው እሳት ፈጀው። ያልተመታ ልጅ፥ ሲቆጡት ያለቅሳል። ያልተመታ፥ ግልግል ያውቃል። ያልተማረ አይምርም፤ ያልተወቀረ አያደቅም። ያልተማረ አይጸድቅ፤ ያልተወቀረ አያደቅ። ያልተማረ ዋናተኛ፥ ከዳኛ ፊት እንቢተኛ። ያልተረታ አይረታ፤ ያልጠገበ አይማታ። ያልተሾመ አያዝ፤ ያልቀሰሰ አያናዝዝ። ያልተቀጣ ልጅ፥ ቢቆጡት ያለቅሳል። ያልተቀጣ ልጅ፤ ያልታጠበ እጅ። ያልተነካ፥ ግልግል ያውቃል። ያልተደራጀ ተፈጀ፤ ያልመከተ ተፈነከተ። ያልተገላበጠ ያራል። ያልተገላበጠ ያራል፤ ያለ ይበዚል አለ ወፍጮ። ያልተገራ ፈረስ፥ ይጥላል በደንደስ። ያልተጠናከረ፥ ድንገት ተሰበረ። ያልተጨበጠ ተስፋ፥ የያዙትን ያስጥላል። ያልተፈተነ ወዳጅ፥ ያልተተኮሰ ሸክላ (ነው)። ያልታረመ አፍ፥ ከዋንጫ ይሰፋል። ያልታየ እንጂ ያልተሰማ፤ ያልተደረገ እንጂ፥ ያልተባለ ነገር የለም። ያልታደለ ልጅ፥ በድርቅ ይወለዳል። ያልታደለ ቆዳ፥ ሲላፋ ያደራል። ያልታደለ በረድ፥ ከድንጋይ ላይ ያርፋል። (ያርፋል ~ ይወድቃል) ያልታደለ ከንፈር፥ ሉፕስቲክ ያበዚል። ያልታደለ ከንፈር፥ ሳይሳም ያረጃል። ያልታደለ ከንፈር፥ ቻፕስቲክ ያበዚል አሉ። ያልታደለች ወፍ፥ በመስከረም አይኗ ይጠፋል። ያልታደለች ወፍ፥ አይኗ በጥቅምት ይጠፋል። ያልታደልሽ፥ እንዳት አደርሽ? ያልታጣ ገበያ፤ ጑ያ ሸመታ። ያልነበረ ያፈርሳል፤ ቀዳዳ ያፈሳል። ያልወለደ አንጀት ጨካኝ ነው። ያልወለደ አይነሣ፤ የሽንብራ ማሳ። ያልወለደ፥ አጋድሞ አረደ። ያልወለደት ልጅ፤ ያልወቀሩት መጅ። ያልወለደኩት ልጅ አባ አባ ቢለኝ፥ አፌን ዳባ ዳባ አለኝ። (አባ አባ ~ አባባ) ያልወለደ ዅሉ ጊደሮች ይባላሉ። ያልወለደኩት ልጅ አባቴ ቢለኝ፥ አፌን ዳባ ዳባ አለኝ። ያልወለድኩት ልጅ አባዬ ቢለኝ፥ አፌን ዳባ ዳባ አለኝ። ያልወጋኝ ነቀሰኝ። ያልደረሰበት፥ ግልግል ያውቃል። ያልገራ (ጥሬ) ያደክማል፥ የድንብላል በሶ ልብ ያቆስላል። ያልገደለ በሽታ፥ ምሥጋና የለውም። ያልገደለ ዗ማች፤ ያልወለደ አማች። ያልጠሩት መካሪ፤ ያልሾሙት ፊታውራሪ። ያልጠሩት ሰርገኛ፥ በትረኛ። ያልጠረጠረ ተመነጠረ። ያልፋል፥ እስኪያልፍ ያለፋል። ያል዗ሩት አይበቅልም። ያል዗ራኹት በቀለብኝ፥ ደባ ያልኩት ቅል ሆነብኝ። ያል዗ራውን የሚበላ፥ ዝንጀሮ ነው። ያሎትን ጥላ፤ ያላሎትን አንጠልጥላ (መጣች)። ያመጣል አንበሴ፤ ይበላል ኮሳሴ። ያምማል ዝኆን፥ የኛ ወገን ሉሆን። ያምራል ብለው፥ ለነብር ልጅ አይድሩም። ያምራል ብለው ከመናገር፤ ይከፋል ብል መተው። ያምራል ብለው ከተናገሩት፤ ይከፋል ብለው የተውት። (የተውት ~ ያስቀሩት) ያምራል ብል ከመናገር፤ አያምርም ብል መተው። (አያምርም ~ ይከፋል) ያምራል ብል ከመናገር፤ ይከፋል ብል መተው ይሻላል። (ይከፋል ~ ያምራል ብል ይሸልሟል፤ ያውቃል ብል ይሾሟል። ያምሯል ይታደሎል። ያሞላቀቁት ልጅ፥ አይሆንም ወዳጅ። ያሳደጉት ውሻ፥ መልሶ በንክሻ። ያስታርቀኛል ሙተራ፥ እያንዳንደ እየኮራ። ያሽላል ያሉት ኩል፥ አይን ያጠፋል። ያች በቅል፥ ምን ይገርማት? ሰባራውን ቢጭኑባት። ያን አንካሳ፥ በለው በዋመሳ። ያው በገላ አለች ድመት። ያው እንዳያችኹኝ ቅዳሜ የወጣኹ፥ ይቆጡኛል ብዬ አርብ ማታ መጣኹ። (ሳምንት ሳይሞላው ማለት ነው) ያውልኹ እማገሩ፤ ክፉ አትናገሩ። ያውቃል ብል ያሟል፤ ያምራል ብል ይሸልሟል። ያውቃል ብል ይሾሟል፤ ያምራል ብል ይሸልሟል። ያውጡብሽ እንቢ፤ ያግቡብሽ እንቢ። ያዙኝ ልቀቁኝ። ያዚቆነ ሰይጣን፥ ሳያቀስ አይቀርም። (ያዚቆነ ~ ያዳቆነ፥ አይቀርም ~ አይተውም) ያዝ በስልቻችን፥ ለነገ ምሳችን። መስጠት አያውቅም እጃችን፥ አልነገሩንም መምሕራችን። ያዢ ሲይ዗ው፥ ብረት ያራል። ያዩትን ቢያጡ፥ ያላዩትን ይቀላውጡ። ያድናል ያሉት ኩል፥ አይን አጠፋ። ያገለገለ ተቀማጠለ። ያጉመተምቱ ~ ያጉተመትሙ ያ጑ኑት ድንጋይ፤ ተመልሶ ራስን (ይመታል)። ያ጑ኑት ድንጋይ፥ ተመልሶ ይገምሳል። ይሄ እንግዳ ቸኮለ፥ ሉያድር ነው መሰለኝ። ይህ ዅሉ መሽሞንሞን ስለ አንድ ጉዳይ ነው። ይህ ዅሉ፥ መጊያጊያጥ ለመላላጥ። ይህ ለእኛ፥ ብሩ ለአንጥረኛ። ይህ ሬሳ በምን ከበደ ቢሉ፥ አሳቡን በሰው ጥል። ይህ አለም ለምኔ? ለረፋድ ጎዳና፥ ለግማሽ ቀን ዕድሜ። ይህ አንበሳ ደም ደም አገሳ። ይህ እንግዳ ቸኮለ፥ ሉያድር ነው መሰለኝ። ይህ ከርከሬሻ፥ ዳቦዬን ለማንሻ። ይህ ዅሉ እንጣጥ እንጣጥ፥ ማን ትከሻ ላይ ቀጠጥና ዗ርፈጥ። ይህ ዅሉ ከርከሬሻ፥ በአንቺ የተነሣ። ይህ ዅሉ ከች ከች፥ ከእኛ ቤት ሥጋ ክጀላ ነው። ይህ ዅሉ ጠባሳ፥ በአንቺ የተነሣ። ይህቺም ከተማ ሆነችና፥ ቂጥኝ አፈራች። ይህች ሞት ተሸጋገረች፥ አሉ እማሆይ። ይህች ባቄላ፥ ከአደረች አትቆረጠምም። ይህች ባቄላ ያደረች፥ እንደሆን አትቆረጠምም። ይህች ተፍ ተፍ፥ እኔን ለመመንተፍ። ይህን ብሰጥ፥ ምን እውጥ? ይህን ብትሰጥ፥ ምን ትውጥ? ይህን ብታገኝ፥ (ባሰኸና) ከፋኸና። ይህን ወሬ ብለህ፥ ለሰው አትንገረው። ይሉ አይሉ፥ የት አለ ቅሉ? ይሉሽን በሰማሽ፥ ገበያም ባልወጣሽ። (በሰማሽ ~ ባልሰማሽ) ይሉሽን ባወቅሽ፥ ገበያም ባልወጣሽ። ይሉሽን ብትሰሚ፥ ጎንደር ላይ ክረሚ። ይሉኝ ብለህ፥ የሚበጅህን አትተው። ይሉኝ አይል ውሽማ፥ ድሮ ሲጮህ ይማለላል። ይሉኝ አይል፥ የኋላውን አያይ። ይሉኝ አይል ጸሀፊ፥ ከሙሴ ይገድፋል። ይሉኝታ ተፈርቶ፥ እስከመቼ ተቆራምቶ። ይሉኝታ፥ ደረት አይሆንም። ይሉኝታ፥ የራስ አሉን ቤት ፈታ። ይሉኝታና መጠቀም (በ)አንድነት አይገኝም። ይሉኝታና ጥቅም፥ በአንድ ላይ አይገኝም። ይልማና ዳንሳ ቁሞ ይሟገታል፤ ይህን በጌምድር ማን ዳኝ አድርጎታል። ይመሰክረዋል ለነፍሱ፥ ይፈተፍተዋል ለከርሱ። ይመስል አይመስል፥ የጠይብ እጁ ከከሰል። ይመታሉ የሚጠሉ ይመስል፤ ይስማሉ የሚወደ ይመስል። ይሙት የገደለ፤ ይካስ የበደለ። ይማሰላል ካሉ፤ ይዚመዳል አይገድም። ይማሩኝ እያልክ፥ ከምትታማበት አትገኝ። ይምሰል አይምሰል፥ ጠይብ እጁ ከሰል። ይሰጠኝ መስል፥ ሉሸጠኝ። ይሰጡ ብል ከሰጠ፤ ቆጥቦ የበላ በለጠ። (ይሰጡ ~ ይሰጡኛል) ይሰጣል መስል ይሸጣል። ይስበረኝ ይሰንጥረኝ የሚሉ፥ የሰውን ልብ ሉሰብሩ። ይስጡ ብል ከሰጠ፥ ቆጥቦ የበላ በለጠ። ይሸጣል፥ እንደ ውሃ ይኼዳል። ይሻገር ቢሻው ይዋኛል፤ ይቀማ ቢሻው ይዳኛል። ይቀላል ያሉት፥ ተቸነከረ። ይቀማ ቢሻው ይዳኛል፤ ይጠጣ ቢሻው ይዋኛል። ይቅር ለእግዛር፤ ወድቆ እማይሰበር። ይቅር ለእግዛር፤ ወድቆ አይሰበር፤ ሞቶ አይቀበር። ይቅደም ደግነት፤ ይከተል ቸርነት። ይበላ እንደ ቤቱ፤ ይሠራ እንደ ጉልበቱ። (ጉልበቱ ~ ጎረቤቱ) ይበላው ከአጣ፤ ይበላበት የአጣ። ይበጃል ያሉት መድኀኒት፥ አይን አጠፋ። ይበጃል ያሉት ኩል፥ አይን አጠፋ። ይብላኝ ለወለደሽ፥ የአገባሽስ ይፈታሻል። ይብራና ይብራ ተጣሉ፥ በሰው ሽንብራ። ይታደሉታል፥ እንጂ አይታገሉትም። ይታደሎል እንጂ፥ ይታገሎል። ይታወቃሉ ይታወቃል ሀሰተኛ፥ ብርቱ ወንጀለኛ። ይቺ ባቄላ፥ የአደረች እንደሆን አትቆረጠምም። ይቺም እንጀራ ሆና፥ ሚጥሚጣ በዚባት። ይቺም ያቺም ቆንጆ፥ ኧረ እንዳት ሆኖ ነው የሚወጣው ጎጆ። ይቺን ለእኛ፤ ጥሬን ለጌኛ። (ለጌኛ ~ ለደገኛ) ይቺን በላህ ብለህ ጦሜን አታሳድረኝ አለ አሉ። ይነግረው የለው፥ ያሙት አይመስለውም። ይካስ የበደለ፤ ይሙት የገደለ። ይወልደዋል ካሉ፥ ይመስለዋል አይገድም። ይኸን ውሃ፥ ማ ይሻገረዋል ቢሉ፥ ተዝካር ያየ ተማሪ። ይኹንልህ ካለ፥ (አላህ) በሣር ምሰሶ ያነሣል። ይሆናል መስልኝ፥ ጎሽ ጠመድኹ፤ ባይሆንልኝ ፈትቼ ሰደድኹ። (ሰደድኹ ~ ለቀቅኹ) ይሆናል ብዬ ጎሽ ጠመድኹ፥ የማይሆንልኝ ቢሆን ፈትቼ ሰደድኹ። ይሆናል ያሉት መድኀኒት፥ አይን አጠፋ። ይሆን ቢሆን፥ ዝኆን ይበላ ቢሆን። ይወደዋል ካሉ ይመክረዋል፤ ይመክረዋል ካሉ ይመስለዋል አይቀርም። ይወዶል ከሆድ፤ ይታጠቧል ከክንድ። ይወዶል ካሉ ይመክሯል፤ ይወልዶል ካሉ ይመስሎል። ይውደደኝ፥ የጀርባዬ ቅማል አለች አንዶ። ይውጋህ ብል ይማርህ። ይውጋሽ ብል ይማርሽ። ይደርሳል ባይ፥ ብዙ አብሳይ። ይደንቃል ይገርማል፥ አህያ ከጅብ ይከርማል። ይገርመኛል ገንፎ፥ ከራቴ ተርፎ። ይገርማል! አህያና ጅብ አብሮ ይከርማል። ይግቡ በደጃፉ፥ በአጠገቡ ሰው የለም ይላሉ። ይጠላኝ ይመስል ይመታኛል፤ ይወደኝ ይመስል ይስመኛል። ይጥሉህ አትጥላቸው፤ ይበድሉህ አትበድላቸው። ይጥሉሀል። ይጸድቅ አይጸድቅ አይታወቅ፥ ቤተ ክርስቲያን ያጫንቃል። (ያጫንቃል ~ ያጫንቅ) ደለቱን የበሉት ቄሱ፤ እማሆይ ፈርስ አገሱ። ደላ ለባለጌ፤ ምርኩዝ ለአሮጌ። ደላ የሚጠላው፥ ሸክላ ብቻ ነው። ደላን ይዝ፥ ላባን መጠየቅ? ደመና በሰማይ፤ የጨዋ ልጅ በአደባባይ። ደመና ጠቅሶ፤ ከአሰበው ደርሶ። ደመናን የጨበጠ፤ ሰማይን የቧጠጠ የለም። ደመወዙ ስንዳ፤ ሥራው ምን ግዳ። (ምን ~ የምን) ደመወዝ የለው፤ ቀልብ የለው። ደመወዝ ያጣ ልላ፥ ይኮበልላል በሀምላ። ደም ቢያለቅሱ፥ ድንጋይ ቢነክሱ። ደም ተቀብቶ፥ ዝንብ አይፈሩም። ደም ተበክለህ፥ ዝንብን አትጥላ። ደም ከአልፈሰሰ፥ ሥርየት የለም። ደም፥ ከውሃ ይቀጥናል። ደም ጥልቀት፤ ሥጋ ልደት። ደሞዙ ስንዳ፤ ሥራው የምንግዳ። ደሞዝተኛ፥ አርፈህ (አት)ተኛ። ደስታ በሽታ። ደረቅ ቁጢ፥ ሲያዩት መክበደ፥ ሲያነሡት ግን መቅለሉ። ደረቅ በደረቅ፥ አላህም አይታረቅ። ደረቅ ያደርቃል። ደረቅ ይቀመጠላል፤ ርጥብ ይጎብጣል። ደረቴ ይቅላ፤ ሆዳ ይሙላ። (ብለው) ደረቴን ቢያመኝ፥ እግሬን አገመኝ። ደረጃ፥ ለፍቶ መኼጃ። ደረቅ፥ ሞራ ይጨርሳል። ደርዬ የአገባ፥ በሬው በሠኔ ገደል የገባ። ደቄት በአመድ ይሥቃል። ደስታና መከራ፥ ቀኝና ግራ (ናቸው)። ደረስኹ ልጅ፤ ፈላኹ ጠጅ። ደባ ራሱን፤ ስለት ድጉሱን (አያጣውም)። ደባል ሲሰነብት፥ ይሆናል ባለቤት። ደባ በአገሩ፥ ጋን ያህላል አሉ። ደባና ቅል፥ አበቃቀሉ ለየቅል። ደባልና ሹመት አለሰበብ አይኼድ(ም)። ደብር ለላስታ፤ ድግድግታ ለጌታ። ደባና ቅል አበቃቀሉ አንድ ይመስላል፥ አበላሉ ለየቅሉ። ደባና ቅል አብሮ ይበቅል፥ አበላሉ ለየቅል። ደባን ሀረግ ሳበው። ደብተራ ሲኮራ፥ እቤተ ክርስትያን ገብቶ፥ ጭራ ይይዚል። ደብተራ ወገቡን ረግራጊ፥ አቴና ወጊ። ደብተራ የ዗ኬ ጎተራ፥ ዗ኬውን ሲቋጥር፥ አነቀው ነብር። ደብተራ፥ የ዗ኬ ጎተራ። ደብተራና ተማሪ፤ ሰናፊልና ሱሪ። ደኅና ሲታጣ፥ ይመለመላል ጎባጣ። ደኅና ወገን ያጣ ወየው ያለበት ጣጣ። ደኅና ጦር ያለው፥ ለግንብ ይሞክረው። ደመና ለዝናብ፤ ድግስ ለሆዳም። ደንቆሮ ከሚያጫውተኝ፥ የሚሰማ ያውጋኝ። ደንቆሮ የሰማ፥ ዕለት ያብዳል። ደንቆሮ፥ ምላሽ አያጣም። ደንብሮ የሸሸ በሬ፥ ራሱን ገደለ። ደካማ ቀበላ በአህያ ይወረራል። ደኮ ታጥቆ፥ ተክል አጽድቆ። ደወል ለአንበሳ ባማረለት፥ ታዱያ ማን ይሰርለት? ደወል፥ እንደ ጠዋቱ ትጮሀለች። ደጁን አይተህ እቤት ግባ፥ እናቷን አይተህ ልጅቷን አግባ። ደጃቸውን አይ዗ጉ፥ ሰውን ላባ ይላሉ። (አይ዗ጉ ~ ከፍተው) ደጃፉን ጥል በ጑ሮ ይመጣል። ደጃፍ የመለሰው፤ ማጀት የጎረሠው። ደጅ የጠና፥ ፍሬውን ይበላል። ደገኛ ሲያርስ፤ ቆለኛ ያነፍስ። ደጉ ሳያልቅብኝ ክፉ ተናግሬ፤ መ኱ንንቱ ታለ ተባሪያ መክሬ፤ ጠበሱት መሰለኝ ሸተተኝ አገሬ። ደጉ ነገር ሳያልቅ፥ ክፉ መናገር። ደግ ሰው ሲለግስ፥ እንደ ፏፏቴ ያርስ። ደግ ሰው:_ ከእንጀራው ቆርሶ፤ ከወጡ አጥቅሶ። ደግ ሳይበላ፥ ክፉ ይመራ። ደግ ብሠራ የጠሉኝ፤ ክፉ ባደርግ ምን ይሉኝ። ደግ አማችን መጦር፤ ክፉ አማችን በጦር። ደግ አማጭን መጦር፤ ክፉ አማጭን በጦር። ደግ አባት ርስት ያቆማል፤ ክፉ አባት ዕዳ ያቆያል። ደግ አድራጊ አበደረ፤ ክፉ አድራጊ ተገደረ። ደግ ጌታ ሲለግስ፥ እንደ ፏፏቴ ያርስ። ደግ ጎረቤት፥ እቃ አያስገዚም። ደግ ጎረቤት ውሻ ያሳድጋል፤ ክፉ ጎረቤት ግን ድሮ ያረባል። ደግ ጎረቤት፥ ያወጣል ከመዓት። ደግ ጎረቤት፥ ውሻና ድመት ያሳድጋል። ደግነቱ፥ የሰው ፊት አለ መፋጀቱ። ደግነት አይታረስ፤ ልጅነት አይመለስ። ደግና ማለፊያ፤ ትግልና ልፊያ። ደፋር ሴት፥ ጉልቻ ረግጣ ትወጣለች። ደፋር፥ ወጥ ያውቃል። ደፋርና ጭስ መውጫ። (ቀዳዳ) አያጣም። ደፋርና ጭስ ምን ያመጣሉ። ደፋርና ጭስ ዝዋይ ገቡ። ዱያቆን ሲጠግብ በጧፍ ይማታል፤ ወይፈን ሲቦርቅ ድንበር ያፈርሳል። ዱያቆን ከ዗ፈነ፤ ፍየል ከቀ዗ነ። ዱያቆን ከ዗ፈነ፤ ፍየል ከቀ዗ነ መዳኛም የለው አይድንም። ዱያብልስ በክፋቱ፤ ተወጋ ዳቢቱ። (በክፋቱ ~ በትእቢቱ) ዳሩ ምን ይሆናል፥ ሆነና ሆነና። ዳሩ ሲወረር፥ መሀሉ ዳር ይሆናል። ዳር ሲፈታ፥ መሀል ዳር ይሆናል። ዳር ቆሞ የሣቀ፥ መሀል ገብቶ ያለቅሳል። ዳር ቢፈታ፥ መሀል ዳር ይሆናል። ዳር ዳር ያለ፥ በመሀል የከበረ። ዳባ ራሱን፤ ስለት ድጉሱን። ዳባ ታጥቀው፤ ዕርፍ አርቀው። ዳቦ ሲበሉ ልብ ልቡን፥ ዳገት ሲወጡ ጥግ ጥጉን። ዳቦ በወጥ፤ በእግዛር ማምለጥ። ዳቦ በገና፤ ቡና በጀበና። ዳቦ ካልበሉት ድንጋይ፤ ልሚ ካልመጠጡት እንቧይ። ዳቦ ያለ ቅርፊት፥ ጠላ ያለ ምርጊት። ዳቦውን ጎርሦ፤ ደሙን አብሶ። ዳን ላለው፥ መድኀኒት አለው። ዳኛ፥ ኹን እንደ እኛ። ዳኛ ለዳኛ ያወርሳል፤ ጉም ተራራ ያለብሳል። ዳኛ ምን ያደላ? ከተረታ(ው) ሉበላ። ዳኛ ሰበር፤ በእጁ ከበር። ዳኛ ሲመረምር፥ ከራስ ይዝ እስከ እግር። ዳኛ ሲቆጣ፥ ማር ይዝ ከደጁ። ዳኛ ሲገኝ ተናገር፤ ውሃ ሲጎድል ተሻገር። ዳኛ ሲገኝ ተናገር፤ ውሃ ሲጠራ ተሻገር። (ሲገኝ ~ ሳለ) ዳኛ ስበር፤ በእጅ ክበር። ዳኛ ቢንቁ፥ ከመከራ ይወድቁ። ዳኛ ቢንቁ፥ የተያ዗ እህል(ን) ይወቁ። ዳኛ ቢያዳላ በዳኛ፤ አህያ ቢያጋድል በመጫኛ። ዳኛ ቢያጎድል፥ በዳኛ። ዳኛ አውጥቼ፤ ዗ንግ አቅንቼ። ዳኛ አይነቀፍ፤ እሳት አይታቀፍ። ዳኛ ከአዳላ፥ ጭነት ቀላል። ዳኛ ከፈረደበት፤ መርከብ የተሰበረበት። ዳኛ የወል፤ ምሰሶ የመካከል። ዳኛ የፈረደበት፤ መርከብ የተሰበረበት። ዳኛ የፈረደው፤ ስለት የቀደደው። ዳኛ ያደላበት፤ እሳት የበላበት። ዳኛ ያፈሰሱለት፤ ፈረስ የከሰከሱለት። (የከሰከሱለት ~ የከለከሉለት ~ ያከሰከሱለት) ዳኛ ይመረምራል፤ ጣዝማ ይሰረስራል። ዳኛ፥ ገን዗ቡን ተቀማ። ዳኛ ፍርድ አይከላ፤ እህል ጎታ ይሞላ። ዳኛም ይመረምራል፤ ጣዝማም ይሰረስራል። ዳኛና በሬ ሀብታም ነው። ዳኞች ከመረመሩ፥ ይናገራል ምድሩ (ይገኛል ነገሩ)። ዳኞች ከመረመሩ፥ ይገኛል ነገሩ። ዳክዬን ከውሃው፤ ፈረስን ከገለባው። ዳዊት በሹክሹክታ፤ ሰአታት በጋጋታ። ዳዊት በገናውን፤ ዕዝራ መሰንቆውን። ዳዊትን ያህል መዝሙር፤ ጨለማን ያህል ጥቁር (የለም)። ዳዋ በበላ፤ ጎመን በደላ እንዱሉ። ዳገት ለወዳጁ አይሰንፍ፤ ሀብታም ካለ ወዳጅ አይተርፍ። ዳገት ሲወጡ ጥግ ጥጉን፤ ዳቦ ሲበሉ ልብ ልቡን። ዳገት ዕርሙ፤ ሜዳ ወንድሙ። ድል በመታደል፤ ሙያ በመጋደል። ድል እድል፤ በአንድ ድልድል። ድል፥ የባለ እድል። ድሀ ለወዳጁ አይሰንፍ፤ ሀብታም ካለወዳጁ አይተርፍ። ድሀ ማታ አሥር ይጠምዳል፤ ጧት አንድ ያጣል። (ማታ ~ በሕልሙ) ድሀ፥ ምን ትሠራለህ እንጂ፥ ምን ትበላለህ የሚለው የለም። ድሀ ሰው ድሮ ከአረደ፥ ከኹለት አንዳቸው ቢታመሙ ነው። ድሀ ሲቀልጥ፥ አመድ አመድ ይሸታል። ድሀ ሲቀልጥ፤ አመድ ይቀልጣል። ድሀ ሲቀመጥ፥ እጁን ይ዗ህ አወዚው዗ው። ድሀ ሲቀማጠል፥ ከወገቡ ቀምጠል። (ቀምጠል ~ ቅምጥል) ድሀ ሲቆጣ ከንፈሩ ያብጣል፥ መንገደን ያሰልጣል። ድሀ ሲናገር ሬት ኮሶ፥ ሀብታም ሲናገር የማር በሶ። ድሀ ሲንቀባረር፥ ያለቀሰ ይመስላል። ድሀ ሲቆጣ፥ መንገድ ያፈጥነዋል። (መንገድ ያፈጥነዋል ~ እግሩ ይፈናጠራል) ድሀ ሲቆጣ፥ እግሩ መንገድ ያሰልጣል። ድሀ ሲያስለቅሱ፥ ከሥላሴ ይወቀሡ፥ መንግሥተ ሰማያትን አይወርሱ። ድሀ ሲያገኝ፥ ያጣ አይመስለውም። ድሀ ቅቤ ወድ፥ ማን ሉሸከም ነድ? ድሀ በሕልሙ ቅቤ ባይጠጣ ኖሮ፥ እከክ በወረሰው። (ኖሮ ~ ኑሮ) ድሀ በሕልሙ ቅቤ ባይጠጣ ኖሮ፥ እከክ ይጨርሰው ነበር። ድሀ በሕልሙ ቅቤ ባይጠጣ፥ እከክ በፈጀው። (እከክ ~ ንጣት) ድሀ በሕልሙ ቅቤ ባይጠጣ፥ እከክ ይጨርሰው ነበር። (ይጨርሰው ~ ይገድለው) ድሀ በሕልሙ፥ ቅቤ ባይጠጣ (ኖሮ)፥ ንጣት ይገለው ነበር። ድሀ በሕልሙ ቅቤ ባይጠጣ፥ ንጣት በገደለው። ድሀ በመሆኔ፥ ተባልኩኝ ቦ዗ኔ። ድሀ በሽታ አያውቅም፤ ሀብታም ጤና የለውም። ድሀ፥ በቤቱ ንጉሥ ነው። ድሀ በአመደ፤ ንጉሥ በ዗መደ። ድሀ በጉልበቱ፤ ባለጸጋ በከብቱ። ድሀ ቢናገር አያደምቅ፤ ቢጨብጥ አያጠብቅ። ድሀ ቢያስለቅሱ፥ ከሥላሴ ይወቀሡ፥ መንግሥተ ሰማያትን አይወርሱ። ድሀ ባይ፤ አይኔን አመመኝ። ድሀ ተበድል ራሱ ይታረቃል፤ ሀብታም በድል ተመልሶ ይሥቃል። ድሀ አገር እንጂ፥ ቤት የለውም። ድሀ ተበድል፥ ማሩኝ ይላል ቶል። ድሀ እስኪለብስ፤ ሸንጎ ይበተናል። ድሀ ከንቡ፥ ይደላ። (ይዳላ ~ ይዳራ) ድሀ ከንቡ ይደላል። ድሀ ከአለቀሰ፥ ቀኑ መች አነሰ። ድሀ ከአልጣረ፥ ድሮ ከአልጫረ፥ ማን ያበላው ነበረ? ድሀ ከዕርሻ፥ ዳቦዬን ለማንሻ። ድሀ ከአል዗ራ፤ ድሮ ከአልጫረ (ማን ያበላው ነበረ)? ድሀ ከአልጋረ፤ ድሮ ከአልጫረ። ድሀ ውሃውን ጠጥቶ እሳቱን ይሞቃል፤ ሀብታም ስለ ገን዗ቡ ይጨነቃል። ድሀ የሚበላው እንጂ፥ የሚከፍለው አያጣም። ድሀ የሚበላው እንጂ፥ የሚከፍለው አያጣም። (የሚበላው ~ ይበላው ~ ይከፍለው) ድሀ ያልፍልኛል ይላል፤ ጌታ ቀኑን ይቆጥራል። ድሀ ያመልክት፤ ዳኛ ያሟግት። ድሀ ይበላው እንጂ፥ ይከፍለው አያጣም። ድሀ ይ዗ረጋ፤ ደረቅ ቆዳ ይጮህ። ድሀ ጉልበቱን፤ ባለጸጋ ከብቱን። ድሀና ሹም ተሟግቶ፤ ድንጋይና ቅል ተማትቶ። (የማይሆን ነው ከቶ) ድሀና እመቤት፤ እልፍኝና ማድቤት። ድሀና እጦት፤ አህያና አመድ (አይተጣጡም)። ድሀና ድመት፥ ሉሞት ሲል ያምርበታል። ድሀና ገበያ፥ ሳይገናኙ ይሞታል። ድሀና ጌታ ተሟግቶ፤ ድንጋይና ቅል ተማትቶ የማይሆን ነው ከቶ። ድሀና ጨ጑ራ፥ እየጮኸ ይበሎል። ድሀን ምን ትሠራለህ እንጂ፥ ምን ትበላለህ የሚለው የለም። ድሀን ቢያስለቅሱ፥ በሥላሴ ይወቀሡ፥ መንግሥተ ሰማያትን አይወርሱ። ድሀን ከአስለቀሱ፥ በሥላሴ ዗ንድ ይወቀሡ። ድሀን ፈርቼ፥ ደጄን በቀን ዗ግቼ። ድህነት፥ ከአምላክ መስማማት። ድህነት፥ ከአምላክ መስተካከል። ድል ድል፤ እድልህ እንዳይጎድል። ድልህን፥ በርበሬ አስመሰገነው። ድመት ላመሎ፥ ዚፍ ላይ ትወጣለች። ድመት መንኰሳ፥ መናከሷን አትረሳ። (መናከሷን ~ አመሎን) ድመት በታች ከሆነች፥ ታሸንፋለች ውሻን። ድመት፥ ውስጥ ውስጡን አውሬ ናት። ድመትና ቁንጫ፥ ባድ ቤት ይወዳል። ድመትና አይጥ፤ እሳትና ጭድ። ድመትን፥ በቆል መጠርጠር። ድመትን አይጥ ገደለቻት፥ ወይ ጥቃት ወይ ጥቃት። ድምፅና ቁንጫ፥ ባድ ቤት ይወዳል። ድምፁን የማያሰማ ባል። ድሪቶ ከነቅማሉ፤ መጥፎ ሰው ከነአመሉ ወዱያ በሉ። ድሪያ፥ የዝሙት ዋንጫ ዋዛማ። ድር ቢያብር፥ አንበሳ ያሥር። ድር ቢያብር፥ ጋቢ ይሠራል። ድርብርብ፥ እንደ ደጋ ንብ። ድርና ማግ፤ ለሀጭና ልጋግ። ድርጎ ራቱ፥ ድርጎ ቢቀር ሞቱ። ድርጎ የለመደች መበለት፤ ወተት ያየች ድመት። ድርጭት ፈንጠር፤ ምዝግዝግ ጎንደር። ድሮ ላትበላው፥ ታፈስ። ድሮ በልቶ ብስና፤ ጎመን በልቶ ጤና። ድሮ በልቶ ከብስና፥ ጎመን በልቶ በጤና። ድሮ በልጇ አንጀት ትጫወታለች። ድሮ በማሰሮ፤ ገደል ለዝንጀሮ። (ማሰሮ ለድሮ ገደል ለዝንጀሮ) ድሮ በጋን። ድሮ ቢያማት፥ በሬ ተሳሉላት። ድሮ ቢጠፋ ከቤቱ፥ መነኮሰች እናቱ። ድሮ ብታልም፥ ጥሬዋን። (ሕልም ብታይ ) ድሮ ብትታመም፥ በግ አረደላት። ድሮ ነበር እንጂ፥ መጥኖ መደቆስ፥ አዅን ምን ያደርጋል? ወጭት ጥድ ማልቀስ። ድሮ ከቆጥ፤ በሬ ከጋጥ። ድሮ ከቤት ውላ፥ ዝናብ ይመታታል። ድሮ ከተከተተ፤ ጅብ ከአኮተኮተ። ድሮ ከአልበሎት፥ አሞራ ናት። ድሮ ከአልጫረ፤ ድሀ ከአል዗ራ። ድሮ ከአያታችን፥ ከአጤ ነው ትውልዳችን። ድሮ ከጋጥ፤ በሬ ከቆጥ። (በሬ ~ አህያ) ድሮ ከጮኸ ላሉት የለም፤ ከደብረ ታቦር ወዱያ ክረምት የለም። ድሮ ከጮኸ የለም ላሉት፥ ከቡሄ ወዱያ የለም ክረምት። ድሮ ከጮኸ ላሉት፤ ከደብረ ታቦር ወዱያ ክረምት የለም። ድሮ ካልጫረ፤ ድሀ ካል዗ራ። ድሮ ጭራ መታረጃዋን፥ አወጣች ማረጃዋን። ድሮ:_ ጭራ የምታወጣው ምሥጢር። ደሮ ጭራ ጭራ፥ አወጣች ማረጃዋን ካራ። ደሮ ጭራ ጭራ፥ የራሷን አጥንት አወጣች። ድሮ:_ ጭራ ጭራ መታረጃዋን ታወጣለች። ድሮ ጭራ ጭራ፥ ታወጣለች ካራ። ድሮ፥ ሲሉ ሰምታ፥ ሞተች በጢስ ገብታ። (በጢስ~ ከጢስ ~ እጢስ ~ እጪስ) ድሮ፥ ቢጠፋት፥ ብታስገኝልኝ በቅል እስጥሀለኹ ባል ተሳለች። ድሮ፥ ባሎ ሲሞት፥ ሞተች እጢስ ገብታ። ድሮ፥ አንደን እንቁላል በወለደችበት፥ ወታቦ ትሞላለች። ድሮ እቤት ውላ፥ ዝናብ ትመታለች። ድሮ፥ እኔ ባልበላው፥ ጭሬ አላፈሰውም ወይ አለች። ድሮ ከቆጥ፤ ሴት ከማጀት። ድሮ(ን) ሲቀጣጥቧት፥ በመጫኛ ጣሎት። ድሮም ላባ ሲሰርቅ እንጂ፥ ሲካፈል አይስማማም። ድሮም እንዳይሆን ነው፥ የቄስ ልጅ መኮንን (አለ)። ድሮም የቂጥ ወሮታው፥ ፈስ ነው። ድሮና ቀበሮ፥ ተገናኝተው ጑ሮ። (ተገናኝተው ~ ተገናኝቶ) ድሮና ሴት ከቤት ውላ፥ ዝናብ ትመታ። ድሮን ሲያታልሎት፥ በመጫኛ (ጠልፈው) ጣሎት። ድሮን ሲያታልሎት፥ አንቺ ሩጭ እኛ እንከተልሽ አሎት። ድሮን ሲያታልሎት፥ ጥምር መንግሥት አሎት። ድሮን ሲያታልሎት፥ ፎቶ አነሧት። ድሮ(ን) ሲደልሎት፥ በመጫኛ ጣሎት። ድክተር ሲበዚ፥ በሽተኛ ይሞታል። ድሮን ቢያማት፥ በሬ ተሳሉላት። ድስት ግጣሙን አያጣም። ድበላ፥ አንዳንድ ጊዛ ይበላ። ድንቀኛ ተ኱ሽ፥ ድር ይበጥሳል። ድንቁርና፥ ከልብህ መካከል፥ ተራራ ያህል። ድንቢጥ እንደ አቅሟ በብዕር ትታገማለች። ድንቢጥ እንዳቅሟ፥ በብርዕ ትታገም። ድን኱ን ተገልጦ፤ ዙፋን ረግጦ። ድንጋይ ለረገጠ ፍለጋ የለውም፤ ውሃ ለጠጣ ሽታ የለውም። ድንጋይ ላይ ተቀማጭ፥ የባለጌ ተለጣጭ። ድንጋይ ሲያረጅ፥ መጭ ያበቅላል። ድንጋይ በድንጋይ ላይ ትልቅ ቤት ይሆናል። ድንጋይ ቢቆሉት፥ አይሆንም ቆል። ድንጋይ ቢያጎኗት፥ ተመልሳ ከአናት። ድንጋይ ትራሱ፥ ዳዋ ልብሱ፥ ኮቾሮ ጉርሡ። ድንጋይ እና ቅል አይፈናከቱም። ድንጋይ ወርድ እ዗ብጥ ያርፋል፥ ያገኘው ይተርፋል። ድንጋይ ወርድ ከ዗ብጥ ያርፋል፥ ሰው በሞቱ ወደ መቃብር ያልፋል። ድንጋይ ወደ ሰማይ ቢወረወር፥ ተመልሶ (ወደ) ምድር። ድንጋይ ውሃ ውስጥ ስለኖረ ዋና አይለምድም። ድንግል አልቅሳ፥ አወጣች አንድ አበባ፥ ያን አበባ፥ አስረው ገረፉት እንደ ላባ። ድንቢን ያየ ባለጌ። ድንቢን ገልጦ፤ ዙፋን(ን) አጊጦ። (አጊጦ ~ አግጦ ~ ረግጦ) ድንገተኛ ስሕተት፤ የቁልቁለት ውድቀት። ድከሚ ያላት ጥቁር ሴት፥ እጇን ትነቀሳለች። ድሀ ኹለት፤ ድንበር አለው። ድክተሮች ሲበዙ፥ በሽተኛው ይሞታል። ድግስ የላለው ዋዛማ፥ ምልክት የላለው ዛማ። ድግርና ገባር፥ ሲተካከል ያምር። ድጥ ማንሸራተቱን፤ ባለጌ ማሽሟጠጡን አይተውም። ድማ ለመማሻ፤ ማረሻ ለመፈለሻ። ጀማሪ ይጥፋ፤ ሰካራም ይትፋ። ጀምሮ የማይፈጽም፤ ፈጭቶ የማያልም። ጀምሮ ይጨርሳል፤ ለጉሞ ይተኩሳል አልሞ። ጀርባ ለባለቤቱ ባዕድ ነው። ጀርባ ጀርባው ይታያል። ጀርባው ከብድታል። ጀርባዬን አሳከከኝ፥ ተንጠራርቼ ማከክ ተሳነኝ። ጀርባዬን እከከኝ፥ ለእኔ ራቀኝ እከክልኝ። ጀንበር ሳለ ሩጥ፤ አባት ሳለ አጊጥ። ጀግና የሚታወሰው፥ ወይም ከሞተ ወይም ከተለየ በኋላ ነው። ጀግናን ከደረቱ፤ አበባን ከአናቱ። ጀግኖች በነፍጣቸው፤ ሉቃውንት በቅኔያቸው (ይፎክራሉ)። ጃርት፥ ልጅሽን እንዳት አድርገሽ ትልሻታለሽ ቢሎት፥ እንደ ወለድ኱ት አለች። ጃርት ያስደነገጠው ደባ ይመስላል። ጅል ሲጃጃል፥ ዕቃ ይፈጃል። ጅል ስለላ ላይ ኼድ፥ ምግብ ቢቀርብለት ስለላ ላይ ነኝ ብል ዕርፍ። ጅምር ይጨረሳል፤ ልጉም ይተኮሳል። ጅምርን ለነገ አያሳዩም። ጅራትና ሀሜት በስተኋላ ነው። ጅራትና ጉድ፥ በስተኋላ ነው። ጅራትና ጉድ፥ ከወደኋላ ብቅ ይላል። ጅራቷ፥ ታደርሰኝ ከአናቷ። ጅራፍ መትቶ ያለቅሳል፤ ባለጸጋ በድል ተመልሶ ይወቅሳል። ጅራፍ እሱው ይገርፍ፥ እርሱው ይለፈልፍ። ጅራፍ እራሱ መትቶ፤ እራሱ ይጮሀል። (መትቶ ~ ገርፎ) ጅብ ሉሰር ኺድ፥ ተሰሮ ገባ። ጅራፍ እሱው ይገርፍ፤ እሱው ይለፍ። ጅራፍ፥ መትቶ ያለቅሳል። ጅብ ምነው የሰው ከብት ትበላለህ ቢሉት፥ አለጊዛ እየኼደ እኔን በደለኛ ያደርጋሉ። ጅብ ምን ይመስላል? እግሩ ያነክሳል፥ አፉ ይነክሳል። ጅብ ሲበላህ፥ በልተኸው ተቀደስ። ጅብ በላይ እየጠጣ፥ አህያን ውሃየን አታደፍርሥብኝ ይላል። ጅብ በቀደደው፥ ውሻ ይገባል። ጅብ አንዳ በበላበት፥ አሥሬ ይመላለስበት። ጅብ አያውቁት አገር ኼድ፥ ቆርበት አንጥፉልኝ አለ። ጅብ፥ አጥንት ባየበት ይመላለሳል። ጅብ እማያውቁት አገር ኼድ፥ ሩም ሰርቪስ ያዚል። ጅብ እማያውቁት አገር ኼድ፥ ቴላ ሴንተር ከፈተ። ጅብ እሰር ብል፥ ተሰሮ ገባ። ጅብ እስኪነክስ፥ ያነክስ። ጅብ እንደ አባቱ ይ዗ርጥጥ፤ አህያ እንደ አባቱ ይፈርጥጥ። ጅብ፥ እንደ አገሩ ይጮሀል። ጅብ እንደ አገሩ ይጮሀል፤ የደላው ሙቅ ያኝካል። ጅብ እንደ ጉልበቱ፥ ልብ የለውም። ጅብ እን኱ን ጑ደኛውን ይጣራል። ጅብ፥ እንደ ቁመቱ፥ ልብ የለውም። ጅብ ከሚበላህ፥ በልተኸው ተቀደስ። (በልተኸው ~ በልተህ) ጅብ ከሚበላህ፥ ጅብ በልተህ ተቀደስ። ጅብ ከማያውቁት አገር ኼድ፥ ቆርበት አንጥፉልኝ አለ። (አለ ~ ይላል ) ጅብ ከአመድ ይበርዳል። ጅብ ከአኮተኮተ፤ ሰው ከተከተተ። ጅብ ከኼደ፥ ውሻ ጮኸ። ጅብ ውሃ ሲጠጣ፥ ታች ያለችውን አህያ አታደፍርሽብኝ አለ። ጅብ የማያውቁት አገር ኼድ፥ ቆርበት አንጥፉልኝ አለ። ጅብ፥ የእኔ ስለው፥ ወናፌን ቀማኝ። ጅብ የእኔ ነው ስለው፥ ወናፌን ቀማኝ። ጅብ:_ ጥጆቹን ጠብቅ ሲባል ይጠፉብኛል አለ። ጅብና ሸማኔ፥ ከጉድ጑ድ አይወጡም። ጅብ፥ በአጥንት የተገደገደ በጅማት የተማገረ ቤት አለ ቢሉት፥ ወዳት ነው ሳይል ገደል ገብቶ ሞተ። ጅብና አህያ አታድርገን። ጅብና እህል፥ ሳይተዋወቁ ይኖራሉ። ጅብን ለመግደል፥ ከአህያ ተጠለል። ጅብን ሉወጉ፥ ከአህያ ይጠጉ። ጅብን ሲቀርቡ፥ በአህያ። ጅብን ሲወጉ፥ በአህያ ተጠግቶ ነው። ጅብን ሲወጉ፥ በአህያ ይጠጉ። ጅብን ከምን መታኸው? ከአፉ አሰፋኹለት። ጅብን ፈርቼ፥ ከዚፍ ብወጣ፥ ነብር ቆየኝ። ጆሮ ለባለቤቱ፥ ባዳ ነው። ጆሮ ምነው አታድግ ቢሉት፥ ጉድ እየሰማኹ በየት ልደግ (አለ)። ጆሮ በላ፥ ሆድ ጦሙን አደረ። ጆሮ ባይጦም፥ ይመስላል ሆዳም። ጆሮ ተቀምጦ አስወለደ፥ በኋላ የተወለደው ቀንድ በለጠው። ጆሮ ነገርን ይለያል፤ ጐረሮ እህልን ይጥማል። ጆሮ አይጦምም፤ አይን አይጠግብም። ጆሮ፥ ዕዳውን አይሰማም። ጆሮ የሰማውን ለማየት፥ ይኼዳል አይን። ጆሮ፥ የቀድሞዎቹ እኩያ ነው። ጆሮ የሰማውን፤ ልብ ያውቀዋል። (ያውቀዋል ~ ያውቃል) ጆሮ የሰማውን ለማየት፥ አይን ይንከራተት። ጆሮ ዳባ ልበስ አለ። ጆሮ፥ ለባለቤቱ ተቃዋሚ ሆነ። ጆሮ፥ ከአያቱ ያረጃል። (ከአያቱ ~ ከአያት) ጆሮ፥ ገን዗ቡን አይሰማም። ጆሮህ የት ነው ቢሉት፥ እዙህ አለ አሉ። ጆሮውን ቢቆርጡት፥ መስሚያው ይቀራል። ጆንያን ያቆመው፥ እህል ነው። ገለፈንት፥ የሴት ጋለሞታ። ገላጋይ አጥቼ፥ ግልገላን በላኋት። ገልቱ ቢመክር፥ አይ዗ክር። ገልፋጣ፥ የሴት ጋለሞታ። ገመድን ሲበጠስ መቀጠል፤ አባይ መስካሪን ገደል። ገረመኝ፥ የማላውቀው ሰው ቢስመኝ። ገረድ፥ የቤት ሞረድ። ገር ገሩን ተጫውቶ ይበሎል፥ ተስማምቶ ይኖራል። ገርነት፥ የእግዛር ቸርነት። ገርነት፥ የእግዛር ገነት። ገርና ልል፤ ሙዳይና አገልግል። ገርን ልጅ፥ እናቱ(ም) አትወደው(ም)። ገርገሩን ተጫውቶ፤ ይበሎል ተስማምቶ። ገበሬ በንጉሥ፤ መበለት በቄስ። ገበሬ በአረሰ፥ መናኛ ዅሉ ጎረሠ። ገበሬ አቆጣጠረኝ፤ ወታደር አወራወረኝ። (አወራወረኝ ~ አወራውረኝ) ገበሬ አክባሪውን፤ ባለጌ መካሪውን ይጠላል። ገበሬ አክባሪውን ይጠላ(ል)። ገበሬና ወላድ አንድ አያጣም። ገበታ ለአዋቂ፤ ወሬ ለጠያቂ። ገበያ ለአርፋጅ፤ ቤተክርስቲያን ለማላጅ። ገበያ ቢመቻት፥ ልጇን ሸጠቻት። ገበያ ቢያመቻት፥ ልጇን አስማማቻት። ገበያ ቢያመቻት፥ እናቷን ሸጠቻት። ገበያ ነሽ ብለው፥ ይሻሻጡብሻል። ገበያ እንደሰጠህ እንጂ፥ እናትህ እንደላከችህ አይሆንም። ገበያ እንዳት ዋለ? ቢለው አንደ ባንደ ሲሥቅ። ገበያ ከደራ፥ ነጋዳም አይፈራ። ገበያ ወጣ፥ ነገር ያመጣ። ገበያ የሚሰጥህን፥ እናት አትሰጥም። (የሚሰጥህን ~ የሚሰጥን) ገበያ የወጣች ገረድ፥ እመቤቷን መታች። ገበጣ ለአዋቂ፤ ወሬ ለጠያቂ፤ ዋዚ ፈዚዚ ለሣቂ። ገበጣ ገበጥባጣ፥ ከኢየሩሳላም የመጣ። ገበጣ ለአዋቂ፤ ወሬ ለጠያቂ። ገቢ በእናት፥ ልጅ ትገቢ። ገቢ ያፈርሳል፤ ቀዳዳ ያፈሳል። ገቢህን ሳታውቅ፥ ይሉኝ አትበል። ገቢውን ባለቤት ያውቃል። ገባ ወጣ፥ ነገር ያመጣ። ገባር፥ የአህያ ግንባር። ገባርና ድግር፥ ሲተካከል ያምር። ገብርኤል ይሠራል፤ ኒኮላ ይበላል። ገብያ ቢያመቻት፥ ልጇን ሸጠቻት። ገብጋባ ውሻ፥ ነክሶ ለጅብ ይሰጣል። ገብሱ የሚደርሰው ለፍልሰታ፥ እኔ የምሞተው ዚሬ ማታ። ገብስ ሲበስል፥ አባቱን ይመስል። ገብስ፥ የእህል ንጉሥ። ገብስና ሽንኩርት፥ ቂጡ ሲለብስ። ገብስና ሽንኩርት፥ ቂጡ ሲበስል ነው። ገብስና ገብስ፥ አብሮ ይነፍስ። ገብርኤል ያየው ምሥጢር። ገና በርቆ፥ ገና ዗ንቦ። (:_ ያልተወጠነ ሥራ) ገና እሄን ፈርቼ፥ በቀን ዗ግቼ፥ ገና ዗ንቦ ባርቶ። ገና ዗ንቦ፥ ባርቶ። ገና ዗ንቦ፤ ገና በርቶ። ገናም በሙክቱ፥ ሐዳዳም በእልበቱ ይታወቃል። ገናና ጥምቀት፥ እኩል አውዳመት። ገንፎ ለጉንፋን ያበስላል፥ እግረ መንገደንም ለሆድ ይበጃል። ገንፎ ለጉንፋን ደግ ነው፥ እግረ መንገደንም ለሆድ ይበጃል። ገንፎ ማላመጥ፤ በእግዛር ማልመጥ። ገንፎ ለጉንፋን ይበጃል፥ ወዱህም ለሆድ ይበጃል። ገንፎ ሠርታ ለራት፥ ቢያጎርሣት ተኮሳት። ገንፎ ሠርታ ለራት፥ ቢያጎርሣት ፈጃት። ገንፎ ሲበሉ ልጅ አስወግድ፤ ጠላ ሲጠጡ እሳት አንድድ። ገንፎ በሙቅ ተደግፎ። ገንፎ በድስት፤ ጎመን በምንቸት። ገንፎ እፍ እፍ ቢሉሽ፥ ሉውጡሽ ነው። እውነት አይምሰልሽ። ገዝቶ የማይቆጣ፤ አጥቦ የማያነጣ። ገንፎ እፍ እፍ፥ ቢሉሽ ሉውጡሽ። ገንፎ፥ እንክ እንክ ቢሉሽ ሉበሉሽ። (ሉበሉሽ ~ሉውጡሽ) ገንፎ፥ እፍ እፍ ቢሉህ፥ ሉውጡህ። (እፍ እፍ ~ እፍፍ) ገንፎ እፍ እፍ፥ ቢሉሽ ሉበሉሽ። ገን዗ቡ የሰው ቢሆን፥ አዳዩ የእኔ ይዅን። ገን዗ቤ፥ አትውጪ ከቤቴ። ገን዗ቤ አትውጪ ከቤቴ፥ ታጣዪኛለሽ ከጎረቤቴ። ገን዗ብ ለዕዳ፤ ሙግት ለባዳ። ገን዗ብ ማግኘቱ ይቀላል፥ ከማከማቸቱ። ገን዗ብ ሲናገር፥ እውነት አፏን ትይዚለች። ገን዗ብ በስተእርጅና፥ ወዳት ትገኚና? በልጅነትማ፥ ማን ይይዝሺና? ገን዗ብ ቢያብር፥ ላጥ ያለ ሀብታም ያረጋል። ገን዗ብ አክባሪውን፤ ባለጌ መካሪውን ይጠላል። ገን዗ብ እንደ ጌታው ነው። ገን዗ብ ከእጄ፤ ዗መድ ከደጄ። ገን዗ብ ከእጅ፥ ከወጣ ይመጣል (ይዝ) ጣጣ። ገን዗ብ ከእጅ፤ ዗መድ ከደጅ። ገን዗ብ ካለ፥ በሰማይ መንገድ አለ። ገን዗ብ የላለው፤ ጑ደኛ የለው። ገን዗ብ የልብ ሥር ነው። ገን዗ብ የልብ ሥር ነው፥ አጥፊውም ሰው ነው። ገን዗ብ የሚገኝ በሀያ ዓመት፤ ልብ የሚገኝ በአርባ ዓመት። ገን዗ብ የተውሶ፥ ጠፋ ተጨርሶ። ገን዗ብ የአጣ፥ ገበያም አልወጣ። ገን዗ብ የጠፋበት፥ ብዙ ኀጢአት አለበት። ገን዗ብ ያልያ዗ መንገደኛ፥ አይፈራም ቀማኛ። ገን዗ብ ገን዗ብን ይወልዳል። ገን዗ብ፥ በልጅነት ማን ሰበሰብሽ? በእርጅና ማን አግኝቶሽ። ገን዗ብህ ከእጅህ፤ ፍርድ (ዳኛ) ከደጅህ። ገን዗ብህን ከፊትህ አትለይ። ገዥዎች ግብዝችንና፥ ሸንጋዮች ይወዳሉ። ገደል ለዝንጀሮ፤ ጉድ጑ድ ለቀበሮ። ገደል ለገባ ሰው፥ በትርህን እንጂ እጅህን አትስጠው ጎትቶ ይከትሀልና። ገዳም የገባ አይወጣ፤ ከል የገባ አይነጣ። ገዳ ገድሽ ለእኔ፥ ሥጋሽ ለአረመኔ። ገድለኛ፥ መንፈሳዊ አርበኛ። ገዳይ ሲሸሽ፥ ሟች ይከተላል። ገዳይ ሲደርስ፥ አዳኝ ይደርስ። ገዳይ ሳይገኝ፥ ጉሮ ወሸባዬ። ገዳይ በበለሱ፤ ድሀ በንጉሡ። ገዳይ ቢ዗ገይ፥ ተገዳይ ይገሰግሳል። ገዳይ ቢያረፍድ፥ ሟች ይገሰግሳል። ገዳይ ከጥይቱ፤ ሥጋ ከብልቱ። ገድለው ከአላመለጡ፥ ምንድነው ጌጡ? ገድል በአለቃዬ፤ ከሶ ከጠበቃዬ። ገድል ነበር፥ ሞተ። ገድል ከአለቃዬ፤ ከሶ ከጠበቃዬ። ገጣባ አህያ ትሰለቻለች፥ ጭና ታበላለች። ገጣጣ ቢሞት፥ የሣቀ ይመስላል። ጉልበት አለኝ የበላ፤ ምላስ አለኝ የሰላ። ጉልበት አለኝ የዝኆን፤ አፍ አለኝ ለአንተ የሚሆን። ጉልበት አለኝ የዝኆን፤ አፍ አለኝ የመስፍን። ጉልበት አለኝ የዝኆን፤ አፍ አለኝ የመኮንን። ጉልበት የላለው ወንበዳ፤ ትርፍ የላለው ነጋዳ። ጉልበት የላላት ወይ዗ሮ፤ ገደል የላለው ዝንጀሮ። ጉልቻ ቢለዋወጥ፥ ማይክሮ ዌቭ አይሆንም። ጉልቻ ቢለዋወጥ፥ ወጥ አያጣፍጥም። ጉልቻ ቢቀየር፥ ወጥ አያጣፍጥም። ጉልቻ ቢቀያየር፥ ወጥ አያጣፍጥ(ም)። ጉልቻ የላቀኝ፤ አመድ ያጠለቀኝ አለ አማኑኤል ማን ጠየቀኝ። ጉልቻ የላቀው፤ አመድ ያጠለቀው። ጉም መግመጥ፥ ውሃ መግመጥ። ጉም ሲለቅ የታባትህ ትገባ፥ አንተ ላባ። ጉም ተራራን ያለብሳል፥ ሹም ለሹም ያወርሳል። ጉም ያፈነው፤ ጭጋግ የሸፈነው። ጉረኛ ወታደር ጋሻየን ሉቀማኝ፥ አኹንሳ ወሰደዋ! ጉሬዚ ቢውል ከጦጣ፥ ጥፋት ለምድ መጣ። ጉሮ ወሸባ፤ አጣልቶ ድረባ። ጉሽ መጥራቱ፤ ገፈት መንሳፈፉና፤ አተላ መዝቀጡ አይቀርም። ጉበትን በሳንባ አይለውጡም። ጉቦ የለመደ ዳኛ፤ አህያ የለመደ ጅብ አንድ ነው። ጉቦ የበላ ዳኛ፤ የወጋ መጋኛ። ጉቦና ላባ፤ በር አይወድም። ጉቦኛ፥ የባሰ መጋኛ። ጉታዬን አታጉድይብኝ፤ አሽከሮቼን አትሰርቢብኝ። ጉትቻ ለጆሮ፤ ጥሬ ለድሮ። ጉቶም ይቸግራል። ጉትቻ ለጆሮ፥ ትንሽ ትመስላለች ዚፈ ጎበዝ ትመልሳለች። ጉትቻ ለጆሮ፤ እልፍኝ ለወይ዗ሮ። ጉንዳን ሳይደርስ፥ አመድ ነስንስ። ጉንዳን ሳይደርስ፥ አስቀድመህ አመድ ነስንስ። ጉንዳን ባልንጀራው ሲሞት፥ ብቻውን ተሸክሞ ይዝረዋል። ጉንዳን ቤቱን ይመራል። ጉንዳን እስኪወጣ ብቻ ተኛኹ። ጉንዳን እስኪወጣብኝ ተኛኹ። ጉንዳን፥ የባልንጀራውን ሬሳ ብቻውን ያነሣ። ጉንዳን ያየህ፥ በአመድ። ጉንጭ አልፋ። ጉንፋን ሲያ጑ድደት፥ በሽታ ይሆናል። ጉንፋን የተያ዗ና፥ ፍየል ይዝ የተደበቀ፥ ሳይጋለጥ አይቀርም። ጉንፋን የታመመ:_ ውሻ፥ ልጅ፥ ፍየል ይዝ የተደበቀ አይሰወርም። ጉደኛ ውሻ፥ ሥጋ ተቀምጦ ቆል ትሻ። ጉዳት ከመጣ፥ መከራ አይታጣ። ጉዳት የደረሰበት እረኛ፥ እረጭ አያባርርም። ጉዳይ ሳይኖርህ፥ ገበያ አትውረድ፤ የአንደን (ሰው) ነገር ሰምተህ አትፍረድ። ጉዳይ አሳልፍ እንድትታማ፥ አሮጌ ኹን ልትፎክር፥ ሙት ልትመሰገን። ጉዳይ የላለህ ገበያ አትውረድ፥ ያንደን ነገር ሰምተህ አትፍረድ። ጉድ ለባለቤቱ፥ ልግም በገላ ነው። ጉድ ለባለቤቱ፥ የአንገት ልብስ ነው። ጉድ ሲፈላ፥ ይገኝ የለ ኋላ። ጉድ ሳይሰማ፥ መስከረም አይጠባም። ጉድ ሳይታይ፥ መስከረም አይመጣም። ጉድ ነሽ የአንኮበር ቅጠል፥ በየኼድሽበት ነገር ማንጠልጠል። ጉድ ነሽ የአንኮበር ቅጠል ነሽ፥ ከመለብለብሽ የመቆጥቆጥሽ። ጉድ ነሽ የአንኮበር ቅጠል፥ እያደር ትለበልቢያለሽ። ጉድ ነሽ የአንኮበር ቅጠል፥ ከመለምለምሽ የመለብለብሽ። ጉድ ነው፤ ሲዳሩ ማልቀስ፥ ሲታጩ ደስ ደስ። ጉድ ነገር፥ አበድሮ መቸገር። ጉድ እስከ እሐድ። ጉድ እንግዳ ነገር፥ አሳድሮ መቸገር። ጉድ ያለው ገንፎ፥ አድሮ ይፋጃል። ጉድ ይገርማል ጅብ ከአህያ ጋር እንዳት ይከርማል። ጉድ ጉድ፥ ምን ያንተን ጉድ፥ እየው የኔንም ጉምድ። ጉድ ይገርማል፥ አህያ ከጅብ ይከርማል። ጉድ ፈላ:_ ሴት ተቀምጣ፥ ወንደ ቡና አፈላ። (ወንደ ~ ወንድ) ጉድሽ፥ ድንቅሽ ና ብለሽ፥ ወዳት ኼድሽ? ጉድና ብርቅ እስከ ሦስት ቀን ያስጨንቅ። ጉድና ድንቅ አለ አንድ ጊዛም አይደምቅ። ጉድና ድንቅ፥ አንድ ሰሞን ነው። ጉድና ድንቅ፥ አላንድ ሰሞን አይደምቅ። ጉድና ድንቅ እስከ ሦስት ቀን ያስጨንቅ። ጉድና ጅራት በስተኋላ ነው። ጉድና ጅራት፥ ከወደኋላ ብቅ ይላል። ጉድ጑ድ፥ በራሱ አፈር አይሞላም። ጉጉት ብትጠቃ፥ እርኩም ሆነ ጠበቃ። ጉፋያ ሲነደ ይሸከሙ። ጉፋያ ከመብላት፥ ሥብ መሸከም ይሻላል። ጉፋያ ከመብላት፥ ጮማ መሸከም። ጉፋያ ከሚያርደ፥ ሥብ ይቀላውጡ። ጉፋያን ሉበሉ፥ ሥብ ይቀላቅሉ። ጉፋያን ሉበሉ፥ ሥብ ይቀላውጡ። ጊዛ መስተዋት ነው። ጊዛ ሲከዳ፥ መሬቱ ያድጣል። ጊዛ አለው ለሰው፥ ዕድሜ ከአላነሰው። ጊዛ እስኪያልፍ፥ የአባቴ ባሪያ ይግዚኝ። ጊዛ ወርቅ ነው፥ ግን ኀላፊ ነው። ጊዛ የላለው የለም ግን፥ ከእድሉ የሚያልፍ የለም። ጊዛ የሰጠው ቅል፥ ድንጋይ ይሰብራል። ጊዛ የሰጠው ቅል፥ ጋን ይሰብራል። ጊዛ የሰጠው ቅጠል፥ ሪከርድ ሰበረ። ጊዛ የሰጠው ቅጠል፥ ብረትን ያንገረግራል። ጊዛ የሰጣት አይጥ፥ ከፈረሰኛ እኩል ትሮጣለች። ጊዛ የጣለው፥ በቁሙ ይወድቃል። ጊዛ ያለው፥ ጊዛ አይጠብቅ። ጊዛ ያደርጋል፥ የእንስሳ ሚዛ። ጊዛ ያፈርሳል፤ ቀዳዳ ያፈሳል። ጊዛ ገቢር ለእግዙአብሔር። ጊዛና ቂጣ ተገልባጭ ነው። ጊዛና በሽታ፥ ቀን አይቶ ይጥላል። ጊዛው ጊዛ ሆኖ ወራቱ ቢመቻት፥ ዗ንድሮስ ድመቴን አይጥ ገደለቻት። ጋለሞታና ጌታ፥ ደጅ የጠኑ ለታ። ጋማ ልሠራ ነው፥ አለችው። ጋሪ፥ ድሀን አኩራሪ። ጋራና ጉባ፤ ቅልና ደባ። ጋሻ ለግንባር፤ መጫሚያ ለጠጠር። ጋሻ ለግንባር፤ ጫማ ለጠጠር። ጋሻ ስቀል በኼት ደርሼ? ግማሽ ብላ ከማን አንሼ? ጋሻ ስቀል እንዳት ደርሼ? ግማሽ ብላ ከማን አንሼ? ጋሻ እሰጥ፥ ጋሻ እሰጥ ሲሉ፥ ጦር አገባ። ጋሻ ከንግቡ፤ ነገር ከግቡ። ጋሻ፥ ድሮ ቀረሻ። ጋሻና ግንባር አይሸሸግም። ጋሻን ውጊያ እንዳት ነው? ቢለው ጋሻ ወርውሮ፥ ጦር መመከት ነው አለው። ጋቢ ቢያብር፥ ብርድ ይከላከላል። ጋብቻ ለአንድ ሳምንት ብቻ፥ ተመልሶ ጠብና ሽኩቻ። ጋን ሠሪ፥ ምጣድ አይዋጣለትም። ጋን ሲለቀለቅ፥ ማድጋን ይሞላል። ጋን ሲያሟጥጡት፥ ምንቸት ይሞላል። ጋን በጠጠር ይደገፋል። ጋን ቢለቀልቁት፥ ምንቸት ይሞላል። ጋን ቢያሟጥጡት፥ ምንቸት ይሞላል። ጋን ቢያንጫልጡት፥ ማሰሮ ይሞላል። ጋኖች አለቁና፥ ምንቸቶች ጋን ሆኑ። ጋይ የለ፥ እሸት ስጡኝ አለ። ጋጋሪ ያበስላል፤ ተናጋሪ ያስመስላል። ጌታ ለልላው፥ ነጋዳ ለአሞላው (ያስባል)። ጌታ ሲሰጥ፥ ማን ይከለክላል? ጌታ ሲወድ ማን ይጠላል፤ ጌታ ሲሰጥ ማን ይከለክላል። ጌታ ቢጫወት፥ ያልኮራ ይመስላል። ጌታ ባወቀው ይፈርዳል፥ ሰው ባላወቀው ይጎዳል። ጌታ የዕለቱን፤ አባት የመሠረቱን። ጌታ ያዚል፤ ውሃ ያነዝዚል። (ያነዝዚል ~ ያነፃል ~ ያነጻል ~ ይለዚል ~ ይነዚል) ጌታዅን እንዳሻህ ኹን። ጌታና ልላ ተሟግቶ፤ ጅብና አህያ ተጋብቶ አይሆንም። ጌታና ልላ ተጣልተው፤ ደባና ቅል ተማተው ኧረ አይመስልም ተው። ጌታና ልላ ተጣልቶ፤ ቅልና ድንጋይ ተማቶ። ጌታና ገበታ አቅራቢ ነው፤ ሰጭው እግዛር ነው። ጌታና ጋለሞታ፥ ደጅ የጠኑ ለታ። ጌታዅን እንደፈቃድህ (ት)ዅን። ጌታዋን የምታምን ውሻ፥ ፍሪዳ ሲታረድ እወንዝ ትወርዳለች። ጌታዋን የምታምን ውሻ፥ ፍሪዳ ሲታረድ እወንዝ ወረደች። ጌታውን ከአልናቁ፥ ውሻውን አይመቱ። ጌታዋን የምትወድ ላም፥ ትወልዳለች በመስከረም። ጌታዋን ያመነች ላም፥ በመስከረም ትወልዳለች። ጌታዋን ያመነች በግ፥ ላቷ ውጭ ያድራል። ጌታውን ያመነ በግ፥ ላቱን ውጭ ያሳድራል። ጌታውን ያየ አሽከር፥ ይጥላል በትግል። ጌታውንና በሽታውን የሚንቅ፥ እያደር ይወድቅ። ጌታዬ ምን አልኩህ? ጠጅ አጠጥተህ ውሃ። ጌታዬ ከአሉበት አግሙኝ። (አግሙኝ ~ እገሙኝ) ጌታዬ ያለበት እገመኝ። ጌታዬን ያማ ሰው፥ ነጭ እከክ ይውረሰው። ጌቶች ወደውኛል፥ ጨርቃቸው ነክቶኛል። ጌጥ ያለቤቱ፥ ቁምጥና ነው። ግልብጥ ሲሉ ግልብጥ። ግልግልና ገንፎ፥ ትኩሱን አያስገባም። ግመል ለተጫነ፥ አህያ ጮኸ። ግመል ምን ተጭነሀል? ሽመል ምን ያወዚውዝሀል? አመል። ግመል ሰርቆ፥ ኼደ አጎንብሶ። ግመል ሰርቆ፥ ተጎንብሶ (ኼደ)። (ተጎንብሶ ~ አጎንብሶ) ግመል ሰርቆ፥ ጎንበስ ጎንበስ። ግመልን የምትውጡ፥ ትንኝ የምታጠሩ። ግማሹን ተላጭታ፥ ግማሹን ተቀብታ። ግማሽ ልጩ፥ ግማሽ ጎፈሬ። ግማሽ ተላጭቶ፥ ግማሽ ተሠርቶ። ግም ለግም፥ ቢተቃቀፍ አይነቃቀፍ። ግም ለግም፥ አብረህ አዝግም። ግረፍ (ግን)፥ ከባት አትለፍ። ግራ መብል፥ ቀን ገንፎ፥ ላሉት ድፎ። ግራ መብል፥ ቀን ገንፎ፥ ላሉት ድሮ። ግራ ነገር፥ ከወንዝ ማድ ፍቅር፥ ከጎረቤት ጥል። ግራር ሲበቃው፥ ልምጭ ይወቃው። ግራኝ እና ግንቦት፥ ደረቆች ናቸው። ግርግርታ ለላባ ደስታ። (ለላባ ~ የላባ) ግባ ያላለው ገን዗ብ፥ አጥር ቀድ ይወጣል። ግብ እንደ ግቡ፤ ሙክት እንደ ስቡ። ግብር እስከ መቃብር። ግብር ይውጣ። (:_ የማይቀር ዕዳ) ግብዝና፥ መቼ እንደ ድቁና። (ድቁና ~ ዱቁና) ግብዝን፥ ኹለት ጊዛ እባብ ነከሰው። ግና ዗ንቦ ባርቶ። ግንብና ልጅ፥ ስምን ያስጠራሉ። (ግንብና ~ ሕንጻና) ግንብና ድንጋይ፤ ጌታና አባይ። ግንቦት ቢዳምን የሚ዗ንብ ይመስላል፤ ሀምላ ቢባራ በጋ ይመስላል። ግንቦት ቢዳምን የሚ዗ንብ ይመስላል፤ አሮጌ ቢፎክር የሚዋጋ ይመስላል። ግንቦት ቢዳምን ይ዗ንብ ይመስላል፤ ሀምላ ቢባራ በጋ ይመስላል። ግንድ ለሺ አይከብድ። ግንድ ለሺ አይከብድም። ግዚኝ ብለው፥ ለመሸጥ አሰበኝ። ግዚኝ ብዬ ብፈቅድለት፥ ሉሸጠኝ አሰበ። ግዚኝ፥ ግዚኝ ብለው፥ ሉሸጠኝ አሰበ። ግደፈኝ ብትለኝ፥ ግድፍ አደረግኋት። ግዳይ ለከንፈሬ፤ ጥምጥም ለመምሬ። ግዳይ አምሯቸው ዗መቱ። እሳቸውም ሞቱ። ግጦ ከወጥ ባለጌ፤ መረን አግድም አደግ። ግፈኛ የሰይጣን መላክተኛ። ግፍ ሲቆም፤ ጸልት አያሻም። ግፍ ሲናኝ፥ ኩበት ሰጥሞ ድንጋይ ይዋኝ። ግፍ ሲናኝ፥ ኩበት ሲጠልቅ ድንጋይ ይዋኝ። ግፍ በአገር ሲሞላ፥ ርስ በርስ ያባላ። ግፍ በአገር ሲናኝ፥ ኩበት ይጠልቃል ድንጋይ ይዋኛል። ግፍ በአገር ሲናኝ፥ ኩበት ጠልቆ ድንጋይ ይዋኝ። ግፍ አይቀርም፤ ስም አይቀበርም። ግፍ አይፈሬ መሬት፥ እንክርዳድ ያበቅላል። ግፍ የላለበት ጠላ፥ ያለ ብቅል ይበስላል። ግፍ የተሠራብን በእኛ፤ ካሱ ይሉናል በዳኛ። ግፍስ በባሕር ይመላል፤ አሣ አሣውን ያበቅላል። (ያበቅላል ~ ይበላል) ጎልማሳ በሚስቱ፤ ንጉሥ በሠራዊቱ። ጎልማሳ ቢታጠቅ ከደረቱ፥ ሲሮጥ ከጉልበቱ። ጎልማሳ እበቀለበት ላም አይማረክም፥ ሽማግላ እበቀለበት ነገር አይሳሳትም። ጎልማሳ፥ እንደ በላ አንበሳ። ጎልማሳ ከአለበት ከብት አይሰረቅ፤ ሽማግላ ከዋለበት ነገር አይነጠቅ። ጎልማሳ ከአለበት ከብት አይነጠቅ፤ ሽማግላ ከዋለበት ነገር አይወድቅ። ጎመን ለአጡለት፥ ሀር ቀደደለት። ጎመን በጤና። ጎመን ባወጣው ነፍስ፥ ቂጥጥ አለች ገብስ። ጎመን ባወጣው ነፍስ፥ አትኩራ ገብስ። ጎመን ጠነዚ፥ ሴት ከበዚ። ጎረምሳ እንደበላህ፥ አንሣ። (አንሣ ~ አግሳ) ጎረቤት አያውቅ ነገር፤ ወንጠፍት አያጠራው አሰር። ጎረቤት የላለው፥ አንባ጑ሮ የለው። ጎረቤት ይሆናል ጠላት፥ ያችን ሴት አት዗ንጊ በሎት። ጎረቤት ጤና ይደር፥ አንተ ጤና እንድታድር። ጎረቤትህን ሲያማ፥ ለእኔ ብለህ ስማ። ጎረቤት፥ ይሆናል ጠላት። ጎራዳ ለወንበዳ፤ ሱቅ ለነጋዳ። ጎራዳህ ጎመዳም፤ ሚስትህ አመዳም። ጎራዳና ምስጥ፥ ውስጥ ለውስጥ። ጎርፍ ሲወስድ እያያሳሣቀ፥ ተንኮለኛ ሰው ሲጎዳ እየተራቀቀ ነው። ጎሽ ለልጇ (ስትል) ተወጋች። ጎሽ ለልጇ (ብላ) ትወጋ። ጎሽ ላይሉኝ ወሶ፥ ደርሼ ነበር እረጋ ለቅሶ። ጎሽ ጠመድኩ ይሆናል ብዬ፥ ፈትቼ ሰደድኩ አይሆንም ብዬ። (ይሆናል ~ ይሆነኛል) ጎበዝ ጎበዝ ቢሎት፥ የባሎን መጽሀፍ አጠበች። ጎበዝ:_ ፊት ሰማይ ሰማይ ያያል፥ ኋላ ምድር ምድር ያያል። ጎባጣን ሲቀብሩ፥ እንደ አመሉ። ጎበዝ፥ ስለ በለስ። ጎበዝ፥ አደባባይ አያንቧትርም፥ እበረሓም አይለቅም። ጎበዝ ዳኛ፥ ቆይቶ አራጋቢ ይሆናል። ጎባጣን ቀንና፥ ቅዝምዝምን አጎንብሰህ እሳልፈው። ጎባጣን እንዳት ይቀብሩ፥ ቢሉ እንዳመሉ። ጎባጣን ይቀብሩ፥ እንደ ምግባሩ። (ይቀብሩ ~ ይቅበሩ) ጎኑ ቀኜ፤ ቀኑ ለእኔ። ጎኑ የእኔ፤ ቀኑ ሠኔ። ጎንደሬ ሲናገር፥ እን኱ን ሸዌ ጎጃሜም አይሰማው። ጎንደር ወጣህ፥ ምን ይ዗ህ መጣህ? ጎንደር ወጣሽ፥ ምን አመጣሽ? ጎንደር ወጣሽ፥ ምንድር አመጣሽ? ጎንደር ወጣ፥ ምን ይዝ መጣ? ጎንደርን በመከራ፤ ጎጃምን በከ዗ራ። ጎዳ ከብት፥ ከቀንዳም ይብሳል። ጎዳናና መንገድ፤ ጉንጉንና ገመድ። ጎዳው ፍየል፥ ቀንዳሙን ወጋው። ጎድል ነበር ሞላ፤ ሞልቶ ነበር ፈላ። ጎጃም ሲያምጥ፤ በጌምድርን በፍልጥ። ጎጃም በ዗ነበ፥ ሳይንት እህል ሆነ። ጎጆ ወጭ ሙሽራ፥ በገፍ ወጥ ትሠራ። ጐረሮ የሚውጠውን፥ እጅ ይመጥነዋል። ጉረኛ ዕውር ቴላቭዥን ይገዚል። ጠላ ሲሉት ሽምጥጥ፤ ኮሶ ሲሉት ስቅጥጥ። ጠላ በማቶቱ፤ እንጀራ በላማቱ። ጠላ ቢመላ ሦስት ነገር ያጠፋል። መጀመሪያ አፍ ያሞጠሙጣል፤ ኹለተኛ እርሱ ይፈሳል፤ ሦስተኛ ልብስ ያበላሻል። ጠላ ባለቤቱን አያውቅም። ጠላ ከማቶት፤ እንጀራ ከላማት። ጠላ ከአሰከረው፥ ወተት ያሰከረው። ጠላ ከአሥር፤ ነገር ከአገር። ጠላ የባዕድ፥ አሳላፊ ዗መድ። ጠላ ያለ አተላ፤ ጠጅ ያለ አንቡላ። ጠላሽ መለኛ፤ ወ዗ወ዗ኛ። ጠላሽ በቀጠነ፤ ዳቦሽ ባረረ። ጠላቴን ሳማ፥ እኔ እጎዳለኹ እንጂ እሱ አይጎዳም። ጠላት ሲነሣብህ፥ የወዳጆችህን ቁጥር አበርክት። ጠላት ሳይነቀል፥ ሰብል አይለቀም። ጠላት በጥርስ ሲገኛ፥ (እባክህ) አታስጎምጀኛ። ጠላት በጥርስ ሲገኝ። ጠላት ቢያብሉት፥ ወዳጅ አይሆንም። (ቢያብሉት ~ ቢያባብሉት) ጠላት ባጭር ታጥቆ፤ ዗ገር ነቅንቆ ። (ነቅንቆ ~ ነጥቆ) ጠላት ከውጭ አይመጣም። ጠላት የላለው፥ ወዳጅ አያሻውም። ጠላት ያማል፤ ወዳጅ ይወቅሳል። ጠላት ያነቃል፥ ያተጋል። ጠላት ይገፋል ዱቃላ፤ ረኃብ ይከላል ባቄላ፤ ቀን ያሳልፋል ነጠላ። ጠላት ይገፋል ዱቃላ፤ ወራት ይገፋል ባቄላ፤ ያግደረድራል ነጠላ። ጠላትህን ውሃ ሲወስደው፥ እንትፍ ብለህ ጨምርበት። ጠላት፥ ይቀባል፥ ጥላት። ጠላትን በጦር፤ አባትን መጦር። ጠላትህን የምትጠነቀቀው አንድ ጊዛ፤ ወዳጅህን የምትጠነቀቀው ኹል ጊዛ። ጠላትን ለማግኘት ሲጎረጉሩ፥ በወዳጅ ይጀምሩ። ጠላና ወጥ ያነሰው፥ ደረቅ። ጠላና ዝና ዕለቱን አይደርስም። ጠላና ጉተና፥ በአንድ ቀን አይደርስም። ጠላና ጉተና ዕለቱን አይደርስም። ጠላኝ ማለት ያስጠላል፤ ልግደል ማለት ያስገድላል። ጠላው ሳይገባ፥ ማቶቱ። ጠላው ሳይገባ ማቶቱ፤ ቀንደ ሳይገባ ጅራቱ። ጠላው አልበጀ፤ ቅራሪው ሰው ፈጀ። ጠላው የባዕድ፥ አሳላፊው ዗መድ። ጠላዬ በቀጠነ፤ ቆልዬ ባረረ ማሩኝ። ጠልቶ ለጠላት፤ አስሮ ለእስራት። ጠመንጃ ራሱ ገድል፥ ራሱ ይጮሀል። ጠመንጃ ያለ ጥይት ደላ፤ ወንድ ያለ ሴት ቀውላላ። ጠመደና በሬና ዝኆን፥ መቸም እንዳይሆን። ጠማማ ሰው፥ ክፋትን ከዅሉ ያደርሳል። ጠማማ ዚፍ፥ በየጊዛው ከአልቀና አይስተካከልም። ጠረፍ ያለ ባላንጣ፥ ቤት ያለ ጣጣ። ጠሪታው፥ ወይ ባዩን አስቆጣው። ጠርሙስ በልታ። ጠርቦ ለደጁ፤ ፈርድ ለልጁ። ጠርጥር፥ በገንፎ ውስጥ እንዳለ ሥንጥር። ጠርጥር፥ ከምግቡ ውስጥ አለ ሥንጥር። ጠርጥር፥ ከገንፎም አለ ሥንጥር። ጠቋሚ ከእናሪያ ይመጣል፤ አጥፊ ከጉልበት ይወጣል። ጠቋሚ ጠቃሚ። ጠበቃ ታፈጀ፤ በርበሬ ታረጀ። ጠበቃና ቅል፥ ባጠገብ ይውላል። (ይውላል ~ ይውል) ጠበንጃ፥ ራሱ መቶ፥ ራሱ ይጮሀል። ጠቢብ፥ ይበላል በገል። ጠባ ለኪዳን፤ መሸ ለቁርባን። ጠባቂ ያላት በግ፥ ላቷን እደጅ ታሳድራለች። ጠባቂ ያላት በግ፥ ላቷ እደጅ ያድራል። ጠባብ አልጋ፥ የግድ ያስተቃቅፋል። ጠባብ አልጋ፥ ያለውድ ያስተቃቅፍ። ጠባብ የወፍ ቤት፥ በግድ ያስተቃቅፋል። ጠባዩ ያውሬ፤ መልኩ የበሬ። ጠባይ ሲደረጅ፥ ባሕርይ ይሆናል። ጠብ ያለሽ በዳቦ። ጠብ ባለበት ቤት፥ ድሮ (ከቆጥ) ትሞት። ጠብ ተጀመረ፤ አንበሳ ላምን ሰበረ። ጠብ ተጀመረ፤ ያ ልጅሽ አለ? ልጄ ሲል የነበረ። ጠብ ከአለበት ቤት፤ ድሮ ከጋጥ ትሞት። ጠብ የሻ መኮንን፥ አምጡ ይላል የድሮ ሻኛ። ጠብ ያለበት፤ ቤት ድሮ ትሞት። ጠንቋይ ለራሱ አያውቅም። ጠንቋይ ለራሱ አያውቅ፥ ለአዋይ። ጠንቋይ ባያሳምን፥ ያጠራጥራል። (ያጠራጥራል ~ ያጠራጥር) ጠንቋይ ባያሳምንም፥ ያጠራጥራል። ጠንቋይ፥ አባይ ቤት ያስፈታል። ጠዋት ሽሮ፤ ማታ ድሮ። ጠዋት ከበላተኛ፤ ማታ ከአድመኛ። ጠዋት ከበላተኛ፤ ማታ ከጦመኛ። ጠዋት ከጀንበር፤ ማታ ከጨንገር። ጠዋት ከጾመኛ፤ ማታ ከአድመኛ። ጠዋት ጆሮ፤ ማታ ጆሮ። ጠያቂ ባይኖር፥ ዅሉ መምህር። ጠያቂ የለም እንጂ፥ ከድሀ ምክር ይገኛል። ጠይቆ ከማፈር፤ ወድቆ መሰበር። ጠይብ፥ በገል ይበላል። ጠጅ ለወረት፤ ወዳጅ ለችግር ዕለት። ጠጅ ለጨዋ ልጅ መጫወቻው፤ ለባለጌ ልጅ መማቻው። (ለባለጌ ~ ለድሀ) ጠጅ በብርላ፤ ነገር በምሳላ። ጠጅ በብርላ፤ ዛማ በሃላ። ጠጅ የላለበት አበጋዝነት። ጠጅ የወረት፤ ወዳጅ የበላ ዕለት። ጠጅ የጠጣ ከሰረ፤ ውሃ የጠጣ ከበረ። ጠጅ ይሻላል በመጠኑ፤ የጨዋ ልጅ ይበልጣል በቀጭኑ። ጠጅና መኮንን፤ ድሀና ጎመን። ጠገብኹ ያለውን ብላ አትበለው፤ ፈራኹ ያለውን ድፈር አትበለው። ጠጉረ ሉጫ፤ አይነ መጭማጫ። ጠጉራም ውሻ አለ፥ ሲሉት ይሞታል። ጠፍር መጫኛ፤ ቁርበት መገኛ። ጠፍር በሉታ ብትኼድ፥ ል጑ም በሉታ መጣች። ጡት መጥባት፥ የእናት። ጡጥም ከፈስ ተቆጠረች። ጢም የላለው መምህር፤ አጸድ የላለው ደብር (አምሮም አያምር)። ጢምህን እጠላለኹ፤ መሳምህን እወዳለኹ። ጢሰኛ ሲቆይ፥ ባለርስት ይሆናል። ጣል በደጅ፤ እሰር በፍንጅ። ጣል በግድ፤ እሰር በግንድ። ጣመኝ ድገመኝ። ጣት ገማ ብል፥ ቆርጦ አይጣልም። ጣዝማ ሰርሳሪ፤ ዳኛ መርማሪ። ጣዝማ ይሰረስራል፤ ዳኛ ይመረምራል። ጣይ ብልጭ ሲል፤ ወፍ ጭጭ ሲል። ጣይ ያየውን፥ ሰው ሳያየው አይቀርም። ጣጣ ፈንጣጣ። ጣጣ ፈንጣጣ፤ ድንጋይ ፈለጣ። ጣፊያ ቢነሧት፥ ታናሽ ታላቅ ላኩልኝ አለች። ጣፋጭ ፍቅር ሲያረጅ፥ ፍቅረኞችን ያፋጅ። ጤና ከሀብት፤ ወፍጮ ከከብት አይቆጠርም። ጤፍ መፍሰስሽን ቢያይ፥ ገበሬ ባል዗ራሽ። ጤፍ ቢሰኩ፤ ሰማይን ቢያኩ አይገኝም ልኩ። ጤፍ አይቆላ፤ የጨዋ ልጅ አይጠላ። ጤፍ አጎደለ፤ ቢለው ገብስ እንዳይሰማ አለው። ጤፍ ከአላረሙ አይለማ፤ ሥጋ ከአልሰነበተ አይገማ። ጤፍ ከአቅሙ፥ እንክርዳድ ከፈለ። ጤፍ ከ዗መዶ፥ ጎታ ትሞላ። (ትሞላ ~ ትሞላለች) ጥለውት የመጡትን ጑ደኛ፥ ዙረው አያዩትም። ጥላና ሸኝ ቤት አይገቡም። ጥል ያለሽ፥ በዳቦ። ጥል ያጠላላ፤ ኮሶ ለአፍ ይጠላ። ጥልቅ ብዬን፥ ውሃ ወሰዳት። ጥልቅ ጥብቅ ሀሳቡና ነገሩ፤ ጠባዩና ግብሩ። ጥምድ እንደ በሬ፤ ቅንት እንደ ገበሬ። ጥምጥም የላለው መምህር፤ አጸድ የላለው ደብር። ጥሩ መስል አተላ፤ ፍሬ መስል ገለባ። ጥሩ እንደ ብርላ፤ ቀይ እንደ በርበሬ። ጥሩ ከአደፍ። ጥሩ ወዳጅ፤ ጥሩ ጠላት፤ ጥሩ ጠላት፤ ጥሩ ወዳጅ ይሆናል። ጥሩ ድህነት፤ ጥሩ ነጻነት፤ ጥሩ ሀብት፤ መልካም ርስት። ጥሩ ጠላት፤ ጥኑ ወዳጅ ይሆናል። ጥሩ ወዳጅ፥ ጠላት ይሆናል። ጥሩ ወዳጅ፤ ጥሩ ጠላት ይሆናል። ጥራትና ንጋት፥ እያደር። ጥሬ ለድሮ፤ ግልገል ለቀበሮ። ጥሬ ጠብ፤ ድሮ ቀርቀብ። ጥሬና ነገር ሆድ ያሻክራል። ጥሬና ክፉ ንግግር፥ ሆድ ያሻክራል። ጥርሴስ ልማደ ነው፥ አይኔን አታሥቀው። ጥርስ የላላት፥ ጥርስ ያላትን ነክሳ፥ አነካከስ ታስተምራለች። ጥርስ፥ ለብርድ ይሥቃል። (ለብርድ ~ ለነፋስ) ጥርስ ሳይገጥ፤ ከንፈር ሳይገለጥ። ጥርስና ከናፍር፥ ቢደጋገፍ ያምር። (ቢደጋገፍ ~ ተደጋግፎ ~ ሲደጋገፍ) ጥርስና ከንፈር አብሮ ይደማል። ጥቁር፥ አሥር ቢበላ አይነጣም። ጥቂት ሕመም ታመህ፥ ወዳጅ ጠላትህን እየው። ጥቂት ሥጋ፥ እንደ መርፌ ትወጋ። ጥቂት ሽሮ፤ ማታ ድሮ። ጥቂት ያለው ዅሉ፥ ብርቁ ነው። ጥቂት ያላት፥ እረፍት የላት እንቅልፍ። ጥቂት ጥቂት ዔሉም ትኼዳለች፥ ከአሰበችበት ትደርሳለች። ጥቃት ከጥንብ ይገማል። ጥቅልል ላለ ጠጉር፥ ዗ር዗ር ያለ ሚድ። ጥቅልል ያለን ጠጉር፥ ዗ር዗ር ያለ ሚድ ያነሣዋል። ጥበበኛ ባሪያ፥ ጌታውን ይገዚል። ጥበብ ያስከብራል፤ ሀብት ያስጨፍራል። ጥበብና ዕውቀትን፤ ማስተዋልና እውነትን። ጥኑ ወዳጅ፤ ጥኑ ጠላት ይሆናል። ጥኑ ወዳጅ፤ ጥኑ ጠላት፤ ጥኑ ጠላት፤ ጥኑ ወዳጅ ይሆናል። ጥንብ ባለበት፥ ቁራ ይዝራል። ጥንብ ባለበት፥ ጅብ አያጡም። ጥንቱ የተውሶ፥ ያውም ጠፋ ጨርሶ። ጥንቱን ሲሉህ ቡዳ፥ ቆዳ ይ዗ህ ሜዳ። ጥንቱን ባል዗ፈንሽ፥ ከ዗ፈንሽም ባላሳፈርሽ። ጥንቱንም ባል዗ፈንሽ፥ ከ዗ፈንሽ ባላፈርሽ። ጥንቱንም የተውሶ፥ ያውም ጠፋ ጨርሶ። ጥንቱንም የተውሶ፥ ጠፋ ተመልሶ። (ተመልሶ ~ ጨርሶ) ጥንት የነበረ ሃይማኖት ተዋሕድ ነበር፥ ቅባት ካራ የሚሉ ሃይማኖት ተጨምሮ፥ ሥጋ አለቀ ዗ንድሮ። ጥንቸል እንደ አቅሟ ታግታለች። ጥንቸል እንደ ዝኆን እጮሀለሁ ብላ ተሰንጥቃ ሞተች። ጥንቸልም ለሆዶ ዝኆንም ለሆደ አብረው ውሃ ወረደ። ጥይት እይር፤ ፈትል ድውር። ጥይት፥ የፈራትን ትወጋለች። ጥይትና ማጣትን፥ ተኝቶ ማሳለፍ ነው። ጥድ ዗ለል። ጥጃ መጫወቷ እንጂ፥ መራገጧ አያምርም። ጥጃ ሲጠባ፥ በአፉ እናቱን ይለትማል። ጥጃ ሣር ይበላል፤ ቤቱ ዕዳ ይሞላል። ጥጃ በጥሶ ኺድ ማሰርያው ይጮሀል፥ ቅሉ ተሰብሮ ወተቱ ተሰቅሎል። ጥጃ ቢሳሳት ከእናቱ፤ ነገር ቢሳሳት ከጠዋቱ። ጥጃ ቢሳሳት ከእናቱ፤ ነገር ቢሳሳት ከጠዋቱ፤ ሰይፍ ቢመለስ ከአፎቱ። ጥጃ ቢፈነጭ በሜዳ፤ ውሃ ቢሮጥ በጎድ጑ዳ ቢኼድ። ጥጃ ጠባ፥ ከሆድ ገባ። ጥጋበኛ ከርከሮ፥ የነፍጠኛ ጎጆ ይታከካል። ጥጋበኛንና ውሃ ሙላትን፥ ቁመህ አሳልፈው። ጥጋቡን የማይችል፥ አህያ ነው። ጥጋብ ቢሻህ ባቄላ፤ ኑሮ ቢሻህ ችላ። ጥጋብ ቢያምርህ ጠላ፤ መግዚት ቢያምርህ ችላ። ጥጋብን ወደኛ በል፤ ጥጋበኛን ወዱያ በል። ጥጋብን የማይችል፥ አህያ ነው። ጥጥ ለፈታይ፥ ሽልማት ላገልጋይ። ጥጥ ቂጥ ይወዳል ቢሎት፥ ጠቅልላ ቁጭ አለችበት። ጥጥና ሹም፥ እያደር ይከዳል። ጥፌ ለችፌ። ጦሙን የሚውል ሆድ፥ ማለዳ ይርበዋል። ጦም ከማደር፤ ዳቦ ቀርቅር። ጦም የሚያድር ሆድ፥ በጠዋት ይራባል። ጦር ለወረወረ፤ መሬት ለገበረ። ጦር ለወረወረ፤ ጎራዳ ለሰነ዗ረ። ጦር መጣ፤ ሲባል ሶማያ ቆረጣ። ጦር ሲመጣ፤ ዚቢያ ቆረጣ። ጦር እንደ ወረወሩት፤ ጎራዳ እንደ ሰነ዗ሩበት። ጦር እንደ ወጊው፤ ልጅ እንደ አሳዳጊው። ጦር ከወጋው፤ ምላስ የወጋው። ጦር ከፈታው፤ ወሬ የፈታው። ጦር ከፈታው፤ ወሬ የፈታው ይብሳል። (ይብሳል ~ ይበዚል) ጦርና ጭሬ፤ አራሽና ገበሬ። ጦጣ ባለቤትን ታስወጣ። ጦጣ፥ ተይዚ ት዗ፍን። ጦጣ ከዚፍ ላይ ሆና፥ ከአንበሳ ጋር ጸብ ትጭራለች። ጦጣና ዝንጀሮ፤ ተኩላና ቀበሮ። ጦጣ፥ መጀመሪያ የመቀመጫዬን አለች አሉ። ጦጣ ምን ትወጃለሽ ቢሎት፥ ከዚፍ ላይ ትግል። ጦጣ በልታ፥ በዝንጀሮ አፍ አበሰች። ጦጣ፥ ባለቤቱን ታስወጣ። (ባለቤቱን ~ ባለቤቷን) ጦጣ፥ ባለቤቱን አስወጣ። ጧሪ በፈጣሪ። ጧሪና ተዝካር፤ አውጪ አያሳጣህ። ጧት ከበላተኛ፤ ማታ ከዕድምተኛ። ጧት ከበላተኛ፤ ማታ ከጦመኛ። ጧት ከበላተኛ፤ ማታ ከጦመኛ፤ እንደ ሽመላ በኹለት ይበላ። ጧፍ ያበራል፤ ከሳሽ ይመራል። ጨለማ ለብሶ የሚመጣ፥ ክፉ ነው። ጨልጠሽ ጋግሪ፤ ካለ ፈጣሪ። ጨምሪ ጨምሪ፥ በወንድ ልጅ ተበከሪ። ጨረቃ ብትደምቅ አታሞቅ፤ የሰው ቤት አያደምቅ። ጨረቃ ብትደምቅ፥ አትሞቅ። ጨረቃና ሴት፥ ዚሬ ብርሃን፥ ነገ ጽልመት። ጨርቅ አጠርቅሞ፤ መስቀል ተሸክሞ። ጨቅጫቃ ሚስትና፤ የሚያፈስ ቤት አንድ ናቸው። ጨቅጫቃ ባል፤ የሚያፈስ ቤት። ጨብጦ የቀረ፤ ተጨብጦ ቀረ። ጨካኝ፥ ሰይጣን መሳይ። ጨካኝ አልሞተ፥ ፈሪም አልሞተ፥ አ጑ጉለኛ ሞተ። ጨካኝና ጭስ መውጫ አያጣም። ጨዋ አይነቅፍ፤ እሳት አይታቀፍ። ጨዋታ ለአዋቂ፤ ወሬ ለጠያቂ። ጨዋታን አዳምጦ፤ እህልን አላምጦ። ጨዋነሽ ቢሎት፤ ሣቁ ገደላት። ጨው ለራስህ ስትል ጣፍጥ፥ አለዙያ ድንጋይ ነው ብለው ይጥሉሀል። ጨው ለራስህ ስትል ብትጣፍጥ፥ ጣፍጥ። ባትጣፍጥ? ድንጋይ ነው ብለው ጨው ለራስህ ብለህ ጣፍጥ፥ አለበለዙያ ድንጋይ ነው ብለው ይወረውሩሀል። ጨው ሲበዚ ያቅራል፤ በርበሬ ሲበዚ ይመራል። ጨው ሻጭ በገበያ፤ ጦር በሶማያ። ጨው ቢያልጥ በምን ይጣፍጣል? ዳኛ ቢደላ በማን ይሟገቷል። ጨው የላለው ምግብና ሰው የላለው ሰው አንድ ነው። ጨው ይወደኝ ብለህ ጣፍጥ፥ አለበለዙያ ግን ድንጋይ ነው ብለው ይጥሉሀል። ጨውተው ወይም አጫውተው። ጨውና በርበሬ፤ ጆሮና ወሬ። ጨ጑ራ ለመፍጨት፤ አንጀት ለመጎተት ብለው ዋተት ዋተት። ጨ጑ራና እግር ሳይሸት፤ ሽማግላና አሮጊት ሳይሸብት (እንዳት ይሆናል። ) ጩኸት ለሲላ፤ መብል ለአሞራ። (ለሲላ ~ ለቁራ) ጩሀ የማታውቅ ወፍ እርሟን ብትጮህ፥ ዕለቁ ዕለቁ። ጫማ ምንም ወርቅ ቢሆን፥ ከእግር በታች ነው። ጩኸት ለአሞራ፤ መብል ለቁራ። ጫማ የለንም ብለው የሚያጉረመርሙ፥ እግር የላላቸውን አይተው ይጽናኑ። ጫማ የለኝም ብለህ አት዗ን፤ እግር የላለው አለና። ጫማን፥ መደብ ላይ አያወጡም። ጫት ሳይቅሙ ምርቃና። ጫን ካለ፥ ጫን ይፈጃል። ጫን ያለው ኮርቻውን፤ ለምን ያለው ስልቻውን (አያጣውም)። ጫንቃዬን ተገርፌ፤ ጨርቄን ተገፍፌ። ጫጩትን አትቁጠር፥ አይሆኑም አጥር። ጭልፊትና ሲላ ተጋብተው ጉጉት ጭልፊትን የወደደ መንጠቅን የለመደ። ጭምት ሲሞት ልቡን፤ ንጉሥ ሲሞት ግንቡን። ጭምት ያበደ እንደሆን፤ የጤፍ ቆረን ደኑ። ጭምጭምታ፥ ክፉኛ ያስመታ። ጭራሮ፥ የምጣድ ጐረሮ። ጭራሮ~ ሰንበላጥ~ ብልኬት~ አስቤስቶስ ~ ኖራ የነገሩ ኹነኛ፤ የጦሩ አርበኛ። ጭሰኛ ከአለበት፥ እሳት አይጠፋም። ጭስ እጨሰበት፥ እሳት አይጠፋም። ጭስ ካለ፥ እሳት አለ። ጭቃን ማጠብ እንጂ፥ ማስለቀቅ አይቻልም። ጭቅጭቅ ነው፥ አቶ ጨረች ገዝተኹ ልበሱ። ጭብጥ ቆል ይ዗ህ፥ ተአሻሮ ተጠጋ። (ተአሻሮ ~ ከአሻሮ ~ ወደ አሻሮ) ጭብጥ ያዥ፤ ውርድ ነዥ። ጭነት ሽንብራ፤ በመቀንጠብ ያልቅ። ጭንቅ ሲመጣ የሚወደት ይቀር፤ ልጅ ሲመጣ ወላጅ ይቀር። ጭንቅ አልጋ ያስታቅፋል። ጭንቅ ያለመቃብር የለም። ጭንቅላትህ ከቅቤ የተሠራ ከሆነ፥ ዳቦ ጋጋሪ አትኹን። ጭድ ይዝ እሳት፤ ሳል ይዝ ስርቆት። ጭድ ይዝ ወ዗ት፤ ሳል ይዝ ስርቆት። ጭድና ጭቃ፥ ቡሀና ቦቃ። ጭጭ እንደ ጫጩት፥ እንደዝረው ጭልፊት። ጮሀ የማታውቅ ወፍ አንድ ቀን ብትጮህ፥ እለቁ እለቁ አለች። ጮላ ሲያረጅ፥ መጋዣ ይሆናል። ጮማ ሥጋ የበላችኹ፥ ጎመን ቅጠል የበላነ፥ ነሀሴን አብረን ትክክል ወጣነ። ጮማ በልቶ ከብስና፤ ጎመን በልቶ በጤና። ጳጉሜ ቢለግስ፥ ጎታህን አብስ። ጳጉሜ ቢወልስ፥ (ገበሬ) ጎተራህን አብስ። ጳጉሜን ሲወልስ ጎታህን አብስ፤ ጳጉሜን ብራ አህያህን አብላ። ጸልት በጽሞና፤ ነገር በደመና። ጸልት በፍቅር፤ ሃይማኖት በምግባር። ጸልት ከፍቅር፤ ሃይማኖት ከምግባር ይበጃል። ጸልት ከፍቅር፤ ሃይማኖት ከግብር። ጸልት ያለ ፍቅር፤ ሃይማኖት ያለ ግብር አይረባም። ጸደቅኩ ብዬ ባዝላት፥ ተንጠልጥላ ቀረች። ጸጉራም ውሻ፥ አለ ሲሉት ይሞታል። ጸጸት እያደር ይመሠረት። ጺም የላለው መምህር፤ አጸድ የላለው ደብር። ጻድቃን ሳይቀጣጠሩ ይገናኛሉ። ጻድቃን ሳይቀጣጠሩ ይገናኛሉ፥ ኀጥአን ግን በተቃጠሩበት ይተጣጣሉ። ጻድቅ ሰባት ጊዛ ቢወድቅ፥ ሰባት ጊዛ ይነሣል። ጻድቅ ተኩላ፥ የበግ ላት ይልሳል። ጽሕፈት በብራና፤ ዗ፈን በበገና። ጽኑ ወዳጅ፤ ጽኑ ጠላት ይሆናል። ጽዋ በተርታ፤ ሥጋ በገበታ። ጽዋውን የገለበጡ፤ ጋኑን የጨለጡ። ጽዳት ለምኔ፤ ቁናስ ባሕላ። ጽዳት ከራስ፤ ምሕረት ከመቅደስ (ይጀመራል)። ፀሓይ ሳለ ሩጥ፤ አባት ሳለ አጊጥ። ፀሓይ ሳለ ይሮጧል፤ አባት ሳለ ያጌጧል። ፀሓይ ብልጭ፤ ወፍ ጭጭ ሲል። ፀሓይ እያለች የአላስቀመጡት፥ ሲመሽ አያገኙትም። ፀሓይ እያለች፥ የመሸበት (አታድርገን)። ፀሓይ ከአልወጣ ከሰፈረበት አይነሣ አንበጣ፤ ሴት ምክንያት አታጣ። ፀሓይ የጠዋት፤ አደኛ የሽበት። ፀሓይ ያየውን፥ ሰው ሳያየው አይቀርም። ፀሓይና ንጉሥ ሳለ፥ ዅሉም አለ። ፀሓይና ጣውንት መልክ ያጠፋል። ፀሓይን በእጅ መከለል። ፈላ ገነፈለ፤ ተሞላ ጎደለ። ፈረሰኛ የወሰደው(ን)፥ እግረኛ አይመልሰው(ም) ፈረሰኛ ሲሮጥ፥ እግረኛን ምን አቆመው? ፈረሰኛ ሲሸሽ፥ እግረኛን ምን አመጣው? ፈረሰኛ ሲሸሽ፥ እግረኛ ምን ይቆማል? ፈረሱም ይኸው፤ ሜዳውም ይኸው። ፈረስ ለጦርነነት፤ በቅል ለጌትነት። ፈረስ መውጣት፥ የማያውቅ እጥፍ ይ዗ላል። ፈረስ ሲያጠብቅ፥ ል጑ም አይለቀቅ። ፈረስ በራሪ፤ በቅል ሰጋሪ። ፈረስ ቢያነክስ፤ አህያ ታጉዝ። ፈረስ ቢጠፋው፥ ኮርቻውን ገልቦ አየ። ፈረስ አውቃለኹ፤ ስገታ እወድቃለኹ። ፈረስ የጠፋው፥ ኮርቻ ገልብጦ አየ። ፈረስ ያደርሳል እንጂ፥ አይዋጋም። ፈረስ ጥል ይደነግጣል፤ በቅል ጥል ይረግጣል። ፈረስና ገብስ ያጣላል። ፈረንጆች እንደመርፌ ይገቡ፥ እንደ ዋርካ ይሰፉ። ፈሩ ፈሩ፥ ማጀት አሩ። ፈሪ ለሀገሩ። ፈሪ ለእናቱ። ፈሪ ለእናቱ ይገባል። ፈሪ ለእናቱ፤ ጀግና ለጀግንነቱ። ፈሪ ቢሸፍት፥ እስከ ጑ሮ። ፈሪ እንዳይሉኝ አንድ ገደልኹ፥ ጀግናም እንዳይሉኝ አልደገምኹ። ፈሪ፥ ከላይ ቢል፥ እኔ አለኹ አለ። ፈሪ ፈራና እጉድባ ቢኛ፥ ጆሮውን በላው ያይጥ ቀበኛ። (ቢኛ ~ ቢተኛ) ፈሪና ንፉግ እያደር ይቆጨዋል። ፈሪ፥ ለ዗መቻ መጣስ? ቀረስ? ( ምን ያጎድላል)። ፈሪ፥ በገዚ ጠቡ፥ ገላጋይ ይሆናል። ፈሪ፥ ከአልጋ ላይ ወድቆ ይሞታል። ፈሪ፥ ከአልጋ ላይ ይወድቃል። ፈሪ፥ ከውሃ ውስጥ ያልበዋል። ፈሪ፥ ውሃ ውስጥ ሆኖ ያልበዋል። ፈሪ፥ የሚያባርረው ሳይኖር ይሸሻል። ፈሪ፥ የእናቱ ልጅ ነው። ፈሪን ከውሃ ውስጥ ያልበዋል። (ከውሃ ~ ውሃ) ፈሪን የገዚ ጥላው ያሯሩጠዋል። ፈርተው ድንጋይ ሲጥሉ፥ ጅብ ወጣ ከደሩ። (ሲጥሉ ~ ቢወረውሩ ~ ቢጥሉ) ፈርቶ ድንጋይ ቢጥሉ፥ ጅብ ወጣ ከደር። ፈስ በወረንጦ እየተለቀመ ነው። ፈስ ያለበት ቂጥ፥ ዝላይ አይችልም። ፈስ ያለበት፥ ዝላይ አይችልም። ፈስቶ፥ ቂጥን መያዝ። ፈሷን ፈስታ፥ ቂጧን ጨበጠች። ፈቅደሽ ከተደፋሽ፥ ቢረግጡሽ አይክፋሽ። ፈትል ሲረዳዳ፥ አንበሳ ያስራል። (ያስራል ~ ያስቀራል) ፈትል ቢያብር፥ አንበሳ ያስር። (ያሥር ~ ያስራል) ፈንድሻ፥ ሲቆሉት ድምፅ፥ ሲበሉት ድምፅ። ፈክሮ መሸሽ፥ ታሪክ ያበላሻል። ፈዚዚ፥ እያንቀላፋ ይገባል ፈፋ። ፈጅቶ ከሚያጠግበኝ፥ እስኪበርድ ይራበኝ። ፈገግታ፥ የልብ አለኝታ። ፈጣሪን የሚያህል ጌታ፥ ርስትን ያህል ቦታ። (ርስትን ~ ገነትን) ፈጥነው የገመደት፥ ፈጥኖ ይበጠሳል። ፈጥኖ መስጠት፥ ቶል ለመጸጸት። ፈጭታ የነበረች፥ ላመልማል ኮራች። ፉት ቢሉ፥ ጭልጥ። ፈጥኖ መስጠት፥ ኋላ ለመጸጸት። (ለመጸጸት ~ ለማጣት) ፈጥኖ መስጠት፥ በኋላ መጸጸት። ፊተኛው ወዳጅህን፥ በምን ቀበርከው? በሻሽ፥ ኋለኛው እንዳይሸሽ። ፊት፥ በላህ ፍትፍት። ፊት ከወጣ ጆሮ፥ ኋላ የበቀለ ቀንድ በለጠ። ፊት ወዳጅህን በምን ቀበርከው? በሻሽ፥ የኋለኛው እንዳይሸሽ። ፊት የበሰለውን ወፍ ይበላው፤ ቀድሞ የተናገረውን ሰው ይጠላው። ፊት የተናገረን ሰው ይጠላው፤ ፊት የደረሰን ወፍ ይበላው። ፊት የወጣን ጆሮ፥ ኋላ የበቀለ ቀንድ በለጠው። ፊት የደረሰን ወፍ ይበላው፤ ፊት የተናገረን ሰው ይጠላው። ፊት ያልፈጁት፥ ነገር ያፋጃል። ፊት ያሞጠሙጧል፥ ኋላ ይስሟል። (ይስሟል ~ ይፏጯል) ፊት ጆሮ ይፈጠራል፥ ኋላ ቀንድ ይበቅላል። ፊት፥ አንቺ አንቺ፥ ኋላ እንቺ እንቺ። ፊት አይቶ የማያዳላ፥ መምህርና መካሪ። ፊደልን የአወቀ፥ ዅሉን አስለቀቀ። ፋሲል ሲፈርስ፥ ጎንደር ይታረስ። ፋሲካ የላለው ጦም፤ ደስታ የላለው አለም። ፋሲካን ሉያገኙ፥ ሐዳዳን ይመኙ። ፋቂ ቁርበቱን፤ አናጢ ዕንጨቱን። ፋኖ ቢሰማራ፥ ከጠላት ሉበላ። ፌቆ ስት዗ል፥ አትፈራ ገደል። ፌንጣ ብትቆጣ፥ (አንድ) እግሯን ታጣ። ፌንጣ ብትቆጣ፥ እግሯን ጥላ ኼደች። ፌንጣ፥ አቅሟን አታውቅ ትንጣጣ። ፍላጎት አይረግፍም፥ ካልከሰሙ እንደፍም። ፍልፈል ሳትጠረጥር፥ አጥር አትመነጥር። ፍረድ ለነፍስህ፤ ብላ ለከርስህ። ፍሪክና ጻድቅ አይቀጣጠርም። ፍሬ ለመብል፤ ሥንቅ ባገልግል። ፍሬ በመስጠቱ ባልታወቀ ሾላ፥ የወፎች ዝማሬ ቀደመ አሉ። ፍሬ ፍሬ ላይ ቆሞ፥ ጎተራ ይሞላል። ፍርሀቴ ለእናቴ አለች ጫጩት። ፍርሀት ሲመጣ፥ ዚቢያ ቆረጣ። ፍርሀት የናላ ነው፥ ከቁም ይጥላል። ፍርደ ገምዳይ፤ እውነት አጉዳይ። ፍርድ ለልጅ፤ ጥራቢ ለደጅ። (ጥራቢ ~ ጥራጊ) ፍርድ ለተቀማጭ፤ ወጥ ለቀላዋጭ። ፍርድ ልበስ የእኔ ጌታ፥ አሽከር አስነሣኝ ከገበታ። ፍርድ ሲ጑ደል፥ ድሀ ሲበደል። ፍርድ እንደ አሉላ፤ ጽድቅ እንደ ላሉበላ። ፍርድ ጎደለ፥ ድሀ ተበደለ የሚል ንጉሥ አይታጣ። ፍርድና ፍትፍት በየፊት። (በየፊት ~ ወደፊት) ፍቅር መያዣ የላለውን የሰውን ልብ ማሰሪያ ገመድ ነው። ፍቅር ሲጠና፥ ቆል ያ጑ርሣል። ፍቅር በደልን ዅሉ ይፍቃል። ፍቅር እንደሞት፥ ጽኑ ናት። ፍቅር ካለ፥ ቡጢ ራት ነው። ፍቅር ካለ፥ ዗ጠኝ ቂጣ ለባልና ሚስት ይበቃል። ፍቅር ካለ፥ የቁንጫ ቆዳ ለሦስት ሰው ይበቃል። ፍቅር ያመናቅር። ፍቅር ያሰከረው፥ ነግቶም ያገረሻል። ፍቅር ያስራል፤ ዕውቀት ያስከብራል፤ ጥበብ ያኮራል። ፍቅር ያስራል፤ ዕውቀት ያኮራል፤ ጥበብ ያስከብራል። ፍቅር ይታወቃል፥ በእግር። ፍቅር ፍቅር ሲሉ፥ ድሀ ሆነው ቀሩ። ፍቅርና ጉርሻ ከአላስጨነቀ አያምርም። ፍቅርና ጦር ይጥላል ከአጥር። ፍቅርን የአገኘ፥ ስምምነትን፥ ስምምነትን የአገኘ ድልን። ፍትፍቱን አሳይቶ፥ እበቱን አጎረሠኝ። ፍቅርህን የፈለገ ልጅህን፥ ጥልህን የፈለገ የላም ልጅህን። ፍቅርና ድን኱ን፥ የትም ይተከላል። ፍትፍት ለልጅ፤ ጥራጊ ለደጅ። ፍንክች ያባ ቢላዋ ልጅ። ፍንጥር ፍንጥር እንደ ሽንብራ፥ ያባ ምን ይዋብ ፉከራ። ፍየል ኹለት ወልዳ፥ አንደ ለመጽሀፍ፥ አንደ ለወናፍ። ፍየል ለአምስት፤ ድሮ ለባልና ለሚስት። ፍየል ልጅ እወልዳለኹ ብላ፥ ባል የሚሆናትን ወለደች። ፍየል መሀል ግመል። ፍየል መንታ ትወልድ፥ አንደ ለወናፍ፥ አንደ ለመጽሀፍ። ፍየል መንታ ወልዳ፥ አንደ ለመጽሀፍ፥ አንደ ለወናፍ። ፍየል ሲሰባ፥ ሾተል ይልሳል። ፍየል ሲቀናጣ፥ እናቱን ይሰርራል። ፍየል በልታ፥ በበግ አሳበበች። (አሳበበች ~ አበሰች) ፍየል በግርግር፥ እናቱን ይሰርር። (ይሰርር ~ ይሰርራል) ፍየል ብትመነኩስም፥ መቀነጣጠሷን አትተውም። ፍየል ከመድረሷ፥ ቅጠል መበጠሷ። ፍየል ከቀ዗ነ፤ ዱያቆን ከ዗ፈነ፥ አይድንም ይሞታል እየመነመነ። ፍየል ወዱህ፥ ቅዝምዝም ወዱያ። ፍየል ከቀ዗ነ፤ ዱያቆን ከ዗ፈነ። ፍየል የለኝ፥ ከነብር አልጣላ። ፍየል ፈጁን አውሬ፥ ፍየል አርደህ ያ዗ው። ፍየል(ም) የለኝ፥ ከነብር ምን አጣላኝ። ፍየልና ምን እየረገሙት ይረባል። ፍየልና ቀበሮ፤ ምጥማጥና ድሮ። ፍየልና የከተማ ሰው፥ ዝናብና ጭቃ አይወድም። ፍየሎን እንደበግ። ፍዳ ለኀጥአን፤ እሴት ለጻድቃን። ፍጥም አያናግር፤ የጎርፍ ሙላት አያሻግር። ፍጥም አፍራሽ፤ ቤተክርስቲያን ተ኱ሽ። ፍጥም ያቆማል፤ እርቅ ይጠቀልላል። ፍጥም ያዋውላል፤ አቧራ ያስላል። ፎክሮ መሸሽ፥ ታሪክ ያበላሽ። (ያበላሽ ~ ያበላሻል) ፖለቲካ በደቦ፤ ክብር በአግቦ። ፖለቲካና ኮረንቲን በሩቁ። ኱ስ ለራስሽ ስትይ ጎል ግቢ፥ አለዙያ ፎሪ ብለው ይጠልዙሻል። ኱ደሬ በንጉሥ፤ መበለት በቄስ መቅናት አይችልም። ዘላለም ከመፍሳት፥ አንዳ መቅ዗ን። ዘመነ ግርምቢጥ:_ ውሻ ወደ ሰርድ፥ አህያ ወደ ሉጥ። ዗መናይ ቅል ድንጋይ ይሰብራል። ዗መኔ፥ ከሸማኔ መወርወሪያ ይቸኩላል። ዗መን ሲበላሽ፥ አይጥ መጥረቢያ ይቆረጥማል። ዗መን እንደ ንጉሡ፤ አውድማ እንደ ንፋሱ። ዗መን የሚወልደውን፤ ንጉሥ የሚፈርደውን የሚያውቅ የለም። ዗መን የሚወልደውን፤ ንጉሥ የሚፈርደውን። ዘመን የሰጠው ቅል፥ ድንጋይ ይሰብራል። ዘመን የወለደው፤ ንጉሥ የወደደው። ዘመን ያነሣው ቅል፥ ድንጋይ ይሰብራል። ዘመን ያነሣው ታላቅ ዛማ፥ ዕንቅርት ያፈርጣል። ዗መደ ብዙ፥ ጠላሽ ቀጭን ነው። ዘመደ ብዙ፥ ጠላው ቀጭን ነው። ዗መደን የሚያማ፥ ገማ። ዗መደን ያማ፤ (ለ)ራሱ ገማ። ዗መደን ያማ፥ ገማ። ዗መድ ሲፈራ፤ ላሉበላ ሲኮራ። ዗መድ በየወንዙ ይርባ። ዗መድ በ዗መደ አይጨክንም ሆደ። ዗መድ ቢረዳዳ፥ ምን ችጋር ሉጎዳ? ዗መድ ቢረዳዳ፥ ችግርም ባልጎዳ። (ባልጎዳ ~ አይጎዳ) ዗መድ ከ዗መደ፤ አህያ ከአመደ። ዗መድ የላለው፥ ቁስል ይገድለዋል። ዗መድ ያረጀ፥ በልቶ ያፈጀ። ዗መድ፥ ሲጣላ ያረክሳል። ዗መድቿ ዅሉ ይሎታል፥ ግንድ አልብስ። ዗መድና መቃብር፤ ባዕድና መንገድ። ዗መድና መድኀኒት፥ በተቸገረ ቀን ይፈለጋል። ዗መድና መድኀኒት፥ በቸገረ ቀን ይፈለግ። ዗መድና መድኀኒት፥ የተቸገሩ ዕለት። (የተቸገሩ ~ የቸገረ) ዗መድና ሚዚን፥ ከወገብ ይይዚል። ዗መድና ሥዕል፥ በሩቁ ያምራል (ይባላል)። ዗መድና ሳንቲም ከመንገድ ወድቀው፥ ሳንቲሙን አነሱ ዗መድን ጥለው። ዗መድና እሳት በሩቅ። ዗መድና ዋንጫ እያለቀሰ ይመጣ። ዗መድና ገን዗ብ ሳያስቡት ይገኛል። ዗መድና ፍየል ቤት አጥፊ ነው። ዗መድን ከ዗መድ ጋር ማማት፥ ዳቦ እንደመግመጥ ነው። ዗መድን ከ዗መድ ጋር ማማት፥ ጮማ እንደመቁረጥ ይቆጠራል። ዗መድን የሚወጉበት ጦር፥ ጀንፎው አይለቀቅም። ዗ማ ብታረጅ፥ አማጭ ትሆናለች። ዗ማች ለባልንጀራው እኔ የገደልኹት ደም አልወጣውም ቢለው፥ ቤት ሠሪውን ገድለህ ይሆናል አለው ይባላል። ዗ምቶ ከአረጀ፤ በልቶ ከአፈጀ። ዗ምቶ ያረጀ፥ በልቶ ያፈጀ። ዗ረፋና ቀን ከአልተሻሙበት ያልቃል። ዗ሪው ጣቴ፤ ምድሩ የአባቴ። ዗ር ልትበደር ኺዳ፥ እህል ሲሸት መጣች። ዗ር ልትበደር ኼዳ፥ መኸር ሲደርስ መጣች። ዗ር ከል጑ም ይስባል። (ይስባል ~ ይጠቅሳል) ዗ር ከበረከት፤ ትውልድ ከምርቃት። ዗ር የጣቴ፤ ምድሩ የአባቴ። ዗ርቶ መቃም፤ ወልድ መሳም። ዗ርቶ አይቅም፤ ወልድ አይስም። ዗ርቶ ያልበላ፤ አምላክን ጠላ። ዗ቅዝቀው ቢቀብሩት፥ ቀና ብል አደገ። ዗ባራቂ፥ ላባ ቀረሽ፥ እብድ አስተኔ። ዗ባራቂ፥ ይወዳል ምራቂ። ዗ንድ ለሆደ ሲል፥ በሆደ ይኼዳል። ዗ንድ ከባሕር ላይ ተኝቶ፥ ጤዚ ይልሳል። ዗ንድ፥ የዳገት በረድ። ዗ንጋዳ ተቆረጡት አገዳ፤ እዳኛ ከደረሱ ዕዳ። ዗ንጋዳ ከቆረጡት አገዳ፥ ሚስት ከፈቷት ባዳ። ዗ንጋዳ የገለበጠ፤ አባቱን የገላመጠ። ዗ንጋዳና ወታደር በመከር ጊዛ ይታይ ነበር። ዗ንግ ከተተከለ፥ ልብ ተከፈለ። ዗ኬውን ሲቋጥር፥ አነቀው ነብር። (ተማሪ ~) ዗ወትር ዋይ ዋይ ጐረሮ ያሰለቻል። ዗ገየች ከረመች፥ ቆይታ መጣች። ዗ጠኝ ሞት መጣ ቢለው፥ አንደን ግባ በለው (አለው)። (አለው ~ አለ) ዗ጠኝ ቦላላ ፈስ አያድንም። ዗ጠኝ ድሀ ዗መድ ያለው፥ በዓመቱ እርሱ አሥረኛ ይሆናል። ዗ጠኝ ጠጥቶ፤ አሥረኛውን የወደደ በሙሉ ነደደ። ዗ጠኝ ጠጥቶ፤ አሥር የወደደ በሙሉ ተናደ። (በሙሉ ~ ዗ጠኙ) ዗ጠኝ ፈሳም ጎማ አይነፋም። ዗ጠኝም ቢታለብ፥ ለእኔ ያው ገላ ነው። ዗ጥ ጥ፤ አቁማዳ ቂጥ። ዗ፈን ለገና፤ ነገር ለዋና። ዗ፈን በበገና፤ ነገር በዋና። ዗ፈን በከበሮ፤ አዋጅ በደበል። ዗ፈን በገና፤ ነገር በዋና። ዗ፈን አለ በገና፤ ነገር አለ በዋና። ዗ፍኖ አያምር፥ እን኱ን አልቅሶ። ዗ፍኖ ያልዳረ፤ አልቅሶ ያልቀበረ ዗መድ አይባልም። ዙሮ በላን፥ ተኝተህ ቀላውጠው። ጑ሳና ድንግል፥ ያላንድ ጊዛ አይበቅል። ጑ዞን ትጠብቃለች። አንድ አይና፥ በአፈር አይጫወትም። ጑ያ ነቃይ፥ የፊት የፊቱን። ጑ደኛህ ሲታማ፥ ለእኔ ብለህ ስማ።