|
Proverb,Description |
|
ለለአሐዱ በከመ ምግባሩ።,ለእያንዳንዱ እንደሥራው፡፡ |
|
ለሰብእ ጸሩ ሰብአ ቤቱ፡፡,የሰው ጠላቱ፣ ቤተሰቡ |
|
ለዘቦ ይሁብዎ፤ ወይዌስክዎ፤ ወለዘለ አልቦ አለሂ ቦ የህይድዎ፡፡,ላለው ይለጡታል፣ ይጨምሩለታልም፡፡ የሌለውን ግን ያለውንም እንኳን ይነጥቁታል፡፡ |
|
አኮ በሲበት አላ በአእምሮ,በሽበት አይደለም፤ በማስተዋል ነው እንጅ። |
|
መጥወኒ እመጥወ,ስጠኝ እስጥህለሁ |
|
ምዉት የሀውር ሀበ ምዉት,ሙት ወደ ሙት ይሄዳል |
|
ወእመ ሖርከ ብሔረ ባዕድ ኩን ከማሆሙ,ሌላ አገር ብትሔድ፤ እንደነሱው ሁን |
|
ዘበልዐ በአቅም የሀድር በሰላም,በልኩ የበላ ስላማዊ ዕንቅልፍ ይተኛል |
|
ሀቡ ዘነጋሚ ለነጋሚ፤ ወዘእግዚአብሔር ለእግዜአብሔር,የቂሳርን ለቁሳር፤ የእግኢአብሔርን ለአግዚአብሔር ስጡ |
|
ሀብ ለኩሉ ለዘሰአለክ,ለለመነህ ሁሉ ስጥ |
|
ህብ ፍኖተከ ለእግዚአብሔር,መንገድህን ለእግዚአብሔር አደራ ሰጥ |
|
ሃይማኖት እንተ አልባቲ ምግባረ ሠናይ ምውት ይእቲ,በጎ ሥራ ያልተሠራባት ፃይማኖት የሞተች ናት |
|
ህየንተ አበውኪ ተወልዱ ለኪ ደቂቅ,በአባቶችሽ ፋንታ ልጆች ተተኩልሽ |
|
ለልላነ አጓለእመሕያውሰ አልቦ ዘይክል አግርሮታ,ምላስ ይተባል፤ ጥርስ ይወጋል |
|
ለሰሚዕ እጹብ,ለሰሚው አስደናቂ |
|
ለስሒት መኑ ይሴብዋ,ስህተትን ማን ያስተውላታል |
|
ለእመ ረክብከ ሰብአ በፍኖት ኢትጻባሕ፤ ወለእመ ተጻብሐክ ኢታውስኦ,በመንገድ ካገኘኸው ጋራ አትጣላ እሱ ነገር ቢፈልግህም አትመልስለት |
|
ለአመ ብከ ህብ ወለእመ አልብከ ኀሊ,ካለህ ስጥ ከሌለህ እዘን |
|
ለእመ ብከ ጥበብ ጸሐፍ,ዕውቀት ካለህ ጻፍ |
|
ለወሀቤ ዝናም ማየ ከልእዎም,ለዝናብ ጌታ ውሃ ነሱት |
|
ለውሂብ ኢትጉጔእ ወውሂበከ ኢትናፍቅ,ለመስጠት አትቸኩል፤ ሰጥተህም አትጸጸት |
|
ለዘመጽአ በለላም በዝ አባርኮ ወለዘመጽአ በኀኬት በዝ እዘተርኮ,በለላም የመጣውን በዚህ እባርከዋለሁ፤ በክፋት የመጣውን በዚህ እዘተርከዋለሁ |
|
ዘመጽአ ኀቤየ ኢይሰድዶ፤ ወኢያወጽኦ አፍአ,ወደኔ የመጣውን ወደ ውጭ አላወጣውም |
|
ዘቦ ይሁብዎ፤ ወይዌስክዎ፤ ወለዘለ አልቦ አለሂ ቦ የህይድዎ፡,ላለው ይለጡታል፣ ይጨምሩለታልም፡፡ የሌለውን ግን ያለውንም እንኳን ይነጥቁታል |
|
ለዘኢይሰቲ ወይነ ምንት ውእቱ ሕይወቱ,ወይን የማይጠጣ ሰው ምን ሕይወት አሰው? |
|
ለዘየአምን ኩሉ ይትከሃል,ለሚያምን ሁሉ ይቻላል |
|
ለጠቢብሰ አሃቲ ቃል ትበቁእ,ላሰተዋይ ሰው አንድ ቃል ይበቃዋል |
|
ልሳነ እጓለ እመህያው ሐጽ ወኩናት,የሰው አፍ እንደ ተሳለ ጦር ነው |
|
ልደትሰ በኩሉ ልደት ጸውኡኒ በካልእ ዕለት,የልደት ድግስ በሁሉም ነው፤ ሌላ ቀን ጥሩኝ |
|
ሎቱ ስብሐት,ምስጋና ለርሱ ይሁን |
|
ሐለሙ ሕልመ ወአልቦ ዘረከቡ,ሕልም አለሙ፣ ያገኙት ነገር ግን የለም |
|
ሐንካስ በአግረ ዕውር ሖረ! ዕውርኒ በዐይነ ሐነካስ ነጸረ ወበክልዔሆሙ ወይንየ ተመዝበረ,አንካሳ በዕውሩ አግር ሄደ፤ ዕውሩም በአንካሳው ዐይን አየ፤ በሁለቱም አታከልቴ ተመዘበረ |
|
ሕሙማን ይፈቅድዎ ለዐቃቤ ሥራይ ወአኮ ጥዑያን,ባለመድኃኒቱን በሽተኞች ይፈልጉታል ጤነኞች አይሹትም፡ |
|
ሕማማ ለዐይን ርዕየተ ጸላኢ,ያይን በሽታዋ፣ ጠላትን ማየቷ |
|
ሕንጻ ወውሉድ ያዐብዩ ስመ,ግንብና (ሕንጻ) ልጅ፤ ስምን ያስጠራሉ |
|
ሕያዋን ይስእሉ ለሙታን፤ ሙታን ይስአሉ ለሕያዋን,ያሉት ለሞቱት ይጸልያሉ፤ የሞቱት ያሉትን ያስባሉ፡፡ |
|
ሕይወት ወሞት ውስተ እደ ልሳን,ህይወትም ሞትም በአፍ ይመጣሉ |
|
መምህራነ ኮኑ በበደወሉ፤ ፊደላተ በሆለቆ ኩሉ,ፊደል የቆጠሩ ሁሉ፤ በያካባቢው አስተማሪዎች ሆኑ |
|
መምህር ወመገሥጽ ዘኢያደሉ ለገጽ,ፊት አይቶ የማያዳላ መምርና መካሪ |
|
መሠረተ ሕይወት ማርያም ወጥንተ መድኃኒት ዘእምቀዲሙ,የሕይወት መሠረትና የድኅነት መገኛ ማርያም ናት |
|
መስዋዕቱ ለእግቢአቢሔር መንፈስ የዋህ,የእግዚአብሔር መስዋዕቱ ቅን መንፈስ ነው |
|
መስገርትስ ተቀጥቀጠት ወንህነስ ድኅነ,ወጥመድ ተሠበረች፤ እኛ ግን አመለጥን |
|
መኑ ከመ አምላከነ?,እንደ እግዚአብሕር ያላ ማን አለ? |
|
መኑ ዘደመሮ ለብርሃን ምስለ ጽልመት?,ብርሃን ከጨለማ ጋር ምን ኅብረት አለው? |
|
መኑ የአቁር እሳተ ውስተ ኅጽኑ?,እሳትን በጭኑ ማን ይሸከማል? |
|
መንግሥት እንተ ትትናፈቅ በበይናቲሃ ኢተጸንእ,እርስ በርሷ የምትለያይ መንግሥት አትጸናም |
|
መዐር ኢይጥዕሞ ለአድግ,ለአህያ ማር አይጥማትም |
|
መዓተ ንጉሥ ከመ መልአክ ሞት,የንጉሥ ቁጣ፣፤ የመልአከ ሞት ያህል ያሰፈራል |
|
መጋቢ እንበለ ሊሳይ፤ ጸባቲ እንበለ ማይ,ያለ ምግብ መጋቢ የለ ውሃ ዋናተኛ |
|
መጠኑ ለረድእ በከመ ሊቁ፡፡,የተማሪ ደረጃው (ከብሩ) እንደ መምሩ ነው፡፡ |
|
መጥወኒ አመጥወከ፡፡,ስጠኝ አለጥህለሁ |
|
ማኅቶቱ ለሥጋክ ዐይንክ ውእቱ,የሥጋህ መብራት ዐይንህ ነው። |
|
ማዕረሩ ብዙኅ ወገባሩ ህዳጥ,መኸሩ ብዙ ሠራተኛው ጥቂት፡፡ |
|
ማይ ብዙኅ ኢይክል አጥፍአታ ለፊቅር፡፡,ብዙ ውሃ ፍቅርን አያጠፋትም |
|
ምሉዕ በኩለሄ,በሁሉ የተሟላ |
|
ምሕረተ እፈቅድ ወአኮ መስዋዕተ,ምሕረትን እወዳለሁ፤ መስዋዕትን አይደለም። |
|
ምንት ብክ ዘኢነሳእከ እም ካልዕከ?,ከስው ያልወስድከው ምን አለህ? |
|
ምንዳቤያትሰ ኢኮና ርሁቃተ እምኔከ፤ አላ ይነቅአ እምታህተ እገሪከ፡,ችግሮችህ ሩቆች አይደሉም፤ ከአንተው ከራስህ ይመነጫሉ አእንጅ።፡ |
|
ምክር ሠናይት ለኩሉ ዘይገብራ።,ለሚተገብራት፤ ምከር መልካም ናት |
|
ሞቱ ሰኃጥኣ ጸዋግ,የኃጢአተኛ አሟሟት የከፋ ነው |
|
ሞታ ለነፍስ ርቅ እም አግዚብሔር፡፡,የነፍስ ሞቷ፤ ከእግዚአብሔር መራቋ |
|
ምውት የሐውር ኀበ ምውት፡,ሙት፣ ወደ ሙት ይሄዳል፡፡ |
|
ምኩራብ አነመት ፀምረ፤ ወቤተ ክርሰቲያን ተአጽፈቶ፡፡,ምኩራብ ግምጃ ፈተለች፤ ቤተክርስቲያን ለበሰችው፡፡ |
|
ሠናይ ለብእሲ መቅበርቱ ለእመ ኮነ በውስተ ርስቱ፡፡,የሰው መቃብሩ፣፤ በአገሩ ቢሆን መልካም ነው፡ |
|
ሠናይ ብእሲ ያወጽኣ ለሠናይት፣ እም ሠናይት መዝገበ ልቡ፡፡,በጎ ሰው ከበጎ ልቡ በጎ ነገርን ያወጣል፡ |
|
ሠናይ እገሪሆሙ ለአለ ይዜንዉ ሠናየ ዜና፡፡,መልካም ዚና የሚነግሩ አብሣሪዎች፣ እግሮቻቸው ያማሩ ናቸው፡፡ |
|
ሣህል ወርትዕ ተራከባ፤ ጽድቅ ወሰላም ተሰዐማ።,ቅንነትና ይቅርታ ተገናኙ እውነትና ሰላም ተሰማሙ |
|
ሥርዉ ለኩሉ እኩይ፣፤ አፍቅሮ ንዋይ፡,የክፉ ተግባር ሁሉ ሥሩ የገንዘብ ፍቅር ነው፡፡ |
|
ሥጋ ትሄይላ ለነፍስ፤ በከዊነ ማኅደር፡፡,ማደሪያ በመሆኗ፤ ሥጋ ነፍስን ትጨቁናታለች |
|
ርቱዕ አበው ይዝግቡ ለውሉዶሙ፤ ወአኮ ውሉድ ለአዝማዲሆሙ,ወላጆች ለልጆች እንጅ፤ ልጆች ለወላጆች ሀብት ሊያከማቹ አይችሉም |
|
ርኅቀተ ሀገር፤ ኢይከልኣ ለፍቅር፡፡,የሀገር ርቀት፣ ፍቅርን አያስቀራት |
|
ሰላም ለላም ለሰራቄ ቅኔ ናሁዳ፤ ዳር ዳሩን ኮርኩሞ፣ መሀሉን ሳይጎዳ፡,ቀነጣጥቦ ለሚሰርቅ የቅኔ ሌባ ሰላም ይሁን |
|
ሰብአ ቤቱ ይጻረሮ ለለብእ,ሰውን የገንዛ ቤተሰቡ ይቃወመዋል፡፡ |
|
ሰብአሰ ገጸ ይሬኢ፤ ወእግዚአብሔርሰ ልበ ይሬኢ፡፡,ሰው ፊትን እግዚአብሔር ግን ልብን ያያል፡፡ |
|
ሰብእ አልብየ,ለው የለኝም፡፡ |
|
ሰብእ ወጣኒ፤ እግዚአብሔር ፈጻሚ,ሰው ይጀምራል፣ እግዚአብሔር ይፈጽማል፡ |
|
ሰብእ ይሠምር በዘይጌይሶ ለሥጋሁ።,ሰው ሰሥጋው የሚጠቅመውን ይወዳል፡፡ |
|
ሰብእ ይቄድሶ ሰመካን፤ መካን ይቄድሶ ለሰብእ፡፡,ሰው ቦታን ያሰከብረዋል፤ ቦታም ሰውን ያሰከብረዋል፡፡ |
|
ሰብእ ይከብር በእንተ ልብሱ፡፡,ሰው በልብሉ ይከበራል፡፡ |
|
ሰንበት ተዐቢ እምኩሉ ዕለት፤ ወሰብእ ይከብር እም ዙሉ ፍጥረት፡፡,ሰንበት ከዕሰታት፣ ሰው ከፍጥረታት፣ ሁሉ ይበልጣሉ፡ |
|
ሰአሉ ወይትወህበክሙ፤ ኅሥሠ ወትረክቡ፤ ጐድኮጐዱ ወያርህዉ ለክሙ፡፡,ለምኑ ይሰጣችኋል፤ ፈልጉ ታገኛላችሁ፤ እንኳኩ ይከፈትላችቷል፡፡ |
|
ሰይፍ ዘክልዔ አፉሁ፡,ሁሰት አፍ፤ ያለው ሠይፍ፡፡ |
|
ሲሲታ ስነፍስ ቃሰ እግዚአብሔር፡፡,የነፍስ ምግቧ የእግዚአብሔር ቃል ነው፡፡ |
|
ስማዕ ወልድየ ሕገ አቡከ,ልጄ ሆይ! ያባትህን ትእዛዝ ስማ፡ |
|
ስብሐት ለእግዚአብሔር!,እግዚአብሔር ይመስገን! |
|
ስብዓ ይወድቅ ጻድቅ ወይትነሣአእ፡,ጻድቅ ሰባት ጌዜ ቢወድቅ ሰባት ጌዜ ይነሣል፡፡ |
|
ሰታይ ወአንስት ያስሕታሆሙ ለመምህራን፡፡,መጠጥና ሴቶች መምህራንን ያስቷቸዋል፡፡ |
|
ሶበ ተሐውር ምስስ ፅድውከ ኅበ መልአክ ተዐረቅ በፍኖት,ወደ ዳኛ በምትሄድበት ገዜ፣ በመንገድ ሳለህ ከባላጋራህ ጋር ታረቅ |
|
ሶበ ትረክቦ ኃጢአቱ ይጸልኣ፡,ጥፋቱን ሲያውቃት ይሰቀቃታል፡፡ |
|
ሶበ ኢያሥራሕክምዋ ሰእጐልትየ እም ኢረከብክምዋ ሰአምሳልየ፡፡,በጥጃዬ ባላረሳችሁ፤ የእንቁቅልሼን ፍች ባላወቃችሁ፡ |
|
ቀዳሚሃ ለጥበብ ፈሪሃ አግዚአብሔር,የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው፡፡ |
|
ቀዳሜ ሕይወቱ ሰሰብእ እክል ወማይ፣፤ ወይን ወሥርናይ,እህልና ውሃ ወይንና ስንዴ ለሰው ሕይወት፣ መሠረት ናቸው፡፡ |
|
ቀጥቅጥ መዝራዕቶ ሰኃጥእ ወሰእኩይ፡፡,ክፉና ተንኮለኛን ሰው ድቅቅ ስብርብር ማድረግ ነው፡፡ |
|
ቃለ መዋቲ ጽንዕት ይኣቲ፡፡,የሙት ቃል አይሻርም፡፡ |
|
ቅኑተ ይኩን ሃቁየክሙ ወኅትወ መኀትዊክሙ።፡,ትጥቃችሁ የጠበቀ መብራታችሁ የበራ ይሁን። |
|
ቅድመ አውጽእ ሠርዌ እም ዐይንክ,በመጀመሪያ ባንተ ዐይን ያለውን ግንድ አውጣ፡፡ |
|
ቅድመ ይባኡ ውስተ ኅርየት ይምሃርዎሙ ቃለ ሃይማኖት፡,ከመሾማቸው በፊት የሃይማኖትን ቃል ያስተምሯቸው |
|
በስሐቅ ወበስላቅ ይበውእ ጸላኤ ሠናያት፡፡,ክፉ መንፈስ በሳቅ በስላቅ ይገባል |
|
በሳምናዊት ዘመን ትሴኮስ ፍቅር፡፡,በስምንተኛው ሽህ ፍቅር ትቀዘቅዛለች፡፡ |
|
በስምዐ ክልዔቱ ወሠለስቱ ይቀውም ኩሉ ነገር፡፡,ነገር ሁሉ በሁለትና በሦስት ምሥክሮች ይጸናል።፡ |
|
በቀዳሚ ጉየይ፤ ወበካልዕ ጉየይ፤ ወበሳልስ ተንሥእ ወተቃተል፡፡,በመጀመሪያውና በሁለተኛው ሽሽ፣ በሶስተኛው ግን ተነስተህ ተፋለም |
|
በብዙኅ ጻማ ሀሰወነ ንባእ ውስተ መንግሥተ እግዚአብሔር፡፡,ወደ እግዚአብሔር መንግሥት፣ በብዙ ድካም እንገባለን |
|
በትዕግስትክሙ ታጠርይዋ ለነፍስክሙ፡፡,በመታገሳችሁ ነፍሳችሁን ታድናላችሁ፡፡ |
|
በአርምሞ ይመስል ጠቢብ፡፡,ዝም በማለቱ ብልህ ይመስላል፡፡ |
|
በአይቴ ኀሊፈኪ ድጓ ተምሂረኪ?,በየት አልፈሽ ድጓ ተማርሽ? |
|
በከንቱ ዘነሳእክሙ ሀቡ በከንቱ፡፡,ያለ ዋጋ የተቀበላችሁትን ያስ ዋጋ ስጡ፡ |
|
በዘሠፈርክሙ ሎሙ ይሠፍሩ ለክሙ፡፡,በሰጣችኋቸው ልክ ይስጧችኋል። |
|
በዝ ግብርኪ፣ ተገደፍኪ፡፡,በዚህ ሥራሽ፤ ወጥተሽ ወደቅሽ፡፡ |
|
በጽባሕ ዘተናገረ ኢይደግም በሠርክ፡፡,ጧት የተናገረውን ማታ አያስታውሰውም፡ |
|
በሞተ ዚአሁ ሀዮነ ቁስለነ፡፡,በርሱ ሞት እኛ ተፈወስን፡፡ |
|
ቢጽ ለቢጹ ይትራድዖ፡,ጓደኛ ጓደኛውን ይረዳዋል |
|
ቢጽ ምስለ ቢጹ።,ጓደኛ ከጓደኛው፡፡ |
|
ባኡ እንተ ጸባብ አንቀጽ፡፡,በጠበበው በር ግቡ፡፡ |
|
ቤዛ ነፍሉ ለሰብእ ጥሪተ ብዕሉ,ሃብት ለሰው ቤዛው ነው |
|
ብላዕ በሐፈ ገጽከ,ጥረህ ግረህ ብላ |
|
ብእሲ ማእምር ኀዘን ለነፍሱ,አስተዋይ ሰው ያዝንበት እያጣም |
|
ብአሲት አዛል (አዚዝ) አክሊል ለምታ,መልካም ሴት ለባሏ ዘውድ ናት |
|
ብእሲ እኩይ የኃብል አእርክተ,ክፉ.ሰው በነገር ሥራ ወዳጆችን ይለያያል |
|
ብእሲ ወብእሲት እሐዱ አካል እሙንቱ,ባልና ሚስት አንድ ከካል ናቸው |
|
ብእሲ ጠዋይ ይልዕክ እከየ,ጠማማ ለው ክፋትን ከሁሉ ያደርሳል |
|
ብዙኃን መኳንንት እለ ወድቁ ውስተ ምድር ወቦ ባሕታዊ ዘተቄጸለ አክሊለ,በዚህ ዓለም በመከራ የወደቁ ባለሥልጣኖች ብዙ ናቸው! ዘውድ የተቀዳጀ ባሕታዊም አለ |
|
ብዙኃን አለ ወድቁ በሐጺን ወአኮ ከመ እለ ወድቁ በልሳን,በጦር ተደብድበው የወደቁ ብዙዎች ናቸው፤ ነገር ግን በነገረ ሠሪ አንደበት እንደጠፉት አይሆኑም |
|
ብዙኃን ይመውኡ,ብዙዎች ያሸንፋሉ |
|
ብዙኃን ጽዉኣን፤ ወኅዳጣን ኅሩያን,የተጠሩ ብዙዎች፤ የተመረጡ ግን ጥቂቶች ናቸው።፡ |
|
ብየ ሥልጣን ላዕለ ኩሉ ዘኮነ ወአኮ ዙሉ ዘይበቁዓኒ,ሁሉ ተፈቅዶልኛል፤ ሁሉ ግን አይጠቅመኝም |
|
ብፁዓት መካናት ዘኢወለዳ,ያልወለዱ ብፁዓት ናቸው |
|
ብፁዓን ገባርያነ ሰሳም,የሚያስታርቁ ብፁዓን ናቸው |
|
ብፁፅ ዘይሁብ አም ዘይነስእ,ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ በፁዕ ነው |
|
ብፁዕ ዘይደበድባ ለከርሱ,ሰውነቱን የሚንከባከባት ብፁዕ ነው |
|
ቦ እለ ተሐርዩ እምከርሠ እሞሙ፡,ከናታቸው ማህጸን ጀምሮ የተመረጡ አሉ |
|
ቦ ጊዜ ለዙሉ,ለሁሉም ጊዜ አለው |
|
ተልዒልየ ተትህትኩ፤ ወተመነንኩ፡,ተከብሬ ሳበቃ ተዋረድኩ |
|
ተሰአሎ ለአቡከ ይነግረከ፤ ወለሊቃውንቲከ ይዜንዉከ,አባትህን ጠይቀው ይነግርሃል |
|
ተበአስ በአንተ ጽድቅ እስክ ለሞት,ለአውነት እስከ ሞት ድረስ ተጋደል |
|
ተንተንኩ ለወዲቅ፤ ወእግዚአብሔር አንሥአኒ,ልወድቅ ተንገዳገድኩ፤ እግዚአብሔር ግን አነሣኝ |
|
ተአምሑ በበይናቲከሙ በአምሐ ቅድሳት,በተቀደሰ ስላምታ እጅ ተነሳሱ |
|
ተዓቀብ አምጸላእትከ አሐደ ጊዜ ወተኣቀብ እም ፍቁርክ ፲፻ ጊዜያተ,ከጠላትህ አንድ ጊዜ፣ ከወዳጅህ ሽህ ጊዜ ተጠንቀቅ |
|
ተዘከሩ መኳንንቲክሙ፣ ዘነገሩከሙ ቃለ እግዚአብሔር,የእግዚአብሔርን ቃል የነገሯችሁን፤ አስተማሪዎቻችሁን አስታውሱ |
|
ተገሃሥ እም እኩይ፤ ወግበር ሠናየ,ከክፋት ራቅ፤ መልካምንም አድርግ |
|
ተፋቀሩ በበይናቲከሙ,እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ |
|
ተፋቅሮሰ ፍጹም ሕግ,ፍቅር የሕግ ፍጻሜ ነው |
|
ትበልዒ ወኢትጸግቢ,ትበያለሽ ግን አትጠግቢም |
|
ትንቢት ይቀድሞ ለነገር,ድርጊትን ትንቢት ይቀድመዋል |
|
ትእቢትሰ ጸሩ ስሰክርስቶስ,ትቢተኛ የክርስቶሰ ጠሳት ነው |
|
ትውልደ ጻድቃን ይትባረኩ,የደጋግ ሰዎች ልጆች ይባረካሉ |
|
ኅላፊ ንብረት፣ ክመ ጽላሎት,ሀብት እንደ ጥላ አላፊ ነው |
|
ኀበ ሀሎ መዝገብክሙ ሀየ ይሄሉ ልብክሙ,ሀብታችሁ ባለበት ልባችሁም ይገኛል |
|
ኀበ ሀሎ ገደላ ሀየ ይትጋብኡ አንሰርት,ጥንብ ባስበት አሞሮች ይሰበሰባሉ |
|
ሃዘን ለአብዳን፤ ወፍስሐ ለጠቢባን,ሀዘን ለሰነፎች፣ ደስታ ለብልሆች |
|
ኀጺን ለነጺን ይትባልሁ,ብረት ብረትን ይስስዋል |
|
ኃይሉ ስስብእ በአምጣነ ቆሙ,የስው ኃይሉ በቁመቱ ልክ |
|
ኅዳጣን ይትጌበሩ፤ ወብዙኃን የዐርሩ,ጥቂቶች ይሠራሉ፤ ብዙዎች ይስበስባሉ |
|
ኅድጉ አበሳ ቢጽክሙ,የወንድማችሁን በደል ተዉለት |
|
ኅድጋ ለመዓት ወግድፋ ለቁጥዓ,ብስጭትን ተዋት፤ ቁጣንም ጣላት |
|
ኅድግዎሙ ለሕጻናት ይምጽኡ ኀቤየ,ሕጻናትን ተዉአቸው ወደኔ ይምጡ |
|
ኀድግዎሙጮ ለምጢዉታን፤ ይቅብሩ ምዉታኒሆሙ,ሙታንን ተዉአቸው፤ ሙታኖቻቸውን ይቅበሩ |
|
ነባህነ ነባህነ ከመ ዘኢነባህነ ኮነ,ጮህን ጮህን አንዳልጮህን ሆን |
|
ነገሥት ያፈቅሩ ጽልሕዋነ ወመደልዋነ,ገዥዎች ግብዞችንና ሸንጋዮችን ይወዳሉ። |
|
ነገረ አማጽያን ኃየለነ,የነገረኞች ወሬ በጠበጠን |
|
ነገረ ዘርቅ,ተራ ወሬ አሉባልታ |
|
ነፍስ ርኅብት መሪርኒ ጥዑመ ያስተርእያ,የተራበች ነፍስ መራራው ሁሉ ጣፋጭ ይመሰላታል። |
|
ነፍስየ ትጻእ ምስለ ኢሎፍላውያን፡,ከኢሎፍኣውያን ጋር ነፍሴ ትውጣ |
|
ነፍስ ጽግብት ጸቃውዓ መዓር ትሜንን,የጠገበች ነፍስ የማር ወለሳ ትረግጣስች |
|
ናሁ ሠናይ ወናሁ አዳም ሶበ ይፄልዉ አኃው ኅቡረ,እነሆ ወንድሞች ተባብረው ሲኖሩ መልካም ነው |
|
ንሕነ ነአምር ግብሮን ለቆራብት,የቆራቢዎችን ተግባር እኛ እናውቃለን |
|
ንሥኣ ወብልዓ ለአእንታከቲ መጽሐፍ,አንካ ይችን መጽሐፍ ብላት |
|
ንቃህ መዋቲ,የተኛህ ንቃ |
|
ንባብ ይቀትል፤ ወትርጓሜ ያሐዩ፡,ንባብ ይገላል፤ ትርጓሜ ያድናል |
|
ንነግርሂ ወኢንዘብጥ,እንናገራለን እንጅ እንማታም። |
|
ንዋይ ከመ እግዜኡ,ገንዘብ እንደጌታው ነው |
|
ንዋይከ በቅድሜከ፡፡,ገንዘብህን ከፊትህ አትለይ፡፡ |
|
ንግባአኬ ኀበ ጥንተ ነገር፡፡,ወደ ቀደመው ነገር አንመለሰ፡፡ |
|
አልቦ በቁዔት በከሲተ ኅሊናየ,የልቤን ብናገር ጥቅም የለውም፡፡ |
|
አልቦ ክዱን ዞኢይትከለት፤ ወአልቦ ኅቡእዕ ዘኢያስተርኢ,የማይገለጥ ሽሸግ የማይታይ ሥውር የለም፡፡ |
|
አልቦ ዘያበርህ ማኅቶተ ከመ ያንብራ ታህተ ከፈር፡፡,መብራት አብርቶ እንቅብ የሚደፋባት የለም፡፡ |
|
አልቦ ዘይእህዝ እርፈ ወየሐርስ ድኅሪተ፡፡,እርፍ ይዞ ወደ ኋላ የሚያርስ የለም: |
|
አልቦ ገብር ዘየዐቢ እም እግዚኡ፤ ወአልቦ ረድእ ዘየዐቢ እም ሊቁ፡,ከጌታው የሚበልጥ አገልጋይ፤ ከመምሩ የሚበልጥ ተማሪ የለም፡፡ |
|
አልቦ ገብር ዘይክል ተቀንዮ ለከልዔ አጋአእዝት፡፡,ለሁለት ጌቶች ሊገዛ የሚችል አገልጋይ የለም፡፡ |
|
አሐቲ ይእቲ ለእማ ።,ለእናቷ አንዲት ናት። |
|
አሐደ ቀለመ ዘነገረከ ይኩን ከመ አቡከ፤ ክልዔተ ቀለመ ዘነገረከ ይኩን ከመ ፈጣሪከ፡፡,አንድ ቀለም የነገረህ እንደ አባትህ፣ ሁለት ቀለም የነገረህ እንደ ፈጣሪህ ይሁንልህ፡፡ |
|
አሐደ ይኩን ቃልክሙ፤ እመኒ እወ አወ ወእመኒ አልቦ አልቦ፡፡,ቃላችሁ አንድ ይሁን፤ አዎ ከሆነ አዎ አይደለም ከሆነም አይደለም በሉ፡፡ |
|
አቅረብኩ ለከ እሳተ ወማየ፣ ደይ እዴከ ኀበ ዘፈቀድከ,እሳትና ውፃ አቀረብኩልህ፤ እጅህን ወደምትሻው ስደድ፡፡. |
|
አቅድሙ ስንቀከሙ፡፡,ስንቃችሁን አስቀድሙ። |
|
አበውኒ ኢታስተቆጥዑ ውሉደክሙ፡፡,አባቶች ልጆቻችሁን አታስቆጡ |
|
አብዝኖ መጻሕፍት ያዘነግእ ልበ,መጻሕፍትን በብዛት ማንበብ ዝንጉነትን ያመጣል፡፡ |
|
አብድ ይነውም በጊዜ ማአኣረር፡,ሰነፍ በአዝመራ (በሥራ) ጊዜ ይተኛል፡፡ |
|
አነ አዐብዮ ሰአቡየ ዕዝን፣ ደኃራዊ ዘበቁልኩ ቀርን።,በኋላ የበቀልኩ ቀንድ አባቴን ጆሮን እበልጠዋለሁ፡፡ |
|
አነ ዘጳውሎሰ፣ ወአነ ዘአጵሎስ፣ ወአነ ዘኬፋ፡፡,ኦኔ የጳውሎስ፣ አኔ የአጵሎሰ፣ አኔ የኬፋ። |
|
አንብብዋ ለመልእክት፤ አም ጥንታ እስከ ተፍጻሜታ፡፡,መልአክቲቱን ከመጀመሪያዋ እሰከ መጨረሻዋ አንብቧት፡፡ |
|
አንተ ኮኩህ!,አንተ መሠረት ነህ! |
|
አንትሙስ ኅሱ እንተ አፍኣ ወእንተ ውሰጡስ የአምር አግዚአብሔር፡፡,እናንተ የላዩን መርምሩ፤ የውስጡን እግዚአብሔር ነው የሚያውቀው፡፡ |
|
አንትሙ ተሐውሩ ግድመ ግድመ፤ አነኒ አሐውር ግድመ ግድመ፡፡፥,እናንተ ግራ ግራውን ትሄደሳችሁ፤ እኔም ግራ ግራውን እሄዳለሁ፡፡ |
|
አንፄዋ ለኅልፈታ አንፈ ፄሴሜት ታጹኑ።,አይጥ ለሞቷ የድመት አፍንጫ ታሸታለች፡፡ |
|
አክብር አባክ ወአመክከ፡,አባትና እናትህን አክብር፡፡ |
|
አኮ ለዘሮጸ ባህቱ ለዘበደረ፡፡,በሮጠ አይደለም በቀደመ እንጅ፡፡ |
|
አኮ በሲበት አላ በአአምሮ።,በሽበት አይደለም፤ በማስተዋል እንጅ፡፡ |
|
አኩቴቶሙ ዕረፍቶሙ፤ ዕረፍቶሙ አኩቴቶሙ።፡,እረፍታችው ማመስገናቸው፤ ማመስገናቸው አረፍታቸው ነው፡፡ |
|
አድኅን ርእስከ፡፡,ራስህን አድን።፡ |
|
አጽንእ ዘብከ ከመ አልቦ ዘይነሥእ አክሊሰከ፡፡,ጸጋህን ማንም እንዳይወስድብህ፣ ያለህን አጥብቀህ ያዝ፡፡ |
|
አፉሁ ለጻድቅ ይትሜህር ጥበብ፡፡,የደግ ሰው አፍ ጥበብን ይማራል፡፡ |
|
አፍቅር ቢጸከ ከመ ነፍስክ፡፡,ባልንጀራህን እንደራስህ ውደድ፡ |
|
አፍትን ርእሰከ ለካህን፡፡,ራስህን ለካህን አሳይ፡ |
|
አፍኒ ወልብኒ ኅቡረ ይእመኑ።,አፍም ልብም በአንድነት ይመኑ፡፡ |
|
አፍ ይጸውአ ለሞት፡፡,አፍ ሞትን ይጠራል፡፡ |
|
ኢተህቡ ፍኖተ ለሠይጣን፡,ለሠይጣን በር አትስጡት፡፡ |
|
ኢታልምድዎ ወኢትክልእዎ፡፡,አታስለምዱት፤ አትከልክሉት፡፡ |
|
ኢታትህት ርአስክ ለብእሲ አብድ,ለሰነፍ ለው ራስከን ዝቅ አታድርግ፡፡ |
|
ኢታንሥእ ዘኢያንበርከ፡፡,ያላስቀመጥከውን አታንሣ፡፡ |
|
ኢታንክር ዘንተ ዘይብእስ ሀሎ፡፡,የባስ አለና ይህን አታድንቅ፡ |
|
ኢታድልዉ ለገጸ ሰብአ፡፡,የሰው ፊት አይታችሁ አታዳሉ፡፡ |
|
ኢታፍቅሩ ወርቀ ወኢብሩረ፡፡,ብርና ወርቅን አትውደዱ፡፡ |
|
ኢትህሚ ሰብአ ውስተ ቤትከ፤ አስመ ዖፈ ሰማይ ያወጽኦ ለነገርከ፡፡,ቤትህ ውስጥ እንኳ ቢሆን ሰውን አትማ፤ ነገርህን የሰማይ ወፍ ያወጣብህልና፡፡ |
|
ኢትልበሱ ልብሰ ሐራ።,የማይገባችሁን ልብስ አትልበሱ። |
|
ኢትማዖ ሰአኩይ በእኩይ፤ አላ በገቢረ ሠናይ፡፡,ክፉን በክፉ አታሸንፈው መልካም በመሥራት እንጅ፡፡ |
|
ኢትርአይ ግርማ ርእየቱ ለኤልያብ፡፡,የኢያልያብን ግርማ ሞገስ አትይ፡፡ |
|
ኢትርፍቅ ውስተ ርእስ ምርፋቅ፡፡,ከላይኛው መቀመጫ አትቀመጥ። |
|
ኢትስርቁ ትብል ወለሊከ ትሰርቅ፡፡,አትስረቁ ትላለህ፤ አንተ ግን ትዘርፋሰህ፡፡ |
|
ኢትስተይ ማይ እራቆ፤ አላ ቶስህ ወይን በአንተ ህማመ ከብድከ፡፡,ውሃ ብቻ አትጠጣ፤ ስለሆድህ ህመም ትንሽ ወይን ጨምር እንጅ |
|
ኢትቁም አራቀክ ቅድመ ነቢየ አግዚአብሔር፤,በእግዚአብሔር ሰው ፊት ባዶ እጅህን አትቅረብ፡፡ |
|
ኢትቅናዕ ላዕለ አኩያን፡፡,በክፉዎች አትቅና፡፡ |
|
ኢትኅድግ ዐርከክ ዘትካት፤ እስመ ኢይከውነክ ከማሁ ዐርከ ግብት፡፡,ድንገተኛ ወዳጅ እንደሱ አይሆንልህምና የቀድሞ ወዳጅህን አትተው |
|
ኢትንአዶ ሰለብእ ዘእንበሰ ትርዐይ ተፍጻሜቶ፡።፡,ሰውን መጨረሻውን ሳታይ አታመስግነው፡ |
|
ኢትኩኑ ከመ መደልዋን፡፡,እንደግብዞች አትሁኑ፡፡ |
|
ኢትኩን ጻድቀ ፈድፋደ፤ ወኢትጠበብ ፈድፋደ፡፡,እጅግ ጻድቅ እጅግም ጠቢብ አትሁን፡፡ |
|
ኢትክሉ ተቀንዮ ለአግዚአብሔር ወለንዋይ፡፡,ለእግዚአብሔርና ለገንዘብ መገዛት አትችሉም፡፡ |
|
ኢትክሉ ተቀንዮ ለክልዔ አጋእዝት፡,ለሁለት ጌቶች መገዛት አትችሉም፡፡ |
|
ኢትክል ተከብቶ ሀገር፤ እንተ ተሐንጸት መልእልተ ደብር,በተራራ ላይ የተሠራች ህገር መሠወር አትችልም፡፡ |
|
ኢትዛለፍ በማእከለ ሊቃውንት፡፡,በሊቃውንቱ መካከል አትጥቀስ፡፡ |
|
ኢትግሥሠ መሲሃንየ ወኢታህስሙ ዲበ ነቢያትየ፡፡,መልእክተኞቼን አታስጨንቁ፤ በነቢያቶቼም ላይ ከፉ አታድርጉ |
|
ኢትፍርህዎ ለሞት ፍርህዋ ለኃጢአት,ሞትን አትፍሩት፤ ኃጢአትን እንጀ፡፡ |
|
ኢትፍጽሞ ለብዕራይክከ ሶበ ታከይድ እክለክ፡፡,እህልክን ስትወቃ የሚያበራየውን በሬ አፍ አትለጉመው፡፡ |
|
ኢየኃድጋ ለሀገር ዘእንበለ አሐዱ ሔር፡፡,ሀገርን ያለ አንድ ቸር ለው አይተዋትም፡፡ |
|
ኢየአርሩ በለለ እም አስዋክ፤ ወኢይቀስሙ አስካለ እም አሜከላ፡፡,ከአሾህ በለስን አይለቅሙም፤ ከደንደርም ወይንን አይቆርጠም፡፡ |
|
ኢያስህትከ ላህያ ለብእሲት፡፡,የሴት ውበቷ አያታልህ፡፡ |
|
ኢይመውያ ሰሚዕ ለርእይ፡፤,መስማት ማየትን አያሸንፍም፡፡ |
|
ኢይትፈቀድ ምክንያት ለኢአሚን፤ ዳዕሙ ይትፈቀድ ለአሚን,ለማመን እንጅ ላለማመን ምክንያት አያሻም፡፡ |
|
ኢይከብር ነቢይ በሀገሩ፡፡,ነቢይ በሀገሩ አይከበርም፡፡ |
|
ኢይድህን ንጉሥ በዝኀ ሠራዊቱ፡፡,ንጉሥ በሠራዊቱ ብዛት አይድንም፡፡ |
|
ኢይጥዕሞ መዓር ለአድግ ዘእንበለ እጉስታር፡፡,ላህያ ገለባ እንጅ ማር እይጥማትም፡፡ |
|
ኢይፈቅድ ይንግርዎ ግኦእዞ ለሰብእ,የሰውን ማንነቱን አንዲነግሩት አይሻም፡፡ |
|
ኤፍሬም ይበልዖ ለምናሴ፤ ወምናሴ ይበልዖ ለኤፍሬም፡,ወንድም ወንድሙን ያጠፋዋል፡፡ |
|
እለ መጥባሕተ ያነሥኡ በመጥባሕት ይመውቱ፡፡,በሾተል የገደሉ፣ በሾተል ይሞታሉ፡፡ |
|
እለ ትነብሩ ተንሥኡ፡፡,የተቀመጣቸችሁ ተነው፡፡ |
|
እለ ከርሦሙ አምላኮሙ።፡,ሆድ አምላኩዎች፡፡ |
|
እለ ጻጹተ ትነጥፋ ወእለ ገመለ ትውህጡ።,ግመልን የምትውጡ፣ ትንኝን የምታጠሩ፡፡ |
|
እመሰ ይትከሃለክሙ ምስለ ዙሉ ሰብእ ተእኅዉ፡፡,ቢቻላችሁስ ከሰዉ ሁሉ ጋር ተወዳጁ፡፡ |
|
እመሰ ጼው ለስሐ በምንት እንከ ይቄስምዎ?,ጨው አልጫ ቢሆን በምን ያጣፍጡታል? |
|
አመ ተናገርኩ ጽድቀ ሰብእ ዛቲ ዓለም ይጸልኡኒ፤ ወከመ ኢይንብብ ሀሰተ ኩነኔ ዚእከ ያፈርሃኒ፤ ወእም ኩሉሰ አርምሞ ይቴይስ ወይሜኒ፡፡,እውነት እንዳልናገር የዚህ ዓለም ሰዎች ይጠሉኛል፤ ሀሰትም እንዳልናገር ፍርድህ ያስፈራኛል፡፡ ከሁሉም ዝምታ ይሻለኛል፡፡ |
|
እመ ወሀበ ብእሲ ኩሎ ንብረቶ ለፍቅር መንኖ አይሜንንዎ፡፡,ስው ስለፍቅር ንብረቱን ሁሉ ቢሰጥ ፈጽሞ አይንቁትም፡፡ |
|
እመ ይሰድዱክሙ እም አሐቲ ሀገር ጉዩ ኀበ ካልዕታ፡,ካንዱ አገር ቢያሳድዷችሁ ወደ ሌካው ሽሹ |
|
እም ተናግሮ ይሄይስ አርምሞ፡,ከመናገር ዝም ማለት ይሻሳል፡፡ |
|
እምነ መንግሥት የዐቢ ክህነት,ከቤተ መንግሥት ቤተ ክህነት ይበልጣል፡ |
|
እምነ ረፃብ የሄይስ ኩይናት፡፡,ከረሀብ ጦርነት ይሻሳል፡፡ |
|
እም ንጉሥ እቡድ ይቴይስ ገብር ጠቢብ፡፡,ከሰነፍ ንጉሥ ብልሀ አገልጋይ ይሻካል።፡ |
|
እም አሐዱ አፍ ይወጽኡ ቡራኬ ወመርገም፡,እርግማንና ምርቃት ከእንድ አፍ ይወጣሉ፡፡ |
|
እም እፈ በላዒ ወጽአ መብልዕ፤ ወእም አፈ ኃያል ተረክበ ጥዑም፡፡,ከበላተኛ መብል ወጣ፤ ከብርቱም ውስጥ ጥፍጥ ወጣ፡፡ |
|
እም ከመ ተፈስሐ ልብ ይበርሀ ገጽ፡፡,ልብ ሲደስት ፊት ይበራል፡፡ |
|
እም ከመ ኀዘነ ልብ ይዴምን ገጽ፡,ልብ ሲያዝን ፊት ይጠቁራል።፡ |
|
እም ድኅረ ሞቱ ለስብእ አልቦቱ ንስሐ፡፡,ስው ከሞተ ንስሐ የሰውም፡ |
|
እም ዙሉ ምግባረ ጽድቅ የዓጽብ ጽሙና፣ ወእም ኩሉ መዓርግ ይትሌዓል ብሕትውና።,ከጽድቅ ሥራ ሁሉ ጭምተኝነት፣ ከማዕረግም ሁሉ ምንኩስና ይበልጣሉ፡፡ |
|
እስመ ሰውዳሴኒ ክንቱ ይልዕካ ዝሙት፡፡,ውዳሴ ከንቱን ዝሙት ይልካታል፡፡ |
|
እስመ ልብሱ ለሥጋ ሞገሱ,ልብስ ለሰውነት ክብሩ ነው፡፡ |
|
እስመ መብልዕ ወመስቴ ያስተፋቅር፡፡,ምግብና መጠጥ ያዋድዳል፡፡ |
|
እስመ ስሙ ይመረሖ ኅበ ግብሩ፡፡,ስሙ ወደ ሥራው ይመራዋል፡፡ |
|
እስመ በብዝኃ ጥበብ ብዙኅ ኀዘን፡፡,በጥበብ መብዛት ትካዜ ይበዛል፡፡ |
|
እስመ በትህትና ረከበ ልዕልና፡፡,በትህትና ክብርን አገኘ፡ |
|
እስመ በአሐዱ ፍቁር ይስሀብ ካልኡ፡፡,በአንዱ ፍቅር ሌላው ይሳባል፡ |
|
እስመ ተፋቅሮ ይደፍኖን ለኩሎን ኃጣውአ፡፡,ፍቅር በደልን ሁሉ ይፍቃል፡፡ |
|
እስመ ነፍስ ተሐድር በደም፡፡,ነፍስ በደም ታድራለች፡፡ |
|
እስመ ነፍስ ተዓጽብ እምሲሲት፤ ወሥጋ የዓጽብ እም ዓራዝ፡፡,ሥጋ (ስውነት) ከልብስ ነፍስም ከምግብ ይበልጣሉ፡፡ |
|
እስመ አልቦ ነገር ዘይስአኖ ሰእግዚአብሔር፡፡,ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የሰም፡፡ |
|
እስመ እም ቃልከ ትጸድቅ ወእም ቃልከ ትትኳነን፡፡,በአነጋገርሀ ይፈረድብሀል፤ ወይም ይፈረድልሀል፡፡ |
|
እስመ እምተረፈ ልብ ይነበብ አፍ።፡,ከልብ ሞልቶ የተረፈውን እፍ ይናገራል፡፡ |
|
እስመ ዘአፍቀረ ይጌሥጽ እግዚአብሔር፡፡,እግዚአብሔር የወደደውን ይገሥጻል።፡ |
|
እስመ ፍቅር ከመ ሞት ጽንእት ።,ፍቅር እንደሞት ጽኑ ናት፡፡ |
|
እስመ ኩሉ ለቤቱ ይሄሊ።,ሁሉም ለቤቱ ያስባል፡፡ |
|
እስመ ኩሉ ጾሮ ይጸውር፡፡,ሁሉም እዳውን ይሸከማል፡፡ |
|
እስመ ቁር ወረሃብ ያረስዕ ጸሎተ፡,ብርድና ረሃብ ጸሎትን ያስረሳል፡፡ |
|
እስከ ማዕዜኑ ተሐነከሱ በክልዔሆን ጌጋያቲክሙ?,በሁለት ሃሳብ እለከ መቸ ታነከሳሳችሁ? |
|
አቀትሎ ለኖላዊ ወይዘረዉ አባግዒሁ።፡,እረኛውን እገድለዋለሁ፤ በጎቹም ይበተናሉ፡፡ |
|
እንበለ መከራ፤ ኢይትረከብ ጸጋ፡፡,ያሰመከራ ጸጋ፤ ያለ ድካም ዋጋ አይገኝም፡፡ |
|
እንበለ ዝናም ደመና፤ እንበለ ንጽህ ምንኩስና:,ያለዝናብ ደመና፤ ያሰንጽህና መንኩስና፡፡ |
|
እንተ ኢትልህቅ ጣዕዋ ትመርሕ እማ፡፡,የማታድግ ጥጃ እናቷን ትመራለች፡፡ |
|
እንዘ ቦ ልሂቅ ኢይትናገር ደቂቅ፡፡,አዋቂ ሽማግሌ እያለ ልጅ አይናገርም፡፡ |
|
እንዘ ቦ ርሁብ ውስተ ቤትከ አታውጽእ አፍእ፡፡,ከቤትህ ራብተኛ እያለ ውጭ አውጥተህ አትስጥ። |
|
እኩይ ብእሲ ያወጽኣ ለእኪት እም እኪት መዝገበ ልቡ።,ክፉ ስው ከክፉ ልቡ ክፋቱን ያወጣታል |
|
እክል ያጸንእ ኃይለ ሰብእ።,እህል (ምግብ) የለውን ኃይል ያጠነክራል፡፡ |
|
እድ ጽኑእ ብእሴ ያብዕል፡፡,የትጉህ እጅ ታበለጽገዋለች፡፡ |
|
እግዚአብሔር ወኀበ ወአግዚአእብሔር ነሥአ፡፡,እግዚአብሔር ለጠ፤ እግዚአብሔር ነሳ፡፡ |
|
እጽብሰ እጹብ ውእቱ፤ እሰመ ለእጹብ ትርጓሜ እልቦቱ፡፡,እጹብ እጹብ ነው ለእጹብ ትርጉም የለውም፡፡ |
|
ኦሆ በሀሊ፡፡,አሽ ባይ። |
|
ከመዝ ንግሩ፤ ወከመ ዝ ግበሩ፡፡,እንዲህ ንገሩ፤ እንዲህ ሥሩ። |
|
ከንቱ ውዳሴ፡፡,የማይገባ ምስጋና |
|
ኩኑ ቅዱሳነ፤ እሰመ አነሂ ቅዱስ አነ።,እኔ ቅዱስ እንደሆንኩ እናንተም ቅዱሶች ሁኑ፡፡ |
|
ኩኑ ከመ ይእዜ እለ ተወልዱ ሕጻናት,ዛሬ እንደ ተወለዱ ሕጻናት ሁኑ። |
|
ኩኑ ጠቢባነ ከመ እርእዌ ምድር፤ ወየዋሃነ ከመ ርግብ፡፡,እንደ እባብ ብልህ፤ እንደ ርግብ የዋህ ሁኑ። |
|
ኩን መሃይምነ እስከ ለሞት፡።,እለከሞት ድረስ የታመንከ ሁን፡፡ |
|
ኩን ጠቢበ ለእድውከ,ለባለንጋራህ ብልህ ሁንበት፡። |
|
ካህናቲከ ይለብሉ ጽድቀ።፡,ካህናቶችህ ጽድቅን የጎናጸፋሉ። |
|
ካህን ይነብር በየማነ ንጉሥ፡፡,ካሀን በንጉሥ ቀኝ ይቀመጣል፡፡ |
|
ከቡር ሞቱ ለጻድቅ፡፡,የደግ ሰው ሞት የከበረ ነው፡፡ |
|
ከቡር እውስቦ በኩለሄ ወለምስካቡኒ አልቦቱ ስእበት፡፡,መጋባት በሁሉም ዘንድ ከቡር፤ መኝታውም ቅፃዱስ ነው፡፡ |
|
ኮከብ እም ኮከብ ይሄይስ ክብሩ,በክብሩ ኮከብ ከኮከብ ይበልጣል፡፡ |
|
ወለሊሁ ሠይጣን ይትሜሰል ከመ መልአከ ብርሃን፡፡,ሳይጣን ራሱ የብርፃን መልእከን እስኪመሰል ይለወጣል፡፡ |
|
ወለእመ ሖርከ ብሔረ ባዕድ ኩን ከማሆሙ።፡,ሌላ አገር ብትሄድ እንደ እነሱው ሁን |
|
ወለእመ ይለድድዱክሙ እም አሐቲ ሀገር ጉዩ ኅበ ካልዕታ፡፡,ካንዱ ሀገር ቢያሳድዷችሁ ወደ ሌላው ሽሹ።፡ |
|
ወለደቂቀ መንግሥትሰ ያወጽእዎሙ አፍኣ፡፡,የመንግሥትንም ልጆች ወደ ውጭ ይጥሏቸዋል፡፡ |
|
አግዚእ አእምሮ በጠጅ፣ እነወለቡ በደጅ፡፡,ሀገሬ ኢትዮጵያ ሞኝ ነሽ ተላላ፤ የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ፡፡ |
|
ወሙጻኡ ለቅስት የሃልቅ በመሐላ፡፡,ከርክር በመሐላ ይዘጋል፡፡ |
|
ወቀላለ ኮነት ዘመንየ ከመ ነገረ ከየአንም፡፡,ዘመኔ ከሸማኔ መወርወሪያ ይልቅ ይቸኩላል፡፡ |
|
ወቀደምትኒ ይከውኑ ድኅረ፡፡,ፊተኞች ኋለኞች ይሆናሉ፡፡ |
|
ወትወርድ አመጻሁ ዲበ ድማሁ፡፡,ክፋቱ በራሉ ላይ ትደርሳለች፡፡ |
|
ወነገረ ቢጽ ኢይጥዕሞ ስሰቢጹ፡፡,የባልንጀራው ሃሰብ ለባልንጀራው አይጥመውም፡፡ |
|
ወነገርከ ያዔውቀከ፡፡,አነጋገርህ ማንነትህን ይገልጽብሃል፡፡ |
|
ወኢይጻእ ዐቢይ ነገር እም አፉክሙ፡፡,ክፉ ነገር ካፋችሁ አይውጣ፡፡ |
|
ወእምኩሉ የዐቢ ተፋቅሮ፡፡,ከሁሉም ፍቅር ይበልጣል |
|
ወክልዔቴ ይስድድዎሙ ለእልፍ፡፡,ሁሰቱ ሺህዎቹን ያሳድዷቸዋል፡፡ |
|
ወዘአዝለፊ ትዕግሥቶ ውእቱ ይድኅን፡፡,ትዕግሥትን ያዘወተረ እርሱ ይድናል፡፡ |
|
ወያገብእ እሁ እኅዋሁ ለሞት፡,ወንድም ወንድሙን ለሞት አሳልፎ ይሰጣል |
|
ወይን ወማኅሌት ያስተፌስሁ አልባበ፡፡,ወይንና ማኅሌት ልብን ያስደስታሉ፡፡ |
|
ወይን ያስተፌስሕ ልበ ለብእ፡፡,ወይን ጠጅ የሰውን ልብ ያስደስታል፡፡ |
|
ወድሶ ለለብእ በዘይደሉ፡፡,ስውን በሚገባው አመስግነው፡፡ |
|
ወኩሉ ዘተጽሕፈ ሰተግሣጸ ዚእነ ተጽሕፈ፡፡,የተጻፈው ሁሉ እኛ አድንመከርበት ተጻፈ። |
|
ውሂብሰ እም ልማድ ውእቱ፡፡,መስጠት ከመልመድ ይመጣል፡፡ |
|
ውሂብሰ እም ረኪብ ውእቱ፡፡,መስጠት ከማግኘት ይመጣል፡፡ |
|
ውሂብ እም ድኅረ ስኢል እስረተ እድ ውእቱ፤ ወውሂብስ ቅድመ ስኢል ፈቲሐ እድ ውእቱ።,ከተለመኑ በኋሳ መስጠት እጅ መታሠር፤ ሳይለመኑ መስጠት ልግስና ነው፡፡ |
|
ዐቃቤ ሥራይ ፈውስ ርእሰከ፡፡,ባለ መድኃኒት ሆይ! ራስህን ፈውስ፡፡ |
|
ዓስምስ ያፈቅር እሊእሁ፡፡,ዓለም የራሱ የሆኑትን ይወዳል፡፡ |
|
ዕብን ዘመነንዋ ነደቅት፤ ወይእቲ ኮነት ውስተ ርእስ ማዕዘንት፡፡,አናጢዎች የናቋት ድንጋይ እርሷ የማዕዘን ራስ ሆነች፡፡ |
|
ዕውር ለዕውር ይትማርሑ ወይወድቁ ውስተ ግብ፡፡,ዕውር ዕውርን ቢመራ ተያይዞ ገደል፡፡ |
|
ዕውር ኢይባእ ውለተ ዝማሜ ወመሳጣ አይሠራዕ ጋሜ፡፡,ዕውር አይዘም፣ መላጣ ጋሜ አይሠራ፡፡ |
|
ዘላዕለ ነፍሱ ይኤብስ ለመኑ ኄረ ይከውን?,ራሉን የሚነፍግ ለማን ቸር ይሆናል? |
|
ዘልህቀ በውስቴታ፤ የአምር ሥርዓታ፡፡,በውስጧ ያደገ ሥርዓቷን ያውቃል፡፡ |
|
በመሀሩክሙ ዕቀቡ ወዘከመ ምግባሮሙሰ ኢትግበሩ።,ያስተማሯችሁን ተግብሩ፤ የሚሠሩትን ግን አትሥሩ፡፡ |
|
ዘምር በመጠንከ,በልክ ዘምር! |
|
ዘምስለ ጠዋይ ተጠዊ፤ ወምስለ ኅሩይ ኅሩየ ትከውን፡,ከጠማማ ጋር ጠማማ ከቀና ጋር ቀና ትሆናለህ፡፡ |
|
ዘረከበ ብአሲተ ሄርተ ረከበ ሞገስ፡፡,ቸር ሚስት ያገኘ በረከትን አገኘ፡፡ |
|
ዘሰ በዐቅሙ ይበልዕ ጥዑይ ነፍሱ፡፡,መጥኖ የሚበላ፣ ጤውነቱ ጤና፡፡ |
|
ዘበውሁድ ምዕመን በብዙኅኒ ምዕመን፡፡,በትንሹ የታመነ በብዙዉም ይታመናል። |
|
ዘቦ ብዙኅ ኢያትረፈ፤ ወዘቦ ውጉድ ኢያኅጸጸ።,ብዙ ያለው አልተረፈውም፤ ትንሽ ያለውም አልጎደለበትም፡፡ |
|
ዘተወክፈ ጻድቀ በስመ ጻድቅ፣ ዐስበ ጻድቅ ወእሴተ ጻድቅ ይረክብ፡፡,ጻድቁን በጻድቁ ስም የተቀበለ የጻድቁን ዋጋ ያገኛል፡፡ |
|
ዘኀሠሠ ክልዔ ኢይረክብ አሐደ፡፡,ሁለት የሻ አንድም አያገኝ |
|
ዘኒ ትፈቅዱ ይግበሩ ለክሙ ሰብእ አንትሙኒ ግበሩ ሎሙ፤ ወዘኒ ኢትፈቅዱ ይግበሩ ብክሙ ኢትግበሩ ቦሙ,ሰዎች ሊያደርጉላችሁ የምትሹትን አድርጉላቸው፤ ቢያደርጉባችሁ የምትጠሱትንም አታድርጉባቸው፡፡ |
|
ዘንስቲት ባቲ፤ ዕረፍት አልባቲ,ትንሽ ያላት፣፤ ዕንቅልፍ የላት፡፡ |
|
ዘአሀዙ ወርቀ ወዘኢአህዙ፣ ክልዓሆሙ ኅቡረ ተከዙ።፡,ወርቅ የያዙትም ሆኑ ያልያዙት በአንድነት አዘኑ።፡ |
|
ዘአልቦ ብእሲት ምንዱብ ውእቱ፡፡,ሚስት የሌለው የተበደለ ነው፡፡ |
|
ዘአልቦ ኃጢአት ለይገራ፡፡,ኃጢአት የሌለበት ይውገራት፡፡ |
|
ዘአልቦ ጽልቱጉት፡፡,ማስመስል የሌለበት፡፡ |
|
ዘአልዐለ ርእሶ የኃስር፤ ወዘአትሀተ ርአሶ ይከብር,ራሱን ከፍ ከፍ ያደረገ ይዋረዳል፤ |
|
ከኢተሰምዐ ተሰምዐ፤ ዘኢተገብረ ተገብረ፡፡,ያልተለማ ተለማ፤ ያልተደረገ ተደረገ፡፡ |
|
ዘኢተገብረ ለመላአክት ተገብረ ለካህናት፡፡,ለመላእክት ያልተደረገው ለካህናት ተደረገ |
|
ዘኢኮነ ዕድውክሙ ቢጽክሙ ውአቱ፡፡,የማይቃወመን እርሱ ከኛ ጋር ነው፡፡ |
|
ዘኢይክል ሠሪዐ ቤቱ እፎ ያስተሐምም ቤተ አግዚአብሔር?,የራሱን ቤት በሥርዓት ያላደራጀ ቤተ አግዚአብሔርን እንዴት ያስተዳድራል? |
|
ዘኢይፈቅድ ይትጌበር ኢይሴሰይ፡፡,ሊሠራ የማይወድ አይብላ፡፡ |
|
ዘእም ተረፈ ልብ ይነብብ አፍ፡፡,ከልብ ሞልቶ ከተረፈው አፍ ይናገራል፡፡ |
|
ዘአግዚአብሔር አስተጻመረ ኢይፍልጥ ሰብእ፡፡,አግዚአብሔር አንድ ያደረገውን ሰው አይለየው፡፡ |
|
ዘከዐወ ደመ ሰብኣ ይትከዐው ደሙ፡፡,የሰው ደም ያፈሰሰ ደሙ ይፈሳል።፡ |
|
ዘክልዔ ልቡ ህዉክ ውአቱ።፡,መንታ ልብ ያሰው የታወከ ነው፡፡ |
|
ዘወጠነ ይፌጽም፡።,የጀመረ ይፈጽም፡፡ |
|
ዘዐቀበ አስኪቶ የዐቅብ ህይወቶ፡፡,ህፍረተ ሥጋውን የጠበቀ፣ ህይወቱን ጠበቀ፡፡ |
|
ዘዘገኑ ወርቀ ወዘኢዘገኑ፤ ክሌዔሆሙ ኅቡረ ኀዘኑ።፡,ወርቅ ያገኙም አዘኑ፤ ያላገኙም አዘኑ፡ |
|
ዘየሐውር መርድአ የኀሥሥ ምክንያተ፡፡,የሚሄድ ተማሪ ምክንያት ይሻል |
|
ዘየዓቅብ አፋሁ ይትመሐፀን ነፍሶ፡፡,አፉን የሚጠብቅ ነፍሱን ይጠብቃል፡፡ |
|
ዘያፈቅር ቢጾ ውስተ ብርሃን ይነብር ።,ወንድሙን የሚወድ በብርሃን ይኖራል። |
|
ዘይትናገር ዘኢይደልዎ ይሰምዕ ዘይጸልኦ።፡,የማይገባውን የሚናገር የማይወደውን ይሰማል፡፡ |
|
ዘይከሪ ግበ ለቢጹ ይወድቅ ውስቴቱ፡፡,ለጓደኛው ጉድጓድ የሚቆፍር ራሉ ይወድቅበታል፡፡ |
|
ዘይወጽእ እም አፉሁ ለሰብእ ውእቱ ያረኩሶ።፡,ካፉ የሚወጣው ስውን ያረክሰዋል፡፡ |
|
በድኅረ መጽአ ዐይነ አውጽአ፡፡,ከኋላ የመጣ ዐይን አወጣ፡፡ |
|
ዘጸንአ ዴዴሃ ይበልዕ ፍሬሃ,ደጅ የጠና ፍሬውን ይበላል፡፡ |
|
ዘጻመወ በዓለም የሐዩ ለዝሉፉ፡,በዚህ ዓለም የደከመ ለዘላለም ህያው ይሆናል፡፡ |
|
ዚአከ ለዚአየ፤ ዚአየ ለዚአከ፡፡,አንተ ለኔ እኔ ላንተ፡፡ |
|
ዛቲ ተግሣጽ ትኩነኒ እምዮም፡፡,ከዛሬ ጀምሮ ይች ተግሣጽ ትዝ ትበለኝ፡፡ |
|
ዝልፎ ለጠቢብ ከመ ይዌስክ ጥበበ፤ ኢትዝልፎ ለአብድ ከመ ኢይጽላእከ፡፡,ብልህን ገሥጸው ጥበብን ይጨምራል፤ ሞኝን አትገሥጸው አንተኑ ይጠላሃል፡ |
|
ዝክረ ጻድቅ ለዓለም ይሄሉ።,የደግ ሰው ሥራ ለዘላስም ይኖራል |
|
ዝ ኩሉ ሥርጋዌ በአንተ አሐዱ ነገር፡፡,ይህ ሁሉ መሽሞንሞን ለላንድ ጉዳይ ነው፡፡ |
|
የሀጉል ርአሶ ዘኀልያነ ይነሥአ፡፡,መማለጃን የሚጠላ በሕይወት ይኖራል፡፡ |
|
የአምነከ ሰብአ ሶበ ታሴኒ ሎቱ፡።,ሰው ስትውልለት እምነት ይጥልብሃል፡፡ |
|
ያኃሥረከ በአኅደርኮ፤ ወይዘረክየከ ዘለቃሕኮ፡፡,ያሳደርከው ያዋርድሀል፤ ያበደርከው ይሰድብሀል፡፡ |
|
ያዕቆብሃ አፍቀርኩ፤ ወኤሳውዛ ጸላእኩ,ያዕቆብን ወደድኩ፤ ኤሳውን ግን ጠላሁ፡፡ |
|
ይቤ አጋግ «ከመ ዝኑ ሞት መሪር»,«በውነት ሞት አንዲህ መራር ነውን» አጋግ፡፡ |
|
ይብሉ «ሰላም ሰሳም!» ወአልቦ ስላም፡፡,«ሰላም ስላም!» ይሳሱ ሰላም ግን የላቸውም፡፡ |
|
ይብል አብድ በልቡ አልቦ እግዚአብሔር,ሰነፍ በልቡ አምላከ የለም ይላል፡፡ |
|
ይብእስከ ረጊጽ ውስተ ቀኖት በሊህ።፡,የመውጊያውን ብረት ብትረግጥ ለአንተው ይብስብሃል፡ |
|
ይትወለወል ሰብእ እም ገዜ ልደቱ እስከ ጊዜ ሞቱ፡፡,ሰው አሰኪሞት ድረሰ ሲያመነታ ይኖራል፡፡ |
|
ይሄይስ ህዳጥ ዘበጽድቅ አምብዙኅ ብዕለ ኃጥአን,በዓመፅ ከተሰበሰበው ከብዙው፤ በሥራ የተገኘው ትንሹ ይበቃል፡ |
|
ይሄይስ ብሂም እምነቢበ ሀሰት፡።,ውሸት ከመናገር ዲዳነት ይሻላል።፡ |
|
ይሄይስ ብእሲ ዕጉስ እም ኃያል,ከኃይለኛ፤ ይሻላል ትዕግሥተኛ፡፡ |
|
ይሄይስ ነዳይ ጥዑይ ሥጋሁ ወፍቱሕ ነፍሱ፤ እምነ ባዕል ዘድውይ ሥጋሁ ወእሱር ነፍሱ፡,ሰውነቱ ከታመመና ሆዱ ከታሰረ ባለጸጋ ሰውነቱ ጤነኛ የሆነና ሆዱ የተከፈተ ደሀ ይሻላል |
|
ይሄይሰ አሐዱ እም ፲ ፻፤ ወይሄይስ መዊት ዘእንበሰ ውሉድ እም ወሊድ ወልደ እኩየ፡፡,ከሺዎች ይልቅ እንድ አዋቂ ልጅ ይሻላል፤ ከፉ ከመውለድም ሳይወልዱ መሞት ይሻላል፡፡ |
|
ይሄይስ አርክ ቅሩብ እም እሁ ዘርቀ የኀድር።,ከሩቅ ዘመድ የቅርብ ጎረቤት፡፡ |
|
ይሄይስ ፍተ ሐምል ፍቅር ዘቦቱ አመግዝዕ ዘአልህምት፡፡,የጎመን ወጥ በፍቅር መብላት ጥል ባበት የሰባ ፍሪዳ ከመብላት ይሻላል፡፡ |
|
ይኩን ኩሉ ብእሲ ፍጡነ ለሰሚዕ፤ ወጉንዱየ ለነቢብ ወለመዓት፡፡,ለው ሁሉ ለማዳመጥ ፈጣን፤ ለመናገርና ለቁጣ ግን የዘገየ ይሁን፡ |
|
ይወድስከ አፈ ነኪር ወአኮ አፈ ዚአከ,ራስክን አታወድስ! ሌላው ያመስግንህ እንጂ |
|
ይደልዎ ለዘያነብብ ይዝክር ስሞ ለበዓሰ መጽሐፍ,አንባቢ የባለ መጸሐፉን ስም ሊያስታውስ ይገባዋል፡፡ |
|
ይደልዎ አስቡ ለዘይትቀነይ።፡,ለሠራተኛ ደመወዙ የገባዋል፡፡ |
|
ይጹም ዐይን፤ ይጹም ልሳን፤ ዕዚንኒ ይጹም።፡,ዐይን ይጹም፤ አፍ ይጹም፤ ጆሮም ይጹም፡፡ |
|
ድልዋኒክሙ ንበሩ!,ተዘጋጅታችሁ ኑሩ! |
|
ድክምት ቃል ትሰብር አጽመ,የተለሳለስች ቃል እጥንት ትለብራለች፡፡ |
|
ገብአተኒ ወርቅየ፡፡,ገንዘቤን አገኘኋት፡፡ |
|
ጊዜሁ ለመብልዕ ረሃብ ወለስትይ ጽምእ፡,የመመገቢያ ጊዜው መራብ፣ የመጠጫም ጊዜው መጠማት ነው፡፡ |
|
ጊዜ ሰአልኩከ ጸግወኒ ፍታ፤ እስመ ኢየአምር ስብእ ዘትወልድ ሳኒታ፡፡,የስው ልጅ ነገ የሚሆነውን አያውቅምና በለመንኩህ ጊዜ የዕለት እንጀራየን ስጠኘኝ፡ |
|
ጊዜ ገቢር ለእግዚአብሔር፡፡,እግዚአብሔር የሥራ ጌዜ አለው፡፡ |
|
ጌሰምሰ ትሄሊ ለርእላ፡፡,ነገ ሰለ ራሷ ታስባለች፡ |
|
ግብር ዘአልቦ ምጣኔ ገዐር ውዕቱ፡፡,ልክ የሌለው ሥራ ብክነት ነው፡ |
|
ጠቢብ ገብር ይሜብል እግዚኡ፡,ጥበበኛ ባሪያ ጌታውን ይገዛል፡፡ |
|
ጥበብ ትትበደር እምወርቅ፡፡,ከገንዘብ ጥበብ ትመረጣለች፡፡ |
|
ጥበብ ትሄይስ እመኩሉ መዛግብት፡፡,ከሀብት ሁሉ ጥበብ ትበልጣለች፡፡ |
|
ጸላእተከሙ አፍቅሩ።,ጠላቶቻችሁን ውደዱ።፡ |
|
ጸሎቱ ለመስተቀይም ኢውክፍት ቅድመ እግዚአብሔር፡,የቂመኛ ጸሎት በአግዚአብሔር ፊት ተቀባይነት የለውም |
|
ጸሎቱ ለመስተቀይም ከመ ዘርዕ ዘወድቀ ማዕከስ አስዋክ፡፡,የቂመኛ ጸሎት ከእሾህ ላይ እነደ ወደቀው ዘር ነወ |
|
ጸጋ በዲበ ጸጋ፡፡,በጸጋ ላይ ጸጋ፡፡ |
|
ጻማ ከናፍር፡፡ ,ጉንጭ አልፋ፡፡ |
|
ጻድቅስ ይምሕር ወይሁብ፡,ደግ ይራራል፤ ይሰጣልም፡፡ |
|
ጽጋብ ያመጽእ ግብረ ቅንጻዌ! ወቅንጻዌ ያፈደፍድ ደዌ,ጥጋብ ያዘልላል፤ ዝላይም ለከፋ ሕመም ያጋልጣል፡፡ |
|
ፀሩ ለከርሥ አፍ፡፡,የሆድ ጠላቱ አፍ ነው፡ |
|
ፈታሒ በጽድቅ ኩናኒ በርትዕ፡፡,እውነት ፈራጅ ቅን ገዥ፡፡ |
|
ፍሬ ከናፍር።,የንግግር ፍሬ ቃል፡፡ |
|
ፍዳ ለኃጥአን ዕሴት ለጻድቃን፡፡,ለኃጥእን ቅጣት፤ ለጻድቃን ሽልማት፡፡ |
|
ፓፓ ዘኢይስሕት፡፡,ፓፓዉ አይሳቱም፡፡ |
|
ኩሉ ማእምር፣ ይገብር በምክር፡፡,ዐዋቂዎች ሁሉ ተማክረው ይሠራሉ፡፡ |
|
ኩሉ ቡሩክ፡፡,ሁሉ መልካም፡፡ |
|
ዙሉ ነፍስ ይሴብሖ ለእግዚአብሔር።,ነፍስ ሁሉ እግዚእብሔርን ያመሰግናል፡፡ |
|
ኩሉ ንጹሕ ለንጹሓን፡፡,ለንጹሖች ሁሉም ንጹሕ ነው፡ |
|
ኩሉ ከንቱ፡፡,ሁሉም ከንቱ ነው፡፡ |
|
ኩሉ ዐረየ ወኅቡረ አለወ,ሁሉም ተባበሮ ከፋ፡፡ |
|
ዙሉ ዕፅ ዘኢይፈሪ ፍሬ ሠናየ ይትገዘም፤ ወውስተ እላት ይትወደይ፡፡,መልካም ፍሬ የማያፈራ ዛፍ ሁሉ ይቆረጣል፤ ወደ እሳትም ይጣላል፡ |
|
ኩሉ ዘነፍስ፤ ይበሊ ከመ ልብስ፡፡,ሰው ሁሉ እንደ ልብስ ያረጃል፡፡ |
|
ኩሉ ዘገብራ ለሠናይት ይረከብ ሠናየ፡,መልካም የሠራ መልካም ነገር ያገኛል፡፡ |
|
ኩሉ ይሴኒ ሰአመ ንሴኒ ንህነ,እኛ ጥሩ ከሆን ሁሉም ነገር ጥሩ ይሆናል፡፡ |
|
ኩሉ ይሄሊ ትካዘ ርእሱ፡፡,ሁሉም የራሱን ጭንቅ ያሰባል፡፡ |
|
ኩሉ ጻድቅ በጊዜ ርቱፅ፡፡,መልካም ጊዜ ሁሉም ደግ ይሆናል፡፡ |
|
ኩሎ አመክሩ ወዘሠናየ አጽንኡ,ሁሉን ፈትኑ መልካሙን ያዙ። |
|
ጐንዱየ እብጽሕ እገሪከ ኀበ እርከከ፤ ከመ ኢይጽገብከ፤ ወኢይጽላእክ፡፡,እንዳይሰለችህ፣ እንዳይጠላህም የባልንጀራህን ቤት አታዘውትር፡፡ |
|
ጉየያ ለፍትወተ ውርዙትከ፡፡,የወጣትነት ፍላጎትህን ሽሻት፡፡ |