[ { "question": "ሞክሼ ፊደላት ___ ቅርፅ አላቸው፡፡", "a": "ተመሳሳይ", "b": "የተለያየ", "c": "ሁለቱም መልስ ይሆናሉ", "d": "", "answerKey": "a", "context": "", "grade": 1, "preamble": "", "category": "Grammar" }, { "question": "በዓረፍተነገሮች ውስጥ የቃላቶች ሚና ከፍተኛ ነው፡፡ በሚለው ዓረፍተነገር ውስጥ ስህተት እንዲኖር ያደረገው ቃል የትኛው ነው;", "a": "ቃላቶች ", "b": "ከፍተኛ ", "c": "ሚና ", "d": "ዓረፍተነገረ", "answerKey": "a", "context": "", "grade": 10, "preamble": "", "category": "Reading comprehension" }, { "question": "… ከማህበሩ ስርዓት አንድ ነቁጥ እንኳን አይተላለፍም፡፡ በሚለው ሃሳብ ላይ ለተሰመረበት ቃል አቻ የሚሆነው ቃል ከሚከተሉት መካከል የትኛው ነው?", "a": "ነጥብ", "b": "ስርዓት", "c": "ትዕዛዝ", "d": "ምልክት", "answerKey": "a", "context": "ምንባብ:\nሰው በተፈጥሮው የረሃብና የጥም ፣የበቀልና የመሳሰለው ፍልጎቱ ሁሉ እንዲፈጸምለት ይፈልጋል፤ነገርግን ማህበሩ እያንዳንዱ ሰው የተፈጥሮ ፍላጎቱን ለመፈጸም ሲል ሌሎቹን ሰዎች እንዳይጎዳ የሚወስንበት የጽህፈትና የልማድ ሕግ ሠራ፡፡ስለዚህ የተፈጥሮ ፍልጎቱን ለመፈጸም የማህበበሩን የጽህፈትና የልማድ ሕግ የተላለፈ ነውረኛ ተብሎ ይፈረድበታል፡፡\nአንድ ሰው ከሌላው የሚያስቆጣ ነገር ቢደርስበትና ለቁጣው ምክንያት የሆነውን ሰው ለማጥፋት ቢወድ፣ በማህበሩ ህግ ቅጣት እንደሚያስከትል ስለሚያውቅ ቁጣውን ለማብረድ ፣ሌላ የሚበቀልበት አማራጭ መንገድ መመፈለግ አለበት፡፡ስለዚህ የሰው ሰውነት የነጻነትና የጭቆና ውጤት ነው ማለት ይቻላል፡፡ይህ ነጻነትና ጭቆና ማህበሩ በረጅም ዘመን ዕድሜው ከልማዱ፣ከወጉ፣ከህጉ አዋህዶና አስማምቶ የሰራው ነው፡፡ስለዚህ እያንዳንዱ ሰው ተወልዶ ውስጡ ሲገባ በሱ ተመርቶ መኖር አለበት፤ከማህበሩ ስርዓት አንድ ነቁጥ እንኳን አይተላለፍም፡፡\nበጠቅላላው የማህበር ትምህርት እያንዳንዱ ሰው ሲወለድ ይዟቸው የሚወለደውን ጠቃሚ ውጥኖች ነጻነት በመስጠትና በልዩልዩ መንገድ በመርዳት ጎጂዎቹነንም እንዲሁ በልዩልዩ መንገድ በመጠቆምና በማረም ሰውዬውን ማህበራዊ እንዲሆን ያደርገዋል", "grade": 10, "preamble": "ከዚህ በታች የቀረበውን ምንባብ መሰረት አድርጋችሁ ለሚከተለው ጥያቄ ከተሰጡት አማራጮች መካከል ትክክለኛውን መልስ ምረጡ፡፡", "category": "Reading comprehension" }, { "question": "ሰው በተፈጥሮው ---------------------", "a": "ግላዊ ነው ፡፡", "b": "ማህበራዊ ነው", "c": "ማህበራዊነትን ይዞ ይወለዳል፡፡", "d": "በቀለኛ ነው፡፡", "answerKey": "a", "context": "ምንባብ:\nሰው በተፈጥሮው የረሃብና የጥም ፣የበቀልና የመሳሰለው ፍልጎቱ ሁሉ እንዲፈጸምለት ይፈልጋል፤ነገርግን ማህበሩ እያንዳንዱ ሰው የተፈጥሮ ፍላጎቱን ለመፈጸም ሲል ሌሎቹን ሰዎች እንዳይጎዳ የሚወስንበት የጽህፈትና የልማድ ሕግ ሠራ፡፡ስለዚህ የተፈጥሮ ፍልጎቱን ለመፈጸም የማህበበሩን የጽህፈትና የልማድ ሕግ የተላለፈ ነውረኛ ተብሎ ይፈረድበታል፡፡\nአንድ ሰው ከሌላው የሚያስቆጣ ነገር ቢደርስበትና ለቁጣው ምክንያት የሆነውን ሰው ለማጥፋት ቢወድ፣ በማህበሩ ህግ ቅጣት እንደሚያስከትል ስለሚያውቅ ቁጣውን ለማብረድ ፣ሌላ የሚበቀልበት አማራጭ መንገድ መመፈለግ አለበት፡፡ስለዚህ የሰው ሰውነት የነጻነትና የጭቆና ውጤት ነው ማለት ይቻላል፡፡ይህ ነጻነትና ጭቆና ማህበሩ በረጅም ዘመን ዕድሜው ከልማዱ፣ከወጉ፣ከህጉ አዋህዶና አስማምቶ የሰራው ነው፡፡ስለዚህ እያንዳንዱ ሰው ተወልዶ ውስጡ ሲገባ በሱ ተመርቶ መኖር አለበት፤ከማህበሩ ስርዓት አንድ ነቁጥ እንኳን አይተላለፍም፡፡\nበጠቅላላው የማህበር ትምህርት እያንዳንዱ ሰው ሲወለድ ይዟቸው የሚወለደውን ጠቃሚ ውጥኖች ነጻነት በመስጠትና በልዩልዩ መንገድ በመርዳት ጎጂዎቹነንም እንዲሁ በልዩልዩ መንገድ በመጠቆምና በማረም ሰውዬውን ማህበራዊ እንዲሆን ያደርገዋል", "grade": 10, "preamble": "ከዚህ በታች የቀረበውን ምንባብ መሰረት አድርጋችሁ ለሚከተለው ጥያቄ ከተሰጡት አማራጮች መካከል ትክክለኛውን መልስ ምረጡ፡፡", "category": "Reading comprehension" }, { "question": "ከሚከተሉት መካከል ‹‹ትዳር ›› የሚለው ቃል በእማሬያዊ ፍችው የገባው በየትኛው ዓረፍተነገር ነው፡፡", "a": "ትዳር ይዛለች፡፡", "b": "የሞቀ ትዳር አለኝ፡፡", "c": "ትዳሩ ፈርሷል፡፡", "d": "ትዳሩ ተናግቷል፡፡", "answerKey": "a", "context": "", "grade": 10, "preamble": "", "category": "Reading comprehension" }, { "question": "ሁሉአማረሽን----------------- በባዶ ቦታው ሊገባ የሚችለው አባባል ከሚከተሉት የትኛው ነው?", "a": "ገበያ አታውጧት", "b": "ገበያ ላኳት", "c": "", "d": "", "answerKey": "a", "context": "", "grade": 10, "preamble": "", "category": "Reading comprehension" }, { "question": "ከሚከተሉት መካከል የግጥም ባህርይ ያልሆነው የትኛው ነው?", "a": "ስድጽሁፋዊነት", "b": "ምዕናባዊነት", "c": "ተጨባጭነት", "d": "ሙዚቃዊነት", "answerKey": "a", "context": "", "grade": 10, "preamble": "", "category": "Reading comprehension" }, { "question": "የሶስተኛን ሰው ንግግር ለመግለጽ የሚገለግል የስርዓተነጥብ ዓይነት ምንድን ነው?", "a": "ትዕምርተ ጥቅስ", "b": "ትዕምርት ጥያቄ", "c": "ትዕምርተ አንክሮ", "d": "ትዕምርተ ስላቅ ", "answerKey": "a", "context": "", "grade": 10, "preamble": "", "category": "Reading comprehension" } ]